ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, October 31, 2016

የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ምስረታ በተመለከተ (የጉዳያችን ምልከታ)



ጉዳያችን / Gudayachn
ጥቅምት 21፣2009 ዓም 
================
  • ምስረታው ማዕከላዊ እና አሰባሳቢ ሚናው ላይ ያተኩር። 
  • ዐማራው ላይ የደረሰውን በደል እና እየወጣ ያለውን የፖለቲካ ኃይል ማዳመጥ ይገባል።
  • የአገራዊ ንቅናቄው ድምፁን የሚያሰማበት አንድ የሚድያ ፕሮግራም ሊኖረው ይገባል።

ምስረታው ማዕከላዊ እና አሰባሳቢ ሚናው ላይ ያተኩር
=======================================
ጥቅምት 20፣2009 ዓም ዋሽንግተን ዲሲ ላይ በአራት ድርጅቶች ፊርማ የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ መመስረቱን ኢሳት በቀጥታ ከስፍራው ዘግቧል።ምስረታው ወቅታዊ እና አስፈላጊ ነው።በስራው ላይ የደከሙ ምሁራን ምስጋና ይገባቸዋል።የእዚህ አይነቱ ስብስብ ሲፈጠር ማዕከላዊ እና አሰባሳቢ ሚናው የጎላ መሆኑ ጥቅም አለው። ኢትዮጵያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታት ውስጥ ሁለት የመንግስት ለውጥ አልፋለች።በሁለቱም ለውጥ ወቅት ግን የተዘጋጀ ማዕከላዊነትን እና የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችን ሃሳብ የሚያንፀባርቅ ተቋም አለመኖሩ ሽግግሩ እንዲጠለፍ ሆኗል።አሁንም የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ማዕከላዊ እና አሰባሳቢ ሚናውን የሚያጎሎ ስልታዊ ስራዎች ላይ ማተኮር አለበት።

ዐማራው ላይ የደረሰውን በደል እና እየወጣ ያለውን የፖለቲካ ኃይል ማዳመጥ ይገባል
========================================
በኢትዮጵያ ውስጥ ጉልህ ብቻ ሳይሆን በስብጥሩም ሆነ ለኢትዮጵያ እንደ ሀገር መቀጠል ከፍተኛ መስዋዕትነት ከከፈሉት ውስጥ የዐማራው ኅብረተሰብ አንዱ ነው።ባለፉት 25 ዓመታት ውስጥ በሕወሓት የፖለቲካ ፕሮግራም (ማንፌስቶ) ውስጥ ´´ጠላት´´ በሚል ቃል የተፈረጀ ኅብረተሰብ ነው። ለእዚህ ፍረጃ እስካሁን ሕወሓት ይቅርታ አልጠየቀም።ይልቁንም ይህንን ኅብረተሰብ በትውልዱ ብቻ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ በይፋ ስነዛበት ሰንብቷል።ይህ ብቻ አይደለም።በቀጥታ በሕወሓት እና እርሱ በቀሰቀሳቸው ሁሉ በአደባባይ ደሙ ፈሷል፣እንደ አውሬ እየተሳደደ አንገቱ ተቀልቷል፣ከሶስት ትውልድ በላይ ከኖረበት መሬት እየተገፋ ስደተኛ ሆኗል።ይህ ሁሉ ሲሆን የሕወሐት መንግስት አንዳችም የዜግነት ክብሩን አልጠበቀለትም።

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ ላይ ይህንን በደል በሚገባ አለመረዳት በእራሱ ትልቅ ችግር ይዞ ይመጣል።አሁን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኙ ወጣቶች  የእዚህን ኅብረተሰብ ብሶት የሚያንፀባርቁት በቅርብ በሀገር ቤት የደረሰውን ሁሉ ስለሚረዱ እና ለመረጃው ቅርብ መሆናቸውን ማመን ይገባል።በደሉ ይህ ፅሁፍ እየተፃፈ በዛሬው እለት ብቻ ከ200 በላይ በሚሆኑ የዐማራ ተወላጆች ላይ የግድያ ትዕዛዝ ወጥቷል።በሺህ የሚቆጠሩ ወደ እስር ቤት ተግዘዋል።በኢትዮጵያ ምድር በአሁኑ ወቅት በስፋት እና በብዛት የጦር መሳርያ አንስቶ እየተፋለመ ያለ ኃይል በእዚሁ ዐማራ  መሬት ላይ ይገኛል።ይህ በእራሱ ማንም የፖለቲካ ኃይል ይህንን ክፍል አርቆ ወደፊት ሊሄድ እንደማይችል አይነተኛ ማሳያ ነው።በተለይ የትጥቅ ትግሉ ከሕወሓት ጋር ብቻ ሳይሆን ከሱዳን ወታደሮች ጋርም መሆኑ የእዚህን ኃይል አካባቢያዊ ተፅኖ ከወዲሁ ለመረዳት ያስችላል።

ይህንን የፖለቲካ ክስተት በአግባቡ አለመያዝ በእራሱ ለነገዋ ኢትዮጵያ ትልቅ ስጋት ነው።እጅግ የመረረ ስሜት፣እንቅስቃሴ እና ቁጭት እየተሰማ ነው።ይህንን ስሜት ማዳመጥ፣የተፈፀመውን በደል መረዳት እና ወደ ጋራ ኢትዮጵያዊ አጀንዳ መቀየር የኢትዮያ የጋራ ንቅናቄ ሊሰራው ከሚገባቸው ቀዳሚ ተግባሮች ውስጥ አንዱ መሆን አለበት።ይህ ማለት በደል በሌላው ላይ አልደረሰም ማለት  አይደለም።ሆኖም ግን  በአንዳንድ የአገራችን ማኅበረሰቦች በተለይ በዐማራው ላይ የሚፈፀሙት ጥቃቶች ተቋማዊ እና ኢትዮጵያን በእረጅም ጊዜ የመበታተን እቅድ ያላቸው ሁሉ በስልታዊ ኢላማነት  የሚፈፀሙ ከመሆናቸው አንፃር ልዩ ትኩረትን ይሻሉ ለማለት ነው።


የአገራዊ ንቅናቄው ድምፁን የሚያሰማበት አንድ የሚድያ ፕሮግራም ሊኖረው ይገባል
===================================
የአገራዊ ንቅናቄው ትናንት በአዳራሽ እንደተመለከትነው በሚቀጥሉት ጊዜያት ምንም ድምፁን ሳያሰማ ወራት ካስቆጠረ ፍሬ ቢስ ይሆናል።አሁን ያቀፋቸው እና ወደፊት የሚያቅፋቸውን ድርጅቶች የጋራ ተግባራት፣ርዕዮች እና ዕቅድ ሁሉ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያደርስበት ድምፅ ያስፈልገዋል።ይህ ድምፅ ደግሞ ሌሎች የበለጠ እንዲገናኙት የሚያደርግ ብቻ ሳይሆን እግረ መንገዱን ላለፉት 25 ዓመታት የተጎሳቆለውን አገራዊ እና ኢትዮጵያዊ አጀንዳ በአዲሱ ትውልድ ላይ ይቀርፃል።ይህ ትውልድ በእጅጉ ተጎድቷል።ይህ ትውልድ አፋር ተወላጅ ኢትዮጵያዊ የሚል የማይመስለው የወያኔ የሚያደነቁር ፕሮፓጋንዳ ሰለባ ነው።የእዚህ አይነት አገራዊ ንቅናቄ ኢትዮጵያዊነት በአፋሩ፣በኦሮሞው፣በሲዳማው ሁሉ ሲወሳ የማሰማት ኃላፊነት አለበት።

የአገራዊ ንቅናቄው ባለ አደራ እና ጠባቂ ሕዝብ ነው።ዋስትናውም ሕዝብ ነው።ከአገራዊ ንቅናቄው አፈንግጦ የግል እና የቡድን ጥቅሙን ከአገራዊ አጀንዳ ለማስቀደም የሚፈልግ ድርጅት የሚዳኘው በሕዝብ ነው።ይህንን ለማድረግ ግን አገራዊ ንቅናቄው ለሕዝብ መገለጥ አለባቸው የሚላቸውን መረጃዎች እና ልዩ የሚድያ ፕሮግራም በቶሎ መጀመር አለበት።ለምሳሌ በኢሳት ላይ ሳምንታዊ የግማሽ ሰዓት ቪድዮ ፕሮግራም ሊኖረው ይችላል።ይህ ካልሆነ ግን በመሬት ላይ የሚሰሩ የጋራ ስራዎችን ከሕዝብ ጋር ለማቀናጀት ችግር ይገጥመዋል።

ባጠቃላይ የአገራዊ ንቅናቄው ዋና መሰረት ያደረገው ችግራቸውን በኢትዮጵያዊነት እና በኢትዮጵያ ስር ለመፍታት የተዘጋጁ ድርጅቶችን ማሰባሰብ መጀመሩ ቁልፍ እና አስፈላጊው ጉዳይ ሲሆን በእዚህ ፅንሰ ሃሳብ ዙርያ በኢትዮጵያ ያሉ ለዘመናት የቆዩ ችግሮችን በእየደረጃው ለመፍታት ትልቅ በር ከፋች ነው።ይህ የሚሆነው ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ የእኔ ብሎ ንቅናቄውን ሲደግፍ እና ንቅናቄውም እራሱን ሁሉን አቀፍነቱን እያሰፋ ሲሄድ ነው።



ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Thursday, October 27, 2016

ሰበር ዜና/ Breaking News Ethiopia - አራት ቁልፍ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅቶች የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ (Ethiopian movement) መሰረቱ። Four key Ethiopian political organisations form one huge movement.

Gudayachn update

የኢትዮጵያ ንቅናቄን የመሰረቱት አራቱ ድርጅቶች በተስማሙበት ሰነድ ላይ ፊርማቸውን ዛሬ ጥቅምት 20፣2009 ዓም ዋሽግተን ዲሲ ላይ አሰፈሩ።
Today as at of October 30,2016.
Four Ethiopian political organisations leaders and high officials put there signature on their agreed document in Washington D.C

=================================================
አራት ቁልፍ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅቶች የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ (Ethiopian movement)  መሰረቱ።

ድርጅቶቹ : -

1/ አርበኞች ግንቦት ሰባት፣

2/ በአቶ ሌንጮ ለታ የሚመራው የኦሮሞ ሕዝብ ዲሞክራስያዊ ግንባር (ኦዲግ)፣

3/ የአፋር ሕዝብ ፓርቲ እና

4/ የሲዳማ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ መሆናቸውን ኢሳት ቴሌቭዥን በሰበር ዜናው በኢትዮጵያ የሰዓት አቆጣጠር ከሌሊቱ 8 ሰዓት ላይ አስታወቀ።የአራቱም ድርጅቶች መሪዎች ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ የስምምነት ፊርማቸውን በእዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ ዋሽንግተን ዲሲ ላይ እንደሚያሰፍሩ ይጠበቃል።

ድርጅቶቹ በኢትዮጵያ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ላይ ትልቅ ተፅኖ ፈጣሪዎች ናቸው።የኢትዮጵያን ትንሣኤ ያሳየን።

Breaking News Ethiopia
====================
Four Ethiopian political organisations form a single movement called Ethiopian movement. ESAT (Ethiopian Satellite Television) from Washington D.C disclosed it with its breaking news. For the past 25 years, Ethiopia never seen such a political movement. The political organisations are: -
1. Patriotic-Ginbot 7 movement for justice and democracy
2.  Oromo Democratic Front (ODF)
3. Afar Peoples Paty (APP) and
4. Sidama Peoples Democratic Movement ( SPDM)

It is becoming quite clear that the Political change  in Ethiopia is coming soon.

