ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, September 27, 2021

የመስቀል ደመራ በመቀሌ እና ሌሎች የትግራይ ከተሞች በመስቀል አደባባይ ላይ ያልተከበረበት እውነተኛ ምክንያት እና የቪኦኤ መቀሌ ዘጋቢ ጋዜጠኛ ሙሉጌታ የተዛባ ዘገባ


==============
ጉዳያችን / Gudayacn
==============
ከዜናው ስር የዘንድሮ የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ  ሙሉ አከባበር ቪድዮ ያገኛሉ።
===============

የመስቀል ደመራ በዓል በመላው ኢትዮጵያ በደመቀ እና ካለምንም የፀጥታ ችግር መከበሩን ለማወቅ ተችሏል።በተለይ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ፣ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እና ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያሪኮች፣የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ፣የባህል ሚኒስትር እና አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች በተገኙበት ቁጥሩ ከግማሽ ሚልዮን በላይ የሚሆን ሕዝብ በተገኘበት ተከብሯል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በትግራይ መቀሌ የመስቀል ደመራ በመስቀል አደባባይ  አለመከበሩን ለማወቅ ተችሏል።በዓሉ በአጥብያ አብያተ ክርስቲያናት ግን ቁጥሩ ውሱን ሕዝብ በተገኘበት ከስጋት ጋር ተከብሯል።ይህንኑ ሁኔታ የቪኦኤ አማርኛ እና ትግርኛ የመቀሌ ዘጋቢ ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አረጋግጧል።ሆኖም ግን ጋዜጠኛ ሙሉጌታ የደበቀው እውነትም አለ። 

በመቀሌም ሆነ በሌሎች የትግራይ ከተሞች የመስቀል ደመራ በአደባባይ ያልተከበረበት እውነተኛ ምክንያት  የሚከተለው ነው። የመጀመርያው ምክንያት ሽብርተኛው ህወሓት የግዳጅ አፈሳ በከተሞች ውስጥ ከመቼውም ጊዜ በባሰ አፈሳ ላይ በመሆኑ እና ወላጆች ልጆቻቸውን በቤት ውስጥ እየደበቁ እና የቻሉት ደግሞ ራቅ ወዳሉ የገጠር ቦታዎች ከመላካቸውም በላይ ትግራይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት ካህናትም  የመስቀል ደመራ በአደባባይ እንዲከበር በማድረግ ልጆቻችንን ወደ ጦርነት አንልክም በማለት በእየአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት እንዲከበር ወስነዋል።በአጥብያ አብያተ ክርስቲያናትም ወጣቶች በተቻለ መጠን ለመደበቅ የሞከሩ ሲሆን በዕድሜ የገፉ እና ታዳጊ ወጣቶች እየፈሩም ቢሆን በአጥብያ አብያተ ክርስቲያናት ተገኝተው በዝማሬ እና በደመራ አክብረዋል። 

በሌላ በኩል የትግራይ ክልልን በውስን ደረጃ ተቆጣጥሮ የሚገኘው የህወሓት ቡድን በዓሉ በመቀሌ በአደባባይ እንዲከበር ለማስገደድ የሞከረ ቢሆንም የበዓሉ በአደባባይ ሲከበር የተደበቁ ወጣቶች እንዲወጡ እና ለማፈስ በማቀድ መሆኑን ያወቁት የቤተክርስቲያኒቱ ኃላፊዎች አልተቀበሉትም።አንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች ስጋት ደግሞ ከአፈሳም በዘለለ የሄደ ነው።በትግራይ የሚገኙ የዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ሰራተኞች ያሾለኩትን ዜና ያገኘችው ጉዳያችን እንደተረዳችው፣ህወሓት በመቀሌ በመስቀል አደባባይ የመስቀል በዓል እንዲከበር  የፈለገበት ምክንያት ከፍተኛ የህዝብ እልቂት እንዲፈፀም አድርጎ የፌደራል መንግስት የአየር ጥቃት በሕዝቡ ላይ ፈፀመ ወይንም የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች እንዲገኙ ተደርጎ ፍንዳታ ፈፅሞ መንግስት አደረገው በሚል የደረሰበት ሽንፈት ላይ ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ በመጮህ ነፍስ ለመዝራት የመስቀል ደመራን ሊጠቀምበት ይፈልጋል የሚል ጥርጣሬ በሕዝቡ ውስጥ ሲወራ ነው የሰነበተው። 

በመጨረሻም ከመቀሌ ለአሜሪካ ድምፅ ራድዮ የአማርኛ እና ትግርኛ ዘጋቢ ጋዜጠኛ ሙሉጌታ በዓሉ በአጥብያ አብያተ ክርስቲያናት ተወስኖ እንዲከበር የተደረገበትን ምክንያት ከእውነተኛ ምክንያት ከመደበቁም በላይ አንድም ጉዳዩ የሚመለከታቸውን የቤተ ክርስቲያኒቱን ኃላፊዎች ወይንም የህወሓት ተጠሪዎችን ሳያቀርብ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ዘንድሮ ለማክበር አያስፈልግም አሉ በሚሉ ቀላል ቃላት አልፎታል። የአሜሪካ ራድዮ ከላይ በጉዳያችን የደረሳትን ምክንያቶች አንስቶ ጋዜጠኛ ሙሉጌታን እንደሚጠይቀው ተስፋ አለን። አሁን የትግራይ ሕዝብ እውነታውን ሰብሮ መውጣት አለበት።ህወሓት ማለት ትግራይ አይደለም።ትግራይ ካለህወሓት መኖር ትችላለች።ይህን ሳይናገሩ እና ለእዚህም ሳይታገሉ የትግራይ ሕዝብ በህወሓት ሲፈጅ እየተመለከቱ የራሳቸውን የምቾት ኑሮ በውጭ ሀገር እና በመሃል ሀገር የሚኖሩ የትግራይ ኤሊቶች የትግራይ ሕዝብ በታሪክ ይፋረዳቸዋል።

የ2014 ዓም የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ቪድዮ ክፍል 1 እና 2 
ምንጭ - ኢቢሲ 
ክፍል 1

ክፍል 2 







Saturday, September 25, 2021

Tigray forces went door-to-door killing men and teenage boys. ''የህወሓት ኃይሎች በር ለበር እየሄዱ አዋቂ ወንዶችና ታዳጊ ወንዶችን እየመረጡ ገደሉ'' አሶሼትድ ፕሬስ መስከረም 15/2014 ዓም (ሴፕቴምበር 25/2021)


አሶሼትድ ፕሬስ ዛሬ መስከረም 15/2014 ዓም የህወሓት ጀሌዎች በር ለበር እየሄዱ ወንዶች እና ታዳጊ ልጆችን እየመረጡ በቆቦ ስለፈፀሙት ግድያ የዓይን ምስክሮች ጨምሮ የሰራው ዜና ሙሉ ፅሁፍ 
  • Tigray forces went door-to-door killing men and teenage boys.
  • ''የህወሓት ኃይሎች በር ለበር እየሄዱ አዋቂ ወንዶችና ታዳጊ ወንዶችን እየመረጡ ገደሉ'' አሶሼትድ ፕሬስ መስከረም 15/2014 ዓም (ሴፕቴምበር 25/2021)

‘Then the killing started’: Witnesses accuse Tigray fighters

Source: AP

NAIROBI, Kenya (AP) — One man said he counted 55 corpses as he escaped from his town in northern Ethiopia, stepping over bodies scattered in the streets. Another asserted he was rounded up with about 20 men who were shot in front of him. Yet others claimed Tigray forces went door-to-door killing men and teenage boys.

The allegations from the town of Kobo are the latest against Tigray forces as they push through the neighboring Amhara region, in what they call an attempt to pressure Ethiopia’s government to end a 10-month war and lift a deadly blockade on their own home. Both Amhara and Tigrayan civilians have joined the fight, and calls by the United States and others for peace have had little effect as war spreads in one of Africa’s most powerful countries.

The accounts from Kobo are the most extensive yet of one of the deadliest known killings of Amhara in the war. The estimates of deaths there range from the dozens to the hundreds; it is not clear how many were killed in all or how many were fighters as opposed to civilians, a line that is becoming increasingly blurred.

The Associated Press spoke with more than a dozen witnesses who were in Kobo during the killings, along with others who have family there. They said the fighting started on Sept. 9 as a battle but quickly turned against civilians. At first, Tigray forces who had taken over the area in July fought farmers armed with rifles. But after the Tigray forces briefly lost and regained control of the town, they went door-to-door killing in retaliation, the witnesses said.

“We did our best, whether we die or kill, but what is heartbreaking is the massacre of innocent civilians,” said one wounded resident, Kassahun, who was armed. Like others who spoke to the AP after fleeing, he gave only his first name to protect family members still in town.

His account was echoed by a health worker who gave first aid to several wounded people. The health worker said Tigray forces withdrew from Kobo on the afternoon of Sept. 9 and returned several hours later, once local militia units had run out of ammunition and retreated.

“Then the killing started,” he said, speaking on condition of anonymity for fear of retaliation.

The area of fighting is under a communications blackout, complicating efforts to verify accounts. Calls to the local administrator went unanswered. Ethiopia’s state-appointed Human Rights Commission this week said it had received “disturbing reports” of alleged “deliberate attacks against civilians in Kobo town and surrounding rural towns by TPLF fighters.”

The acronym stands for the Tigray People’s Liberation Front, which dominated Ethiopia’s repressive national government for 27 years but was sidelined by current Prime Minister Abiy Ahmed. What began as a political dispute erupted into war in November in the Tigray region, with thousands killed.

While atrocities have been reported on all sides, the worst massacres recounted by witnesses have been against the civilians of Tigray, along with gang-rapes and deliberate starvation. They were blamed on the Ethiopian government, Amhara militias and Eritrean soldiers.

However, since the Tigray forces in June retook much of their region and entered Amhara, accusations have been piling up against them, too. Amhara civilians in multiple communities have alleged that the Tigray fighters are killing them in retaliation, as the war grows bigger and more complex.

Most allegations cannot be verified immediately, given a lack of access. But in September, the AP reached the scene of an alleged massacre in Chenna Teklehaymanot, where at least dozens of Amhara were reported killed, both fighters and civilians. The AP saw bodies scattered on the muddy ground, some in the uniforms of fighters and others in civilian clothing, and residents alleged at least 59 people were buried in a nearby churchyard.

The Tigray forces have denied targeting civilians. Tigray forces spokesman Getachew Reda told the AP that the accounts from Kobo “are just a figment of someone’s imagination. There was no such thing as our forces going in every house and targeting civilians.” He blamed local militia, “irregular units,” and that “people who were hiding their guns” joined them.

“They fought and our forces had to fight back,” Getachew said. Asked about the calls for peace, he said “this cessation of hostilities thing needs to be taken seriously, but it takes two to tango,” referring to Ethiopia’s government.

As in Tigray, civilians are caught in the middle.

One resident, Mengesha, said he counted 55 corpses in the town. It was not clear whether they were of fighters or unarmed civilians. “I escaped by stepping over the dead bodies,” he said. Like other witnesses, he fled to Dessie town 165 kilometers to the south.

Birhanu, a farmer, said he and his friend were walking home on Sept. 9 when they were rounded up with about 20 other men.

