ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, October 29, 2013

የደቡብ ሱዳን ግዛት የአብዬ ህዝበ ውሳኔ የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ትኩሳትን እያጋለው ነው።


ጉዳያችን ጡመራ ጥቅምት 19/2006 ዓም
አብዬ ክልል በደቡብ እና ሰሜን ሱዳን መካከል የምትገኝ የሁለቱ ሃገራት አጨቃጫቂ ግዛት ነች።የ10,546 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ያላት አብዬ በነዳጅ ሃብቷ ከእሩቅ እስከ ቅርብ ያሉ ማላዮችን አይን ስባለች።የምዕራቡ ዓለምም ሆነ የአካባቢው ሃገራት ጉዳዩን ከሚገባው በላይ እንዲጮህ ያደረጉት የሰብአዊ መብት ጉዳይ ብቻ ቢሆን በጣም ደስ ይል ነበር። ግን ጉዳዩ ከሃብት ጋር መያያዙ እና ይህ ሃብት በሰሜን ሱዳን እጅ ከገባ የሚኖረው የኃይል ሚዛን ሃያላኑንም ሆነ የቅርብ ቡና አጣጪ ጎረቤቶችን ቀልብ ስቧል።

በአብዬ ግዛት አረብኛ እና እንግሊዝኛ ይነገራል።የተባበሩት መንግሥታት በግዛቲቱ ላለው ግጭት ሰላም አስከባሪ  ኃይል የሲቪልያንን ሕይወት እንዲታደጉ 4,200  የኢትዮጵያ ወታደሮች እንዲመደቡ ማድረጉ ይታወቃል።

ትናንት ጥቅምት 18/2006 ዓም ታዲያ ግዛቲቱ ወደ ሰሜን ወይንም ወደ ደቡብ ሱዳን ለመቀላልቀል የሕዝበ ውሳኔ አድርጋለች።ህዝበ ውሳኔውን የተባበሩት መንግሥታት እውቅና አልሰጠውም።ሆኖም ግን የውጭ ኃይላት የሉበትም ለማለት አይስደፍርም።
ዛሬ አልጀዚራ ''ኢንሳይድ ስቶሪ'' ፕሮግራሙ ''የአብዬ ህዝበ ውሳኔ ለሰላም ስጋት ነውን?'' በሚል አርዕስት ስር ያቀረበውን ውይይት ይመልከቱ።





ጉዳያችን GUDAYACHNgetachewb221@gmail.com

Monday, October 28, 2013

ክፍል ሁለት ከመቃብር የተላከ ደብዳቤ-ጥቃቅን ቀበሮዎች ዘውጋቸው ቋንቋቸው


.....ምን ይጠቅም መሰለህ? አዎን ሰዎችን ስትመለከታቸው ዘውጋቸው ቋንቋቸው ሲሆን ተመልክተህ ይሆናል።ናላቸው በቋንቋ እና የትውልድ መንደር ብርብራ እንደቀመሰ አሳ ተሳክረው ይሆናል።ይህ ሁሉ ግን ኢትዮጵያዊነትህ ላይ ነቁጥ እንዳያንጠባጥብበት ተጠንቀቅ።ልብ አለማለታቸውን ልብ አላሉት ይሆናል እንጂ በዙርያ ንግግር እናትህ ስትወልድህ የት መውለድ እንዳለባት እየመከሩህ አንተም ከመወለድህ በፊት በእናትህ ሆድ ሳለህ ለእናትህ የት መውለድ እንዳለባት ማሳሰብያ ቢጤ አለመስጠትህን ከኃጢያት ቆጥረውብህ እኮ ነው።

እናት ምን አጠፋች? ልጅስ ምን አጠፋ? እናት መውለጃዋ ሲደርስ መንደር መምረጥ  ነበረባትን? ቆይ የመውለጃ ጊዜዬ ደረሰ ልጄን ይህንን አልያም ያኛውን  ቋንቋ ከሚናገሩት መንደር ወይንም ሀገር ወስጄ ልውለድ ልትል ይቻላታልን? ልጅስ የት መወለድ እንዳለበት በእናቱ ሆድ ሳለ መወሰን ይገባው ነበርን?  እናቱንስ ገና ከማህፀን ሳለ የለም እናቴ ከእዚህ መንደር አትውለጅኝ ከዛኛው መንደር ውለጅኝ ፣ይህንን ቋንቋ አልናገር ያኛውን ግን ልናገር ማለት ይችላልን? ደግሞስ ኢትዮጵያ ሁሉ እንደየ እጣው የመጣባት ምድር አይደለችምን?

ሰዎች እንደፈለጉ በጥላቻ እና በቋንቋ ለመለያየት ይጋልቡ።ባለስልጣኖቹ በአፈሙዝ በነጠቁት ስልጣን ህዝብን ከህዝብ ጋር እያጋጩ እና እየለያዩ ደቂቃዋን ያራዝሙ አንተ ግን እራስህን ከጥቃቅን  ቋንቋን እና ትውልድ መንደርን እየሸነሸኑ ኢትዮጵያዊነትህን ልያዘናጉህ ''ለእኔ እስካልተመቸችኝ ስለመንደሬ ብቻ የማትዘምር ኢትዮጵያ ምን ታድርጋለች'' ከሚሉህ ጥቃቅን ቀበሮዎች እራስህን ጠብቅ።

ጥቃቅን ቀበሮዎቹ ሲጮሁ፣ሲፅፉ፣እንደፈለጉ ህዝብን ከህዝብ ጋር ሲያጋጩ ሀገሬ፣እኔነቴ፣ሰላሜ ኢትዮጵያ ነች መንደሬ አይደለም ያሉቱ ወይ አይፅፉ ወይ ተዉ አይሉ ዝናብ እንደመታው የደጋ በግ ቢፈዙብህም አንተ ግን አሁንም እራስህን ከጥቃቅን ቀበሮዎች ጠብቅ።ከመንደርህ ሀገርህ፣ከእድርህ ኢትዮጵያዊነትህ በመጨረሻ ላይ እንደሚያሸንፍ ቅንጣት ታክል አትጠራጠር።
ክፍል ሁለት ከመቃብር የተላከ ደብዳቤ ተጠናቀቀ።
ክፍል ሶስት ካልተወሰነ ጊዜ በኃላ ከመቃብር እንደሚላክ ይጠበቃል።
ጉዳያችን GUDAYACHN
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ጌታቸው በቀለ 
ኦስሎ ጥቅምት 15/2006 ዓም 




ጉዳያችን GUDAYACHN

Friday, October 25, 2013

በኢትዮጵያ ከግማሽ ክ/ዘመን በላይ የቆየ ማንዴላን የተመለከተ የደህንነት ሚስጥር ዛሬ ይፋ ሆነ።ሚስጥሩን ማንዴላም እስካሁን ድረስ አይውቁትም።

ለኔልሰን ማንዴላ ወታደራዊ ስልጠና የሰጡት አፄ ኃይለሰላሴ  ከከዮርዳኖሱ ንጉሥ ሐሰን ጋር


ምንጭ- ሸገር ራድዮ 
ቅንብር- ጉዳያችን ጡመራ 
ቀን ዓርብ ጥቅምት 15/2006 ዓም

ኔልሰን ማንዴላ የደቡብ አፍሪካ የፀረ-አፓርታይድ (የዘር-መድሎ) ተዋጊ አርበኛ መሆናቸው ይታወቃል።በደቡብ አፍሪካ ዘረኛ መንግስት ለእስር የተዳረጉት ኢትዮጵያ ውስጥ ወታደራዊ ስልጠና ወስደው እንደተመለሱ ነበር። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ 1962 ዓም ማንዴላ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ኢትዮጵያ ፓስፖርት በመስጠት አጋርነቷን የገለፀች ብቸኛ ሀገር ነበረች።

ከዘመናት በኃላ ማንዴላ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ወቅት  የግድያ ሙከራ ሴራ ተደርጎ እንደነበር ሚስጥሩን ከግማሽ ክፍለዘመን በላይ ይዘው የቆዩ በቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ዘመን የኢትዮጵያ ፖሊስ መኮንን ዛሬ ጥቅምት 15/2006 ዓም ለመጀመርያ ጊዜ በሸገር ራድዮ የዜና እወጃ ላይ ገልፀዋል።

ኔልሰን ማንዴላ እና ጄኔራል ታደሰ(የማንዴላ አሰልጣኝ በወቅቱ ኮ/ል የነበሩ)ኮልፌ ፖሊስ ማሰልጠኛ

ሻምበል ጉታ ዲንቃ በንጉሡ ዘመን የፖሊስ መኮንን ነበሩ። ማንዴላን በከፍተኛ ሚስጥር እንዲጠብቁ ኃላፊነት ከተሰጣቸው ጄኔራል ታደሰ(የማንዴላ አሰልጣኝ በወቅቱ ኮ/ል የነበሩ)፣ኮ/ል ፍቃደ እና ሻምበል ፈቃደ ውስጥ ነበሩ።ዛሬ የ76 አምቱ የእድሜ ባለፀጋ  ሻምበል ጉታ ዲንቃ ለሸገር ሲናገሩ እንዲህ አሉ።

'' ማንዴላን እንድጠብቅ ኃላፊነት የተሰጠኝ እኔ ነበርኩ።ማንዴላ የሚያድሩበት እና ወታደራዊ ስልጠና የሚወስዱበት የኮልፌ የፖሊስ ማሰልጠኛ ቦታ ነበር ።በተለይ እርሳቸው የሚገኙበት ቦታ 'የፈንጅ ወረዳ' ነበር የሚባለው።ከአራታችን በቀር ማንም ወደ እርሳቸው ቦታ ዝር ማለት አይችልም። ሲተኙ መስኮት ከፍተው ነው የሚተኙት።...አንድ ቀን ታድያ አብሮኝ ከሚሰራው የፖሊስ ባልደረባዬ በጥብቅ እንደሚፈልገኝ ነገረኝ።ጣይቱ ሆቴል ተቀጣጠርን እና ሃሳቡን ገለፀልኝ።'' ካሉ በኃላ  አሁን አዲስ አበባ ላፍቶ አካባቢ ነዋሪ የሆኑት ሻምበል ጉታ በመቀጠል እንዲህ ብለዋል-

''ጣይቱ ሆቴል የወሰደኝ ሰው ለጊዜው 2000 ፓውንድ በወቅቱ አስቡት 2000 ፓውንድን እና  ሰጥቶ እንዲህ አለኝ- 'ሁለት ዕድል ከፊታችን ተቀምጧል።ሊያመልጠን አይገባም።ከፍተኛ ገንዘብ እናገኛለን።ቀጥሎም ወደ ውጭ ሀገር የመሄድ ዕድል አለን።ከአንተ የሚጠበቀው ማንዴላ በተኛበት ዛሬ ሌሊት በመስኮት ገብተህ በገመድ አንቀህ ግደል እና ውጣ እንደወጣህ መኪና ተዘጋጅቶ ይጠብቅሃል ከእዚህ የውትድርና ሕይወት እንገላገላለን' አለኝ። እኔም ጉዳዩን ከሰማሁ በኃላ በጉዳዩ የተስማማሁ መስዬ ቀጥታ  ለጀኔራል ታደሰ ነገርኩኝ። ጉዳዩ በሚስጥር ተይዞ ይህንን ያደረጉት ሰዎች ተደረሰባቸው እና ከሀገር እንዲወጡ(እንዲባረሩ) ተደረጉ ይህ ሚስጥር ለዘመናት ከእኔ ጋር የኖረ ነው።ጉዳዩን ማንዴላም አያውቁትም።'' ብለዋል።
ኢትዮጵያ ለኔልሰን ማንዴላ የሰጠቻቸው ፓስፖርት 

ኔልሰን ማንዴላ በወቅቱ እንደ ሻምበል ጉታ ዲንቃ አይነት ታማኝ የኢትዮጵያ የፖሊስ መኮንን ባይገጥማቸው ኖሮ የደቡብ አፍሪካ የነፃነት ታሪክ ሂደትም ሆነ የነፃነት ትግሉ ታሪክ ሌላ መልክ በያዘ ነበር።ይህ ጉዳይ እጅግ ትልቅ ጉዳይ ነው።የኢትዮጵያ ፖሊስ ለአፍሪካ ያደረገው አስተዋፆ የሚያጎላ በመሆኑ በኢትዮጵያ የዜና አገልግሎቶች ሁሉ ትኩረት ተሰጥቶት የዓለም አቀፍ የዜና ሽፋን እንዲያገኝ ጥረት ማድረግ ለኢትዮጵያ ፋይዳው ብዙ ይመስለኛል።እስካሁን ድረስ ማንዴላ በኢትዮጵያ ምን ያህል ድጋፍ ተደርጎላቸው እንደነበር የማያውቅ አፍሪካዊም ሆነ ደቡብ አፍሪካዊ እንዲሁም የዓለም ሕዝብ አለ።በመሆኑም ይህ ጉዳዩን ለማጮህ የሚረዳ ወርቃማ አጋጣሚ ነው።

በመሆኑም ቢያንስ ለሻምበል ጉታ ዲንቃ የኢትዮጵያ ፖሊስ ጠርቶ ማዕረግ እና ሽልማት ከእዚህ ባለፈም ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠት እና  ማንዴላ  በሕይወት ዘመናቸው ሳሉ ሻምበል ጉታ ደቡብ አፍሪካ ድረስ ሄደው እንዲያገኙዋቸው ማድረግተገቢ ይመስለኛል።።ጉዳዩ የደህንነት ሚስጥር የነበረ በመሆኑ በወቅቱ ግድያውን ሊፈፅም የሞከረው አካል ወይንም ሀገር (ማንነቱን ሻምበል ጉታ የተባረሩት ዜጎች የየት ሀገር እንደነበሩ አልገለፁም) ዛሬ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ለሚኖረው ግንኙነት ላይ ጥላ እንዳያጠላ ስጋት ስለሚሆን ዜናው በተፈለገው ደረጃ ለዓለም ሕዝብ እንዳይደርስ የሚደረጉ ስውር ስራዎች እንደማይጠፋ ማጤን ሌላው ሥራ ሊሆን ይችላል።
በመጨረሻም ሻምበል ጉታ ዲንቃ ለሕዝብ ወጥተው ዛሬ ላይ ምንም ምስጢርነት የሌለውን ጉዳይ ለሕዝብ በመንገራቸው ሊመሰገኑ ይገባል።
ማንዴላ ከእስር እስኪፈቱ ድረስ በኢትዮጵያ ፓስፖርት ነበሩ።ይህ የደቡብ አፍሪካ ፓስፖርት ከእስር በተፈቱ በ 8ኛ ቀን ያገኙት ነው።