ማሪኝ ኢትዮጵያዬ!
በዳዊት ፅጌ



ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

የፈረንሣይ ራድዮ የእንግሊዝኛ ክፍል ከፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጋር ያደረገው ቃለ መጠይቅ The latest Radio France International (RFI) interview with Prof. Birhanu Nega,the chairman of Ethiopian Patriotic-Ginbot 7 movement from Eritrea

ድምፁ መሃል ላይ ከቆመ በአንዲት ቃል ያክል  አሳልፉት።ይቀጥላል።


You can listen also on ECADF  video  http://ecadforum.com/2016/10/26/prof-berhanu-nega-on-radio-france/ 

ጉዳያችን GUDAYACHN

www.gudayachn.com

Monday, October 24, 2016

በፈሰሰው የኢትዮጵያውያን ደም ላይ ተረማምዶ የሚመሠረት የሕወሓት የተቀባባ ካቢኔ ለኢትዮጵያ ´´ኢንፌክሽን´´ ያለበት ቁስል ነው (የጉዳያችን ማስታወሻ)



ኢትዮጵያ  በለውጥ ማዕበል ውስጥ ነች።ከለውጥ መለስ መፍትሄ የላትም።ማንም የመሰለውን ትንታኔ ሊሰጥ ይችላል።ይህ ግን በኢትዮጵያ ያለውን እውነታ አይቀይረውም።የኢትዮጵያ ሕዝብ በቴሌቭዥን መስኮት ላይ የሚያያቸውን ሰዎች ለውጥ ሳይሆን የኢትዮጵያ እንደ ሀገር መቀየር እና የማኅበረሰብ ሽግግር ይፈልጋል።ይህ ሽግግር ደግሞ በተቀባባ የሕወሓት መሠረትነት ሳይሆን ኢትዮጵያን እንደ ሀገር የሚያቆም፣ ሁሉንም በእኩልነት የሚያሳትፍ እና የሕወሓትም ሆነ የማንም የበላይነት የማይታይበት መንግስት ማቆምን ያለመ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ሕወሓት የተቀባባ መንግስት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ለማሳየት ሽር ጉድ እያለ ነው። ዛሬ ጥቅምት 14፣2009 ዓም የመጀመርያው የተቀባባ ካቢኔ ለኦሮምያ ተበርክቷል።የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የኦሮምያ ምክርቤት አዲስ ካቢኔ እና የክልሉ ፕሬዝዳንት መሾሙ ተነግሯል።ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ ከአንድ ሺህ  በላይ ኢትዮጵያውያን ከተገደሉ እና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ከታሰሩ በኃላ ይልቁንም መሰረታዊው የሕወሓት የጎሳ ፖለቲካ በኢትዮጵያውያን ጫንቃ ላይ በአዋጅ ስም ይበልጥ በተጫነበት ሰዓት የተቀባባ ካቢኔ በመመስረት የኢትዮጵያውያንን ጥያቄ መልሻለሁ ብሎ መመፃደቅ የሚያስከትለው አደጋ ቀላል አይደለም።

´´አሳማ ሊፒስቲክ ብትቀባ አሳማነቷን አትቀይረውም´´ የሚባለው የፈረንጆቹ አባባል ሕወሓት ለኢትዮጵያ ሕዝብ መደለያ ሊያቀርብ ያሰበውን  የተቀባባ ካቢኔ በሚገባ ይገልፀዋል።ሕወሓት ከኃላ ሆኖ በማሽከርከር የነበረ የጎሳ ፖለቲካውን በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በባሰ መልኩ ኢንድጭን መፍቀድ በፈሰሰው የኢትዮጵያውያን ደም ላይ መረማመድ ነው።ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያ መሰረታዊ የፖለቲካ ችግር ምንም አይነት መፍትሄ አይሰጥም። ይልቁንም ቆይቶ ለባሰ ችግር ኢትዮጵያን የሚዳርግ
´´የኢንፌክሽን´´ቁስል ማለት ነው ይቻላል።በኢንፌክሽን የተመታ ቁስል ስር የሰደደ እና በቀላሉ የማይድን ይልቁንም የሰውነት መቆረጥ ድረስ የሚያደርስ አደጋ ያለው ነው።

ሕወሓት ለገጠመው የህዝብ ተቃውሞ ማስታገሻ ክኒን አድርጎ ያቀረበው የካቢኔ አባላትን መቀየር ነው።ለእዚህም እንዲረዳው ታማኝ ተቃዋሚዎች እና በከፍተኛ ትምህርት ቋማት አካባቢ ያሉ ለስርዓቱ የሚቀርቡ ግለሰቦችን ጊዚያዊ ክኒን ሁኑኝ እያለ እየተማፀነ ነው።ይህ የሕወሓት መሰረታዊ ባህሪ ነው። ባለፉት ታሪኩም ስልጣኑ አጣብቂኝ ውስጥ ሲገባ ´´ከፀሐይ በታች የማንደራደርበት ጉዳይ የለም´´ የሚል የማባባያ ቃላት ተጠቅሞ ለማለፍ ይሞክራል።በ1997 ዓም ከቅንጅት ጋር አቶ መለስ ሲደራደሩ ወቅቱን በዘዴ ለማለፍ ብቻ አልመው እንደነበረ በማስከተል የቅንጅት አመራሮችን በሙሉ እስር ቤት ሲያስገቡ ታይቷል። ኢትዮጵያ ከገባችበት የጎሳ አጣብቂኝ ተላቃ በሰላማዊ መንገድ ወደ ሽግግር መንገድ ብትመጣ የማይወድ የለም።ሆኖም ግን ይህ በሕወሓት ዘመን ይሆናል ብሎ ማመን እራስን ማታለል ነው።ለእዚህ ሁለት ምክንያቶችን ማቅረብ ይቻላል። 

የመጀመርያው ምክንያት ሕወሓት እንደ ሌላው ሀገር ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ ኢትዮጵያውያን የመሰረቱት ሳይሆን የአንድ ክልል ሰዎች ብቻ የመሰረቱት ነው።እነኝህ ግለሰቦች ደግሞ ስልጣናቸውን መጠበቅያ አጥር አድርገው የሚከተሉት ጎሰኝነትን ማራገብ እና ስልጣንን በጠበንጃ አስገድዶ መጠበቅ ነው። ሁለተኛው ምክንያት ሕወሓት ለአርባ ዓመታት የሰራቸው በሀገር ውስጥም ሆነ  በውጭ ሃገራት ከባድ ወንጀሎች አሉ።ስለሆነም ከስልጣን ከወረድኩ በእነኝህ ወንጀሎች እጠየቃለሁ ብሎ ስለሚያስብ ስልጣኑን የህዝብ ደም እያፈሰሰ ማቆየትን ይመርጣል።

እንደመደምደምያ በእዚህ ሁሉ መካከል የዘውግ ተቃዋሚም ሆነ በኢትዮጵያዊነት ስር የተጠለሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ወሳኝ ደረጃ መድረሳቸውን ማወቅ አለባቸው። ወቅቱ በጥቃቅን ጉዳዮች ላይ እያተኮሩ ከመተባበር የሚሸሹበት ሳይሆን በግልፅ የጋራ የማግባቢያ ማታገያ አጀንዳ ቀርፆ ወደ ተግባር መሄድ አለባቸው።ወደ እዚህ ህብረት ለመግባት ፈቃደኛ ያልሆኑትንም በመጠበቅ ሌላ አመታትን ማባከን በሕዝብ ስቃይ መቀለድ ነው።አሁን የፖለቲካ ድርጅቶች መሰረታዊ የፍልስፍና መርህ ነጥሮ የሚወጣበት እና በሕዝብ የሚደገፉ እና የማይደገፉ መሆናቸው መለየት አለባቸው።በአላማ እና በአስተሳሰብ አንድ የሆኑት  ሰፊ መሰረት ይዘው ሕዝብ የሚያታግሉበት ወቅት ነው። ከእዚህ በዘለለ በዓላማ ከተለዩት ጋር የጎንዮሽ ንትርክን ባለማድረግ ነገር ግን ግልፅ የሆነ የመስመር ልዩነትን ለሕዝብ ግልፅ በማድረግ እና ፍርዱን ለሕዝብ በመተው ትግሉን መግፋት  ብቸኛው አማራጭ ነው።


ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

This weekend, over 100,000 Ethiopians attended conference live on the roadmap for transition and constitution of the country ከአንድ መቶ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን በቀጥታ የተከታተሉት በኢትዮጵያ የሽግግር ሁኔታ ላይ የተነጋገረ ጉባኤ ተካሄደ።


የአማርኛ ዜና ከእንግሊዝኛው  ስር ያንብቡ።

October 22 & 23,2016 were so crucial days to Ethiopian politics. The conference organised by Vision Ethiopia in collaboration with Ethiopian Satellite Television (ESAT) was held in Washington D.C.  A number of intellectuals, religious leaders and activists presented their papers and outlooks on the future structure and nature of Ethiopian Government, after the overthrow of the current brutal regime. The conference was followed live by over 100,000 Ethiopians in all over the world. The below ESAT news article explained properly about this particular conference.
=======================================

ESAT News (October 24, 2016)

A conference that deliberated on “roadmap for transition and constitution making in post-conflict Ethiopia” recommended the formation of transitional council “with tasks of peacemaking and peace building” in Ethiopia.

The conference, organized by Vision Ethiopia in collaboration with ESAT that was held from October 22 and 23, 2016 in Washington, DC, brought together political scientists, representatives of political organisation, activists and members of Ethiopian community from all across the globe.

The transitional council, according to a communique issued by the organizers, would, among others, “conduct a fair, free, credible election and transfer political power to the newly elected party or coalition of parties.”

Conference participants also called on the Ethiopian regime to immediately lift the state of emergency declared early this month.

The conference, which discussed the atrocities being committed by the ruling party in Ethiopia, also called on the regime to stop the killings perpetrated against innocent citizens and immediately “release all political prisoners and prisoners of conscience, including those in secret concentration camps without any precondition.”

The conference also called on opposition political parties to “immediately convene a national conference to establish a new political order in Ethiopia and negotiate and agree, in good faith, to establish a transitional/interim council/government.”

The conference also called upon the international and donor community to  “facilitate the effort of the Ethiopian people towards establishing a post-conflict political order,” and to “put pressure and encourage the ruling party to seriously consider convening an inclusive conference for a national charter.”

It is the third such conference for Vision Ethiopia, an independent team of Ethiopian scholars, that have been focusing on creating forums to discuss issues of political significance to Ethiopia.


የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ከስልጣን መውረድ እንዳለበት በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ የተካሄደው የምሁራን ጉባዔ ጠየቀ
================================
ኢሳት (ጥቅምት 14 ፥ 2009)

በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ የሚገኘው ገዢው የኢህአዴግ መንግስት የህዝቡን ጥያቄ በመቀበል ከስልጣን መውረድ እንዳለበትና በሃገሪቱ የሽግግር ስርዓትና የህገ-መንግስት ረቂቅ እንደሚያስፈልግ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ የተካሄደው የምሁራን ጉባዔ አስገነዘበ።
የቪዥን ኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው የጉባዔውን መጠናቀቅ አስመልክተው ለኢሳት እንደገለጹት “ህወሃት የሚመራው መንግስት ህዝብን እየገደለና ሰብዓዊ መብት እየረገጠ በመሆኑ ስልጣኑን ሊለቅ ይገባል።

በቪዥን ኢትዮጵያና በኢሳት ትብብር በሳምንቱ መገባደጃ ቅዳሜና እሁድ የተዘጋጀው ኮንፈረንስ ሲጠናቀቅ እንደተገለጸው አሁን ባለው የኢትዮጵያ ሁኔታ የሽግግርና አዲስ ህገመንግስት ያስፈልጋል።

በኮንፈረንሱ ማጠቃለያ ላይ በኢትዮጵያ አዲስ ስርዓት ለማበጀት የሽግግር ካውንስል ማቋቋም እንደሚያስፈልግ መግባባት ላይ መደረሱ ተገልጿል።

የቪዥን ኢትዮጵያ ዋና ጸሃፊ ዶ/ር አሸናፊ ጎሳዬ ለኢሳት እንደገለጹት፣ የሰላም ሚና ያለውና ሃገሪቱን ወደ ሽግግር ሂደት የሚወስደው ካውንስል የተለያዩ አካላት እንዲወስኑበት ማድረግ ያስፈልጋል።
አሁን ያለው ገዢ ፓርት ህወሃት/ኢህአዴግ ግድያውን እንዲያቆምና ለሰላም በሩን በመክፈት ለድርድር ፈቃደኛ እንዲሆን ጥሪ መተላለፍን ገልጸዋል።

ዶ/ር አሸናፊ እንዳሉት በኢትዮጵያ በተካሄደው ግድያና የሰብዓዊ መብት ረገጣ እጃቸው ያለበት ባለስልጣናት ማንኛውም የገዢው ፓርቲ አባላት በህግ መጠየቅ ይኖርባቸዋል።

በቪዥን ኢትዮጵያ የተካሄደውን ስብሰባ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በፌስቡክና በኢሳት ድረገጽ ቀጥታ ስርጭት መከታተላቸው ታውቋል። የስብሰባውን አጠቃላይ መግለጫና የተደረሰበትን ድምዳሜ ቪዥን ኢትዮጵያ በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

በደርግ ዘመን ይሰሙ የነበሩ ሃገራዊ መዝሙሮች እና ውጤታቸውን በማስታወስ ትምህርት እንውሰድ (ቪድዮ)

ይህ በሕወሓት ዘመን ለተወለዱ አዲስ እንደሚሆን አልጠራጠርም። አጀንዳው ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነበር።



ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com 

Friday, October 21, 2016

ህዝቡ ዲሽ ሊነቅሉ የሚመጡ የሕወሓት ወታደሮችን የመምታት ሙሉ መብት አለው።ንብረትን መከላከል የሞራል ግዴታ ነው!መረጃ የማግኘት መብት ዓለም አቀፍ ድንጋጌ ነው።

ጉዳያችን
ጥቅምት 12፣2009 ዓም
====================================
ዲሽ (የሳተላይት መቀበያ ሳህን)  የዓለም አቀፍ ዜናዎችን ከዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች የምንከታተልበት የመገናኛ መሳርያ ነው።ሰሞኑን የሕወሓት ቅልብ የአጋዚ ሰራዊት እና ሚሊሻ በእየቤቱ እየገባ ዲሽ መንቀል እና መስበር መጀመሩ ተሰምቷል።የቴሌቭዥን ቻናል መቀበያ ዲሽ አንድ ኢትዮጵያዊ ለፍቶ ካገኘው ንብረት ውስጥ ዋጋ አውጥቶ የገዛው የግል ንብረቱ ነው።ዲሽ መስቀል እና ዓለም አቀፍ ዜናዎችን መከታተል ወንጀል አይደለም።

