ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Saturday, July 31, 2021

በህወሓት የትምህርት ሚንስትር በገነት ዘውዴ የተጨቆነው የአዲስ አበባ ንግድ ሥራ ኮሌጅ ዛሬም ሊጠቃ አይገባም ከመንግስት ፈጣን እና ልዩ ትኩረት ይፈልጋል።

በ1956 ዓም የአዲስ አበባ ንግድ ሥራ ኮሌጅ ማኅበረሰብ 
Photo credit to Peace core

በእዚህ ፅሁፍ ስር የሚከተሉትን ነጥቦች ያገኛሉ።
  • የህወሓት ትምህርት ሚኒስትር ገነት ዘውዴ እና የአዲስ አበባ ንግድ ሥራ ኮሌጅ 
  •  ኮሌጁ ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ስር መውጣት አለበት። ለምን?
  • የንግድ ሥራ ኮሌጅ ምሩቃን ማኅበር የት ገባህ? ኮሌጁ ለምን ቦታውን እንዲለቅ ይደረጋል?

የአዲስ አበባ ንግድ ሥራ ኮሌጅ በኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ስምንት  ዓመታት ቀድሞ በ1935 ዓም የተመሰረተ በወቅቱ የንግድ ትምሕርት ቤት በሚል ነበር።የንግድ ትምሕርት ቤቱ ወደ ኮሌጅ ካደገ በኃላም ሆነ በፊት በኢትዮጵያ የመንግስትም ሆነ የግል ዘርፍ የሚያገለግሉ ብቃት ያላቸው ባለሙያዎችን አፍርቷል።የአዲስ አበባ ንግድ ሥራ ኮሌጅን ያህል ዕድሜ ጠገብ የሆነ የንግድ ሥራ ላይ አትኩሮ የሚሰራ ኮሌጅ በአፍሪካ በጣት የሚቆጠሩ ናቸው።ከሳሃራ በታች ያሉ ሀገሮች ለምሳሌ እንደ ዩጋንዳው ማካረሬ የመሰሉ በቅኝ ግዛት ዘመን የተመሰረቱ ኮሌጆችም ቢሆኑ በንግድ ሥራ ላይ ብቻ አትኩረው የሚሰሩ አይደሉም።በመሆኑም ከእጅ ያለ ወርቅ ሆኖ እንጂ የአዲስ አበባ ንግድ ሥራ ኮሌጅ በዓለማችንም ረዘም ያለ ጊዜ ካስቆጠሩ የንግድ ሥራ ኮሌጆች ውስጥም የሚመደብ ነው።

የአዲስ አበባ ንግድ ሥራ ኮሌጅ በአፍሪካ ብቻ ሳይሆን ከአውሮፓ ስመ ጥር የንግድ ኮሌጆች ጋር እኩል የተመሰረተ ነው።ችግሩ እኛ እራሳችንን አናውቅም። ለምሳሌ በኖርዌይ የሚገኘው እና ዝነኛው የንግድ ሥራ ዩቨርስቲ 'ቢአይ' BI የተመሰረተበት ዓመት እና የአዲስ አበባ ንግድ ሥራ ኮሌጅ የተከፈተበት ዓመት እኩል 1935 ዓም (እኤአ 1943 ዓም) ነው።የኖርዌይ የንግድ ዩንቨርስቲ 'ቢአይ'  በአሁኑ ጊዜ  ከመላው ዓለም የሚመጡ ተማሪዎች የሚመርጡት እና በጥራቱም በዓለም ካሉት ምርጥ የንግድ ሥራ ዩንቨርስቲዎች በእርሱ ደረጃ ያሉት 1% ብቻ ናቸው። ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ንግድ ሥራ ኮሌጅን ቢያንስ በአፍሪካ ደረጃ ያለ ምርጥ የንግድ ሥራ ኮሌጅ ማድረግ ነበረባት።ነገር ግን ላለፈው ግማሽ ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ዛሬም ሰላም ከሚነሷት በታኝ ኃይሎች ጋር ስትዋጋ፣በኃላም እነኝሁ ሲያደሟት የኖሩት ህወሓት ሆነው ቤተ መንግስት ሲገቡ  ኮሌጁን ለማቆርቆዝ ሲደክሙ ነው የኖሩት።

የህወሓት ትምህርት ሚኒስትር ገነት ዘውዴ እና የአዲስ አበባ ንግድ ሥራ ኮሌጅ 

ህወሓት የኢትዮጵያን የፖለቲካ መድረክ ሲቆጣጠር የአዲስ አበባ ንግድ ሥራ ኮሌጅ ቀደም ብሎ በወታደራዊው መንግስት መውደቂያ ዓመታት  ጀምሮ በኢትዮጵያ ከታወጀው ቅይጥ ኢኮኖሚ አንፃር እየተነቃቃ ነበር።ቀደም ብሎም ኮሌጁ በአሜሪካ እና አውሮፓ ከሚገኙ መሰል ኮሌጆች ጋር ባለው የረጅም ጊዜ መልካም ግንኙነት አንፃር ኮሌጁ በወታደራዊው መንግስት ዘመንም ዕድገቱን አላቆመም። በተለይ ከካናዳ መንግስት ጋር ባለው መልካም ግንኙነት ኮሌጁ ተጨማሪ ክፍሎችን ብቻ ሳይሆን ዘመናዊ መፅሐፍት ቤቱን የሰራው በወታደራዊ መንግስት ዘመን ነበር።በእዚሁ ዘመንም ብዙ መምህራኑ የሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ ወደየተለያዩ ሀገሮች እየሄዱ የመማር አድል ገጥሟቸዋል። በእዚህ ደረጃ የተደራጀው ኮሌጅ በህወሓት የትምህርት ሚኒስትር ገነት ዘውዴ (እውቁ የቀዶ ጥገና ሐኪም ፕሮፌሰር አስራት ዮዲት ጉዲት ነው የሚሏት) ዘንድ በበጎ አልታየም። ወ/ሮ ገነት ዘውዴ የትምህርት ሚኒስትር በሆኑበት ጊዜ በኢትዮጵያ አዳዲስ የግል ኮሌጆች ብቅ እያሉ ከመምጣታቸውም በላይ የመጀመርያ ዲግሪ መጀመርም ሆነ በዩንቨርስቲ ደረጃ መጠራት ከትምህርት ሚኒስትር ማግኘት ቀላል ነበር።

