ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, March 28, 2019

የአርበኞች ግንቦት ሰባትን ጨምሮ ስድስት በዜግነት ፖለቲካ የሚያምኑ ድርጅቶች ውሕደት ለፈፅሙ ነው ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድም ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።(የሁለቱንም መግለጫ ቪድዮዎች ይመልከቱ)

ጉዳያችን / Gudayachn
መጋቢት 19/2011 ዓም (ማርች 28/2019 ዓም)

በዜግነት ፖለቲካ የሚያምኑ ስድስት የፖለቲካ ድርጅቶች ማለትም የአርበኞች ግንቦት ሰባት፣ሰማያዊ ፓርቲ፣ኢዴፓ፣የጋምቤላ  ክልል ብሔራዊ ንቅናቄ፣የቀድሞው አንድነት ፓርቲ እና መኢአድ ናቸው።ዛሬ መጋቢት 19/2011 ዓም ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የቀድሞው አንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር አንዱዓለም አራጌን ጨምሮ የሁሉም ፓርቲዎች ሊቀመንበሮች መግለጫ ሰጥተዋል።በእዚሁም መሰረት ድርጅቶቹ ከተዋሃዱ በኃላ የምመሰረተውን ፓርቲ ስያሜ እና ዓርማ በግንቦት 1 እና 2 በሚሰጡ መግለጫዎች  እንደሚብራራ ተገልጧል።
በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት ከጋዜጠኞች ለተነሱ በርካታ ጥያቄዎች ምላሾች ሰጥተዋል።

የሁለቱንም መግለጫ ቪድዮዎች ከእዚህ በታች ይመልከቱ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ ለጋዜጠኞች የሰጡት ምላሽ 


የስድስቱ ፖለቲካ ድርጅቶች ውህደት አስመልክቶ የተሰጠው መግለጫ ቪድዮ
=============================================== 


ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Tuesday, March 26, 2019

የኢትዮጵያውያን የጋራ መድረክ በኖርዌይ ''የኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ተስፋዎቹና ተግዳሮቶቹ '' በሚል ርዕስ ህዝባዊ ስብሰባ በኦስሎ፣ኖርዌይ ጠርቷል።

ጉዳያችን / Gudayachn
መጋቢት 18/2011 ዓም (ማርች 27/2019 ዓም )

የኢትዮጵያውያን የጋራ መድረክ በኖርዌይ መንግስት ተመዝግቦ በሕጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀስ በዲሞክራሲያዊ ውይይቶች፣ሀሳቦች በነፃ በማንሸራሸር እና በሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ባልወገነ እና ሁሉንም የፖለቲካ እና የሲቪክ ድርጅቶች እኩል ዕድል በመስጠት የሚንቀሳቀስ ኢትዮጵያዊ መድረክ ነው።መድረኩ በመጪው ቅዳሜ መጋቢት 23/2011 ዓም (ማርች 30/2019 ዓም) ቦአስሎ በኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ተስፋዎቹና ተግዳሮቶቹ በሚል ርዕስ በጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ በርካታ የኦስሎ እና አካባቢዋ ነዋሪዎች እንደሚገኙ ይጠበቃል።

የቅዳሜው ውይይት ባብዛኛው ለሚታድሙ ኢትዮጵያውያን በፖለቲካው እድሎች እና ተግዳሮቶች ዙርያ እና መወሰድ በሚገባቸው እርምጃዎች ዙርያ ሃሳብ እንዲሰጡ እድሉን የሚያመቻች እንደሚሆን ለማወቅ ተችሏል። በስብሰባው ላይ ለመገኘት ዝርዝር መረጃውን እና የጋራ መድረኩን በተመለከተ ምንነት የሚያሳይ አጭር የቪድዮ ቃለ መጠይቅ ከስር ይመልከቱ።
አዘጋጅ = የኢትዮጵያውያን የጋራ መድረክ በኖርዌይ
የውይይቱ ርዕስ : - የኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ተስፋዎቹና ተግዳሮቶቹ
የውይይቱ ቀን = ማርች 30/2019
ሰዓት =14 ሰዓት ጀምሮ (ሰዓት ይከበራል)
የስብሰባው ቦታ= Veterinærhøgskole
Ullevålsveien 72,0454,Oslo
(የዘንድሮው የዓድዋ በዓል ያቀበርንበት አዳራሽ)
ሁላችሁም ተጋብዛችኃል!
የኢትዮጵያውያን የጋራ መድረክ በኖርዌይ
===================================
የኢትዮጵያውያን የጋራ መድረክ በኖርዌይ ዓላማው፣ተግባሩ እና አጭር ክንውኖች ዙርያ በመስከረም/2009 ዓም የተደረገ አጭር ቃለ መጠይቅ


Attachments area


ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Saturday, March 23, 2019

ኢትዮጵያን ከመጪው ቀውስ የምትታደጋት ታላቅ ምሽት በጉጉት እየተጠበቀች ነው።


ጉዳያችን/ Gudayachn
መጋቢት 15/2011 ዓም (ማርች 24/2019 ዓም)

ኢትዮጵያ ጥገናዊ ለውጥ ውስጥ ከገባች ድፍን አንድ ዓመት ሊሞላት አስር ቀናት ብቻ ቀርተዋታል።ሰሞኑን የተለያዩ ሚድያዎች የአንድ ዓመት ጉዞውን በመገምገም እና መጪውን በማመላከት ላይ ያተኮረ ስራዎች ላይ ተጠምደዋል።በእነኝህ ጉዳዮች ላይ ከእዚህ በፊት ብዙ ስላልኩበት እና ብዙዎች ብዙ ስላሉበት እዚህ ላይ በአንድ ዓመት ሂደት ላይ የምለው የለም። ኢትዮጵያ በቀጣይ በሚገጥማት ግልጥ እና የጠራ ሂደት ላይ ግን ብዙ ማለት ይቻላል።  

በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ በአራት አስተሳሰቦች እና ኃይሎች ውስጥ እንዳለች ግልጥ ሆኗል።

የመጀመርያዎቹ  በኢትዮጵያ ላለፉት 27 ዓመታት በህወሓት/ኢህአዴግ የተጫነው የጎሣ ፖለቲካ የሚያቀነቅኑ እና በከረረ መልክ ለማስቀጠል የሚሞክሩ ናቸው።እነኝህ ውስጥ የቀድሞው ህወሓት፣የአሁኑ ኦደፓ፣የኦነግ አንጃዎች  እና በደቡብ ክልል ውስጥ የተደባለቁ አመራሮች ሁሉ ይካተቱበታል።

በሁለተኛ  የሚጠቀሱት እንዲሁ ብሔርተኛ አስተሳሰብ የሚያራምዱ ነገር ግን በኢትዮጵያ የነበረ መሰረት ማናጋት እና አዲስ ትርክት መፃፍ አያዋጣም የሚሉ እና ፅንፍ የረገጡ ኃይሎች  ሕዝብ አፈናቅለዋል፣ለመጭዋ ኢትዮጵያም አደጋ ናቸው የሚሉ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ መከበር አለበት፣አሁን ያለው ሕገ መንግስት እኛን ያላሳተፈ ነው የሚሉ ናቸው።በእዚህ ውስጥ ዓማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)፣አዴፓ ውስጥ ያሉ ባለሙያ እና አንዳንድ አመራሮች ሁሉ ይገኙበታል።

ሶስተኛው ተጠቃሾች ደግሞ ላለፉት 27 ዓመታት ኢትዮጵያ የገባችበት የጎሳ ፖለቲካም ሆነ አሁን በየትኛውም መልኩ በተለያዩ ቡድኖች እና ፓርቲዎች የሚራመደው የጎሳ ፖለቲካ ኢትዮጵያን የሚያጠፋ እና ወደ ለየለት የእርስ በርስ ጦርነት የሚከት ስለሆነ ፈፅሞ ተቀባይነት የለውም። ፖለቲካ ብሎ የጎሳ ፖለቲካ ማራመድ ፈፅሞ አይቻልም ምክንያቱም ፖለቲካ በተፈጥሮው ሁሉን አቀፍ እንጂ የእዚህኛው ወገን ነኝ ብለህ ፖለቲካ ልታራምድ አትችልም።የሚል ሲሆን እንደ መፍትሄ የሚያቀርቡት የዜግነት ፖለቲካን ነው።አንድ ሰው ዜጋ በመሆኑ ብቻ ከየት መጣህ ሳይባል እንደ ግለሰብ እና የቡድን መብቱ ሊከበር ይገባል የሚል ሃሳብ ያቀርባሉ።ከእዚህ ሃሳብ ጋር የሚስማሙት እና ዋነኛ ተጠቃሽ በቅርቡ ወደ ፓርቲነት እንደሚቀየር ያስታወቀው የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ነው። 

አራተኛው እና ከላይ ከተጠቀሱት ፖለቲካዊ አስተሳሰቦች እና አደረጃጀቶች ጋር ልንዘለው የማንችለው እና እራሱን የቻለ ቅርፅ ያልያዘው (ፍኖተ ካርታ ስላልወጣ) የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖለቲካ ዕሳቤ ነው።ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መጋቢት 24/2010 ዓም በመንበረ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ከተሰየሙ በኃላ በመጡበት በቀድሞው ኦህደድ የዛሬው ኦዴፓ (ምርጫ ቦርድ ገና አልመዘግብኩትም መጥቶ ይመዝገብ ብሏል) አስተሳሰብን ሙሉ በሙሉ እያስፈፀሙ ነው ብሎ መናገር አይቻልም።ከእዚህ ያልቅ እርሳቸውም በባዛኛው በኢትዮጵያዊነት ንግግሮች በታጀበ የፖለቲካ ስሪት እንደሚያምኑ የሚገልጥ ግን ሁሉን አቀፍ የሆነ ''መደመር'' በሚል ዕሳቤ ውስጥ የሚያጠነጥን ፖለቲካ ይዘው ወጥተዋል።