ዲሽ ሊነቅል የሚመጣ ማናቸውም ፖሊስ ሆነ ወታደር፣ካድሬ  መመታት አለበት።ሕዝብ ንብረቱን የመከላከል ሙሉ መብት አለው።በእዚህ ጉዳይ ላይ መወላወል አይገባም።ኢትዮጵያዊ ሁሉ ቤቱ መጥቶ ንብረቱን ሊሰብር የመጣን ማንኛውንም ሰው በግልም ሆነ በቡድን ማጥቃት  የሞራል ልዕልና ነው።ሃገርን መከላከል የግል ንብረትን ከመጠበቅ ይጀምራል።መረጃ የማግኘት ሙሉ መብት እንዳለህ/ እንዳለሽ ማወቅ አለብህ።መረጃ የማግኘት መብት  በዓለም አቀፍ ደረጃ የተደነገገ መብትም ነው። በእዚህ ጉዳይ አክትቪስቶች ህዝብን ማንቃት አለባቸው።የእዚህ አይነቱን ተግባር ሕዝብ አምርሮ እንዲታገል አለማድረግ ባርነትን እንዲለምድ ማበረታታት ነው።ስለሆነም በእዚህ ጉዳይ ላይ ሕዝብ አምርሮ ንብረቱን እንዲከላከል ማንቃት ከመገናኛ ብዙሃንም ብዙ ይጠበቃል።


ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤትን በንግድ ዘርፍ ማኅበራት ስም ዛሬም እያነታረኩት ነው (የጉዳያችን ማስታወሻ)


ጉዳያችን/ Gudayachn
ጥቅምት 12/2009 ዓም
==========================
ሕወሓት ካመሳቸው በኢትዮጵያ ጠንካራ አደረጃጀት ካላቸው ተቋማት ውስጥ  የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት አንዱ ነው። ይህ በ1940 ዓም (1947 እኤአ) በቀዳማዊ አፄ ኃይለ ስላሴ ክትትል የተመሰረተው እና የኢትዮጵያን የንግድ እንቅስቃሴ ዘመናዊ መልክ ለማስያዝ ትልቅ ሚና የተጫወተ ተቋም የሕወሓት ዱላ ያረፈበት ገና ከጅማሮው መሆኑ ይታወቃል። 

ምክር ቤቱን ለማዳከም እና በአንድ ጎጥ ስር ለመቆጣጠር ከመሞከር ጀምሮ እስከ በክልሎች የመከፋፈል ሥራ ከተሄደ በኃላ  ሕወሓት አማራጭ መንገድ አድርጎ ያቀረበው  ሌላው መንገድ ተለጣፊ ማደራጀት እና የዘርፍ ማኅበራት የሚባሉ እንዲለጠፉ እና  የምክር ቤቱን ቅርፅ የመቀየር ሙከራ ነበር።ሆኖም ግን በብዙ ትግል በኃላ የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ስሙ ላይ የዘርፍ ማኅበራት የሚል ጨምሮ እንዲቀጥል ተደረገ።

በእዚህ መሰረት የዘርፍ ማኅበራት የሚባል መስርቶ በጥቃቅን ያደራጃቸውን ሳይቀር በካፒታል ከፍ ያሉትን አስርጎ አስገባ። እዚህ ላይ ለመድረስ ግን የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት እስከ ፍርድ ቤት ድረስ ያመላለሰው በርካታ ክርክሮች ሁሉ መደረጉ ይታወሳል።ምክር ቤቱን ይመሩ የነበሩት እነ አቶ ብርሃነ መዋ  እና አቶ ኢየሱስ ወርቅ ዛፉ የገቡበት የተለያዩ አጣብቂኞች ነበሩ። አቶ እየሱስ ወርቅ ዛፉ በተለይ ከንግድ ዘርፍ ማኅበራት ጋር የነበሩ ክርክሮች ላይ የንግድ ምክር ቤቱን ለማቆየት በርካታ ውጣ ውረዶች አልፈዋል ።

ለእዚህ ማስታወሻ ምክንያት የሆነኝ እግር ጥሎኝ ዛሬ ጥቅምት 11፣2009 ዓም ሸገር ዜና ስሰማ ከተወሰኑ ዓመታት ስንሰማው የነበረው የንግድ ምክር ቤቱ ንትርክ አቶ ገብረ ሕይወት ከሚባሉ ሰው ጋር ቀጥሎ መስማቴ ነው።ነገሩ እንዲህ ነው። የንግድ ዘርፍ ማኅበራት  አቶ ገብረ ሕይወት ገ/ እግዚአብሔር የሚባሉ የቦርድ ባለስልጣን እና የደቡብን ዘርፍ ማኅበራት በመወከል ደግሞ አቶ አሸናፊ የተባሉ ሰው ምክር ቤቱ ጭቅጭቅ ላይ መሆኑን የተለዋወጡትን ቃላት የሚያሳየው የነበረውን ስዕል ነው።የደቡቡ አቶ አሸናፊ ቦርድ ሁለቴ እንዳይመረጥ ሕጉ ያዛል  ካሉ በኃላ አቶ ገብረ ሕይወት እንዴት ሁለቴ ተመረጡ? በማለት ይጠይቃሉ።
በምላሹ አቶ ገብረ ሕይወት ሕጉን ቆይተን ነው ያየነው በማለት በቦርድ ደረጃ ያሉ ሰው ስንቴ መመረጥ እንደሚችሉ በደንብ ሕጉን ሳያዩ በመቅረታቸው ድጋሚ ለምርጫ እንደመጡ ይገልፃሉ።

አቶ አሸናፊ ድሮ ገና ነው ሕጉን የተናገርኩት አልሰማ ብለው ነው በማለት ይመልሳሉ።ጉዳዩ የስርዓቱ የመከፋፈል እና ቀጥሎ የመቆጣጠር አባዜ ነው።ይህ ማለት የንግድ ምክር ቤት አንድ እንዳይሆን በክልል ይከፋፍሉታል።ቀጥለው እርስ በርስ ያነታርኩታል። ለሚቀርበው ክርክር ደግሞ ፍርድ ሲሰጡ እንደሚመቻቸው ወይንም ክርክሩን የበለጠ በሚያባብስ መንገድ ያደርጉታል።እንዲህ እያደርጉ ኢትዮጵያን በእየዘርፉ ያደማሉ፣ይዘርፋሉ።

ይችን ንትርክ ከላይ ካልኩት ጋር አገናኙት።ንግዱን የመቆጣጠር አባዜው 100% የሚያረካ አልሆነም።ከሁሉም የሚያሳፍረው ግን የንግድ ምክር ቤት ከደረጃ ዝቅ ያለ መሆን ማለት ለአንድ አገር ያለው አሉታዊ ተፅኖ ቀላል አይደለም።በሌሎች አገሮች በአፍሪካም ጭምር ከፍተኛ ክብር ያላቸው የንግዱ ማኅበረሰብ የሚወከሉበት እና የውጭ ኢንቨስተሮች ስለ አንድ ሀገር የፖለቲካም ሆነ የምጣኔ ሀብት ሁኔታ ለመረዳት ከፖለቲካ ሰዎች ይልቅ የንግድ ምክር ቤት አባላትን የበለጠ የሚያምኑበት ሁኔታ የሰፋ ነው።የአሁኑ የሕወሓት ምልምል የንግድ ምክር ቤት ግን ይህንን የሚያሟላ አልመሰለኝም።ምናልባት በቦታው ያሉትን በቅንነት የሚሰሩትን መንካት እንዳይሆንብኝ አይመስለኝም የሚለውን ያዙልኝ።

በአንድ ወቅት የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት በግል ሕይወታቸው ዙርያ ከኢቢኤስ ቴሌቭዥን ጋር ያደረጉት ቃለ መጠይቅ ብዙ የሕይወት ተሞክሮን ያስተምራል።ከእዚህ በታች ያለውን ተጭነው ይመልከቱት። 

ጉዳያችን GUDAYACHN 

Monday, October 17, 2016

´´ የባርነት አዋጁን ተግባራዊ ለማድረግ የሚንቀሳቀሱ ሁሉ የሕዝባዊ ትግሉ የግልም ሆነ የቡድን ኢላማዎች ናቸው´´ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አዲስ መልዕክት ለኢትዮጵያ ሕዝብ አስተላልፈዋል። (ቪድዮ)

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ዛሬ ጥቅምት 8፣2009 ዓም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያስተላለፉት መልዕክት
ከኢሳት ዩቱብ ላይ የተወሰደ
ESAT Youtube


ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Sunday, October 16, 2016

ሕወሓት በአሰቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሊያሳካ ያሰበው ግልፅ እና ድብቅ ግቦች


ጉዳያችን / Gudayachn  
ጥቅምት 7፣2009 ዓም
www.gudayachn.com
=====================

የአሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ በኢትዮጵያ ላይ ከታወጀ ጥቂት ቀናት ውስጥም በሕወሓት ላይ የሚደረገው ተቃውሞ የመቀነስ አዝማምያ አላሳየም።በባህር ዳር የስራ ማቆም አድማ የተደረገው ከአዋጁ በኃላ ነው፣ አሁንም ከአዋጁ በኃላ በሰሜን ጎንደር የትጥቅ ትግሉ ቀጥሏል፣ ባለፈው ዓርብ በጎንደርም የስራ ማቆም አድማ እንዲደረግ ጥሪ ቀርቧል።ይህ ሁሉ የሚያሳየው የአዋጅ ጋጋታው ያመጣው ለውጥ አለመኖሩን ነው።እርግጥ የኢትዮጵያን ሕዝብ መስዋዕትነትን ሊጨምረው ይችላል።ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን አዋጁ በወጣ በሳምንቱ አዋጁ ምን ምን እንደሚከለክል የመከላከያ ሚኒስትር በሚል ስም ስር በሚገኙ ግለሰብ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተገልጦለታል።እዚህ ላይ የተከለከሉ እና ያልተከለከሉ የተባሉትን የገዢው ስርዓት  መገናኛ ብዙሃን ያሉትን መድገም አያስፈልግም።ባጭሩ አዋጁ በአዲስ አበባ የሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቦች ከአዲስ አበባ 40 ኪሎ ሜትር በላይ እንዳይርቁ ተነግሯል።በተጨማሪም መሰረታቸውን ውጭ ያደረጉ የቴሌቭዥን እና የራድዮ ጣብያዎችን ኢሳት እና ኦኤምኤን ጨምሮ መስማት የተከለከለ መሆኑም ተነግሯል።አሁን ጥያቄው ሕወሓት ይህንን አዋጅ ያወጣበት እና እግረ መንገዱን ሊያሳካው ያሰበው ግልፅ እና ድብቅ ግብ ምንድነው? የሚለውን ጥያቄ መመለሱ ነው።

ሕወሓት በአዋጁ ሊያሳካ ያሰበው ግልፅ እና ድብቅ ግቦች 

1ኛ/ ግልፅ ግብ  

አዋጁ በዋናነት ለሁሉም ግልፅ እንደሆነው የሚታየው ዓላማ የሕወሐትን የስልጣን ዘመን ማራዘም ነው።ይህም የሚቃወሙትን በሙሉ አንገት አስደፍቶ እና አሸማቆ በስልጣን ዘመኑ መቆየት ነው። ማሸማቀቅ እና አንገት ማስደፋት ብቻ አይደለም ጎን ለጎን በፈረሰው የኦህዴድ እና የብአዴን ድርጅቶች ምትክ አዲስ አሽርጋጆች እና መስሎ አዳሪዎችን ወደ መድረኩ እያመጣ የተቀባቡ ግለሰቦች እና ድርጅቶችንም ይፈጥርበታል።ለእዚህም ነው እንደ ልደቱ አይነቶቹን መድረክ መስጠት የፈለገው።በእዚህ ሂደት ውስጥ ግን መንገዱ አልጋ በአልጋ እንዳልሆነ በእርግጠኝነት አብዛኛው የሕውሓት አቀንቃኝ ያውቀዋል።ሆኖም ግን ተስፋ መቁረጥ እና ከወንጀል ነፃ ሆኖ ለመኖር እንደ ብቸኛ መፍትሄ የተወሰደው ዛሬ እየገደሉ እና እያሰሩ ነገን በተስፋ መጠበቅ ነው። ይህ ሁኔታ ግን ተቃውሞው እየጠነከረ ሲመጣ እና የበላይነት መያዝ ሲጀምር ለሕወሓት የበለጠ ወደ አዘቅት ብቻ ሳይሆን እርስ በርሱም የመከፋፈል ዕጣ እንደሚገጥመው የሚያጠራጥር አይደለም። 

2ኛ/ ድብቅ ግብ 

ሕወሓት በአዋጁ ዋናውን እና ግልፅ ግቡን ለማሳካት ከሚሄድበት መንገድ በተጨማሪ ሁለት ድብቅ ግቦችን ማሳካት ያስባል። 

አሰቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንደ አካባቢ ስጋት እንዳልሆነ የሚነገረው በትግራይ አካባቢ ነው።በተቀረው የኢትዮጵያ ክፍል ከስጋት አልፎ ለበለጠ ትግል መነሳት አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ብቸኛ አማራጭ ሆኖ ቀርቧል።የአዋጁ አፈፃፀም ለምሳሌ የአደጋ ቀጠና ተብለው ከተጠቀሱት መንገዶች ውስጥ አንድም የትግራይ ክልል መንገድ የለም።ይህ ማለት ሕወሓት በአንደኛ ደረጃ ስጋት አለብኝ የሚለው ያውም ተቃዋሚዎች መሽገውባታል የምትባለው ኤርትራ ጋር የሚያዋስን መንገድ ለምን አንዱም ቀይ መስመር አልተባለም? ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል።ይህ ብቻ አይደለም አዲስ አበባ ዙርያን ለዲፕሎማቶች የስጋት ከተማ አድርጎ  ያስቀመጠበት አግባብ እንደተባለው ሕዝባዊ ተቃውሞው የውጭ ሀገር ዜጎችን ኢላማ አድርጎ ነው? ባለፈው በሰበታ መስመር መገደሏ የተገለፀው አሜሪካዊት በእውነት በተቃዋሚ ሕዝብ ነው የተገደለችው? ከእዛ በፊት የሚኒባስ ጥቃት ያውም ተሳፋሪ ባለበት ተደብድቧል? እነኝህ ሁሉ ጥይቄዎች በአግባቡ መመለስ አለባቸው። በሌላ በኩልም መጠየቅ ያለብን ጉዳይ አለ በኦሮምያ እና በአማራ የተቃጠሉት ፋብሪካዎች እና እርሻ ቦታዎች በእውነት ሁሉም በተቃዋሚ ነው የተቃጠሉት? በጎንደር ገበያ ላይ የተፈፀመው እና በኃላም ሌላ የጎንደር ቦታዎችን ልታቃጥል ስትል የተደረስባት ከትግራይ የመጣች ነች የተባለችው ሴት ሰሞኑን ከሚቃጠሉት ቃጠሎዎች አንፃር ምን ይነግረናል? ይህችው ወንጀል ለመስራት ሙከራ ላይ እንደሆነች የተነገረው ሴት በወታደር ታጅባ እጇ ላይ ሰንሰለት ሳይገባ እንድትሄድ የሆነበት ጉዳይስ ምን ያሳየናል?