“They were shot in front of us,” he said. “The fighters took us to their camp and made us line up and then picked who would be shot. I managed to run away with my friend.”

He said the Tigray fighters fired at them as they fled, severing two fingers on his right hand.

Another resident, Molla, said he bandaged his wounds with grass and walked for days to safety.

“(The Tigray forces) were indiscriminately killing people, especially men,” he said. “They dragged them out and killed them while their mothers were crying. They killed my uncle and his son-in-law on his doorstep.”

A third resident, Ayene, said he watched out a window as fighters took his three brothers out of their nearby home and shot them on the street at point-blank range, along with four others.

“Then the fighters called me outside to shoot me, but luckily a woman intervened and I was saved,” he said. “There were so many bodies, I lost my mind.”

Before fleeing, Kobo residents said they spent days recovering bodies. One shop assistant, Tesfaye, said he locked himself inside his house, and then counted 50 bodies once the firing stopped.

“I saw many of my friends who were dead on the street,” he said. “I was just crying, then I went to bury them.”

___

Cara Anna in Nairobi, Kenya contributed.

Friday, September 24, 2021

የኢትዮጵያ አዲሱ የፌድራል ሀገረ መንግስት ምስረታ እና የክልል መስተዳድሮችን በስምንት ቀናት ውስጥ መመስረትና የተከበሩ የፓርላማ አባል ሙ/ጥ/ዲ/ን ዳንኤል ክብረት በሽብርተኛው ህወሓት የተወረሩ ቦታዎች ላይ የተመለከቱትን የተናገሩ - ህወሓት ለትግራይ ሕዝብ የማይራራ አደገኛ ቡድን ነው (አዲስ ቪድዮ)

የኢትዮጵያ ምክርቤት (ፓርላማ) 

=================
ጉዳያችን/ Gudayachn
=================

የኢትዮጵያ አዲሱ የፌድራል ሀገረ መንግስት ምስረታ እና የክልል መስተዳድሮችን በስምንት ቀናት ውስጥ መመስረት

ኢትዮጵያ አዲስ ሀገረ መንግስት ከስምንት ቀን በኃላ ይመሰረታል።በእዚህ መሰረት ሰኞ መስከረም 24/2014 ዓም አዲሱ የኢትዮጵያ ምክርቤት (ፓርላማ) ይሰበሰባል።በእዚህ ስብሰባም ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚመርጥ ሲሆን በዕለቱ ተመራጩ ጠቅላይ ሚኒስትር ታሪካዊ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።አሁን ባለው ሁኔታ የምክር ቤቱን አብዛኛውን ወንበር የያዘው የብልፅግና ፓርቲ ዕጩ አድርጎ የሚያቀርበውም ሆነ ድምፅ የሚሰጠው ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ እንደሚሆን ይጠበቃል።እንደ ብዙዎች የኢትዮጵያውያንም ሆነ አሁን ያለውን የኢትዮጵያ ሁኔታ እና ያለፉት ሦስት ዓመታት ኢትዮጵያን በመምራት ሂደት በሁሉም ዘርፍ ችግሮችን ተጋፍጦ በማሻገር ሂደት አቅማቸውን ያሳዩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ በቀጣዩ አምስት ዓመታት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን እንዳለባቸው ከገጠር እስከ ከተማ የሚኖሩ የብዙ ኢትዮጵያውያን ፍላጎት ነው።በመስከረም 24 የምክር ቤቱ ስብሰባም ከእዚህ የተለየ አካሄድ እንደማይኖር ከወዲሁ ይጠበቃል። 

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከፌድራል ሀገረ መንግስት ምስረታ በፊት የክልል መስተዳድሮች ይመሰረታሉ።በእዚህም መሰረት ክልሎች በምርጫ ያሸነፉት ተመራጮችን በነባሮቹ በመተካት አዳዲስ የክልል ፕሬዝዳንቶች እና የክልል ምክር ቤት አፈጉባኤዎች እንደሚመረጡ ይጠበቃል።በእዚህ መሰረት የክልል መስተዳደሮች የሚመሰረቱበት ቀናት እንደሚከተለው ነው። 

የኦሮምያ ክልል=                መስከረም 15/2014 ዓም  

የአዲስ አበባ አስተዳደር=      መስከረም 18/2014 ዓም  

የደቡብ ክልል=                   መስከረም 19/2014 ዓም 

የአማራ ክልል=                   መስከረም 20/2014 ዓም  

የጋምቤላ ክልል=                 መስከረም 20/2014 ዓም  

የሲዳማ ክልል=                   መስከረም 20/2014 ዓም  

የድሬዳዋ አስተዳደር=            መስከረም 21/2014 ዓም 

በመጨረሻም መስከረም 24/2014 ዓም የኢትዮጵያ ፌደራል ሀገረ መንግስት ምስረታ አዲስ አበባ ላይ ይከናወናል።


የተከበሩ የፓርላማ አባል ሙ/ጥ/ዲ/ን ዳንኤል ክብረት በሽብርተኛው ህወሓት የተወረሩ ቦታዎች ላይ የተመለከቱትን የተናገሩ -  ህወሓት ለትግራይ ሕዝብ የማይራራ አደገኛ ቡድን ነው (አዲስ ቪድዮ)
ቪድዮ = አሚኮ መስከረም 14/2014 ዓም 


============
ማስታወቂያ 
============
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

Ethiopian Government has the ability to resolve its own issues without foreign interference - strong statement from China Government to US


''የኢትዮጵያ መንግስት ያለማንም የውጭ ጣልቃ ገብነት የራሱን የውስጥ ጉዳይ የመፍታት አቅም አለው'' ቻይና ለአሜሪካ መንግስት ያስተላለፈችው መልዕክት - 

Gudayachn

China's Foreign Ministry Spokesperson Zhao Lijian's was on Regular Press Conference on September 23, 2021. In his press conference, he has reflected the China’s stand on US new sanction against Ethiopia. Here is the China's embassy in Norway website posted on how the China Foreign Minister spokesman responded for the question, concerned Ethiopia.

Shenzhen TV: US President Biden signed an Executive Order a few days ago authorizing a new sanctions regime regarding the conflict in Ethiopia. I wonder if China has any comment on this?

Zhao Lijian: China opposes the new US sanctions regime on Ethiopia. China always holds that international law and basic norms governing international relations must be adhered to in state-to-state relations. We oppose the wanton exertion of pressure through sanctions or the threat of imposing sanctions to interfere in other countries' internal affairs. The US should prudently handle relevant issues and play a constructive role in restoring peace and stability in the country.

Ethiopia is China's important cooperation partner in Africa. We believe that the parties concerned in Ethiopia have the wisdom and capability to properly resolve internal differences. It is our sincere hope that Ethiopia could realize national reconciliation and restore peace and stability at an early date.

On the other side, today, September 24,2021 Bloomberg wrote the following on the China's stand regarding the US sanction against Ethiopia.

Bloomberg Report concerning China's respond against US sanction on Ethiopia.September 24,2021

China criticized a U.S. threat to impose sanctions on Ethiopia over a conflict in the Horn of Africa nation, saying the government has the ability to resolve its own issues without foreign interference.

“We oppose the wanton exertion of pressure through sanctions or the threat of imposing sanctions to interfere in other countries’ internal affairs,” Chinese Foreign Ministry spokesman Zhao Lijian said at a briefing Wednesday. “The U.S. should prudently handle relevant issues and play a constructive role in restoring peace and stability in the country.”

Biden last week authorized the Department of Treasury and the State Department to pursue individuals and entities in Ethiopia and Eritrea involved in the conflict that erupted in Ethiopia’s northern Tigray region in November. The U.S. threat of sanctions  aims to bring warring parties to the negotiating table.China is Ethiopia’s biggest bilateral lender, with $6.5 billion in loans, or 23% of the total public debt burden of $27.8 billion, according to World Bank data. China is co-chairing a creditor committee that seeks to reorganize Ethiopia’s external debt.

The conflict in Ethiopia erupted when Prime Minister Abiy Ahmed ordered his military to respond to an attack by Tigrayan state forces on a federal military base. Troops from neighbouring Eritrea supported Abiy’s army in a conflict that has left more than 5 million people in need of humanitarian assistance. No fuel or medicine has been delivered to Tigray since Aug. 16.

Abiy is expected to form a new government in October, after a landslide win by his political party in elections earlier this year. Zhao said China wants Ethiopia to “realize national reconciliation and restore peace and stability at an early date.” 

Source: China Embassy in Norway and Bloomberg 

================================


Monday, September 20, 2021

የተከበሩ የምክር ቤት አባል ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ላይ ነቁጥ ቢፈልጉ ያጡት የህወሓት አፈቀላጤዎች አጣመው ለማቅረብ የሞክሩባቸው ሦስቱ አሉባልታዎች እና እውነታው።

ከፅሁፉ መጨረሻ ላይ ሙ/ጥ/ዲ/ዳንኤል ለአዲስ ዓመት ከኢቢሲ ጋር ያደረገው አዲስ ቃለ መጠይቅ ቪድዮ ያገኛሉ።

================ 
ጉዳያችን/Gudayachn
================
የተከበሩ የምክር ቤት አባል እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የኢትዮጵያዊነት፣የሀገር መውደድ፣በእምነት የመፅናት፣ሁሉንም ኢትዮጵያዊ እንደ ዕምነቱ የማክበር እና የመከባበር ምሳሌነት ሁሉ ምሳሌ በመሆን ያሳየ ኢትዮጵያዊ ነው።ዳንኤል አሁን በአንድ ሰውነት የሚታይበት ጊዜ አይደለም።ሲጀምር ላለፉት 30 ዓመታት በመላው ዓለም እየዞረ ወገኖቹ ኢትዮጵያውያንን አስተምሯል።ትምህርቱ ስለ ሃይማኖት ብቻ አይደለም።ኢትዮጵያን መውደድ እና ኢትዮጵያውያንን ማቀራረብ ላይ ከሀገር ውስጥ እስከ ባሕር ማዶ ሰርቷል።በውጭ ሀገር ያያቸውን አዳዲስ አሰራሮች ሁሉ ለባለሙያዎች ለማካፈል ለፍቷል።ዛሬ ላይ ደግሞ ዳንኤል ከአንድ ሰውነት ባለፈ በሕዝብ ድምፅ ሕዝብ እንዲወክል የኢትዮጵያ ፓርላማ አባል ሆኖ ተመርጧል።በእዚህ አጭር ፅሁፍ ስለ ዳንኤል ለእዚህ ትውልድ እና ለኢትዮጵያ ያደረጋቸውን ለመዘርዘር ጊዜ አይበቃም። ታሪክ ወደፊት በራሱ መንገድ የሰራቸው መልካም ስራዎች እና በጎ ተፅዕኖዎች በራሱ ጊዜ የሚዘከር ስለሆነ ዛሬ እዚህ ላይ መዘርዘር አያስፈልግም።