ይህ መደመር በተግባር ላለፉት አንድ ዓመታት ሲታይ በርካታ መልኮች እና ፈፃፀሞች እንደታዩበት ዛሬ ላይ ሆኖ መናገር ይቻላል። አንዳንዶች ኢትዮጵያን በሂደት ወደ አንድ የሚያመጣ ነው ሲሉ፣ሌሎች በተግባር  የበለጠ ለፅንፈኛ የኦህዴድ (ኦዴፓ) እና ኦነግ ኃይሎች ቦታ የሚያደላድል ነው በማለት ያወሳሉ።በርግጥ በሁሉም መልክ ለመደምደም ጊዜው ገና ነው።ሆኖም ግን የሕግ የበላይነትን ማስከበር  ላይ በርካታ ግድፈቶች ታይተዋል።እዚህ ላይ ከአስራ አምስት በላይ ባንኮች በኦነግ ስም መዘረፉ፣በብዙ ሺህ የሚቆጠር ሕዝብ አሁንም በኦነግ ስም በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች አንፃር የተወሰደው እርምጃ እና ድርጊቱን ለመውቀስ ሳይቀር የዶ/ር ዓቢይ አስተዳደር ያሳየው እጅግ የበዛ መቅለስለስ በብዙ አስተችቶታል። 

ኢትዮጵያን ከመጪው ቀውስ የምትታደጋት ታላቅ ምሽት በጉጉት እየተጠበቀች ነው

ይህ ኢትዮጵያን ከመጪው ቀውስ የምትታደጋት ታላቅ ምሽት በጉጉት እየተጠበቀች ነው  የሚለው  የእዚህ ፅሁፍ ርዕስ የሃሳቡ መነሻም መድረሻም ነው።ጉዳዩ እንዲህ ነው ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ከላይ በተጠቀሱት ኃይሎች አስተሳሰብ ተወጥራ ለምርጫ በሰላም የመድረስ ዕድሏ ፈታኝ ነው።ምርጫው እራሱ በጎሳ እና በኢትዮጵያ የዜግነት ፖለቲካ መሐል ለመምረጥም የማይቻልበት ፍትሓዊ መደላድሉ ከአሁኑ ትንፋሽ ማጠር ይታይበታል።እዚህ ላይ ያለው አማራጭ ምንድን ነው? የሚለው ወሳኝ ጥያቄ ነው።መልሱ በአጭሩ ኢትዮጵያ በህወሓት/ኢህአዴግ ወለድም ሆነ በፅንፈኛ የኦነግ ኦዴፓ የጎሳ ፖለቲካ የምትራመድበት አንዳችም መንገድ የላትም። የችግሩ ክብደት አንዲት የዶሮ ላባ ቢጨመር የሚንኮታኮት ቁልል መስሏል።ከሁሉም በላይ የጎሳቸውን በደል ለማሰማት እና ጎሳቸውን ለመቀስቀስ ብቻ አልመው የተነሱ ሚድያዎች ጧት ማታ አዳዲስ ጎሳቸውን የሚቀሰቅስ አጀንዳ እየመዘዙ ባሉበት ወቅት መጪው ምርጫ ይደረጋል ማለት ለፅንፈኞች  ወንበር ለመስጠት እና ኢትዮጵያን አዲስ ትርምስ ውስጥ ለመክተት ካልሆነ በቀር ውጤት የለውም።ገና ተመርጠው ስልጣን ሳይዙ ትዕግስት አጥተው ከአዲስ አበባ ጀምሮ እስከ ወሎ ሁሉ የእኛ ንትርክ ውስጥ የገቡት ኃይሎችም ሆኑ በጎሳ ነፍጥ ሁሉን አንበርክከን እንገዛለን የሚሉት አዳዲስ ምልምል የጎሳ ፖለቲካ አራማጆች ሁሉም የነገ የኢትዮጵያን ተስፋ የሚያጨልሙ ናቸው።

ስለሆነም ኢትዮጵያ አንድ ከመጪው ቀውስ የምትታደጋት ምሽት ያስፈልጋታል።ይህች ምሽት ቆራጥ፣ኢትዮጵያዊ፣ትውልድ አዳኝ ምሽት ሆና በታሪክ የምትዘከር ምሽት ትሆናለች። በእዚህ ምሽት ላይ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እና ራድዮ የምሽት ሁለት ሰዓት ዜና ላማሰማት ይዘጋጃሉ።በዜናው ላይ ማንኛውም ሰው፣ፓርቲ፣ሚድያ፣ትምህርት ቤት፣ የሃይማኖት ድርጅት፣የንግድ ድርጅት፣ባንክ፣አከላለል ሁሉ በጎሳ እና በብሔር ስም ማድረግ፣ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጭ ንግግር መናገር፣ጎሳን መሰረት ያደረገ ማናቸውም የጥላቻ ንግግሮች ሁሉ፣ይህ ክልል የእኔ ነው ያኛው የእገሌ ነው ማለት፣ባጠቅላይ ላለፉት 28 ዓመታት ሲሰራበት የነበረው የጎሳ ፖለቲክ በሕግ ታግዷል የሚል ዜና ይሰማል።ይህ ሕልም አይደለም።ብቸኛው የኢትዮጵያን የአሁኑ ችግር የሚፈታ ወሳኝ ውሳኔ ነው።ጉዳዩ ከሕገ መንግስቱ ጋር ወዘተ የሚለውን እንደፈለገ ቅርፅ ስጡት፣ተንትኑት።ኢትዮጵያን መምራት የፈለገ መውሰድ ያለበት ወሳኝ እርምጃ ግን ይህ ነው።እዚህ ላይ የጎሳ ፖለቲካ አራማጆች ከፍተኛ ተቃውሞ ያስነሳሉ፣ኢትዮጵያን ወደ ባሰ ብጥብጥ የምወጽዳት የሚመስላቸው አሉ።ይህ ግን ከተወሰነ መንገጫገጭ ውጪ ኢትዮጵያን አንድ እርምጃ የምያስፈነጥራት፣ አብዛኛውን ሕዝብ በተለይ በጎሳ ምክንያት ስፈናቀል የኖረው የሱማሌ፣የደቡብ፣የዓማራ እና የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ ስለሆነ ከፍተኛ ደስታ ይፈጥራል።የንግዱ ማኅበረሰብ እና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሳይቀር በከፍተኛ ደረጃ አብሮን የሚቆምበት ትልቅ እና ወሳኝ አጀንዳ ነው። ዕርምጃው በአንድ ጊዜ የጎሳ ፖለቲካ አራማጆችን ባያከስም ሀገራዊ መብታቸውን ሳይነጠቁ እና ተከብሮ የማሰብያ የፅሞና ጊዜ የሚሰጣቸው ነው።

በመጨረሻም ይህችን ምሽት ማን ይሰራታል? የሚለው ጥያቄ ይነሳል።ዶ/ር ዓቢይ ይህንን ብቸኛ አዋጪ መንገድ ይወስዳሉ? ወይንስ ሁሉንም ለማስደሰት በሚል መሐል ላይ ሆነው ለማጫወት ይሞክራሉ? መልሱ ቀላል ነው።ዶ/ር ዓብይ ነገሮችን ተንትነው እንደሚያወሩት ለኢትዮጵያ አንድነት ከቆሙ ይህችን የምፈልጋትን ምሽት ያምጡ። ይህንን ማድረግ ካላመኑበት ግን የኢትዮጵያ ታሪክ በወርቅ ቀለም ታሪኩን የሚፅፍለት ከጦር  ሰራዊቱም ይምጣ፣ከትግራይ፣ከጎንደርም ይምጣ ከአፋር እና ሱማሌ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊቀበለው ዝግጁ ነው።የኢትዮጵያ ሕዝብ ከ150 ዓመት በኃላ አይደለም አካላቸውን ፀጉራቸውን አክብሮ በሙዜም በዛሬዋ ዕለት ከእንግሊዝ አስመጥቶ በክብር ያስቀመጠላቸው አፄ ቴዎድሮስ ጎንደር መወለዳቸው ሳይሆን ለአንድነቱ በድፍረት በፈንጅ ላይ የመራመድ ያህል ከዘመነ መሳፍንት የገላገሉት ጀግና ስለሆኑ ነው።ዛሬም ምርጫው አንድ ነው።እንደ አሮጌ የሹራብ ክር እየተረተረ የማያልቅ መዘዝ ይዞ ከሚመጣ የጎሳ ፖለቲካ በአንዲት ምሽት አዋጅ መገላገል ነው።ከአዋጁ በፊት ምንም ሥራ የለም እያልኩ አይደለም።ከእዚህ ውጪ ዶ/ር ዓቢይ ለውጡን ወደፊት ማስኬድ ይቸግራቸዋል። ያቺን ምሽት ማንም ያምጣት ማንም በእርግጠኝነት አትቀርም።ጥያቄው ብዙ ሕዝብ ሳያልቅ ያችን ምሽት ማምጣታችሁ ላይቀር መሽኮርመሙ ይብቃ። ኢትዮጵያን ከመጪው ቀውስ የምትታደጋት ታላቅ ምሽት በጉጉት እየተጠበቀች ነው።  


ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Tuesday, March 19, 2019

Thursday, March 14, 2019

Forced Eviction and Resettlement, the Jawar Factor and the Absence of International Scrutiny

