ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Friday, December 29, 2017

ኢትዮጵያ ከሥርዓት ለውጥ በኃላም ከእራሷ ጋር የታረቀች፣ ከሕዝቡ ባህል እና ስነ ልቦና ጋር የሚሄድ የችግር አፈታት መከተል እንዳለባት የሚያሳይ ልዩ ጥናታዊ ዝግጅት - ሽምግልና እና እርቅ በኢትዮጵያ (ኦድዮ)

 • ከእዚህ በፊት ፈፅሞ ሰምተዋቸው የማያውቋቸው በርካታ የሀገራችን ታሪኮች የተካተቱበት ልዩ  የድምፅ ዝግጅት 
የልዩ ጥናታዊ ዝግጅቱ አቅራቢ = ሸገር ኤፍ ኤም ስንክሳር ፕሮግራም 

ኢትዮጵያ በመንግስት ስርዓት ስትኖር የሃያ ስድስት አመታት እድሜ ያስቆጠረች አይደለችም።ከሶስት ሺህ አመታት በላይ በመንግስት ስርዓት ታቅፋ በየዘመኑ የሚገጥሟትን ፈተናዎች እያለፈች የሄደችበት ምስጢር ከባዕድ ምድር የተፈበረከ ርዕዮት ዓለም በመጠቀም አይደለም።ይልቁንም በሕዝቧ ባህል፣ስነ ልቦና፣መልካም ግንኙነት እና እምነት ሁሉ ጋር በተናበበ መልክ መሪዎቿ ከእያንዳንዱ ግለሰብ እስከ ሹማምንቶቿ ድረስ ያሉትን ችግሮች የሚፈቱባቸው ሃገራዊ የሆኑ ዘዴዎችን በመጠቀማቸው ነበር። የሸገር ራድዮ በያዝነው ታህሳስ/2010 ዓም ስንክሳር በተሰኘ ሳምንታዊ መርሃ ግብሩ 'ሽምግልና እና እርቅ በኢትዮጵያ'' በሚል ርዕስ ተከታታይ መርሃ ግብሮችን አስደምጧል።ኢትዮጵያ እንዴት እንደኖረች እና እንዴት መኖር እንዳለባት ይህ መርሃ ግብር ያመላክታል። ዝግጅቶቹን እስከመጨረሻ ቢያዳምጡ ይጠቀማሉ።

ሽምግልና እና እርቅ በኢትዮጵያ ክፍል አንድ 

ሽምግልና እና እርቅ በኢትዮጵያ ክፍል ሁለት 

ሽምግልና እና እርቅ በኢትዮጵያ ክፍል ሶስት 

ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

Friday, December 22, 2017

"የስኳር ኮርፖሬሽን እና ፕሮጀክቶቹን አስመልክቶ በዋናው ኦዲተር በወጣው ሪፖርት መሰረት አቃቢ ሕግ ክስ እንዲመሰረት ነበር የጠየቅነው እስካሁን ምላሽ የለም።እየጠበቅን ነው" ዋናው ኦዲተር መስርያ ቤት ድጋሚ ማሳሰቢያ።

ጉዳያችን ዜና / Gudayachn News
  
አቶ ገመቹ ዱቢሶ የዋናው ኦዲተር ቢሮ ኃላፊ 
 • መስርያ ቤቱ ለሕዝብ ይፋ ያደረጋቸው 'ጆሮ የሚጠልዙ' የሌብነት እና ዝርክርክ አሰራሮች በመተሃራ፣ወንጂ እና ተንዳሆ ፋብሪካዎች ላይ ያደረሰውን ጉዳት ያጋልጣል።
በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት መንግስታዊ መስርያ ቤቶች የመስርያ ቤቶችን የተዝረከረከ አሰራር የህወሓትን አምባገነናዊ ማሸማቀቅ በማለፍ በድፍረት ሙስናዎችን ለሕዝብ ይፋ በማድረግ በአቶ ገመቹ ዱቢሶ የሚመራው የዋናው ኦዲተር መስርያቤት አርአያነት ያለው ሥራ ሰርቷል። መስርያ ቤቱ የስኳር ኮርፖሬሽን በአቶ አባይ ፀሐዬ እየተመራ የደረሰበትን ክስረት ለሕዝብ በዝርዝር እና የኦዲት ሕግ እና ስርዓት በጠበቀ መልኩ በማቅረብ እና ሰነዱንም ለክስ በሚቀርብ መልኩ በማስረጃ አስደግፎ በመያዝ በኩልም ብዙ እርቀት እንደሄደ ይነገራል።
ይህም ሃገራዊ ኃላፊነት በሚሰማቸው የመስርያ ቤቱ ኃላፊ እና ሰራተኞቹ ብርቱ ትጋት እንደሆነ ይነገራል።

መስርያ ቤቱ በዛሬው እለት ታህሳስ 13፣2010 ዓም በዋና ኦዲተር ቢሮ ኃላፊው አቶ ገመቹ ዱቢሶ አማካይነት ለሸገር ራድዮ በሰጠው መግለጫ አቶ ገመቹ ዱቢሶ "  "የስኳር ኮርፖሬሽን እና ፕሮጀክቶቹን አስመልክቶ በዋናው ኦዲተር በወጣው ሪፖርት መሰረት አቃቢ ሕግ ክስ እንዲመስረት ነበር የጠየቅነው እስካሁን ምላሽ የለም።እየጠበቅን ነው" ማለታቸው ተሰምቷል።

