ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, May 29, 2012

ግንዛቤ ቁ. 1= በ አፍሪካ ልጆችን ለ ጉዲፈቻነት ከሚልኩት አስር ቀዳሚ ሃገራት ውስጥ የኢትዮጵያ የ ቀዳሚነት ስፍራ



ዛሬ ግንቦት 21/2004ዓም  በ አዲስ አበባ የተባበሩት መንግስታት ስብሰባ አዳራሽ  በተደረገ አምስተኛው የ አፍሪካ ህጻናት ፖሊሲ (የ ጉዲፈቻ ህጻናት ላይ ባተኮረ) ስብሰባ ላይ በ አፍሪካ  ልጆችን ለ ጉዲፈቻነት ከሚልኩት አስር ቀዳሚ ሃገራት ውስጥ ኢትዮጵያ የ ቀዳሚነት ስፍራ መያዟን ሪፖርቱ አመልክቷል።  ወ/ሮ ዘነቡ ታደለ የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ሚንስትር ሲናገሩ:-
'' ኢትዮዽያ የጉዲፈቻ ህጻናትን ወደ ውጭ የምትልከው ብዛት በ 2009ዓም    6,000 ነበር:: ዛሬ ግን 2,000 ደርሰናል''ብለዋል።
  •   በስብሰባው ላይ እንደተጠቆመው በ አመት ከ ሁለት ሺ በላይ ህጻናት ''ኤክስፖርት''   ይደረጋሉ ማለት ነው።
  •  ከሚላኩት ህጻናት ከ እያንዳንዱ የሚገኝ ገንዘብ አለ- ለ መንግስት። 
  • ወላጅ በከፋ ችግር ውስጥ ካልሆነ እንዴት ልጁን ወደ አልታወቀ ምድር ይልካል? 
  • ይህ የሃገራችንን  የ ችግሩን ''ዲግሪ'' አያሳይም? 
  •  ምን ያህል በ ስነ -ልቦና የተጎዱ ልጆች በ ባህር ማዶ እያደጉ እንዳሉ ልብ እንበል።
  •  አዎን 'በሃገር ቤት በችግር ከሚያድጉ ወደ ባህር ማዶ ቢሄዱ ይሻላል' የምንል እንኖራለን። ሆኖም ግን ኢትዮጵያ በንጉሱ ዘመን  ልጆችን መንግስት በሃላፊነት ወስዶ ያሳድግ ነበር። ደርግ እንኳን ባቅሙ 'የ ህጻናት አምባ' የሚባል ተቋም አቋቁሞ ያሳድግ ነበር።ከሌላው የ አፍሪካ ሃገራት የእኛ ለምን ይህን ያህል ከፋ ? የሃገርን ችግር በሃገር ልጅ መፍታት እንጂ ገንዘብ እየተቀበሉ መላክ ሞራላዊ ስራ ነው? 
ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ስላሤ በ አዳሪ ትምርት ቤት መመገብያ አዳራሽ በድንገት ደርሰው ሲቆጣጠሩ::






 ምንጭ:- የ አሜሪካ ራድዮ የ አማርኛ ክፍል ግንቦት21/2004ዓም   ዜና

Sunday, May 20, 2012

ጋዜጠኛ አበበ ገላው፣ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ እና ሂላሪ ክሊንተን

ሰኔ 11፣2011 ዓም የ አሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን አዲስ አበባ በሚገኘው የ አፍሪካ ህብረት ተገኝተው  40 ደቂቃ የፈጀ ንግግር አድርገው ነበር።በንግግራቸው ላይ የ አዲሱ ትውልድን ፍላጎት መስማት አስፈላጊ መሆኑን  እና ሁሉም የ አፍሪካ መሪዎች ቸል እንዳይሉት የመከሩበት ነበር።
ንግግራቸውን በጀመሩ በ ስድስተኛው ደቂቃ ላይ ታድያ የ አዳራሹ መብራት ጠፋ። ቀሪውን ንግግር በድንግዝግዝ መብራት ማንበብ ነበረባቸው። ይህን የሚያህል ትልቅ አዳራሽ ጀነረተር እንደሚኖረው ማንም አይጠራጠርም። የነበረው መብራት ግን (በፊልሙ እንደሚታየው) በግማሽ የተለቀቀ ይመስል ነበር።