Thursday, October 24, 2013

Tuesday, October 22, 2013

ፕሮፌሰር ጋቢሳ እጄታ በተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ ባንኪሙን የሳይንቲስቶች ቦርድ አባል ሆነው ተመረጡ።


ፕሮፌሰር ጋቢሳ እጄታ
ፕሮፌሰር ጋቢሳ እጄታ በተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ ባንኪሙን በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ ላሉት ድርጅቶች የበላይ አመራር አካል (executive heads of U.N. organizations) በሳይንስ በቴክኖሎጂ እና በፈጠራ ክህሎት ዙርያ ምክር የሚሰጠው የሳይንቲስቶች ቦርድ አባል ሆነው ተመረጡ። ሃያ ስድስት አባላት ካሉት የሳይንቲስቶች ቦርድ አባላት ውስጥ ፕሮፌሰር ጋቢሳ እጄታ ብቸኛ የእርሻ ሳይንቲስት መሆናቸው ተነግሯል።

ፕሮፌሠር ጋቢሳ የመጀመርያ ዲግሪያቸውን በ 1965 ዓም ከአለማያ ዩንቨርሲቲ በእፅዋት ሳይንስ፣የማስትሬት እና የዶክትሬት ዲግሪአቸውን  ከፕዩድረ ዩንቨርሲቲ በእፅዋት ማዳቀል እና ጄኔቲክስ አግኝተዋል።

በሥራ ዓለም በተለያዩ ድርጅቶች በፕዩድረ ዩንቨርስቲ በረዳት ፕሮፌሰርነት ጨምሮ በዓለም አቀፍ የእርሻ ምርምር ማዕከል -International agricultural research centers (IARCs)፣በዓለም የምግብ ድርጅት (FAO)፣በሮክ ፌለር ግብረ ሰናይ ድርጅት፣በሳሳካዋ አፍሪካ ፕሮግራም (Sasakawa Africa Program) በቦርድ አባልነት አገልግለዋል።

ይህ ብቻ አይደለም  ፕሮፌሰር ጋቢሳ በ2002 ዓም የዓለም የምግብ ሽልማት አሸናፊ የሆኑበት እና ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት ያስገኘላቸው በምርምር ያገኙት ድርቅ እና በሽታን የመቋቋም ችሎታ ያለው የማሽላ ዝርያ  ግኝት ባለቤትም ናቸው።ኢትዮጵያውያን ብቃታቸው በተመሰከረላቸው ባለሙያዎቻችን መኩራትም መጠቀምም መቻል አለብን።መልካም የስራ ዘመን ለሳይንቲስቱ ፕሮፌሰር ጋቢሳ።

Sunday, October 20, 2013

የኢትዮጵያ ስነ-ህዋ ሳይንስ ምርምር ማኅበር አመርቂ ተግባራት (ጉዳያችን ጡመራ ልዩ ጥንቅር)




ስለ ስነ-ህዋ መመራመር ለበለፀጉ ሃገራት ብቻ መስጠት በብዙዎች ዘንድ የታመነበት ተግባር ነው።ኢትዮጵያ በምጣኔ ሃብት በማነሷ ብቻ ስለህዋው ጉዳይ ለማጥናት መብት የሌላት ያህል ዝቅ አርገው የሚመለከቱ አይጠፉም።እሳቤያቸው ከበጎ አስተሳሰብም የሚነሳ አሉ።''ኢትዮጵያ ብዙ ወጪ የሚጠይቀውን የህዋው ምርምር ላይ ከመትሰራ መጀመርያ እርሻው በአግባቡ በታረሰ'' መሰል ጥያቄ የሚያነሱ አሉ።ይህ ግን የተሳሳተ እሳቤ ነው።በዓለም ዙርያ የአሜሪካውን የህዋ ምርምር ጣቢያ (ናሳን) ጨምሮ የሚያማክሩ እና በከፍተኛ ኃላፊነት ላይ ያሉ የመጀመርያ ዲግርያቸውን ግን በኢትዮጵያ የሰሩ ተመራማሪዎች አሏት -ኢትዮጵያ።

ይህ ብቻ አይደለም ''የኢትዮጵያ ስነ-ህዋ ምርምር ማኅበር'' (Ethiopia Space Scince Society- http://www.ethiosss.org.et/index.php/en/ ) በአዲስ አበባ አበረታች እንቅስቃሴ እያደረገ ነው።በ2004 ዓም እአአ የተመሰረተው ማኅበር  በወቅቱ ሃሳቡን ሲገልፅ አንዳንዶች በቀልድ መልክ ተመልክተውት ነበር።''የእብድ ማኅበር '' በማለት የተሳለቁም ነበሩ።ሆኖም ግን ዛሬ ማኅበሩ በምስራቅ አፍሪካ በጥራቱም ሆነ በብቃቱ ተወዳዳሪ የሌለው የስነ-ህዋ ማጥኛ ማዕከል ወደመሆን እራሱን ቀይሯል።

ማኅበሩ እስካሁን 1500 በዘርፉ ዙርያ ምርምር የሚያደርጉ እና ለዘርፉ ድጋፍ የሚሰጡ አባላትን አሰባስቧል።በእዚህ አላቆመም። በእንጦጦ ተራራ ላይ ከመሰረተው ጣብያ ላይ በቅርቡ ከሁለት ዓመት በፊት እንዲሰሩ ያዘዛቸውን 80 ሚልዮን ብር የሚያወጡ እጅግ ዘመናዊ ቴሌስኮፖች በቅርቡ ከጀርመን ሀገር እንደሚያስመጣ እና እንደሚተክል ለማወቅ ተችሏል።

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ከባህር ጠለል በላይ ከ2000 ሜትር በላይ መገኘቷ እና ባብዛኛው ወራት ሰማይዋ በደመና ያለመሸፈኑ ታክሎበት ለዘርፉ ምርምር ተፈጥሮ ያደላት መሆኑን ብዙዎች ያወሳሉ።በነገራችን ላይ የስነ-ህዋ ምርምር ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች ይሰጣል።ይሄውም ለዘመናዊ እርሻ እድገት፣ለኢንዱስትሪ ልማት፣ለሕዋ ቱሪዝም ለመሳብ(ቱሪስቶች ወደ እንጦጦ ተራራ ሄደው በክፍያ ህዋውን በልዩ ቴሌስኮፕ እንዲመለከቱ በማድረግ-Astronomy tourism) ወዘተ ጥቅም አለው።

በመጨረሻም በጥቂት ተነሳሽ አባላት ስራውን የጀመረው ማኅበር አሁን የምርምር ጣቢያውን ከከፈተበት ከእንጦጦ ተራራ በተጨማሪ ከላሊበላ ከተማ በስተሰሜን ላይ ከሚገኘው በከፍታው ከባህር ጠለል በላይ 4200 ሜትር ከፍታ ላይ ሌላ የመመልከቻ ማማ  እንደሚከፍት ለመረዳት ተችሏል።በእዚህ አላቆመም።ኢትዮጵያ የሕዋ-ፖሊሲ እንዲኖራት ለመንግስት ሃሳቡን አቅርቦ ፖሊሲው እንዲወጣ እየሰራ ይገኛል።በመላው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በተለይ በዘርፉ ሙያ ያላቸው ሊደግፉት የሚገባ ተግባር ነው።በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን መኪና ወደሀገራችን ሲገባ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ነዳጅ የለን፣መንገድ የለን፣ሹፌር የለን ብለው የመኪና ወደሀገራችን መግባትን አልተቃወሙም ዘመን አሻግረው አስፈላጊነቱን ተረዱ። ዛሬም ይህ ማኅበር አርቆ የተመለከተው ለአንዳንዶች ሕልም የሚመስለው ነገር ፍሬ ማፍራቱ አይቀርም።ለነገሩ ዓለም እራሱ ስለህዋ የተማረው ከኢትዮጵያ መሆኑን ልብ ይሏል።መፅሐፈ ሄኖክ የተሰኘው የቤተክርስቲያን መፅሐፍ በመላው ዓለም ጠፍቶ የተገኘው ኢትዮጵያ ነው።መፅሐፉ እግዚአብሔር ስለፈጠራቸው ስነ-ህዋ በሚገባ እንደሚናገር ይታወቃል።

ማገናዘብያ 
http://www.ethiosss.org.et/index.php/en/ 

http://www.channelnewsasia.com/news/lifestyle/ethiopia-unveils/852640.html 

http://voicesofafrica.co.za/tag/ethiopian-space-science-society/ 

''ያልተከፈለ ዕዳ'' የደርግን ''የአስናቀ ገፀ ባህሪ በ ሰው ለሰው ድራማ '' ኢህአዲግን?



''ያልተከፈለ ዕዳ''
''ያልተከፈለ ዕዳ'' የተሰኘ ድራማ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በልጅነት ዘመኔ ማየቴ ትዝ ይለኛል።ድራማው ላይ በዋና ተዋናይነት ትጫወት የነበረችው አለምፀሐይ ወዳጆ ነበረች።ድራማውን ካልዘነጋሁት አለምፀሐይ ባለቤቷ በስውር ታፍኖ ይገደልባታል።የገደለባት ደግሞ የእራሷ ወዳጅ መሳይ ነው።ዘግይታ ግን ደረሰችበት።
አንድ ቀን ታድያ አለምፀሐይ ያልተከፈለ ዕዳ ያለበትን ሰው ልትቀጣው ሽጉጧን በቦርሳዋ ይዛ ሄደች።ከቤቱ ደረሰችና ግቢ ውስጥ ትገባለች እንደገባች ሶፋ ላይ ተቀምጦ የነበረ  ገዳይ ወዳጇን ሰው ውስኪ ሲጠጣ ታገኘዋለች....በቦርሳዋ የያዘችውን ሽጉጥ ታወጣለች።ሰውየው ምን እንዳጠፋ እየጠየቀ ይማፀናታል። ''ያልተከፈለ ዕዳ  አለብህ!'' ብላ ትተኩሳለች።ፊልሙ   ''ያልተከፈለ ዕዳ'' ነውና ከሶፋው ስር የወደቀው ሟች እራሱ እንደገደለው ለማድረግ ሽጉጡን በእጁ እንዲይዝ ይደረጋል።ፖሊሶች ይመጣሉ።ምርመራው ይቀጥላል።

በማግስቱ ነፍሱን ይማረውና ለአባቴ የማታው ድራማ ደስ እንደማይል ስነገረው።ዝም ብሎ ቆየ እና ድራማው ሚስጥር ያለው ይመስለኛል አለኝ።ቀጠለናም  በወቅቱ የነበረውን የደርግ ዘመንን እንደሚያመላክት ነገረኝ።ታፍነው የተገደሉ ንጉሱን የሚወክል ገፀ ባህሪ እንደሚሆን አፍኖ የገደለው ደርግ እንደሆነ ወዳጅ የመሰላት አለምፀሐይ የኢትዮጵያ ገፀ ባህሪ እንደያዘች፣''ያልተከፈለ ዕዳ'' ያለችው ኢትዮጵያ ልጆቿን በደርግ ቀይሽብር አጥታ ያልተከፈላት ዕዳ እንዳለ ስታመላክት ነው አለኝ።በልጅነት አዕምሮ የነገረኝን አሰብኩት።በተለይ በደርግ ዘመን ዘፈኑ ሲወጣ የሚሰጠው ትርጉም ሁሉ ስለነበር ይህ ድራማ አባቴ ካለው ጋር ለመዛመዱ ቅንጣት ታክል አልተጠራጠርኩም።

''ሰው ለሰው ድራማ ተዋናይ የአስናቀ ገፀ ባህሪ ኢህአዲግን?''

በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በተከታታይ የሚታየው የሰው ለሰው ድራማ ዋና ተዋናይ አስናቀ የኢህአዲግን ገፀ ባህሪ ሌሎቹ ደግሞ ከሀገር ውስጥ ተቃዋሚ እስከ ባህር ማዶ፣ከኢትዮጵያ እስከ ልጆቿ፣ከኢህአዲግ ''አቦ አቦ'' ባዮች እስከ ውስጥ አሸርጋጅ የሚወክል ገፀ ባህሪ እንደተካተተበት የኢሳቱ አቤ  ቶክቻው በዛሬው በእሁድ ጥቅምት 10/2006 ዓም ''በዋዛ እና ቁምነገር'' በተሰኘ ፕሮግራሙ ያቀረበበት አቀራረብ አስደናቂ ነበር።
ፕሮግራሙን ከእዚህ በታች ባለው ሊንክ ተጭነው ይመልከቱት።
http://ethsat.com/video/waza-ena-kumneger-oct-20-2013/

Saturday, October 19, 2013

በቤተ ክርስቲያን ላይ የአስተዳደር፣ የፍትሕና የጸጥታ አካላት የሚፈጽሟቸው በደሎችና ተጽዕኖዎች – የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ትችት፣ ጥያቄና ምስክርነት ሙሉ ቃል


ምንጭ - ሐራ ዘተዋህዶ
http://haratewahido.wordpress.com/2013/10/18/በቤተ-ክርስቲያን-ላይ-የአስተ/#more-2179
የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ፴፪ኛ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ‹‹የሃይማኖት መቻቻል›› በሚለው መርሐ ግብር ‹‹የብዝኃነት አያያዝ፣ አክራሪነት/ጽንፈኝነት ዝንባሌዎቹና መፍትሔዎቹ›› በሚል ርእስ አቶ ገዛኸኝ ጥላሁን፣ አቶ ታዴዎስ ሲሳይ እና አቶ ጣሰው ገጆ በተባሉ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሦስት ከፍተኛ አማካሪዎችና ባለሞያዎች ጽሑፍ መቅረቡና ውይይት መካሄዱ ተዘግቧል፡፡

በውይይቱ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ከየአህጉረ ስብከታቸው ተጨባጭ ኹኔታ በመነሣትና ጽሑፉ በቀረበበት ይዘቱ በመገምገም በተለይ በመቻቻል፣ በመንግሥትና ሃይማኖት ግንኙነትና በኢትዮጵያ የክርስትና ታሪክ ዙሪያ ጥያቄ አንሥተዋል፤ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ቃል በተነገረበት አኳኋን ወደ ጽሑፍ ተመልሶ ቢቀርብ በተለይ በስፍራው ላልነበሩና በሌሎችም መንገዶች ለመከታተል ዕድል ላላገኙ ወገኖች ይጠቅማል በሚል በጡመራ መድረኩ ተስተናግዷል፡፡

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ በጉዳዩ ላይ የሰነዘሩት ትችት፣ ያቀረቡት ጥያቄና የሰጡት ምስክርነት በሁሉም የዓመታዊ ስብሰባው ተሳታፊዎች ዘንድ ቤተ ክርስቲያናችን የመንግሥትን ተቋማት በሚመሩ ዓላውያንና መናፍቃን ጫናዎች መማረሯን ከመግለጽ ባሻገር በደሎችና ተጽዕኖዎች እስካልተወገዱ ድረስ መጪውን የከፋ አደጋ የጠቆመችበት፣ የመንግሥቱንም ተወካዮች በብርቱ የመከረችበት ታሪካዊ አጋጣሚ ስለመኾኑ ከፍተኛ መግባባት ተደርሶበታል፡፡

ይልቁንም የውይይቱ ቁም ነገሮች፣ መንግሥት የፀረ አክራሪነት እንቅስቃሴዎቹን በሚያብራራባቸው ሰነዶቹ እንደሚያትተው፣ በፕሮቴስታንት ሃይማኖት ሽፋን የጠባብነት አመለካከት ፖሊቲካ ከሚያራምዱ አካላት ጋራ ትስስር መፍጠሩና ሽፋን መስጠቱ፣ ‹‹ከማቆጥቆጥና አዝማሚያነት›› አልፎ በገሃድ መገለጹን የሚያረጋግጡ ናቸው፡፡ ‹‹የመልካም አስተዳደርና ሴኩላሪዝም ጥያቄን እንደ መንሥኤ ወስዶ ሕዝብን የጽንፈኝነት አመለካከት በማስያዝ›› ሰላማዊ መስተጋብሩን የማናጋት ሙከራው ለማቃናት አዳጋች ወደሚኾንበት ዳርቻ እየነጎደ መኾኑን ነው፡፡ ስለዚህም ‹‹ለመንግሥት መዋቅር የሚቀርቡ ጥያቄዎች ከአድሏዊ አሠራር በጸዳ መልኩ እንዲሰጡና ፍትሐዊ ጥያቄዎች አለምንም ማጉላላት እንዲፈጸሙ ጥብቅ ክትትል እንዲደረግ›› በቃል የሰፈረው በተግባር ተተርጉሞ መታየት ይኖርበታል፡፡

ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ

የሰሜን ወሎና ዋግ ኽምራ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤

ስላስተማሩን እናመሰግናለን፡፡ እንግዲህ ቤተ ክርስቲያኗ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የምትነፍገው ነገር የለም፤ ያላትን ሁሉ ታበረክታለች፤ ታገለግላለች፡፡ አክራሪነት፣ ጽንፈኝነት የሚለውን ቋንቋ እናንተ ናችኹ ያስተዋወቃችኹን፤ እናንተው ናችኹ ያሰማችኹን፤ ከዚያ በፊትም አይታወቅም፤ በደርግም ይኹን በሌላ፡፡ እንደገና ደግሞ ብዙ ጊዜ ጽንፈኝነት፣ አክራሪነት እያላችኹ ዕድሜ ሰጥታችኹ ያበለጸጋችኋቸው እናንተው ናችኹ፡፡

አባቶቻችን፣ የእረኛ ሰነፍ ከቅርብ ሲሉት ከሩቅ ይላሉ፡፡ ወዲያው በአጭሩ መቅጨት ሲገባ ታሪካቸው እየተተረከ፣ እየተተረከ፣ እየተተረከ ብዙ ሕዝብ አተራመሱ፡፡ አዎ፣ ጥያቄዬ÷ ‹‹መረባቸውን በላይ ዘርግተዋል፤ መሬት ግን አልነኩም፤›› አሉ፡፡ እንዴ፣ ነክተው አይደለም ይህ ሁሉ የሚተራመሰው! መረባቸውንማ መሬት ዘርግተው ሕዝብ መካከል ገብተው፣ ሙስሊሙ ሕዝብ እንኳ ‹‹እኛ አናውቃቸውም፤ የእኛ አይደሉም›› እያለ እየጮኸ፣ እየጮኸ መረባቸውንማ መሬት አስነክተው ወጣቱን ትውልድ የመረዙት እነርሱ ናቸው፡፡ እንዴት መሬት አልነኩም፤ መረባቸው ወደ ላይ ነው ይላሉ? እንደ እናንተ መረባቸው መሬት ሲነካ እንዴት ሊያረጉን ይኾን?

ሁለተኛ ጥያቄዬ፣ ‹‹መሬትም ሕዝብም የነገሥታቱ ነበር›› ብለዋል፡፡ አሁንስ የማን ነው? ይልቁንም ከአንድ ቤት ‹ግድግዳው የቤቱ ባለቤት ነው፤ ሳሎኑ የመንግሥት ነው› የሚለው ዐዋጅ የአሁን አይደለም እንዴ? ለኢትዮጵያዊነቱ ዋስትና የለውም፤ ይኼ የእኔ ነው የሚለው ከሌለ ምንድን ነው? ይህች የእኔ የኢትዮጵያዊነቴ መገለጫ ናት ካላለ ምንድን ነው ኢትዮጵያዊነት? አሁንም መሬቱም ሕዝቡም የእናንተው ኹኖ ሳለ ለፊቱ፣ ለነገሥታቱ መስጠታችኹ በምን ተመልክተውት ነው?

ሌላው፣ ተቻቻሉ፣ ተቻቻሉ. . .እንዴት ነው መቻቻል? እስከ ምን ድረስ ነው መቻቻል? መቻቻል ጥሩ ነው፡፡ እንደውም ከዚያ በላይ ነው የእኛም የሚያውጀው፡፡ ይህን ጉንጭኽን ቢመታኽ ይህን ስጠው፤ ይህም ለማንም ወንበዴ ሳይኾን የቤተሰብ ግጭት እንዲያልፍ ነው፤ ከወንድምኽ ጋራ ያልፋል ጠቡ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ መለስ÷ ‹‹ማንም ሰው እኔን መላጣ ብሎ መሳደብ ይችላል፤ መላጣውን ግን መንካት አይችልም፤›› ነው ያሉት፡፡

እንዴ! በእውነቱ ለምሳሌ፣ አንድ ሙስሊም ሙተዋል በደቡብ ወሎ፡፡ በጠቅላላ፣ ሴቱም ወንዱም በሰላማዊ ሰልፍም በሁሉም ነገር ጩኸቱን ሲያሰማ ቆይቷል፡፡ በእኛ ቤተ ክርስቲያን ግን ብዙ ሰዎች ታርደዋል፤ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል፤ ነገር ግን በማስ ሚዲያ እንኳ እንዳይነገር ነው የተደረገው፡፡ እዚያው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዳሉ ቤተ ክርስቲያኑም ተቃጥሎ ሰዎቹም በቢላዎ ታርደው በማስ ሚዲያ እንኳ እንዳይሰማ ተደርጓል፡፡ አሁን ወለጋ ያለው አካሄድ፣ ሂደት መንግሥት በአገሩ ያለበት ይመስላል እንዴ! በእውነቱ፣ እንችላለን፤ ነገር ግን አንድ ሰው እግሩን እሳት እየበላው ቻል ይባላል? እሳት እያቃጠለው? እንድንቻቻል አድርጉን፤ እንችላለን፡፡ እግዚአብሔር ይስጠልኝ፡፡



ብፁዕ አቡነ ኄኖክ

የምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋና አሶሳ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤

ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን፣ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፤ የዚህ ታላቅ ታሪካዊ ጉባኤ ተሳታፊዎች በሙሉ፣ ስለተፈቀደልኝ አመሰግናለኹ፤
በዛሬው ዕለት በዚህ ታላቅ ጉባኤ ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ትምህርት ለመስጠት የመጣችኹ እንግዶቻችን እናመሰግናለን፡፡

በምዕራብ ወለጋ ሀ/ስብከት በሦስት ወረዳዎች የደረሱብን ተጽዕኖዎችና በደሎች እናንተን ስለሚመለከት ማስታወሻ ይዛችኹ ለሚመለከተው የበላይ አካል እንድታሳውቁልን ለማሳሰብ ነው፡፡ ጉዳዩ በትላትናው ዕለት ለአጠቃላይ ጉባኤው ባቀረብነው የሀ/ስብከታችን ሪፖርት በሰፊው ተነሥቷል፤ ሰዓት እንዳልሻማ በአጭሩ ለመግለጽ እሞክራለኹ፡፡

በምዕራብ ወለጋ ነጆ ወረዳ ከዐሥር በላይ የፕሮቴስታንት ጸሎት ቤቶች አሉ፡፡ የሙስሊም አምስት መስጊዶች አሉ፡፡ የእኛ ቤተ ክርስቲያን ሁለት ብቻ ነው ያለው፡፡ ሦስተኛ ቤተ ክርስቲያን ለመሥራት ለማዘጋጃ ቤት ወረዳ ቤተ ክህነቱ ጠይቆ ተፈቅዶላቸው፣ ቤተ ክርስቲያን ሠርተው፣ ጉልላት አስቀምጠው ከጨረሱ በኋላ አፍርሱ የሚል ጥያቄ ተነሣ፡፡ ወደ ስድሳ የሚኾኑ ምእመናን አናፈርስም ብለው በመቃወማቸው ግብግብ ተፈጠረ፤ ስድሳዎቹንም አሰሯቸው፡፡ ከስድሳዎቹ ምእመናን ሁለቱ የመንግሥት አካላት ነበሩና ‹‹ባለሥልጣናትን ደፍሯችኋል፤ ሰድባችኋል›› በሚል በዐቃቤ ሕግ ተመስክሮባቸው ወደ ሦስት ዓመት እንዲታሰሩ ተወስኖባቸው ነበር፡፡ በአካል ወደሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ቀርበን ከጠዋቱ 4፡00 – 11፡00 በመጨቃጨቅ ሁሉም እንዲፈቱ አድርገናል፡፡

ይኹንና ከዚህም በኋላ ‹‹ቤተ ክርስቲያኑ መፍረስ አለበት›› የሚለው አቋም ቀጠለ፡፡ እኛም እየተከራከርን ጉዳዩ በፍ/ቤት ተይዞ ነው ያለው፡፡ ምንድን ነው ለማሳሰብ የምፈልገው÷ እዚያ ያሉቱ ባለሥልጣናት፣ ከቀበሌ እስከ ወረዳ ያሉ ባለሥልጣናት ተባብረው ‹‹ካቢኔ አልወሰነም›› በማለት ነው ቤተ ክርስቲያኑ እንዲፈርስ ውሳኔ ያስተላለፉት፡፡ በዚህ ተጽዕኖ በሕዝባችን ላይ የሥነ ልቡና ጫና እየደረሰ ነው፡፡ የመንግሥት አካላት ኾነው ይህን በማድረጋቸው አዝነናል፡፡ ገዳዩ በፍ/ቤት ተይዞ ስላለ ይህን ለሚመለከተው ክፍል እንድታሳውቁልን ነው፡፡

ሁለተኛ፣ ባቦ በተባለው ወረዳ በቤተ ክርስቲያን ዕጣን አዙር መሬት ላይ አንድ ካህን እርሻ እያረሱ፣ ለእርሻ የሚገባውን ሥራ እየሠሩ እያለ የወረዳውን የጸጥታ ዘርፍ ሓላፊና ፖሊሶችን ይዞ ካህኑን በሰደፍና በዱላ ከመደብደብም አልፎ፣ ‹‹ይህን አገር ጠዋት ለቀኸ ውጣ! ይህች አገር የነፍጠኛ አገር አይደለችም፤ ይህ የኦሮሚያ ክልል ነው›› በሚል ደብድበዋቸው፣ በቤተ ክርስቲያኑ አካባቢ ያሉትን ምእመናንንም ‹‹ቤተ ክርስቲያን ልትሠሩ ያሰባችኁበት ቦታ የቱ ነው? ይህን ዐውጡ›› ብለው ወደ ሦስት የሚደርሱ ምእመናንን ይደበድቧቸዋል፡፡ ሁለቱ ሮጠው አመለጡ፤ አንዱ ሽማግሌ ነበሩና ይዘው አንበርክከው፣ ‹‹ፀሐይን ትክ ብለኽ ተመልከት›› ብለው ለ15 ደቂቃ ያህል አሠቃዩዋቸው፡፡ በዚህ የተነሣ ባለቤታቸው ደንግጠው ወድቀው በሦስተኛው ቀን ዐረፉ፡፡ ይኼ ቤተ ክርስቲያን ለምን ትሠራላችኹ በሚል በምእመኖቻችን ላይ የደረሰባቸው በደል ነው፡፡

