ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, August 27, 2015

ጥንታዊቷ እና የዓለም ቅርስ የሆነችው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በማየሽቷ ኦስሎ ትታያለች Ancient and world heritage Ethiopian church is now visible in Majorstuen church, Oslo. እናመሰግናለን ኖርዌይ!! Thank you Norway!! Tusen Takk Norge !!

 ማየሽቷ ቤተ ክርስቲያን (Majorstuen kirks)፣ Majorstuen Church 
 ማየሽቷ ቤተ ክርስቲያን (Majorstuen kirke)፣ Majorstuen Church

እናመሰግናለን ኖርዌይ!!

ጥንታዊቷ እና የዓለም ቅርስ የሆነችው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በማየሽቷ ኦስሎ ትታያለች።

ከመጪው ቅዳሜ ነሐሴ 23/2007 ዓም (ኦገስት 29/2015) ጀምሮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኦስሎ ቅዱስ ገብርኤል፣አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ቀድሞ ከነበረችበት ''ጋምለ ኦስሎ'' ወደ ''ማየሽቷ ካቴድራል'' ትገባለች።የቤተ ክርስቲያኗ የህንፃ ኮሚቴ ቤተ ክርስቲያኗ የእራሷ መሬት በግዥ እንዲኖራት እና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን የህንፃ ዲዛይን የያዘ ቤተ ክርስቲያን ለመስራት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ሲሆን እስካሁን በአጭር ጊዜ ውስጥ በእግዚአብሔር እርዳታ አስደናቂ እርምጃዎችን እየሄደ ለመሆኑ ብዙዎች ምስክር ናቸው። ኮሚቴው ላለፉት አምስት አመታት ቤተ ክርስቲያኗ ስትገለገልበት የነበረው ''ጋምለ ኦስሎ የሚገኘው ቤተ ክርስቲያን በመጥበቡ በኦስሎ ከተማ ከሚገኙት ካቴድራል ውስጥ አንዱ የሆነው ''የማየሽቷ ካተድራልን'' ቤተ ክርስቲያን እንድትጠቀም የኖርዌይ ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ኃላፊዎችን  ከአቡነ ኤልያስ ጋር ሆኖ በማነጋገር ካቴድራሉን እንድንጠቀም የኖርዌይ ከፍተኛ የቤተ ክርስቲያኒቱ ኃላፊዎች ከወራት በፊት መወሰናቸው ይታወቃል። በእዚሁም መሰረት ከመጪው ቅዳሜ ጀምሮ የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልግሎት በእዚሁ በማየሽቷ ካቴድራል ይሆናል።የቤተ ክርስቲያኑ አድራሻ  Kirkeveien 84, oslo; Majorstua,Oslo.  ''ኖርዌይ እናመሰግናለን!! ለኖርዌይ ሕዝብ እና ሰላም እንፀልያለን'' አንድ የቤተ ክርስቲያኑ አገልጋይ ዜናውን ስሰማ የተናገረው።አዎን! በዘመናችን ከሀገር ወጥተን በተገኘንበት ሀገር ሁሉ በጎ ያደረጉልንን ልናመሰግን ውለታቸውንም ልናስብ ይገባል።

Thank you Norway!!

Ancient and world heritage Ethiopian church is now visible in Majorstuen church, Oslo.


Ethiopian Orthodox Tewahedo St.Gebriel-Abune Teklehaimanot Church started its spiritual service in Majorstuen church,Oslo. It was known the church was providing full weekly service at Gamle Oslo for the past 5 years.The Norwegian church top leaders have negotiated with Ethiopian Orthodox Tewahedo church bishop Abune Elias some months back and allowed the church to provide its service in Majorstuen church starting from the coming Saturday,August 29/2015.

''Thank you Norway!! I pray for Norway and beloved people too to be save for long time and ever!!'' one Ethiopian Orthodox church service man explained his happiness, when he has heard as the church will shift from Gamle Oslo to Majorstuen church.

Tusen Takk Norge !!

 Ancient og verdensarv Etiopiske kirke er nå synlig i Majorstuen kirke, Oslo.

Etiopiske ortodokse Tewahedo St.Gebriel-Abune Teklehaimanot kirke startet sin åndelige tjeneste i Majorstuen kirke, Oslo. Det var kjent at kirken var å gi full ukentlig service på Gamle Oslo de siste 5 år.The norske kirketoppledere har forhandlet med den etiopisk-ortodokse kirke biskop Abune Elias noen måneder tilbake, og tillot kirken for å tilby sine tjenester i Majorstuen kirke fra den kommende lørdag august 29/2015.

'' Takk Norge !! Jeg ber for Norge og elskede folk for å være redde for lang tid og noen gang !! '' en Etiopisk-Ortodokse kirks service mann forklarte sin lykke, når han har hørt som kirken vil skifte fra Gamle Oslo til Majorstuen kirke.

ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
ነሐሴ 21/2007 ዓም (ኦገስት 27/2015)

Thursday, August 20, 2015

በአንደኛ ዙር 14 ሚልዮን ርሃብተኛ አምራቹ የኢህአዴግ/ወያኔ የትራንስፎርሜሽን እቅድ በሁለተኛው ዙር ስንት ሊያመርት አቀደ? እና አቶ ኃይለ ማርያም፣እውነት ለርሃብ መንስኤ የአየር ንብረት ለውጥ ብቻ ነው? (ጉዳያችን GUDAYACHN )

????????????????????