ከላይ ከተነሱት ጥያቄዎች አንፃር አዋጁ ሊያሳካ የሚያስባቸው ድብቅ አላማዎች እንዳሉት እና እነኝህ ድብቅ አላማዎች ደግሞ ከሕወሐት የረጅም ጊዜ ስልቶች ጋር ሁሉ የተቆራኙ እንደሆኑ መረዳት ይቻላል።በእዚህ አዋጅ ሕወሓት ግልፅ ከሆነው ስልጣኑን ማስጠበቅ በተጨማሪ ሁለት ድብቅ አላማዎች (ግቦች) አሉት። እነርሱም ; - 

ሀ/ የመሃል ሃገሩን እና የደቡብ አካባቢን በአዋጁ አማካይነት ሙሉ በሙሉ በመምታት ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መሰረቱን ማናጋት እና የበለጠ ማደህየት።

በእዚህ አዋጅ መሰረት በሕወሓት መዘውር ውስጥ በሚገባ ያልገቡ የንግድ ድርጅቶች በሰበብ አስባቡ እና የሽብርተኛ ታቤላ እይተለጠፈባቸው ይዘጋሉ፣ይወረሳሉ ወይንም ከገበያ እንዲወጡ ይደረጋሉ።
በእዚህም የሕወሓት ሰዎች እንዲቆጣጠሩ ይደረጋሉ።የበለጠ ድሃ እንዲሆን  የተደረገው ሕዝብ የበለጠ የእነርሱ ተገዢ እንዲሆን እና አመፁን ዝም ማሰኘት ይቻላል ብለው ያስባሉ።ለእዚህ ነው የሚቃጠሉት ድርጅቶች ሁሉ የሕወሓት ሳይሆኑ እንደ ጎንደር ገበያ ሕወሓት እራሱ የሚያቃጥላቸው ድርጅቶች እንዳሉ ማወቅ ያለብን።

ሌላው የማደህየት ሥራው የሚገልጠው የአዋጁ አስፈፃሚ ኮማንድ ፖስት ስር ያሉ  ወታደሮቹ እንዲዘርፉ የውስጥ በጎ ፈቃድ አሳይቷል። ለእዚህም ማስረጃው በአዲስ አበባ በተደረጉ አሰሳዎች የውጭ ምንዛሪ እና ሞባይል ስልኮች መዘረፋቸው እና ወታደሮቹ በግላቸው መውሰዳቸው ነው።ይህ በትንሹ የተጀመረ ሂደት ነገ ኮማንድ ፖስቱ የእገሌ ድርጅት በሽብር ተግባር ሊሰማራ ሲል ተይዞ ድርጅቱ ተወረሰ ሲል እንደምንሰማ መጠራጠር የለብንም።

ለ/ የትግራይን ምጣኔ ሃብታዊ እና ማኅበራዊ ልዕልና በቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በሚገባ መስፈኑን ዋስትና ለመስጠት 

ሕወሓት ከመነሻው ዋና ግቡ መሃል እና ደቡብ ኢትዮጵያን ከቻለ ለሚገነባው የትግራይ ኢምፓየር በግብዓትነት እንዲያገለግሉ ማድረግ እና  የተወሰነ ልማት እያሳዩ የቀረውን ግን ማጋበስ ነው።ይህ የሚሆነው ግን ሕዝብ በተቃውሞ እስካልተነሳበት ድረስ ነው።ሕዝብ በተቃውሞ ከተነሳበት ግን ሊያደርግ የሚያስበው መሃል ሃገሩን እና ደቡብን በብሄር ግጭት  እና በምጣኔ ሀብት ቀውስ አተራምሶ ቀጥሎም ማውደም እና የትግራይ ምጣኔ ሀብት የመሳብ (puling role) ወይንም የማዕከላዊ ሚናውን(central role) እንድትጫወት ማድረግ ነው። ይህም የአዲስ አበባን የዋና ከተማነት እና የኢንዱስትሪ ማዕከልነት በተለያየ መንገድ አውድሞ ልማቱ ወደ ትግራይ ማዕከልነት እንዲቀየር ማድረግ ነው። ይህ ደግሞ የእረጅም ጊዜ ሂደት ነው።ሆኖም ግን የእዚህ አይነቱ ግርግሮች እንደ አንድ አጋጣሚ ሕወሓት ይመለከተዋል እና የእረጅም ጊዜ ሂደቱን ያፋጥናል ብሎ ያስባል። 

ባጠቃላይ ሕወሓት በአዋጁ ግልጥ እና ድብቅ ዓላማዎች እንዳሉት መረዳት ይገባል።ብዙ ሕዝብ የሚያወራው ስለ ግልጡ እና የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ነው የሚለውን እንጂ እግረ መንገዱ እየሰራ ያለው የእረጅም ጊዜ ግቡ የተከሰተለት አይመስለኝም።የፖለቲካ መፍትሄዎችን የማይሰጥበት ዋናው ምክንያት ድብቅ አላማውን እንደሚያሳኩለት ስለሚያምን ነው።የጎንደርም ሆነ የኦሮምያ ተቃውሞዎች ከመጀመርያው ፍፁም ሰላማዊ ነበሩ።በጎንደር በመቶ ሺህ የሚቆጠር ሕዝብ ታሪካዊውን ሰልፍ ሲያደርግ አንዳች ኮሽታ አላሰማም።ነገር ግን ሕወሓት ቀላል መነሻ የነበራቸውን ጉዳዮች እያከረረ እና የህዝቡን ሰላም እየነሳ እዚህ አድርሶታል።በእዚህም የአማራ እና የኦርሞ አካባቢዎች የስጋት ቀጠና አድርጎ ትግራይ ግን ሰላማዊ ቀጠና አድርጎ አቅርቧል።ይህ ማለት አንድ ቱሪስት ጎንደር ከምትጎበኝ መቀሌ ብትሄድ የተሻለ ነው እያለ የሕዝብ ምጣኔ ሀብት እድገትን በማቀጨጭ የእረጅም ጊዜ የእድገት ማዕከልን የመቀየር ሂደቱን ያጧጡፍበታል።በተመሳሳይ መንገድም መሃል ሀገር ያለውን ባለ ሀብት ለ25 አመታት ያህል ከከተማ ይዞታው ከማፈናቀል ጀምሮ ከገበያ እንዲወጣ እያደረገ እና የንግድ መስመሮቹን በሙሉ በእራሱ ሰዎች በማስያዝ የምጣኔ ሀብቱንም ሆነ የማኅበረሰባዊ የበላይነትን ለመቆጣጠር ይጠቀምበታል።

ስለሆነም እንደ ኢትዮጵያዊነት መኖር ካለብን እኩልነት በቅድምያ መምጣት አለበት።ይህ እኩልነት ደግሞ የጥቂቶች (minority ) መንግስት የሆነው የሕወሓት መንግስት ስልጣኑን ለሕዝብ ማስረከብ እና የሁሉንም ሕዝብ ውክልና ያገኘ መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ መመስረት የእያንዳንዱ ዜጋ ግዴታ ነው።ከእዚህ ውጭ አዋጁ በእራሱ ከፋሺዝም አዋጅ ያልተለየ እና ከፍተኛ ጦርነት የሚቀሰቅስ አደጋውም በበለጠ ለሕወሓት ህልውና ቆምያለሁ በሚለው ላይ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም።ይልቁንም እነኝህ አደጋዎች ከመድረሳቸው በፊት የሕወሓት ደጋፊዎች በመጨረሻው መጨረሻ ሰዓት ላይም ሆነው ሊያስቡበት ይገባል።የማይስኬድ መንገድ ለጊዜው የሚያራምድ ይመስላል እንጂ በማንኛውም ሰዓት ይርዳል።ይህ ደግሞ ያለፉት ጥቂት ወራቶችም በሚገባ አስተማሪ ናቸው።


ጉዳያችን GUDAYACHN


 www.gudayachn.com

Thursday, October 13, 2016

ኢቲቪ በፕሮፌሰር ብርሃኑ፣በጀዋር እና ግብፅ ዙርያ በሚሰራው ፕሮፓጋንዳ የሕዝብ መሳቅያ ሆኗል።

ጉዳያችን / Gudayachn
ጥቅምት 5፣2009 ዓም 
====================
  • ኢቲቪ = ´´ሕወሓት ስልጣን ላይ ካልቆየ ትጠፋላችሁ´´ 
  • ሕዝብ=´´ውረዱ እንጂ እንደማንጠፋ ታያላችሁ´´ 
ኢቲቪ ሰሞኑን አክቲቪስት እና የኦኤምኤን ቴሌቭዥን ጣብያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጀዋርን፣ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን እና የግብፅ መንግስትን የሚወቅስልኝ ያለውን ፕሮፓጋንዳ ተያይዞታል።ጉዳዩ ግን ሕዝብን በእራሱ ዜጎች የማስፈራራት ሙከራ ካልሆነ በቀር በእዚህ ደረጃ ያለ የህዝብ ጥያቄን ማደባበስ አይቻልም።ለመሆኑ ሕወሓት ከመቼ ወዲህ ነው የሀገር ጠበቃ የሆነው? እስኪ ሶስቱን የፕሮፓጋንዳው መነሻ የሆኑትን ተራ በተራ ባጭሩ እንመልከት።

ጀዋር 
======
ጃዋር ገና በልጅነቱ የተናገራቸውን (ሰውነቱም ቀጭን ሆኖ ነው በኢቲቪ የሚታየው) ንግግሮች ኢቲቪ እየመዘዘ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሊያስፈራራበት ይሞክራል።ጀዋር ቀድሞ ያላቸውን አባባሎች በተለያየ ጊዜ ማስተባበያ ሰጥቶበታል።ጀዋር ባለፈው ለሕወሓት የጋበዘው እና ፌስ ቡኩ ላይ የለጠፈውን  የአማርኛ እስክስታ  ኢቲቪ ለምን ደበቀው? ኢቲቪ በሚለው ደረጃ ጀዋር በኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ውስጥ ያልተፈጠረ አስመስሎ ለማቅረብ የሚደረገው ሙከራ ውሸት መሆኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ ማወቅ አለበት።የኢትዮጵያ ሕዝብ በመተዳደርያ ማንፌስቶ ላይ ሕዝብን ጠላት ብሎ ከፈረጀ ድርጅት ጋርም 25 ዓመታት ኖሯል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ 
==========
ኢቲቪ ፕሮፌሰር ብርሃኑን በፕሮፓጋንዳው ላይ ደጋግሞ የሚያቀርበው ንግግር የወያኔ ንብረት ላይ ስለሚፈፀሙ ጥቃቶች ነው።ፕሮፌሰር ብርሃኑ የወያኔ ንብረት ጥቃት ላይ ተናገሩ እንጂ የትግራይ ንብረት አጥፉ አላሉም።የፕሮፌሰር ብርሃኑን ያህል ከትግራይ ሕብረተሰብ ጋር ተከባብሮ የሚኖር ሰው ለማምጣት መሞከር ሌላው የወያኔ ማጨናበርያ ነው። ይልቁንም ፕሮፌሰርን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደዛ በበረሃው ሰውነቱ ተጎሳቁለው ሲመለከት ግሎባል ሆቴል ትዝ ይለዋል።ይህ ሰው እንዲህ የጠቆረው ለእኔ አይደለምን?  የኢትዮጵያ ሕዝብ መበደል የአገሩ ጉዳይ ቢያሳዝነው አይደለምን? እኔስ ኃላፊነቴ ምንድነው? እንዲል አድርጎታል። ስለሆነም ኢቲቪ እዚህም ላይ አልተሳካለትም። 