የአዲስ አበባ ንግድ ሥራ ኮሌጅ አስተዳደር የጠየቀው ደግሞ በጣም ቀላል ሁለት  ጥያቄዎችን ነበር።እነርሱም የዲግሪ መርሃግብር ለመጀመር እና ወደ ዩንቨርስቲ ደረጃ ለማደግ ነበር።ለእዚህ ደግሞ በወቅቱ ዩንቨርስቲ ከተባሉት እና በዲግሪ ደረጃ እንዲያስተምሩ ከተፈቀደላቸው  የግል ኮሌጆች አንፃር የአዲስ አበባ ንግድ ሥራ ኮሌጅ በአያሌው ልቆ የሄደ ነበር። ሆኖም ግን ወ/ሮ ገነት ከለከሉ።በወቅቱ የግል ጋዜጦች ሳይቀሩ ይህንን ጉዳይ ፅፈውበት ነበር።ለመከልከሉ አንዱ ምክንያት የነበረው የመቀሌ ዩንቨርስቲ እየተመሠረተ ስለነበር የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲን ጨምሮ ሌሎች ዩንቨርስትዎችን የማቆርቆዝ ፕሮጀክት አካል እንደነበር በግልጥ ህዝቡ ያወራ ነበር። ቆይቶ የሆነውም ይሄው ነበር።የአዲስ አበባ ንግድ ሥራ ኮሌጅ በግፊት የዲግሪ መርሃግብር ቆይቶ ቢጀምርም ኮሌጁ ሕልውናውን ይዞ እንዲያድግ ከማድረግ ይልቅ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ስር እንዲገባ ተደረገ።በወቅቱ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ፋክልቲ ያለው ቢሆንም የንግድ ሥራ ኮሌጅ እዚያው እንዲገባ ተደረገ።

 ኮሌጁ ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ስር መውጣት አለበት። ለምን?

ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው የአዲስ አበባ ንግድ ሥራ ኮሌጅ የኢትዮያን ንግድ በዘመናዊ መልክ ለማሳለጥ ትልቅ እና ቁልፍ የሚባል ሚና የተጫወተ ነው።ይህ ኮሌጅ ለኢትዮጵያ ንግድ እድገት ቀያሽ ከመሆን አልፎ የአፍሪካን ዘመናዊ ንግድ ላይ አሻራ ለማስቀመጥ የሚችል ነው። ብዙ ሀገሮች በንግድ ሥራ ላይ ይልቀት ደረጃ ያላቸውን ኮሌጆች ሆነ ዩንቨርስቲዎች ከሌሎች ጋር በመቀላቀል አያዳክሙም። ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ንግድ ሥራ ኮሌጅን አስፍታ እና የበለጠ አልምታ ለኢትዮጵያም ሆነ ለአፍሪካ እድገት ቁልፍ ሚና እንዲኖረው ማድረግ አለባት።ስለሆነም ኮሌጁ ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ስር ከመታሰር ወጥቶ በራሱ በመላው ኢትዮጵያ ልዩ ልዩ ኮሌጆች በስሩ እንዲከፍት ሊደረግ ይገባል።ለእዚህም ለኮሌጁ ጥራት እና ብቃት እንዲሁም ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ቢሮክራሲያዊ አካሄድ ወጥቶ በራሱ የንግድ ከባቢ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ዩንቨርስቲ መሆን ይገባዋል።እዚህ ላይ መሰመር ያለበት በተለይ በአሁኑ ጊዜ  የንግድ ሥራ ሙያ በራሱ እጅግ ሰፊ እና ውስብስብ ከመሆኑ የተነሳ እና እንደቀድሞው የአካውንቲንግ፣ባንክ እና አስተዳደር ላይ ብቻ ያተኮረ ሳይሆን በኢንፎርሜሽን ዘመን ስልታዊ ስልጠናዎች ከተለያዩ የሙያ ክህሎቶች ጋር መሰጠት ስላለበት በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ስር ሆኖ የቢሮክራሲ ሰለባ መሆን ለንግድ ሥራ ዩንቨርስቲዎች እጅግ አስቸጋሪ ከባቢያዊ ሁኔታ ከመፍጠሩም በላይ እድገታቸውን ያቀጭጨዋል ተወዳዳሪ ዓለምንም አልፏቸው እንዲሄድ ያደርጋል። 

በአዲስ አበባ ራስ አበበ አረጋይ መንገድ በተለምዶ ሰንጋ ተራ ከሚባለው ቦታ ለ80 ዓመታት የንግድ ሥራ ኮሌጅ ያለበት ግቢ 

የንግድ ሥራ ኮሌጅ ምሩቃን ማኅበር የት ገባህ? ኮሌጁ ለምን ቦታውን እንዲለቅ ይደረጋል?

የአዲስ አበባ ንግድ ሥራ ኮሌጅ አንዱ ዝነኛ የውጪ አካሉ ወይንም አጋሩ ውስጥ የሚቆጠረው የንግድ ሥራ ምሩቃን ማኅበር ነው። የንግድ ሥራ ምሩቃን ማኅበር የተመሰረተው በ1941 ዓም ሲሆን የማኅበሩ አባላት ከሚንስትርነት ማዕረግ እስከ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ከፍተኛ ባለሙያዎች ድረስ አባላት ናቸው።በኢትዮጵያ የግልም ሆነ የመንግስት መስርያ ቤቶች የማኅበሩ አባላትን ማግኘት ከባድ አይደለም። አሁን የማኅበሩ አባላት የንግድ ሥራ ኮሌጅን ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ስር ወጥቶ በራሱ የሚተዳደር የንግድ ዩንቨርስቲ እንዲሆን ማድረግ እና አሁን በተለይ የተጋረጠበትን በሰንጋ ተራ ራስ አበበ አረጋይ መንገድ የሚገኘው እና ላለፉት 80 ዓመታት  የነበረበትን ህንፃ እንዲለቅ መጠየቁን ሪፖርተር እንግሊዝኛ ዛሬ ሐምሌ 24/2013 ዓም ዘግቧል።ጉዳዩን በመቃወም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ የንግድ ሥራ ኮሌጅ በቅርስነት መመዝገቡን የሚገልጥ ደብዳቤ ፅፏል።