 ሂላሪ ክሊንተን  ስለ አፍሪካ ዲሞክራሲ መናገር ሲጀምሩ መብራት በመጥፋቱ የ ኢትዮዽያ መንግስት የ መብራት ሃይል መስርያ ቤት ያልተጻፈ ህግ እንደሚያዘው ''ማስጠንቀቅያ ሳይሰጥ መብራት ማጥፋት ህገ-መብራት ሃይላችን ያዛል''ሊል እንደሚችል የመገመቱን ያህል ባለፈው የ ጂ 8 ጉባዔ ላይ ለ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የ ጋዜጠኛ አበበ ገላው'' ነጻነት!ነጻነት! የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ! አቶ መለስ አምባገነን ናቸው!'' ለሚሉት ድምጾች የ አሜሪካ መንግስት ምላሽ ''የ አሜሪካ ህገ መንግስት ሃሳቡን እንዲገልጽ ይፈቅድለታል ''እንዳለ ለአበበ ፖሊሶቹ ባሳዩት ትህትና አሁንም ይገመታል ።
በሚቀጥለው ቀን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ  በጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ ውስጥ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ሲነጋገሩ  ከውጭ እንግዳ መቀበያ ክፍል ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ስለነበር ጋዜጠኞች በጉጉት ሲጠባበቁ ነበር። ሆኖም ከንግግራቸው በኋላ በ ሹሉክታ በር ሄዱ።ለምክንያቱ እስካሁን ድረስ  በቂ መልስ የተሰጠ አይመስለኝም። እናም ሂላሪ  አዲስ አበባን ደስ ብሏቸው እንዳለቀቁ ሁሉ አቶ መለስም ዋሽግተንን እንዲሁ።
ጉዳዩ በዲፕሎማሲ ቋንቋ አንድ ለ አንድ ነው እንዴ?
 የ አበበን ሃሳብ በሚጋሩት ዘንድ የማስደሰቱን ያህል የ መለስ አድናቂዎችን በ እጅጉ አናዷል። ቁም ነገሩ ግን ያ አደለም። ወደድንም ጠላንም ግን ለ ኦባማ ጉዳዩ ያን ያህል አያናድዳቸውም። ምክንያቱም ሃሳብን መግለጽ አደለም የተናደደ ጋዜጠኛ  ጫማ የተወረወረበት መሪ ያላት ሃገር ነች- አሜሪካ። የሃገሪቱ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች በ ቀድሞው የ አሜሪካ ፕሬዝዳንት ቡሽ  ላይ ስለተወረወረው ጫማ ከ ኮሜዲ ፊልም ጀምሮ ትልቅ ውይይት አድርገውበታል።

 ወደ እኛ ሃገር ሲመጣ ግን' ተደፈርን' የሚል ስሜት ይዞ ዛቻ እና ማስፈራራት ይጎርፋል። እዚህ ላይ ነው ፈተና ያለው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ

Sunday, May 13, 2012

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከመቸውም በባሰ ሁኔታ 'አደጋ' የሚለው ቃል የማይገልጠው አደጋ ላይ ነች።