ከሰሞኑ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ላይ በአዲስ መልክ የተከፈተ የስም ማጥፋት ዘመቻ መሰል እየታየ ነው።ከእዚህ በፊት በተለያዩ ጊዜያት የሐሰት የስም ማጥፋት ሙከራዎች ሲደረጉ የነበረ ቢሆንም ከሰሞኑ ዲያቆን ዳንኤል ንግግር ባደረገበት አንድ ስብሰባ ላይ ''እነርሱ'' የምትለዋን አባባል ''እኛ እና የትግራይ ሕዝብ አንድ ነን'' ባዮቹ የተረፈ ህወሓት አፈቀላጤዎች ከካናዳ እስከ አሜሪካ በመቀጠል ደግሞ ዛሬ  የህወሓት አፈቀላጤዎች የሚያቀርቡለትን እንደ የገደል ማሚቱ የሚያስተጋባው ማርቲን ፕላውት ከእንግሊዝ በትውተር ገፁ ላይ ይህንኑ ህወሓት ሲነቀፍ የትግራይ ሕዝብ ማለት ነው የሚሉትን የሐሰት ወሬ ሲያሰራጭ ተስተውሏል።ከእዚህ ባለፈ የህወሓት ቲቪ (ዩቱብ) አፈቀላጤው አሉላን አቅርቦ ከሰሞኑ የላንቃ መክፈቻ ያደረጉት ዲያቆን ዳንኤልን ነው። ይህ ሁሉ መንጫጫት የሚያሳየው ግን ዳንኤል በእውነትም በምን ያህል ስፋት እና ጥልቀት ተፅኖ እየፈጠረ ብቻ ሳይሆን የጁንታውን ስስ ብልት እንደነካበት የሚያመላክት ነው።

ትናንትም፣ዛሬም ነገም የተከበሩ የምክር ቤት አባል ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ላይ ነቁጥ ቢፈልጉ ያጡት የህወሓት አፈቀላጤዎች አጣመው የሚያቀርቧቸው ሦስቱ ነጥቦች በአጭሩ እናንሳቸው እና እውነታዎቹን በአጭር እንመልከት -

1) የመጀመርያው ሰሞኑን እየቀረበ ያለው ዲያቆን ዳንኤል የህወሓት ከፋፋይ አስተሳሰብ፣አሰራር እና የጥፋት መንገድ ሁሉ ከምድረገፅ መጥፋት አለበት፣ከአእምሮአችን ሁሉ መፋቅ አለበት።ለመጪው ትውልድም ማውረስ የለብንም።የሚለውን ንግግር የትግራይ ሕዝብ ላይ የተነገረ በማስመሰል ከንግግሩ መሃል ገብተው በመቁረጥ ''እነርሱ'' የሚለውን ሁሉ ለትግራይ ሕዝብ እንደተነገረ አጣመው በእንግሊዝኛ ለማቅረብ ሞክረዋል።በንግግሩ ላይ ከፍ ብሎ የሚሰማው ግን በትክክል ያነሳው የህወሓት አመራር እና አስተሳሰቡን ነው።እነርሱን ያለውም ህወሓትን እንጂ የትግራይን ሕዝብ አይደለም።ዳንኤል የትግራይን ሕዝብ የትግራይ አፈቀላጤ ነን ከሚሉት በላይ በታሪክም በአካልም ያውቀዋል።ለአክሱም ሙዚየም የልማት ኮሚቴ  ውስጥ ሲያገለግል፣የዛሬ አፈቀላጤዎች ዱባይ እና ሸራተን ውስኪ ሲያንቃርሩ ነበር።እነርሱ መቀሌን የሚያውቁት ለለቅሶ ወይንም ሰርግ ሲጠሩ ወይንም ለስብሰባ እንጂ ኑሯቸው በአዲስ አበባ ቅምጥል ቤቶች አድርገው ነው የኖሩት።ዛሬ ደርሰው እነርሱ ማለት የትግራይ ሕዝብ ነው ለማለት ሲንደረደሩ መመልከት የቀልብ መሳት ካልሆነ ምን ሊሆን ይችላል?

2) የእስልምና እምነትን ነቀፈ የሚለው ቪድዮም ተመሳሳይ የቅጥፈት እና የሐሰት አቀራረብ ይዟል። በውጭ ሀገር እና በሀገር ውስጥ  ዲያቆን ዳንኤል ካደረጋቸው ገለጣዎች ውስጥ በአክራሪ እና ፅንፈኛ እስልምና ላይ የተናገረው ነው።ፅንፈኛ እና ነውጠኛነትን እስልምና ሆነ ክርስትና የሚቀበሉት አይደለም።የእምነት እኩልነት መከበር በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት የተቀመጠ ነው።ፅንፈኛነት እና ነውጠኛነት ግን ከሁለቱም እምነቶች ውጭ ነው።አሁንም ነውጠኝነት እና ፅንፈኛነት መደገፍ በየትኛውም የዓለም ክፍል ተቀባይ አይደለም።ይህንኑ ጉዳይ የእስልምና ተከታይ ወገኖቻችንን ለመንቀፍ እንደቀረበ ተደርጎ ለማቅረብ የሚደረገው ሙከራ ሁሉ ደካማ ሙከራ ነው።

3) ሦስተኛው እና ውሃ የማይይዝ ጉዳይ መናፍቅነት የሚለው ነው።ይህንን በተመለከተ አንዲት መድረክ ላይ መናፍቅ የሚለው ሌላ ትርጉም አለው ወይ? ስድብ ነው ወይ? የሚል ጥያቄ መጠየቁን የህወሓት አፈቀላጤዎች የሚያሳዩት ቪድዮ ነው። መናፍቅ የሚለው ቃል መጠራጠርን የሚያሳይ ነው።ማንም ዕምነት የእርሱን እምነት የማይቀበል የእኔን ይጠራጠራል ሲል ምንፍቅና ይለዋል።መናፍቅ የሚለው ቃል ደግሞ በትርጉምም በአገላለጥም በቤተ ክርስቲያን የሚሰጥ ቃል ነው።ይህንን ዛሬ ዲያቆን ዳንኤል ተነስቶ የፈጠረው አዲስ ቃል አይደለም።ቃሉንም ሊቀይረው አይችልም። የህወሓት አፈቀላጤዎች በአዲስ አበባ አንዲት መፃህፍት ቤት ሳይሰሩ 30 ዓመታት ስላሳለፉ ማገናዘብ ብሎ ነገር አልፈጠረባቸውም።

በሌላ በኩል ትውልድ ስያንኮላሹ ስለኖሩ በለመደ ስለታቸው ዛሬ እውነትን በመመስከሩ እና ከሁሉም በላይ ለሀገሩ ትልቅ ፍቅር ያለውን፣ሀገሩን በመውደዱም ሕዝብ በድምፁ በፓርላማ ወክለን ብሎ የመረጠውን ሙሐዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ላይ ያልተናገረውን እያጣመሙ በእንግሊዝኛ በውሸት ትርጉም ሰዎችን ለማሳሳት የሚሞክሩት ሰዎች የስብዕናቸው ደረጃ በምን ያህል  መውረዱን እራሳቸውን በራሳቸው አጋልጠውበታል።ዩንቨርስቲ መግባት፣መማር በእዚህ ደረጃ በውሸት ያሳብዳል እንዴ? እስኪባል የእዚህ ዓይነት የሃሰት የእንግሊዝኛ ትርጉም ከቪድዮ ጋር የሚያቀናብሩት ውስጥ ለዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የዓለም ጤና ድርጅት ውድድር በዘር ገመድ ብቻ እና ብቻ በመተብተብ ላብ እያጠመቃቸው ዘመቻ ሲያደርጉ የነበሩ ናቸው።ዛሬ የዘረኝነት ጭጋግ ዓይናቸውን  ሸፍኖት በአንድ ወቅት ሲሰብኩት የነበረውን በሐሰት አትመስክር እና ወንድምህን እንደራስህ ውደድ የሚለውን ቃል ዛሬ ማላገጫ አድርገውት የህወሓት ጀሌ በአማራ እና በአፋር ንፁሃን እጁን በደም ሲታጠብ ስለት አቀባይ ሆነው ቀርበዋል።

ባጠቃላይ የሐሰት የስም ማጥፋት ዘመቻው ይቀጥላል።በኢትዮጵያዊነት እና በኢትዮጵያ ላይ የተነሱ ሁሉ ግን ውርደታቸውን በቀሚሳቸው  እና በሙሉ ሱሪያቸው ስታቀፉ እንጂ አንዳች እርምጃ ስራመዱ ታሪክ እና ሕዝብ አይቶ አያውቅም።የኢትዮጵያ እውነተኛ ልጆች፣ለኢትዮጵያ የለፉ፣ሕዝብ ከህዝብ ለማለያየት ሳይሆን አንድ ለማድረግ የደከሙ፣የራሳቸውን ጥቅም ሳይሆን የሀገር ጥቅም ያስቀደሙ እና  ሕልማቸው ሁሉ የሀገራቸው ማደግ እና ነፃነት የሆኑት እንደ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ያሉት ሁል ጊዜ ስማቸው በሕይወት እያሉ ብቻ ሳይሆን ከመቃብር በኃላም ትውልድ የሚያነሳው ነው።ምናምንቴ አስተሳሰብ የያዙ ያፍራሉ።የእርጅና ዘመናቸውንም በትካዜ ይገፉታል። ኢትዮጵያ በትዝብት እያየች እንዳሸማቀቀቻቸው ዕድሜ ዘመናቸውን ይፈጃሉ። 

ከእዚህ በታች ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ለዘንድሮው አዲስ ዓመት በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ያደረገው ቃለ መጠይቅ ይመልከቱ።
ርዕስ = የመሻገሪያ ዘመን- ለሙኃዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ጋር የተደረገ ቆይታ
        መስከረም 1፣2014 ዓም 
        ኢ ቢ ሲ 



Urgent National and International Humanitarian Organizations Investigation on the latest TPLF Massacre in Amhara and Afar People in Ethiopia must be started. ህወሓት በአማራ እና አፋር በቅርቡ ለፈፀመው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ብሔራዊ እና ዓለምአቀፋዊ የምርመራ ሥራ በቶሎ መጀመር አለበት።

==============

Gudayachn

==============


Tigray People Liberation Front (TPLF) is categorized under the Terrorist group by the highest authorized body in Ethiopia, the House of Representative. In the last Nine months TPLF militia has made massacres on innocent people in North Gonder in Maikadra, North Wello in Kobo and Mersa and in Afar region too. In Afar over 107 children were part of the TPLF Massacre. All these have not yet got proper international attention. Rather, the current Biden Administration of the US Government, the UN Humanitarian office, Amnesty International and some western media are not reflecting the  TPLF’s crimes. However, contrary to the fact, these western media and the current US Government are busy criticizing the legally elected Ethiopian Government.


Now it is more than enough. The Ethiopian Government and the International Humanitarian Organizations need to establish a special investigation committee to investigate the TPLF massacre in Amhara and Afar regions. This is an international call to be a voice for the voiceless. The massacred people's blood is screaming and needs an immediate judge.


No matter how some western countries including the current US Government are showing their unfair judgement and illegal approach to the TPLF move, the situation on the ground is changing. That means Ethiopian National Defence Force is in a good capacity to enforce law and regulations in Ethiopia.Those who have ambitions on Geo-Politics of the horn will be obliged to revise their wrong approach towards the sovereignty of Ethiopia. It is important to stand with the truth and humanity and the necessity of starting a National and International investigation on the TPLF Massacre in Afar and Amhara regions is so crucial for the future peace and stability of Ethiopia and the Horn as a whole.