ሰሞኑን የአራት ኪሎ ቅምጥሎች በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ለሌላ ዙር የጥፋት ተግባር ለመሰማራት ደፋ ቀና እያሉ ናቸው።ርሃቡን በአየር ንብረት ሰበብ የጥፋት ተግባራቸውን ማጠብያ ሰበብ አድርገው በማቅረብ እና 14 ሚልዮን ርሃብተኛ ያፈራውን የመጀመርያ ትራንስፎርሜሽን እቅድ ተብዬ በሌላ ማደናገርያ ሁለተኛ ትራንስፎርሜሽን እቅድ በሚል ማደናገርያ ለመተካት።

በአንደኛው የትራንስፎርሜሽን እቅድ ውጤት መሰረት 14 ሚልዮን ርሀብተኛ አመረታችሁ። በሁለተኛውስ ትራንስፎርሜሽን እቅድ ስንት ርሀብተኛ ልታፈሩ አቀዳችሁ? 

የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ጧት ማታ ኢትዮጵያ አደገች እያለ እንደሚለቀው ተራ ፕሮፓጋንዳ ሳይሆን ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የ2015 ዓም እ አ አቆጣጠር የሰው ልማት ሪፖርት የሚያሳየው ከ186 የዓለም ሃገራት ውስጥ ኢትዮጵያ  173ኛ መሆኗን እና ከአብዛኛዎቹ የሳሃራ በታች ካሉ ሃገራት አንፃርም መጨረሻ ላይ መሆኗን ነው። ''Even though Ethiopia is one of the 10 countries globally that has attained the largest absolute gains in its HDI over the last several years, it still ranks 173rd out of 186 countries in the latest UNDP Human Development Report.'' UNDP National Human Development Report 2015 Ethiopia.

ይህንን ውርደታችንን ለእሩብ ክ/ዘመን ማሻሻል ያልቻለው ወያኔ በምርጫው 100% አሸነፍኩ እያለ አይን ያወጣ ፕሮፓጋንዳውን በሚነዛባት ሀገር ለሌላ ድህነት ሕዝቡን ለመዳረግ ''ሁለተኛ የትራንስፎርሜሽን እቅድ'' እያለ ማደናገር ይዟል።እውነታው ግን ከቅኝ ግዛት ከተላቀቁ ሃገራት አንፃር ሲታይም በካድሬ ምሁር ነን ባይ እቅድ የሚነደፍልን እኛ በብዙ ደረጃ ወደኃላ የቀረን መሆናችንን ነው።ለምሳሌ በ 2014 እአውሮፓውያን አቆጣጠርም በወጣው ዘገባ መሰረት አንዳችም ለውጥ አለማሳየታችን የዘንድሮው የተባበሩት መንግሥታት ዘገባም ያሳያል።በእዚህም መሰረት- 
ሱዳን  በሰባት ደረጃ ቀድማን 166ኛ፣
ጋና በሰላሳ ሰባት ደረጃ ቀድማን 138ኛ፣
ኬንያ በሃያ ስድስት ደረጃ ቀድማ 147ኛ፣
ዑጋንዳ በዘጠኝ ደረጃ ቀድማ 164ኛ፣
ናሚብያ በአርባ ስድስት ደረጃ ቀድማን 127ኛ፣ይቀጥላል። ዝርዝሩን ይህንን በመጫን ይመልከቱ። 

እውነታው ይህ ሆኖ ነው እንግዲህ የመጀመርያው ትራንስፎርሜሽን እቅድ ተብዬ ጥቂት የስርዓቱን ሰዎች በሀብት ማዕበል ውስጥ መክተቱ እና ነውራቸው ለዓለም አደባባይ ተርፎ በለንደን አየር መንገድ ሳይቀር በእዚህ ሳምንት መጀመርያ በዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች እንደተዘገበው ከ5 ሚልዮን የእንግሊዝ ፓውንድ በላይ በግለሰቦች ቦርሳ ተይዞ ሲወጣ እየታየ አቶ ሃይለማርያም ''አይናቸውን በጨው አጥበው'' ስለ ''ሁለተኛው ትራንስፎርሜሽን'' እያሉ መስበክ ጀምረዋል።ስለሀገር አስተዳደርም ሆነ ስለልማት አንዳች በማያውቁ የካድሬ ስብስብ የተዘጋጀው ሁለተኛው ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ኢትዮጵያን ለበለጠ መቀመቅ ለመክተት ካልሆነ በቀር ለኢትዮጵያ ሕዝብ አንዳች የማይፈይድ ለመሆኑ ብዙ እማኝ ምክንያቶችን ማቅረብ ይቻላል።


ኢትዮጵያን የሚያህል በርካታ የተማረ የሰው ኃይል ያላትን ሀገር ምሁራኑን በእስር ቤት አጉራችሁ የቀረውን ከሀገር አሰድዳችሁ ከመሰል ካድሬዎቻችሁ ጋር የአምስት ዓመት እቅድ እያላችሁ ስትዘባበቱ መስማት በእራሱ የሀገሪቱን የውርደት ደረጃ አመላካች ነው።የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት፣ፖለቲካ፣እና ማህበራዊ ሕይወት ዘረኛ ለሆነ ርኩስ መንገዳችሁ እንዲመች እያደረጋችሁ መቀየሳችሁን እናንተ ብቻ የምታውቁት ከመሰላችሁ መሳሳታችሁን እወቁት።በወረደ አስተሳሰብ ውስጥ ተዘፍቃችሁ በኢትዮጵያ ስም በአደባባይ ላይ ስትናገሩ ከመስማት በላይ ምን ውርደት አለ? ሰሞኑን አቶ ኃይለ ማርያም የከሸፈውን ያለፈውን እቅድ እያድበሰበሱ ስለመጪው ማውራት ሰሞኑን የተያዘ አዲሱ ፋሽናቸው ሆኗል።ለመሆኑ የሚቀጥለውን የአምስት ዓመት እቅድ የሚቀይሱት ምሁራን ሳይሆኑ ካድሬዎች መሆናቸውን ''ሪፖርተር ጋዜጣ'' በአንድ ወቅት የዘገበውን መመልከት በእራሱ ነገሩ ሁሉ ''ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ'' መሆኑን ለመረዳት አያዳግትም።ለሌላ 5 አመታት የ90 ሚልዮን ህዝብን ዕጣ እንወስናለን ብለው ሁለተኛ ትራንስፎርሜሽን እቅድ እናቅድላችሁ ያሉንን ባለ ጊዜዎች ይህንን በመጫን ተመልከቱ። 

