የጦር ኃይል አንዲት ሀገር ለህልውናዋ እና እንደ ሀገር ለመቀጠልም ሆነ ላለመቀጠል ወሳኝ ከሆኑት ጉዳዮች ውስጥ ነው።ዓለም የሚመራው በሕግ እና በሥርዓት ብቻ ነው ብሎ ለማመን የሚያዳግተው ያለፉትን የዓለማችንን ሁኔታ ስንቃኝ ነው።ከኢንዱስትሪው አብዮት ወዲህ ኢትዮጵያ ዘመናዊ የጦር ኃይል መገንባት ከጀመረች ከአንድ መቶ ዓመት በላይ ሆኗታል።ይህ ማለት የአፄ ምኒሊክ የመጀመርያውን መደመብኛ ወጥቶ አደር (ወታደር) ከመሰረቱ ጊዜ ያለውን ታሳቢ ያደርጋል።በቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዘመን ኢትዮጵያ በኢጣልያ ወረራ በተለይ ከአየር ላይ በሚጣሉ የመርዝ ጋዝ መበለጧ በንጉሱም ሆነ በተራው ኢትዮጵያዊ ዘንድ እጅግ የሚያንገበግብ እና የትምህርት እና የስልጣኔን አስፈላጊነት ከሁሉም በላይ ቀዳሚ መሆን እንዳለበት ከነፃነት በኃላ እንዲታመንበት ያደረገ ጉዳይ ነበር።''በምድር የመጣው መች አቃተን በሰማይ በማናውቀው መንገድ መጣብን እንጂ'' የምትለው አባባል ከአዝማሪ እስከ ንጉሡ ድረስ የምትነገር አባባል እንደነበረች በወቅቱ የተከተቡ ፅሁፎች በተለያየ መንገድ ገልፀውታል።
የኢትዮጵያ ባህር ኃይል
የቀዳማዊ ሃይለስላሴ መንግስት ካደራጃቸው የጦር ክፍሎች ውስጥ በብቃቱ እና ከፍተኛ የተማረ የሰው ኃይል በመያዝ የአየር ኃይል እና የባህር ኃይል ሰራዊት ላቅ ያለ ስፍራ ነበራቸው።በተለይ የአየር ኃይላችን በመጀመርያ በእንግሊዞች ቀጥሎ በአሜሪካኖች በኃላ ላይ በስዊድን ያገኘው ስልጠና እና የባህር ኃይል ደግሞ ከኖርዌይ መንግሥታት በተደረጉ የስልጠና ድጋፎች በልምድም በችሎታም ብቃት ያለው የሰው ኃይል ለማፍራት ችለዋል።የቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዘመን አንዱ በጎ አጋጣሚው በእነኚህ ስልጠናዎች የተገኘው የሰው ኃይል በተከታታይ ጦርነት በመሳተፍ የሰው ኃይሉን አለማመናመኑ ነበር።
ቀዳማዊ አፄ ሃይለስላሴ ከቀድሞዋ ዩጎዝላቭ መሪ ጆስፕ ብሮዝ ቲቶ ጋር የባህር ኃይል ሲጎበኙ
በዘመነ ደርግ ከተመለከትን የኢትዮጵያ የጦር ኃይል በብቃት የሚታማ ደረጃ አልነበረም።ከምዕራባውያን ይገኝ የነበረው የመሳርያ እና የስልጠና ድጋፍ ወደ ምስራቅ አውሮፓ እና ወደ ቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት መዞሩ አንዱ አይነተኛ ለውጥ ሆነ። በዘመነ ደርግ የነበረው አንድ በጎ ነገር ከውስጡ የወጡ የሰራዊቱን ሕይወት የሚያውቁ የበታች መኮንኖች ስልጣን ላይ መምጣታቸው ብቻ ሲሆን ነገር ግን ለሰራዊቱ ምን አዲስ ነገር መጣ? ለሚለው ጥያቄ በእዚች ትንሽ ፅሁፍ ለማንሳት አልፈልግም።