Here below, you will find an interview with the former Ethiopian Diplomat during TPLF brutal rule in Ethiopia.The video is a very good tip to know the historical background of TPLF and its internal nature,

Video Source = Break Through News (BT)







Saturday, September 18, 2021

በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ ከ3.6 ሚልዮን ብር በላይ ለሀገራቸው አዋጥተው ልከዋል።ከእዚህ ውስጥ 1ነጥብ 8 ሚልዮን ብር በእዚህ ሳምንት የላኩት ነው።

የኢትዮጵያ አየርመንገድ አብራሪ ካፒቴን አምሳለ፣ ኦስሎ ዓለም አቀፍ አየርማረፍያ  
(Photo - VG March 8,2019) 
-----------------------------
ጉዳያችን / Gudayachn
----------------------------
ኢትዮጵያውያን በሥራ፣በስደት እና በኑሮ ከሚገኙባቸው የአውሮፓ ሀገሮች ውስጥ ኖርዌይ አንዷ ነች። በኖርዌይ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት የሚጀምረው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከመጀመሩ ጥቂት ዓመታት ጊዜ ቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ በእንግሊዝ በስደት በነበሩበት ጊዜ ከኖርዌይ ንጉሳዊ ቤተሰብ ጋር ያደረጉት ግንኙነት መሰረት ሆኖ አገልግሏል።በመቀጠል ኖርዌይ በኢትዮጵያ መዋለ ንዋይ የሚያፈሱ ጥቂት ባለሀብቶች ለምሳሌ በመሃል አራዳ ታዋቂው የሞዝቭኦልድ ኩባንያ ይጠቀሳሉ።በሌላ በኩል ኖርዌይ የኢትዮጵያ የመጀመርያ ባሕር ኃይል በማሰልጠን ረገድም አስተዋፅኦ ነበራት።

የኢትይጵያ እና የኖርዌይ ግንኙነት ወደየተሻለ ደረጃ ያደረሰው ሌላው የግንኙነት መስኮት ደግሞ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1954 ዓም ቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ በኖርዌይ ያደረጉት ጉብኝት ነበር። በአሁኑ ጊዜ ኖርዌይ በዓለም ላይ 12 ቁልፍ የልማት አጋሮች ከምትላቸው ሀገሮች ውስጥ ኢትዮጵያ አንዷ መሆኑና የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድረ-ገፅ ያሳያል።በእዚሁ ገፅ ላይም ኢትዮጵያ የሚገኘው የኖርዌይ ኤምባሲ በአፍሪካ ኖርዌይ ካሏት ኤምባሲዎች ትልቁ እና ሰፋ ያሉ ስራዎች የሚሰሩበት መሆኑን ይገልጣል።

በኖርዌይ እና በኢትዮጵያ መካከል የሁለትዮሽ ትብብር እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1995 ዓም የተፈራረሙ ሲሆን በ2017 ዓም እኤአ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኦስሎ የቀጥታ በረራ ጀምሯል።በአሁኑ ጊዜ አየር መንገዱ የሰሜን አውሮፓን ከአፍሪካ ጋር ከሚያገናኙት ቀዳሚ አየር መንገዶች ውስጥ ገብቷል።

ይህ በእንዲህ እያለ በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ ወደ 3ነጥብ 6 ሚልዮን ብር ወይንም 640ሺህ የኖርዌይ ክሮነር አዋጥተው ወደ ሀገር ቤት ልከዋል። ይሄውም በኖርዌይ የሚገኙ የሲቪክ ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ኮምንቲ በኖርዌይ ጋር በመተባበር ባለፈው ግንቦት ወር ለዓባይ ግድብ 331,659 የኖርዌይ ክሮነር አዋጥተው ወደ ግድቡ ፕሮጀክት ያስገቡ ሲሆን በያዝነው ሳምንት ውስጥ ብቻ 1 ነጥብ 8 ሚልዮን ብር (342 ሺህ 411 የኖርዌይ ክሮነር) ወደ ሀገር ቤት ልከዋል።በሰሞኑ የተላቀው ገንዘብ ለሰብዓዊ አገልግሎት የሚውል ሲሆን በአማራ እና አፋር ክልል በሽብርተኛው የህወሓት ቡድን ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ እና በችግር ላይ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሚውል መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

በመጨረሻም በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከመቼውም ጊዜ በተለየ ለሀገራቸው መድረስ ያለባቸው ወሳኝ ጊዜ አሁን ሲሆን፣በውጭ ከሚኖረው ኢትዮጵያዊ ብዛት እና አቅም አንፃር ከእዚህ በላይ ለማድረግ አሁንም እንደሚቻል ለማወቅ ይቻልል።
============================

============
ማስታወቂያ 
============
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

Thursday, September 16, 2021

ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር ነች አንድ ሚልዮን ወታደር ሊኖራት ይገባል። ወጣቶች 12ኛ ክፍል እንደጨረሱ ለስድስት ወራት የብሄራዊ ውትድርና አገልግሎት ቢሰጡ ይጠቀማሉ።መጪው አዲሱ ፓርላማ በፍጥነት ተወያይቶ መወሰን ያለበት ቀዳሚ አጀንዳ መሆን አለበት።

ከአጭር ፅሁፉ ስር ከ800 ሰው በላይ የተሳተፈበት ኢትዮጵያዬ የተሰኘው አዲስ ዜማ ያገኛሉ።

ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር ነች።ከ115 ሚልዮን በላይ ለሆነው ህዝቧ እና የእንግሊዝን መሬት አራት ጊዜ ለሚበልጥ መሬቷ አንድ ሚልዮን ሰራዊት ያስፈልጋታል።ይህ ሰራዊት በሰላም ጊዜ ያመርታል።በጦርነት ጊዜ የሀገር ሰላም ያስከብራል።ሰራዊቱ የሀገር ሸክም አይሆንም።የራሱ ግዙፍ ዘመናዊ የእርሻ ቦታዎች፣ዘመናዊ ፋብሪካዎች እና በመከላከያ ስር ያሉ ሌሎች የልማት ድርጅቶች ሊኖሩት ይችላሉ።በመሆኑም ሰራዊቱ በሰላም ጊዜ የመንግስት በጀት የሚበላ ሳይሆን ራሱን በራሱ የሚያግዝ ይሆናል።

በሌላ በኩል ወጣቶች 12ኛ ክፍል እንደጨረሱ ለስድስት ወራት የብሔራዊ ውትድርና ስልጠና እንዲወስዱ ቢደረግ ይጠቀማሉ።የስድስት ወር ስልጠናው ከሱስ ነፃ ሆነው የአካል እና የአዕምሮ ስልጠና ከመውሰድ ባለፈ ተጨማሪ የሙያ ክህሎት እና ስለሀገራቸው ታሪክ፣ባሕል እና በኢትዮጵያ እና ዙርያዋ ባሉ ጂኦ ፖለቲካ ዙርያ ከፍተኛ ባለሙያዎች የሚሰጧቸው ስልጠናዎች እንዲከታተሉ ይረዳቸዋል።በእዚህም ወደ ዩንቨርስቲ ሲገቡም ሆነ ወደ ሥራ ዓለም ሲሰማሩ በሁሉም ዘርፍ ብቁ ዜጋ ያደርጋቸዋል።ይህ ቀጠሮ የማያስፈልገው እና አሁኑኑ መንግስት ሊጀምረው የሚገባው ሥራ ነው።

መጪው አዲሱ ፓርላማ በፍጥነት ተወያይቶ መወሰን ያለበት ቀዳሚ አጀንዳ መሆን አለበት።የኢትዮጵያ የሆነ ዕውነተኛ ዘመን ተሻጋሪ ትውልድ ማፍራት የሚቻለው በእዚህ መልክ ነው። የብሔራዊ ውትድርና ስልጠና በአውሮፓ ኖርዌይን ጨምሮ አሁንም በብዙ የሰለጠኑ ሀገሮች የሚሰጥ ነው።በእዚህ ስልጠና ላይ የተሳተፉ የዩንቨርስቲ መግቢያ ነጥባቸው ዝቅ እንዲደረግ ከመደረጉ በላይ ለስራ በምወዳደሩባቸው ቦታዎች ሁሉ ቅድምያ እንዲያገኙ ይደረጋሉ።

ኢትዮጵያዬ (አዲስ የወጣ ሀገራዊ ዜማ)
ድምፃዊት ራሄል ጌቱ 
ዳይሬክተር ቅድስት ይልማ 
ከአውታር ቲቪ ዩቱብ የተወሰደ 






አቶ ልደቱ አያሌው - የህወሓት የተኩስ ሽፋን ሰጪ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ 

አቶ ልደቱ አያሌው የፖለቲካ ሂደቱ ሁሉ ለተመለከተ የሴራ ፖለቲካ ወራሽ ለመሆን የሚደክም ሰው መሆኑን እያስመሰከረ ነው።የኢትዮጵያን ችግር የተረዳበት ወይንም አውቆ ሊያታልለን የሚሞክርበት መንገድ ሁሉ የዕቃ ዕቃ ጫወታ እየሆነ ነው።ሌላውን ሁሉ ትተን ላለፉት ሦስት ዓመታት ብቻ ያለውን  በአጭር ዓረፍተ ነገር ለማስቀመጥ የነገሮች መዘባረቅ ያሳያል።ለውጡ እንደመጣ ወደ ፖለቲካው መጣሁ አለ፣ቀጥሎ ከፖለቲካ ወጣሁ አለ። በመቀጠል በኦኤምኤን ከጀዋር ጋር ቀርቦ ከመስከረም 30፣2013 ዓም በኃላ በኢትዮጵያ መንግስት የለም በሚል ንግግር ኢትዮጵያ ላይ እጅግ አደገኛ ጦር ወረወረ።መስከረም 30 አለፈ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ትዝብቱን በጉያው ይዞ ዝም አለ።ልደቱ ግን ቀጠለ ምርጫው የተራዘመው ለስልጣን ጥም ነው እንጂ በኮሮና ምክንያት አይደለም አለ።

ልደቱን አንዳንድ በአማራ ስም የህወሓትን አጀንዳ የሚያራምዱ  በዘውግ ፖለቲካ ሊያሞግሱት ይሞክራሉ።ሆኖም ግን እነኝህ ዘውገኞች የአማራንም ሕዝብ የማይወክሉ ነገር ግን ጥቂቶችን ለማጭበርበር የሚሞክሩ ናቸው።ልደቱ ይህንን ስለሚያውቅ አንዴ ከአማራ ዘውግ ሌላ ጊዜ ከኦኤምኤን እያለ የኢትዮጵያ መሰረታዊ ጥቅሞችን የሚነኩ ነገር ግን ህወሓትን በተዘዋዋሪ ሊረዳ ይችላል  ያላቸውን አጀንዳዎች እያነሳ አትርሱኝ የሚል መልዕክቶቹን ይለቃል።