የአዲስ አበባ አስተዳደር ለኮሌጁ መነሳት የሰጠው ምክንያት ደግሞ በዙርያው  የፋይናንስ ድርጅቶች እየተስፋፉ ስለሆነ ለእነርሱ ማስፋፍያ በሚል ነው። ይህ አስቂኝም አስገራሚም ነው። አንድ ልጅ  ያሳደገውን ወላጁን የመግፋት ሥራ ማለት ነው።የንግድ ሥራ ኮሌጅ ከምንም አንስቶ ኢትዮጵያ ዛሬ የበርካታ ባንኮች ባለቤት አደረጋት።ይሄውም ለ80 ዓመታት ብቁ የሰው ኃይል በማሰልጠን ሲሆን ዛሬ ያደጉት ልጆቹ ኮሌጁን ወደ ተሻለ ቦታ ማድረስ ሲገባቸው ግቢውን ይጋፉት ጀመር።ኮሌጁ ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጠው ምላሽ የገንዘብ ድርጅቶች ዙርያውን መኖራቸው የበለጠ ኮሌጁ እና ድርጅቶቹ ተመጋግበው እንዲኖሩ የሚያደርግ እንጂ ተቃርኖ እንደሌለው ገልጦ ጉዳዩ ትክክል አለመሆኑን ማስታወቁ ተገልጧል።እዚህ ላይ የገንዘብ ድርጅቶች እና ባንኮች የንግድ ሥራ ኮሌጅ ቦታን ከመፈለጋቸው የተነሳ ባላቸው የገንዘብ አቅም የአዲስ አበባ አስተዳደር ቢሮን ተጋፍተው እንዳይሄዱ የሕዝብ ከኮሌጁ ጎን መቆም አስፈላጊ ነው።ምክንያቱም ይህ የኢትዮጵያ የንግድ ታሪክ በዘመናዊው ዘመን የነበረውን አሻራ የማጥፋት አደገኛ አካሄድ ነው።

ባጠቃላይ ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ደረጃ ማድረስ ማለት የነበራትን መስራች ኮሌጆችም ሆነ ድርጅቶች ማንነት አሻራቸው እና ማንነታቸው ሳይነቀል ማሳደግ፣ማበልፀግ እና ለትውልድ ማስተላለፍ ነው።የአዲስ አበባ ንግድ ሥራ ኮሌጅም ከቦታው የማንሳቱን ሙከራ በብርቱ መቃወም ያስፈልጋል። ይህ ብቻ አይደለም።የንግዱ ማኅበረሰብ፣የገንዘብ ድርጅቶች፣ባንኮች፣የንግድ ምክር ቤት እና የንግድ ሥራ ኮሌጅ ምሩቃን ማኅበር ድርጊቱን ከመቃወም አልፈው ኮሌጁ ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ስር ወጥቶ በራሱ የተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ቅርንጫፍ ኮሌጆች እንዲከፍት በማድረግ የኢትዮጵያን የንግድ ሥራ እንዲሁም የአፍሪካ የንግድ ሥራ የልቀት ማዕከል ለማድረግ መነሳት ያስፈልጋል።ለእዚህም የመንግስት አካላትን ቀርቦ ማስረዳት እና አፈፃፀሙን መከታተል ይፈልጋል።

==========================
ማስታወቂያ /Advertisement 
===============================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

Thursday, July 29, 2021

ኢትዮጵያን ለመከፋፈል በምዕራባውያን የተሴረው የሴራ ሰነድ ተጋለጠ! ሙሉ ፅሁፉን ያንብቡ። From Basma to Ethiopia – How C2FC is Using Lethal Journalism to Conduct Information Warfare and Lawfare against Ethiopia

Prime Minister of Ethiopia  Abiy Ahmed (PhD) 
Photo credit to National Interest.org

The sabotage against Ethiopia is exposed.

Project Basma enabled intelligence operations to be cloaked as humanitarian activism, which allowed for covert priming of Syria for regime change. C2FC is using Project Basma’s scheme to attack Ethiopia’s will for survival as a sovereign nation-state, besides priming it for either regime attenuation or regime change. Upcoming narratives will call on rebel coalition to execute regime change so as to stabilize Ethiopia as a Federal Republic, or non-belligerently break it up, while enabling the trial of Abiy Ahmed Ali in an international court.
=====================
Source = Geopolitics Press Realism
=====================

On November 10, 2020, a 7-page report that discussed the potential unraveling of Ethiopia – due to outbreak of war between the Federal Military and TPLF – was concluded and forwarded to a carefully selected team of EU officials, who would then present it to the EU council. The scenario considered in the report was a potential deluge of refugees into Europe from a disturbed region, the Horn of Africa (HoA). The report cautiously analyzed the then 7-day-long armed conflict between ENDF and an alliance of Tigray armed groups, including Tigray Regional Forces and Special Police, and expressed concern about the cohesion of ENDF and possibility of spill-over of the conflict into Oromia region.


The report also cautioned against the tripartite alliance of Abiy Ahmed of Ethiopia, Isaias Afwerki of Eritrea, and Mohamed Abdullahi Mohamed of Somalia. Additionally, the report noted the concerns of Saudi Arabia, which feared the crisis could negatively impact the Gulf region – a concern shared by United Arabs Emirate. Another notable prospect raised by the report was cutting off of the Ethiopia-Djibouti terrestrial transport corridor should the conflict continue unabated (ibid). In May 2021, Goitom Gebreluel opinionated that the HoA is falling under an axis of tyranny led by the 3 aforementioned leaders, and that the tripartite alliance was destabilizing the region.