By Dawit Wolde Giorgis
The former high commissioner and  military commander, Dawit Wolde Giorgis, has served with Ethiopian Government for over two decades.  He  was also an advisor to the UN mission at Rwanda peace and reconciliation program that is as soon as the genocide ended. Currently he is working with International peace and security field. 
The below article is his assessment regarding the extremist's  dangerous move in Ethiopia.
================
I was able to go back to my country after 33 years in exile in Dec of last year.  I have thanked the government and the people of Ethiopia for creating the condition that enabled me to go back home. I am an old man by any standard. My purpose in continuing to write about Africa and Ethiopia is to share the wisdom that can only be gained only through age and experience. I have both. I have no other motives. I know some people would not like some of the contents in this article. I have no right or capacity to prescribe any solution but I have certainly the obligation to present and critically analyze the  situation.
In 1984 during the great famine, the international community viciously condemned the Ethiopian government (dergue) for the resettlement program it conducted. It accused the regime  for gross human rights violation.  The case was discussed in the UN Human Rights Council and in the US Congress several times. Though the Relief and Rehabilitation Commission (RRC) I headed, was not in charge of the resettlement program, it was responsible for the provision of food to the settlers. The program was condemned for it’s political motivation and for moving the people against their will, though the stated goal of the project was humanitarian. It was to move people from drought affected, highly congested  and degraded lands to a more productive areas of Ethiopia, to Wolegga, to Gambela and some to Bale.  Looking back, it was indeed amazing how these settlers, mostly from Tigray, Wollo and Northern Showa  regions were received. People mostly Oromos were lined up on the streets to cheer and welcome the new settlers. They later helped in the construction of their new homes, invited them to their own homes until they adjusted and helped them in every possible way without any coercion from the government. There was no doubt in anybody’s mind that the welcoming was sincere and in the best tradition of Ethiopians.  Those living, remember those days as the best of ‘Ethipiaiwinet’ and indeed it was.
Some members of the international community reported that the program had political motives particularly for those who were moved from Tigray.  I have discussed the resettlement in general and this particular project in detail in my book ‘Red Tears page 281 to 308’.   There were many such experiments on resettlement in Ethiopia but none were done to change the demography of a given area.
The last one was the brainchild of Mengistu: moving 300,000 families (1.5 million people)  from Wollo and Tigray to South Western Ethiopia, in nine months.  The stated objectives were then purely humanitarian though Mengistu included his own political agenda in this project.  The international community was merciless and consistently and strongly condemned these as human rights violations and placed sanctions on the Ethiopian regime.  It created an uproar within the international community.
Human Rights Watch states:   “ The details of the implementation of the program varied from place to place; at its worst, it was a brutal form of counter-insurgency, at its best, a fierce attack on the independence of the peasantry….In addition to the direct human cost of the resettlement program, it involved enormous indirect human costs, by the diversion of resources. Resettlement sites and transit camps received priority allocations of relief food from the RRC.” [1]

The Paradox
There was a very close scrutiny of the activities of the government then, partly because it was the times of the cold war and partly because the government’s (dergue) policies were brutal in many aspects. Fast-forward, and Ethiopia went through a 27-year ordeal that included not only forced eviction and resettlement but also ethnic cleansing, crimes against humanity, suppression of freedom of speech corruption and torture unprecedented in Ethiopian history. And yet the world kept silent. Instead it went on talking tirelessly of the fake economic growth of the nation. Meles was the darling of the West and East and there were little told about what went on behind the prison walls and the booming constructions across urban Ethiopia.  It was not because the West did not know because there were several witnesses and independent sources  which confirmed  the crimes committed by the Ethiopian regime.
In 2017 Forbes Magazine wrote about the UN Secretary General Guterres, speaking from Addis at the 28th Summit of the African Union, described Ethiopia as a “pillar of stability” in the tumultuous Horn of Africa, praised the government of Ethiopia and asked the world to show “total solidarity” with the regime. This was being said as the economy of Ethiopia was collapsing under the weight of its own corruption and the wide spread anger and rebellion of the people.
Forbes (the global media company) asks: “Why, despite ever-increasing amounts of foreign support, can’t this nation of 100 million clever, enterprising people feed itself? Other resource-poor countries facing difficult environmental challenges manage to do so. Two numbers tell the story in a nutshell:
  1. The amount of American financial aid received by Ethiopia’s government since it took power: $30 billion.
  2. The amount stolen by Ethiopia’s leaders since it took power: $30 billion
The West, including the so-called global financial institutions like the World Bank and IMF kept on hammering on the myth that that Ethiopia’s economy was the fastest growing economy.

This government, under the  previous PM, had conducted forced resettlements and the international community did not give it serious attention. Human Rights Watch reports:  “Ethiopia’s government has been accused of forcing tens of thousands of people off their land so it can be leased to foreign investors. People are being forcibly relocated to new villages that lack adequate food, farmland and facilities. Ethiopia has already leased out more than 3.6 million hectares (8.8m acres) of land – an area the size of The Netherlands “ [2]
Somehow the Ethiopian government escaped the harsh scrutiny of the UN, the US and the international community despite the obvious corruptions, oppression and human rights violations that they now shamelessly condemn while keeping silent while Ethiopian people suffered for 27 years.

Forced Eviction and Resettlement
This year, when Ethiopia and the world were expecting improved governance under  PM Abiy and the Lemma Team, the world is once again witnessing gross human rights violations, approved and told publicly by the most senior people in the government.  Some of the incidents are happening right in front of the doorsteps of the international community in Addis. These are the forced evictions of thousands of people from the homes they have lived in for over a decade and the demolition of their homes reminiscent of the destruction of houses in the occupied territories of Palestine.
People also witnessed the forced resettlement of Oromo farmers and villagers from their ancestral lands to places they have never been, without their consent. The President of the Oromo region Lemma Megersa revealed publicly, boldly and arrogantly that the forced resettlement of 500,000 Oromos was necessary. It was stated that the idea of moving people without their consent to Addis and surrounding areas was to change the demography of Addis Abeba, in favor of the Oromo tribe. It outraged and shocked people particularly because it came from Lemma, the man who was in the forefront of unity and human rights in Ethiopia. The shock reverberated across the nation putting in doubt the agenda of the leaders whom Ethiopians were quick to reward with a saintly image.  Besides creating a wave of discontent this action was also  a clear and gross human rights violation.
The AU, whose head quarter is in Addis Abeba, the  international community, the UN and the US have not condemned this blatant violation of human rights of evicting people from their homes and moving people to remote parts of Ethiopia for political reasons. Forced evictions and forced resettlements are human rights violations under international law.

United nations Human Rights Commission states:
“ Forced evictions commonly result in people being pushed into extreme poverty and as such pose a risk to the right of life itself. They have also been found to be tantamount to cruel, inhuman or degrading treatment, particularly when carried out with violence or with discriminatory intent. During forced evictions, people are frequently harassed or beaten and occasionally subjected to inhumane treatment or killed. Women and girls are particularly vulnerable to violence, including sexual violence, before, during and after an eviction. Forced evictions may also result in indirect violations of political rights, such as the right to vote, if persons are rendered homeless. They can also have a profound detrimental psychological impact on evictees, in particular children, who have been found to suffer both short- and long-term effects.”[3]

The silence of the PM while thousands of people were being evicted and illegally resettled, put people’s mind in doubt as to whether he was really the head of the country. International law is clearly against this

The United Nations Human Rights Commission states:
“Forced evictions commonly result in people being pushed into extreme poverty and as such pose a risk to the right to life itself. They have also been found to be tantamount to cruel, inhuman or degrading treatment, particularly when carried out with violence or with discriminatory intent. During forced evictions, people are frequently harassed or beaten and occasionally subjected to inhumane treatment or killed. Women and girls are particularly vulnerable to violence, including sexual violence, before, during and after an eviction. Forced evictions may also result in indirect violations of political rights, such as the right to vote, if persons are rendered homeless. They can also have a profound detrimental psychological impact on evictees, in particular children, who have been found to suffer both short- and long-term effects”[4]
There are numerous UN resolutions and declarations that make forced evictions and resettlement a human rights violation. The Expert Seminar on the Practice of Forced Evictions (Geneva, 11-13 June 1997) establishes guidelines for the practice of forced evictions under the international human rights provisions and instruments.  The guidelines state:
“Forced evictions constitute prima facie violations of a wide range of internationally recognized human rights and can only be carried out under exceptional circumstances and in full accordance with the present Guidelines and relevant provisions of international human rights law.”
Forced and violent evictions and displacements are taking place throughout Ethiopia, and the demolishing of houses by the regional authority in Legetafo is just the latest example.  The dispute over the ownership of Addis Abeba, the attempt to change the demography of the capital city and the forced evictions are   the most serious problems  that can trigger a countrywide unrest.  The international  community has been largely silent.  It is possible that the silence of the international community can  be perceived by the Ethiopian government as a green light.   PM Abiy is not a man deserving a Nobel Prize for peace unless he comes out clean from these crimes.  There could either be tacit or explicit agreement. But certainly it happened on his watch. It must be remembered hundreds of thousands of people have signed a petition calling for Burmese leader Aung San Suu Kyi  to be stripped of her Nobel Prize  because of her country’s persecution of its Rohingya  Muslim minority.
For the sake of political stability, the Ethiopian government should rescind the policy of forced evictions, resettlement and land grabbing without due process of law.   If forced evictions continue unabated, Ethiopia can plunge into a civil war a political tensions rise

Hate Speech and Radicalization: The Jawar Factor.
The government has allowed extremists like Jawar Mohamed, the CEO of the Oromo Media Network (OMN), legally registered in Ethiopia to spread ethnic and religiously motivated hate speech.   PM Abiy’s tolerance of Jawar is perplexing.   Giving unchecked political power to extremists like Jawar can only further exacerbate the already tense political environment.   Some political observers suspect that there is either an explicit or implicit understanding between the PM and Jawar.  If that is the case, PM Abiy is allowing Jawar’s extreme voice to influence the youth, particularly in the Oromo region.  In any other country Jawar would have ended up in prison and prosecuted for crimes of incitements and possibly for terrorism.