መስርያ ቤቱ ለሕዝብ ይፋ ያደረጋቸው ስኳር ፋብሪካዎች ጋር የተያያዙ የሌብነት እና ዝርክርክ አሰራሮች 

በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ያለው
ስኳር  እጥረት አቶ መለስ እና ኃይለማርያም እንደሚሉት ሕዝብ በብዛት ስኳር ስለተጠቀመ ነው የሚለው ተረት ተረት ፀሐይ የሞቀው ውሸት መሆኑን ይህንን ሪፖርት የተመለከተ ሰው በቀላሉ መረዳት ይችላል። በእዚህ በህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት እና ተባባሪ ሹማምንት በተመራ የዝርፍያ እና ዝርክርክ ተግባር በኢትዮጵያ ላይ የደረሰው የጥፋት መጠን ሪፖርቱ በገለጠው የገንዘብ መጠን ብቻ ይወሰናል ብሎ መገመት ፈፅሞ እንደማይቻል መረዳት ይገባል።ከእዚህ በታች የዋናው ኦዲተር ቢሮ ያወጣው ሪፖርት በሶስቱ ፋብሪካዎች ብቻ ላይ የተጠቀሰው ዋና ዋናው ብቻ ተዘርዝሯል።

የተንዳሆ ፋብሪካን በተመለከተ 

 • የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ አፈጻጸምን አስመልክቶ ዓመታዊ የግርድፍ መሬት፣ የውሃ ገብ መሬት ርክክብና የሸንኮራ አገዳ ተከላ እቅዶች አለመሳካታቸው፣ የፋብሪካው ግንባታና ተከላ በ6 ዓመት የዘገየ ፕሮጀክት ሆኗል፣ ለፋብሪካው በአማካሪነት ከተቀጠረው ድርጅት ጋር የተገባው ውል ለ7 አመታት መራዘሙና ይህም ወደ 9.5 ሚልየን ብር ጭማሪ (713.4%) እንዲከፈል ማድረጉ፣ ለ499 ቤቶች ግንባታ ከ300 በላይ ለሆኑ ተቋራጮች ካለውል ስራ መሰጠቱ፣
 • በእዚሁ ፋብሪካ በርካታ ማሽነሪዎች ለብልሽት መዳረጋቸው፣ በማስከተልም በህወሓት ጀነራሎች የሚመራው ብረታ ብረት ኮርፖሬሽን ጋር 44 ሚልዮን ብር የሚያወጣ ለማሽነሪ መግዣ  ውል ቢፈራረምም ብረታ ብረት ኮርፖሬሽን ማሽኖቹን ሳይሰራ ከአንድ ዓመት በላይ ስለሆነ የሀገር ንብረት እንደባከነ ገልጧል፣
 • ለፋብሪካው የቲሹ ካልቸር ሥራ በሚል የተመደበው በጀትም ሆነ የወጣው ወጪ ተደብቆ እስካሁን ግልጥ አልተደረገም፣
 • ፋብሪካው ወደ ሥራ ባለመግባቱ ከ300 ሄክታር በላይ ላይ የተተከለው የሽንኮራ አገዳ ወደ ምርት ሳይቀየር እንዲገለበጥ  መደረጉ፣1349 ሄክታር ላይ የነበረ ቀደም ብሎ የደረሰ ሸንኮራ አገዳም ወደ ምርት መግባት ባለመቻሉ እንዲጣል መደረጉ እና ይህ ከፍተኛ ብክነት መሆኑ፣ 
የመተሐራ ፋብሪካን በተመለከተ 
 • የኢታኖል ፕላንት ግንባታና ተከላ ጨረታ ሂደትን የሚያሳይ ሰነድ አለመገኘቱ፤ ለግንባታና ተከላ ከተመደበው መነሻ የኮንትራት ዋጋ በላይ በብልጫ ለተፈጸመው የብር 33,859,495.41 ክፍያ ምክንያቱን የሚገልጽ የውል ማስረጃ አልተገኘም፣
 • የእንፋሎት ሀይል ማቅረብ ባለመቻሉ ከምርት ሊገኝ የሚቻል ከ68,6 ሚልየን ብር በላይ መታጣቱ እንዲሁም በግብዓትነት ሊውል የሚችል  ብር 39,193,770 የሚያወጣ ሞላሰስ መባከኑ ብሎም ብር 3,915,328.10 የሚያወጣ ከተሽከርካሪዎች ነዳጅ ጋር የሚቀላቀል 412,139.8 ሊትር ኢታኖልና ለተለያዩ የመጠጥ ኢንዱስትሪዎች በግብዓትነት የሚሸጥ ብር 2,559,388.99 የሚያወጣ 176,631.4 ሊትር ረክቲፉይድ ስፕሪት አልኮል ባለመመረቱ በድምሩ ብር 6,474,717.09 ሀገሪቱ እንድታጣ መደረጉን ደርሶበታል፣
 • በውል አፈጻጸምና ግዥ በኩል ከስኳር ኮርፖሬሽኑ ግዥ አፈፃፀም መመሪያ ውጪ ግዥ በመፈፀሙ ፋብሪካው ያልተገባ ተጨማሪ ወጪዎች እንዳወጣና በውል ያልታሰሩ ግዥዎችን እንደፈጸመም ተገልጾ በአብነት ለሥራ ላይ አደጋ መከላከያ አልባሳት ተጨማሪ ብር 168,834.89 ለሠራተኞች ዩኒፎርም ግዥ ደግሞ ብር 437,368.75 ተጨማሪ ወጪ ለሁለት አቅራቢዎች እንደከፈለ ተጠቅሷል፡፣
 • የእንፋሎት ሀይል ለማመንጨት የሚያስፈልገውን ውሃ እንዲያጣራ በብር 1,906,362 ለፋብሪካው ተገዝቶ ከህንድ የመጣና ሌሎች ልዩ ልዩ ክፍያዎች ተፈጽመውለት የተተከለ መሳሪያ ፋብሪካው ከሚጠቀምበት ነባር ቴክኖሎጂ ጋር ባለመግጠሙ ምክንያት ከሁለት ዓመታት በላይ አገልግሎት ሳይሰጥ መቀመጡ ለከፍተኛ ኪሳራ አስከትሏል፣