Among the issues discussed in the West concerning the future of Ethiopia are if Ethiopia can be peacefully broken up if a rebel coalition takes power in Addis Ababa, and then allows the ethno-regional states to use referendum to vote for secession, which the central government will accept. This is to avoid the Somaliland-like limbo where the semi-autonomous state cannot gain full recognition as a republic unless the national government in Mogadishu consents to its secession. For USG and its European Allies, this will allow for a peaceful Yugoslavia-like breakup, while enabling the trial of Abiy Ahmed Ali for crimes against humanity in an international court just as it happened to the last President of Yugoslavia, Slobodan Milosevic.


If Ethiopia accepts regime attenuation, then there will be need for a national dialogue supervised by a Government of National Unity that includes the TPLF (and even excludes Abiy Ahmed), which will oversee a constitutional review that will strengthen decentralization. So far, there has been no assessment of whether Abiy Ahmed can develop a strong personality or valor like Xi Jinping who defeated enhanced political warfare, or if Abiy can take bold decisive actions to survive political warfare. It also overlooks the fact that the Ethiopian people have not shown strong dislike for the government. Even so, popular perception can be changed using witful narrative management that is tailored to drive a wedge between the people and GoE.

Relatedly, how is the USG-EU alliance going to manage the crisis in Ethiopia, while promoting their agenda for Ethiopia?

…this will allow for a peaceful Yugoslavia-like breakup, while enabling the trial of Abiy Ahmed Ali for crimes against humanity in an international court just as it happened to the last President of Yugoslavia, Slobodan Milosevic

Geopolitics.Press

Command and Control Fusion Center (C2FC) Running a Basma-like Campaign on Ethiopia


In a previous post, it was reported that C2FC “has delegated some of its tasks to disparate subsidiary fusion cells that enjoy some degree of operational autonomy but organizational dependence on the fusion center”. So, what are the functions of C2FC and who staffs these fusion cells?

The key functions of C2FC can be summarized as advisory, facilitation, capacitation, and intelligence operations. This post focuses on the information capacitance function of the C2FC and some intelligence operations of its allied military and intelligence organizations. The other functions of C2FC will be discussed in later posts.


Information Capacitance


Information capacitance is key to any propaganda campaign, and in the Ethiopian crisis, it involves moderating and controlling media coverage of the war in Tigray – and armed rebellion in Oromia – in a way that disadvantages GoE. This managed media coverage is quite helpful for fusion cells located in Kenya where they work with anti-Abiy elements in the Kenya Defence Forces (KDF) and National Intelligence Service (NIS) to shape public opinion in favor of supporting TPLF and Oromo secessionists. This clique in KDF and NIS has partnered with other national intelligence agencies and private intelligence firms to train media activists and promote the idea of 2 parallel governments-in-exile – the Oromia Regional National Transitional Government and the Government of the National State of Tigray.


As will be explained later, the current information capacitance operation uses methods and techniques developed in Project Basma, which was a regime change campaign conducted against the government of Syria. The same methods and techniques were then used against Xi Jinping as part of an enhanced political warfare campaign to weaken the Communist Party of China.


Fusion Cells


The staffs of these fusion cells are made up of popular media personalities, journalists, university-educated intellectuals, lawyers, democracy activists, humanitarian aid workers (HAW), private intelligence firms, non-governmental organizations (including the Europe External Programme with Africa [EEPA]), and researchers affiliated with Western humanitarian aid agencies and research institutions. The current conjecture by Geopolitics.Press is that Stratfor and Janes Information Group – which is owned by Montagu Private Equity – do aid the operations of these cells. Among the democracy activists working in, or with, these fusion cells are prominent democracy activists from Kenya, Tanzania, Ethiopia, Somalia, and Uganda; as well as democracy activists based in Europe, Oceania, and North America.


The staff help to create narratives, repurpose description of events, and find ways to deny GoE media publicity. The narrative created by these cells is processed by C2FC before being issued to “media actors” for amplification. The most prized media actors are the multinational media agencies that have a global network of influence which can be leveraged in information warfare campaigns. Consider Reuters with its global network of about 4,000 journalists, and one can get an idea of how a created narrative can be popularized worldwide by these journalists, and even be made the vogue narrative. This was evident during the execution of Project Basma.

Project Basma


In 2014, it was revealed that the Foreign and Commonwealth Office (FCO), Department for International Development (DfID), and Ministry of Defence – which are all part of the Government of the United Kingdom (GUK) – have been running a joint program to capacitate information campaigns and kinetic operations in Syria. This joint program used the methods of “strategic communications, research, monitoring and evaluation, and operational support to Syrian opposition entities” to achieve its goals. The revelations also showed that FCO favored building of “local independent media platforms” to outbid the government in narrative management. This joint program is now known as Project Basma, and it fronted an entity called Basma (after which the project is named).


Basma was cloaked as a civil society group that provided a citizen journalism platform. This can be related to the obtuse civil society organization called Civil Society Reference Group, which is a front for the anti-Abiy clique in KDF and NIS to lobby the Kenyan government to support rebels fighting against GoE.

As a citizen journalism platform, Basma was able to plant stories in international media outlets and run a network of journalists who doubled as intelligence agents. It is still not clear if the Integrity Initiative and Institute for Statecraft played any roles in Project Basma.


Basma Program for Regime Change


In September 2020, leaked documents – which were later acknowledged – revealed that GUK has been funding a propaganda campaign to promote regime change in Syria, as well as buy public sympathy for the armed opposition to Bashar al-Assad’s regime. To cultivate media activists who would serve as stringers in Syria, GUK used the Basma program to train these activists and deploy them to the field. These activists were paired with public relation (PR) firms, which edited and modified their reports before forwarding them to mainstream media outlets as journalistic pieces. The media agencies named in the expose are BBC, Al-Arabiya, Al-Jazeera, and Orient TV.


Private intelligence contractors that were involved in this Syrian campaign include The Global Strategy Network (TGSN), Albany, Analysis Research Knowledge (ARK), and Innovative Communication & Strategies (InCoStrat). InCoStrat and Albany helped the armed opposition to handle media relations. Albany even admitted that its core task was defined as “collecting and organising stories and content that support and reinforce the core narrative”.