OMN reminds one of Radio Télévision Libre des Milles  Collines (RTLM),  the hate radio that was instrumental in the Rwandan Genocide. “ It’s stated aim was “to create harmonious development in Rwandese society” but nothing could have been further from the truth, It was set up and financed by Hutu extremists to prepare the people of Rwanda for genocide by demonizing the Tutsi and encouraging hate and violence. Some people –including the Belgian ambassador and staff of several aid agencies –recognized the danger and asked for international help in shutting down the broadcast, but it was impossible to persuade Western diplomats to take it seriously. They dismissed the station as a joke” [5]
General Romeo Dallaire, the Canadian commander of the UN peacekeeping operation in Rwanda at the time of the genocide, said: “Simply jamming [the] broadcasts and replacing them with messages of peace and reconciliation would have had a significant impact on the course of events.” His advise was ignored and the UN and the international community regrets with great humility and embarrassment that, had it acted earlier the genocide would probably have not taken place.  There is a red line between freedom of expression and hate speech,  oratory and incitement. It is well established in the international legal instruments.
Security Council resolution 1624 (2005) further
“1. Calls upon all States to adopt such measures as may be necessary and appropriate and in accordance with their obligations under international law to:
(a) Prohibit by law incitement to commit a terrorist act or acts
(b) Prevent incitement to commit a terrorist act or acts
(c) Deny safe haven to any persons with respect to whom there is credible and relevant information giving serious reasons for considering that they have been guilty of incitement to commit a terrorist act or act
The UN resolution clearly leaves the responsibility to governments what to define what constitutes a terrorist act.  Many governments have defined it to use it
Based on these general guidelines the AU defines terrorism  as follows
Terrorist act means:
  • Any act which is a violation of the criminal laws of a State Party and which may endanger the life, physical integrity or freedom of, or cause serious injury or death to, any person, any number or group of persons or causes or may cause damage to public or private property, natural resources, environmental or cultural heritage and is calculated or intended to:

  • 3 (i) intimidate, put in fear, force, coerce or induce any government, body, institution, the general public or any segment thereof, to do or abstain from doing any act, or to adopt or abandon a particular standpoint, or to act according to certain principles; or

(ii) disrupt any public service, the delivery of any essential service to the public or to create a public emergency; or

(iii) create general insurrection in a State.
(b) any promotion, sponsoring, contribution to, command, aid, incitement, encouragement, attempt, threat, conspiracy, organizing, or procurement of any person, with the intent to commit any act referred to in paragraph (a) (i) to(iii). “
Though the previous regime in Ethiopia defined terrorism to stifle dissent and freedom of expression, there are ways for  democratic governments to define it in the genuine interest of the people. The implications of the absence of a universal definition of terrorism for legal purposes are wide-ranging.  I believe that Ethiopian government is conducting a study to replace the revamped pervious anti terrorism law. In doing so care will be taken so that the new law does not define terrorism in a manner that can restrict the freedom of people and violate the individual rights of expression, movement and actions. A suitable universal definition is elusive because different governments   have different definitions to suit their own particular politics and agenda. The UN and the AU, as indicated above,  have established the parameters and for now that should be sufficient to investigate people like Jawar Mohamed for terrorism or crime under the criminal law of the country or deport him to face the law in the US if he is a  US citizen.
A reasonable government should investigate all the activities, speeches, source of funds, affiliations   and their effects on current and future peace and stability and make him accountable through due process of law. Not doing so makes the government itself an accessory or a silent collaborator in what are believed to be  serious crimes.
END
[2] https://www.bbc.com/news/world-africa-16590416


ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

Monday, March 11, 2019

አዲስ አበባ በራሷ ፍልስፍና ነች።ፍልስፍናዋን የመጠበቅ ታላቅ ሀገራዊ እና ታሪካዊ አደራ ተጥሎባታል።

የአዲስ አበባ ጉግል ካርታ እኤአ 2019 ዓም 

ጉዳያችን / Gudayachn 
መጋቢት 3/2011 ዓም (ማርች 12/2019 ዓም)
==================================
በእዚህ ፅሁፍ ስር  የሚከተሉት ርዕሶች ይገኛሉ። 
አዲስ አበባ ማን ነች?
አዲስ አበባ የኢትዮጵያ መርገም እና መርገም ያረፈባት የኢትዮጵያ አሻራ
አዲስ አበባ በበቀል በትር ስር 
አዲስ አበባ ፍልስፍና ነች  እና 
- ቪድዮ (ከቦሌ እስከ ፒያሳ አራዳ እና ከጀሞ እስከ ፒያሳ አራዳ የአውራ ጎዳና ጉብኝቶች)
=================================
አዲስ አበባ ማን ነች?

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፊት ድረ ገፅ ላይ አዲስ አበባን ሲገልጣት እንዲህ የሚለው ፅሁፍ በቀዳሚነት ሰፍሯል።    
''አዲስ አበባ ተብላ የተሠየመችው እቴጌ ጣይቱ ኅዳር ፲፬ ቀን ፲፰፻፸፱ ዓ/ም ፍልውሃ ፊል-ፊል ወደሚልበት መስክ ወርደው ሳሉ ከዚህ በፊት አይተዋት የማያውቋት አንዲት ልዩ አበባ አይተው ስለማረከቻቸው ቦታውን ‹‹አዲስ አበባ!›› አሉ ይባላል። አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ስትሆን በተጨማሪ የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ እንዲሁም የብዙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቅርንጫፎችና ሌሎችም የዓለም የዲፕሎማቲክ ልዑካን መሰብሰቢያ ከተማ ናት። ራስ-ገዝ አስተዳደር ስላላት የከተማና የክልል ማዕረግ ይዛ ትገኛለች። አብዛኞቹን የሀገሩ ቋንቋዎች የሚናገሩ ክርስቲያኖች እና ሙስሊሞች የሚኖሩባት ከተማ ናት። ከባሕር ጠለል በ2500 ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኘው ከተማ ነች።'' ይላል።


 ፖላንዳውያኑ የታሪክ ፀሐፊዎች አንድርዜይ እና ማንቴል ኒየችኮ ''የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጀመርያው እስከ አሁን ዘመን'' በሚል በፖላንድኛ የፃፉትና በኃላ ወደጀርመንኛ በተተረጎመው መፅሐፍ ላይ አዲስ አበባ ቀደም ብላ በ13ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ ጀምሮ የኢትዮጵያ ነገስታት መቀመጫነት ትታወቅ እንደነበር ይገልጣሉ። በዓለማየሁ አበበ አማካይነት  ከጀርመንኛ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ በ2003 ዓም ባለ 592 ገፅ ሆኖ ታትሟል።በእዚሁ መፅሐፍ ውስጥ በገፅ 367 ላይ አዲስ አበባ ቀድማም ከሰባት መቶ ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ነገስታት መቀመጫ እንደነበረች እንዲህ በማለት ገልጠውታል። እንዲህ ይነበባል : -
‘’ አዲሱ የምንሊክ መቀመጫ የሆነው ስፍራ (አዲስ አበባ) ከ13ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ ጀምሮ የኢትዮጵያ ነገስታት ይቀመጡበት በነበረው ቀበሌ ውስጥ የሚገኝ መሆኑ ሊጠቀስ ይገባል’’

አዲስ አበባ የኢትዮጵያ መርገም እና በረከት ያረፈባት የኢትዮጵያ አሻራ 
አዲስ አበባ ከላይ ከተሰጡት ገለጣዎች በላይ ነች። አዲስ አበባ የኢትዮጵያን መርገምንም ሆነ ፀጋ ሁለቱም እንደክረምት እና በጋ የተፈራረቁባት ከተማ ነች።አዲስ አበባ ፋሺሽት ጣልያን በሶስት ቀናት ውስጥ ከሠላሳ ሺህ በላይ የሆኑ ነዋሪዎቿን በአካፋ እና በዶማ የተጨፈጨፉባት ከተማ ነች።አዲስ አበባ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ወጣት እና ጎልማሳ ነዋሪዎቿን በቀይ ሽብር በመሐል አስፋልት የተዘረሩባት ነች።አዲስ አበባ ታንክ በጎዳናዋ እየተሽከረከረ ''ኢትዮጵያ ትቅደም ካለምንም ደም'' ሲባል ፀሐይ ወጣ ብላ ጨፍራለች።አዲስ አበባ መሬት አርሳ አዝመራ አዝምራ ባታጭድም የካቲት 25።1967 ''መሬት ላራሹ'' ሲታወጅ ሆ! ብላ ወጥታ ዘምራለች።

አዲስ አበባ በታሕሳስ/1953 ዓም እና በግንቦት 8/1981 ዓም የጦር ሰራዊቱ በመንግሥታቱ ላይ ስያምፅ አብራ አምጣለች።አመፁን ያስነሱ የጦር መኮንኖች በንጉሱም ሆነ በኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም ሲገደሉ አብራ አምጣለች።አዲስ አበባ በዩንቨርስቲዋ ምሁራን አማካይነት የለውጥ መርሕ ጠንስሳ ወደ ሕዝብ አስርፃ፣መላው ኢትዮጵያጵያን ቀስቅሳ የለውጥ ሐዋርያ ሆናለች።አዲስ አበባ መሬት ላራሹ! ብላ ስታስተጋባ ስለ ዳር ሀገር ብቻ ሳይሆን ስለ አምቦ፣ቢሸፍቱ፣ሰላሌ፣ወለጋ፣ባሌ እና ሐረር ገበሬ ሁሉ የመሬት ባለቤትነት ብላ እንጂ ዘር እና ጎሳ ቆጥራ አይደለም።

አዲስ አበባ በ1997 ዓም በኢትዮጵያ ታሪክ ዓይነተኛ መልክ አለው የተባለውን ምርጫ በግንባር ቀደምትነት በመምራት ህወሓት/ኢህአዴግ መራሹን መንግስት ስልጡን በሆነ የምርጫ ካርድ በመዘረር ዓለምን ያስደነቀ እና የአውሮፓ ኅብረት ወክለው ለምርጫው ታዛቢነት የመጡትን ፖርቹጋላዊ ወ/ሮ አና ጎሚዝን በቁጭት ያንገበገበች፣ከምርጫው አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ሚያዝያ 30/1997 ዓም ሚልዮን ነዋሪዎቿን ይዛ አደባባይ ወጥታ ስለ ሰላማዊ ዲሞክራሲያዊ ትግል ፈር የቀደደች አሁንም አዲስ አበባ ነች።አዲስ አበባ በእዚህ በ1997 ዓም ምርጫ የሰጠችውን ድምፅ አቶ መለስ እና ስርዓታቸው ሲክዷት ልጆቿን ይዛ አደባባይ ወጥታ ተቃውማለች።በእዚህም የስርዓቱ ኃይል ከ193 በላይ ልጆቿን በአውራ ጎዳናዎቿ ላይ ከተረሸኑባት ገና አስራ አምስት ዓመት አልሞላትም።

አዲስ አበባ በበቀል በትር ስር 
አዲስ አበባ የነቃ፣የተጋ እና የበቃ የፖለቲካ፣ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሐብታዊ አቅም እንዳላት የተረዳው የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስት የጅራፍ እሾሁን ማስወንጨፍ የጀመረው አርባ የሚሆኑ የዩንቨርስቲ መምህሮቿን ካለምንም ምክንያት በማባረር ነበር።ከመምህራኑ ውስጥ በፋሺሽት ጣልያን አባታቸው የተገደሉባቸው ፕሮፌሰር አስራትን ጨምሮ በርካታ ምሁራን ከስራ ውጭ ተደረጉ።