ግብፅን በተመለከተ 
===============
ሰሞኑን ኢቲቪ ግብፅን አስመልክቶ የሚያስተላልፈው ፕሮግራም ኃላፊነት የጎደለው ነው።
የፕሮፓጋንዳው ጭብጥ አንድ የቴሌቭዥን ጣብያ ስለ ኦነግ አወራ ነው።ከእዚህ ጋር አስታኮ የአባይ ግድብ ይነሳል።እዚህ ላይ አንድ ማወቅ ያለብን ነገር ከኢትዮጵያ በስተቀር በሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ለቁጥር የሚያታክቱ የግል ቴሌቭዥን ጣቢያዎች አሉ።ባለፈው ሳምንት አንድ የኬንያ ተወላጅ ወጣት በሀገሩ ስንት የግል ቴሌቭዥን ጣቢያዎች እንዳሉ ስጠይቀው የመለሰልኝ በጣም ብዙ እንደሆነ እና  አላውቅም የሚል ነው።በእርግጥ በኬንያ ያሉት ቴሌቭዥን ጣብያዎች ከቁጥር በላይ ሆነው ሳይሆን ብዛት ያላቸው ቴሌቭዥን ጣብያዎች መኖር ለአፍሪካውያን ብርቅ አለመሆኑን ነው።

ግብፅን ደግሞ በእዚሁ መልክ ማየት ይቻላል።በእዚህ ፅሁፍ አቅራቢ መሰረት በግብፅ ውስጥ ከ120 በላይ የሳተላይት ተሌቭዥኖች መኖራቸውን ከድረ-ገፅ ላይ ተመልክቷል። ይህ ማለት አንድ ዩንቨርስትም የእራሱ ሳተላይት ቴሌቭዥን የመክፈት መብት ያላቸው የአፍሪካ ሀገሮች ውስጥ ያሉ ቴሌቭዥኖች በማናቸውም ጉዳዮች ላይ ተመልካች ለማግኘት ከመጣር አንፃር ፕሮግራሞች ያቀርባሉ። ኢቲቪ የወሰደው ከእነኝህ ቴሌቭዥኞች አንዱን መዞ ´´ኦነግን እየረዳን ነው፣ አባይ ቆመ መንገዱ ተዘጋ´´ ይለናል። 

ይህንን በምሳሌ እንየው ለአቅመ ነፃ ሚድያ አልደረሰም እንጂ እንበል እና ሚሚ ስብሃቱ ቅልጥ ያለ ኬንያን የሚሰድብ ፕሮግራም አቅርባ ስትሳደብ ብትውል እና የኬንያ ቴሌቭዥን የኢትዮጵያ መንግስት እንዲህ እያደረገ ነው ብሎ ሲናገር ይታያችሁ።ጤነኛ መንግስት በመጀመርያ የሚያደርገው በተቅራኒው ሀገር የመደበውን  ኢምባሲ ስለቴሌቭዥን ጣቢያው ምንነት ይጠይቃል።በመቀጠል ጉዳዩን ከሀገሩ አምባሳደር ማብራርያ ይጠይቃል።በግብፅ አንፃር ግብፅ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስራቤቷ በኩል ምላሽ ሰጥታለች።በሌላ አንፃር ግብፅ ስለግድቡ መከታተሏን የኢትዮጵያ ሕዝብ ባትነግሩትም ያውቀዋል።ይህ ምን ይደንቃል? ከእዚህ ይልቅ ግብፅ ሕወሓት በትጥቅ ትግል ላይ እያለ ምን ያህል እንደረዳች ቢነገረን ጥሩ ነበር።

ባጠቃላይ ኢቲቪ´´ውሸት ሲደጋገም እውነት ይባላል´´ በሚል የተሳሳተ እሳቤ ሕዝብን ያስፈራራልኛል ያለውን ፕሮግራም ያለውን እየመረጠ ሕዝቡን እያሸበረው ነው።የመልክቱ አጠቃላይ ይዘት ሲመዘን ´´ሕወሓት ስልጣን ላይ ካልቆየ ትጠፋላችሁ´´ የሚል ነው።ሕዝብ ደግሞ የሚለው ´´ውረዱ እና እንደማንጠፋ እናሳያችሁ´´ የሚል ሆኗል።ከእዚህ ሁሉ ይልቅ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሁሉንም ንግግር በጉጉት እየተከታተለ እና የበለጠ መረጃ እያገኘ ከመሆኑም በላይ በእየለቅሶ ቤቱ ሁሉ በኢቲቪ መቀለድ የተለመደ ሆኗል።በኢቲቪ ፕሮግራም እራሳቸውን በእራሳቸው እያስደሰቱ ያሉት የስርዓቱ አቀንቃኞች ብቻ ናቸው።ጀዋርም ሆነ ፕሮፌሰር ብርሃኑን ወደ እንዲህ አይነቱ የትግል መስመር ያስገባቸው የሕወሓት የ25 ዓመታት በደል እና ግፍ ነው።የኢትዮጵያ ህዝብም ጥያቄ የግለሰቦች ስብዕና አይደለም።አምባገነንነት እና ዘረኝነትን የሌለበት ሁሉም በሕግ የምተዳደርባት ኢትዮጵያን ማምጣት ነው።ይህ ደግሞ ከሕወሓት ጋር እንደማይሆን ካወቀው ቆይቷል።


ጉዳያችን GUDAYACHN

 www.gudayachn.com

Wednesday, October 12, 2016

ሰበር ዜና - የሩስያ እና የአሜሪካ ፍጥጫ ከፍተኛ ደረጃ ደርሷል

Photo = independent.co.uk 

ጉዳያችን/ Gudayachn
ጥቅምት 4/ 2009 ዓም 
=======================
የሩስያ እና የአሜሪካ ፍጥጫ ከፍተኛ ደረጃ ደርሷል።መገናኛ ብዙሃን ሶስተኛው የዓለም ጦርነት እና የሁለተኛው ቀዝቃዛ ጦርነት ጅማሮ ብለውታል። በሶርያ ጉዳይ ላይ መስማማት አለመቻላቸው እንደዋና የፍጥጫ መነሻ ይወሰድ እንጂ ጉዳዩ ሩስያ ወደ ምስራቅ የመስፋፋት ዝጋት እና የቻይና በምጣኔ ሀብት መለጠጥ የፈጠራቸው ስጋቶች ናቸው ።ላለፉት ወራት ሶስቱም አገሮች በከፍተኛ የሳይበር ጦርነት ላይ እንደነበሩ ተገልጧል።አሁን ጎንቶ የወጣው ፍጥጫ ግን የሩስያ እና የአሜሪካ ሲሆን የሚታየው ምክንያት የሶርያ ጉዳይ ሆኗል።

የፍጥጫውን ደረጃ ለመረዳት የሩስያው ፕሬዝዳንት ዛሬ ባለሥልጣኖቻቸውን ያዘዙትን ትዕዛዝ መመልከቱ በቂ ነው።በዛሬው እለት ፕሬዝዳንት ፑቲን ባለሥልጣኖቻቸው በውጭ ሀገር የሚገኙ ዘመዶቻቸውን ሁሉ ወደ ሀገር ቤት እንዲጠሩ ማዘዛቸውን ´´ዴይሊ ሜል´´ ´በድረ-ገፁ ገልጧል። ለእዚህ ደግሞ የተሰጠው ምክንያት ሩስያ ወደ ጦርነት የምትገባ መሆኑ ሲሆን ሩስያ በሌላ በኩል የኒኩለር አረሯን ወደ ፖላንድ ድንበር ማስጠጋቷ ተሰምቷል። (www.dailymail.co.uk Russia orders all officials to fly home any relatives living abroad, as tensions mount over the prospect of a global war

በጦርነቱ ወሬ ላይ የአሜሪካም ሆኑ የሩስያ መገናኛ ብዙሃን እያሟሟቁት ነው። ወደ ሀገራችን ጉዳይ እንምጣ እና በተባለው ፍጥነት ፍጥጫው ከመጣ በኢትዮጵያ ያለውን የኃይል አሰላለፍ ላይ ተፅኖ ይኖረዋል? የውጭ ፖሊሲዎች መቀያየር ይታይ ይሆን? ወይንስ እንደተለመደው የአንድ ሰሞን ወሬ ሆኖ ይቀራል።

ከእዚህ በታች ያለው አጭር ቪድዮ የውጥረቶቹ እድገቶች በያዝነው ዓመት ብቻ ያለውን ገፅታ ያሳያል።


ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Friday, October 7, 2016

ሕወሓትን በፍጥነት ከስልጣን ማስወገድ ማለት ኢትዮጵያን ከበለጠ የጎሳ ግጭት ማዳን ማለትነው

ጉዳያችን / Gudayachn
መስከረም 28/ 2009 ዓም
========================
በኢትዮጵያ የተነሳው ሕዝባዊ አመፅን ለማፈን ሕውሐት  ጎሳ ከጎሳ ማጋጨቱን ተያይዞታል።በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በማዕከላዊ፣ደቡባዊ እና ምዕራባዊ ክፍሎች የተነሱ የህዝብ አመፆችን ለማፈን በቀጥታ በሰራዊቱ ለመጨፍለቅ ከሚያደርገው ጥረት በተጨማሪ በነዋሪዎች መካከል የሚያደርገውን የእርስ በርስ ማጋጨት ቀጥሎበታል።ከእዚህ በፊት በ1997 ዓም ምርጫ ወቅት አድርጎት እንደነበረው ሁሉ በዛሬው እለት ብቻ  በአርሲ ነገሌ መቂ፣ በሲዳማ ይርጋ ጨፌ እና ዲላ ላይ እርስ በርስ ሕዝቡ እንዲመታታ እየተደረገ ነው።ቀደም ብሎም በአዲስ አበባ ዙርያ ቡራዩ እና ወለቲ  ተመሳሳይ ግጭቶች በሕወሓት ካድሬዎች መሪነት ለመፍጠር ሙከራ መደረጉን እና ሕዝብ በፍጥነት እንዳወቀው ተሰምቷል።

ከእዚህ በፊት በዐማራ ክልል ቅማንትን ከአማራ ጋር፣ ኦሮሞን ከሱማሌ እና ዐማራ ጋር  በደቡብ ደግሞ ጌድዎን ከሲዳማ፣አማራ እና ጉራጌ ጋር እያጋጨ መሆኑ ተሰምቷል።ከእዚህ በተጨማሪ ሆን ተብሎ በሕወሓት ወኪሎች እሳት መለኮሳቸው የተረጋገጡ የጎንደር ገበያ እና የኮንሶ መኖርያ ቤቶችን መጥቀስ ይቻላል።ይልቁንም ጎንደር ላይ ተጨማሪ እሳት ለማያያዝ የተላከች ሴት በአደባባይ መያዝዋ ይታወሳል።በቅርቡም በአዲስ አበባ ዙርያ እና ደብረዘይት የደረሱ የእሳት ቃጠሎዎች ውስጥ የስርዓቱ አገልጋዮች የሆኑ ግለሰቦች ድርጅቶች ከሆኑት ውጭ ያሉት ላይ አሁንም የሕወሓት እጅ ሊኖርበት ይችላል የሚሉ ብዙዎች ናቸው። 

በእየቦታው ሆን ተብሎ ለሚጫሩ የእርስ በርስ ግጭቶች ከመነሻው የጎሳ ፖለቲካ አውጆ ሕዝብ እያባላ የስልጣን ዘመኑን ለማርዘም የሚፈልገው ሕወሓት ከእዚህ በከፋ ደረጃም ማስፋፋቱ ስለማይቀር በቀጣይ ጊዜዎች የአካባቢ ሽማግሌዎች ሚና ቀላል አለመሆኑን መረዳት ያስፈልጋል።
ስለሆነም የአካባቢ ሽማግሌዎች የእራሳቸውን መንገድ እየተጠቀሙ ሕዝቡን ማረጋጋት ይጠበቅባቸዋል።ሕወሓት ስልጣኑን ሲለቅ የእዚህ አይነት ግጭቶች ፈፅሞ አይኖሩም ምክንያቶቹም ሶስት ናቸው። እነርሱም - 

አንድ፣ የግጭቱ ጠንሳሽ እና አንዱን ´አጋር´ ሌላውን ´ጠላት´ እያለ የሚያበላልጠው ሕወሓት ስለሆነ። ሁለተኛ፣ከሕወሓት ውድቀት በኃላ የመገናኛ ብዙሃን  ስለማይታፈኑ የግጭት ችግር ያለባቸውን ቦታዎች ሁሉም ሕዝብ እንዲሰማ ስለሚደረግ እና ምክር በመገናኛ ብዙሃን ስለሚሰጥ እንዲሁም የወቅቱ መንግስት ማስጠንቀቅያ ግጭት በሚፈጥሩት ላይ እንዲደርስ ስለሚደረግ ሕግ በቀላሉ ማስከበር ስለሚቻል እና በሶስተኛ ደረጃ፣  የሕበረትሰቡ የጋራ እሴቶች እና አደረጃጀቶች እንዲሁም የሃይማኖት አካላት በነፃነት ሕዝቡን ለመምከርም ሆነ ለመገሰፅ ስለሚችሉ።ይህንን እንዲያደርጉም በነፃ ሚድያ ዕድል ስለሚያገኙ ሕዝብ አብሮ የመኖር እድሉ ትልቅ ነው። አሁን እነኝህ የሃይማኖት አካላት ሲናገሩ የአንዱ ወገን ደጋፊ ስለሚባሉ እና በሙሉ ልብ ለመናገር ስለማይችሉ ተገቢውን ሚና እየተጫወቱ እንዳልሆኑ ይታወቃል።ይህንን ሆን ብሎ ያደረገው ገዢው ስርዓት ሕዝብ ከፋፍሎ ለመግዛት ብሎ መሆኑ ይታወቃል።