Basma was able to plant stories in international media outlets and run a network of journalists who doubled as intelligence agents. 
The Dubai-based ARK describes itself as a humanitarian NGO that has worked with the State Department, FCO, European Union, United Nations, and the Governments of Australia, Canada, and the Netherlands. TGSN prides itself of having Richard Barrett among its directors. Richard Barrett is the former director of global counter-terrorism for the Secret Intelligence Service (popularly known as Military Intelligence Section 6 or MI6). This implies that he knew that some of their Syrian allies had ties – either direct or indirect – to AlQaeda. ARK, which describes some of its functions as “developing civil defence capabilities”, “preventing and countering violent extremism” and “promoting accountability for war crimes, boasts of having operational presence in Kenya and Somalia.

 

 ARK started developing the political narrative for the opposition in 2011 while still in Gaziantep, Turkey; and later partnered with TGSN to run “97 video stringers, 23 writers, 49 distributors, 23 photographers, 19 in-country trainers, eight training centers, three media offices, and 32 research officers”. ARK was tasked with rebranding the public image of Salafi jihadi rebels, and their civil front (or civilian-facing front). Benjamin Norton states that “ARK ran the social media accounts of the White Helmets, and helped turn the Western-funded group into a key propaganda weapon of the Syrian opposition”.


ARK has boasted of providing “regular branded and unbranded content” to “well-established contacts”, which included top media outlets like “Reuters, the New York Times, CNN, the BBC, The Guardian, the Financial Times, The Times, Al Jazeera, Sky News Arabic, Orient TV, and Al Arabiya”. It also sent dozens of articles to be published by Al Hayat and Asharq Al-Awsat (ibid).


When the Supreme Military Council (SMC) of the Free Syrian Army (FSA) was globally denounced for working with violent Salafi mujahideen, ARK was mandated “to establish the image of (SMC and FSA as) a functioning, inclusive, disciplined and professional military body”. A similar situation is ongoing in Ethiopia where TPLF and TDF are being presented in mainstream media outlets as “ functioning, inclusive, disciplined and professional” political party and military body respectively.


TDF field commanders have enjoyed laudatory coverage in mainstream media, with Lieutenant-General Tsadkan Gebretensae of TDF giving an interview to Kenya’s The Elephant in July 2021, where he marketed TDF as the armed military force of the Government of Tigray, not the armed wing of TPLF. In the Interview, Tsadkan presented an image of TDF that is a functioning, disciplined, and professional military body (ibid).



TPLF recently, in an error of judgement, paraded armed children, an act that led to condemnation in Ethiopia.

PHOTO SOURCE: Jeff Pearce.


TPLF has also been accused of trying to achieve moral equivalence by dressing children in Tigray with flags of the Amhara regional State and giving them rifles. Still, the public image of TDF can be softened using clever narrative management and media framing.

ARK is known for “softening the image” of armed groups that Westerners may find troubling as is evidenced in these photographed stickers that it made for the AlQaeda-laced Free Syrian Army.



PHOTO CREDIT: The Grayzone.


Fusion Cells for Intelligence Activities and Lethal Journalism


Understanding the functions and methods of Project Basma makes it easier to understand how C2FC works, and why it chooses the methods it uses to achieve its goals. As mentioned, C2FC’s tasks are delegated to fusion cells.These fusion cells collect and collate raw information about the state of affairs in Ethiopia. This information is obtained through social media posts, direct communication with TPLF cadre, and testimonies of HAW and Tigray diaspora who had spoken with their kin in Tigray.


Also, these cells work with C2FC to fast-track verification of social media accounts of their political and military allies. This explains why the Twitter handle of Getachew Reda, which was started in September 2020, was quickly verified in the second quarter of 2021. Apart from helping its allies and assets dominate the social media space, they also work to stifle the presence (and voice) of their opponents in social media.


Pro-ENDF Facebook Accounts Suspended enmasse just before TDF’s Offensive


The fusion cells work to identify social media accounts that are operated by, or affiliated with, their targeted organizations and persons. In the second quarter of 2021, these cells identified social media accounts that are operated by, or affiliated with, the Ethiopian Information Network Security Agency (INSA), and compiled them before forwarding them to their American aids, who then pressured US-based social media companies to suspend the accounts.


On June 16, 2021, Facebook announced that “it had removed a network of fake accounts in Ethiopia targeting domestic users”, and that these accounts were associated with INSA. This reduced the ability of GoE to control social media messaging inside Ethiopia, while biasing social media parity between TPLF and GoE in favor of the former. Two days later, an alliance of Tigray armed groups, who had consolidated themselves under the umbrella of the Tigray Defence Forces (TDF), launched an offensive called Operation Alula.

TDF is probably named-so to imply its character as a military organization that aspires to be a national military just like the Kenya Defence Forces (KDF) or Rwanda Defence Force (RDF).

Lethal Journalism


Richard Landes identified 3 forms of partisan war journalism. They are patriotic war journalism (e.g GoE insisting that Ethiopian media should not describe TDF as a military force but instead use TPLF to describe both TPLF and TDF), lethal war journalism (e.g foreign media reports TPLF’s propaganda as authentic news), and own-goal war journalism (where Ethiopian media reports TPLF’s propaganda as authentic news). The latter two forms of war journalism are what constitutes lethal journalism, whose aim is to de-energize the will of the target polity to resist the messaging and acts of C2FC.In June 2021, GoE punished Addis Standard, an Ethiopian Media, for own-goal war journalism; an act which was condemned by the West using carefully scripted words, which reveals the influence of C2FC.


Professor Landes identifies lethal war journalism as prone to promoting narratives, and this is exactly what happens in Ethiopia. Starting from November 2020, GoE has been described as an ego-bloated, incapable, and cruel belligerent fighting to destroy the Tigray people, and this makes TPLF’s armed opposition a moral obligation that the world should support. The coordinated and synchronized delivery of this narrative by Western mainstream media reveals that C2FC manages the media scripting.