በመቀጠል ከተማዋ ቀድማ በማታውቀው ደረጃ በሽሻ፣ጫት ቤት እና ሞራለ ቢስ በሆኑ የዳንስ ቤቶች እንድትወረር ስልታዊ ጥቃት ተደረገባት።በተለይ የጫት እና ሽሻ ቤቶች ሆን ተብለው ከትምህርት ቤቶች ጀርባ ሲከፈቱ ቀበሌዎች እና ክፍለ ከተሞች እያወቁ ምንም አይነት እርምጃ ሳይወስዱ እንዲመለከቱ ተደረጉ።ይህ የማደንዘዝ ሥራ በተለይ በሚያስደነግጥ  ደረጃ ቁጥሩ ያደገው ከ1997 ዓም ምርጫ በኃላ ነው።በ1997 ዓም ምርጫ ተከትሎ አቶ መለስ ከስርዓታቸው ጋር ቂም ይዘውባታል።ስለሆነም ከተማዋን ከፖለቲካዊ ሕይወቷ ለመነጠል ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም።ከእነኝህ የተንኮል ስራዎች ውስጥ አንዱ አዲስ አበባን ከኦሮምያ ክልል ጋር የማጋጨት ተንኮል ነበር።

በተለይ ቅንጅት አዲስ አበባ ሊረከብ ነው ሲባል የኦሮምያ ክልል ፅህፈት ቤቱን ወደ አዲስ አበባ እንዲያዞር ህወሓት ኦህዴድን አዘዘው።ኦህዴድ የቢሮ ዕቅዎቹን እና ሠራተኞቹን ይዞ ወደ አዲስ አበባ መጣ።አዳማ (ናዝሬት) የነበረው የኦህዴድ መስርያቤት ሰራተኞቹ በተለይ ከውሳኔው ድንገተኛነት የተነሳ አዲስ አበባ ቤት ለመከራየት ትልቅ ውክብያ ውስጥ ገብተው ነበር። ውክብያው በእዚህ አላበቃም ቀድሞም ቅንጅትን ከኦህዴድ ጋር የሚያጋጭ መስሎት የጠነሰሰው ስለነበር አዲስ አበባ በባለ አደራ አስተዳደር ላይ ስትወድቅ ኦህዴድ ተመልሶ እንዲወጣ ታዘዘ።በሺህ  የሚቆጠሩ የኦህዴድ ልዩ ልዩ ቢሮ ሰራተኞች ተመልሰው  ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ መልሰው በአዳማ (ናዝሬት) ቤት ለመከራየት ሌላ ውክብያ ውስጥ ገቡ።

አዲስ አበባ ፍልስፍና ነች 
ጉዳያችን አዲስ አበባ ፍልስፍና ነች ያለችው ዛሬ አይደለም። ከሦስት ዓመታት በፊት ''አዲስ አበባ ፍልስፍና ነች። ለፍልስፍናዋ ትዋደቃለች'' በሚል ፅሁፍ ስር ይህንኑ ሐሳብ በህወሓት/ኢህአዴግ ዘመንም ገልጣ ነበር።የአዲስ አበባን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ያላትን አቅጣጫ የመስጠት አቅም ማንም ሊያጣጥል አይችልም።በ1983 ዓም በአዲስ አበባ አራት ኪሎ ተቀምሞ በኢትዮጵያ ገጠሮች ገበሬውን ይዞ አዲስ አበባ የገባው ለውጥ የረጅም ጊዜ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ቀያሽ አዲስ አበባ ሳትገባው እና እርሷም ሳይገባት ሐያ ሰባት ዓመታት ብታሳልፍም አዲስ አበባ ዛሬም ንቁ ነች።አዲስ አበባ ባለፉት ሐያሰባት ዓመታትም ጉልህ የለውጥ ሐዋርያ ከአብራክዋ የውጡ ነበሩ።አንዱዓለም አራጌ፣እስክንድር ነጋ፣የዞን 9 እንቅስቃሴ፣ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ቡልቻ ደመቅሳ፣ብሩቱካን ሜደቅሳ፣ሲሳይ አጌና፣ርዕዮት ዓለሙ እና ሌሎችም ስርዓቱን በሰላማዊ ትግል ሐያሰባቱንም ዓመታት ወጥረው ለለውጥ ከሰሩ አዲስ አበቤዎች ውስጥ ናቸው።

አዲስ አበባ ፍልስፍና ነች።አዲስ አበባ በ1935 ዓም ጣልያን ከሀገራችን ተባርሮ ከወጣ እና የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከኦሜድላ በመቀጠል በከፍተኛ ብሔራዊ ስነ ስርዓት ተመልሶ ከተሰቀለ ጀምሮ አዲስ ዘመን ጋዜጣን ነፃነት በመጣበት ዓመት ማተም ጀምራ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ወደ ላቀ ደረጃ ያሻገረ እና የሚያሻግር ፍልስፍና ባለቤት ነች።የአዲስ አበባ ፍልስፍና የኢትዮጵያውያን ፍልስፍና ነው።የአዲስ አበባ ፍልስፍና የዘር ቀለም፣የጎሳ ድንበር የለውም።አዲስ አበባ ከሰሜናዊ እስከ ደቡባዊ እና ከምስራቃዊ እስከ ምዕራባዊ  ክፍሏ ከዶርዜ እስከ ከምባታ፣ከዓማራ እስከ ሐማሴን ኤርትራ፣ ከትግራይ አድዋ እስከ ሶዶ ጉራጌ፣ከሐረሪ እስከ ኦሮሞ፣ከአፋር እስከ ቤንሻንጉል ያሉ ኢትዮጵያውያንን ኢትዮጵያዊ በሚል አንድ ስሜት አሳፍራ ያኖረች ከተማ ነች።ይህ ሕብረ ብሔራዊ ነገር ግን ኢትዮጵያዊ ፍልስፍናዋ በወረቀት ላይ ብቻ ሳይሆን በመኖር እና የአኗኗር ዘይቤውንም በማሳየት ያስመሰከረች ነች።አዲስ አበባ ውስጥ አንዱ ብሔር ከሌላው ጋር ተጋጨ የሚል ዜና ተሰምቶ አይታወቅም።ይህ የአዲስ አበቤ የአብሮ የመኖር ፍልስፍና እንዲሁ የመጣ ሳይሆን የመጣ እንግዳዋን አስተምራ የመደመር ችሎታዋ ውጤት ነው።

አዲስ አበባ ኢትዮጵያዊ አድርጎ የመኖር ፍልስፍናዋ የመሳብ ኃይል ያለው እጅግ ከባድ ነው።አስራ ሰባት ዓመት በጫካ እና በረሃ ከርሞ የመጣ የህወሓት/ኢህአዴግ ሰራዊት ፀጉሩን አጎፍሮ እና ያደፈ ልብሱን አጥቦ በቤተ መንግስቱ አጥር ላይ አስጥቶ እና ''በረባሶ'' ጫማውን አድርጎ ሲመጣ፣ ልብሱን ቀይራ፣ሽፍን ጫማ አጫምታ፣ኮሮላ የጃፓን መኪና አስይዛ እና የከተማ መንገዶች ምልክቶች አስተምራ ወደ አዲስ አበቤ ኢትዮጵያዊ ፍልስፍና አጥምቃ ቦሌ እና ጃክሮስ ሰፈር አኑራ ሰው ያደረገች ነች አዲስ አበባ።አዲስ አበባ የለውጥ ሐዋርያ እንደመሆኗ ሁሉ ከ1997 ዓም በኃላ በስርዓቱ ላይ ለመነሳት ተቸግራ የቆየችበት መሰረታዊ ምክንያት ነበራት።ይሄውም በህወሓት ተንኮል እና የተሳሳተ ትውልድ በመፈጠሩም ጭምር የኢትዮጵያ ፖለቲካ በጎሳ በመከፋፈሉ አዲስ አበባ ሁኔታዎችን በአንክሮ ከመከታተል ባለፈ የጎላ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ተቸግራለች።ፍልስፍናዋ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ሜዳው ጎሳዊ ሲሆን ለአዲስ አበባ አይመቻትም።የኢትዮጵያ ጉዳይ የሚያነሳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ስመጣ ቀድማ ከፊት በመሰለፍ ግን አዲስ አበባ ነበረች።አዲስ አበባ በሚልዮን የሚቆጠር ልጆቿን ይዛ በመስቀል አደባባይ የተሰለፈች አዲስ አበባ ከኢትዮጵያዊ ፍልስፍናዋ ጋር ነበር።