ባጠቃላይ ሕወሓት ለስልጣን ማቆያ ´ነዳጅ´ ብሎ የሚያስበው የኢትዮጵያ ሕዝብ እርስ በርስ መከፋፈል ነው።ከመነሻውም ሕወሓት ኢትዮጵያን በክልል ሲከፋፍል ትክክለኛ ፈድራሊዝም ለማስፈን እንዳልሆነ ያለፉት 25 ዓመታት ምስክር ናቸው። ሕወሓት የብሔር ብሔረሰቦች መብት ሲል የነበረው ሁሉ ቀልድ እንደነበር እና የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች በታሪካቸው አይተውት ወደማያውቁት ግጭት የከተታቸው አሁንም ሕወሓት መሆኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ ምስክር ነው።ህዝብን ከህዝብ የማጋጨቱ ሥራ ሕወሓት በምን ያህል  ደረጃ ይሳካለታል? የሚለው ጥያቄ እንዳለ ሆኖ በአሁኑ ወቅት ግን ይህ ከፋፋይ ስርዓት ኢትዮጵያን በጎሳ ግጭት እያነደዳት ነው። ስለሆነም ሕወሓትን በፍጥነት ከስልጣን ማስወገድ ማለት ኢትዮጵያን ከበለጠ የጎሳ ግጭት  ማዳን  ማለትነው።




ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከሁሉም ለዲሞክራሲ ስርዓት የቆሙ የፖለቲካ ኃይሎች፣ሲቪክ ማኅበራት እና የህዝባዊ እምቢተኝነት ተሳታፊዎች ያሳተፈ የሽግግር ሰነድ እየተዘጋጀ መሆኑን ገለፁ (ቪድዮ)


ጉዳያችን GUDAYACHN 
መስከረም 27/ 2009 ዓም 
================================
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር በተወለዱባት ቢሾፍቱ (ደብረ ዘይት) በእሬቻ በዓል ፣በጎንደር፣ጎጃም፣ኮንሶ እና ሌሎችም ቦታዎች የደረሰው እልቂት  እንዳሳዘናቸው ከገለፁ በኃላ የሚከተሉት 5 ተግባራት እየተከናወኑ እና ትኩረት የሚሹ መሆናቸውን ገልፀዋል።በንግግራቸው ማጠቃለያ ላይ ያነሷቸው አምስት ነጥቦች በአጭሩ:- 

1/ ድርጅታቸው ዝግጅቱን በቅርቡ አጠናቆ ሊደበቅ በማይችል መልኩ ስራው እንደሚታይ፣

2/ የሕዝባዊ እምብተኝነቱ አንቀሳቃሾች በስርዓቱ የኢኮኖሚ አቅም ላይ ማተኮር እና እምብተኝነቱ በሁሉም አካባቢዎች በተመሳሳይ ጊዜ ማድረግ ወያኔ የህዝቡን አቅም እንዳይከፋፍል ያደርጋል፣

3/ የስርዓቱ ወታደሮች፣ፖሊሶች፣በሕወሓት አጋር ድርጅቶች ውስጥ ያሉ ሁሉ ስርዓቱን ከድተው ሲመጡ በሚገባ መቀበል እና ማበረታት ይገባል፣

4/ ስርዓቱ ሕዝብ ከህዝብ ለማጋጨት የሚሰራው ሥራ በመኖሩ በእነርሱ ወጥመድ ውስጥ እንዳንገባ እና ኢላማችን ሕዝብ ሳይሆን ጥቂት የስርዓቱ አቀንቃኞች ላይ መሆኑን ለይቶ ማወቅ እና ዓላማችንም ይህ ብቻ መሆኑን ወያኔን በገንዘብ ለሚደግፉም ጭምር ማስመስከር አለብን እና 

5/ ከወያኔ በኃላ የሚመጣው ስርዓት እውነተኛ ስርዓት መሆኑን ለማሳየት እና ኢትዮጵያ ፎቅ እና ፋብሪካ  በመገንባት ብቻ ሳይሆን በአስተሳሰብ እና በመንፈስ  እየተሸጋገረች መሆኗን  ለማሳየት  እና የሚመጣው ስርዓት እውነተኛ ዲሞክራስያዊ መንግስት መሆኑን ለማሳየት በሁሉም ለዲሞክራሲ ስርዓት የቆሙ ሁሉም የፖለቲካ  ኃይሎች፣ሲቪክ ማኅበራት እና የህዝባዊ እምቢተኝነት ተሳታፊዎች ሁሉ የሚጋሩት የጋራ የሽግግር ሰነድ ማዘጋጀት እና በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ማሰራጨት እና የጋራ አስተሳሰብ እንዲይዙ ማድረግ  ይገባል።ለእዚህም ይህንንም ከአጋር የፖለቲካ  ድርጅቶች ጋር በጋራ እየሰራን ስለሆነ በቅርቡ እውን ይሆናል።




ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Thursday, October 6, 2016

የትግራይ ሕዝብ ሕወሓት በግብፅ ሊያስመታህ መሆኑን ዕወቅ! እንዴት? (የጉዳያችን ማስታወሻ)






ጉዳያችን / Gudayachn
www. gudayachn.com 
መስከረም 27/ 2009 ዓም 
==============================

ሰሞኑን ኢቲቪ ግብፅ ተቃዋሚዎችን እየረዳች ነው የሚል ዜና የግብፅ ቴሌቭዥን ያቀረበውን ዘገባ በመጥቀስ አሳይቷል።
በመጀመርያ ደረጃ ግብፅ ይህንን የማታደርግ ቢሆን ነው የሚገርመው።ግብፅ ምን እንደምታደርግ ደራሲ እና ጋዜጠኛ ማሞ ውድነህ በትርጉም መፅሃፎቻቸው ሲነግሩን ነው ያደግነው።´´የካይሮ ጆሮ ጠቢ´´ ላይ በጀርመን ዜግነት ግብፅ ገብተው ከላይ እስከ ታች የበረበሯት እነ ዎልፍጋንግ ሎትዝ ታሪክ ትዝ ይለናል።አሁን ቁም ነገሩ ግብፅ ግድብ አትፈልግም፣ተቃዋሚ እረዳች አይደለም።ይህንን ባታደርግ በገረመን።

ዋናው ነጥብ የችግሩ መነሻ እና የችግሩ ውጤት መለየት ላይ ነው።ኢትዮጵያ ውስጥ ላለው የህዝብ መነሳሳት መነሻ ግብፅ ሳትሆን ሕወሓት ነው።ስልጣን አልለቅም ያለው እና ለሕዝብ ታማኝ ያልሆነው ሕወሓት ነው።የሕወሓት መነሻ ችግር ሲመነዘር ውጤቱ ግብፅ ተቃዋሚ እንድትረዳ አደረጋት። እኛ ቤታችን እንድናስተካክል ሕወሓት እንቅፋት ባይሆን ኖሮ ግብፅ ባልረዳች።በሌለ እሳት ላይ እሳት መጫር አትችልም ነበር።

ሕወሓት እያደረገ ያለው ሁሉ ግብፅን ወዴት ይመራል? የሚለው ላይ ጥቂት ላንሳ።ግብፅ ግድብም እንበለው ሌላ አሁን ስልጣን ላይ ያለው መንግስት እንዲወርድ ትፈልጋለች እንበል።በእዚህም ሳብያ ጦርነት ብትከፍት ማን የበለጠ ዕድል አለው? ግብፅ የጋራ ድንበር አትጋራንም።ይህ ማለት በጦርነት ከኢትዮጵያ ይልቅ የተሻለ ዕድል የሚሰጣት ለግብፅ ነው ማለት ነው።

ለምን? 

ኢትዮጵያ ከግብፅ ጋር በጋራ ድንበር እስካልተጋራች ድረስ ጦርነቱ ሲጀመር (መሸጋገርያ መሬት ካልተገኘ በቀር) በአየር እና በሚሳኤል መደብደብ አማራጭ እና በአጭር ጊዜ ጦርነቱን ለመፈፀም ይረዳታል። በአየር ኃይል አቅምም ሆነ በአጭር ርቀት ሚሳኤል ውግያ ግብፅ ከኢትዮጵያ የተሻለ አቅም እንዳላት እገምታለሁ። ግብፅ የተቃዋሚ ኃይል በሚገባ ካልገፋ ግብፅ በአየር ወይንም በሚሳኤል ጥቃት ልትፈፅም ትችላለች።ጥያቄው የት ላይ ጥቃት ልትፈፅም ትችላለች? የሚለው ነው። እንደሚመስለኝ ሁለት የተመረጡ ኢላማዎች ትመርጣለች።

1/ የታወቀው ግድቡ የሚገኝበት ቦታ 

ግድቡ የሚገኝበትን ቦታ  በመምታት የምታገኘው ጥቅም እና ጉዳትስ ምንድነው?  

 1/  ግድቡን ከመታች  የምትጎዳው 

    ሀ/  የግድብ ስራው ላይ በድርድር የተያዘ ጉዳይ ካልሆነ  በመጪ መንግስትም ቢሆን የተራዘመ እና አጨቃጫቂ የካሳ ጥያቄ ማስነሳቱ  አይቀርም እና ለዘለቄታ የውሃ መፍትሄ አይሆንም።ይልቁንም ለትውልድ የሚቆይ ሌላ ውስብስብ ጉዳይ ታቆያለች።ውሃ የአንድ ትውልድ ጥያቄ ሳይሆን የመጪውም ትውልድ ነው።የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትርን የሚያማክር ሰው ይህንን አማራጭ ብሎ ላይወስደው ይችላል።ሆኖም ለጊዜው ለራስ ምታት የሚሆን መፍትሄ ሰጪ (እንደ ፓናዶል) ከሆነ ግን መፍትሄ ሊለው ይችላል።

   ለ/ ከአፍሪካ ሀገሮች እና ከአፍሪካ ህብረት በኩል በአረብ ሀገሮች የመጠቃት ትልቅ ስሜት ይፈጥራል።የግብፅ መዋለ ንዋይ በጥቁር አፍሪካ ሀገሮች  ውስጥ ግንኙነቱ ይበላሻል።የዩጋንዳው መሪ ለእዚህ ምሳሌ ናቸው።በግንባር ቀደምትነት ግብፅ ትዕቢት እንዳይዛት በአደባባይ ተናግረዋል።ብዙ አፍሪካ ሀገሮችም ከመካከለኛ ምስራቅ በኩል የሚመጣ የወታደራዊ ጡንቻ ማፈርጠምያ ልምምድ አድርገው ስለሚያዩት ከኢትዮጵያ ጋር መቆማቸው አያጠራጥርም (ጥሩ መንግስት ስናገኝ በተለይ በቀላሉ ማስተባበር ይቻላል)። ይህም ግብፅ በተቻለ መጠን ከአፍሪካ ጋር ያላት ግንኙነትን ማቆም አትፈልግም።

2/ ግድቡን ከመታች የምትጠቀመው 

ግብፅ ግድቡን ከመታች የምትጠቀመው አንድ ነገር ነው።ይሄውም አሁን ስልጣን ላይ ያለው መንግስት በሀገሩ የግብፅን ሕዝብ ጉራ ያተርፋል፣ህዝቡ ያፏጭለታል፣ግብፅን ከውሃ ስጋት ያዳነ አንበሳው መንግስት ይባላል።እግረ መንገዱን በአካባቢው ተፅኖ ፈጣሪ ግልገል ኃያል መሆኑን ያሳይበታል።ይህ ግን ጊዜያዊ ጥቅም ነው።

ስለዚህ ግብፆች ሊያደርጉ የሚችሉት አስጊው ጉዳይ ምንድነው?