ሌላው በሰንበት ቀን፣ ‹‹ካህኑ ቀዳሹ ብቻ ይቅር፤ እናንተ ውጡ፤ ሥሩ!›› ብለው በሰንበት ቀን እርሻ እንዲያርሱ ያደርጓቸዋል፡፡ በቅዱስ ሚካኤል ቀን፣ በሰንበታት ቀን በቤተ ክርስቲያን በጸሎት ላይ ያሉ ምእመናን እንዲወጡ እየተገደዱ ብዙ ተጽዕኖ እየደረሰብን ነው ያለው፡፡ ይህን የሚያደርጉ የመንግሥት አካላት ናቸው፡፡ ከቀበሌ ጀምሮ በሃይማኖት ተጽዕኖ በሕዝባችን ላይ የሥነ ልቡና ጫና እያደረሱ ነው፡፡ ከብዙ በጥቂቱ እንጂ በዚህ ወረዳ ላይ አያሌ ግፍ ነው የተሠራው፡፡ በ፳፻፭ ግንቦት/ሰኔ እቦታው ድረስ ከዞኑ ባለሥልጣናት ጋራ ሄደን፣ የማጣራት ሥራ ሠርተን አሁን ጉዳዩ በፍ/ቤት ተይዞ ነው ያለው፡፡ ሰዎቹ ለፍርድ ቀርበዋል፤ መቼ እንደሚፈረድ ባናውቅም፡፡

በሦስተኛ ደረጃ፣ ቤጊ የሚባል ወረዳ አለ፡፡ ቤጊ ወረዳ ከምዕራብ ወለጋ ወደ 250 ኪ.ሜ ነው ርቀቱ፡፡ እዚያ አካባቢ ሙስሊሞች ናቸው የሚበዙት፡፡ ያሉት ምእመናን ጥቂቶች ናቸው፡፡ በቤተ ክርስቲያን አካባቢ በቅርብ ርቀት፣ 70 ሜትር ርቀት ላይ ‹‹ቤተ ክርስቲያን ፈቅደናል›› በሚል ለመካነ ኢየሱስ ቸርቻቸውን እንዲሠሩ ፈቀዱላቸው፡፡ ሕዝቡ አይሠራም ብሎ ለተቃውሞ ወጣ፡፡ ከእነርሱም ውስጥ አንድ ዲያቆን ተደብድቦ በሦስተኛ ቀኑ ነው ያረፈው፤ የዛሬ ሁለት ዓመት፡፡ ‹‹በወባ በሽታ ነው የሞተ›› ተብሎ በፍርድ ቤቱ የሐሰት ማስረጃ ከዶክተሩ ታዘዘ፡፡

የዞኑን የሰላምና ጸጥታ ዘርፍ ሓላፊ ሀ/ስብከቱ፣ እኔም ባለኹበት ሔደን እንዲጣራ ተደርጎ በገደሉት ሰዎች ላይ ከአራት እስከ ሰባት ዓመት ተፈርዶባቸዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ነገሩ ሥር እየሰደደ ከሁለት ዓመት በኋላ፣ በ፳፻፭ ዓ.ም ለሰውዬው ብር ሰጥተውት ‹‹መሬቱን ከግለሰብ ገዝተናል፤ የእኛ መሬት ነው፤ እዚህ ላይ ቸርች መሥራት አለብን›› ብለው ሁለተኛ ቅሰቀሳ ጀመሩ፡፡ ሕዝቡ፣ ‹‹በሕግ አምላክ! የዛሬ ሁለት ዓመት ልጃችን ሞቷል፤ አሁንም ደም መፋሰስ ይመጣል፤ እዚህ አትሠሩም›› ብለው ሲከላከሉ እዚያ ያሉት የሰላምና ጸጥታ ዘርፍ ሐላፊ ‹‹መሠራት አለበት›› እያለ ሕዝቡን አስፈራርቶ፣ ከ70 ምእመናን በላይ ለኻያ አራት ሰዓት አስሯቸዋል፤ በበዓል ቀን ተይዘው ወደ ዞኑ ማረሚያ ቤት ወርደው አድረዋል፡፡ የሚመለከታቸውን አካላት፣ ይህ ነገር ትክክል አይደለም ብለን አስፈትተናቸው ቦታው ለእኛ ተወስኖ፣ ለእነርሱ ሌላ ቦታ ተሰጥቶ ሰላሙ ወርዷል፤ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡

ሌላው ግምቢ እና መንዲ ላይ በትምህርት ቤት ከልጆቻችን አንገት ላይ ማዕተባቸውን፣ መስቀላቸውን እየበጠሱባቸው ነው፡፡ ይህን የሚፈጽሙት መምህራን ናቸው፡፡ ወደ ዞን ሄደን ከሠናል፡፡ ስንከሥ ‹‹ከላይ መምሪያ ተላልፎ ነው፤ በሸሪዓ ሕግ ሴቶች ራሳቸውን እንዳይከናነቡ፣ ክርስቲያኖች ደግሞ በአንገታቸው ማዕተብ፣ መስቀል እንዳያስሩ ከላይ መንግሥት መመሪያ አስተላልፎልናል፤ ስለዚህ መስቀል ማሰር አይቻልም›› እያሉ ከአንገታቸው በጣጥሰውባቸዋል፡፡ ፖሊሶች ሳይቀሩ ከአምስት ልጆች ጋራ ከአንገታቸው ማዕተብ ከመበጠስ አልፎ ደብድበዋቸው የማጣራት ሥራ ስንሠራ ከሁለቱ ሳጅኖች አንዱ የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታይ ኾኖ ነው የተገኘው፡፡

እንዲህ፣ እንዲህ ያለ በደልና ተጽዕኖ እየደረሰብን ነው፡፡ ‹አገሩ የፕሮቴስታንት አገር ነው፤ ለእነርሱ ብቻ ነው የሚፈቀደው የተባለ ነው፤› የሚመስለው፡፡ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አታስፈልግም የተባለ ስለሚመስል አፋጣኝ መፍትሔ እንፈልጋለን፡፡

ከተሰጠው ትምህርት ያልገባኝ፣ ክርስትና በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወደ ኢትዮጵያ ገባ የሚል ትምህርት ሰጥተዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ግን በ፴፬ ዓ.ም. በጃንደረባው አማካይነት ክርስትናን እንደተቀበለች ነው የምታምነው፤ የምታስተምረው፡፡ በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ግን አባ ሰላማ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ክርስትናን ያስፋፋበት ነው እንጂ የገባው በ፴፬ ዓ.ም. ነው፡፡ የተናገሩት ነገር ከቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ጋራ ይጣረሳል፡፡ ከምን አንጻር ነው የተናገሩት?



ብፁዕ አቡነ ኤልያስ

የጋሞጎፋና ደቡብ ኦሞ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤

ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጉባኤው ተሳታፊዎች፣ በዕለቱ ከመንግሥት ለውይይት ተወክላችኹ የመጣችኹ፤
ርእሳችን መቻቻል ነው የሚለው፡፡ ከዚህ በፊት ክቡር ዶ/ር ሽፈራው በቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ መጥተው ብዙ ነገሮችን አስጨብጫቸው ነበር፡፡ ምላሹን ግን እስከ አሁን አላገኘንም፡፡ ያን ደግሜ ለማንሣት እገደዳለኹ፡፡ ጉዳዩን እናንተ እንድትሰሙት ለማለትና ሐዘናችንን ጉባኤው መስማቱ አስፈላጊ ስለኾነ እንጂ የጋሞጎፋ ዞን መስተዳድር ባለሥልጣናቱ በሙሉ ከእኛ ጋራ እየረዱን ነው ያሉት፡፡ ችግሩ ወረዳዎች ላይ ነው ያለው፡፡ ዞኖቹ አያዝዙንም እስከ ማለት የደረሱ የመንግሥት ወረዳ ባለሥልጣናት ስላሉና ይህም በብዙ ቦታ የሚያጋጥም ችግር በመኾኑ እንዲታይ ነው፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ፣ በዚህ በመስከረም ወር በኢትዮጵያ ምድር ላይ ተደርጎ የማይታወቅ በሀገረ ስብከታችን የተፈጸመ በጣም አሠቃቂ ጉዳይ ገጥሞናል፡፡ በበቶ ወረዳ በዑባ ደብረ ፀሐይ ለብዙ ዓመታት ሕዝቡ ሲያከብርበት በኖረው ቦታ ላይ ምትክ ቦታ ሳይሰጥ ቦታው ለመናኸርያ ተሰጥቶ፣ ሱቆች ተሠርተውበት ሌላ አገልግሎት ተጀምሮበታል፡፡ ቦታው እንኳ አስፈላጊ ኾኖ ቢገኝ ለልማት እንደሚያስፈልግ ሕዝቡን አወያይቶ በመግባባት፣ ትክ ቦታ ሰጥቶ በመኾን ሲገባው ኻያና ሠላሳ ዓመት ከዚያም በላይ ደመራ ሲለኮስበት የነበረበትን ቦታ ለሌላ ሰጥተው፣ አምናም በጭቅጭቅ ነበር የተከበረው፣ ዘንድሮም በበቶ ወረዳ ዑባ ደብረ ፀሐይ ሕዝቡ የደመራን በዓል ሳያከብር ነው የዋለው፡፡ ይህ ለቤተ ክርስቲያናችን ከባድ ሐዘን ነው፡፡

በሀገራችን ታሪክ ስናነብ ጦርነትም ቢኾን የደመራ በዓል ሳይከበር እንደዋለ ያጋጠመን ርእስ የለም፡፡ ይህ የተፈጸመው በወረዳው ባለሥልጣናት በውይይት ያልተደገፈ አላስፈላጊ ጥናት፣ ዞኑ በደብዳቤ መመሪያ ቢሰጥ ሊቀበሉ ባለመቻላቸው ሕዝቡ የደመራን በዓል ሳያከብር በቤቱ እያለቀሰ፣ እያዘነ ነው የዋለው፡፡ ይህ እንዴት ይታያል? መቻቻል የሚለውን መንግሥት ይሰብካል፤ መንግሥት የመደባቸው ሰዎች ደግሞ መቻቻልን እያበላሹ፣ እያጠፉ ይገኛሉና ሊጠና የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡

በሁለተኛ ደረጃ፣ ለክቡር ዶ/ር ሽፈራው የነገርኋቸው፣ ዋጂፎ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ቦታን አስቀድሞ የእኛ እምነት ተከታይ የነበሩ ሰዎች የቤተ ክርስቲያኑን መሬት ይዘው ያገለግሉ፣ ይሠሩ ነበር – ሰበካ ጉባኤ በመኾን፣ ኮንትራት አርሰን እናስገባለን በማለት ቦታው ይዘው ሲያበቁ በመጨረሻ ሃይማኖታቸውን ወደ ሌላ ቀይረው ቦታውን እንዳለ ወስደውታል፡፡ እነኚህ ግለሰቦች በየግላቸው ከአንድ ሰው በቀር በከተማው ውስጥ የየራሳቸው ቦታ አላቸው፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱን ቦታ በተጨማሪ በመውሰድ ክሥም ቢከሠሥ ፍ/ቤቱ ለእነርሱ ነው የፈረደው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ስለ መሬቱ ይዞታ ባለቤትነቷን በሕግ ያረጋገጠችበት ደብዳቤ እያላት ፍርድ ቤቱ ለእነርሱ ነው የፈረደው፡፡ እንደገና በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ለክልሉ ደብዳቤ ጽፈን ትእዛዝ ደርሶ ቦታው ተጠንቶ እንዲመለስልን ቢወሰንልንም እስከ አሁን አልተመለሰም፡፡ ይኼ በጣም አስቸጋሪ ነገር ነው፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ ልትፈርስ ነው፤ የእኛኑ ቦታ ከልክለውን፣ ሌላ ቤተ ክርስቲያን መሥሪያ ቦታም አጥተን እየተገፋን ከባድ ችግር ላይ ነው ያለነው፡፡ ይህ ሊጠና ይገባዋል፡፡

በተጨማሪ መቻቻል የሚለውን ቤተ ክርስቲያናችን ጌታ ባስተማረው ወንጌሉ መሠረት ጠንቅቃ ታውቀዋለች፡፡ ዛሬ አይደለም መቻቻልን የምታውቀው፡፡ ጌታ በወንጌሉ÷ ስንዴ ተዘርቶ ነበር፤ በስንዴው መካከል እንክርዳድ ተገኘ፤ መላእክቱ ወረዱና እንክርዳዱን እንንቀለው አሉ፤ ኅቡረ ይልሐቊ፤ እኔ በአዝመራ ሰዓት ስንዴውን ለብቻ እንክርዳዱን ለብቻ እለየዋለኹ ነው ያለው ጌታ፡፡ ቤተ ክርስቲያን መቻቻልን የምታውቀው በዚህ ነው፡፡ የመቻቻል መሥመራችን ይኼ ነው፡፡

ዘንድሮ በአርባ ምንጭ ሴቻ ከተማ ባልተፈቀደ ቦታ ላይ ስምንት ቀን የሚፈጅ ጉባኤ ተዘጋጅቶ÷ ጉባኤው ያድርጉ እኛ አንቃወምም፤ ግን በጉባኤው ላይ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ብሎ ማንሣት፣ ጽላቱን፣ መላእክቱን፣ ቅዱሳኑን እያነሡ መቃወም ይኼ ሌላ ክብሪት ነው፤ ነዳጅ የተርከፈከፈበት ክብሪት ማለት ነው፡፡ እንዴት ነው መቻቻል የሚባለው ነገር? ሕዝባችን የተቃውሞ ሰልፍ እንድንወጣ ጠየቀን፡፡ አንወጣም፤ በሕግ ነው የምንጠይቀው፤ አገራችንን እንወዳለን፤ ልማታችንን እንወዳለን፤ ሰላምችንን እንወደዋለን በማለት ሕዝቡን ከልክለነዋል፡፡ አሁንም በሕግ ለመጠየቅ ተዘጋጅተናል፡፡ እኛ ጉባኤውን አይደለም የምንቃወመው፤ ሺሕ ጊዜ ይደረግ አንቃወምም፡፡ የእኛን ስም ማንሣት ምን ማለት ነው? ‹‹ከኦርቶዶክስ ይህን ያህል ሺሕ ሰው የዛሬ ዓመት ይመጣል›› አሉ፡፡ መቻቻል ማለት ይኼ ነው እንዴ? ሊታሰብበት የሚገባ ነው፡፡ እኛ የማንንም መብት አንነካም፤ ስንነካ ግን አቤቱታችንን እናቀርባለን፤ አትንኩንም እንላለን!!