 • በተደረገው የነዳጅ ቆጠራ 3,224.86 ሊትር ፔትሮሊየም እና 8,304.95 ሊትር ዲዝል ከካርድ ባላንስ ጋር ሲነፃፀር አንሶ ተገኝቷል መልስ የሚሰጥ የለም 
 • በሁለት መርከብ ከውጭ ሀገር ተጭኖ ከመጣ ስኳር ውስጥ 3,777 ኩንታል የተበላሸ በመሆኑ ትክክለኛ ማስረጃ ባልተገኘለት መንገድ መቀበሩና ካሳ ያልተጠየቀበት መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ (ዘግይቶ በወጣ ሌላ ምንጭ ተቀበረ የተባለው ውሸት መሆኑ እየተገለጠ ነው።ከእዚህ ይልቅ ወደ ሀገር ውስጥ ከገባ በኃላ ሳይበላሽ እንደተበላሸ ተደርጎ እና እንደተቀበረ የተገለጠው ውሸት መሆኑ እና በድብቅ ገበያ ላይ መሸጡ የሰሞኑ ትኩስ ሆኗል)፣
የወንጂ ስኳር ፋብሪካ በተመለከተ 
 • የስኳር ፋብሪካ ማስፋፊያ የመነሻ ውል ስምምነት ላይ የፋብሪካው መጠናቀቂያ ጊዜ አለመገለጹ በተጨማሪም የፋብሪካ ግንባታና ተከላ ስራውን በአማካሪነት የተከታተለው ኩባንያ ውል ማጠናቀቂያ ጊዜ ለ8 ጊዜ እየተራዘመ ለ9 ዓመታት በመዘግየቱ ከመነሻ ኮንትራት ዋጋው በላይ ዩሮ 4,648,860  (150,190,992.82 ብር) አለአግባብ ተጨማሪ ክፍያ ለኩባንያው መከፈሉን ኦዲቱ አመልክቷል፣
 • የሸንኮራ አገዳ እርሻ ልማት ለማከናወን የመስኖ ግድብና አውታር ግንባታ የወለንጪቲ ቦፋ መስኖ ፕሮጀክት በ3 ዓመት ለማጠናቀቅ ውል ቢገባም ለ2 ዓመት ከ2 ወር ከመራዘሙ በላይ ስራዎቹ በተቀመጠላቸው ጊዜ ባለመጠናቀቃቸው ውሉ 4 ጊዜ የታደሰ በመሆኑ በድምሩ ብር 30,489,214 ከመነሻ ዋጋ ተጨማሪ ክፍያ መፈጸሙ ተገልጿል፣
 • ጂቡቲ ወደብ ተከማችተው የሚገኙ የፋብሪካ እቃዎችን በተመለከተ በፋብሪካው ለኮርፖሬሽኑ የቀረቡ የድጋፍ ጥያቄዎች አለመመለሳቸው፤ ከሞጆ ደረቅ ወደብ ለሚመጡ ዕቃዎች የገንዘብ ጥያቄን አስመልክቶ ብር 22,019,678.78 መከፈል ባለመቻሉ የመወረሻ ጊዜያቸው የተቃረበ 9 ዕቃዎችን በወቅቱ ባለማንሳት ለመጋዘን ኪራይ ብር 393,231.33 መከፈሉ ተመልክቷል፡፣
 • በንብረት አያያዝ በኩል እ.ኤ.አ በ2014/2015 በጀት ዓመት 124 ቀላል እና 41 ከባድ ተሽከርካሪዎች፤ እ.ኤ.አ በ2015/2016 በጀት ዓመት ደግሞ 172 ቀላልና 21 ከባድ ተሽከርካሪዎች በንብረት ቆጠራ ወቅት አለመገኘታቸው እና እነኝህ መኪናዎች የት እንዳሉ ማንም መልስ መስጠት አለመቻሉ፣
ባጠቃላይ የኦዲት ሪፖርቱ በገንዘብ በኩል የደረሰው ጥፋት ላይ ቢያተኩርም በእራሱ በኮርፖሬሽኑ ቀደም ብሎ ለማስፋፍያ በሚል ኢትዮጵያ ከ70 ቢልዮን ብር በላይ መበደሯ እና እስካሁን አንድም ፋብሪካ ወደ ሥራ አለመግባቱ መገለጡ ይታወቃል።ይህ በእንዲህ እያለ ነው ዛሬ ታህሳስ 13፣2010 ዓም የዋናው ኦዲተር ሥራ አስኪያጅ አቶ ገመቹ ከላይ የተጠቀሱት ጉድዮች በሕግ እንዲጣሩ ከማስረጃ ጋር ለአቃቢ ሕግ የላክን ቢሆንም እስካሁን መስርያቤቶቹም ሆኑ አቃቢ ሕግ ምላሽ አልሰጠም።ይልቁንም በባሰ ሁኔታ ችግሮች እየቀጠሉ መሆኑን ይገልጣሉ። ከእዚህ በተጨማሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከ80 ሚልዮን ብር በላይ መፈረም ያለበት ኃላፊ ሳይፈርም ወጪ መደረጉን የኦዲት መስሪያ ቤቱ ቢገልጥም እስካሁን ምላሽ አለመሰጠቱን ዜናው ያብራራል።የኢትዮጵያ የሙስና እና የባለስልጣናቱ የዘረፋ ደረጃ ከምንገምተው በላይ ነው።የስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክት ቅሌት በትንሹ ምን ያህል የሰፋ ምዝበራ እንደሚደረግ የሚያሳይ አንዱ ናሙና ነው።በእዚህ መልኩ በእያንዳንዱ ሴክተር ውስጥ ያለውን የዘረፋ ጥልቀት ምን ያህል እንደሆነ ማወቅ ይቻላል።የኦዲት መስሪያ ቤት ለእያንዳንዱ ክሶቹ በቂ በሰነድ የተያዘ ማስረጃ እንዳለው እና ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ የኦዲት ምርመራ ደረጃ መስራቱን አክሎ ገልጧል። 

ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

Thursday, December 14, 2017

የአድዋ ስርወ-መንግስትነቱን በበለጠ ያረጋገጠው ህወሓት አሁንም በያዘው የመግደል መንገድ ከቀጠለ መውጊያው ለእራሱ ይብስበታል (የጉዳያችን ማስታወሻ )


 • አይናችን የወገኖቻችንን አስከሬን ለመደ ?
 • ኦህዴድ ሳይቀር ያልጠራናቸው እና ያልጋበዝናቸው ታጣቂዎች እንዴት ወደ ክልሉ እንደመጡ እንደማያውቁ እና አለመጋበዛቸውን መግለፁ የይስሙላውም የኢህአዴግ ማዘዣ ጣብያ ሙሉ በሙሉ መፍረሱን ያሳያል።
ኢትዮጵያ ለህወሓት ስልጣን እና ለአድዋ መንደር እና የቤተሰብ ትስስር ሐብት የማጋበስ ሰይጣናዊ ተግባር ሲባል እንድትበታተን ብቻ ሳይሆን አለ የተባለ የህዝቧ ቁስል እየተፈለገ በህወሓት የተንኮል ስለት እየተከፈተ ለዘመናት አብሮ የኖረ ሕዝብ ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለነገም የልጅ ልጆቹ አብረው እንዳይኖሩ  እለት እለት በቢሮ ውስጥ ቁጭ ብለው ተንኮል በሚያደሩ ባለሙያዎች እልቂት እንደተደገሰለት ይታያል።

ስለ ህወሓት አሁን እዚህ አጭር ማስታወሻ ላይ እንደ አዲስ ለመተረክ የማስታወሻዬ አላማ አይደለም።ምክንያት ብዙዎች በሚገባ ተንትነውታል። አሁን የሰሞኑ የህወሓት ድርጊት (ከእዚህ በፊት የነበረ ተግባሩ ቢሆንም)  ገና ከሃያ ሁለት ዓመት ያልዘለሉ ለጋ ወጣቶችን በሀገሪቱ ከአስራ አምስት ዩንቨርስቲዎች በላይ በሚገኙ ካምፓሶች መኝታ ቤት ድረስ ቦንብ እና ክላሽ የታጠቁ የአጋዚ ሰራዊት እያሰማራ፣ የመኝታ ቤታቸውን በር እየሰበረ ከተማሪ ደብተር እና እርሳስ ሌላ በእጃቸው አንዳች የማያውቁ የኢትዮጵያ የነገ ተስፋዎችን በእየሜዳው ላይ አስከሬናቸውን አነጠፈው፣ደማቸው እንደ ውሃ ፈሰሰ።ከወልዲያ እስከ ነቀምት ያሉ ዩንቨርስቲዎች በሽብር ተወጥረው፣ የእናት የአባታቸውን ፊት ሳያዩ ለማደር የሚደነግጡ ታዳጊ ወጣቶችን በቂም እና በዘረኝነት ጥላቻ በተሞላ ስሜት ቁጥራቸው ያልታወቁ ኢትዮጵያውያውን ሕይወት ተቀጥፏል።