ግብፅ የኢትዮጵያን የውስጥ ፖለቲካ መከታተሏ የማይጠረጠር ነው።ስለሆነም አሁን ያለውን ሕወሓት በኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል የፈጠረው ልዩነት ያውቁታል።ይህንን ኢቲቪም አምኗል።ስለሆነም ወደ ኢትዮጵያ የሚወረውሩት እያንዳንዱ በአየር ኃይል የተጫነ ጥይትም ሆነ ሚሳኤል ሁለት ነገሮችን ማሟላት አለበት።

አንድ፣የኢትዮጵያ ህዝብን ሆ! ብሎ ሉዓላውነቴ ተደፈረ ብሎ እንዲነሳ የማያደርግ እና ውስጣዊ ህብረት የማይፈጥር። 

ሁለት፣ ለዘለቄታ ማለትም ከመጪው መንግስት ጋር የማያቃቅር መሆን አለበት።ለእዚህ ደግሞ ቢያንስ የሁለቱን ትልልቅ ብሔሮች ማለትም የዐማራ እና ኦሮሞ ብሔሮችን የማይነካ ያሉትን (ነው አላልኩም ግብፆች የሚገምቱትን)  የሕውሓት መንግስት ላይ ብቻ ያነጣጠረ ጥቃት  ማለትም በትግራይ የሚገኙ ፋብሪካዎችን፣የአየር ኃይል ጣብያ፣መቀሌ እና ሌሎች ቦታዎች ያሉ ግንባታዎችን ላይ ሁሉ ጥቃት ሊፈፅሙ ይቻላሉ። በእዚህ ደግሞ ሁለት ጥቅሞች የሚያገኙ ይመስላቸዋል። እነርሱም : - 

  1/ በሕወሓት የተበደለው ሕዝብ ኢትዮጵያ ተጠቃች የሚል ስሜት ሳይሆን ይልቁንም ሕወሓት ተጠቃ በሚል ስሜት በግብፅ ይደሰታል ብለው ያስባሉ።ለባድማ ደሙን የገበረውን ሕዝብ ሕወሓት ስላስከፋው እና ስለገደለው አሁን እንደ እዚህ በፊቱ አይነሳም የሚል እሳቤ ይይዛሉ። 

2/ ለመጪው መንግስት መቀጣጫ ይሆናል።የውሃ ጉዳይ መንግስት እንደሚያስቀይር ትምህርት ይሆናል ብለው ያስባሉ። 

ስለሆነም ሕወሓት የግብፅ ጉዳይ ሲያነሳ ግብፅ ተቃዋሚን መርዳት የመጀመርያ ሥራ እንጂ በቀጣይ ጥቃት ሊኖር ቢችል  ጥቃቱ አሁን ስልጣን ላይ ያለው መንግስት የተሰበሰበ ኃይል አለ ብላ ግብፅ በምታስበው ላይ ነው የምታደርገው።ለእዚህም ኤርትራ ከምታደርገው ግብፅ ብታደርገው የተመረጠ እንደሆነ የሚመክሩ የጎረቤት ሀገሮች አይጠፉም።

ስለሆነም የትግራይ ሕዝብ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል ጋር ትግሉን አስተባብሮ ሕወሓትን ማስወገድ እና ኢትዮጵያን አብሮ መገንባት ብቸኛ አማራጩ ነው።ይህ ካልሆነ ግን ትግራይ እራሷን እንድትነጥል እያደረገ በግብፅ የሚያስመታት የትግራይ ወዳጅ መስሎ የሚያስጠፋት እራሱ ሕወሓት እንደሆነ ማወቅ ተገቢ ነው።


ጉዳያችን GUDAYACHN

 www.gudayachn.com

Wednesday, October 5, 2016

የኢትዮጵያ ወቅታዊ ፖለቲካ በተመለተ: እየሆነ ያለው፣የፖለቲካ ኃይሎች አሰላለፍ፣የውጭ ኃይሎች አጀንዳ እና ለነገዋ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ያድርጉ? (የጉዳያችን ማስታወሻ)


ኢትዮጵያ ውስጥ የለውጥ እንቅስቃሴው እያየለ ነው።ይህ ለቀባሪው ማርዳት ነው። 
ስለሆነም ከእዚህ በታች ያሉት ወቅታዊ የሀገራችን ጥያቄዎች ላይ ያለኝን ምልከታ ለማስፈር እሞክራለሁ።የኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ አስመልክቶ በብዙዎቻችን ውስጥ የሚንገዋለሉ ጥያቄዎች ብዬ ከምገምታቸው ውስጥ:- ምን እየሆነ ነው? የወቅቱ የፖለቲካ ኃይሎች አሰላለፍ ምን ይመስላል? የውጭ ኃይሎች አጀንዳ ምን መልክ አለው? የነገዋ ኢትዮጵያን ለመገንባት የፖለቲካ ፓርቲዎች  ምን ያድርጉ?  የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

  ምን እየሆነ ነው?


ኢትዮጵያ ውስጥ እየሆነ ያለው ግልፅ ነው።ለ25 ዓመታት ያህል ኢትዮጵያን በመጀመርያ በሽግግር መንግስት ስም ፣ ቀጥሎ በአብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ስም፣በማስከተል በልማታዊ መንግስት ለወደፊቱ ደግሞ ´´በስር ነቀል ታዳሽነት´´ ስም ኢትዮጵያን የገዛው እና ለመግዛት የሚመኘው የሕወሓት መንግስት በሁሉም መስፈርት በሕዝብ ሞራላዊም ሆነ ሕጋዊ መሰረቱን በማጣቱ ከስልጣን እንዲወርድ በሚፈልግ በብዙሃኑ ህዝብ በአንድ በኩል በሌላ በኩል ደግሞ  በሕወሓት እና የጥቅም ተጋሪዎቹ በአንድነት ሆነው የተሰለፉበት የነፃነት ትግል ነው።አሁን እየሆነ ያለው ባጭሩ ይህ ትግል ከሰላማዊ ወደ ትጥቅ እና የመረረ ትግል መሸጋገሩ  ነው አዲሱ ክስተት።

የወቅቱ የፖለቲካ ኃይሎች አሰላለፍ ምን ይመስላል?


በዓላማ እና ግብ አንፃር ስንመለከተው የፖለቲካ ኃይሎቹ እራሱ ሕወሓትን ትተን ተቃዋሚዎች በግልፅ በፖለቲካ ኃይልነትም ሆነ እራሳቸውን በተለያየ አደረጃጀት ያደራጁ፣ ግን ምን ያህል የሀገር ቤት መሰረታቸው የጠለቀ መሆኑ ያልለዩ ኃይሎች አሉ።ይህ ማለት ስርዓቱ አፋኝ እንደመሆኑ መጠን የፖለቲካ ኃይሎችም በተቻለ መጠን ሚስጥራዊ ባህሪ እንዲይዙ ማድረጉ ይታመናል።ሁሉም ተቃዋሚ ኃይሎች ግን  በአንድ ጉዳይ ላይ ተመሳሳይ ዓላማ አላቸው።ይሄውም ሕወሓትን ከስልጣን  በማውረድ ላይ ነው።

ቀደም ብሎ የነበረው የፖለቲካ ኃይሎች አሰላለፍ በሁለት የሚከፈል ነበር።ይሄውም የአንድነት ኃይል እና የብሔር ፖለቲካ ኃይሎች የሚሉ ነበሩ።የአንድነት ኃይሉ ፍፁም አሃዳዊ የመንግስት ስርዓት ሳይሆን የፌድራል መንግስትነትን የሚቀበል ነገር ግን የብሔር አደረጃጀትን አደገኛ ብሎ የሚጠራ ነው።የብሔር ፖለቲካ አራማጆች የእራስን ሀገር እስከመመሥረት የሚሄድ አጀንዳ አስቀምጠው የሚሄዱ ናቸው። ከእዚህ አይነቱ አሰላለፍ ለየት ያለ ብሔርን መነሻ ያደረገ ነገር ግን የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ሳይቀይር ´´ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!´´ በሚል መፈክር ብቅ ያለው የቅርቡ እንቅስቃሴ ደግሞ ´´የዐማራ ተጋድሎ´´ የተሰኘው ነው።ይህ እንቅስቃሴ ትኩረቱ አንድ ብሔር ላይ ሆኖ ግን የነፃነት ጥያቄን ያላነሳ ኢትዮጵያዊነት ውስጥ ያለ የፖለቲካ፣ምጣኔ ሀብት እና ማኅበራዊ መሰረቱ ያልታሰረ የዐማራ ብሔረሰብ ተሳትፎ እንደሚታገል እንቅስቃሴው በተለያዩ መግለጫዎች ገልጧል። 

እዚህ ላይ የአንድነት እና ኢትዮጵያዊነት መነሻ ያደርጉ የፖለቲካ ኃይሎች ለምሳሌ ´´የአርበኞች ግንቦት ሰባት´´ የመሳሰሉ ግልፅ ግብ እና የፖለቲካ ፕሮግራም ሲኖራቸው ብሔርን መሰረት አድርገው የሚንቀሳቀሱት እንቅስቃሴዎች ለምሳሌ የኦሮሞ ተቃውሞ (Oromo protest) እና የአማራ ተጋድሎ በፖለቲካ ፓርቲነት ያልወጡ ግን ተፅኖ የመፍጠር ኃይላቸውን እያጎለበቱ የመጡ ናቸው።

በተለይ የኦሮሞ ተቃውሞ እስከ እዚህ ሳምንት መጀመርያ ድረስ እንቅስቃሴው ወዴት እንደሚሄድ እና ግቡ ምን እንደሆነ አልታወቀም ነበር። በእዚህ ሳምንት መስከረም 23፣2009 ዓም ላይ አቶ ጀዋር  መሐመድ ከኦሮሞ አክትቪስቶች አንዱ ሚኒሶታ ላይ በተደረገ አንድ ስብሰባ ላይ እንደገለፀው  የኦሮሞ ተቃዋሚዎች ´´የኦሮምያ ነፃነት  ሽግግር ቻርተር´´ ለማዘጋጀት እየሰሩ መሆኑን እና የወታደራዊ ክንፍ እንደሚኖረው ገልጧል።እዚህ ላይ ´´የኦሮምያ ነፃነት  ሽግግር ቻርተር´ የሚለው አገላለፅ በበርካታ በኢትዮጵያውያን የኦሮሞ ተወላጆች እና ቀሪው ኢትዮጵያውያን ዘንድ አነጋጋሪ ሁኔታ ፈጥሯል። የፀረ ሕወሓት ትግሉ በሁሉም ኢትዮጵያውያን እየተደረገ እና ለጋራ ሽግግር  የሁሉንም ኃይሎች መሰባሰብ ሕዝብ እየጠበቀ ባለበት በእዚህ ወቅት ´´ኦሮምያ ለብቻዋ የምትሸጋገርበትን ቻርተር ታፀድቃለች´´  የሚለው የጀዋር ንግግር  በርካታ ጥያቄዎች በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሂደት ላይ እንዲፈጥር  ሆኗል። 

ጉዳዩ በተለይ የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች ዝምታ ለበለጠ ጉዳት እንዳይዳርግ የብዙዎች ስጋት ነው።በተለይ  ከእዚህ በፊት በኦሮሞ የመብት ትግል ውስጥ ከወያኔ ውድቀት በኃላ በኢትዮጵያ ውስጥ ችግሮችን  መፍታት ይቻላል የሚል ፅኑ እምነት ያላቸው የኦሮሞ ተወላጆች በርካታ ጥያቄዎች እንዲያነሱ ሆኗል።ከእነኝህ ጥያቄዎች ውስጥ በእኛ ላይ የነፃነት  ወይንም ከኢትዮጵያ የመለየት ቻርተር ማን ነው የሚያፀድቀው? እንቅስቃሴው ባብዛኛው በሙስሊም  ፅንፍ በያዙ አካሎች ነው የሚመራው የሚባለው ሐሰት አይደለም ማለት ነው?  ኦሮምያ ብቻዋን ከሌላው ኢትዮጵያ ተነጥላ  ትሸጋገራለች ማለት ምን ማለት ነው? በእዚህ ሂደት ውስጥ ከኦሮምያ ተወላጆች በተለየ የእምነት ልዩነት ሁለንተናዊ የአቅም ድጋፍ የሚደረግላቸው እና ኦሮምያን ከሌላው ኢትዮጵያ የመነጠል ዋና ግብ ይዘው የሚንቀሳቀሱ አሉ ወይ? የሚሉ በርካታ ጥያቄዎች አስነስቷል። የኦሮምያ የሽግግር ቻርተር በተመለከተ ጃዋር የተናገረውን ለማንበብ ይህንን ይጫኑ።(የኦሮሞ ተቃውሞ መሪዎች የኦሮሚያ ነፃነት ቻርተርና የሽግግር መንግስት ዝግጅት እያደረጉ ነው)።


ባጠቃላይ የፖለቲካ ኃይሎችን አሰላለፍ በእዚህ አጭር ፅሁፍ ብዙ ማለት ባይቻልም የኃይል ሚዛን ለማስተካከል እና አንዱ ከአንዱ ልቆ በመታየት ነገ ሌላ የአምባገነን ስርዓት እንዳናስተናግድ ካሁኑ መታረም የሚገባቸው ጉዳዮች በወቅቱ መታረም አለባቸው።ይህንን ለማድረግም የፖለቲካ ኃይሎች ከአሁኑ መጠናከር እና ሕዝባዊ መሰረታቸውን ማጠንከር ይጠበቅባቸዋል።የኢትዮጵያ ህዝብም ትግሉን ሲያከሂድ መገንዘብ ያለበት ነገ እንደ ሕዝብ የማያኖሩ ፅንፍ አካሄዶች የያዙ በተለይ የኢትዮጵያን መሰረት ከባዕዳን ጋር  በመሻረከ ለማጥፋት የሚፈልጉትን ሕዝባዊ መሰረት እንዳይኖራቸው ከአሁኑ ነቅቶ መጠበቅ አለበት። በኦሮሞ ፖለቲካ ውስጥም ከዳር የተቀመጡ ምሁራን እና ዜጎች የኦሮሞ ፖለቲካ የጥቂቶች ፖለቲካ እንዳይሆን በስፋት ገብቶ ወይንም የመሰላቸውን የፖለቲካ አስተሳሰብ ማራመድ እና የኢትዮጵያ አንዱ እና ትልቁ መሰረት የሆነው የኦሮሞ ሕዝብ ባልሆነ የመለያየት ፖለቲካ ትግሉ እንዳይታገት ሊታደጉት የግድ ይላል።

የውጭ ኃይሎች  አጀንዳ ምን ሊሆን ይችላል? 