ብዙ ፈተና ነው ያለው፤ ‹‹የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ይህን ሁሉ ቦታ ይዛ. . .›› እያሉ እንደውም የወረዳ ተሿሚዎቹ እንዴት መሰላችኁ የሚያዩት÷ እንደ መበቀል፣ ቤተ ክርስቲያኗ ፊውዳል ኾና ሕዝቡን፣ አገሩን ስትበድል እንደቆየች አድርገው የሚያዩ ሰዎች አሉ፡፡ ‹‹ይህን ሁሉ መሬት ለኦርቶዶክስ ማን ነው የሰጠው? ሂዱ ቁረሱና በኦርቶዶክስ ቦታ ላይ ጉባኤ አድርጉ!›› እያሉ ሕዝቡ እርስ በርሱ እንዲጋጭ፣ እንዲጣላ ይገፋፋሉ፡፡ የጋሞጎፋ ዞን ግን በብልህ አስተዳደር ስለሚመራ ብዙ ችግሮቻችንን ፈተውልናል፤ ይህንንም እናንተ እንድትሰሙት ነው፡፡ ተዉ እንድትሏቸው፣ መሥመር ይዘው እንዲኖሩ፡፡

እኛ ማንንም አልነካንም፤ ሲነኩን ግን አቤቱታችንን እናቀርባለን፤ አትንኩንም እንላለን፡፡ ሰላማችንን፣ ልማታችንን፣ አገራችንን እንወዳለን፡፡ ይህ በጥንቃቄ እንዲታይ ነው፡፡ እንግዲህ እናንተንም እጠብቃለኹ፡፡ ይህን ጥያቄ ይዛችኹ ሄዳችኹ የተነጠቀው የቤተ ክርስቲያኗ ቦታ በቀጣዮች ዐሥር፣ ዐሥራ አምስት ቀናት እንድንረከብ ታደርጉ ይኾናል፡፡ እግዚአብሔር ይስጥልኝ፡፡



ብፁዕ አቡነ ያሬድ

የሶማሌ(ጅግጅጋ) ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤

ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጉባኤው ተሳታፊ አባላት በሙሉ፤

ብፁዕ አቡነ ያሬድ

ቅድም ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሲብራራ እንደነበረው፣ ከአራቱ ክልሎች አንዱ የሶማሌ ክልል ነው፡፡ ክልሉ ዘጠኝ ዞን ያለው፣ ብዙ ወረዳዎች የሚገኙበት ክልል ነው፡፡ ከዞን ጀምሮ እስከ ታች ቀበሌ ድረስ የመንግሥት ት/ቤቶች፣ ሆስፒታል፣ ቴሌ፣ መብራት ኃይል፣ ባንክ የመሳሰሉት በሙሉ የሚሠሩ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ ምእመናን አሉ፡፡ ለእኒህ ምእመናን ሁሉ በክልሉ ያሉት አብያተ ክርስቲያናት አምስት ብቻ ናቸው፡፡ የምንጮኸበትም ቦታ የለም፡፡ መንግሥትም ያን አገር ያዝበታል ወይ ለማለት፣ ጥያቄው መልስ ቢያገኝም ባያገኝም እኔ የምጠይቀው፣ ምእመኖቻችን በየዞኑ ላይ፣ በየወረዳው ላይ ቤተ ክርስቲያን እንዲተከል ጥያቄ አለ፡፡ ከወረዳ ጀምረን እስከ ክልሉ መስተዳድር ድረስ ብንከሥም ብንጮኸም፣ የመጨረሻ ውሳኔ ዐጣንም አገኝንም ፌዴራል ሠበር ላይ ነው፡፡ እስከ ክልሉ መስተዳድር ድረስ መዋቅሩ የእነርሱ ነው፡፡ አቤት የምንልበት፣ ቦታ የምንመራበት፣ ያለንን ይዞታ የምናስከበርበት፣ የምእመኖቻችንን ጩኸት የምናሰማበት ቦታ የለም፡፡

ባለፈው ዓመት ግንቦት፣ በኦጋዴን ዞን አንድ በጎ አድራጊ ምእመን ‹‹ቤተ ክርስቲያንን ትረዳለኽ›› ፖሊሱ የመኪና አገልግሎት ስጠኝ ብሎት አሳፍሮት ይዞት ሔዶ ከመሥሪያ ቤቱ ካደረሰው በኋላ ‹‹ገጭተኸኛል›› በሚል ሰበብ ወዲያውኑ ወደ ዞኑ ፍ/ቤት አቅርቦት ብር 280,000 አስፈረደበት፡፡ አገልግሎት ስለ ሰጠው ብቻ፣ ያለ ምንም ማስረጃ ገጭተኸኛል በማለት ብቻ!! በአካባቢው አቤት የምንለው፣ የምንጮኸው ወደ መከላከያ እንጂ ሌላ አካል ፍጹም የለም፡፡ ወደ መከላከያ ጮኸን አንድ ጄኔራል መኰንን ነገሩ በሽምግልና የሚፈታበት መንገድ ቀይሰው ከብር 280,000 ወደ ብር 15,000 ወርዶ ክፍያው እንዲፈጸም ተስማማ፤ በጎ አድራጊው ሰውዬ ይግባኝ ቢጠይቅ እስር ቤት አስገቡት፡፡ በፌዴራል በኩል አቤቱታ አቅርበን በሁለተኛው ቀን ክፍያው ተፈጽሞ ሰውዬው ነጻ ወጡ፡፡

አሁንም በብዙ ቦታዎች ምእመኖቻችን ክርስትና የሚነሡበት፣ ቅዱስ ሥጋውን ክብር ደሙን የሚቀበሉበት ቤተ ክርስቲያን ከአንድ ዞን ወደ ሌላው በጣም ረጅም ርቀት ስላለው ፍጹም አዳጋች ነው፡፡ ምእመኖቻችን እምነታቸውን እየጠበቁ ያሉት በዚሁ በካሴት፣ በዘመናዊ መሣርያ ካልኾነ በቀር በእኛ በካህናት በኩል ተንቀሳቅሰን አገልግሎት የምንሰጥበት መንገድ ፍጹም የለም፡፡ በሶማሌ ክልል በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ላይ ያለው ተጽዕኖ ከሳዑዲ ዐረቢያ የሚበልጥ እንጂ ያላነሰ ኾኖብናል፡፡

በዘጠኙ ዞኖችና ወረዳዎች ላይ ያጠናናቸው ቦታዎች አሉ፤ የምእመናኑን ብዛት፣ የሚያስፈልገውን የጸሎትና የመካነ መቃብር ቦታ ለይተን አጥንተናል፡፡ ይህ በክልሉ መንግሥት በፍጹም መፍትሔ አያገኙምና ይህ በፌዴራሉ መንግሥት በኩል እንዴት ይታይልናል? ጥያቄዬ ይህ ነው፤ የሚመለከተው ክፍል መልስ እንዲሰጠን አሳስባለኹ፡፡ እግዚአብሔር ይስጥልኝ፡፡


ብፁዕ አቡነ ማርቆስ

የምሥራቅ ጎጃም ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤

ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ መላው የጉባኤው ታዳሚዎች፣ ለውይይቱ ምክንያት የኾናችኁ የመንግሥት ልኡካን

ብፁዕ አቡነ ማርቆስ

እኔ የምጠይቀው ዋና ጥያቄ ነበረኝ፤ ታሪክ ላይ፣ ዓመተ ምሕረት ላይ ነበር፤ ተመልሷል፡፡ የኾነው ኾኖ ለሌላው ቀንም መቼም ታሪክ ክፉ ይኹን ደግ እንደዚያው እንደ ታሪኩ ነው የሚተረክ፡፡ እና በመጀመሪያ ለዚህ ታሪክ ወንድማችን [ከዕለቱ የሚኒስቴሩ ተናጋሪዎች አንዱ አቶ ገዛኸኝ ጥላሁን] ይህን ታሪክ ስታቀርብ በዚህ ታሪክ ምን ያህል ላይሰንስ አለኸ? አዎ፣ እውነቴን ነው፤ ነገሮች የሚበላሹ መቼም ከብት ባልዋለበት ኩበት ለቀማ!!

ታሪኩ ሲነገር፣ እንዴ! ኢትዮጵያ ስንልኮ አብራ እዚኹ ናት፤ የሃይማኖቱ መሥራቾች ናቸውኮ፤ ይህን ስንል ሌላ ሰው አይኑር፣ መቻቻል የለም እያልን አይደለም፡፡ ግን አንዳንዴ ስትተርኩ እንዴ፣ መንግሥቱንስ ከምን ተረከባችኹት ያሰኛል፡፡ አገሪቱንስ ከማን ተረከባችኹ? የተሳሳተውን ማስተካከል ዛሬም ነገም ተገቢ ነው፤ ዕድገት ነው፡፡ ግን ልጁ ሁልጊዜ አባቱን እየኮነነ፣ ‹እኔ ከአባቴ በፊት ነበርኹ› የሚለው ታሪክ ምንድን ነው? እንደ ሃይማኖቱ ነው፣ እንደ ሌላው አይደለም፡፡ ስለዚህ ይኼ ክርስትና በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ገባ የሚለው በእውነቱ እንዳይደገም፤ ዛሬ ግራጁዌት አድርጉት፡፡

ብዙ ቦታ ሰምቻለኹ፡፡ ክርስቶስ ዐርጎ ዓመትም አልሞላ፣ ሐዋርያት እዚያው በመዲናው ኢየሩሳሌም እያሉ የብሉይ ኪዳን እምነት ተከታይ ስለነበረች በዓል(የፋሲካን) ልታከብር ሔዳ ያውም ደግሞ ከሰው አይደለም፣ ከራሱ ከእግዚአብሔር ነው፡፡ እንደሌላው አገር የሰባኪ ደም አፍስሳ፣ መምህር ገድላ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ያውም በባለሥልጣኑ በጃንደረባው ነው፡፡ እኔ እንደው አሁን አሁን እየቀፈፈኝ የሄደ ባለሥልጣን አገሩን የሚጠላ ምንድን ነው! በጣም የሚቀፍ ነገር፤ እንዴ! እኛ እኮ ዛሬ ነው የተወለድን፡፡ ስለዚህ ጃንደረባው በዓል አክብሮ ሲመለስ እግዚአብሔር መልአኩን ‹‹ሂድ፣ ተከተለው›› ብሎ መልአኩ ለፊልጶስ. . .በዓለም አቀፉ መጽሐፍ በመጽሐፍ ቅዱስ በሐዋርያት ሥራ ምዕ. ፰÷፳፮ ጀምሮ ተጽፏል፡፡ ይህ ዓለሙ፣ ሳይንቲስቱ ሁሉ ይቀበለዋል፡፡ እናንተስ ለምንድን ነው?

ከብሉይ ኪዳን ጀምሮ እንደው ራስ ወዳድ ያስመስላል እንጂ ከአይሁድ በፊት ነው፡፡ አይሁድነቱን ከአብርሃም በግዝረት ነው የተቀበሉት፡፡ እኛ ከኖኅ ነው፤ የኖኅ የልጅ ልጆች፤ ኖኅ መምለኬ እግዚአብሔር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ይኼ ነው፡፡ ስለዚህ ታሪኩን አታዛቡ ነው! ሲያስፈልግ በእውነቱ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የሠለጠነ፣ ቢቻል የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ የኾነ፣ ስለ ኦርቶዶክስ እምነት የሚያስተምር፣ በጳጳሳቱ ፊት ለመናገር ዕውቀት ያለው መኾን አለበት፡፡ ዐሥር ጊዜ በዲግሪ ቢመረቅ ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ አይኾንም፡፡ ያልኾነ ታሪክ አምጥታችኁ ስትደፉት እንዴት ዝም እንበል? አታስቆጡን!

በተጨማሪ ቱሪዝምን በተመለከተ፣ ይህች ቤተ ክርስቲያን የዚህ ሕዝብ ባለቤት ናት፡፡ ነፍጠኛ ምናምን ስለምትሉት አይደለም፡፡ እርሱ ይሙትም ይኑርም ፈልጉት፡፡ እኛ እያወራን ያለነው ስለ እውነተኛው ነገር ነው፤ እና ቱሪስቱ ዋልድባን ሊጎበኝ ሲሄድ ሙስሊሙ ዋልድባ ሄዶ ስለ ዋልድባ ያወራል፡፡ እንዴ! ምን ጉድ ነው! እንዴት ተደርጎ ይኾናል፤ ለእርሱስ ክብረ ነክ አይኾንም ወይ? መልእክቶች ስለኾናችኁ ይህን ይዛችኁት ሒዱ፡፡ እንዴት አድርጎ ሙስሊሙ ስለ ኢትዮጵያ ገዳማት ይተርካል? ምኑን ያውቀዋል እስኪ? አኹን እኔ ሔጄ ስለ መስጊዱ ተርክ ብባል ውርደት ነው፤ አይገባም፡፡ ቅ/ሲኖዶስ በእውነቱ እዚህ ላይ ደክሟል፡፡ የእኛ ገዳማት በቪዲዮ እየተቀረጹ ገቢው ለሌላ ነው፡፡

በስተቀር መንግሥት ስለ ሰላም፣ ስለ ልማት፣ አንድ ኹኑ የሚለው ምን ችግር አለው፤ እኛ ባለቤቶች ነን፤ ምን ችግር አለ፤ ምንስ አድርጋ? ከእርሷ በኋላ የመጡትን በክብር ተቀብላ ነው ያስተናገደች፡፡ አትጋፋ፣ እንግዳ ተቀብላ፣ እግር አጥባ፣ ሃይማኖትኸ ምንድን ነው አትልም፡፡ ተቀብላ፣ እግር አጥባ፣ ምሳ ራት አብልታ የምትሸኝ ቤተ ክርስቲያን ናት፤ ነገር ግን ልታስተምሩን ስትመጡ ሳብጀክቱን ግራጁዌት እያደረጋችኹ ኑ፡፡



