ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Saturday, October 31, 2020

ጉዳያችን ዜና - ከአራት ሳምንት በኃላም በአዲስ አበባ ሆቴል ክፍል ውስጥ የጀነራሉ ባለቤት አሟሟት ምስጢር ሆኗል።

ዜናውን ለመከታተል ሊንኩን ይጫኑ -

https://www.youtube.com/watch?v=VvA5R96bJRI

Monday, October 26, 2020

ዝነኛው ኢትዮጵያዊው ዓለም አቀፍ ሰዓሊ ሻምበል ለማ ጉያ ማን ናቸው? Who is Lema Guya?

ለማዳመጥ ይህንን ይጫኑ 



ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢትዮጵያ የዓባይ ግድብ ላይ በሰጡት ፀብ ጫሪ አስተያየት ላይ የተሰጠ መግለጫ Ethiopian Orthodox Tewahido Church press release on American President Trump's latest provoking comment on Ethiopian great dam on Blue Nile River.

ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢትዮጵያ የዓባይ ግድብ ላይ በሰጡት ፀብ ጫሪ አስተያየት ላይ የተሰጠ መግለጫ
Ethiopian Orthodox Tewahido Church press release on American President Trump's latest provoking comment on Ethiopian great dam on Blue Nile River.

ጥቅምት 16/2013 ዓም

በአገራችን ኢትዮጵያ የሕዝባችን የዘመናት ድህነትና የኑሮ ጉስቁልና አስወግዶ ለአገራችንም ብልጽግና ሆነ ለሕዝባችን ዕድገት ከፍተኛ ተስፋ የተጣለበት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሥራው ተጀምሮ በአሁኑ ጊዜ ከፍተኛ የዕድገት ደረጃ ላይ መድረሱ ከዚያም በላይ ከሦስት ወራት በፊት በግድቡ የመጀመሪያ ሙሌት ተደርጐ ለሕዝባችን የብስራት ድምጽ መሰማቱ ኢትዮጵያውያን በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ ደስታቸውን መግለጻቸው ይታወቃል፡፡
በቀጣይም የግድቡ የዕለት ከዕለት ሥራ እየተከናወነ ሕዝባችንም የተለመደ ድጋፉን እያደረገ ከሦስት ዓመታት በኋላ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንደሚደርስ ተስፋ የተጣለበት መሆኑ ይታወቃል፡፡
ይሁን እንጂ ሕዝባችን በዚህ ተስፋ ውስጥ በገንዘቡም በጉልበቱም በሙያውም የበኩሉን ድጋፍ እየተረባረበ ባለበት ወቅት ጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ.ም. የአሜሪካው ፕሬዝዳንት በአገራችን ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ግድባችንን አስመልክቶ አገራትን ወደ ግጭትና አለመግባባት ውስጥ የሚከት የጥፋት መልዕክት ማስተላለፋቸውን ቅዱስ ሲኖዶስ በዓመታዊ ጉባኤው ላይ እንዳለ በሐዘን ተመልክቶታል፡፡
የተወደዳችሁ በአገር ውስጥ ሆነ በውጭው ዓለም የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ልጆቻችን እና ሌላውም የዓለምም ሕዝብ
ታሪክ እንደሚያስታውሰን አገራችን ኢትዮጵያ በዘመናት ውስጥ ታፍራና ተከብራ የኖረችውና ለመላው ጥቁር ሕዝብ ምሳሌ የሆነችው አገሪቱ አገረ እግዚአብሔር ሕዝቡ ሕዝበ እግዚአብሔር በመሆኑና በዚህም የሰውና የእግዚአብሔር አንድነት አገራችን በእግዚአብሔር ተጠብቃ የኖረች አገር በመሆኗ ነው፡፡
ከዚህም ጋር በዘመናት አገሪቱን እንዲመሩ የተጠሩ መሪዎችና ሕዝቧ በአገራችን ላይ ይነሳሱ የነበሩ ወራሪዎች ያሰቡት ሳይሳካላቸው አገሪቱ ድንበሯ ከነክብሯ ተጠብቆ የኖረችና የሕዝባችን አገራዊ አንድነት ተጠብቆ የኖረ በመሆኑ ነው፤
ዛሬም ቢሆን ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕም ሆነ ከከሌሎች ተመሳሳይ አካላት በአገራችን ላይ እየተላለፈ ያለው የጥፋት ጥሪ መተዛዘቢያ ከሚሆን በስተቀር አገራችን ጠባቂዋ በሆነው እግዚአብሔርና በሕዝባችን አንድነት ተከብራና ተጠብቃ እንደምትኖር ሙሉ እምነታችን ነው፡፡
የተወደዳችሁ በአገር ውስጥ ሆነ በውጭው ዓለም የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ልጆቻችን እና ሌላውም የዓለምም ሕዝብ
አገራችን ኢትዮጵያ ከአንድ መቶ ሚሊዮን ያላነሱ ልጆቿ እንደየአካባቢያቸውና እንደ አደጉበት አካባቢ የተለያዩ ቋንቋ እየተናገሩ ባሕላቸውንና ሥርዓታቸውን ጠብቀው በመከባበርና በአንድነት መንፈስ እየተረዳዱ የሚኖሩበት እንግዳ በመቀበልና ቤት ያፈራውን ተካፍሎ በመኖር የሕዝባችን ልዩ መታወቂያው እንደሆነ ይታወቃል፡፡