የውጭ ኃይሎች አጀንዳ ብዙም አሻሚ አይደለም።የውጭ ኃይሎችን አካባቢያዊ ጥቅም (Regional Strategic Interest) ያላቸው እና የእሩቅ ፍላጎት ( Geo-political interest) ያላቸው ብለን በሁለት መክፈል እንችላለን። የአካባቢ ውስጥ ሳውዲ አረብያ እና ግብፅ ሲሆኑ በሩቁ ውስጥ ልዕለ ኃያሏ አሜሪካንን መጥቀስ ይቻላል። የሁለቱም ኃይሎች ፍላጎት የተለያየ ቢሆንም በአንድ ነገር ላይ ግን ይስማማሉ።እርሱም  በመጪው መንግስት ላይ ተፅኖ ፈጣሪ መሆን እና የእየራሳቸውን አጀንዳ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እንዲያስፈፅምላቸው መጣር  የሚሉት ናቸው። ይህ አሁን ሕወሓትን ከማስወገድ ትልቁ አጀንዳ ጋር መጋጨት የለበትም።ምክንያቱም በሕወሓት ዘመን የምትኖር የተከፋፈለች ኢትዮጵያ  የበለጠ ለውጭ ኃይሎች የተጋለጠች ነች እንጂ የፖለቲካ ችግሯን የፈታች አገር  አደጋ ላይ ትሆናለች ብሎ ማሰብ አይቻልም። ስለሆነም ሕወሓትን ከስልጣኑ አንስቶ በህዝባዊ መንግስት መተካት ቅድምያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው።

ባጭሩ የውጭ ኃይሎች አጀንዳ የተበታተነች ኢትዮጵያን ከመናፈቅ አንስቶ እስከ አንድነቷ የተጠበቀ እና አካባቢ ተፅኖ የመፍጠር ያላት ግን ከባእዳኑ ጥቅም ጋር ያልተጋጨች ኢትዮጵያን ለማየት እንስከመፈለግ ድረስ ያለመ ሂደት መኖሩን ማወቅ አለብን።

የነገዋ ኢትዮጵያን ለመገንባት ዛሬ ምን መደረግ አለበት?

 

አሁን በተጨባጭ የሚታየው የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሂደት እየመራ ያለው ሀገር ቤት የሚገኘው ወጣቱ ትውልድ ነው።በፀረ ሕወሓት ትግሉም በግንባር ቀደምትነት እየተሳተፈ ያለው አሁንም ወጣቱ ነው።ይህ ወጣት እራሱን ከሕወሓት ታንክ ጋር በባዶ እጁ ሲፋለም አንድ የሚያልመው እና የሚናፍቃት ኢትዮጵያ እንዳለች ለማወቅ ነቢይ መሆን አይጠይቅም።አንድ ነገር ግን እርግጠኛ መሆን ይቻላል የወያኔ አይነት ግልባጭ የጎሳ ፖለቲካን አይናፍቅም።ይህ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ደሙን የወያኔን ዘረኛ ስርዓት ለማውረድ ባልተፋለመ ነበር። ስለሆነም መጪዎቹ የፖለቲካ ኃይሎች አዲስ ነገር ይዘው የማይመጡ ከሆነ እንደ ወያኔ በሕዝብ ታንቅረው እንደሚጠሉ ማወቅ ቀላል ነው። ስለሆነም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች አሁን ላይ መስራት የሚገባቸው የቤት ስራዎች ውስጥ: -

1/ ከአክትቪስት ሥራ ወጥተው የመሪነት ተግባራቸውን መስራት፣

2/ የፖለቲካ መድረኩን ብቃት ያላቸው እና የሚያጋጥሙ ችግሮችን ወደ መልካም ዕድል የመቀየር አቅም ያላቸውን መሪዎችን ወደፊት ማምጣት፣

3/ የፖለቲካ ለውጥ ዋዜማ ላይ እንደመሆናችን መጠን ለእያንዳንዱ የፖለቲካ ክስተት በቶሎ በቂ ምክንያቱን እና ግልፅ ዕይታን ለሕዝብ መግለፅ።በተለይ የእዚህ አይነቱ ተግባር ሕዝብ በአንድ የፖለቲካ ጉዳይ ክስተት ላይ የተለያየ አስተሳሰብ እንዳይይዝ ክስተቱን የሚመለከትበትን ዕይታ ቅርፅ እንዲይዝ ያደርጋል።ስለሆነም ህዝብን በህብረት እና የዓላማ ግብ ዙርያ የበለጠ  ያስተሳስራል፣

4/ ለኢትዮጵያ አንድነትም ሆነ ለሕዝቡ ሰላም አስጊ የሆኑ ኃይሎች ሕዝብ እንዳያታልሉ ትግሉን በማይጎዳ መልኩ  ለሕዝብ መረጃ እንዲደርስ ማድረግ እና ሕዝብ የእራሱን ግንዛቤ እንዲወስድ ማብቃት፣

5/ የመገናኛ ብዙሃንን አቅም በበለጠ ማሳደግ፣ማግነን እና ተአማኒነቱን ማፅናት፣ 

6/ ሕዝብ ለአገሩ የመረጃ ምንጭ እንዲሆን እና ወደ ዲሞክራሲያዊ፣ፍትህ እና እውነተኛ የተባበረች ፌድራላዊት  ኢትዮጵያን እንዲያልም እና ወደዛ የሚወስዱ መንገዶች እና ስልቶችን ከወዲሁ እንዲያውቅ ማድረግ እና  ለአፈፃፀሙም ብቃት ያለው እንዲሆን ማዘጋጀት እና 

7/ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ከኢትዮጵያ ጋር እንዲቆም ለማድረግ አማራጭ ኃይል ሆኖ መገኘት የሚሉት ናቸው። 

በእርግጥ ከላይ የተጠቀሱት በእራሳቸው ሰፊ ማብራርያ ይፈልጋሉ።ሆኖም ግን በእራሳቸውም ደግሞ ሃሳቡን ይገልፃሉ።በእዚህ ፅሁፍ ላይ የሕዝብ ሚና ላይ ያልተጠኮረው ሕዝብ የእራሱን ድርሻ እየተወጣ ስለሚገኝ መሆኑ ከግንዛቤ ውስጥ ይግባ።

ባጠቃላይ ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ ወሳኝ ወቅት ነው።የፖለቲካ መፍትሄውም ከሕወሓት በኩል ፈፅሞ ስለጨለመ ስርዓቱ ይህን ቢያደርግ ይህንን ባያደርግ የሚል ሃሳብ እዚህ ላይ ማካተት አስፈላጊ ሆኖ አልታየኝም። ምክንያቱም ቢያንስ ላለፉት አምስት ዓመታት ይህ ቢደረግ ይህ ባይደረግ ሲባል ተከርሟል። አሁን ወሳኙ ሕዝብ ሆኖ ወጥቷል።የኢትዮጵያ የዛሬውም ሆነ የወደፊቱ  ተስፋዋ እግዚአብሔር እና ሕዝብ ናቸው።ሁለቱም ግን በጥንቃቄ መያዝ ይፈልጋሉ። እግዚአብሔርም ተገቢውን አምልኮ፣ሕዝብም ብቃት ያለው የፖለቲካ አመራር።



ጉዳያችን GUDAYACHN 
  www.gudayachn.com

Sunday, October 2, 2016

ዛሬ በኦሮሞ ወንድሞቻችን ላይ የፈፀማችሁት ያቀዳችሁትን ነው።ትንሽነት ስለሚሰማችሁ የተከበሩ የአገሪቱን ዜጎች ትገላላችሁ።

ዛሬ መስከረም 22፣2009 ዓም በቢሸፍቱ (ደብረዘይት) በነበረው የእሬቻ በዓል ላይ የአጋዚ ወታደር  ምድሪቱን በኢትዮጵያዊው ኦሮሞ ደም አጨቀዩት።ከምድር በመትረጌስ ከሰማይ በኤሊኮፍተር ተኮሱበት።
በእዚህ የመፈራትን ካባ እንቀዳጃለን ብላችሁ ካሰባችሁ እንደልማዳችሁ ተሳሳታችሁ።የበለጠ ለመሞት የቆረጠ፣የበለጠ ወያኔን ከማጥፋት ሌላ አንዳች የቀረ እንጥፍጣፊ ተስፋ እንደሌለ ደግማችሁ አረጋገጣችሁ።ከሁሉም ከሁሉም በእስረኛው መገናኛ ብዙሃናችሁ የተናገራችሁት ልብ ያቆስላል።

ኢትዮጵያ የኦሮሞው አገሩ ነች።ሌላ አገር አያውቅም።
በቄጤማው ውሃውን ቢመታ፣እንደ አባቶቹ ባህል የፈለገውን ቢያደርግ በኢትዮጵያ በምድሩ ነው።ይህንን የእረቻ በዓል ለማክበር ከመላው የኢትዮጵያ ምድር ተጠራርቶ ሲመጣ፣ ከአውሮፓ እና አሜሪካ ድረስ ሁሉ በብሸፍቱ (ደብረ ዘይት) ምድር ሲሰበሰብ የእርሱኑ መልክ ያላቸው የሕወሓት አጋዚ ወታደሮች እንደ ባዕዳን በመትረጌስ ከምድር እና ከሰማይ በኤሊኮፍተር  እገደላለሁ ብሎ አይደለም። 

እናንተ ግን በሚልዮን በሚቆጠር ሕዝብ ላይ የጥይት መዓት አወረዳችሁበት። ኢትዮጵያ ዛሬ ዳግም አነባች። እርግጥ ነው ዛሬ በኦሮሞ ወንድሞቻችን ላይ የፈፀማችሁት ያቀዳችሁትን ነው። 

ለእዚህ ማሳያው የፖለቲካ ድባቡን ታውቁታላችሁ።ማንኛውም ስብስብ በእናንተ ላይ ቢያንስ የመፈክር ተቃውሞ እንደሚኖር ማንም መሃይም የፖለቲካ ስሜቱን ለክቶ ማወቅ ይችላል።ይህ ማለት ለጥቂት ደቂቃዎች መፈክር ይሰማል።ስሜት ይገለጣል።አበቃ!በዓሉ ሲያበቃ ሕዝብ ተሰነባብቶ ወደቤቱ ይሄዳል።ይህንን ማለት ግን ትንሽነት ለሚሰማችሁ ለእናንተ እንደ ትልቅ ውርደት ቆጠራችሁት ይህ ብቻ ሳይሆን የዐማራ ህዝብን እንደምትጠሉት ሁሉ ኦሮሞን ጥንቃላችሁ እና እንዴት ይደረጋል ብላችሁ በሕዝቡ ገንዘብ በገዛችሁት መሳርያ ባለቤቱ ላይ አርከፈከፋችሁ። ብዙ መቶዎችን ገደላችሁ።

የቀረውን በጭስ እያፈናችሁ ወደ ገደል ከተታችሁት።ይህ ፅሁፍ እየተፃፈም የሞተው ቁጥር ከ300 በላይ እንደሆነ እየተነገረ ነው።አሁንም አስከሬን  ተሰብስቦ አላበቃም። አናሳ ስለሆናችሁ ብዙሃንን ትጠላላችሁ።ትንሽነት ስለሚሰማችሁ የተከበሩ የአገሪቱን ዜጎች ትገላላችሁ።ይህ ቀን በትክክል ይቀየራል።

የአቀያየሩ ዋጋን ግን እንዴት ከፍላችሁ እንደምትጨርሱት ሳስብ ለእናንተው አዝናለሁ።




ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Saturday, October 1, 2016

የዐማራ ድምፅ ራድዮ የመጀመርያ አጭር ሞገድ ስርጭቱን ወደ ኢትዮጵያ ጀመረ።

ራድዮ ጣብያው ሰኞ፣ሮብ እና ቅዳሜ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ 3 ሰዓት ወደ ኢትዮጵያ በ19 ሜትር ባንድ እና በኢንተርኔት የሚያሰራጨውን ፕሮግራም ቅዳሜ መስከረም 21፣2009 ዓም መጀመሩ ለማወቅ ተችሏል።

ራድዮ ጣብያው ከሌሎች በብሄር ስም ከተመሰረቱ ራድዮ ጣቢያዎች የሚለየው የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ የሚጠቀም መሆኑ እና በመርሃ ግብሩ ላይ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር! የሚለው ብሔራዊ አገላለጥ ማሰማቱም ጭምር ነው። የራድዮ ጣብያውን የመጀመርያ መርሃ ግብር ጉዳያችን ላይ ያዳምጡ።



ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

በኢትዮጵያ የእገታ ወንጀል ተሳታፊ አራት አካላት ናቸው። ለችግሩ የመፍትሄ አካላት ሁለት ናቸው።ሁለቱ አካላት ምን ይስሩ?

======= ጉዳያችን ======= በኢትዮጵያ ዜጎችን እያገቱ ገንዘብ የሚቀበሉ ወንጀለኞች ከተራ ወንጀለኝነት አልፎ በታጣቂ ቡድኖች የገንዘብ ማግኛነት መዋል ብቻ ሳይሆን ዜጎችን የማሸበርያ ፋሺሽታዊ ተግባር ሆኗል። እገታ የ...