ኮ/ል መንግስቱ ሃይለማርያም ለሰራዊቱ ንግግር ሲያደርጉ
ሆኖም ግን በዘመነ ደርግ ሰራዊቱ የነበሩበት ችግሮች ሶስት እንደነበሩ ማንሳት ይቻላል።እነርሱም
1/ የሰራዊቱ መኮንኖች በባህር ኃይልም ሆነ በአየር ኃይል የነበሩት ከፍተኛ ልምድ እና የትምህርት ዝግጅት ያላቸው ቢኖሩበትም ከፍተኛውን የመንግስት ስልጣን የያዙት የደርግ አባላት በመስመር መኮንነት እና በዝቅተኛ የትምህርት ዝግጅት ላይ በመሆናቸው ውሳኔዎች በትክክለኛ የወታደራዊ ሳይንስ ላይ እንዳይመሰረቱ ማድረጉ፣
2/ ከፍተኛ ልምድ እና የትምህርት ዝግጅት ያላቸው መኮንኖችም ሆኑ የሰራዊቱ አባላት ከደርግ ጋር በነበረው ቅራኔ (ለምሳሌ የግንቦት ስምንቱን በኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማርያም ላይ የተቃጣውን የመፈንቅለ መንግስት መጥቀስ ይቻላል) እንዲዳከም መደረጉ፣
3/ በሰሜናዊ ኢትዮጵያ የነበረው የተራዘመ ጦርነት ሰራዊቱ ያለውን አቅም በሙሉ በእዚህ ውግያ ላይ ለ አስራሰባት ዓመት እንዲያሳልፍ ማድረጉ የሚሉት የሚጠቀሱ ናቸው።
በ 1983 ዓም ኢህአዲግ-ወያኔ አዲስ አበባ ሲገባ የቀደመውን ሰራዊት በጠላትነት ከመፈረጅ ባለፈ የብዙዎች የጡረታ እና የሕክምና ወጪአቸው ተዘጋ።የሰራዊቱ አባላት በየመንገዱ ተመፅዋች ሆኑ።ከሁሉም የሚያሳዝነው ደግሞ ከሁለት ትውልድ በላይ በጦር ካምፖች አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ባሎቻቸው እና አባቶቻቸውን በጦርነቱ ያጡ እናቶች እና ሕፃናት ካለምንም ካሳ መኖርያ ቤታቸውን እንዲለቁ እየተደረጉ በአዲሱ ሰራዊት ቤተሰቦች ተተኩ።በእዚህም ሳብያ ዘመድ ያላስጠጋቸው የጎዳና ተዳዳሪ ሆኑ።ይህ ሁሉ ከሆነ ከሰባት ዓመት በኃላ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ሲነሳ የቀድሞ ሰራዊት አባላትን በመብራት የመፈለግ ሥራ ኢህአዲግ-ወያኔ ተያያዘው።በእስር ቤት የታጎሩ መኮንኖች ''ኑና አማክሩን'' ተብለው ከጥቅማጥቅም ጋር ተጠሩ።በሱዳን እና ኬንያ ሀገር ጥለው ከብዙ ፈተና በኃላ አሜሪካ እና ካናዳ የገቡ የቀድሞ የአየር ኃይል አብራሪዎች ልዩ ልዑክ እየተላከ ተለምነው እንዲመጡ ተደረጉ።ጥቂቶች ለሀገሬ ብለው መጡ።የተቀሩት ''ስልቻ ቀልቀሎ፣ቀልቀሎ ስልቻ'' ለሀገር አስቦ አይድለም ብለው ቀሩ።
አቶ መለስ ዜናዊ እጩ መኮንኖች ሲመርቁ
ጦርነቱ በአጭር ጊዜ የአስር ሺዎችን ሕይወት ቀጥፎ እንዳበቃ ኢህአዲግ-ወያኔ እንደገና ሥራ ጀመረ።በዘመነ ኢህአዲግ-ወያኔ ጊዜ የኢትዮጵያ ሰራዊት የገጠሙት ችግሮች በደርግ ዘመን ከገጠሙት በዓይነትም በይዘትም ይለያያሉ። ችግሮቹን በሶስት ነጥብ ማጠቃለል የሚቻል ይመስለኛል።