በጉዳዩ ዙርያ ወላጆች ስለልጆቻቸው መረጃ እንዳያገኙ ብቻ ሳይሆን ተማሪዎች ወደ ቤተሰብ ቀርቶ ወደ አካባቢው አብያተ ክርስቲያናት እንዳይሄዱ እና እንዳይጠለሉ አስከሬን በወጣበት ግቢ ውስጥ ተማሪዎች በግድ አርፋችሁ ተማሩ  መውጣት አትችሉም ተብለው ዙርያውን በወታደር እያጠረ የቤተሰብ ሰቀቀን ሳምንት ሆነው ሳምንታቱ አልፈዋል። ይህ ብቻ አይደለም። ተማሪዎቹ ለወላጆቻቸው ደውለው ወይንም በማህበራዊ ሚድያ ደህንነታቸውን እንዳይናገሩ ወይንም በግቢው ውስጥ እየተፈፀመ ስላለው ጉዳይ ለተቀረው ዓለም እንዳይገልጡ የኢንተርኔት እና ስልክ አገልግሎት ቆርጦ ወጣቶቹን ሲያሰቃያቸው ነው የከረመው።

የሰሞኑ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች አዲስ  የሚያደርገው አንዱ እና አይነተኛ ምክንያት በመላው ሀገሪቱ ውስጥ ትግራይን ጨምሮ ግጭቶች መፈጠራቸው እና ይህንን ተከትሎም ቀደም ብለው የተጀመሩ ሕዝባዊ አመፆች በአዲስ መልክ መነሳታቸው ነው።ከእዚህ በተለየ የስርዓቱ ታጣቂዎች አድሏዊ ተግባር በሕዝቡ ዘንድ ብቻ ሳይሆን የኢህአዴግ አባል ድርጅት በሚባለው በኦህዴድ ሳይቀር ያልጠራናቸው እና ያልጋበዝናቸው ታጣቂዎች እንዴት ወደ ክልሉ እንደመጡ እንደማያውቁ እና አለመጋበዛቸውን እንዲሁም በመንግስት ደረጃ የጨለንቆ እልቂትን አለማውገዝ ከመተባበር እኩል መሆኑን የገለጡት  የኦሮምያ ፕሬዝዳንት እና ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች መሆናቸው አድዋ መሩ የህወሓት አካል ከአባል ድርጅቶች ከሚላቸው ጋር የተፋጣበት እርቀትን  ነው። እዚህ ላይ የኦህዴድ  ያልጠራናቸው እና ያልጋበዝናቸው ታጣቂዎች እንዴት ወደ ክልሉ እንደመጡ እንደማያውቁ እና አለመጋበዛቸውን መግለፁ የኢህአዴግ የይስሙላውም ማዘዣ ጣብያ ሙሉ በሙሉ መፍረሱን ያሳያል።

የሰሞኑ የኢትዮጵያ ከራሞት ኢትዮጵያ በቀጥታ በአድዋ የፖለቲካ ስርወ መንግስት እና በቀረው የኢትዮጵያ ክፍል መካከል ቀጥተኛ የጎሳ ግጭት እንዳይፈጠር ያሰጋል።ይህ ግጭት ደግሞ እንደ አዲስ አበባ ባሉ ከተሞች ላይ  የሆነ ቦታ በቀን ሰራተኞች መካከል በተነሳ ጠብ ቢጫር በቀጥታ የአድዋ መንግስት ደጋፊዎች በሕዝቡ ላይ የሚያደርሱት እልቂትም ሆነ በበደል የተማረረው እንዲሁም ልጆቹን ለከፍተኛ ትምህርት ልኮ እንደወጡ የቀሩበት በሚልዮን የሚቆጠር ሕዝብ በቀጥታ ወደ ከፍተኛ የቁጣ መገንፈል እንደሚሸጋገር ምንም ጥርጥር የለውም። ይህንን ሁኔታ ደግሞ እያባባሱ ያሉ የአድዋ መንግስት አድናቂዎች እና የጥቅም ተጋሪዎች  በማኅበራዊ ሚድያ በምስኪኑ ኢትዮጵያዊ ላይ የሚያሳዩት ንቀት እና ስድብ እንዲስተካከል የሚመክር አለመኖሩ ብቻ ሳይሆን በሕግ የሚጠይቅ የሕግ አካል አለመኖሩ ነው ጉዳዩን የከፋ የሚያደርገው።