የአዲስ አበባ ዘር አልባ እና ጎሳ አልባ ፍልስፍናዋ ለአሁኗ ኢትዮጵያ በእጅጉ ያስፈልጋታል።ኢትዮጵያን የማያውቁ የተወለዱበትን አካባቢ ብቻ ዓለም የሚመስላቸው የዋሃንን ኢትዮጵያ ምን ያህል ሰፊ እንደሆነች እና የሁሉም መሆኗን ለማሳወቅ የአዲስ አበባ ፍልስፍና ያስፈልጋቸዋል።የአዲስ አበባ ፍልስፍና ጎሳ አልባ ብቻ አይደለም።ይቅር ባይ እና ዓለም አቀፋዊ እሳቤንም የተላበሰ ነው።አዲስ አበባ ይቅር ስትል ፈጣን ነች።በ1997 ዓም ከአንድ መቶ ዘጠና ሶስት በላይ ልጆቿን የገደሉባት አቶ መለስ በሶስት ዓመት ውስጥ የኢትዮጵያ ሚሊንየም በሚሊንየም አዳራሽ ሲከበር የሀገር ልብስ አልብሳ በሱዳን ዘፈን አብራ የተጫወተች የትናንቱን ፈጥኖ የመርሳት ፍልስፍና ባለቤትም ነች አዲስ አበባ።አዲስ አበባ ስሟን ክዶ ''ፊንፊኔ'' እያለ የሚጠራትን ሲፈልግ እጁን ትንፋሽ እንዳጠረው ሕፃን እያወራጨ ''አዲስ አበባ በቀለበት ውስጥ አድርገን ማፈን እንችል ነበር'' እያለ ከአራት ሚልዮን በላይ ሕዝብን ሳህን ላይ እንደዘረገፈው ቆሎ የሚያየውን ጃዋር መሐመድ አዲስ አበባ ሲመጣ ድንጋይ ሳትወረውር፣የሁሉም ሃሳብ ይደመጥ ብላ እያየች እንዳላየች፣እየሰማች እንዳልሰማች ያሳለፈች ነች አዲስ አበባ ብቻ ነች። ይህ ብቻ አይደለም አዲስ አበባ የፅንፍ መስመሩ የወጣ እንደሆነ በትርክቱ የምታውቀው የኦነግ አመራር በባሌ ሳይሆን በቦሌ ሲመጣ አዲስ አበባ ኦነግን ለመቀበል ከሩቅ ገጠር ቦታዎች የመጡ ኢትዮጵያውያንን መንገድ ላይ ምግብ ደርድራ፣የሚጠጣ አዘጋጅታ ለእንግዶቹ ኢትዮያዊ ፍልስፍናዋን ያሳየች ከተማ ነች።ለእዚህ ደግነቷ ቡራዩ ላይ ሕፃናቷ ሳይቀሩ ቢታረዱባትም  አዲስ አበባ በቶሎ የተጎዱትን አክማ፣የሞቱትን ቀብራ፣እንባዋን አበሳ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ ሕይወትን አስቀጠለችው።

ከላይ የተጠቀሰው የአዲስ አበባ ቻይነት፣ታጋሽነት፣ኢትዮጵያዊ ደማሪነት እና ይቅር ባይ ፍልስፍናዋ ግን ገደብ የለውም ማለት አይደለም።ሁሉን ስለፍቅር ብታደርገውም በህልውናዋ ላይ የተረት ተረት ትርክት ይዞ ዱላ እና ገጀራ ይዞ ለሚፎክር ግራ ገብ ግን ቦታ የላትም።መጋቢት 1/2011 ዓም በሺህ የሚቆጠር የአዲስ አበባ ነዋሪ ወጣት በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና የአዲስ አበባ ነዋሪዎች አስተባባሪነት በባልደራስ ሆቴል በተጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ የተገኘው ሕዝብ ዋነኛ ብሶቱ የመሰረታዊ ኢትዮጵያዊ ፍልስፍናው መደፈር ነው።መደፈር ብቻ አይደለም።መኖር አትችልም፣እናስወጣሃለን፣ የሚሉ ስለ ትናንት ያላጠኑ እና ያላነበቡ፣ስለነገ ርዕይ ማስቀመጥ ያልቻሉ በአንድ የመንጋ አስተሳሰብ የሚመሩ ሲዝቱበት የማይነካውን ቀይ መስመር እንዳለፉ አመነበት። ስለሆነም የረጅም ጊዜ ፍልስፍናዋን ይዞ ተነሳች።

ባጠቃላይ አዲስ አበባ በአስራ ዘጠነኛው ክ/ዘመን መጨረሻ ለዓድዋ ዘማች ስንቅ ሰንቃ፣ታቦት አስይዛ ቸር ግቡ ብላ ንጉሷን የሸኘች፣በሐያኛው ክ/ዘመን መጀመርያ በፋሽሽቶች ከሠላሳ ሺህ በላይ ልጆቿን በመገበር የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ገፈት ቀማሽ የሆነች እና በእዚሁ ክፍለ ዘመን ውስጥ በኢትዮጵያ የነበረው ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊ እና ምጣናዊ ሐብታዊ ቅርፅ በመስጠት እና ለማም ከፋ አዳዲስ ሃሳቦችን ከዓለም አቀፍ ለውጥ ጋር በተናበበ መልኩ በማፍለቅ አዲስ አበባ የኢትዮጵያ የለውጥ ፍልስፍና ማዕከል ሆናለች።ይህ ፍልስፍናዋ መሰረታዊ መርሁ ደግሞ ኢትዮጵያዊነት እና ጎሳ አልባ ዕሳቤ ነው።አሁን አዲስ አበባ ይህንን ፍልስፍናዋን በልዩ ክብር የመጠበቅ እና በጎሳ ፖለቲካ ለተጎዳችውን ኢትዮጵያ የማስተማር ዘመቻ ከአዲስ አበባ ይጠበቃል።አዲስ አበባ በዙርያዋ ያለውን የተሳሳተ አስተሳሰብ እና ትርክት በጥቂት ፅንፈኞች እንዲይዝ የተደረገውን ወገን ወደ በጎ ዕሳቤ እንዲመጣ የአስተሳሰብ ለውጥ አምጥቶ ኢትዮጵያዊ ቤተኘነቱን እንዲያፀና በፍቅር የማስተማር ስራዋን በዕቅድ እና በመርህ ላይ በተመሰረተ መንገድ ማካሄድ ይገባታል።ይህ ማለት ግን ገጀራ ይዞ ለመምጣት ለሚያስብ በታኝ ፅንፈኛ ጋዜጠኛ እስክንድር እንዳለው ''ግፍ መስራትን እንጂ ግፈኛን አንፈራም'' ከማለት ሌላ አማራጭ የላትም።የአዲስ አበባ ኢትዮጵያዊ ፍልስፍና ይለምልም! 
================================////=======================
አዲስ አበባ ከቦሌ እስከ አራዳ ፒያሳ የአውራ ጎዳና ጉብኝት (ቪድዮ) 

አዲስ አበባ ከጀሞ እስከ ፒያሳ አራዳ  የአውራ ጎዳና ጉብኝት (ቪድዮ) 


ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Thursday, March 7, 2019

የኢትዮጵያ ፖለቲካ አልተወሳሰበም የበለጠ እየጠራ ነው።ወሳኝ እርምጃ ከሕዝብ እና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ይጠበቃል።


ጉዳያችን / Gudayachn 
የካቲት 29/2011 ዓም (ማርች 8/2019 ዓም)
  • ኦዴፓ ውስጥ ያለው ፅንፈኛ አካል ዶ/ር ዓብይን ከስልጣን  የማውረድ ሴራው ተደርሶበታል ፣
  • የፅንፍ ኃይሎች ካሰቡት ጊዜ በፊት ለምን ወደ ነውጥ እንዲገቡ ተገደዱ?
  • የጠቅላይ ሚኒስትሩ የመረረ እርምጃ የትግራይን የተመረጡ የመሳርያ ክምችት (ሰላማዊ ሕዝብን ባልነካ መልኩ) በአየር ኃይል ከመምታት እስከ ኦዴፓ ውስጥ ያሉ ፅንፈኞችን እና የጃዋር ግልፅ ህዝብን የማሸበር ተግባር  ለፍርድ እስከማቅረብ ድረስ መሄድ  ወሳኝ ሀገር አድን ስራዎች ናቸው።
=============================================
''ዶ/ር ዓብይ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን የለበትም''  ጃዋር  ከአመት  በፊት

ልክ የዛሬ ዓመት የኦሮምያ ሚድያ ኔትዎርክ ላይ ጀዋር መሐመድ ቀርቦ ''ዓቢይ ወደ ስልጣን ፈፅሞ መምጣት የለበትም።ከሆነ ለማ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት መምጣት አለበት '' አለ።ይህንን ሲናገር እንደተለመደው አየር እንዳጠረው ሕፃን እጆቹን እያወራጨ ነበር።በሚቀጥለው ቀን ቃለ መጠይቁም ዶ/ር ዓቢይ ፈፅሞ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ቢመጣ "አንቀበልም" በማለት ተናገረ።የኢትዮጵያ ፓርላማ ግን   ዶ/ር ዓቢይን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መረጠ።

በህዝባዊ አመፅ እና በኢህአዴግ -ህወሓት መሐል ከተፈጠረው ቅራኔ ሳብያ የቀድሞዎቹ ኦህደድ እና ብአዴን የህወሓትን አብዮታዊ ዲሞክራሲን አሽቀንጥረው ለውጥ እና የለውጥ ኃይል በሚል አዲስ እንቅስቃሴ ከተጀመረ እና ዶ/ር ዓብይ የመጋቢት 24/2010 ዓም ንግግራቸው እንደተሰማ በብዙዎች ዘንድ ከፍተኛ ተስፋ ሰጥቶት አንድ ዓመት ዘለቀ።በእነኝህ አስራ ሁለት ወራት ውስጥ ባጭሩ ለማስቀመጥ የነበረው የፖለቲካ ውጥረት መርገብ ችሏል።

ኦዴፓ ውስጥ ያለው ፅንፈኛ አካል ዶ/ር ዓብይን ከስልጣን ለማውረድ ሴራው ተደርሶበታል

ባለፉት አስራ ሁለት ወራት ውስጥ በኦዲፓ እና አዲፓ መሓከል እና እንደ ኢህአዴግ አጠቃላይ በለውጡ ውስጥ የነበረው የስልጣን ድልድል ጠርቶ ስላልታዬ ጉተታው በግልጥ መታየት በተለይ ላለፉት አራት ወራት በግልጥ እየታየ ነው።ይህ በእንዲህ እያለ ኦዴፓ ውስጥ የተነሳው የመደመር አስተሳሰብ አራማጅ ኃይልን ለመሸርሸር  የኦነግ እና የጃዋር አንጃዎች ቀድሞ ከነበራቸው የኦዴፓ ወኪሎቻቸው ጋር መዋቅር የማስፋት ሥራ ጀመሩ።በእዚህ የመዋቅር ማስፋት ሥራ ውስጥ ፅንፈኛው አካል እንደ አሜባ እራሱን እያሰፋ መጥቶ አቶ ለአቶ ለማ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አጀዳ መስጠት ሲፈልግ ያለችው አንዲት የከረመች አጀንዳ የአዲስ አበባን ጉዳይ አገኝቶ እርሷኑ ማጮህ ጀመረ።አጀንዳው የተነሳበት ጉዳይ ፅንፈኛው ኦዴፓ ውስጥ ያሉ ለዘብተኞች የሚባሉትን እና የአንድነት ኃይል ጋር ይሰራሉ የሚባሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይን ጨምሮ  ከስልጣን ለማስወገድ እና ስልጣን ለመንጠቅ የሸረቡት ምንም ዓይነት ሴራ የለም ማለት አይደለም። በእዚህ ጉዳይ ደግሞ ከውጭ ጉዳይ ወርቅነህ ገበየሁ ጀምሮ አንዳንድ የኦዴፓ አባላት ዶ/ር ዓብይን ከስልጣን አውርዶ የፅንፈኛ አካል ወደ ስልጣን እንዲመጣ ለማድረግ የሚሞከሩ እንዳሉ ሲሰማ ከርሟል።