ብፁዕ አቡነ እንድርያስ

የደቡብ ጎንደር ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤


ብፁዕ አቡነ እንድርያስ

በቤተ መንግሥት የወርቅ የብር አገልግሎት የሚሰጥ ዕቃ ብቻ አይኖርም፤ ከዕንጨትም፣ ከጭቃም የተሠራ አገልግሎት ሰጭ ሀብት አለ፤ ይላል ሐዋርያው ሲናገር፡፡ ምን ማለት ነው፣ በቤተ ወንጌል ምእመናን፣ ጻድቃን ብቻ አይኖሩም፤ ወንጀለኞችም አሉ፡፡ በስም የሚጠቀሙ፣ ነግደው የሚያድሩ፣ ቅድም ወንድሜ ተናጋሪው በሃይማኖት ሽፋን እያለ ብዙ ምሳሌዎችን እየሰጠ ቆይቷል፡፡ ይቆይ እንጂ በወሬ ማመን በደል ነው፤ በተግባር ማመን ደግሞ እውነትነት ነው፡፡ ወሬው ያለቦታው እየተወራ አስቸግሮናል፡፡ መንግሥት የራሱ አካሄድ አለው፤ ሲነገር እንደዋለውም ሥልጣኑን ከማን እንደተረከበውም ራሱ ያውቃል፡፡

መንግሥት የሚኖረው በእግዚአብሔር ርዳታ፣ በእግዚአብሔር ሰጭነት ነው እንጂ በራሱ ሥልጣን የለውም፡፡ ይኹን እንጂ ወሬ ያደራጃል፤ ያስጠነቅቃል እንጂ አካልነት የለውም፡፡ ምሁራኑ ይመስክሩ፡፡ ወሬ ያደራጃል፤ ጠላት ወዳጅ ያስለያል፤ ምንነቱን ይገልጣል፡፡ ታማኝነት ያለው፣ በትምህርት ያደገ ሰው አይዋሽም፤ አይዘርፍም፤ አያዘርፍም፤ ሕይወትም አያጠፋም፤ ራሱን ግን ይጠብቃል፤ ሌላውም ራሱን እንዲጠብቅ ይጋብዛል፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ መርሖ ይኸው ነው፡፡ ዘሰ ይትኤገሥ እስከ ተፍጻሜ ውእቱ ዘይድኅን ይላል በሀገሪቱ ቋንቋ፡፡ እስከ መጨረሻው ድረስ የሚታገሥ የሚድን እርሱ ነው፤ ይላል፡፡

ይህን ሁሉ በማለት የተነሣኹት፣ ባለኹበት ሀ/ስብከት ብዙ ችግሮች ተፈጥረው፣ ችግሮቹ መፍትሔ አጥተው ቀርተዋል፡፡ ስድስት አድባራት ተቃጥለዋል፡፡ ያቃጠላቸው አይታወቅም፡፡ ሦስቱ በአንድ አካባቢ፣ ሦስቱ በተራራቀ ኹኔታ በቆላ፣ በደጋ፣ በከተማ አቅራቢያ ተቃጥለዋል፡፡ የዞኑ መንግሥት፣ ክልሉ መንግሥት ቢጮኸለትም አይሰማም፤ መልስም አይሰጥም፤ እንዲያውም ያስተባብላል፡፡

ቅድም ከተለያዩ ሊቃነ ጳጳሳት ሲነገር የነበረው አትንኩን የሚል ነው፡፡ የተበደለ ሰው ሲናገር ፖሊቲካ ተናገረ እየተባለ የውሸት ውሸት ሲያተራምሱን የሚኖሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ ሐቅ ሲወጣ ስውር ነገር የለውም፡፡ አካል ነው፡፡ ቀድሞ የብራና መጻሕፍት፣ የመስቀል ስርቆት ሲያጥለቀልቀው ቆየ፡፡ ዛሬ ደግሞ ወደ ቃጠሎ ተመልሶ ሌትም ቀንም ቤተ ክርስቲያን እየተቃጠለ፣ ምእመናን እያለቀሱ፣ የሚጮኹበት አካል ጠፍቶ፣ የተበሳጨና የነደደው በሃይማኖት ሽፋን እንደተባለው፣ ብዙ መናገር ይቻል ነበር ግን ነፋስ ስለሚወስደው፡፡ ያለው ኹሉ አንድ ቤት ነው፤ በአንድ አቋም ያለ ነው፡፡ ይህ ዘመቻና ቃጠሎ በየኹሉ ይደርሰዋል ብዬ ነው፡፡ ስለዚህ በእኛ ወረዳዎች ስድስት አድባራት ተቃጥለዋል፡፡ ለስድስቱም የሚያጽናናቸው ሰው የለም! መንግሥትም አልጠየቀንም፤ መረጃ ብንሰበስብም እገሌ አቃጠለው የሚል ማስረጃ የለም፡፡ ነገር ግን ሁሉም ጨለማ ለብሶ ነው የሚያቃጥለው፡፡ ሰዓት ጠብቆ ነው የሚያቃጥለው፡፡ ለአቤቱታ ከብዶናል፡፡ ምእመናን እያለቀሱ ይገኛሉ፡፡

እንዴ! የመንግሥት ሥልጣን የተረከቡ ወንድሞች የእኛን አፍ፣ የእኛን አንደበት ብቻ ነው እንዴ የሚጠብቁት? ለሌሎቹ ሞራል ይሰጣሉ ማለት ነው? ጽላቱ ሲሰረቅ፣ መስቀሉ ሲሰረቅ፣ ብራናው ሲሸጥ፣ ሙስሊሞች ሲከብሩበት፣ ቤተ ክርስቲያኑ ተቃጥሎ ዐመድ ሲለብስ፣ የክርስትናው ጥምቀት ሲቀር ምን ይሰማችኋል? ይኼ የሰላም መደፍረስ አይደለም? መቻቻል፣ መቻቻል ትላላችኹ፤ መቻቻል የሚለው አማርኛ ከየት ዘር ነው የወጣው? አማርኛ ነው እንዴ የምታመርቱት? ሐቅ መናገርኮ ኮሶ መቆርጠም ነው፡፡ እኔ በበኩሌ ስለ ከበደኝ፣ እስኪ ዓለም ይወቀው፤ እቢሯቸው ድረስ ሔጃለኹ፣ ጠይቄአለኹ፤ መልስም አላገኘኹም፤ እንዲያውም አንዱ ተቆጣኝ፡፡ ስለ ተቆጣኸ፣ አንተ ተቆጣኸ ብዬ እኔ ዝም አልልም ብዬ ነው የወጣኹት፡፡

ስለዚህ እኛ መመሪያውን እንዲያው ልንገራችኹ፣ እናንተ ከምታስተምሩት ይልቅ ይኸው ዘመን ተቆጥሯል፤ ወደ ዐርባ ዓመት እየተጠጋ ነው፤ በኢትዮጵያ የተገለጸውን ችግር ለመቋቋም ለሕዝቡም ለመንግሥቱም ስናገለግል የምንኖረው እኛው ብቻ ነን – ሐቁን ለመናገር፡፡ እዛው ሥራ መሥራትም ይቻላል፡፡ ቅድም እንደተነገረው አትንኩን ነው እንጂ ተላልፈን የሰው ድንበር፣ የሰው ሥልጣን፣ የሰው ክብር ነክተንም አናውቅም፡፡ ለምንድን ነው ግን በሽፋን የምትጠቀሙብን? መንግሥት እኛን ሽፋን አድርጎ ነው ሲበዘብዘን የምንኖረው፡፡ ሌባውም፣ ቀጣፊውም፣ ሰርጎ ገቡም ሲያጭበረብረን፣ ሲያታኩሰን መንግሥትን ሽፋን አድርጎ ነው፡፡ ይቅርታ አድርጉልኝ፡፡



የወላይታ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ፤

ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን፣ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የዚህ ታላቅ ጉባኤ ዕድምተኞች፤

ወንድሞቻችን ‹‹የሃይማኖት መቻቻል›› በሚል ርእስ ትምህርት አሰምተውናል፤ መልካም ነው፡፡ ነገር ግን እኛን መቻቻል ብላችኹ ከነገራችኹን ከእናንተ ሥር ያሉት ምን እየሠሩ እንደኾን ለመግለጽ ፈልጌ ነው፡፡

በወላይታ ኮንታ ሀ/ስብከት በበዴሳ ወረዳ አንድ የፍርድ ቤት ዳኛ÷ ‹‹ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋራ ቄራ አንካፈልም፡፡ በመሠረቱ ቄራን የምታስተዳድረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሳትኾን ማዘጋጃ ቤት ነው፡፡ በምንም ዐይነት ከኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ጋራ ቄራ አንካፈልም፡፡ ሁለተኛ፣ በትራንስፖርት፣ በመኪና ከኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን እምነት ተከታዮች ጋራ አንሄድም፡፡›› ዳኛው የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ነው፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ ዳኛ ነው፡፡ ሕግ የሚያስተረጉም፣ ጥፋተኛውን በእርምት የሚያስተምር ሰው ነው፡፡ ‹‹እስከ መቼ ድረስ ነው አንገታችኹ ላይ መስቀል የምንታጠለጥሉት›› በሚል እስከ ገጠር ቀበሌዎች ድረስ ኦርቶዶክሳውያንን የማሸማቀቅ ሥራ እየተሠራ ነው፡፡

አሁን እንግዲህ እናንተ እዚህ መቻቻል እያላችኹ ነው፡፡ ዕድር ሙታን የሚሸኙበት የኖረ ማኅበረሰባዊ ተቋም ነው፡፡ ፕሮቴስታንቱ ዳኛ ከኢ/ኦ/ተ/ቤ/ን ጋራ አያስፈልግም በሚል 80 ዓመት የኖረን ዕድር ያስፈረሰ ሰው ነው፡፡ ይህን ጉዳይ ለክልሉ አመለከትን፣ ለዞኑ አመለከትን አጣሪ ተብሎ መጣ፤ የተሰጠ መፍትሔ የለም፤ ሰውዬውም እስከ አሁን በሥራው ላይ ቁጭ ብሏል፡፡ ክርስቲያኖች እየተሸማቀቁ ነው ያሉት፤ ለምን? ግለሰቡ ዳኛ ስለኾነ፡፡ የመንግሥት አካል ስለኾነ፡፡ ይኼ መቻቻልን ያመለክታል ወይ? ዝቅ ብላችኹ ፈትሻችኋል ወይ? ይኼ እንዲሚመስለኝ እግሩን በጅብ እየተቆረጠመ ‹‹ዝም በል፤ ጅብ ነው›› እንዳለው ሰው ያለ ኹኔታ ነው፡፡

ሁለተኛ፣ ከትላንት ወዲያ ወደዚህ ልንመጣ ስንል በደረሰን ደብዳቤ አንድ ካህን፣ አስተዳዳሪ ነው፤ ሕይወቱን የሚመራበት ከቤተ ክርስቲያን ይዞታ ላይ ተቆርሶ ተሰጥቶታል፤ ነገር ግን በውስጥ ግብር ገብሮ ተገኘቷል፡፡ መሬቱን ልቀቅ በሚባል ጊዜ ምንድን ነው ያደረገው፣ ፍርድ ቤት ሄደን ከተካሰሥን በኋላ መጨረሻ ላይ 83,000 ብር ለግለሰቡ ክፈሉ የሚል ውሳኔ ነው የተወሰነብን፡፡ ይኼ ሕዝቡ እየተንጫጫበት ያለ ጉዳይ ነው፡፡ ይህን ሕዝብ እንዲያው ዝም ብለኸ ተቻችለኽ ኑር ማለት እንችላለን ወይ? ለሌሎች የመንግሥት አካላት ብናመለክትም ሁሉም ለግለሰቡ ይከፈል ብለው ነው የፈረዱት፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ ትክፈል የሚባል ከኾነ ታሪክ አይበላሽም ወይ? እንዴት ታዩታላችኹ?

ሦስተኛ፣ ቤተ ክርስቲያኑ ሩቅ ስለኾነ የሥርዐተ ቀብር ማስፈጸሚያ ቦታ ሦስት ዓመት ሙሉ ጠይቀን፣ አስከሬን ይዘን ለቀብር ስንሔድ ውኃ ነጥቆ እየወሰደብን ነው፡፡ ይህን ስንጠይቅ መልኩ ተቀይሮ፣ ‹‹የፖሊቲካ ጉዳይ ነው፤ ሕዝብን በሃይማኖት ሽፋን ታንቀሳቅሳላችኹ›› እየተባልን፣ እየተሸማቀቅን ያለንበት ኹኔታ ነው ያለው፡፡ ይህን እንዴት ታዩታላችኹ? መቻቻልስ የሚመጣው ከምን አኳያ ነው? ዝም ብለን የምንቀመጥ ከኾነ ምናልባት ሓላፊነት ለመውሰድ ስለሚከብደን ይህን ወርዳችኹ እንድትፈትሹ ለማለት ነው፡፡ አመሰግናለኹ፡፡

Friday, October 18, 2013

ትግራይ ኦን ላይን'' በማለት እራሱን የሚጠራው ድህረ-ገፅ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ያሰፈረው ፅሁፍ መሰረተ ቢስ እና ፍርሃት የተቀላቀለበት ነው።

''ትግራይ ኦን ላይን'' በማለት እራሱን የሚጠራው ድህረ-ገፅ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ያሰፈረው ፅሁፍ እጅግ የሚያሳዝን ነው።ፅሁፉ መሰረተ ቢስ እና ፍርሃት የተቀላቀለበት ነው።

ከእዚህ በፊት በማኅበሩ ላይ የሐሰት መፅሐፍ መሰል ፅሁፍ በመፃፉ በኢትዮጵያ ሕዝብ ከትዝብት ላይ ወድቆ የነበረው ግለሰብ ዛሬ ''ትግራይ ኦን ላይን'' ላይ ማኅበሩን እንደፈለገ እንዲሳደብ ተፈቅዶለታል።ግለሰቡ በከፈተው ''ሳልሳዊ ወያነ'' በሚለው ገፁ መግቢያ ላይ ኢትዮጵያን እንደሚጠላት በአደባባይ ማወጁን ለማወቅ ይቻላል።በገፁ መግቢያ ላይ ''ኢትዮጵያዊ ዜግነት እንጅ ኢትዮጵያዊ ማንነት የለም!'' ይላል።

ከግለሰቡ የሐሰት ጥርቅም ፅሁፍ ባለፈ አስገራሚው ነገር ''የትግራይ ኦን ላይን'' ድህረገፅ ሊንኩን ለመንካት በእንግሊዝኛ የለጠፈው አርዕስት፣ ድህረ-ገፁ ከግለሰቡ ከቀረበለት ፅሁፍ ባለፈ የእራሱን የተሳሳተ አስተሳሰብ ያንፀባርቃል።ፅሁፉ በአማርኛ ቀርቦ ሳለ ''ትግራይ ኦን ላይን'' ግን በእንግሊዝኛ ''ማኅበረ ቅዱሳን ፀረ ኢትዮጵያ አንድነት፣ አሸባሪ...'' የሚሉ ቃላትን ከድህረ ገፁ ፊት ላይ ያስነብባል።

በመጀመርያ በትግራይ ሕዝብ ስም የተከፈተ ድህረ ገፅ ቢያንስ በስሙ የተከፈተበት ሕዝብን ትልቅ የሆነ የሃይማኖት ስሜት የሚነካ የሐሰት ወሬ ለማሰራጨት እንዴት ተደፋፈረ? ለእንደዚህ አይነቱ እርካሽ ፅሁፍ ምላሽ መስጠት በእራሱ የጊዜን ጥቅም አለመረዳት ነው።በጉዳዩ ላይ እግዚአብሔር እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍርድ ይሰጡበታል!