አሁን ባለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ በፀረ ህወሓት ትግሉ ላይ እጅግ በበሰለ እና ቀድሞ በሚያቅድ መልኩ ትልቅ ሚና መጫወቱ የሽብርተኛው ህወሓት ጎራን ፀጉር ያስቆመ መሆኑ ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው።አቶ ልደቱ ሰሞኑን የለቀቀው አንድ ፅሁፍ ላይ ብልፅግና ላይ ያተኮረ መስሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ መስከረም ወር ላይ በምክር ቤት እንዳይመረጡ የሚል 'ኡኡታ' መሰል መልዕክት አስተላልፏል።በመልእክቱ ላይ የኢትዮጵያ ዋና ችግር ሽብርተኛው ህወሓትን አንዲት ቃል ሳይናገር የኢትዮጵያ ችግር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ናቸው የሚል ኑ ላሞኛችሁ የሚል ፅሁፍ ወርውሮልናል።

ይህ የአቶ ልደቱ ፅሁፍ ለህወሓት የተኩስ ሽፋን ለመስጠት የታቀደ ነው።በወታደራዊ ስልጠና ላይ የሽፋን ተኩስ የሚባል ነገር አለ። አንድ ልዩ ኮማንዶ እስረኛ ለማስለቀቅ በቡድን ሲያጠቃ ሁሉም የኮማንዶ ቡድን ወደ እስር ቤት አይገቡም።ዋናው ቡድን ወደ ውስጥ እስረኞችን ለማስለቀቅ ሲገባ የቀረው ከውጭ ሆነው የሽፋን ተኩስ ይሰጣል።ይህ የሽፋን ተኩስ አንድም ለማደናገር እና የእስር ቤት ጥበቃውን አቅጣጫ ለማስቀየር ሲጠቅም በሌላ በኩል ደግሞ ከውጭ ሌላ አጋዥ ኃይል ከመጣ ለማስቀረት ነው። የአቶ ልደቱ የአሁኑ ፅሁፍ ለህወሓት የሽፋን ተኩስ ለመስጠት የታቀደች ነች።እርሱ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ እየተኮሰ ለሽብርተኛው ህወሓት መንገድ ለመክፈት ነው።ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና አመራሩ የህወሓትን አከርካሪ በቅርብም ሆነ በሩቅ ስልት እየመታው እንደሆነ ስላወቀ ያለውን ጦር የወረወረው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ነው።

ለማጠቃለል አቶ ልደቱ የግል ሆቴሉ ያለበት ቅዱስ ላሊበላ እና አካባቢው በህወሓት ጀሌ ህዝቡ ላይ የሚደርሰው በደል እንዴት አልሰማም እና ስለወቅታዊ የኢትዮጵያ ዋና ችግር ሽብርተኛው ህወሓትን ትቶ ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ መስከረም ወር ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር አይሁኑ ዘመቻ ላይ ተጠመደ? የኢትዮጵያ ችግር ጠቅላይ ሚኒስትር በመቀየር ይፈታል? የኢትዮጵያ ችግር ሽብረትኛው ሀወሓት ነው ወይንስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ? አቶ ልደቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ችግር ሳይገባው ቀርቶ ሳይሆን የሚደናገርልኝ አገኛለሁ በሚል ተስፋ የፃፋት ነች።ዓቢይን አጥብቀው የሚጠሉ የዓብይ መንገድ አጋንንታዊ መንገዳቸውን እያፈረሰባቸው መሆኑ ያበሳጫቸው ብቻ ናቸው።አቶ ልደቱ የሽፋን ተኩሱ አልተሳካም።
==========///==============

Wednesday, September 15, 2021

በአማራ እና አፋር ላይ ከወረራ ባለፈ ሽብርተኛው ህወሓት እና ጀሌው ንፁሃንን የገደለበት እና ንብረት የዘረፈበት ሦስት ምክንያቶች እና የህወሓትን መርዝ ለማምከን በቀጣይ መደረግ ያለባቸው አምስት ተግባራት።

Picture taken from business2community

==============
ጉዳያችን/ Gudayachn
==============
ሽብርተኛው ህወሓት እና ጀሌው በአማራ እና አፋር ክልል ላይ ለጆሮ የሚከብድ የሰው ልጅ በሰው ላይ ይፈፅመዋል የማይባል የአውሬነት ባህሪው ተገልጧል።ላለፉት ሃምሳ ዓመታት የህወሓት አመራሮች በደም ተነክረው በሕዝብ አጥንት ላይ እየተራመዱ ቢኖሩም የአሁኑ በአማራ እና አፋር ላይ የሰሩት ግን ለምን? ብሎ መጠየቅ እና የሄዱበትን መንገድ ማምከን ያስፈልጋል።

ወደ ሶስቱ ምክንያቶች ከመሄዳችን በፊት ለዓመታት የኖረው በተለይ  በአማራ ማኅበረሰብ ላይ ያላቸው ጥላቻ እንዳለ መሆኑ በሰነድም የተደገፈ ስለሆነ ይህንን ምክንያት በቀዳሚነት እንዳለ ሆኖ ነው የወቅቱን ሦስት ምክንያቶች በደንብ መረዳት ያለብን።

ምክንያት አንድ - በአማራ እና በትግራይ ሕዝብ መሃል ያለውን ማኅበራዊ ግንኙነት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እንበጥሰዋለን ብለው በማሰብ 

ህወሓት ለረጅም ጊዜ የትግራይን ሕዝብ ሌሎች በተለይ አማራ ሊያጠፋህ ነው በሚል ብዙ ፕሮፓጋንዳ ሰርቷል።ከአራት ዓመታት በፊት በጎንደር የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆችን አስደንብሮ ወደ መተማ ካፈናቀለ በኃላ ህዝቡ ውሸት መሆኑን ሲያውቅበት መልሶ በአይሮፕላን ማመላለሱ ይታወቃል። መረጃዎች እንደሚያስረዱት በአዲስ አበባ እና በቀረው የኢትዮጵያ ክፍል ከአንድ ሚልዮን የማያንሱ የትግራይ ተወላጆች ዛሬም በሰላም በሀገራቸው እየኖሩ ነው።ህወሓት በተለያዩ መዋቅሩ ስር በሚያስተላልፋቸው መልዕክቶቹ እነኝህን የትግራይ ተወላጆች ህዝቡ ሊፈጃችሁ ነው፣እኔ ከሌለሁ አበቃላችሁ እያለ መዓት ሲያወራ ከርሞ፣ህወሓት መቀሌ ሲገባ ምንም እንዳልተፈጠረ ሲታወቅ ውሸቱ ተጋልጧል። 

በመቀጠልም መከላከያ መቀሌ ሲገባ ሕዝብ ይፈጃል ጨረሳችሁ በሚል ፕሮፓጋንዳ ሕዝቡን አደናገረ። ሰራዊቱ መቀሌንም ትግራይንም ለቆ ሲወጣ ሕዝብ እየገደለ እና ንብረት እያወደመ ሳይሆን በሰለጠነ መንገድ ነው ወጥቶ የሄደው። ይህንን ሕዝብ ይታዘባል። በመሆኑም እነኝህ ሁኔታዎች እየቆዩ በትግራይ ማኅበረሰብ እና በሚያጎራብቱት ክልሎች ማለትም በአማራ እና በአፋር ሕዝብ እንዲሁም በተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ አንፃር አንድነት መልሶ ይመጣል የሚል ስጋት ላይ ጣለው።ስለሆነም ጀሌዎቹን በጭካኔ በገበሬዎች ላይ ግድያ፣ዘረፋ እና ሴቶችን መድፈር እንዲደረግ እና ሕዝብ ከትግራይ ጋር ተቆራርጦ እንዲቀር ለማድረግ ሞከረ።

ምክንያት ሁለት -  ትግራይን የመገንጠል ሕልሙ የተፈጥሮ ሂደት እንዲሄድ ከማሰብ 

ህወሓት ትግራይን መገንጠል ይፈልጋል።ነገር ግን ይህ ከባድ እንደሆነ ከትግራይ አቀማመጥ ብቻ ሳይሆን ያለው ማኅበራዊ እና ታሪካዊ ትስስር የጠለቀ መሆኑ ገብቶታል።ስለሆነም ይህ የመገንጠል ሕልም የግድ የሆነ መሆኑን ሕዝብ እንዲያምን ለማድረግ የማይበርድ እሳት በትግራይ ሕዝብ እና በተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ መሃል መክፈት እና ይህ ቁርሾ ሌላው ሕዝብ በትግራይ ሕዝብ ላይ በመሃል ሀገር ሳይቀር እንዲነሳ እና የዘር ፍጅት እንዲፈፀም ይፈልጋል። ህወሓት የተፈጥሮ ሂደት የሚለው ይህንን ነው።አንድ ሕዝብ ሌላ ሕዝብ በእኔ ላይ ተነስቷል ሊያጠፋኝ ነው ብሎ ለሕልውናው ከሰጋ እስከ መገንጠል ማሰብ የመጨረሻ ግቡ ነው።ስለሆነም ህወሓት አፋር እና አማራን ሲወር የመግዛት እና የመቆጣጠር ዓላማ ቢኖረው ኖሮ ሰላማውያንን ሳይነካ ወረራውን ያደርግ ነበር።የተፈለገው ግን የዘመናት ቁርሾ በመፍጠር በሕዝብ መሃል ፍጅት ፈጥሮ ትግራይ ከመገንጠል ሌላ አማራጭ የለም የሚል ትውልድ ለመፍጠር ነው። ይህም አልተሳካለትም። የአሁኑ ጦርነትን መነሻ ታሪካዊ ሂደት የታወቀ ነው።ህወሓት ትግራይን ሲጠብቅ የኖረውን የመከላከያ ሰራዊት በተኛበት ገድሎ ለመቆጣጠር ያደረገው ጥረት የነገሩ መነሻ እንደሆነ እራሱ በሰኩቱሬ አማካይነት ያመነው ነው።ስለሆነም ትግራይን በተፈጥሮ ሂደት የመገንጠል ደረጃ ስሜት ለማድረስ ፈፅሞ አልቻለም። 

ምክንያት ሦስት - ሕዝብ በማሸበር ተፈሪ ለመሆን ነው።

ሶስተኛው ምክንያት የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚቀጠቅጠውን ይፈራል ብሎ የሚያስቡ ኃላ ቀር መካሮች አሉት።27 ዓመት የኢትዮጵያን ሕዝብ ስለቀጠቀጥነው  ነው የገዛነው ብለው ያምናሉ።የኢትዮጵያ ሕዝብ ጨካኝ አይፈራም።ጨካኝ ይንቃል፣ያረክሳል በመጨረሻም  በልዩ አቀጣጥ  ይቀጣል።የኢትዮጵያ ሕዝብ ሃገሩ እንዳትበተን ክፉ ቢነግስም ታግሶ ቀን ያሳልፋል እንጂ ፈርቶ አንድ ቀን አያድርም።ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም እንዳሉት ሃገሩ እንዳትበተን  ያደፍጣል።አድፍጦ ሁነኛ አደረጃጀት ተደራጅቶ ይነሳል። ህወሓት በአማራ እና አፋር ላይ በጭካኔ ሰላማዊ ሕዝብ በመግደል ሕዝብ የሚፈራት እና የማትቻል አድርጎ የሚያስባት መስሏት ነበር። የኢትዮያ ሕዝብ ''ባለጌን ካሳደገ የገደለ ፀደቀ'' የሚል ሕዝብ ነው። ጨካኝ እና ባለጌ በመግደል ፅድቅ አለ ማለት ነው።ምክንያቱም እንደ ሽብርተኛ ህወሓት ዓይነቱን ማጥፋት ሌላ እንዳይገድል እና እንዳያበላሽ ማድረግ ስለሆነ ፅድቅ ነው ብሎ ነው የሚያምነው።በመሆኑም ህወሓት ሶስተኛው ምክንያትም አልተሳካላትም።