ይህ በእንዲህ እያለ ግን ሁለት  አደገኛ ሁኔታዎች በሕዝብ ዘንድ እየታየ ነው። ይሄውም የወገኖቻችን መገደል በእየለቱ በመስማት፣አስከሬን በማየት እና የሚፈሰው ደም በተገቢው ደረጃ የማይሰቀጥጠው ሰው የመኖሩ አደጋ እና ስሜቱ የተነካውም በተገቢ የቁጣ ደረጃ ለመብቱ የመነሳት ፍጥነት በተለይ በአዲስ አበባ እየታየ መሆኑ ነው።ይህ ማለት ከንፈሩን ከመምጠጥ ባለፈ ቁጣውን በተገቢው የማይገልጥ ወይንም እንዳላየ የሚያልፍ ሕዝብ በተለይ በአዲስ አበባ ነዋሪ ዘንድ መታየቱ የአዲስ አበባ ሕዝብ የሚከፍለው ዋጋ እንዳይንር ያሰጋል።ይህ ወቅት  የአድዋ የቤተሰብ መንግስት ስልጣኑን እንዲለቅ፣ ሕዝብ በጎሳ እንዳይተላለቅ የማኅበራዊ እና ሃይማኖታዊ አደረጃጀቶች እንዲጠናከሩ የሚሰራበት ጊዜ እንጂ እንዳላዩ የሚያልፉበት ጊዜ አይደለም።ምሁሩ፣ወታደሩ፣ፖሊሱ፣ተማሪው፣ገበሬው እና የከተማ ነዋሪው በአንድነት በኢትዮጵያዊነት ስሜት የሚነሳበት እና በአድዋ መንደር ስር በመጡ ስብስቦች የሚንቀሳቀሰው የህወሓት ድርጅት በተቻለ መጠን የበለጠ ጥፋት ሳያደርስ የሚንቀሳቀሱበት እንጂ በእየለቱ በማኅበራዊ ሚድያ እና በቴሌቭዥን መስኮቶች ለጋ ወጣቶች አስከሬን እያየን አይናችን ተመልክቶ ከማዘን፣ከመበሳጨት እና ከመቆጨት ባነሰ መልኩ አስከሬን እያየን የመልመድ በሽታ እየተጠናወተን እንደሆነ መመልከት ይቻላል።የወጣቶቹ ሞት የኢትዮጵያ ሞት ብቻ ሳይሆን ነገ ለእያንዳንዱ ቤተሰብ የተደገሰ የጥፋት ድግስ መሆኑን  ተረድቶ በኅብረት ለሃገር ማዳን ተግባር መነሳት ይገባል።

ህውሓት በመላ ሀገሪቱ ላይ አንድ ዓመት ፈጅቶ የፈፀመው እና ብዙዎች ያለቁበት  አዋጅ ለውጥ ያላመጣለት መሆኑን ከተረዳ በኃላ በእያነሳውም በተግባር ግን አዋጁ ወትሮም ኢትዮጵያ ስትገዝበት የነበረው የበደል አይነት ሁሉ እየተፈፀመ እየተተገበረ ነው።የግፍ አገዛዙን  የስልጣን መጠበቂያ አጥር አድርጎ የሚመለከተው የአድዋ ዘመዳሞች መንግስትሬም ኢትዮጵያን በደም እየነከረ  አዲስ አበባን በቅርቡ በአመፅ የምትፈነዳ ከተማ አድርጎ የአመፅ ቀለበት ውስጥ ገብታለች።አዲስ አበባ ትንሽ ምክንያት የሚሆን ኮሽታ ብቻ የምትጠብቅ ከተማ እንደሆነች ለማንም ግልፅ ሆኗል።ይህንን የተረዱ ዓለም አቀፍ ድርጅት ሰራተኛ ኃላፊዎች በሰበብ አስባቡ ከሀገር እየወጡ የምከርሙበት አንዱ ምክንያት ይሄው በማንኛውም ጊዜ ሊፈነዳ እንደሚችል የሚነገረው ሕዝባዊ አመፅ ፍራቻ እንደሆነ ጉዳዩን በእገባ የሚያውቁ የቡና ላይ ወሬ ካደረጉት ሰንብተዋል። ምናልባትም በመጪዎቹ ጥቂት ሳምንታት ውስጥ የአዲስ አበባ ድምፅ አይሰማም ማለት አይቻልም። እዚህ ላይ አስገራሚው ጉዳይ ህወሓት ችግሩ የአድዋ ስርወ መንግስት የጎሳ ፖለቲካ መሆኑን የረሳ እየመሰለ ችግሩ ከአቶ ሃይለማርያም ለማስመሰል አቶ ኃይለማርያምን በመቀየር መፍትሄ ያመጣ ለመምሰል ሽር ጉድ እያለ ነው። ቀድሞም የህዝቡን ድምፅ የመጨፍለቅ ሥራ የሚሰራው  እና ትዕዛዙ ለይስሙላ በአቶ ሃይለማርያም ይምሰል እንጂ ዋና ማዘዣ ጣቢያው የሚመጣው ከህወሓት ቢሮ መሆኑ ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው።ትልቁ ቁም ነገር ይህ ሁሉ እልቂት እየተፈፀመ ያለው የህወሓት መንግስት ስልጣን ለሕዝብ አላስረክብም በቀደድኩላችሁ ቦይ ብቻ ፍሰሱ  የሚል የእብሪት ተግባር ምክንያት መሆኑን ሁል ጊዜ መዘንጋት የሌለበት ነው።ህወሓት ኢትዮጵያ ትጥፋ እንጂ ስልጣን አልለቅም ሂደቱ ሁላችንን ኢትዮጵያውያንን መጪውን በመፍራት አርፈን የምንገዛ አድርጎ የማሰብ የአስተሳሰብ ድህነት ብቻ ሳያሆን  የኢትዮጵያን ሕዝብን ስነ ልቦና ደረጃ ያለመረዳት ችግር ነው።

