ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Friday, June 7, 2019

የቶቶ ግብረ ሰዶማውያን በላልይበላ ሊያደርጉት ያሰቡት ጉዞ አፍሪካን ለመተንኮስ የታሰበ ነው።

የቅዱስ ላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት 

ጉዳያችን/ Gudayachn
ሰኔ 2/2011 ዓም (ሰኔ 8/2019 ዓም)

ግንቦት 29/2011 ዓም ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል በለቀቀው ዜና እንዲህ ይነበባል: - 


ግብረ ሰዶማውያን በኢትዮጵያ ለማድረግ ያቀዱትን የቅዱስ ላሊበላ ገዳም ተቃወመው ።
የግብረ ሶዶማውያን አስጎብኝ ማኅበር በኢትዮጵያ ሊያደርግ ያቀደውን የጉብኝት መርሀ-ግብር እንደማይቀበለው የቅዱስ ላልይበላ ገዳም አስታወቀ፡፡
መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው ‹ቶቶ› የተባለ የግብረ ሶዶማውያን አስጎብኝ ድርጅት በቀጣዩ ጥቅምት ወር 2012 ዓ.ም በኢትዮጵያ ጉብኝት እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡ ጉብኝት ከሚያደርግባቸው ቦታዎች መካከል የቅዱስ ላልይበላ ገዳም አንዱ ነው፡፡ ድርጅቱ በማኅበራዊ ሚዲያ የፊት ገጹ ላይ የቤተ ጊዮርጊስን ፎቶ በመለጠፍ ‹‹ላልይበላ እንገናኝ›› የሚል መልዕክት አስፍሯል፡፡
የአካባቢው ማኅበረሰብ እና የገዳሙ አስተዳዳሪ አባ ጽጌ ሥላሴ መዝገቡ ዕቅዱን ከተመለከቱ በኋላ የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል፡፡ አባ ጽጌ ሥላሴ እንደተናገሩት ግብረ ሶዶማዊነት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተወገዘ እና ከተፈጥሮ የወጣ ተግባር ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስም ‹‹ወንድ ከወንድ ሴት ከሴት ጋር ግንኙነት ቢያደርግ የተረገመ ይሁን፤ ከሃይማኖቱ ማኅበርም ይለይ›› በማለት እንደሚያስቀምጥ አስረድተዋል፡፡ በመሆኑም ጉብኝቱ ተገቢ እንዳልሆነና እንደማይደግፉት አባ ጽጌ ሥላሴ መዝገቡ ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያውያን ባሕል፣ እሴት እና ወግም ቢሆን ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ድርጊት ነው፡፡ የሀገሪቱ ሕግም ቢሆን ድርጊቱን በወንጀል አስቀምጦታል፡፡
በመሆኑም አስጎብኝ ድርጅቱ ቢቻል ወደ ሀገሪቱ እንዳይገባ የሚመለከተው አካል መከላከል እንዲችል፤ ካልሆነ ግን ወደ ቤተ ክርስቲያኒቱ እንዲገባ የማይፈቀድለት መሆኑን እንዲያውቅ አባ ጽጌ ሥላሴ አስታውቀዋል፡፡ ይህንን ተላልፎ ቢመጣ ለሚፈጠረው ሁከት እና ግጭት ቤተክርስቲያኒቱም ሆነች የአካባቢው ምዕመን ኃላፊነቱን እንደማይወስዱም አስታውቀዋል፡፡ ‹‹ይህንን አስመልክቶ እኛ አቋማችንን በደብዳቤ አሳውቀናል›› ብለዋል፡፡
የቱሪስት ወደ ሀገሪቱ መምጣት ለአስጎብኝ ድርጅቶች፣ ለሆቴሎች፣ ለቤተ ክርስቲያኒቱም ሆነ ለሀገሪቱ የሚሰጠው ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ከፍተኛ እንደሆነ እንደሚረዱ ያስወቁት የገዳሙ አስተዳዳሪ ‹‹ማንነታቸውን በግልጽ አሳውቀው በቡድን መምጣታቸው በማንኛውም መንገድ ተቀባይነት አይኖረውም›› ብለዋል፡፡
ጉዳዩን አስመልክቶ መንግሥት አቋሙን በአጭር ጊዜ እንዲያሳዉቅ ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት የጎንደር ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናት ኅብረት ጠይቋል፡፡ የግብረ ሰዶማውያን የኢትዮጵያ ጉብኝት መርሀ-ግብር ከሃይማኖት፣ ከሕግ፣ ከሞራል እና ከሀገሪቱ ባሕል ጋር የሚጻረር ስለሆነ መርሀ-ግብሩ እዉን የሚሆን ከሆነ ለሚፈጠረዉ ማንኛዉም ችግር መንግሥት ኃላፊነቱን እንደሚወስድም አስታውቋል፡፡
ኅብረቱ ለኢፌዴሪ ባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በጻፈዉ ደብዳቤ ‹ቶቶ› የተባለዉ አስጎብኚ ድርጅት ሊጎበኛቸው ካሰባቸው ቦታዎች መካከል ታሪካዊቷ ጎንደር እና በዉስጧ የሚገኙ ጥንታዊ አድባራትም ተጠቅሰዋል፡'' ይላል።የዜናው መጨረሻ ።