የሽብርተኛው ህወሓት መርዝ ለማምከን መደረግ ያለባቸው አምስት ተግባራት 

የህወሓት ሽብርተኛ ቡድን አሁን የመጨረሻው መጨረሻ አፋፍ ላይ ደርሷል።ይህም በወታደራዊው ብቻ ሳይሆን በርዕዮት አንፃርም በራሱ በትግራይ ሕዝብ ውስጥም መሞቱ አይቀርም።ለእዚህ የትግራይ ሕዝብ በቀላሉ ስሌት ሊደርስበት ይችላል።የትግራይ ህዝብም ሆነ መሰረተ ልማቱ የወደመው የኢትዮጵያ መከላከያ ከመቀሌ ከመውጣቱ በፊት ነው ወይንስ በኃላ ብሎ እነ ደብረ ፅዮን ተመልሰው መቀሌ ከገቡ በኃላ ስንት የትግራይ የህክምና ዶክተሮች፣የዩንቨርስቲ መምህራን እንዳስጨረሱ እና መሰረተ ልማቱን በማይገባ ጦርነት ውስጥ እንደማገዱ መመልከት  በቂ ነው።አሁን መደረግ ያለበት - 

1) በሕግ ማስከበር ሂደቱ ላይ በትግራይ ተፈፀሙ የተባሉት የሰብዓዊ ጥፋቶች ላይ መንግስት በራሱ፣የተባበሩት መንግሥታት ሰብዓዊ ኮሚሽን ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ ኮሚሽን ጋር በጋራ እያጣሩ መሆኑ ይታወቃል።ይህ በመንግስትም ሆነ በሰብዓዊ ኮሚሽኖች የተመሰረቱት አጣሪዎች በአማራ ክልል እና በአፋር የተፈፀመውን ጥቃት እና ጥፋት አብሮ እንዲያጣሩ ማድረግ እና ይህ ሂደት ያለበትን ሁኔታ ከስር ከስሩ ለሕዝብ ማሳወቅ እና ከተጣራ በኃላ መጪው የኢትይጵያ ምክር ቤት ሁኔታዎቹን የሚያርሙ ውሳኔዎች በማሳለፍ አጥፊዎች እንዲታረሙ የተጎዱ ደግሞ ተገቢው ካሳ እንዲሰጥ መወሰን።

2) በህወሓት በኩል የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት ከማቀናበር እስከ መፈፀም የደረሱ እና በኃላ በአማራ እና አፋር ላይ ወረራ ያደረጉ፣ያስተባበሩ፣የረዱ ሁሉ ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ።

3) የትግራይ ሚሊሻ እና ልዩ ኃይል ትጥቅ እንዲፈታ ማድረግ እና ህዝቡ ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለስ ማድረግ።

4) ህወሓት በትግራይ ሆነ በየትኛውም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሂደት ውስጥ እንዳይሳተፍ እግዱን ማፅናት።

5) በትግራይ፣አማራ እና አፋር ክልሎች መሃል ያለውን ግጭት በተመለከተ ሕዝብ ከህዝብ እየተነጋገረ በሃይማኖትም ሆነ በሽምግልና እንዲፈታው ማድረግ።የወልቃይት እና ሰሜን ወሎ አከላለሎች ቀድሞ ከሕወሓት በፊት ለዘመናት ወደነበረበት አከላለል መመለስ እና ማኅበራዊ ግንኙነቱን ማለስለስ የሚሉት ናቸው። 
===========////==============

================================
ማስታወቂያ 
============
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 


Tuesday, September 14, 2021

ሰበር ዜና - ደብረፅዮን እና ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ከፍተኛ የተረፈው የህወሓት አመራር የአዕምሮ መዛባት ቀውስ ላይ እንዳሉ ታማኝ መረጃዎች እየወጡ ነው።የትግራይ ሕዝብ እና ዲያስፖራ መመርያ ከእነማን እየተቀበለ እንዳለ ደግሞ ማሰብ አለበት።



Breaking News - Reliable sources confirm Top TPLF leaders, including DebreTsion and Getachew Reda, are in Mental disorder.

የደብረፅዮን እና ጌታቸው ረዳ ጀሌ ሆኖ ያገለገለው የትግራይ ወጣት በአስር ሺዎች እየሆነ በሰሜን ወሎ፣ሰሜን ጎንደር እና አፋር ለመውረር የገባው ወጣት እንደቅጠል እረግፏል።ጦርነቱን በድል የሚያጠናቅቁ የመሰላቸው የህወሓት አመራሮች ከገበሬ ልጆች እስከ መምህራን፣ከመምህራን እስከ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የህክምና ዶክተር እና የጤና ባለሙያዎች፣ከዩንቨርስቲ ሰራተኞች እስከ ጋዜጠኞች ሁሉን እያንጋጋ ወደ ጦርነቱ ከከተተ በኃላ ትግራይን ባዶ አድርጎ አንድ ትውልድ አስፈጅተዋል።

ይህ እልቂት መጀመርያ የትግራይ ሕዝብ እንዳይሰማው ቢሰማም አዲስ አበባ ልንገባ ነው በሚል ድለላ ሕዝቡን ሊያፅናና ሞክረው ነበር።ሆኖም ግን ቆይቶ የትግራይ ሕዝብ በባትሪ ራድዮ ከአሜሪካ ራድዮ እና የጀርመን ድምፅ ሳይቀር እውነቱን ተረዳው።በመቀጠልም በአማራ ሕዝብ ላይ የተፈፀመው ዘረፋ ሳይቀር ትግራይ ተሰምቷል።የትግራይ ወጣቶች ማለቅ በተመለከተ የተደናገጡ ወላጆች ለቅሶ መቀመጥ ጀምረዋል።በተለይ ከደቡብ ጎንደር እና ሰሜን ወሎ እያመለጠ ወደ ትግራይ ለመመለስ የሚሞክረው የትግራይ ወጣት ላይ የህወሓት ታማኝ ጀሌ ወዴት ትመለሳለህ እያለ ተኩስ እየከፈተ መሆኑ እና ብዙ ወጣት ማለቁን ከተኩሱ ያመለጡ ወደ ወላጆቻቸው ተደብቀው የተመለሱ መቀሌ ሳይቀር ወሬውን አድርሰዋል።

አሁን ህወሓት የሰራዊቱ እልቂት እና የመዋጋት ፍላጎት መውረድ፣የኢትዮጵያ መከላከያ ምን ዓይነት እርምጃ ቀጥሎ እንደሚወስድ ምንም መረጃ አለመኖር እና የትግራይ ሕዝብ ልጆቼን ብሎ እየጠየቀ መሆኑ የህወሓት አመራሮች የሚይዙት የሚጨብጡት አሳጥቷቸዋል።በቂ መረጃ አለን የሚሉ ወገኖች እንደገለጡት በሳተላይት ስልክ ከፍተኛ የህወሓት ባለስልጣናትን ለማናገር የሞከሩ የምዕራብ የመረጃ ሰራተኞች እና በትግራይ ያሉ የእርዳታ ድርጅቶች ሰራተኞች ሳይቀር  የህወሓት ባለስልጣናት አእምሮ ቀውስ ላይ እንዳሉ ለመረዳት እንደቻሉ እና ይህም ጊዜያዊ የስካር ስሜት አለመሆኑን ከንግግራቸው በመረዳታቸው ደጋፊ የውጭ አካላትን ሳይቀር አስደንግጧል።የህወሓት ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ሰራዊት መቀሌን ለቆ ከወጣ በኃላ በትግራይ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ግድያ ስለፈፀሙ የኢትዮጵያ መከላከያ ወደ መቀሌ ቢመጣ ህዝቡ እንደቀደመው ጊዜ እንደማይደብቃቸው ይልቁንም እንደሚነሳባቸው አውቀዋል።ትግራይን ትተው ወደ ውጭ እንዳይወጡ የሁመራ መስመርን ማስከፈት አልቻሉም።የምዕራብ መስመር ቢከፈት ኖሮ የተወሰነ አመራር ከውጭ ሆኖ እንዲያታግል ተወሰነ በሚል በርካታ አመራሮች በሱዳን በኩል ለመውጣት አቅደው ነበር።በመሆኑም ህወሓት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መቀሌን በተቆጣጠረ ጊዜ ካለበት ሁኔታ ሳይቀር ማሽቆልቆሉ ግልጥ እና የሚታይ ነው።አሁን የህወሓት ባለስልጣናት ከመሃል የትግራይ ሕዝብ፣ከሰሜን ኤርትራ፣በደቡብ የኢትዮጵያ ኃይሎች ከበውታል።የህወሓት ባለስልጣናት በእዚህ ጊዜ የአዕምሮ መዛባት ላይ መሆናቸው ሲያንስ ነው። 

የአዕምሮ መዛባት ከከፍተኛ ጭንቀት እና ተስፋ መቁረጥ የሚመጣ ሲሆን የነገሮች መደባለቅ እና ቅደም ተከተሎችን ከማዛባት በላይ የሚሰሩትን እንዳያውቁ የሚያደርግ አደገኛ የመቀወስ መገለጫ ነው።ይህ የአዕምሮ መዛባት ያለባቸውን አመራሮች ትዕዛዝ የትግራይ ሕዝብ እየተቀበለ መሄድ ከቀጠለ ሙሉ ትውልዱን የማጣት ዕጣ እንደሚገጥመው ባለሙያዎች የሚያሳስቡት ጉዳይ ነው።የአዕምሮ መዛባቱ ደረጃ በደረጃ ባሉ የህወሓት አመራሮች ላይ የታየ ሲሆን ጉዳዩ በሕዝቡም ውስጥ ሳይቀር እየተወራ እና ከአማራ እና አፋር ተደብቀው የተመለሱ የህወሓት ዝቅተኛ እና ከፍተኛ አዋጊዎች ላይ ሁሉ የታየ መሆኑን ሕዝቡ እየተናገረ ነው።

የትግራይን ጦርነት ለማቆም የትግራይ ሕዝብ ደብረፅዮን እና ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ከፍተኛ የህወሓት ባለስልጣናትን ይዞ ለመንግስት አሳልፎ መስጠት ብቻ ነው የሚጠበቅበት። ይህ ሳይሆን ሕዝብ እና ክልሉ ይጥፋ የሚል ውሳኔ ይዞ በጦርነት ሕዝብ ለመማገድ የሚፈልጉ በጦርነት ለማትረፍ የሚሯሯጡ መሆናቸው ግልጥ ነው።አሁን የታወቀው ጉዳይ ከፍተኛ የህወሓት ባለስልጣናት የአእምሮ መዛባት ህመም ላይ መውደቃቸው ነው።ይህንን ለመረዳት ጌታቸው ረዳ በትውተር ገፁ፣ደብረፅዮን ደግሞ በድምፅ እየሰጡ ያለውን ቃለ መጠይቅ በቀላሉ መመልከት በቂ ነው።
==========================
ማስታወቂያ /Advertisement 
===============================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