በልማት ጥናት ዘርፍ እቅድ አዘገጃጀት ልምድ ያላቸው ምሁራን እና የሀገሪቱን ሕዝብ ማወያየት 100% አሸነፍኩ ላለን እፍረተ ቢስ ምኑ ነች?  ከሁለት ሳምንት በኃላ ኢህአዴግ አዲስ እቅድ አወጣ ብለው እየተዘጋጁ እና መስከረም ላይ ምክርቤቱ አፀደቀው ሊሉን አፋቸውን እያሟሹ ባለበት ወቅት ሕዝብ አወያየን ለማለት አቶ ሃይለማርያም ዛሬ ነሐሴ 13/2007 ዓም ኢቲቪ ላይ ቀርበው ግራና ቀኛቸውን ያልለዩ ምልምል ካድሬዎች ሰብስበው በሁለተኛው ትራንስፎርሜሽን እቅድ ላይ ተወያዩ የሚል ፌዝ አይሉት ቀልድ ማስደመጣቸው ነው።''ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ያፅናሽ'' ማለት የእዚህ ጊዜ ነው።የሀገር ሀብት በጥቂት ካድሬዎች ያውም በዘር እና በጎሳ በተጠራሩ እጅ መውደቁ ይዘገንናል።

አቶ ኃይለ ማርያም እውነት ለርሃብ መንስኤ የአየር ንብረት ለውጥ ብቻ ነው? 

የዓለም ምግብ ፕሮግራም (FAO) በድረ-ገፁ ላይ ''ለረሃብ ምክንያት የሚሆኑት ምክንያቶች ምንድናቸው? '' በሚል ርዕስ ስር ባሰፈረው ጥናታዊ ፅሁፍ ላይ የአየር ንብረት መዛባት አንዱ ምክንያት እንጂ ዋናው አለመሆኑን ያብራራል።በዓለም አቀፍ የልማት ጥናት ባለሙያዎች ገለፃ መሰረት ርሃብ ሰው ሰራሽ ክስተት እንደሆነ ያስረዳሉ።ይህ ማለት ግን የአየር ንብረት መዛባትን የሰው ልጅ ያስተካክለዋል ማለት ሳይሆን ከአየር ንብረቱ መዛባት በላይ የመንግስት  ቸልተኝነት እና ከሁሉም በላይ የተዝረከረከ አሰራር ውጤት መሆኑን የዓለም ምግብ ድርጅት ይገልፃል።

በእዚህም መሰረት በዓለም ምግብ ድርጅት ማብራርያ መሰረት የርሃብ ምክንያቶች በርካታ መሆናቸውን እና በዋናነት ግን ስድስት መሆናቸውን ይገልፃል። በቅድምያ ፅሁፉ በመግቢያነት የሚይስቀምጠው ነጥብ ''ዓለም ለ7 ቢልዮን የዓለማችን ሕዝብ በቂ ምርት ያመርታል'' በማለት ይጀምርና ስድስቱን በአንድ ሀገር ላይ ርሃብ የሚከሰትባቸውን ምክንያቶች ይዘረዝራል።

1/ ድህነት (Poverty trap)

2/ በእርሻ ላይ በቂ መዋለ ንዋይ አለመመደብ ( Lack of investment in agriculture)

3/ የአየር ንብረት ለውጥ ( Climate and Weather)

4/ ጦርነት እና የህዝብ ከስፍራው መፈናቀል (War and displacement)

5/ ያልተረጋጋ የምግብ ገበያ ( Unstable Market) 

6/ የተረፈ ምግብ ብክነት ( Food Wastage)
ዝርዝሩን ለማየት ይህንን ይጫኑ።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በሚልዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የርሃብ አደጋ እንዳንዣበበባቸው በዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች መዘገቡ ይታወሳል።አቶ ኃይለ ማርያምን ለናሙናነት ያስቀመጠው የወያኔ መንግስት ግን ለሕዝቡ ትክከለኛውን የአደጋውን ጥልቀት ከማስረዳት ይልቅ ''ድርቅ በአሜሪካም፣አውስትራልያም አለ'' እያለ ከመግለፅ ያለፈ ተግባር ሲፈፅም አይታይም።የሰው ሕይወትን የማዳን ሥራ ከመስራት ይልቅ የማደናገርያ ቃላትን መደርደር ከተጠያቂነት አይድንም።አቶ ሃይለማርያም የድርቅ መንስኤ የአየር ንብረት መዛባት ብቻ እንደሆነ አድርገው የገለፁበት ንግግር ባለፈው ሳምንት ስሰማ አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚናገረው ንግግር አይመስልም።በሃያ አንደኛው ክ/ዘመን ላይ ተቀምጠው ህዝብን ለማታለል ለሚታትር ያውም በጠቅላይ ሚኒስትር ደረጃ የተቀመጠ ሰው ከማየት የበለጠ ምን ያሳፍራል? 

ከላይ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከዘረዘራቸው ምክንያቶች ውስጥ አምስቱ የማን ተግባራት ናቸው? ለአቶ ሃይለማርያም እና ለአራት ኪሎ ቅምጥል ባለስልጣናት የሚቀርብ ጥያቄ ነው።የተረጋጋ የምግብ ገበያ መፍጠር የማን ሥራ ነው? የህዝብ መፈናቀልን መከላከል የማን ሥራ ነው? (አፈናቃዩ በመንግሥትነት የተሰየመ መሆኑ ደግሞ ሌላው አስደንጋጭ ጉዳይ መሆኑን ሳንረሳ)፣ጦርነት እና የጦርነት ስጋት እንዳይኖር ማድረግ የማን ሥራ ነው?  በእርሻው ዘርፍ ላይ በቂ መዋለ ንዋይ እንዲኖር ማድረግ የማን ሥራ ነው? ድህነትን መቀነስ የማን ሥራ ነው?  