As Landes notes, lethal journalism works to promote a narrative using stories and claims of events, and “when (these) claims (are) disproven…these news outlets (do) nothing to correct their errors“. This was evident in July 2021 when Amnesty International purposely misguided its audience by using photographs – taken by Amanuel Sileshi – of Ethiopians being frisked, before entering a polling station, to condemn GoE for ethnic profiling in Addis Ababa.


Lethal journalism can be augmented by tweaking the algorithms of search engines. This can allow C2FC to exploit search engine algorithms so as to bias internet search results, with the goal being to improve the ranking of any article that sheds positive information about TPLF. This helps achieve information dominance, where the information provided by a specific actor dominates the reporting by mass media and social media.


Information capacitance as applied to lethal journalism allows for deployment of a legally-sound, short-term media strategy that is laden with propaganda value and good optics. This explains why almost the same message against the Ethiopian government has been released by supposedly different Western governments, aid agencies, journalists, reports (published by research institutions), and social media personalities.

Lawfare


In 2011, ARK partnered with Tsamota to develop a subproject within Basma called the Syrian Commission for Justice and Accountability. This name was later changed in 2014 to the Commission for International Justice and Accountability (CIJA). CIJA used seed fund provided by the Conflict Pool of GUK to build a transitional justice architecture to execute lawfare against the Assad government should the plan for regime change fail. The goal was to bring cases against top Syrian government officials in international courts, and then use these cases to justify specified narratives, as well as call for sanctions to be imposed on Syria.


During the Ethiopian crisis, there have been coordinated calls by pro-TPLF intellectuals, lawyers, democracy activists, NGOs, and private intelligence firms for Abiy Ahmed to be tried in an international court for crimes against humanity. In February 2021, the National Interest published a post with a self-revelatory title: Abiy Ahmed: The First Nobel Laureate On Trial at the International Criminal Court? The author, Michael Rubin, called for Abiy to “face war crimes charges”. However, this trial can only happen if Abiy is removed from power, failure of which, the calls for his prosecution will be used to justify sanctions against GoE and its top officials. This can result in sanctions being imposed on the Ethiopian people.


Source of the above article = Geopolitics Press


==========================
ማስታወቂያ /Advertisement 
===============================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 


Tuesday, July 27, 2021

ተረፈ ህወሓት እና ጀሌው እየተነሳ ነው? ወይንስ ሊነሳ ወደማይችልበት አዘቅት እየወረደ? ብሔራዊ ጦር ሙሉ በሙሉ ወደ ጦርነቱ አለመግባቱስ የሚደነቅ ስልት ወይንስ የሚነቀፍ?

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ (ዶ/ር)

የሁሉንም ጥያቄዎች ምላሾች በእዚህ ፅሁፍ ውስጥ ያገኛሉ።

አንድን ጉዳይ ከስር መሰረቱ መመልከት እና ዕውነታውን ሀቅን መሰረት ባደረገ መልኩ መመልከት ተገቢ ነው።ከእዚህ በተለየ  በሆይሆይታ እና በየቦታው በተበጣጠሱ የማኅበራዊ ሚድያ ሽርፍራፊ ቪድዮዎች እና በውሸት ሰበር ዜና በተጥለቀለቀው የዩቱብ ተዳዳሪዎች የህልም ወሬ እና እየሆነ ያለው እውነታ ፈፅሞ የተለያየ ነው። 

ሽብርተኛው ህወሓት አመራሩ ከ70 በመቶ በላይ ሳይደመሰስ በፊት ማለትም የዛሬ 9 ወር ገደማ  ከ300 ኪሎ ሜትሮች በላይ የሚወነጨፍ ሚሳኤል ይዞ ነበር።በአንድ ወቅት በጠቅላይ ዓቢይ እንደተገለጠው የኢትዮጵያን የመከላከያ አቅም እስከ 80 በመቶ በእጁ ነበር።በልዩ ኃይል ስም ያሰለጠነው ሰራዊት ወደ 200 ሺህ ይጠጋ ነበር።በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጦር ውስጥ ከመገናኛ ክፍሉ እስከ አየር ኃይል የራሱ የሚላቸው ከፍተኛ መኮንኖች ነበሩ።የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብትን ከአስመጪ እና ላኪ እስከ ሆቴል እና ማዕድን ማምረት ውስጥ ሁሉ እጁ ነበረ።ይህ ሁሉ በእጁ የነበረው በኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ እየተመራ ያለው የለውጥ አስተዳደር ወደ ስልጣን ከመጣ በኃላ ሁሉ ነው።

በሕዝባዊ ማዕበል ፈርጥጦ መቀሌ የገባው የህወሓት አመራር እና ጀሌው ፈርጥጦ ሲገባ ሁለት ነገሮችን ታሳቢ አድርጎ ነበር።እነርሱም - የመጀመርያው የመሃል ሃገሩን  የአማራ እና የኦሮሞን እንዲሁን የሱማሌ እና ደቡብን ጭምር የጦርነት ማዕከል ማድረግ እና ትግራይን እጅግ ሰላማዊ መዳረሻ ማድረግ ሲሆን፣ሁለተኛው ደግሞ በመሃል ሀገር በሚለኩሰው ጦርነት ህዝብም ሆነ ዓለምአቀፍ የጥቅም ተጋሪ ባዕዳን አዣዞቹ ወደ ስልጣን ተመልሶ ሀገር እንዲረጋጋ እለመናለሁ የሚሉ ሕልሞች ነበሩ።በእዚህም መሰረት ከቡራዩ እስከ ጌድዮ፣ከጅጅጋ እስከ መተከል፣ከሻሸመኔ እስከ ኮንሶ ከፅንፈኛ ኃይሎች ጋር በመሆን በቆሰቆሳቸው እና ባስቆሰቆሳቸው ግጭቶች ብዙ ሺዎች ተፈናቀሉ፣አያሌዎች ሞቱ፣የእምነት ቦታዎች ተቃጠሉ፣በርካታ ንብረት ወደመ።ሆኖም ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላቱን ለይቶ አውቆ የተፈናቀሉትን እየመለሰ፣ቤተሰቦቻቸው የሞቱባቸውን እያፅናና ሁሉን መሻገር ቻለ።በህወሓት ወደ መሃል ሀገር የተወረወረው ትኩስ የመከራ ድንች መሃል ኢትዮጵያን እንደፈለጉት ሊያተራምስ አልቻለም።ስለሆነም ''ጥራ ቢሉት እራሱ መጣ'' እንዲሉ መጨረሻ ላይ የመከላከያ ሰራዊት ላይ የተቀናጀ ጥቃት ከፍቶ ኢትዮጵያን ከመከላከያ ሰራዊት ውጪ አድርጎ ኢትዮጵያን ለባዕዳን ለማስረከብ ተደራደረ።አንዳንድ ባዕዳን የህወሓትን በመከላከያ ላይ የሚፈፅመው ጥቃት ቀድመው እንደሚያውቁ ቆይቶ የታዩ ምልክቶች ያሳያሉ።