Monday, September 13, 2021

በኖርዌይ ሀገራዊ ምርጫ በስልጣን ላይ የነበረው የቀኝ ክንፉ ፓርቲ በግራ ዘመሙ የሰራተኛ ፓርቲ ተበልጧል።ኖርዌይ አዲስ ጠቅላይ ሚንስትር ይኖራታል።

የኖርዌይ ሰራተኛ ፓርቲ ሊቀመንበር እና አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዮናስ ጋር ስቶረ Jonas Gahr Støre

====================
ጉዳያችን/Gudayachn Report
====================

በኖርዌይ አጠቃላይ ሃገራዊ ምርጫ ሲደረግ ነበር የሰነበተው።ዛሬ ሰኞ መስከረም 3 እኩለ ሌሊት አካባቢ በሀገሪቱ የቴሌቭዥን ጣብያዎች የቀጥታ ስርጭት ውጤቱ እየተገለጠ ነበር በእዚህ መሰረት የሰራተኛ ፓርቲ የተሰኘው የግራ ዘመም ፓርቲ ማሸነፉ ተገልጧል።ስለሆነም አሁን በስልጣን ላይ ያለው የቀኝ ክንፍ ፓርቲ የመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ሱልበርግ ስልጣናቸውን ለሠራተኛ ፓርቲ ሊቀመንበር ዮናስ ጋህር ስቶረ  (Jonas Gahr Støre) ያስረክባሉ

ከምርጫው በፊት በኖርዌይ ዋና ከተማ የተሰቀሉ የምርጫ ቅስቀሳ ፖስተሮች ላይ አሁን ያሸነፉት የሰራተኛ ፓርቲ ሊቀመንበር እና መጪው የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዮናስ ጋህር ስቶረ   ከተለያዩ የውጭ ሀገር ተወላጆች ጋር በፈገግታ ሆነው ሲነጋገሩ የሚያሳዩ ፎቶዎች በከተማው ውስጥ ይታዩ ነበር።የኖርዌይ ሰራተኛ ፓርቲ ለኖርዌይ በርካታ ታዋቂ ፖለቲከኞች እና ዓለም አቀፍ ስም ያላቸው ሰዎችን አፍርቷል።ለምሳሌ  አሁን የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ፕሬዝዳንት የንስ ስቶልተንበርግ (Jens Stoltenberg) ዛሬ ያሸነፈው የኖርዌይ ሰራተኛ ፓርቲ የቀድሞ  ሊቀመንበር እና የቀድሞው የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደነበሩ ይታወቃል።

የኖርዌይ ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች  

በቀኝ አክራሪው እና አሁን በእስር ላይ የሚገኘው ቤቭርክ አቀናባሪነት 77 ንፁሃን የኖርዌይ ወጣት የሰራተኛ ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች የፓርቲውን የወጣት ክንፍ አባላት ኡታያ በተባለ ደሴት ላይ ልዩ ዝግጅት ላይ እንዳሉ የተገደሉት የዛሬ አስር ዓመት ሐምሌ 22፣2011 ዓም እኤአቆጣጠር ነበር።ይህ ድርጊት የኖርዌይ ሰራተኛ ፓርቲ ሃዘን ብቻ ሳይሆን የመላው ኖርዌጅያን እና የሰው ዘር ሁሉ ሃዘን ሆኖ አልፏል።

ዛሬ የኖርዌይ የሰራተኛ ፓርቲ ማሸነፉ ከታወቀ በኃላ የፓርቲው ሊቀመንበር እና መጪው አዲሱ የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር በሀገሩ የምርጫ ውጤት እንደታወቀ የሚደረገው ባህል መሰረት እኩለ ሌሊት ገደማ ከፓርቲያቸው ቢሮ በፓርቲው ባለስልጣናት እና ጋዜጠኞች ታጅበው በእግራቸው በቀጥታ ወደ ኖርዌይ ፓርላማ አምርተዋል።ይሄውም ከእዚህ በፊት እንደሚደረገው በቀጥታ በቴሌቭዥን ለሕዝቡ ተላልፏል።

በመጨረሻም ተሰናባቿ የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ክብርት ወይዘሮ አርነ ሱልበርግ ፓርቲያቸው ለመጪው ጠቅላይ ሚኒስትር መልካሙን እንደሚመኙ ገልጠው ፓርቲያቸው በእየጊዜው እያደገ መምጣቱ እና መሻሻሻሉ አሁን ያገኘው ውጤትም ቀላል አለመሆኑን ገልጠዋል።
============///============
ከጉዳያችን የሚያገኙትን ዜና በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ሲያስተላልፉ ምንጭዎ ጉዳያችን መሆኑን መጥቀስ ስነምግባራዊ ግዴታ ነው።


Thursday, September 9, 2021

ወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ምጥን መረጃዎች -

በእዚህ ምጥን መረጃዎች ውስጥ - 

- የጦርነቱ ሁኔታ፣
- የባዕዳን እንቅስቃሴ እና 
- ያልተሰሙ አዳዲስ  መልካም ዜናዎች ያገኛሉ።

=============
ጉዳያችን ምጥን 
============

ጦርነቱ 

- የኢትዮጵያ ኃይሎች በሁሉም ግንባሮች የሽብርተኛውን ህወሓት ጀሌ ከሰሜን ወሎ እስከ ሰሜን ጎንደር የበላይነታቸውን አሳይተዋል።
  • ህወሓት ለቆ በሚሄድባቸው ቦታዎች ላይ የዘር ማጥፋት መፈፀሙ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተጋለጠ ነው።
  • እስካሁን ባለፉት ሦስት ወሮች ውስጥ ብቻ ህወሓት የዘር ማጥፋት የፈፀመባቸው ቦታዎች 
    • አጋምሳ ወሎ 
    • ጋሊኮማ አፋር 
    • በትግራይ በሚኖሩ የኤርትራ ስደተኞች እና 
    • ባሳለፍነው ሳምንት ደግሞ በጭና ደባርቅ ወረዳ የሚጠቀሱ ናቸው።
  • በአማራ ክልል ገበሬው ከመቼውም ጊዜ በላይ ተነስቷል።ከጁንታው ላይ መልሶ መታጠቅ ችሏል።
  • ከኦሮምያ፣አፋር፣ሱማሌ እና ደቡብ የተውጣጡ ልዩ ኃይሎች በግንባሮቹ ውጊያ ላይ ተሳትፈዋል።ትልቁን ድርሻ ግን መከላከያ እና ፋኖ ወስደዋል።

የባዕዳን እንቅስቃሴ 
  • ባዕዳኑ ከካርቱም እስከ ካይሮ፣ከካይሮ እስከ ዲሲ በህወሓት መሸነፍ ተደናግጠዋል።
  • የውሸት ዘመቻውን እንደገና ለመቀስቀስ እየሞከሩ ነው።
  • ለውሸታቸው በተለይ ከትውተር ሰራዊት እየገጠማቸው ያለው ምላሽ ግን ቀላል ሆኖ አላገኙትም 
  • የምዕራባውያን ዜጎችም የራሳቸው ሀገሮች ሚድያዎች እየዋሹ እንደሆነ በእዚህ የኢትዮጵያ ትውተር ዘመቻ እና ማስረጃ ሲቀርብ ትልልቆቹን ሚድያዎች አላስጨነቀም ማለት አይቻልም።
  • ትናንት በእንግሊዝ ፓርላማ በትግራይ ጉዳይ ላይ ስብሰባ ነበር።በስብሰባው ላይ ጫፍ የረገጠ ውሸት ለማውራት የሞከሩ የምክር ቤት አባላት ቢኖሩም፣ኢትዮጵያ እጅግ አስፈላጊ ሀገር ነች።ከሱማሌ ሰራዊቷን እያወጣች ነው ይህ ማለት ከባድ አደጋ አለው ኢትዮጵያን ልንገነዘባት ይገባል ይህች ሀገር ትልቅ ታሪክ ያላት ሀገር ነች በማለት ያስረዱ የምክር ቤት አባላት ነበሩ።
  • ይህ የምክር ቤት ስብሰባ ግን በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ትኩረት አልሳበም።ትኩረት አለመሳቡ እንግሊዞች የፈለጉትን ተፅኖ ፈጣሪ ነን የሚል  ፍላጎታቸውን ባለማሟላቱ አልተናደዱም ማለት አይቻልም።የእንግሊዝ ምክር ቤት ስብሰባን የኢትዮጵያ ማኅበራዊ ሚድያም ትኩረት አልሰጠውም።
  • የሽብርተኛው ህወሓት መመታት ያስደነገጣቸው ባዕዳን በተለይ ግብፅ እና ሱዳን ከጀርባ አይዟችሁ በሚሏቸው ሃገራት ግፊትም ጭምር በሱዳን ድንበር በኩል ግጭት ለመፍጠር እንደሚፈልጉ ነገር ግን በቅድምያ ሱዳን የሰለጠነው ሳምሪ የተባለው በማይካድራ የዘር ማጥፋት ላይ የተሳተፈው ቡድን ለመላክ እንደሚሞክሩ ግልጥ ነው።
  • ባዕዳኑ ኢትዮጵያን በምጣኔ ሀብት ለማዳከምም መሞከራቸው እንደማይቀር የታወቀ ነው።ስለሆነም ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ ምርቷ ላይ መትጋት እና የህዝቡን መሰረታዊ ፍላጎቶች ከውጭ ተፅኖ ማላቀቀ አስፈላጊ ነው።ለምሳሌ የመጪው የመከር ምርት በቁጠባ መሰብሰብ እና ስርጭቱ ላይ ቁጥጥር ማድረግ ያስፈልጋል።
መልካም ዜናዎች 

በእዚህ ሁሉ ውስጥ በኢትዮጵያ እጅግ አበረታች የሆኑ መልካም ዜናዎች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ -

  • መንግስት ከውጭ የሚገቡ ምግቦች ላይ ሙሉ በሙሉ ቀረጥ አንስቷል።በሀገር ውስጥም በምግብ ላይ የነበረውን የቫት ቀረጥ አንስቷል።በእዚህ መሰረት የምግብ ፍጆታዎች ዋጋ በተወሰነ ደረጃ ከአዲስ ዓመት በኃላ መሻሻል ያሳያል ተብሎ ይጠበቃል።በተለምዶም የክረምት ወራት የምግብ ዋጋ የሚንርበት ነው።ምክንያቱም ገበሬው የምርቱን ሁኔታ ካወቀ በኃላ ነው ያለውን ወደገበያ የሚያወጣው።የገንዘብ ሚኒስትር ዴታ ዶ/ር ኢዮብ ለኢትዮጵያ መገናኛዎች እንደገለጡት የቀረጥ ማንሳቱ ሥራ ላልተወሰነ ጊዜ የሚቀጥል ነው።
  • የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በአፍሪካ የ6ኛ ደረጃ ይዟል።ዩንቨርስቲው በዘመነ ህወሓት በጣም እየወረደ መጥቶ እንደነበር ይታወቃል። አሁን በለውጡ የዩንቨርስቲው አዳዲስ የቦርድ አባላት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ እየሰራ ሲሆን ባለፈው ዓመት ከነበረበት 10ኛ ደረጃ ዘንድሮ አራት ደረጃ አሻሽሎ 6ኛ የሆነ ሲሆን ከምሥራቅ አፍሪካ ደግሞ ቀዳም መሆኑን በዓለም አቀፍ የዩንቨርስቲ መስፈርት ላይ የሚሰራ በአሜሪካ ሀገር የሚገኝ ደረጃ አውጭ በሰጠው መስፈርት መሆኑን ዩንቨርስቲው ገልጧል።
  • የኢትዮጵያ አዲሱ የትምህርት ፖሊስ በአዲስ ዓመት የሙከራ ትግበራ በ2015 ዓም ደግሞ ሙሉ በሙሉ ሥራ ላይ እንደሚውል የትምህርት ሚኒስቴር ገልጧል።የኢትዮጵያ የትምህርት ፖሊሲ በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ወደ ስልጣን እንደመጡ በመጀመርያ የተገኙበት ስብሰባ የትምህርት ፖሊሲ የተመለከተ ስብሰባ ነበር።አሁን ተጠንቶ ሥራ ላይ በሚውለው አዲሱ ፖሊሲ ላይ በርካታ ለውጦች የተደረጉበት ሲሆን ከእዚህ ውስጥ የስነምግባር ትምህርት እስከ 6ኛ ክፍል መስጠት እና ከ6ኛ ክፍል በኃላ የስነ ዜጋ ትምህርት ይሰጣል።
  • ኢትዮጵያ ዘንድሮ የነበረባትን ዕዳ ካለፉት ዓመታት በተሻለ መቀነሱ ተነግሯል።በእዚህ መሰረት ከጠቅላላ ምርቷ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ለእዳ ክፍያ ታውል የነበረች ሀገር ዘንድሮ ከጠቅላላ ምርቷ የብድሯ መጠን ከ50% በታች ከመድረሱ በላይ በእዚህ ዓመት በጀት የሀገር ውስጡን ጨምሮ 1ነጥብ 6 ቢልዮን ዶላር ከዘንድሮ በጀቷ ከፍላ እዳዋን ዝቅ አድርጋለች። በዘመነ ሕወሓት ኢትዮጵያ የመበደር አቅሟ ከመውረዱ በላይ የውጭ የግል ባንኮች ደረጃ ወርዳ መበደር ጀምራ ነበር።ዘንድሮ ኢትዮጵያ የንግድ ብድር ካለመውሰዷ ባለይ ሁሉም የመንግስት የልማት ድርጅቶች አንዳቸውም ኪሳራ  ሳያሳዩ ማሳለፋቸው ነው የተገለጠው።
  • በከፍተኛ ኪሳራ እና አላግባብ የሆነ ብድር በተለይ ለህወሓት ሰዎች በመስጠት ችግር ላይ ወድቆ የነበረው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከኪሳራ ወጥቶ ዘንድሮ 3ነጥብ 3 ቢልዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን ገልጧል።ባንኩ ዓመታዊ በዓሉን በአዲስ አበባ ግራንድ ኤልያና ሆቴል ሲያከብር የባንኩ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮሐንድ አያሌው እንደተናገሩት ባንኩ ከፍተኛ የመዋቅር ለውጥ እያደረገ ሲሆን  ወደ ዓለም አቀፍ ባንክ ለማሸጋገር እየሰሩ መሆኑን ገልጠዋል።
  • ጎንደር ጫት መቃም፣ማስቃም እና መሸጥ ተከልክሏል።የከተማው አስተዳደር ይህንን ሕግ ከነሐሴ 28/2013 ዓም ጀምሮ ሥራ ላይ የዋለ ሲሆን ከእዚህ በፊት በጫት ንግድ ላይ የተሰማሩ በሌላ የንግድ ዘርፍ እንዲሰማሩ ክልሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጧል።ጫት እንደ እንግሊዝ እና ሳውዲአረብያ ያሉ ሀገሮች በአደገኛ ዕፅነት የተመደበ ሲሆን የምቅም ሰው በወንጀል እንደሚጠየቅ ይታወቃል። በዘመነ ህወሓት ህዝቡ ጫት እንዲቅም ከመቸውም ጊዜ በላይ የተለቀቀ ሲሆን በተለይ የጫት መቃምያ ቦታዎች በትምህርት ቤት እና ዩንቨርስቲ አካባቢ ሆን ተብሎ ሲከፈት መንግስት አንዳች እርምጃ ወስዶ አያውቅም። በአንድ ወቅትም አቶ መለስ ወጣቶች በሚሊንየም አዳራሽ ሰብስበው እራሳቸው ጫት እንደሚቅሙ የተናገሩበት ጊዜ እንደነበርም እናውስታውሳለን።
  • በአዲስ አበባ አራት ኪሎ ፓራላማ ፊት ለፊት የሚገኘው ቦታ እየተሰራ ያለው መፃሕፍ ቤት በቅርቡ ይመረቃል።መፃህፍት ቤቱ 38687 ካሬ ላይ ያረፈው መፃህፍት ቤት በአንድ ጊዜ 3500 ሕዝብ የሚይዝ ሲሆን የሕፃናት እና ያዋቄዎች ክፍሎች አሉበት።በተጨማሪም ሶስት አዳራሾች፣ትያትር ቤት እና በቂ የመኪና ማቆምያ ያለው ነው።
የአዲሱ መፃህፍት ቤት ፎቶዎች በከፊል ከስር ይመልከቱ
 
 









============
ማስታወቂያ 
============
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

Tuesday, September 7, 2021

የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር እና የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በመንፈሳዊ ዕይታም ብንመለከተው የሙስሊሙም የክርስቲያኑም እኩል መነሻ ታሪክ እና ሀብቶች ናቸው።የሁለቱም እምነቶች ሊቃውንት ይህንን ያውቃሉ።ህዝቡም ማወቅ አለበት።

==========
ጉዳያችን ምጥን 
==========
የእንቁጣጣሽ ቀን በኦስሎ ምን አለ? (የአንድ ደቂቃ ቪድዮ ከስር ያገኛሉ)

ሰንደቅ ዓላማችን እና የዘመን አቆጣጠራችን በመንፈሳዊ ዓይንም  የክርስቲያኑም የሙስሊሙም የጋራ ሀብት 

ኢትዮጵያ የፈጣሪ ልዩ ሀገሩ ነች።ሁለቱ ቀደምት የኢትዮጵያ እምነቶች ክርስትና እና እስልምና ለዘመናት ተከባብረው፣ተደጋግፈው እና ሕዝብ በአንድነት አስማምተው የኖሩት የሁለቱም እምነቶች መሪዎች መፃህፍቶቻቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁ ሊቃውንቶቻቸው ስለሚመሯቸው እምነታቸውን ጠብቀው ኢትዮጵያን በተመለከተ ያስቀመጡልን ውርሶች ሁሉ የጋራ ሀብቶቻችን ሆነው ኖረዋል ወደፊትም ይኖራሉ።አላዋቂነት ክፉ ነው እና በዘመናችን በተለይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማን የአንድ ወገን መለያ ብቻ የምትመስላቸው ቢኖሩ የእምነታቸውን ሊቃውንት ጠጋ ብለው አለመጠየቃቸው ያመጣው እንጂ ኢትዮጵያ ስንዱ እመቤት ነች ሲባል ለሁሉም ማለት መሆኑን የበለጠ ባወቅናት ቁጥር የምንረዳው ነው።

የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እና የዘመን አቆጣጠራችን ሙሉ ኢትዮጵያዊ ነው።

እውቁ ፀሐፊ ከበደ ሚካኤል “ታሪክና ምሳሌ አንደኛ መጽሃፍ” መግቢያ ላይ “ሰንደቅ ዓላማ የነፃነት ምልክት፣ የአንድ ህዝብ ማተብ፣ የኅብረት ማሰሪያ ጥብቅ ሐረግ ነው….. ሰንደቅ ዓላማ ትዕምርተ ሃይል ትዕምርተ መዊዕ ነው፡፡ ሰንደቅ ዓላማችን አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ፣ ሦስት ቀለማት ናቸው፡፡ ምሳሌያቸውም አረንጓዴው ተስፋ፣ ልምላሜና ሀብት፣ ብጫው ሃይማኖት አበባና ፍሬ፣ ቀዩ ፍቅር መስዋዕትነትና ጀግንነት ነው፡፡”በማለት ገልጠውታል።

በእዚህ ምጥን ፅሁፍ ላይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማን በመንፈሳዊ ዓይን ለሚተረጉሙ አንዱ መነሻ ለኖህ የተገባለት ቃል ኪዳን በሰማይ መታየቱን ነው። የኢትዮጵያ ዘመን መለወጫም አንዱ መገለጫ የጥፋት ውሃ ጎድሎ ኖህ መሬት ወርዶ ለፈጣሪ ምስጋና ያቀረበበት ነው።አብርሃም እና ኖህ ደግሞ የክርስቲያኑም የሙስሊሙም ጥንት አባቶች ናቸው።ገና በእግዚአብሔር ለሚያምነው የሙሴ ሕግ ሳይሰጥ፣ በአላህ ለሚያምነውም ቁራን ሳይወርድ በቁራንም በመፅሐፍ ቅዱስም  የኖህ ታሪክ ሁለቱም ላይ ተከትቧል።ኢትዮጵያ እንዲህ ነች። እርስ በርሷ የታረቀች!

ለእዚህ ነው ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችም ሆነ ሙስሊሞች ሰንደቅ ዓላማቸው እና ዘመን አቆጣጠራቸው ከእምነት አንፃርም የጋራ ሀብታቸው ነው።ይህንን ለልጆች ማስታወቅ ይገባል።

ስለ ኖህ ቁራን እንዲህ ይላል -

''አላህ ለእነዚያ ለካዱት ሰዎች የኑህን ሴትና የሎጥን ሴት ምሳሌ አደረገ።ከገቢዎቹም ጋር አላትን ግቡ ተባሉ'' 
 ቁርአን ሱረቱ 66፣10
'' ኑሀንም አለ ጌታዬ ሆይ ከከሃዲዎቹ በምድር ላይ አንድንም አትተው።'' ቁርአን ሱረቱ 71፣26

ስለ ኖህ መፅሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል - 

 ''እግዚአብሔርም አለ። በእኔና በእናንተ መካከል፥ ከእናንተም ጋር ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል፥ ለዘላለም የማደርገው የቃል ኪዳን ምልክት ይህ ነው፤ ቀስቴን በደመና አድርጌአለሁ፥ የቃል ኪዳኑም ምልክት በእኔና በምድር መካከል ይሆናል።በምድር ላይ ደመናን በጋረድሁ ጊዜ ቀስቲቱ በደመናው ትታያለች፤'' ዘፍጥረት 9፣12-14

ስለሆነም የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር እና የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በመንፈሳዊ ዕይታም ብንመለከተው የሙስሊሙም የክርስቲያኑም እኩል መነሻ ታሪክ እና ሀብቶች ናቸው።

የእንቁጣጣሽ ቀን በኦስሎ ምን አለ? ቪድዮውን ይመለከቱ።



 

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...