ባጠቃላይ ኢህአዴግ/ህወሓት የሩብ ክ/ዘመን ተግባሩ ከበቂ በላይ ማንነቱን እና ሀገር የመምራት ደካማ አቅሙን ብቻ ሳይሆን በመጪው ዓመታት ኢትዮጵያን ሊከታት ያሰበበት ትልቅ አዘቅት መጠን በትክክል እየታየ ነው።የመጀመርያ፣ሁለተኛ ትራንስፎርሜሽን እያሉ ማደናገር ጊዜ ያለፈበት የፈዘዘ እቅድ ነው።ለርሃቡ የአየር ንብረትን ብቻ ተጠያቂ ማድረግ ደግሞ የበለጠ ምን ያህል ከሳይንስ የራቁ ቅምጥሎች እየመሩን እንዳሉ አመላካች ነው።በእርግጥ ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ ይህንን ስርዓት የምትገላገልበት ጊዜ መፋጠን እንዳለበት አእምሮ ላለው ሰው ሁሉ ከላይ የተጠቀሱት ሁኔታዎች በእራሳቸው በቂ ናቸው።


ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
ነሐሴ 14/2007 ዓም (ኦገስት 20/2015) 

Sunday, August 16, 2015

ሰበር ዜና - ''በምግብ እራሳችንን ችለናል'' ብለው የነበሩት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በኢትዮጵያ የድርቅ አደጋ ካለፈው የካቲት/2007 ዓም ጀምሮ እንደነበር ዛሬ እሁድ ነሐሴ 10/2007 ዓም አመኑ (የጉዳያችን አጭር ጥንቅር)

ፎቶ - የዓለም ምግብ ፕሮግራም

ኢትዮጵያ የድርቅ አደጋ እንደተጋረጠባት የሰሞኑ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መግለጫዎች እና የዜና አውታሮች ያረጋገጡት ሀቅ ነው።ይህ ሁሉ ሲሆን ግን የሁለት አሃዝ እድገት ላይ ነኝ ያለው የኢህአዴግ/ህወሓት ስርዓት ስለ ስጋቱም ሆነ ሊከሰት ስለሚችለው አደጋ አንዳችም ማብራርያ አልሰጠም።ይልቁንም በየካቲት ወር ላይ የህወሓት 40ኛ ዓመት በሚል በሚልዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከሀገሪቱ ካዝና ወጥቶ መባከኑ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።

ዛሬ ነሐሴ10/2007 ዓም ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ''የዲያስፖራ ድግስ ማጠቃለያ'' በተባለ ዝግጅት ላይ ከትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ድርቁን አስመልክቶ በተጠየቁት ጥያቄ ላይ የሰጡትን ምላሽ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በምሽት የዜና እወጃ መርሃ ግብሩ ላይ አቅርቦታል።በዘገባው መሰረት የድርቁ አደጋ ከየካቲት ጀምሮ የተከሰተ መሆኑን አቶ ሃይለማርያም በንግግራቸው ወቅት ጠቁመዋል።ቀደም ብለው  ስለድርቁ አንዳችም ያልተነፈሱት አቶ ሃይለማርያም በዛሬው ንግግራቸው ላይ ግን  ''ድርቅ ካሊፎርንያም አለ (ተሰብሳቢው አጨበጨበ)፣አውስትራሊያም ድርቅ አለ'' (አሁንም ግራ በሚያጋባ ሁኔታ አጨበጨበ በማጨብጨብ ችግር ይፈታ ይመስል)  አቶ ሃይለማርያም ቀጠሉ  ''ከየካቲት እስካሁን ድረስ ድርቁ ቢኖርም አንድም ሕፃን ወደ እርዳታ ካምፕ አልገባም '' ሲሉ ተደምጠዋል።ይህ የአቶ ሃይለማርያም ንግግር ስርዓታቸው ድርቁን ከአለፈው የካቲት ጀምሮ መከሰቱን በትክክል ያውቅ እንደነበር እና ለሕዝብ ይፋ ሳያደርግ መቆየቱን በማያሻማ ሁኔታ አመላካች ነው።

አቶ ሃይለማርያም በዛሬው ንግግራቸው ላይ ሁለት የተምታቱ ነገሮችም ተናግረዋል።በአንድ በኩል ድርቅ ቢኖርም ረሃብ አልተከሰተም የሚል መልእክት ካስተላለፉ በኃላ መልሰው ''ከፍተኛ የዝናብ መቆራረጥ በምሥራቃዊው ክፍል ከላይ እስከታች አጋጥሞናል መንግስት ውሃ በማሰባሰብም ጥረት እያደረገ ነው'' ሲሉ ግራ አጋብተውናል። በድርቅ ወቅት የትኛውን ውሃ ነው መንግስታቸው እያሰባሰበ ያለው? ''መንግስት ውሃ ለማሰባሰብ እየሞከረ ነው'' ማለት በራሱ ምን ማለት ነው? 

