ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, August 2, 2021

ከየትኛውም የዓለማችን ክፍል ሆነው የታላቁን ዓባይ ግድብ ሥራ ማጠናቀቂያ ገንዘብ በስልክዎ በቀጥታ ወደግድቡ የባንክ ሂሳብ ማስገባት የሚችል አዲስ ድረ ገጽ እና አፕ ተዘጋጅቶ ባሳለፍነው ሳምንት ተመረቀ። የኢትዮጵያ መብራት ኃይል የአፑ ባለቤት ሲሆን ንግድ ባንክ የገንዘብ ፍሰቱን ያከናውላል ።ይጠቀሙበት! ለሌላውም ያስተዋውቁ!


===================
የኢትዮጵያ ዓባይ ግድብ 80% መጠናቀቁ ይታወቃል።አሁን የቀረው ወሳኝ ሥራ በገንዘብ እጥረት እንዳይዘገይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል።
ይህንን ሥራ ለማቀላጠፍ ከቪዛ፣ማስተር ካርድ በመጠቀም በእጅ ስልክዎ በቀላሉ በአፕ ወይንም ገፁን በመክፈት መደገፍ የሚችሉበት የቴክኖሎጂ መንገድ ተዘጋጅቷል።አፑ የተዘጋጀው በከፍተኛ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት ሲሆን በእዚህ መሰረት በዝግጅቱ የተሳተፉት:- 
  • ከኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ድጋፍ ለዓባይ  (Ethiopia International Professional Support for Abay
  • ከኢትዮጵያ የሰላም እና እርቅ ኅብረት (United Ethiopia for Peace and Reconciliation) 
  • የኢትዮጵያ መብራት ኃይል፣
  • የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና 
  • ኤግሌ ቴክኖሎጂ ሲስተም (Eaglelion Technology System) የተሳተፉ ሲሆን በተጨማሪም 
  • የኢትዮጵያ ኢምባሲ በለንደን
  • የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ
  • የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስተር
  • በአሜርካ እና አውሮፓ የሚገኙ የሕግ ባለሞያዎች
  • የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበርያ  የተሳተፉበት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
አጠቃላይ ሥራውን ከጅምሩ አንስቶ ዶ/ር በላቸው ጨከነ፣ዶ/ር ዓለማየሁ ገብረየስ፣አቶ ሲራክ ሙሴ እና ዶ/ር ልዑልሰገድ አበበ ከእንግሊዝ ላለፉት አራት ወራት ያህል ከላይ የተዘረዘሩትን ባለድርሻ አካላት በማስተባበር መርተውታል።

ድረ ገጹን እና አፑን ለመክፈት እንዲሁም በቀጥታ በድረ ገፆቹ ለመጠቀም የሚከተሉትን ማስፈንጠርያ (ሊንኮች) መክፈት ይችላሉ።


በተያያዘ ዜና ከአንድ ሳምንት በፊት የኢትዮጵያ መብራት ኃይል የገንዘብ መለገሻ mygerd ድረ ገጽ 
www.mygerd.com  መልቀቁ ይታወቃል። 




=============================
ከእዚህ በታች ያለው ማስታወቂያ ከላይ ከተፃፈው ጽሁፍ ጋር አይገናኝም።የጉዳያችን ማስታወቂያ ነው።
==========================
ማስታወቂያ /Advertisement 
===============================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

No comments:

በኢትዮጵያ የእገታ ወንጀል ተሳታፊ አራት አካላት ናቸው። ለችግሩ የመፍትሄ አካላት ሁለት ናቸው።ሁለቱ አካላት ምን ይስሩ?

======= ጉዳያችን ======= በኢትዮጵያ ዜጎችን እያገቱ ገንዘብ የሚቀበሉ ወንጀለኞች ከተራ ወንጀለኝነት አልፎ በታጣቂ ቡድኖች የገንዘብ ማግኛነት መዋል ብቻ ሳይሆን ዜጎችን የማሸበርያ ፋሺሽታዊ ተግባር ሆኗል። እገታ የ...