1/ የኢህአዲግ-ወያኔ ታጋይነትን ከብቃት በፊት ማስቀደም ይህም ከወያኔ የትጥቅ ትግል ጋር የነበሩትን በችሎታም ሆነ በትምህርት ዝግጅት ምንም ያህል ብቃት ባይኖራቸው እስከ ጄኔራልነት ማዕረግ እየሰጡ ከዓለም አቀፍ የወታደራዊ ሳይንስ አሰራር በወጣ መልክ መሄድ፣
2/ ሰራዊቱን ሕዝባዊ ለማድረግ አለመቻል።እዚህ ላይ በዋናነት የሚጠቀሰው የብሔር ተዋፅኦ ሁሉን ባማከለ አለመሆኑ ሲሆን እዚህ ላይ ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ከከፍተኛ መኮንኖች እስከ መስመር ድረስ ያሉትን ከአንድ አካባቢ በመጡ ሰዎች መሙላት እና ይህም ሃገራዊ ራዕይን በአካባቢያዊ ራዕይ እንዲተካ ያደረገ አደገኛ አዝማምያ ነው።
3/ ሰራዊቱ የቆመለት ቀዳሚው የሀገር ሉዓላዊነት ጥያቄ ከኢትዮጵያ ጥቅም አንፃር የሚወስዳቸው እርምጃዎች አለመታየታቸው።ኢትዮጵያ ከሉአላዊነት አንፃር የሚነሱ በእንጥልጥል ላይ ይሉ በርካታ ጉዳዮች አሁንም አሉ።ለምሳሌ ከሰማንያ ሚልዮን ሕዝብ በላይ በሃያ እና በሰላሳ ኪሎሜትሮች እርቀት ሆኖ ነፃ የባህር ወደብ አገልግሎት አለማግኘቱ እና ከሱዳን ጋር ያሉት የድንበር ጉዳይ በተዝረከረከ መልክ ሲታዩ እና አንዳንዴም ለሱዳን ተቆርሶ ሲሰጥ ዝም መባሉ የሚጠቀሱ ናቸው።
ሁለቱ የአስተሳሰብ ጥጎች
ይህንን ፅሁፍ እንድፅፍ ካነሳሳኝ ጉዳይ ሰሞኑን አራት የአየር ኃይል አባላት መንግስትን ከድተው ሄዱ የሚለው ዜና ነው።ይህ ጉዳይ ከሁለት ጥግ አንፃር ማየት ተገቢ ነው።የመጀመርያው ከላይ በተበላሸ መንገድ ላይ ያለውን የሰራዊቱን ችግር መቃወማቸው በጎ ተግባር መሆኑን ሲሆን ሌላው ጥግ ግን እንደ አትዮጵያዊ ሆነን ስናየው የእዚህ አይነቱ ውስጣዊ የፖለቲካ ችግራችን ከውጭ ሆነው ሀገሪቱን ለማዳከም ሌት ከቀን ለሚጥሩ ኃይሎች ያለው አንደምታ ምንድነው? የሚለው ነው።ሁል ጊዜ ከመጀመርያው ጥግ ብቻ ካየን ሌላውን እና የሁሉም የጋራ አደጋ የሆነውንም ጥግ እንዳይረሳ የሚል ስጋት አለኝ።ይህንን ስጋት ማንም ኢትዮጵያዊ እንደማይጠፋው አስባለሁ።የፖለቲካው ጭቅጭቅ ይዞን እንጂ ሁሉም የኢትዮጵያ ሰራዊት ነው።ጥቂቶች ከላይ ተቀምጠው አላማቸውን ሊጭኑበት ይችላሉ።እውነታው ግን ከእዚህ ይለያል ነገ ይህ ሁሉ ችግር እንደ ኩፍኝ ይወጣል።ኢትዮጵያ ግን በኢትዮጵያውነቷ ትቀጥላለች።ኢህአዲግ-ወያኔ የቀድሞውን ሰራዊት አለመቀበሉ ጥፋት ነው እያልን አሁን ያለውን ሰራዊት ኢትዮጵያዊ አይደለም ለማለት አይቻልም።