ማሳሰብያ ዘግይቶ የተገኘ - 
''ትግራይ ኦን ላይን'' ድህረ ገፅ ትንሽ ኤዲት ዛሬ ከቀትር በኃላ አደረገ። በእንግሊዝኛ ከራሱ ጨምሮት የነበረው ባለ 4 መስመር ማኅበሩን የሚያጥላላ አረፍተ ነገር ከቀትር በኃላ አንስቶ ወደ ፅሁፉ የሚያመራውን የገፅ ''ሊንክ'' ግን እንዳለ አስቀርቷል። የእንግሊዝኛ ትርጉሙ ከላይ እንደተገለፀው እንዳለ ተቀምጧል።
አሁንም የእግዚአብሔር እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍርድ አይለየን!




ጉዳያችን GUDAYACHN

Thursday, October 17, 2013

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ለእምነታቸው ዘብ ቆመው ዋሉ! ምንጭ - ሐራ ዘተዋህዶ

ከጥቅምት ፬ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ጀምሮ እየተካሄደ የሚገኘውና ሦስተኛ ቀኑን ያስቆጠረው ፴፪ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ በዛሬው ዕለት ከቀትር በኋላ በነበረው ውሎ የተለየ ክሥተት አስተናግዷል፡፡ ‹‹የሃይማኖት መቻቻል›› በሚል ርእስ በ፴፪ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ በተካሄደው ውይይት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ባለሥልጣናት ጋራ በተለይም በመቻቻልና በኢትዮጵያ የክርስትና ታሪክ ዙሪያ ሲከራከሩና በአንዳንድ ኹኔታዎችም ኤክስፐርቶቹን ሲገሥጹ ውለዋል፡፡

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ÷ ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ፣ ብፁዕ አቡነ ኄኖክ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ፣ ብፁዕ አቡነ ያሬድ፣ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ እና ብፁዕ አቡነ እንድርያስ÷ ከየአህጉረ ስብከታቸው ተጨባጭ ኹኔታና ከቀረበው ጽሑፍ እየተነሡ በመረጃ፣ በጥያቄና በትችት ስለ መቻቻል ጽሑፍ ያቀረቡ የሚኒስቴሩን ባለሥልጣናት ፈተና ላይ ጥለዋቸው አምሽተዋል፡፡ የሊቃነ ጳጳሳቱ ምስክርነት ‹‹የባዕድ እምነት አራማጆች በቤተ ክርስቲያንና በካህናት ላይ ልዩ ልዩ ተጽዕኖ እንደሚያደርጉና ሕገ መንግሥቱን የጣሰ ታላቅ ድፍረት እንደሚፈጽሙ›› ቀደም ሲል ለአጠቃላይ ጉባኤው የቀረቡ ሪፖርቶችን በገሃድ የሚያረጋግጡ ናቸው፡፡

የሚኒስቴሩ አማካሪዎችና ባለሞያዎች በበኩላቸው፣ ቅሬታዎቹ በተጨባጭ ማስረጃዎች ተደግፈው በሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በኩል ቢቀርቡላቸው መፍትሔ እንደሚሰጧቸው፣ በሊቃነ ጳጳሳቱ ከተገለጹት በላይ ያልተነገሩ ቅሬታዎች ስለመኖራቸው በየወረዳው ተዘዋውረው መረጃዎችን አሰባስበው ማረጋገጣቸውን አስታውቀዋል፡፡ በ‹‹ሕግ የተያዙት ጉዳዮች በሕግ እንደተያዙ ጠብቀው እንዲቀጥሉ›› ለዚህም የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ጥንካሬ አስፈላጊ መኾኑን አሳስበዋል፡፡

የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን ጥያቄ፣ አስተያየትና ትችት በከፍተኛ ጥሞና የተከታተለው የአጠቃላይ ጉባኤው ተሳታፊ የሞቀ ድጋፉን ሰጥቷቸዋል፡፡ በዚህ የውይይት አጀንዳ አጋጣሚውን እንደ ምቹ ኹኔታ ለመጠቀም ያሰቡ የሚመስሉትና ልዩ ፍላጎት የነበራቸው የሚመስሉት አቡነ ሳዊሮስ ውይይቱን ሳይጨርሱ አቋርጠው ሲወጡ ታይተዋል፡፡

‹‹አክራሪነት/ጽንፈኝነት የሚለው ቋንቋ እናንተ ናችኹ ያሰማችኁን፤ ከዚህ በፊት አይታወቅም፤ ዕድሜ ሰጥታችኁም ያበለጸጋችኋቸው እናንተው ናችኹ፡፡ አባቶቻችን የእረኛ ሰነፍ ከሩቅ ይመልሳል ይላሉ፤ በሩቅ መቅጨት ሲገባ ታሪካቸው እየተተረከ ብዙ አተራመሱት፤ [የአክራሪነት]መረባቸውን ከላይ ዘርግተዋል፤ መሬት አልነኩም ተባለ፤ መረባቸውን መሬት ዘርግተው፣ ሕዝብ እያተራመሱ ሙስሊሙ ራሱ እኛ አናውቃቸውም እያለ እየጮኸ እንዴት መሬት አልነኩም ይባላል? በእናንተ አነጋገር መሬት ሲነኩ እንዴት ሊያደርጉነጅ ኖሯል? . . .ተቻቻሉ? እስከ ምን ድረስ ነው መቻቻል? ምንድን ነው መቻቻል? አሁን በወለጋ ያለው ኹኔታ መንግሥት በአገሩ ያለ ያስመስላል? ሰው እግሩን እሳት እየበላው ቻል ይባላል? እንድንቻቻል አድርጉን፤ እንችላለን!!›› /ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ፣ የሰሜን ወሎና ዋግ ኽምራ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ/

‹‹በምዕራብ ወለጋ ሀ/ስብከት በሦስት ወረዳዎች – ነጆ፣ ባቦ ገምቤል፣ ቤጊ – በፖሊቲካና የመናፍቃን አባላት የኾኑ ባለሥልጣናት በሥነ ልቡና ጦርነት ምእመኖቻችንን እየነጠቁን በደል አድርሰውብናል፡፡ አገሩ ለፕሮቴስታንት የተፈቀደና ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አታስፈልግም የተባለ ነው የሚመስለው፡፡›› /ብፁዕ አቡነ ኄኖክ፣ የምዕራብ ወለጋና አሶሳ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ/
 
‹‹ከዚህ በፊት በዚህ መድረክ ክቡር ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም መጥተው ብዙ ነገር አስጨብጫቸው ነበር፤ ምላሽ አላገኘኹም፤ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ታይቶ የማይታወቅ ነገር በጋሞጎፋ ሀ/ስብከት ተፈጥሯል፡፡ የደመራ በዓል በሚከበርበት ቦታ ላይ ምትክ ሳይሰጥ ተወስዶ ሱቅ በመከፈቱ ዘንድሮ በመቶ ወረዳ የደመራ በዓል ሳይከበር ሕዝቡ እያዘነ፣ እያለቀሰ ቤቱ ውሏል፡፡ በሴቻ ከተማ ባልተፈቀደ ቦታ ለስምንት ቀን ጉባኤ አዘጋጅተው የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናችንን፣ ጽላት፣ ቅዱሳን መላእክት እያነሡ ሲቃወሙ ነበር፡፡ ይህ ነዳጅ የተረከፈከፈበት ክብሪት ማለት ነው፡፡ ሕዝብ ሰልፍ እንውጣ ሲለን ሰላማችንን፣ ልማታችንን እንወደዋለን፤ መብታችንን በሕግ ነው የምንጠይቀው ብለን ከልክለናል፡፡ ጉባኤ ማካሄዳቸውን አንቃወምም፤ ግን ስማችንን ማንሣት ምን ማለት ነው? ይሄ ነው መቻቻል? እኛ ሌላውን አንነካም፤ ስንነካ ግን መብታችንን እንጠይቃለን፤ ቤተ ክርስቲያኗ መሬት መያዟን የወረዳው ባለሥልጣናት መሬቷን ቆርሳችኹ ጉባኤ አድርጉ ይላሉ፤ ይህን እንደ በቀል ነው የሚያዩት›› /ብፁዕ አቡነ ኤልያስ፤ የጋሞጎፋና ደቡብ ኦሞ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ/

‹‹በሶማሌ ክልል እስከ ቀበሌ ድረስ ባሉ የመንግሥት መሥ/ቤቶች ብዙ ሠራተኞች ምእመናን አሉ፡፡ ያሉን አብያተ ክርስቲያናት ግን አምስት ብቻ ናቸው፡፡ በየወረዳው ቤተ ክርስቲያን እንዲሠራ ምእመናን ይጠይቃሉ፡፡ እስከ ክልሉ መስተዳድር ድረስ ለምእመናን የምንጮኸበት፣ መብታችንን የምናስከበርበት ኹኔታ ግን የለም፡፡. . .ምእመናን እምነታቸውን በካሴትና በዘመናዊ መሣርያ ካልኾነ እኛ ተንቀሳቅሰን ለማገልገል የምንችልበት ኹኔታ የለም፡፡ በክልሉ ሁሉም ወረዳዎች የምእመናኑን ብዛት ዐውቀንና አጥንተን ያዘጋጀነው ስላለ የሚመለከተው ክፍል መፍትሔ እንዲሰጠን እንጠይቃለን፡፡›› /ብፁዕ አቡነ ያሬድ፣ የሶማሌ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ/

‹‹ታሪክ ክፉ ይኹን ደግ እንደ ታሪኩ ነው የሚተረክ፤ ወንድማችን [ከዕለቱ የሚኒስቴሩ ሦስት ተናጋሪዎች አንዱ የነበሩት አቶ ገዛኽኝ ጥላሁን] ይህን ታሪክ ስታቀርብ ምን ያህል ላይሰንስ አለኽ? ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ፤. . .ክርስትና በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነው የሚለው ሌላ ጊዜ እንዳይደገም፣ ዛሬ ግራጁዌት አድርጉት፤ ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ክርስቶስ ካረገ ዓመት አልሞላውም፤ ገና ከኢየሩሳሌም አልተወጣም፤ ከሰው አይደለም ደግሞ ከእግዚአብሔር ነው የተቀበለችው፡፡ (የሐዋ.8÷26) ባለሥልጣን ሁሉ አገር የሚጠላ ምንድን ነው? በዓለም በትልቁ መጽሐፍ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፏል፤ በእግዚአብሔር ማመንንም የተቀበልን ከአይሁድ በፊት ነው፡፡ ታሪኩን አታዛቡ፤ ከዚህም ስትመጡ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የሠለጠነ፣ ቢቻል ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ የኾነ፣ በጳጳሳቱ ፊት ለመናገር የሚገባው መኾን አለበት፤ አታስቆጡን!. . .ቤተ ክርስቲያን እንግዳ ሲመጣ ሃይማኖትኸ ምንድን ነው አትልም፡፡ እግር አጥባ፣ አብልታ ነው፤ ግን ልታስተምሩን ስትመጡ ሳብጀክቱን ግራጁዌት አድርጋችኹ ኑ!›› /ብፁዕ አቡነ ማርቆስ፣ የምሥራቅ ጎጃም ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ/

‹‹. . .ችግሮቹ መፍትሔ አጥተው ቀርተዋል፡፡ ስድስት አድባራት ተቃጥለዋል፤ ሦስቱ በአንድ አካባቢ፣ ሦስቱ በተራራቀ ኹኔታ፡፡ ቢጮኽ የክልሉ መንግሥት አይሰማም፤ መልስም አይሰጠም፤ እንዲያውም ያስተባብላል፤ የተበደለ ሲናገር ፖሊቲካ ነው እያሉ ያተራምሱናል፤ ሐቅ ሲነገር ድብቅ የለውም፤ ሌትም ቀንም ቤተ ክርስቲያን እየተቃጠለ፣ የሚጮኽበት እየታጣ ነው፡፡. . .የመንግሥት ሥልጣን የተረከቡ ወንድሞች የእኛን አንደበት ብቻ ነው እንዴ የሚጠብቁት? ለሌላው ብቻ ነው የቆሙት? ይህ የሰላም መደፍረስ አይደለም? መቻቻል የሚባለው አማርኛ ምንድን ነው? አማርኛ ነው እንዴ የምታመርቱት? በየቢሯቸው ሄጃለኹ፣ አንዱ እንደውም ተቆጣኝ፤ ይኸው ዘመን ተቆጥሯል፤ ዐርባ ዓመት ኾኗል፤ ለሕዝቡም ለመንግሥትም የምንኖረው እኛ ብቻ ነን፡፡ ለምንድን ነው በሽፋንነት የምትጠቀሙብን? ሁሉም ሲያጭበረብረን፣ ሲያታኩሰን፣ ሲያቃጥለን የሚኖረው መንግሥትን ሽፋን አድርጎ ነው፡፡ ይቅርታ አድርጉልን፡፡›› /ብፁዕ አቡነ እንድርያስ፣ የደቡብ ጎንደር ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ/
ምንጭ - ሐራ ዘተዋህዶ
http://haratewahido.wordpress.com/2013/10/16/ብፁዓን-ሊቃነ-ጳጳሳቱ-ለእምነታቸው-ዘብ-ቆ/#more-2160 