አሁንም ከኃያላኑ መሪዎችም ሆነ ሌሎች አገራችንን በሩቅ ሁነው ከሚጐመጇት አካላት እየተጐሰመ ያለው የጥፋት ጥሪ ኢትዮጵያን እንደትናንት አባቶቻችን በአንድነት በመከባበርና በመመካከር በመደማመጥም ጭምር መቆም ከቻልን ከአቅማችን በላይ የሚሆን ነገር እንደሌለ ከእኛ ይልቅ የአገራችንን እድገት የማይፈልጉ ከእኛ የበለጠ ይገነዘቡታል፤ ያውቁታልም፡፡
ዓለማችን በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ ያጣችው ነገር ቢሆን ሰላምን ነው፡፡ ሰላም እንደሚታወቀው ከአንድ አቅጣጫ ብቻ የሚገኝ ሳይሆን በጋራ ለአለም ሰላም መቆም ሲቻል ብቻ ነው፡፡
ስለዚህ ይህንን የአገራችን ሰላምም ሆነ ጥቅም ሊያሳጣ በሚችል መልኩ ጥቅምት 13 ቀን 2013ዓ.ም. የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአገራችን ላይ ያስተላለፉት የጦርነት ጥሪ ቅዱስ ሲኖዶስ አጥብቆ ይቃወማል፡፡ መላውም የዓለም መንግሥታትና ሕብረተሰብ ችግሩን በጥልቀት እንዲገነዘቡት ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፡፡
በአገር ውስጥ ሆነ ከአገር ውጭ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ልጆቻችን እንዲሁም አገር የመምራት ኃላፊነት የተጣለባችሁ የፌዴራልና የክልል መሪዎች ከዚህም ጋር በአገሪቱ ውስጥ የምትገኙ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በአሁኑ ጊዜ ሁላችንም ኢትዮጵያውያን የትኛውንም የየግልና የቡድን አመለካከታችንን ወደጐን በመተው አንድነታችንን ልናጠናክርበት የሚገባ ወቅት መሆኑን በመገንዘብ ኢትዮጵያዊ አንድነታችሁን ከምንጊዜውም የበለጠ ጠብቃችሁ ለአገራችን ሕልውና እንድትቆሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ፤ ይቀድስ፤
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
አሜን!!
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም.
አዲስ አበባ

Sunday, October 18, 2020

ኢሳትን መደገፍ የኢትዮጵያን ሚድያ ወደፊት ማስፈንጠር ነው።

ከእዚህ በታች ያለው ከኢሳት ማኅበራዊ ድረ-ገፅ የተገኘ ነው።

ኢሳት እስከዛሬ የዘለቀውና ማስመዝገብ የቻላቸውን ውጤቶች ያስመዘገበው በመላው አለም በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ሁሉአቀፍ ድጋፍ መሆኑ ይታወቃል። የኢሳት ስራዎች ቀጥለው ለሀገርና ለህዝብ ከትናንቱም የበለጠ ማከናወን ይችል ዘንድ የእርስዎ ድጋፍ እጅጉን አስፈላጊ ነውና ኢሳትን በሚችሉት የገንዘብ መጠን ይደግፉ። ኢሳት ትናንትን የተሻገረውና ነገም የሚቀጥለው የኢሳትን አስፈላጊነት በተረዱ ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ ነውና በተሻለ አቅምና ተደራሽነት ህዝባችንን እንድናገለግል ዛሬም ኢሳትን እንዲደግፉ ጥሪያችንን እናቀርብልዎታለን።
ኢሳትን ለመደገፍ ከእዚህ በታች የተያያዘውን ሊንክ ከፍተው ይርዱ።

ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።