ፅንፈኛው አካል በመስቀል አደባባይ በጠቅላይ ሚኒስትሩ  ላይ የግድያ ሙከራ ሲደረግ ከህወሓት ጋር አልተባበረም ወይ? የሚለው ጥርጣሬ ወደፊት የሚገለጥ ይሆናል።በሰሞኑ የፅንፈኛው ኦዲፓ  ለስልጣን ነጠቃ የሚያደርገው ሙከራ ጃዋር ፊሽካ እንዲነፋ ሲመድበው  አደጋ ላይ መውደቁን ከተረዳ በኃላ ነው።የፈድራል የደኅንነት መስርያ ቤት ድምፁን አጥፍቶ እያንዳንዱን የጃዋር እንቅስቃሴ ብቻ ሳይሆን  ኦዴፓ ውስጥ ያሉትን ፅንፈኛ አካሎች የመለየት ሥራ አልሰራም ብሎ መገመት አይቻልም።

የፅንፍ ኃይሎች ካሰቡት ጊዜ በፊት ለምን ወደ ነውጥ እንዲገቡ ተገደዱ?

ኢህአዴግ ውስጥ የነተሳው  የለውጥ ኃይል ሁሉንም መንገድ ክፍት ሲያደርግ ኡጋዴን እንገነጥላለን ብለው ከተነሱ ኃይሎች እስከ ኤርትራ የመሸጉት ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡ  ብዙ ጉድዮች እንደሚፈጠሩ ይታወቅ ነበር።በተለይ በኢትዮጵያ የፖለቲካ መስመር ውስጥ ፅንፍ የዘር እና አክራሪ እስልምና የሚያራምዱ ሁሉ የሚፈጥሩት ግጭት እንደሚኖር ይታወቃል።ይህ ሁኔታ በሂደት ይረግባል ብለው የሚያስቡ የመኖራቸውን ያህል በኃይል ብቻ መፈታት ያለባቸው የፅንፈኛ አካላት መኖራቸው ላይ ሕዝብ ስነ ልቦናዊ ዝግጅት እንዳለው የታወቀ ነው። በተለይ እነኝህ የፅንፍ ኃይሎች ከህወሓት ድጋፍ እንደሚያገኙ ከመታወቁ ጋር አሁን ከሰሞኑ የሚታየው ውጥረት ሲጠበቅ የነበረ እንጂ ድንገት ደራሽ አይደለም።

የኢትዮጵያ ፖለቲካን ወደ ባሰ የፅንፍ ጥግ ለመውሰድ የሚሯሯጡት አካሎች የመጀመርያ ስጋታቸው አንድ በሆነች ኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈልጉትን የስልጣን መንበር እንደፈለጉ ልቆናጠጡ አለማስቻሉ ሲሆን በሌላ በኩል በመንጋ አሰባስብ ያሰባሰቡት ኃይል እየከዳቸው ሄዶ ወደ ግል ስራው  ውስጥ ከገባ እና እራሱን ከቻለ የእነርሱ ባርያ የመሆን እድሉ መቀነሱ ነው። ስለሆነም ከምርጫው በኃላ እናነሳዋለን ያሉትን ግርግር  ሳይፈልጉ ከሰሞኑ ለማንሳት ተገደዋል።ምክንያቱም እስከ አንድ ዓመት ድረስ መጠበቅ የሰበሰቡት ኃይል  ሊበተንባቸው መድረሱ አስግቷቸዋል።

መፍትሄዎቹ 

 መፍትሄው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመብቱ እና ለአንድነቱ የፅንፍ ኃይሎችን ጠንክሮ ካለምንም ርኅራኄ መታገል  እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ግልጥ ውሳኔ መስጠት የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ ነን። ሕዝብ የኢትዮጵያ ጉዳይ የሕልውና ጉዳይ ነው።ሕልውናው ደግሞ ከጊዜ ጋር የሚሄድ ነው።መፍዘዝ መደንዘዝ አይፈልግም። ስለሆነም በአዲስ አበባ ዙርያ ከሚደረገው የመደራጀት ሥራ ጀምሮ እስከ ገጠር የዘለቀ እንቅስቃሴ ሕዝብ ማድረግ አለበት።ይህ እንቅስቃሴ ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው ከጊዜ እና ከፍጥነት ጋር  ግን ደግሞ በከፍተኛ ግለት የፅንፈኛ ኃይልን ወደ መስመር የማስገባት ሥራ ያስፈልጋል።

በሁለተኛ ደረጃ  የስልጣን እርካቡን የያዙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ካለምንም ማወላወል መውሰድ የሚገባቸው ርምጃ አለ። የመጀመርያው እርምጃ የኢትዮጵያን ፀጥታ እና አንድነት የሚገዳደሩ ማናቸውንም ኃይሎች የማንበርከክ ሥራ እንደፈድራል መንግስት መስራት አለባቸው።እነኝህ ኃይሎች ከፅንፈኛ አመለካከት ይዘው ሊገለብጧቸው ከሚያሴሩት  የኦደፓ መረብ እስከ የጀዋር ቡድን እና እንዲሁም እስከ  የህወሓት የታጠቀ ኃይል ላይ ፈጣን ምት መምታት አለባቸው።ለምሳሌ ጀዋር መሬት የመንግስት ነው በተባለባት ሀገር በአደባባይ ጦርነት ማወጁ በራሱ በሕግ የሚያስጠይቀው ነው።ስለሆነም በሕግ ጀዋርን ፍርድ ቤት ማቅረብ የዶ/ር ዓቢይ መንግስት  ካልቻለ እና በልዩ ኃይል ስም ከመከላከያ ውጭ ማንም እንዲይዝ ያልተፈቀደው ከባድ መሳርያ የታጠቀው ህወሓት የተመረጡ የመሳርያ ማከማቻ እና ካምፕ በአየር ነጥሎ እስከመመታት ድረስ ፈጣን እርምጃ መውሰድ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ይጠበቃል።ይህንን የምንለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጦር ኃይሎች አዛዥ እንደመሆናቸው ኃላፊነት አለባቸው።እነኝህን ስራዎች ከሰሩ በኃላ በዓማራ እና በትግራይ መሐል የተነሳውን ችግር የመፍታት እና ልዩ ኃይል የሚባሉ አካሎች በእየክልሉ መጠናቸው እና  የሚይዙት የመሳርያ ዓይነት በሕግ መደንገግ ይቻላል።ከእዚህ ባነሰ ግን አሁን ያለው ችግር አዲስ ነፍጠኛ አካል ወደ ስልጣን የመምጣቱ ሐቅ ከፊት ለፊት የተቀመጠ አጀንዳ ነው።

ባጠቃላይ የኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ እየጠራ ነው።እየጠራ ማለት ፅንፈኛው አጀንዳውም የመሸገበትም ቦታ ተለይቷል።በኢትዮጵያ አንድነንት እና ዲሞክራሲ ስር ሆኖ ሀገር ለመገንባት የተዘጋጀውም ተለይቷል።በኢትዮጵያ ሱማሌ ያለው የዑጋዴን  ታጣቂ ሳይቀር ወደ ሰላም መምጣት በራሱ የፖለቲካ መጥራቱ አካል ነው።አሁን ሕዝብ በጠነከረ መልኩ መቆም እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የመረረ እርምጃ የትግራይን የተመረጡ የመሳርያ ክምችት ከሕዝብ በለየ መልኩ በአየር ኃይል ከመምታት  ኦዴፓ ውስጥ ያሉ ፅንፈኞችን እና የጃዋር ግልፅ ህዝብን የማሸበር ተግባር  ለፍርድ እስከማቅረብ ድረስ መሄድ  ወሳኝ ሀገር አድን ስራዎች ናቸው።በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ በመጪው ዕሁድ  መጋቢት 1/2011 ዓም ጧት ለጋዜጠኞች በሚሰጡት መግለጫ ላይ ብዙ ነገሮች ከሰሩ በኃላ መግለጫ መስጠት አለባቸው።ከእዚህ ባለፈ በመግለጫቸው ላይ የቀደመ ተቻቻሉ መሰል ምክሮች ይዘው ከመጡ የነበራቸውን ድጋፍ በከፍተኛ ደረጃ የሚያጡበት እንዳይሆን ያሰጋል። መግለጫው ከዕርምጃ በኃላ መሆን አለበት።


ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Wednesday, March 6, 2019

በዓማራ እና በትግራይ መሐል ሕዝብ የጠራው ጦርነት የለም! የድርጅቶች ግጭት የሕዝብ ግጭት አይደለም።


ጉዳያችን / GUDAYACHN 
የካቲት 28/2011 ዓም (ማርች 7/2019 ዓም)

  • ሕዝቡን በጎሳ ከፋፍላችሁ በማጫረስ ጎልምሳችሁ እና አርጅታችሁ፣ ዛሬም ደም ለማፋሰስ የምትጣደፉ የዕርግማን ትውልድ አካሎች ሆይ! ይልቅ የዕርጅና ዘመናችሁን የመፀፀቻ እና የንስሐ ዘመን አድርጉት።

ህወሓት ከሻብያ ጋር ገጥማ እንዳ ስላሴ ላይ ሦስተኛውን ክፍለ ጦር ስታጠቃ እና መቀሌን ስትይዝ ከኢሕአፓ የወጡት የእነታምራት ላይኔ ቡድን በኢሕዴን ስር መኖሩ የበለጠ ወደ ወሎ እና ጎንደር ለመሻገር እንደሚረዳት አመነችበት።ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከአንዱ ክፍለ ሀገር ወደ ሌላው ስትሄድ እንደ መንገድ ዳር ሱቅ የብሔር ድርጅቶች እየፈለፈለች አዲስ አበባ ደረሰች።የፈለፈለቻቸው የብሔር ድርጅቶች ግን ዛሬ አድገው እራሷኑ የሚገዳደር አቅም ገንብተው ህወሓትን አሽቀነጠሯት።