አቶ ኃይለ ማርያም ይህንን ይበሉ እንጂ እውነታው ግን የተለየ ነው።በምስራቃዊ፣ደቡባዊ እና ሰሜን ምስራቃዊ የኢትዮጵያ ክፍል በከፍተኛ የዝናብ እጥረት ውስጥ እንደሚገኙ እና በተለይ ከእዚህ ወር በኃላ አመታዊ የክረምቱ የዝናብ ወቅት ያላገኙ ሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች እንደሚጠቁ የሰሞኑ አለማቀፍ ዘገባዎች ያመለክታሉ።''ኦል አፍሪካ ዶት ኮም'' ባለፈው አርብ ነሐሴ 8/2007 ዓም ድርቁን አስመልክቶ ባወጣው ዜና ላይ የአፋር ክልል ብቻ ከ300 ሚልዮን ዶላር በላይ የአፋጣኝ እርዳታ ጥያቄ ማቅረቡን ይገልፃል።በእዚህ ሳምንት ታዋቂው የአሜሪካ ''ኤን ኤ ቢሲ'' የተሰኘው የቴሌቭዥን ጣቢያ ቀዳሚ አርእስቱ ውስጥ የኢትዮጵያ ረሃብ አንዱ እና ዋናው የዜና አርስቱ ነበር።''ኤን ኤ ቢሲ''  ቪድዮ ለመከታተል ይህንን ይጫኑ።

አቶ ሃይለማርያም ዝናቡን ያስቀረው ስርዓታቸው አለመሆኑን ለማስረዳት ''መሃላ ቀረሽ'' ንግግራቸው ተቀንጭቦ በቀረበበት ክፍል ላይ ''ዝናብን የአውስትራሊያ መንግስትም ማምጣት አይችልም'' በማለት ዝናብ አውርዱ የተባሉ የሚመስል ንግግር በመናገር ጉዳዩን ለማድበስበስ ሲሞክሩ ትዝብት ላይ ወድቀዋል።አሁንም ድርቁ የውሃ እጥረት ብቻ ሳይሆን የኢህአዴግ/ወያኔ የተሳሳተ የእርሻ  እና የመሬት ፖሊሲ በአንድ በኩል እና በሌላ በኩል ገበሬውን ከመሬቱ በማፈናቀል ገበሬው ዋስትና እንዲያጣ የማድረግ ተግባር ሁሉ ድምር ነው።ድርቅ በማንኛውም ሀገር ይከሰታል።ሆኖም ግን አንድ እራሱን መንግስት ብሎ የሚጠራ አካል የሚወቀሰው ለምን ዝናብ አላወረድክም ተብሎ እንዳልሆነ አቶ ኃይለ ማርያም ከጠፋቸው ሌላው አሳዛኝ ገፅታቸው ነው ማለት ነው።ጥያቄው ድርቅ ስመጣ ከሌላ የሀገሪቱ ክፍል ምርቱ ተገዝቶ ለተጠቃው ሕዝብ ማከፋፈል የአንድ መንግስት ግዴታ ሀሁ ነው።

እዚህ ላይ አቶ ኃይለ ማርያምን መጠየቅ የምፈልገው ''በምግብ እራሳችንን ችለናል'' የሚል ንግግር ከተናገሩ ገና አንድ ዓመት ማስቆጠሩ ነው።ዛሬ ስለ ድርቁ የሚነግሩን መልሰው ደግሞ ''ጥረት ይደረጋል'' እና ሌሎችም ቃላት የሚያሰሙን ለምንድነው? የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚራበው በዝናብ እጥረት ብቻ አይደለም የሀገሪቱን ገንዘብ ለህወሓት፣ኦህዴድ ወዘተ እያላችሁ በሚልዮን የሚቆጠር ሀብት ስለምታባክኑ እና ብሔራዊ ባንክ የስንዴ መግዣ መስጠት ስለማይችል ነው።የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚራበው በካድሬ የሚመራው መንግስትዎ ለችግሮች ቅንጣት ታክል መፍትሄ የማምጣት አቅም ያላቸው ስብስብ ስላልሆነ ነው።የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚራበው በሙስና የተተበተቡ ባለስልጣናት በሕግወጥ መንገድ ሀብት እያሸሹ ሀገሪቱ በእራሷ መንገድ እንዳትቆም ስላደረጉ ነው።በመጨረሻም ከአቶ ኃይለ ማርያም ንግግር በኃላ ኢቲቪ ለድርቁ የእንግሊዝ ሰንደቅ አላማ የታተመበት የእርዳታ እህል በማዳበርያ ተጭኖ ሲወርድ ያሳያል።ይህ የሆነው ''የዲያስፖራ በዓል'' ብለው ከሸራተን በውድ ዋጋ በመጣ ምግብ እና ውስኪ የሀገሪቱን ሀብት ሲያባክኑ በከረሙ ተመሳሳይ ሳምንት ውስጥ ነው።ይህ ብቻ አይደለም ይህ የሆነው ቀደም ብለው አቶ ሃይለማርያም ''ወዳጆቻችን የውጭ ሀገር መንግሥታት ''እስኪ እንያቸው'' ብለው  ዳር ቆመው እየተመለከቱን ነው'' ማለታቸው በተሰማ በደቂቃዎች ውስጥ ነው።


ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

ነሐሴ 11/2007 ዓም (ኦገስት 17/2015)

Monday, August 3, 2015

ሰበር ዜና -ኢህአዴግ/ህወሃት ያፀደቀው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ላይ የተለጠፈው ''ኮከብ'' ''ቢቢሲ'' የሰይጣን ተከታዮች ሰሞኑን አስመረቁት ባለው ሃውልት ሁሉም ላይ ተለጥፎ ተገኘ።(ፎቶዎቹን ይመልከቱ ጉዳያችን ''ሾት ስክሪን'')