መግቢያ
«ተዋሕዶ» ከልሣነ ግእዝ የመነጨ ቃል ሲሆን፡ ትርጒሙም «አንድ ሆኖ» ማለት ነው።  ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስትያናት ቃሉ  የክርስቶስ ባሕርይ በ«ሰብዓዊ» እና በ«መለኮታዊ» ተለይቶ ሳይሆን መለኮት ከስጋ ጋር ተዋሃደ - አንድ ሆነ  ማለት ነው።
443 ዓ.ም. (451 እ.ኤ.አ.) በሮማ ንጉሥ መርቅያን ዘመነ መንግሥት 650 ኤጲስ ቆጶሳት በተገኙበት የተሰበሰበው የኬልቄዶን ጉባኤ ከሮማው ሊቀ ጳጳሳት ቀዳማዊ ልዮን "ክርስቶስ ሁለት የተለያዩ ባሕርያት አሉት" የሚል ጽሑፍ አቅርቦላቸው ነበር። ዳሩ ግን የእስክንድርያው ፓትርያርክ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ "ጌታ ሁለት ባሕርያት አሉት" የሚለው ትምሕርት ስሕተት ነው ብሎ ልዮንን አውገዘው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት በእምነት ተለያዩ። የቅዱስ ዲዮስቆሮስን ትምሕርት የሚከተሉ ዛሬአርሜኒያ፣ የሕንደ፣ የግብጽ፣ የሶርያ፤ የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስትያናት ናቸው።
የቤተክርስቲያን መመስረት በኢትዮጵያ የተጀመረው በ ቅዱስ ፊልጶስ መሆኑ ይታወሳል (ሐዋርያት ምዕራፍ 8)፦
«እነሆም፥ህንደኬ የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት አዛዥና ጃንደረባ የነበረ በገንዘቧም ሁሉ የሰለጠነ አንድ የኢትዮጵያ ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር...»ሐዋርያት ምዕራፍ 8
በዚህ ንባብ ዘንድ ፊልጶስ ጃንደረባውን  በክርስትና አጠመቀው። ንግሥት ግርማዊት ህንደኬ 7ኛ ከ34 ዓ.ም. እስከ 44 ዓ.ም. ገደማ በኢትዮጵያ የነገሡ ናቸው።
በ4ኛ ምዕተ ዘመን በወንድማማቾቹ ንጉሥ ኤዛና እና ንጉሥ ሳይዛና ዘመን በፍሬምናጦስ አማካይነት ክርስትናየኢትዮጵያ ይፋዊ ሃይማኖት ሆነ። ይህ ፍሬምናጦስ በኢትዮጵያ «አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን» ተብሎ ይታወቃል። በወጣትነት ዕድሜው ከአጎቱ ከፈላስፋው ከመሮፔዎስ እና ከወንድሙ ከሲድራኮስ ጋራ መርከባቸው ስለሰመጠች ከወንድሙ ጋር ከሞት ተርፈው ምጽዋ አጠገብ ተገኙ። ወደ ንጉሦቹም ግቢ አመጡዋቸውና ቀስ በቀስ ከፍተኛ ተጽእኖ ያለበት ደረጃ አገኙ። ንጉስ ኤዛና ደግሞ ወደ ክርስትና ለውጠው እንዲጠመቁ አደረጉ። ኤዛና ፍሬምናጦስን ለኢትዮጵያ አቡነ እንዲሾም ለመጠይቅ ወደ እስክንድርያ ላኩዋቸውና የእስክንድርያ ጳጳስ አትናቴዎስ ፍሬምናጦስን ሾሞ ላከው። ፍሬምናጦስ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ሲሆን የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስ ደግሞ 111ኛው መሆናቸው ነው።
'አደጋ' የሚለው ቃል የማይገልጠው አደጋ
ባለፈው ሳምንት የተጀመረው በሃገር ቤት የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ እንደተለመደው አሳዛኝ ዜናዎች እየተነበቡበት ጉባዔውን ጀምሯል። ካለፉት ሶስት ተከታታይ ዓመታት ወዲህ ቅዱስ ሲኖዶስ አግባብነት የሌላቸውን የ ፓትሪያሪኩ ድርጊቶች በ አደባባይ በመኮነን እና ውሳኔ በማሳለፍ ላይ በመሆኑ ከፍተኛ መዋከብ ውስጥ ሆን ተብሎ እንዲገባ እየተደረገ ነው። አሁን ፍንትው ብለው የሚታዩ አደጋዎች ከመቸውም ወቅት በላይ በ ቤተ ክርስቲያን ላይ እያንዣበቡ ነው።
የወቅቱ የቤተ ክርስቲያን አደጋ መገለጫዎች፣አደጋው በቤተ ክርስቲያን ላይ እና በሃገር ላይ የሚያመጣው መዘዝ ምን ሊሆኑ ይችላሉ? መፍትሄዎቹስ?