ቀደም ብዬ ከላይ ከጠቀስኩት የስጋት ጥጎች አንፃር የውስጥ ትግሉ የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ለውጭ ኃይሎች እንዳያጋልጥ ብለው የሚሰጉ አሉ።ስለእዚህም በተለይ የመገናኛ ብዙሃን የእዚህ አይነቱን የደህንነት ጉዳይ ሲዘግቡ ጥንቃቄ የሚሹ ሁኔታዎች መኖር እንዳለባቸው ማሰብ ይገባል።በእርግጥ ''ሕልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም'' የውጭ ኃይላት ማሰፍሰፍ አለ ተብሎ የእኩልነት እና የነፃነት ትግል ሊኖር አይገባም ማለት አይቻልም። በቅርቡ ከአየር ኃይል ለቀው ከወጡት መኮንኖች ውስጥ ሻለቃ አክሊሉ መዘነ ለኢሳት ራድዮ በተናገሩት ንግግር ግን መደምደም ይቻላል።''ኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት በቅርብ ሆነ በእሩቅ ከወያኔ የበለጠ እጅግ አስጊ ጠላት የላትም'' ሻለቃ አክሊሉ መዘነ።
ኢትዮጵያን እንደ ኢትዮጵያዊነቷ ለሚጠሏት
በመጨረሻም ከላይ ከሁለተኛው ጥግ ተመልክተው ለሚሰጉም ሆነ ከውጭ ሆነው ኢትዮጵያን እንደ ኢትዮጵያዊነቷ ለሚጠሏት፣ሀገሪቱን ለማጥፋት'' አጋጣሚ አገኘን'' ለሚሉ ከእዚህ በታች ያለውን መረጃ ማስቀመጡ አስፈላጊ ይመስለኛል።''Global fire power'' የተሰኘ ዓለም አቀፍ ተቅዋም በየዓመቱ የሀገሮችን የወታደራዊ አቅም እየመዘነ ደረጃ ያወጣል።በእዚሁ መሰረት የ 2013 እ ኤ አ ባወጣው ዘገባ ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ከግብፅ ቀጥሎ በሁለተኛነት ደረጃ ሲያስቀምጥ ከዓለም ከሰሜን ኮርያ እና ከእስፔን በላይ በ28ኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል።ድርጅቱ ሀገሮችን የሚ መዝንበት ከአርባ በላይ መስፈርቶች አሉት።ኢትዮጵያ አስር መንግሥታት በተቀያየሩ ቁጥር ደርግ እና ኢህአዲግ- ወያኔ እንዳደረጉት ''እያፈረሱ መስራት'' በሚለው መንገድ የነበራት የማፍረስ ተግባር ማቆም አለባት።እድገት ባለን ነገር ላይ መመስረትን የግድ ይላል።ይህ ክፉ ጠባይ ሊቆም ይገባዋል።ነገ የሚመጣው ለውጥ ዛሬ ያለንን አክብሮ የያዘ ክፉውን በክፉነት በጎውን በበጎነት የሚመዝን መሆን ይገባዋልና።
የ ''ግሎባል ፋየር ፓወር'' የ2013 የሀገሮች የመከላከያ ኃይል ደረጃ ዘገባ ከእዚህ በታች ይመልከቱ።
Countries Ranked by Military Strength (2013) by Country
Authored By Staff Writer | Last Updated: 1/2013
Our full ranked list puts the military powers of the world into full perspective.
The GFP Top 10:
1.United States2.Russia3.China4.India5.United Kingdom6.France7.Germany8.South Korea 9.Italy10.Brazil.