ጥቅምት 24፣2013 ዓም በትግራይ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ሲፈፅም አሁንም 'ትኩስን ድንች' ወደመሃል ኢትዮጵያ ወርውሮ መሃል ሃገሩን ለማጋጨት እና ወደ የማያባራ እልቂት ለመክተት ማቀዱ ግልጥ ነበር። ለእዚህም ዋና ማሳያው በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት እንደፈፀመ ወዲያውኑ ወደ አማራ እና አፋር ክልል ጥቃት ለመሰንዘር ሞክሮ ነበር።ሆኖም ግን የኢትዮጵያ መከላከያ ጦር እንዲሁም የአማራ ልዩ ኃይል እጅግ በፈጠነ እና በሚያስደንቅ ጀግንነት ህወሓት እና ጀሌውን ከመመከት አልፎ ማጥቃት ቻለ።የመከላከያ ኃይሉ በቀናት ውስጥ መላዋ ትግራይን መቀሌን ጨምሮ ከህወሓት ጀሌ ነፃ አወጣት።ይህ ብቻ አይደለም የህወሓት ጥርስ የነበረው የመካናይዝድ ጦር እና ሚሳኤል ጨምሮ መከላከያ ኃይል መልሶ ተረከበ።የህወሓት አመራር ከ70 በመቶ በላይ ያለው አመራሩ እና ጀሌው እርምጃ ተወሰደበት።የቀረውን የጦር መሳርያ ደግሞ መከላከያ ባለበት አመከነው።በእዚህ ተረፈ ህወሓት እና ጀሌው እየተነሳ ነው?  ወይንስ ሊነሳ ወደ የማይችልበት አዘቅት እየወረደ? 

መከላከያ በትግራይ ከቆየ በኃላ ሰኔ  21/2013 ዓም በፖለቲካዊ ውሳኔ መከላከያ ሰራዊት ከመቀሌ ወጣ።ሰራዊቱ ከመቀሌ የወጣበትን ምክንያት በግልጥ ተነግሯል።የትግራይ ገበሬ የሚያርስበት ጊዜ ለመስጠት እና በመጪው ዓመትም የህዝብ እና የሀገር ሸክም እንዳይሆን እና  በህወሓት እና ጀሌው ፕሮፓጋንዳ የተወናበደው ሕዝብ በቂ የጥሞና ጊዜ እንዲያገኝ ነው።ይህም ሆኖ ግን ህወሓት ወደ መሃል ሀገር ልትገፋው የፈለገችው የጦርነት አውድማ እዚያው ትግራይ ውስጥ ገብቶ ትግራይን ሰላም አሳጣት።መከላከያ ከወጣ በኃላ ትግራይ ለትግራይ ሕዝብ ሲኦል ሆናለች።ወጣቶች ይታፈሳሉ፣እናቶች ለተረፈ ህወሓት ስልጣን ሲባል ልጆቻቸውን ካልሰጡ እርዳታ እንደማይሰጣቸው ተነግሯል።ማጅራት መቺው በከተማ፣አድፍጦ የሚዘርፈው በገጠር ተሰማርቶ ሕዝቡን እያመሰ ነው።ሕፃናት እየተነዱ ወደ ጦርነት ተማገዱ። በራያ ግንባር ብቻ በአንድ ቀን ብቻ በአስር ሺዎች የህወሓት ጀሌ ረገፈ።አስከሬኖቹን ለመቅበር ሳምንታት አይበቁንም ሌሊት አስከሬኖቹን ለመብላት የሚመጡት ጅቦች አስቸገሩን ያለው የአፋር አርብቶ አደር በራሱ መቅበር ይዟል።
በእዚህ ተረፈ ህወሓት እና ጀሌው እየተነሳ ነው?  ወይንስ ሊነሳ ወደ የማይችልበት አዘቅት እየወረደ? 

ዛሬ ትግራይ በኢትዮጵያ ካሉት ክልሎች በሙሉ የተጎሳቆሉ ሰዎች የሚኖሩባት፣በ1ነጥብ 2 ሚልዮን ይቆጠር የነበረው በምግብ እርዳታ የሚኖረው ሕዝብ አሁን ሁሉም በሚያስብል ደረጃ ተመፅዋች ሆኗል።ይህንን የተራበ ሕዝብ በምግብ እየደለለ ወደጦርነት ለመክተት ተረፈ ህወሓት እየሞከረች ነው።ትምህርት ቤቶች፣የጤና ጣብያዎች፣ገበያዎች ባዶ ሆነዋል።የትግራይ ወጣቶች በሙሉ ካሉበት ክፍል ወደ የሚቀጥለው ሳይሸጋገሩ ባሉበት ይደግማሉ።የተረፈ ህወሓት እና ጀሌው የመሃል ሀገር ደጀን ኢትዮጵያን ለማተራመስ ሲወራጭ የተደረሰበት ከሆቴል ንግድ እስከ አስመጪ እና ላኪ ሕጋዊ እርምጃ እየተወሰደ ነው።በኤፈርት እና ትግራይ ልማት ማኅበር ስም ሲመዘብር የነበረው የምጣኔ ሀብት ጉልበት ተሽመድምዷል።አሁን የቀረው በአዲስ አበባ በራይድ ታክሲ እየተሹለከለከ ሴራ የሚያሴረው ነው።ይህም በዕይታ ውስጥ ስለሆነ የትም አያመልጥም።በእዚህ ተረፈ ህወሓት እና ጀሌው እየተነሳ ነው?  ወይንስ ሊነሳ ወደ የማይችልበት አዘቅት እየወረደ? መልሱ ግልጥ ነው።ህወሓት እየተናሳ ሳይሆን ሊነሳ ወድየማይችልበት አዘቅት እየወረደ ነው።የቁልቁለት ጉዞው በአዘቅት ውስጥ በመግባት የሚቆም አይደለም።ታሪኩም ይቀበራል።አሟሟቱ እና አቀባበሩ ሲተረክ ህወሓት ለመጪዎቹ ትውልዶች ሁሉ 'በዘራችሁ አይድረስ' በሚል ዓረፍተ ነገር የታጀበ ይሆናል።ዛሬ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ትግርኛ በመናገራቸው ብቻ የተሰለፉ ያፍራሉ።ለልጅ ልጆቻቸውም የሚያቆዩት የባንዳነት ጠባሳ ብቻ ይሆናል።የባንዳነት ጠባሳ አያኮራም።አንገት ያስደፋል።ከእዚህ ውርደት ለመዳን 'አንድ ሐሙስ በቀረው' ተረፈ ህወሓት ላይ ተነስቶ የትግራይን ሕዝብ ነፃ ማውጣት ብቻ ነው ያለው መፍትሄ።