1/ የ ወቅቱ የ ቤተ ክርስቲያን አደጋ መገለጫዎች
  •  ልክ ያጣ ሙስና፣
  • እግዚያብሄርን የማይፈሩ፣ሰውን የማያፍሩ  የ ቤተ ክርስቲያንን አስተዳደር የ ፕትርክናውን ስልጣን ሳይቀር መያዛቸው፣
  • እነኚሁ እግዚያብሄርን የማይፈሩ፣ሰውን የማያፍሩቱ በተለይ ባለፉት ሃያ አመታት የ መንግስት የ ካድሬ ካባ ለብሰው ከ ሹመኞች ጋር በመሞዳሞድ ከስራቸው ሌሎች መሰሎቻቸውን በብዛት ወደ ቤተ ክርስቲያን መዋቅር( ከ አጥብያ ጀምሮ እስከ መንበረ ዽዽስና ድረስ) ማስረግ መቻላቸው፣
  • የነበረውን የ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምሮ ለመበረዝ የተነሱ ጸረ ተዋህዶ ቡድኖች
  • ይህ ቡድን በ ቤተ ክርስቲያን ገንዘብ እርስ በርሱ ሲጎራረስ የከረመ ከመሆኑም በላይ በገንዘቡ የማፍያ ቡድን ለማደራጀት ሁሉ የቻለ መሆኑ። ለምሳሌ የመጎራረሱ መታወቂያዎች ለ ፓትሪያሪኩ 'ጥይት የማይበሳው መኪና አጥብያ አብትያተ ክርስቲያናት' ገዙላቸው ብሎ ከመሳለቅ ጀምሮ ከ ሶስት መቶ ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ ሃውልት ከ ስርዓተ ቤተ ክርስቲያን ውጪ በ ቦሌ ደብረ ሳሌም መድሃኔ ዓለም፣መጥምቀ መለኮት ወ አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን እስከመስራት የደረሰ ታላቅ ድፍረት የሚሉት ይጠቀሳሉ።
2/  በዝምታ የተፈታ ችግር የለም!

ላለፉት ሃያ ዓመታት  በ ቤተ ክርስቲያን ላይ የደረሱት አስነዋሪ አስተዳደራዊ ብልሹነት እና ሃይማኖታዊ መዳፈሮች የሚከተሉትን መዘዞች እንደሚያስከትሉ ሳይታለም የተፈታ ነው።

መዘዙን ስላላወራነው የማይመጣ መስሎን እጅ እና እግራችንን አመሳቅለን የተቀመጥን ካለን እንደተሳሳትን መረዳት አለብን።አሁን በ ቤተ ክርስቲያን ላይ የደረሰው በዝምታ ከታየ ነገ ሊደርስ ከሚችለው ጋር ሲነጻጸር ኢምንት አይሆንም ብሎ የሚናገር ማን ሊኖር ይችላል?


Friday, May 4, 2012

አርበኞቻችንን እናስታውስ።


                                           ሚያዝያ 27 የ ድል አደባባይ

ሚያዝያ 27  የ ኢትዮዽያ አርበኞች የፋሺሽት ኢጣልያን ያሸነፉበት ቀን። የ ኢትዮዽያ ሰንደቅ ዓላማ ዳግም የተሰቀለበት ቀን ።

የ ኢትዮዽያ ገበሬ ሚስቱን፣ልጁን፣ንብረቱን ትቶ ፋኖ ተሰማራ ብሎ ያቆያት ሃገር:- ኢትዮዽያ!

ሚያዝያ 27/1935 ዓ ም ግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ሃይለስላሴ የ ኢትዮዽያን ሰንደቅ ዓላማ በ ቤተ መንግስት ከሰቀሉ በሁዋላ ለ መላው ዓለም ካስተላለፉት መልዕክት

የመልክቱ ግርድፍ ትርጉም
''አዲስ አበባ ከሚገኘው  ቤተ መንግስቴ  የ አትክልት ስፍራ ተገኝታችሁ ይህን ፊልም መቅረጻችሁ መልካም ነው :: በመላው ዓለም  ይህን የሚመለከቱ ሁሉ በ ዕምነት እና በጀግንነት አማካኝነት በ ሃያኛው ክፍለ ዘመንም ዳዊት ጎልድያን እንደመታ ይገነዘባሉ ።'' ሚያዝያ 27/1935 ዓ. ም. ግርማዊ ቀዳማዊ አጼ  ሃይለስላሴ::

                                                                 
                             አርበኞቻችንን እናስታውስ


ቁርጥ ቀን ባይመጣ ሁሉም ጀግና ነበር

ቁርጥ ቀን ባይመጣ ሁሉም ጀግና ነበር፣
የ ውሎ ገድሉን ሲኖር የሚናገር።
እስኪመጣ ድረስ ቁርጥ ቀን በቶሎ፣
ፈሪም ያውቅበታል መኖር ተመሳስሎ።
ጌታቸው በቀለ
ሚያዝያ 27/2004 ዓ.ም
ኦስሎ

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...