ከእዚህ በፊት በተለያዩ ጊዜያት ብዙዎች ኢህአዴግ/ህወሓት በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ላይ የተለጠፈው ኮከብ የሰይጣን ተከታዮች በአርማነት የሚጠቀሙበት ስለሆነ መነሳት አለበት ብለው ሲሞግቱ መክረማቸው ይታወቃል።አንዳንዶች ጉዳዩ ከፖለቲካ ጥላቻ የሚመስላቸው ነበሩ።ሆኖም ግን ኮከቡ ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ላይ እንዲለጠፍ በውቅቱ የነበረው የኢትዮጵያ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያሳልፍ ከእምነቱ ጋር የተያያዘ ጉዳይ ይኖረዋል የሚል ምንም አይነት ግምት እንደማይኖረው ይታመናል።ሆኖም ግን ኮከቡ የተመረጠበት ሂደት እና ማን ይበልጥ እንደገፋፋ የታሪክ አጥኝዎች የራሳቸውን ጥናት ማድረግ ይችላሉ።በአደባባይ ከተገለጠው የብሔር በሄረሰቦች ጉዳይ ሌላ አጀንዳ ነበረው ወይ? የውጭ ኃይሎች ግፊት ነበር? ወይንስ ከባለስልጣናቱ በተለየ መልክ ጉዳዩን የገፋ ነበር? ይህ ሁሉ ለታሪክ አጥኚዎች የሚተው ነው።

አሁን ግን የዓለም አቀፍ ሚድያ በሆነው በ''ቢቢሲ'' ከሁለት ቀናት በፊት ቅዳሜ ሐምሌ 25/2007 ዓም (August 1,2015)  ''Decoding the symbols on Satan's statue'' በሚል አርእስት ስር በፎቶ አስደግፎ ያወጣው ዘገባ ኮከቡ በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ላይ ያለው ኮከብ መሆኑ በማያሻማ መልክ ይታያል።በመሆኑም ይህ ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ እና ክርስትናንም ሆነ እስልምናን በቀደምትነት የተቀበለች ሀገር ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ፈፅሞ የሰይጣን ተከታዮች አርማ ሊደረግበት አይገባም።ጉዳዩ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጠውም እና ኮከቡ ከኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ላይ እንዲነሳ የሚመለከታቸው የኢህአዴግ/ህወሓት ባለስልጣናት ሊጠየቁ ይገባል።

በነገራችን ላይ የዳዊት ኮከብ ተብሎ የሚጠራው ባለ ስድስት ጫፍ ሲሆን የሰይጣን ተከታዮች ግን በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ላይ እንዳለው ባለ አምስት ጫፍ ነው።ከእዚህ በታች ቢቢሲ በዘገባው ላይ ከለጠፈው ፎቶ ኮከቡን ብቻ ጉዳያችን ለይታ ከእዚህ በታች ታሳያለች።ዜናውን ከእዚህ በታች ባለው አርዕስት ''ጉግል'' ላይ ፈልጉት።ከእዚህ ባለፈ በዘገባው ላይ የተለጠፈውን ሃውልት ፎቶም ሆነ ሙሉ ዘገባ መዘገቡ ከሞራልም ሆነ ከሃይማኖት አንፃር አስፈላጊ ሆኖ አልተገኘም።የኮከቦቹን ብቻ  ''ስክሪን ሾት''ከእዚህ በታች ይመልከቱ። 


በጉዳዩ ላይ የዘገበው የቢቢሲ ዘገባ አርዕስት 

                           Decoding the symbols on Satan's statue

  •                        1 August 2015
  •  
  • F
    rom the section Magazine

ከላይ በተፃፈው አርዕስት ስር ቢቢሲ በዘገባው ከለጠፋቸው ፎቶዎች ውስጥ ኮከቡ ዋነኛ አርማ መሆኑን መረዳት ይቻላል።ከእዚህ በታችከሙሉ ፎቶዎች ውስጥ ኮከቡ የሚታይበት ክፍል ''ስክሪን ሾት'' ተደርጉት  ቀርበዋል።ተመልክተው የህሊና ፍርድዎን ይስጡ።





ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

Saturday, August 1, 2015

''ሉዓላዊነት ማለት በውጭ የሚኖር ኢትዮጵያዊን መብት ማስክበርም ጭምር ነው''።ለአውራምባው ድረ-ገፅ አቶ ዳዊት እና ለ''ቲጂ'' ''ዩቱዩብ'' አዘጋጅ አቶ መስፍን በዙ የተዘጋጀ ምላሽ (የጉዳያችን ማስታወሻ)



 ''በባህር ማዶ ኢህአዴግን የሚቃወሙ ከ9 እስከ 10 የሚሆኑ ናቸው።ብዙዎቹን በአካል አውቀዋቸዋለሁ።በታክሲ ሥራ ላይ የተሰማሩ ናቸው'' የአውራምባ ድረ-ገፅ አዘጋጅ አቶ ዳዊት

 ''ሰልፍ የሚወጡት ሰዎች እየተከፈላቸው ነው'' አቶ መስፍን በዙ የቲጂ ''ዩቱዩብ'' አዘጋጅ 

ኢትቪ ዶክመንተሪ ዛሬ ቅዳሜ ሐምሌ 25/2007 ዓም በውጭ የሚኖሩ የሀገራቸው ጉዳይ እንደ እሳት የሚያንገበግባቸው ኢትዮጵያውያንን የሚዘልፍ ፕሮግራም አስተላልፏል።ፊልሙ የአውራምባ ድረ-ገፁን አቶ ዳዊትን፣አቦይ ስብሐት፣መስፍን በዙ ሲናገሩ ያሳያል።አቶ ሬድዋን ልብስ ሊገዙ ሱቅ ሲገቡ የዘለፏቸውን ሰዎች እና ኢሳት ድንቁን ጋዜጠኛ መሳይ መኮንንን አክትቪስቶቹን ሲያወያይ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያሳያል።እዚህ ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢሳትን በኢቲቪ ሲመለከት ''አንበሶቹ መጡ'' ሲል በአይነ ህሊና ይታያችሁ።አቶ መስፍን በዙ አሜሪካ የሚገኘው የቲጂ ዩቱዩብ (ለአቅመ ቲቪ አለመድረሱን የማይስማማ የለም) ''ሰልፍ የሚወጡት ሰዎች እየተከፈላቸው ነው'' ብሉ ሲናገር  የኢትቪ ጋዜጠኛ ነጠቅ አደረገና ''ማን ነው የሚከፍላቸው?'' ሲል በርቀት ተሰማ (ኤዲት ሳይደረግ መሆን አለበት) አቶ መስፍን እንዳልሰማ አለፋት። የአውራምባ ድረ-ገፅ አዘጋጅ አቶ ዳዊት''በባህር ማዶ ኢህአዴግን የሚቃወሙ ከ9 እስከ 10 የሚሆኑ ናቸው።ብዙዎቹን በአካል አውቀዋቸዋለሁ።በታክሲ ሥራ ላይ የተሰማሩ ናቸው'' በማለት ለማቃለል ሲሞክር በጣም ያሳፍራል።

ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ አቶ ዳዊት ቀደም ብሎ ''በአሜሪካ ያሉት ተቃዋሚዎች  ከ 9 እስከ 10 የሚሆኑ ናቸው'' ያለውን እረሳው መሰለኝ  ''የሚቃወሙት በኢሳት ዙርያ ናቸው'' አለ እና የማይገናኝ ነገር ማውራት ጀመረ ''የኢሳት አማካሪዎች እነ ካሳ ከበደ  እና ሻለቃ ወልደ ጊዮርጊስ ናቸው'' በማለት አስቂኝ ንግግሩን ቀጠለ።አላማው ''ኢሳት የደርግ ነው'' የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ነው።እዚህ ላይ ልብ ማለት ያለብን ሁሉንም ነገር ደርግ ደርግ  እያላችሁ ደርግን የማያውቀውን ትውልድ ደርግን አስወድዳችሁት ይሄው ባለፈው ግንቦት በሊብያ ላለቁት ወገኖቻችን አዲስ አበባ ሰልፍ የወጡ ወጣቶች ''መንጌ ና!'' እያሉ እንዲዘፍኑ አደረጋችሁ።ኢሳት ደርግ ነው ካሉ ደርግ ጥሩ መንግስት ነበር።ብለው የሚያስቡ ኢህአዴግ ከገባ የተወለዱ ብዙ ወጣቶች አሉ።ዛሬ አቶ ዳዊት ኢሳትን የሚያማክሩ የደርግ ከፍተኛ ባለስልጣናት ናቸው ሲል ተሰማ።እዚህ ላይ ግን ህወሃት የቤላሩስ የአየር ኃይል አብራሪ እየቀጠረ ሀገር እየጠበኩ ነው የለን የለም እንዴ? በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት የደርግ መኮንኖች ያላቸውን በልመና ከየሀገሩ እየሰበሰበ አማክሩኝ ማለቱን አቶ ዳዊት አላወቁ ይሆን? ኢሳት የሚተዳደረው በሕዝብ የምመከረውም በሕዝብ መሆኑን በአንድ ወቅት አቶ ዳዊት በምድረ አሜሪካ ስለ ኢሳት ታላቅነት በአሜሪካ ለኢሣት በተዘጋጀ መርሃ ግብር ላይ እንዲህ ብሎ ነበር ''ኢሳት ሲጀምር ሀገር ቤት ነበርኩ።መንግስት የተገለበጠ ነበር የሚመስለው።ትልቁ ትግል መሆን በሚድያ ነው።ኢሳትን መደገፍ አለብን'' ብሎ ነበር።የአቶ ዳዊትን ከሁለት ዓመት በፊት ውዳሴ ኢሳት ያሰሙበት የፊልም ድርሳን ለመስማት ይህንን ይጫኑ።

የዛሬ የኢቲቪ ፕሮግራም ቀጠለ። አቶ ዳዊትም እንዲህ አለ '' እነኝህ (ተቃዋሚዎችን ማለታቸው ነው) ዜግነት የቀየሩ ናቸው እና ስለ ኢትዮጵያ ምን አገባቸው?''። ዳዊት አሁን 'ወጥ' ቢጤ እረገጠ።አቶ ዳዊት ጋዜጠኛ በመሆኑ  በመጠኑም ቢሆን የውጭውን ዓለም አይቶታል የሚል ያነበብኩ መስሎኝ ነበር። በምሳሌ ላስረዳው መሰለኝ።ለመረጃ ያህል በውጭ ሀገር ብዙ ኢትዮጵያዊ  ''የአምነስቲ ኢንተርናሽናል'' አባል አለ።እኔም እራሴ አባል ነኝ። አምነስቲ በርማ ለታሰረው ለማላውቀው ወንድሜ ድምፄን እንዳሰማ ይጠይቀኛል።ጠይቆኛልም።እኔም ሳላቅማማ ድምፄን አሰማለሁ፣ፔቲሽን እፈርማለሁ፣ ካስፈለገ ሰልፍ እወጣለሁ።ሌላ ምሳሌ ልጥቀስለት በኖርዌይ ቀይ መስቀል አባልነቴ ደግሞ ለሶርያ ሕፃናት በኦስሎ ጎዳና ''የሶርያ ሕፃናትን እርዱ'' እያልኩ ገንዘብ አሰባስቤ ሰጥቻለሁ።እና እንደ አውራ አምባው ዳዊት በአንዱ ክፍለ ዓለም ያለው ጉዳይ ሌላው ዓለም አያገባውም ሊለን ነው።ትውልደ ኢትዮጵያዊ ስለ በርማ ነፃነት፣ስለ ሶርያ ሕፃናት እልቂት አያገባውም ሊለን ነው።