ባጠቃላይ በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ከመጥፎ መጥፎ ይመረጣል።ሁሉም መጥፎ አካሄድ ቢሆንብህ የተሻለውን መጥፎ መምረጥ ብቻ አማራጭ የሚሆንበት አጋጣሚ በሀገሮች ታሪክ የሚያጋጥም እውነታ ነው።ሳይንገጫገጩ ያሰቡበት መድረስ የለም። ህወሓት በስልጣን ላይ እያለ ከሚመጣው የመከፋፈል አደጋ ይልቅ የተከፈለው መስዋዕትነት ተከፍሎ ሕዝብ ነፃነቱን ማወጅ እንደሚመርጥ እና አሁን እየሆነ ያለው ሁሉ ሕዝብ  ለበለጠው ትግል ከመነሳት ሌላ አማራጭ እንደሌለው  እንጂ አንዳች ወደ ኃላ እንደማይገፋው ማወቅ ተገቢ  ነው።ችግሩ እየገፋ ስመጣ እና ጉዳይ የትግራይ መሬትን እንደ ሌላው የኢትዮጵያ ፍል መቆርቆር ሲጀምር የአድዋው ስርወ መንግስት በእራሱ በትግራይ ሕዝብም ጭምር አደጋ ላይ መውደቁ አይቀርም።ለእዚህ ነው ህወሓት አሁንም ለእውነተኛ ለውጡ ካልተነሳች መውጊያው ለእራሷ ይብስባታል የምለው። ፈተናው ሲበዛ መውጫው ይጠባል።ህወሓት ከሁሉም ስጋት ውስጥ የገባው የትግራይ ሕዝብ በአድዋው የቤተሰብ መንግስት ላይ ይነሳብኛል በሚለው ስጋት ነው።
ይህንንም  ስለሚያውቅ ነው የትግራይ ተወላጆችን ከተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ግጭት ውስጥ ለማስገባት አንዴ በስፖርት ሌላ ጊዜ በዩንቨርስቲ ተማሪዎች መሃከል በሚነሱ ጠቦች ሕዝቡን ለማስደንበር የምሞክረው።ለምሳሌ የወልዲያው የስፖርት ጫወታ ግጭት ላይ ህወሓት ቢያንስ በደህንነቱ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ቀድሞ ያውቃል።የአቶ ጌታቸው ቢሮ ግን ጫወታው እንዲሰረዝ አላደረገም። ይልቁንም ለግጭቱ ምክንያት እንዲሆን በከተማው ውስጥ ከትግራይ የመጡ ወጣቶች በፒክ አፕ መኪና እየተዘዋወሩ አላስፈላጊ ቃላት እንዲሰነዝሩ አደረገ።አንድ የስፖርት ጫወታ አይደለም ውጥረት መኖሩ እየታወቀ ቀርቶ ኃይለኛ ዝናብ በመኖሩም ይሰረዛል። ለህወሓት ግን የትግራይ ሕዝብ ብቸኛ ተከላካይ መሆኑን ለመንገር ይህንን ግጭት እያወቀ ሕዝብ እንዲገባ አደረገ።በምላሹ በአዲግራት ዩንቨርስቲ እና ሌሎች ቦታዎች በፈለገው መንገድ ተቀጣጠለለት ህ አካሄድ ለህወሓት መውግያውን ያስለዋል እንጂ መፍትሄ አይሆንም። የመጨረሻው ብሔራዊ ተቃውሞ በመላ ሀገሪቱ አዲስ አበባን ጨምሮ የተነሳ ጊዜ ህወሓት የቀረ እንጥፍጣፊ ሃሳብ ለማስረዳት ፋታ አገኛለሁ ብሎ ካሰበ ፍፁም  ሕልም እንደሚሆን ከአሁኑ ብረዳው ጥሩ ነው።

እስከመጨረሻው ሊያዳምጡት የሚገባ ቁምነገረኛ ዜማ ከአርቲስት ስለሺ ደምሴ - ጋሽ አበራ ሞላ (ቪድዮ ከስር ይመለቱ)ጉዳያችን GUDAYACHN 

 www.gudayachn.com

Tuesday, December 12, 2017

በሃያኛው ክ/ዘመን የኢትዮጵያን ፊደል በመላው ኢትዮጵያ እንዲዳረስ ያደረጉ የቀኝ አዝማች ተስፋ ገብረስላሴ ሥራ፣ታሪክ እና ስኬት ላይ ያተኮረ ጥናታዊ ፊልም

"ድንቁርና ይጥፋ፣
ዕውቀት ይስፋ!  
ይህ ነው የኢትዮጵያ ተስፋ።"   ቀኝ አዝማች ተስፋ ገብረ ስላሴ መመርያ 

ጉዳያችን/ Gudayachn 

ምንጭ : - ዓውደ ሰብ ዝግጅት 

ክፍል አንድ 

ክፍል 2


ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Saturday, December 9, 2017

የኢትዮጵያውያን የጋራ መድረክ በኖርዌይ የኢትዮጵያ የሲቪክ እና የፖለቲካ ድርጅቶች በወቅቱ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያላቸው ሚና በሚል ርዕስ በቀረበ ውይይት ላይ የአቶ ገረመው እና አቶ ሳሊኒ መነሻ ጽሁፍ (ቪድዮ)

ህዳር 30/2010 ዓም ኦስሎ ላይ የኢትዮጵያውያን የጋራ መድረክ በኖርዌይ የኢትዮጵያ የሲቪክ እና የፖለቲካ ድርጅቶች በወቅቱ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያላቸው ሚና በሚል ርዕስ በቀረበ ውይይት ላይ የአቶ ገረመው እና አቶ ሳሊኒ መነሻ ጽሁፍ በርካታ ጉዳዮችን በርዕሱ ዙርያ የዳሰሰ ነበር። አቶ ገረመው ንጋቱ እና አቶ ሳልህ አብርሃም የቀረቡ መነሻ ሃሳቦች በርካታ ጉዳዮችን የዳሰሱ ነበሩ። አቶ ገረመው ንጋቱ በግጭት አፈታት (conflict resolution) ላይ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን የሰሩ ሲሆን አቶ ሳልህ አብርሃም ደግሞ በኖርዌይ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ራድዮ ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል።