ይህ በእንዲህ እያለ የኢትዮጵያ መከላከያ ሙሉ በሙሉ ወደ ፍልምያው አለመግባቱ ትክክለኛ ስልት ነው ወይንስ ሌላ? ይህንን እያነሱ አንዳንዶች ሕዝብ ለመከፋፈል ጥቂቶች ደግሞ ሳይገባቸው የሚያነሱት ጥያቄ ነው።እዚህ ላይ ኢትዮጵያ በዙርያዋ እና በማዶ ያሉ ባዕዳን ታሪካዊ ጠላቶቿን የማይመለከቱ እና የኢትዮጵያ ጠላቶች ዋና ግብ ያልገባቸው ናቸው።ከተረፈ ጁንታው እና ጀሌው ጋር የኢትዮጵያ መከላከያን በትነው ኢትዮጵያን ለመቀራመት የተነሱ ባእዳን ዋና ግብ እና ስልት የሚያጠነጥነው በመከላከያ ሰራዊትን አቅም ማድከም እና በእርስ በርስ ጦርነት መወጠር ነው። የኢትዮጵያ ጦር ኃይል ከተረፈ ህወሓት ጀሌ ጋር ሲፋተግ በሚፈጠረው መድከም ሁለት ክፍተቶች እንዲፈጠሩ የባንዳው ተረፈ ህወሓት ጀሌ እና የኢትዮጵያ ባዕዳን ጠላቶች ምኞቶች ናቸው።እነርሱም ፣ የመጀመርያው መከላከያው ሲዳከም ባዕዳን በኢትዮጵያ ላይ የቀጥታ ጥቃት እንዲፈፅሙ ስለሚረዳቸው እና ሁለተኛው ደግሞ የመከላከያው ከተረፈ ህወሓት እና ጀሌው ጋር ሲዋጋ በመሃል ሀገር የጎሳም ሆነ የሃይማኖት የፅንፍ ኃይሎች ማዕከላዊ መንግስትን እንዲገዳደሩ በማድረግ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የታቀደ ዕቅድ ነው። 

እነኝህ የኢትዮጵያ መከላከያን በተረፈ ጁንታው ሽብር ውግያ ወጥሮ ኢትዮጵያን የማፍረስ ሙከራ የጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ መንግስት በሚገባ ተረድቶታል።በመሆኑም መከላከያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ''ልፍያ ውስጥ አንገባም'' በማለት የገለጡት የመከላከያውን ወደ የማያበቃ ፍትግያ  በመክተት በመደበኛ ውግያ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ለሚፈልጉ ባዕዳን ሃገርን ከማጋለጥ የሽብርተኛውን የተረፈ ጁንታ እብሪት ከመላዋ ኢትዮጵያ በተውጣጡ የልዩ ኃይሎች፣የደጀን ተዋጊ እና በሚልሻም ጭምር ትዕቢቱን ከአፈር እየደባለቀ የመከላከያ ሰራዊት እና የአየር ኃይል አስፈላጊ በሆኑ ቁልፍ እና ስልታዊ ስራዎች እንዲያግዝ መደረጉ የኢትዮጵያን ባዕዳን ጠላቶች እና ባንዳው ተረፈ ጁንታውን ያስደነገጠ እና ዕቅዱን ሁሉ ያከሸፈበት ነው። ዛሬ ሺዎች ከመላዋ ኢትዮጵያ የተረፈ ጁንታውን እና ጀሌውን ለመደምሰስ ተሟል።የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል እስኪደመም ድረስ ደጀኑ ሕዝብ ታጥቆ ደርሷል።ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚሞክር እንዴት እንደሚፈራርስ ዓይናችን የሚያይበት ቀን ደርሷል።ከውስጥ እና ከውጪ ሆነው በወሬ ኢትዮጵያውያንን ለማተራመስ የመንግስት ተቃዋሚ እና የአማራ ሕዝብ ወዳጅ እየመሰሉ ሊያታልሉ የሚሞክሩ እና የተረፈ ጁንታው የውስጥ አርበኛ ለመሆን ትግርኛ መናገርን እንደ መስፈርት አድርገው የትግራይን ሕዝብ ለማታለል የሚሞክሩ በአዲስ አበባ እና በውጭ በምቾት የሚኖሩ የሕፃናት ደም ተጎንጪዎች ከሃይማኖት ድርጅት እስከ ምሁር ነኝ ባይ፣ከጠጅ ቤት እስከ መንግስት መስርያቤት ያሉ ሁሉ  ከህዝብ ዓይን አያመልጡም።አንድ በአንድ ይጋለጣሉ።ፍርዳቸውን ይቀበላሉ።



==========================
ማስታወቂያ /Advertisement 
===============================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...