ላልይበላ ለምን?
ከላይ በዜናው ላይ እንደተጠቀሰው ቶቶ የተሰኘው የግብረ ሰዶማውያን ድርጅት ''ላልይበላ (ላሊበላ) እንገናኝ'' በሚል ለመጪው ጥቅምት /2012 ዓም ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ማሰባቸው ከፍተኛ ተቃውሞ እያስተናገደ ነው።ይህ ጉዳይ በጠበቀ የሃይማኖት መሰረት ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያን ኢላማ ያደረገበት ዋና ምክንያት ኢትዮጵያን የመተንኮስ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ተደርቦ አፍሪካ ላይ ያለመ ተግባር ነው። በአፍሪካ ውስጥ ካሉት ሀገሮች ውስጥ በግልፅ ግብረ ሰዶማዊነት በሕግ የታገደባቸው ሀገሮች 33  ደርሰዋል።በመካከለኛው ምስራቅ ደግሞ  አስር ሀገሮች በሕግ ግብረ ሰዶማዊነትን መፈፀም በወንጀል እንደሚያስቀጣ ደንግገዋል።በሌላ በኩል የግብረ ሰዶማዊነትን ተግባር አጥብቀው ከሚቃወሙት  ሃገራት ውስጥ ሩስያ ተጠቃሽ ነች። ሩስያ በጉዳዩ ላይ ጥብቅ ሕግ ከማውጣቷ በላይ ፕሬዝዳንቱ በተደጋጋሚ ጉዳዩ የምዕራቡ ዓለም ትንኮሳ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የግብረ ሰዶማውያኑ ድርጅት ከኢትየጵያ ቅዱሳን ቦታዎች ውስጥ አንዱ የቅዱስ ላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ለመገናኘት ቀጠሮ የያዙበት ዋናው ምክንያት ኢትዮጵያ ለአፍሪካውያን ያላትን ቦታ ተጠቅሞ በኢትዮጵያ ተሻግሮ አፍሪካን መተንኮስ ነው።በእዚህ አጋጣሚ ጉዞው ከተሳካ በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉዞ ትልቅ የሚድያ ሽፋን በማሰጠት የቀረው አፍሪካን የመተንኮስ እና በምሳሌነት ለማስያዝ ያለመ ነው።ጉዳዩ በአንዲት ሀገር ፣ሕዝብ እና የከበረ ዕምነት ላይ የተቃጣ ጥቃት ነው።ጉዳዩ የሃይማኖት ብቻ አይደለም፣ጉዳዩ የባህል እና የሞራል ጉዳይ  ብቻ አይደለም።ጉዳዩ ከእነዚህ ሁሉ በላይ ፖለቲካዊ ዓላማ አለው።ይህ እንስሳት ያማይፈፅሙት ከዘመናት በፊት ምድራችን የተቀጣችበት እኩይ ተግባር ዛሬ በእዚህ ትውልድ ጊዜ መታሰቡ በራሱ አሳዛኝ ነው። 

መጽሐፍ ቅዱስ ግብረ ሰዶማዊ ተግባር ኃጥአት እንደሆነ ይነግረናል (ኦሪት ዘፍጥረት 19፤1-13፣ ኦሪት ዘሌዋውያን 18፤22፣ ወደ ሮሜ ሰዎች 1፤26-27፣ 1ኛ ቆሮንቶስ 6፤9)፡፡ በተለይ ሮሜ 1፡26-27 ግብረሰዶማዊነት እግዚአብሔርን የመካድና ያለመታዘዝ ውጤት እንደሆነ ያስተምረናል፡፡ ሰዎች በኃጢአትና በአለማመን በሚቀጥሉበት ጊዜ እግዚአብሔር ከእርሱ የተለየ የከንቱነትንና የተስፋ-ቢስነትን ህይወት ለማሳየት አብዝቶ ለከፋ እና ነውር “አሳልፎ ይሰጣቸዋል”፡፡ 1ኛ ቆሮንቶስ 6፤9 ግብረ-ሰዶምን የሚያደርጉ “ዓመፀኞች” የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱም ይነግረናል፡፡ይህ ግልጥ ሃይማኖታዊ ትዕዛዝ ነው።