አቶ ገረመው ንጋቱ ያቀረቡት 


በአቶ ሳልህ አብርሃም የቀረበው 
ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

Wednesday, December 6, 2017

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ የሞባይል አፕሊኬሽን አስመረቀ።በሞባይል አፕሊኬሽን የሚጠቀሙ ደንበኞች ለትኬት ከሚከፍሉት ክፍያ የ10% ቅናሽ ያገኛሉ።Ethiopian Airlines introduces new mobile app. Customers will enjoy 10% discount on all mobile bookings.
ጉዳያችን ዜና / Gudayachn News

(Read in English below)
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ የሞባይል አፕሊኬሽን አስመረቀ።ደንበኞች በአፕሊኬሽኑ ተጠቅመው ቀድመው ቦታ መያዝ፣ትኬት ማውጣት እና የቦርዲንግ ለውጥ ቢኖርም በቀላሉ ለማወቅ ያስችላቸዋል።
ከእዚህ በተጨማሪ በሞባይል አፕሊኬሽን የሚጠቀሙ ደንበኞች ለትኬት ከሚከፍሉት ክፍያ የ10% ቅናሽ እንደሚያገኙ ዜናው ይጠቁማል። ዝርዝሩን አየር መንገዱ ትናንት የለቀቅውን ሙሉ ዜና ከስር ያንብቡ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ወቅት ወደ አምስቱም አህጉሮች የሚበር ሲሆን ከአንድ መቶ በላይ መዳረሻዎች አሉት።
ኢትዮጵያ አየር መንገድ ማስታወቂያ አጭር ቪድዮ 


Ethiopian Airlines, the largest Aviation Group in Africa and SKYTRAX certified Four Star Global Airline, is pleased to announce that it has launched a brand new Mobile Application, which encompasses an array of features that enhance customers’ travel experience with simplified and end-to-end options for flight booking and management by using their Android mobile devices. 
On the occasion of the launch of Ethiopian Mobile Application, Mr. Tewolde GebreMariam, Group CEO of Ethiopian Airlines remarked:
 “In the age of “the internet of things” and “Artificial Intelligence” I am very happy that our “mobility” project is fast advancing which enabled us to announce to our esteemed customers that Ethiopian Mobile Application has gone live. The Mobile Application is a critical piece of our overall strategy to bring our customers’ travel experience to another level by leveraging on Information and Communication technology and African Flavored Ethiopian Hospitality.  
With this new Mobile Application, customers will be able to use their mobile devices to book their flights, do their flight check-in, issue their boarding pass and self-board their flights, check the status of their flight, get actual arrival and departure times of ET flights and remain connected and informed throughout their journey in real-time.
As a customer focused airline,we are continuously working very hard to avail cutting-edge and user-friendly solutions that will improve our customers ‘overall experience and meet their ever-increasing expectations.”
Customers will enjoy 10% discount on all bookings made through Ethiopian Mobile App.
Click on the link below to download your Ethiopian Airlines Application.
About Ethiopian
Ethiopian Airlines (Ethiopian) is the fastest growing Airline in Africa. In its seventy plus years of operation, Ethiopian has become one of the continent’s leading carriers, unrivalled in efficiency and operational success.
Ethiopian commands the lion’s share of the pan-African passenger and cargo network operating the youngest and most modern fleet to more than 100 international passenger and cargo destinations across five continents. Ethiopian fleet includes ultra-modern and environmentally friendly aircraft such as Airbus A350, Boeing 787-8, Boeing 787-9, Boeing 777-300ER, Boeing 777-200LR, Boeing 777-200 Freighter, Bombardier Q-400 double cabin with an average fleet age of five years. In fact, Ethiopian is the first airline in Africa to own and operate these aircraft.
Ethiopian is currently implementing a 15-year strategic plan called Vision 2025 that will see it become the leading aviation group in Africa with seven business centers: Ethiopian Express & Ancillary Services; Ethiopian International Services; Ethiopian Cargo Services; Ethiopian MRO Services; Ethiopian Aviation Academy; ET In-flight Catering; and Ethiopian Ground Services. Ethiopian is a multi-award winning airline registering an average growth of 25% in the past seven years. 
For more information about this press release, please contact:
Mrs. Aniley Eshetu
A/Manager Corporate Communications, Ethiopian Airlines
Tel :( 251-1)517-89-07/656/165/913/529

ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

ኢትዮጵያ በዘመናዊ ታሪኳ ታላቅ ተልዕኮ የሚኖረው ሀገራዊ የምምክር ኮሚሽን በተመለከተ ምን ያህል እናውቃለን?

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ኮሚሽን አማካሪ ኮሚቴ አባላትን ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል ባካተተ መልኩ አዋቅሯል። በእዚህ ጽሑፍ ስር የሚከተሉት ነጥቦች ምላሽ ያገኛሉ፡  ኮሚሽኑ እንዴት ተመሰረተ?  የኮሚሽኑ 11 ኮሚሽነሮች እንዴት ተመ...