ህወሓት ከአዲስ አበባ በከፍተኛ የሙስና ቅሌት እና ሰብአዊ ጥፋት መቀሌ ከከተተች በኃላ የገጠማት ሁለተኛው ተግዳሮት  የእራሱ የትግራይ ሕዝብ ጥያቄ ነው።መቀሌ ውሃ ሳይኖራት በቢልዮን የሚቆጠር ገንዘብ ያሸሹት ያኔ በነጠላ ጫማ አዲስ አበባ የገቡ የዛሬ  ቱጃር ህወሓቶች በሕዝብ ጥያቄ መድረሻ ጠፋቸው።የአረና አመራሮች  ሳይቀሩ የህዝብ ድምፅ ለማሰማት በመቀሌ ዩንቨርስቲ ውስጥ ሃሳባቸውን ለመስጠት ሲሞክሩ አቦይ ስብሐት ሳይቀሩ በጭብጨባ ለማስቆም ሲሞክሩ ታዩ። የህዝቡ ጥይቄ ግን አልቆመም። ስለሆነም አንድ አይነት ሥራ ለሕዝቡ መስጠት አለባቸው። ይህም ጦርነት መፍጠር ነው።ጦርነት የትግራይን ህዝብም የበለጠ ለመጨፍለቅ ይመቻቸዋል።ስለሆነም ጦርነቱ ይፈለጋል።

ጦርነቱን ደግሞ ''በትግራይ ሕዝብ እና በዓማራ ሕዝብ መሐል'' እንደሚደረግ በአክትቪስቶቻቸው ሲናገሩ ትንሽም እፍረት የለም። እዚህ ላይ የአማራ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲም ሆነ ህወሓት በትግራይ እና በዓማራ ሕዝብ መሐል የሚደረግ ጦርነት የሚል ስያሜ ማቆም እንዳለባቸው ለምድያዎቻቸው መንገር አለባቸው።በፊውዳሉ ስርዓት የሚደረጉ የገዢዎች ጦርነቶችን ታሪክ አባቶቻችን ሲፅፉ ጥንቁቅ ነበሩ።አንድም ታሪክ ላይ ትግራይ እና ጎንደር ወይንም ወሎ እና ትግራይ ተዋግተው አይሉም ራስ እገሌ ከደጃች እገሌ ጋር ወይንም የትግራዩ ገዢ እገሌ ከጎጃሙ ገዢ እገሌ እያሉ ይፅፋሉ እንጂ ሀገር ከሀገር ተጣላ ብለው የፃፉት ታሪክ የለም።የሚጣሉ ገዢዎች ናቸው።ለእዚህ ነው ላሸነፉት የእርስ በርስ ጦርነት አንድም ማስታወሻ ሃውልት ትተው አላለፉም።ምክንያቱም መጪው ትውልድን አርቀው የሚመለከቱ እና ርዕያቸው ሐገራዊ እና ዘመን ተሻጋሪ ስለነበር ነው።

ለማጠቃለል በዓማራ እና ትግራይ መሐል ጦርነት ብሎ ነገር የለም በህወሓት እና አዲፓ መሐል ካለም የጅል ጫወታችሁን እንድታቆሙ ነው የምትጠየቁት።ለመሆኑ ይህ ምስኪን ገበሬ በምን ዕዳው ነው ኢትዮጵያን በብሔር  ከፋፍለው እና ሀገር ዘርፈው ከሄዱ ሙሰኞች ጋር ተሰልፎ እርስ በርሱ የሚዋጋው? ለምንስ ተብሎ ነው የውጭ ጠላት ሳይመጣበት  እርስ በርሱ የምተላለቀው? ይህ የእሳት ዳር ጫወታ ማቆም የሁሉም ኃላፊነት ነው።የፌድራል መንግስትም የሀገር ፀጥታ የማስከበር ተግባሩን መወጣት አለበት።በአሁን ሰዓት ለጦርነት የሚያነሳሳ አንዳችም ምክንያት ሊኖር አይገባውም።ህወሓቶች በህዝባዊ ማዕበል ያጡት ስልጣን ቁጭት  በሌላው ትግራይ ሕዝብ ውስጥ አድሮ ለጦርነት የሚያነሳሳ ምቹ ሁኔታ ያለ መስሏቸው ይሆናል። ይህ ስሜት ያለው እነርሱ ውስጥ ነው እንጂ ሌላው ሕዝብ የዕለት ኑሮውን ለመሙላት እየተውተረተረ ነው።ዶ/ር አረጋዊ ከሳምንት በፊት ለኤል ቲቪ እንደተናገሩት ''ህወሐቶች ሕዝቡን አቆርቁዘውታል።በአሁኑ ሰዓት ከትግራይ ሕዝብ 85% የሚሆነውን ሕዝብ ህወሓት የሚያኖረው በምግብ ለስራ  መርሐግብር ነው '' ብለዋል።የስልጣን ጥማቱ ያለው ህወሓት እና የጥቅም ተጋርዎቻቸው ዙርይ ነው።ሌላው እንዲሁ ስሜት ውስጥ ያለ እና የነገ ተስፋውን የሚጠብቅ ነው።በዓማራ ክልልም ያለው ይሄው ነው።ያለውን መሬት በበሬ አርሶ ቤተሰቡን ለመመገብ የሚታትር ሕዝብ ዛሬ ላይ ጦርነት ናፍቆታል ማለት ዘበት ነው።ስለሆነም በምንም መለኪያ የሚፈለግ ጦርነትም ሆነ ለጦርነት ምቹ የሆነ ነባራዊ ሁኔታ የለም።ሕዝቡን በጎሳ ከፋፍላችሁ በማጫረስ ጎልምሳችሁ እና አርጅታችሁ፣ ዛሬም ደም ለማፋሰስ የምትጣደፉ የዕርግማን ትውልድ አካሎች ሆይ! ይልቅ የዕርጅና ዘመናችሁን የመፀፀቻ እና የንስሐ ዘመን አድርጉት።

ጉዳያችን / GUDAYACHN 
www.gudayachn.com

Monday, March 4, 2019

ከእዚህ በፊት ያልሰሙት የኢትዮጵያ ተፅኖ ፈጣሪነት በአፍሪካም ሆነ በዓለም የነበረበትን ከፍተኛ ደረጃ የሚያሳይ ድንቅ ቃለ መጠይቅ (ቪድዮ)

ጉዳያችን / Gudayachn
መጋቢት 5/2011 ዓም (ማርች 5/2019 ዓም)

ቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ኒውዮርክ ላይ እንደ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር 1956 ዓም ( እ ኤ አ 1963 ዓም) የሰጡት ቃለ መጠይቅ ላይ 
- ስለ ቻይና  ተንብየዋል፣
- አፍሪካን ከቅኝ ግዛት ለማውጣት ጦር ሊጠቀሙ እንደሚችሉ አውሮፓን አስጠንቅቀዋል፣
- ነጮች አፍሪቃውያን ከቅኝ ግዛት ከወጡ በኃላ በአፍሪካ እንዴት መኖር እንዳለባቸው ጠቁመዋል፣
- ከመከላከያ ሚኒስትርነት እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይልቅ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ቻንስለርነት ለምን እንደመረጡ ገልጠዋል።
- ጥቁርነት በአሜሪካ ስቃይ በሆነበት ዘመን በአሜሪካ የውስጥ ጉዳይ ገብተው በአደባባይ አሜሪካንን ወቅሰዋል። 

ባጭሩ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ምን ያህል ተፈሪ እና ተፅኖ ፈጣሪ እንደነበር በእዚህ ቃለ መጠይቅ መረዳት ይቻላል።አውሮፓውያን በአፍሪካ የነበራቸውን የቅኝ መግዛት ሕልም ትንሽ ለማራዘም ቢፈልጉም የንጉሡ ፈጣን አካሄድ በተለይ ብዙዎች የአፍሪካ ሀገሮች በቅኝ ግዛት በነበሩበት ዘመን እ ኤ አ  በ1963 ዓም የአፍሪካ አንድነትን መስረተው አፍሪቃውያንን ከቅኝ ግዛት ቀንበር ማስጣላቸው ቅኝ ገዢዎች እስከመጨረሻው ጥርስ አልነከሱም ማለት አይቻልም።ዛሬም በንጉሡ ላይ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ስም ለማጥፋት የሚሞክሩ የቅኝ ገዢዎች ቂም አስፈፃሚ አይደሉም ማለት እንዴት ይቻላል?



ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com

Sunday, March 3, 2019

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ አንድነት እንደሚያምኑ እና የአንድነት ኃይሉ አሸናፊነት አይቀሬ መሆኑን ገለጡ።የለውጡን ፍኖተ ካርታ ጠቁመዋል።አዲስ የተለቀቀውን ሙሉ ንግግራቸውን ቪዲዮ ይመልከቱ።

 ጉዳያችን / Gudayachn
የካቲት 24/2011 ዓም (ማርች 3/2019 ዓም) 

  • ጉዳያችን የደብረ ብርሐን መግለጫ (ደብረ ብርሐን 'ዲክላሬሽን') ብላዋላች። 

'' ኢትዮጵያን ለመከፋፈል ከሚተጉት ጋር ከመሰለፍ የዚችን ሀገር አንድነት ለመጠበቅ በየትኛውም ደረጃ ማለፍ ኩራት መሆኑን ልገልጥላችሁ እወዳለሁ።'' ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ የካቲት 23/2011 ዓም ከኬንያው ፕሬዝዳንት ዑሁሩ ኬንያታ ጋር በመሆን በደብረ ብርሐን ከዳግማዊ አፄ ምንሊክ ትውልድ ስፍራ አንጎለላ ወረዳ የተገነባው የኢንዱስትሪ ፓርክ ሲመርቁ ካደረጉት ንግግር ።ሙሉውን ንግግር ለመመልከት ቪድዮውን ይክፈቱ።



ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።