The GFP ranking makes use of over 40 factors to determine each nation's Power Index ("PwrIndx") score. From this score, the finalized ranking is generated. The factors are set within our algorithm which provides a fair canvas and allows smaller, technologically advanced nations to compete with larger, lesser-developed ones. Additionally, various bonuses and penalties are added for refinement. In the end, we hope it presents an unbiased ranking and realistic outlook on the potential conventional military firepower and strength of a given country for a given year. At the very least, this list can be used to stir healthy debate amongst visitors to GFP.
There are a total of 68 countries in the GFP database. Keep in mind that the final rankings are always being fine-tuned based on new data becoming available as well as feedback. The last major update occurred on 8/1/2013.
1 United States of America PwrIndx: 0.2475
2 Russia PwrIndx: 0.2618
3 China PwrIndx: 0.3351
4 India PwrIndx: 0.4346
5 United Kingdom PwrIndx: 0.5185
6 France PwrIndx: 0.6163
7 Germany PwrIndx: 0.6491
8 South Korea PwrIndx: 0.6547
9 Italy PwrIndx: 0.6838
10 Brazil PwrIndx: 0.6912
11 Turkey PwrIndx: 0.7059
12 Pakistan PwrIndx: 0.7331
13 Israel PwrIndx: 0.7559
14 Egypt PwrIndx: 0.7569
15 Indonesia PwrIndx: 0.7614
16 Iran PwrIndx: 0.7794
17 Japan PwrIndx: 0.7918
18 Taiwan PwrIndx: 0.8632
19 Canada PwrIndx: 0.8638
20 Thailand PwrIndx: 0.8979
21 Mexico PwrIndx: 0.9144
22 Ukraine PwrIndx: 0.9167
23 Australia PwrIndx: 0.9386
24 Poland PwrIndx: 0.9518
25 Vietnam PwrIndx: 1.0676
26 Sweden PwrIndx: 1.0841
27 Saudi Arabia PwrIndx: 1.1038
28 Ethiopia PwrIndx: 1.1725
29 North Korea PwrIndx: 1.1754
30 Spain PwrIndx: 1.1847
31 Philippines PwrIndx: 1.1871
32 Switzerland PwrIndx: 1.2275
33 Malaysia PwrIndx: 1.2457
34 South Africa PwrIndx: 1.2582
35 Argentina PwrIndx: 1.2961
36 Nigeria PwrIndx: 1.3441
37 Austria PwrIndx: 1.3695
38 Algeria PwrIndx: 1.4107
39 Syria PwrIndx: 1.4706
40 Venezuela PwrIndx: 1.4905
41 Colombia PwrIndx: 1.5049
42 Norway PwrIndx: 1.5138
43 Yemen PwrIndx: 1.5863
44 Denmark PwrIndx: 1.6116
45 Finland PwrIndx: 1.6121
46 Kenya PwrIndx: 1.6237
47 Singapore PwrIndx: 1.6284
48 Afghanistan PwrIndx: 1.6381
49 Greece PwrIndx: 1.6527
50 Romania PwrIndx: 1.6555
51 Chile PwrIndx: 1.7081
52 Belgium PwrIndx: 1.7266
53 Croatia PwrIndx: 1.7413
54 Serbia PwrIndx: 1.7501
55 Portugal PwrIndx: 1.7627
56 Jordan PwrIndx: 1.7775
57 United Arab Emirates PwrIndx: 1.8131
58 Iraq PwrIndx: 1.8133
59 Libya PwrIndx: 1.8428
60 Georgia PwrIndx: 1.8539
61 Mongolia PwrIndx: 2.0267
62 Paraguay PwrIndx: 2.1201
63 Kuwait PwrIndx: 2.1239
64 Nepal PwrIndx: 2.1578
65 Qatar PwrIndx: 2.4842
66 Lebanon PwrIndx: 2.5049
67 Uruguay PwrIndx: 2.5453
68 Panama PwrIndx: 3.0508
SOURCE- http://www.globalfirepower.com/countries-listing.asp