የዳዊት በእርግጥ ደፈር ይላል።ዳዊት ትውልደ ኢትዮጵያዊው እትብቱ ስለተቀበረባት ኢትዮጵያ አያገባውም የሚል የትምክህት ንግግር ነው በማን አለብኝነት ያሰማን።አቶ ዳዊት ይህንን ዘመን አለፍነው እኮ! አሸባሪ እና ህዝብን በጎሳ የሚከፋፍል መንግስት ከስልጣን መውረድ አለበት ብሎ መጮህ ዓለም አቀፍ ግዴታን መወጣት ነው።አይደለም በደሉ የተፈፀመበት ሀገር ተወላጅ ቀርቶል ዳዊትን የምጠይቀው ኢህአዴግ/ህወሓት ለምንድነው አንዴ ሱማሌ፣ሌላ ጊዜ ደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያን ወጣቶች እየላከ በጦርነት የሚማግደው? በእዚህ አነጋገር ፕሬዝዳንት ኦባማም አፍሪካ ህብረት ላይ ቆመው የአራት ኪሎ ቅምጥሎችን ''ስልጣን ልቀቁ ለአዲሱ ትውልድ አስተላልፉ'' ብለው እስከአንገታቸው የነገሯቸው ኢትዮጵያዊ ሆነው እንዴ? አቶ ዳዊት ዓለም ተቀየረ። አራት ኪሎዎች በጎሳ ሲከፋፍሉት ዓለም አንድ ሆነ።እዚህ ላይ ፕሬዝዳንት ኦባማ ሉሲን ካለነገራቸው የጎበኙት የጎጥ ፖለቲካ ድንቡሽት ላይ እንደተሰራ  ለወቅቱ ባለሥልጣኖቻችን  ለመንገር መሆኑን መጠርጠሬን መደበቅ አልችልም።ሉሲን ከጎበኙ በኃላ በንግግራቸው ''ሁላችን ቅድመ ምንጭ ሉሲ'' በማለት የጎጥ ፖለቲካን ''አንድነት 101'' ኮርስ መስጠት እንደፈለጉ የገባን ገብቶናል። 
ዳዊት ግን አቶ ኦባማን እርስዎ አሜሪካዊ ነዎት ስለ አፍሪካ ምን አገባዎት ብሏቸው ይሆን? ይህ ማለት አቶ መለስ የሱማልያ ፓስፖርት ነበራቸው።ይህ ማለት በስህተት ነው ጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው ማለት ጋር እኩል ነው።

 በእዚሁ የቅዳሜው ኢቲቪ ፊልም ላይ ዋሽንግተን መጥቶ የተወቀሰ ባለስልጣን ሁሉ እንዳይቀር የተባለ ይመስል አቦይ ስብሃትም ታድመው ነበር። ለሚሉት ነገር ጠያቂ እና ተቆጪ  የሌለባቸው አቦይ ስብሐት ''እነኝህ ሰዎች (ተቃዋሚዎች ማለታቸው ነው) የሚናቁ አይደሉም'' ብለው ፈርጠም ብለው ተናገሩ።የአቦይ ይሻላል።ቢያንስ አቦይ በተደጋጋሚ መግለጫ የሚሰጡበትን ኢሳትን አልተሳደቡም። ተቃዋሚዎችን የሚናቁ አይደሉም ሲሉ ግን የተቃዋሚዎችን አቅም እንደሚፈሩትም ከፊታቸው ይታይ ነበር።

በእዚሁ ፊልም ላይ አስቂኝ የኢቲቪ አዘጋገብም ትመለከቱ እና አሁን ማንን ነው የሚያታልሉት? የሚያስብል ትዕይንት ታያላችሁ።ቴሌቭዝኑ የኦባማን ንግግር እየቀነጠበ ሲያቀርብ የአፍሪካ ህብረት ንግግራቸውን አንዲት ቃል አላሰማም።የአፍሪካ ህብረት የፕሬዝዳንት ኦባማ ንግግር አሁንም ድረስ በአምባገነኞቹ ጆሮ በምሽትም ያስገመግማል መሰል።በጣም ሲፈሩት ያስታውቃል።ኢቲቪ ፕሮፓጋንዳ አልተሳካለትም። አቦይ ስብሐት፣አቶ ሬድ ዋን እና የሱማልያው ክልል ፕሬዝዳንት ተጠያቂነት አለባችሁ ያሉ አክትቪስቶች በአሜሪካ ሆቴሎች በግልፅ ሲጠይቁ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አሳየው።የኢትዮጵያ ሕዝብ ደግሞ ''ለካ እዚህ አንበሳ ትመስላላችሁ ውጭ ስትሄዱ ግን...'' እንዲል አደረገው።በነገራችን ላይ አክቲቪስቶች የሀገራቸውን መሪዎች እና ባለስልጣናት በውጭ ሀገር ሲያገኙ ማሸማቀቃቸው በኢትዮጵያ የተጀመረ አይደለም በርካታ የአፍርካ እና የእስያ መንግሥታት ያጋጠማቸው ነው።የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ቡሽ ይልቁንም በአደባባይ ጫማ ተወሯሮባቸዋል።ሆኖም አንዳቸውም ተደፈርን ብለው አልፎቀሩም እንደ ኢቲቪ በውጭ የሚኖር ዜጋቸውን ዝቅ የሚያደረግ ፕሮግራም አላዘጋጁም።ውጭ የሚኖረውን ኢትዮጵያዊ በሆነ ባልሆነ ከመስደብ እና ዝቅ አድርጎ ከመመልከት (አቶ ሃይለማርያም ዶሮ ላደርስ ጀርመን ሄጄ ያሉትን ጨምሮ) እና የስድብ ናዳ ከማውረድ በሊብያ ለተሰዉት ወገኖቻችን ሰልፍ የወጡ የአዲስ አበባ ወጣቶች ይዘው የወጡት መፈክር መጥቀስ እፈልጋለሁ።''ሉዓላዊነት ማለት በውጭ የሚኖር ኢትዮጵያዊን መብት ማስክበርም ጭምር ነው''።  


ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
ሐምሌ 26/2007 ዓም (ኦገስት 2፣2015)

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሃራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሐራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)