ይህ የኢትዮጵያን ዕምነት፣ባህል እና ታሪክ ያላገናዘበ ጉብኝት በራሱ ጠብ ጫሪ ከመሆኑ የተነሳ መንግስት በግብረ ሰዶማውያን ዙርይ ወሳኝ የሆነ ውሳኔ ማሳለፍ እንዳለበትም አመላካች ነው። አሁን ባለበት ሁኔታ ከህዝብ ዘንድ የተነሳው ከፍተኛ ቁጣ  አንፃር ምን ሊፈጠር እንደሚችል አይታወቅም። ስለሆነም መንግስት መጪውን ዘመን ያገናዘበ  አሰራር ከአሁኑ መቀየስ አለበት።ጉዳዩ በኢትዮጵያ ሕዝብ ስነ ልቦን፣እምነት እና ስልጣኔ ላይ ሁሉ የተቃጣ ሙከራ ነው።በመሆኑም መንግስት በማያወላዳ መልኩ በጉዞው ለሚሳተፉ የመግብያ ፈቃድ በመከልከል እና ተያያዥ የሕግ ማዕቀፎችን ማውጣት አለበት።የእዚህ አይነቱ እርምጃ መውሰድ ሕዝብ በራሱ ተደራጅቶ በግብረ ሰዶማውያን ላይ ሕዝብ በብስጭት  ለሚወስዳቸው እርምጃዎች ሁሉ ሌላ የፀጥታ ችግር እንዳይሆን የሚረዳ እርምጃ ይሆናል።  

በመጨረሻም ቅዱስ ሲኖዶስን ጨምሮ በኢትዮጵያ ያሉ መንፈሳዊ ማኅበራት ኅብረት ጭምር የግብረ ሰዶማውያንን ጉዞ ከማውገዝ አልፈው ለሚመለከተው የመንግስት አካልም ማሳሰብያ መላካቸው ጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጠው የሚያመላክት ሌላው አመላካች ጉዳይ ነው።የግብረ ሰዶማውያን ጉዳይ በቀጣይ ዓመታትም ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ፣ሕዝብ እና የሃይማኖት አካላት  ጭምር የሚገጥማቸው ከግብረ ሰዶማውያኑ  ስብስብ ብቻ ሳይሆን ግብሩን ባፀደቁላቸው መንግስታቶቻቸው መዋቅር ውስጥ እየገቡ በሌሎች ሀገሮች ላይ ግብሩን ለመጫን የሚያደርጉት ጥረት ከፍተኛ የቁጣ መልስ ከአፍርካውያንም ሆነ ከእስያ መንግሥታት ገጥሟቸዋል።ኢትዮጵያም ካላት ታሪካዊ ኃላፊነትም አንፃር ይህንን ከሃይማኖት፣ከባህል እና ከሰዋዊ ሞራል ጋር ሁሉ የሚቃረን ተግባርን በቀዳሚነት መቃወም አለባት። በተለይ ጉዳዩ ወደ አፍሪካ ሲመጣ  የአፍሪካውያንን እጅ ለመጠምዘዝ የማድረጉ ሙከራ በቀጣይ ጊዜያትም የሚሞከር ሊሆን ይችላል። ስለሆነም ሕዝብ በዕምነቱ እና በሰውነቱ ላይ በጠላትነት የተነሳበት የግብረ ሰዶማውያን ተግባር በኢትዮጵያ እስከመቼውም አለመቀበል እና ይልቁንም ዓለም አቀፍ ፀረ ግብረ ሰዶማውያን እንቅስቃሴን ኢትዮጵያ መቀላቀል እና ማስተባበር  እስከመጨረሻውም መታገል ይገባታል።ይህ ደግሞ በሥጋዊውም ሆነ ነነፍሳዊ ሕይወት ሁሉ ታላቅ በረከት ነው። 

ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

No comments:

ወቅታዊ የዓለም ሁኔታ እንድንነታረክ ዕድል የሚሰጥ አይደለም።ብንነቃ መልካም ነው።

========== ጉዳያችን ወቅታዊ ========== የዓለም ታሪክ እንደሚያስተምረን ዓለም በወሳኝ የእጥፋት(turning point) ታሪኮች ውስጥ አልፋለች። እነኝህ የእጥፋት ጊዜዎች የዋዛና የፈዛዛ ጊዜ አይደሉም።መላው ዓለ...