Wednesday, October 16, 2013

ኢቲቪ የደበቀኝ ልማት

የኢትዮጵያ ሕዝብ የመስራት ባህሉ ጠንካራ ነው።ያጣው ሃብት የማፍራት ዘዴ እና የዘመናዊ እውቀት ክህሎት ነው።በእዚህ ፊልም ላይ የምንመለከተው ''ኮምዩኒት ብሪጅ'' የተሰኘ ድርጅት በጎጃም እና በጎንደር መካከል የሚያገናኘውን ድልድይ የዛሬ ሶስት ዓመት በ 2003 ዓም ግንባታውን ሲያጠናቅቅ ነው።

የህዝቡን ጥንካሬ እና የመስራት ፍላጎት የምንመለከትበት አንዱ መንገድ ድልድይ ባይኖርም ወንዶችም ሆኑ ሴቶች በገመድ ተንጠላጥለው የማለፍ ልምዳቸውን ነው።የእዚህ አይነቱን የማለፍ ድፍረት ያለው ሕዝብ የሚያሰራው እና ለትምህርትም ሆነ ለእውቀት በር የሚከፍትለት ቢያገኝ ትልቅ እድገት ላይ የመድረስ አቅም እና ድፍረት እንዳለው መገንዘብ ይቻላል።

የኢህአዲግ ተቀፅላ የሆነው ''የአማራ ልማት ማኅበር'' በሚልዮን የሚቆጠር ብር እያወጣ የቢራ ፋብሪካ ለሕዝቡ ከሚገነባ እንደዚህ የተረሱ አካባቢዎችን ቢመለከት እና ገንዘቡን እውቀት እና ክህሎት ማዳበርያ ላይ ቢያውለው እንዴት ጥሩ ነበር? ኢቲቪ የደበቀኝ ልማት።




ጉዳያችን GUDAYACHNgetachewb221@gmail.com

Tuesday, October 15, 2013

የእንግሊዙ ባርክሌይስ ባንክ ከትልቁ የሱማሌ የገንዘብ አስተላላፊ- ከደሃብሺል ጋር የነበረውን የስራ ግንኝነት ሊያቆም ነው (ጉዳያችን ጡመራ ልዩ ጥንቅር)



የእንግሊዙ ባርክሌይስ(Barclays) ባንክ መሰረቱን ዱባይ ላይ ካደረገው ከድሃብሺል(Dahabshiil) ጋር የነበረውን የስራ ግንኙነት ሊያቆም መሆኑን ብሉምበርግን ጨምሮ የተለያዩ የዜና ወኪሎች አስታውቀዋል።የእንግሊዙ ባርክሌይስ ባንክ በሃምሳ ሀገሮች ቅርንጫፎቹ ከአርባ አምስት ሚልዮን በላይ ደንበኛ ያለው ባንክ መሆኑ ሲታወቅ የደሃብሺል የገንዘብ አስተላላፊ ጋር የሚያደርገው የስራ ግንኙነት መቆረጥ ከእንግሊዝ ብቻ ወደ ተቀረው ዓለም (በተለይ ወደ ሱማልያ) የሚላከውን በዓመት ከአንድ መቶ ስልሳ ሚልዮን የአሜሪካ ዶላር የሚሆን ገንዘብን ያግዳል።

ከጉዳዩ ጋር ተያይዘው የወጡት ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት እራሷን ችላ መቆም ያልቻለችው ሱማልያ በውጭ ከሚኖሩ ዜጎቿ የሚላከው የገንዘብ መጠን በዓመት እስከ  1.5 ቢልዮን ዶላር እንደሚደርስ ያመላክታሉ።እንደምዕራባውያን አስተያየት በደሀብሺል በኩል ለሱማልያውያን የሚላከው ገንዘብ  ቀጠናው እንዳይረጋጋ ከሚፈልጉ ኃይሎች እጅ እየገባ  መሆኑ  ስጋት ላይ ጥሏቸዋል።

የባርክሌይስ ባንክ ከደሃብሺል ጋር ያለውን የስራ ግንኙነት ማቆም ተከትሎ በትውልድ ሱማልያዊ በዜግነት እንግሊዛዊ የሆነው ታውቂው አትሌት ሞፋራህ የባንኩ ውሳኔ ብዙ ሱማልያውያንን እንደሚጎዳ በማስገንዘብ ያቀረበውን ተማፅኖ ባንኩ አለመቀበሉ ውሳኔው  ምን ያህል ቁርጥ መሆኑን አመላካች ሆኗል።

በሌላ በኩሉ የሱማልያው የወቅቱ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ ጉዳዩን አስመልክተው ሲናገሩ - ''ጉዳዩን በአትኩሮት እየተከታተልነው'' ካሉ በኃላ በሀገራቸው ላይ ስለሚያመጣው አሉታዊ ተፅኖ ሲያብራሩ '''' ህዝባችን ከረጅም እና አሰልቺ ጦርነት ገና ማገገሙ ነው።በሚልዮን የሚቆጠሩ ሱማልያውያን ጥገኛ የሆኑበት እና  የሕይወት አድን መንገድ የሆነውን ሕጋዊውን የገንዘብ ማስተላለፍያ መስመር ዘግቶ ሕዝቡን የመቅጫው ጊዜ አሁን ሊሆን አይገባውም ነበር።ምክንያቱም ጥቂቶች በሚሰሩቱ ወንጀል የዋሃንን መቅጣት ተገቢ አደለም።'' ብለዋል።
 “Our people are now recovering from a long and devastating civil war and this is not the time to punish them again by closing the legitimate lifeline on which millions of Somalis absolutely depend,'' he said. "Innocent millions should not be made to suffer because of the crimes of the guilty few.''

ደሃብሺል ከኢትዮጵያን የግል ባንኮች ጋር በገንዘብ ማስተላለፍ ሥራ ጋር ትብብር ያለው ሲሆን በአንድመቶ ሃምሳ ሀገሮች ውስጥ በሚገኙት ቢሮዎቹ በአብዛኛው የሱማሌ ማህበረሰብን ያገለግላል።በሱማልያ የሚገኙ የረዴት ድርጅቶችም ሆኑ የተባበሩት መንግሥታት ቢሮዎች ማናቸውንም የፕሮጀክትም ሆነ ለተመሳሳይ ሥራ የሚውል ገንዘብ የሚተላለፈው በደሃብሺል በኩል መሆኑ ይታወቃል።ድርጅቱ በአዲስ አበባም የቦሌ ሩዋንድን ጨምሮ ቅርንጫፍ የገንዘብ መክፈያ ቢሮዎች አሉት።

.//////////ከጉዳያችን ጡመራ የሚወጡ ማናቸውንም ፅሁፎችን በተለያዩ ድህረ ገፆች ሲያወጡ የጡመራውን ምንጭነት መጥቀስ ይገባል።/////////

Monday, October 14, 2013

የአፍሪካ ታሪክ ሳምንት በኦስሎ ከጥቅምት 4 እስከ 10/2006 ዓም (Oct.14-20/2013)




የኦስሎ ከተማ ምክርቤት ይህንን ሳምንት ''የአፍሪካ ታሪክ ሳምንት''  በሚል የተለያዩ መርሃግብሮች እንዳሉት ገልጧል።ዝርዝሩን ይህንን ጫፍ(link) በመክፈት ያንብቡ።በኦስሎ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አፍሪካውያን ወንድሞቻቸውን የሚያገኙበት ስለሀገራቸው፣እና ባህላቸው የሚያስተዋውቁበት አይነተኛ አጋጣሚ እንደሚሆን ይታመናል።
ጫፍ (link) = http://www.afrikanhistoryweek.com/index.php
                    ወይንም             http://www.bydelgrunerlokka.oslo.kommune.no/enhet_for_mangfold_og_integrering/kalender/article261961-66178.html


7 day Festival Starts Monday 14th October


We're excited to welcome you to this years Afrikan History Week on 14-20th October 2013!

Over seven days in Oslo, Norway you can see films such as Relentless (with director Andy Okoroafor), and seminars from speakers such as poet Yussef Ahmed. We're also delighted to have Hannah Wozene Kvam attending who is a Norwegian artist, writer and slam poet. Other guests include; Norwegian soul/R’n’B artist Fethawith Hakin, American professor emeritus at the Department of Africana Studies Wade Nobles, and Jamaican Rastafarian dub poet Mutabaruka.

Of course no festival would be complete without our Childrens Day on Saturday 19th, and not to be missed is Sundays finale with Afrika Live: Carmen Souza who has a cool, smoky sound derived from a unique mix of influences from her Cape Verdean background to jazz, modern soul and Brazilian influences.

Tickets available now.

 SOURCE - WWW.oslo.kommune.no/




Sunday, October 13, 2013

የአርሴናል ተጫዋች ኢትዮጵያዊው ጌድዮን ስለ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጫወታ ምን አለ?


ጌድዮን

ለአርሴናል የሚጫወተው ጌድዮን የዛሬውን ጫወታ ከመጀመሩ በፊት በ ፌስቡክ ገፁ ላይ '' for #Ethiopian Nationla team: Good luck boys. I know you can do it '' (ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች መልካም ዕድል! ጫወታውን  በሚገባ እንደምታሸንፉ አውቃለሁ) ነበር ያለው።ጫወታው ካለቀ በኃላ ''እኔ በጫወታ ችሎታ (በቡድናችን) እረክቻለሁ'' ነው ያለው። ጥሩ አባባል ነው።

በነገራችን ላይ ከዛሬው በኢትዮጵያ እና  በናይጄርያ መካከል የነበረው ጫወታ የምንረዳው  ዋልያዎች ናይጄርያን የማስጨነቅ አቅም እንዳላቸው ነው።
እድላችን ጠበበ እንጂ አሁንም በበቂ ዝግጅት በቀጣዩ ጫወታ የማሸነፍ ዕድላችን አልተዘጋም።ናይጄርያ ተዝናንተን (ሰፊ ዕድል ይዘን) ከመሄድ ተጠናቀን ለመሄድ የሚያስገድደን ነው።ተጨንቀን ናይጄርያ ላይ ካሸነፍን ድሉ ይብሱን ይጥማል።
በሩ አሁንም ሙሉ በሙሉ አልተዘጋም።
Getachew Bekele
oslo


Saturday, October 12, 2013

ኢትዮጵያ ሀገሬ! (ከእንባ ጋር)

 የጥበብ ምልክት የፍቅር ማደርያ፣
ኑሪ ለዘላለም ንግስት ኢትዮጵያ!





Friday, October 11, 2013

''የቡርቃ ዝምታ'' ስለተሰኘው መፅሐፍ ከአስር ዓመት በላይ ስፈልግለት የነበረውን ስም ዛሬ አገኘሁት


''የቡርቃ ዝምታ'' የተሰኘውን መፅሐፍ ያነበብኩት ካልተሳሳትኩ የዛሬ አስራ አንድ ዓመት ገደማ ካምፓላ፣ዑጋንዳ ማካሬሬ  ዩንቨርስቲ ሳለሁ ነበር።መፅሐፉን አንብቤ እንደጨረስኩ የፀሃፊውን አላማ፣ስሜቱን እና ግቡን በደንብ ተረዳሁበት።ያለኝንም ሃሳብ ገፅ በገፅ ከሂስ ጋር ወደ ስድስት ገፅ ፅፌ መፅሐፉን ላዋሱኝ ሰው ሰጥቻቸው እንደነበርም ትዝ ይለኛል።.........

.......አንዳንድ ሰው ጥሩ የስነፅሁፍ ችሎታ (የአፃፃፍ ስልት) ሊኖረው ይችላል።ይህ ማለት ግን የተፃፈው ትክክል ነው ማለት አይደለም።ቆንጆ መልክ ያለው ሁሉ አመለ ሸጋ እንዳልሆነ ሁሉ። ጨካኙ ሂትለር ጥሩ ንግግር ሊናገር ይችላል።የንግግር አዋቂነቱ ግን የሚለውን ትክክለኛነት አይገልፅም።አንድ ሰው በጥሩ ንግግር ሃይማኖት ሊያስተምር ይችላል።ጥሩ በመናገሩ ግን የሚለውን ሁሉ የሃይማኖቱ አስተምሮ ከሚለው ጋር ሳላገናዝብ እንድቀበል አያደርገኝም።

ዛሬ የፌስ ቡኬን ገፅ ሳገላብጥ አንድ  ወዳጄ ከላይ ስለጠቀስኩት መፅሐፍ የሰጠው ስም ለአስር አመታት ስፈልግለት የነበረውን ስም ያገኘልኝ መሰለኝ። ወዳጄ ያለው '' የብልቃጥ ውስጥ መርዝ ሆነብኝ'' ነበር።ወዳጄን እንዳመሰግነው ይፈቀድልኝ።የብልቃጥ ውስጥ መርዝ የሚፅፉቱ እና የሚያፅፉቱ ብልቃጡን ማን እንደሚጨልጠው አይታወቅምና እባካችሁ ህዝብን ከህዝብ ጋር ለማጋጨት አትትጉ።


አበቃሁ
ጌታቸው በቀለ
ኦስሎ

Tuesday, October 8, 2013

Ethiopia ready for Nigeria in World Cup qualifier

AFP, Monday 7 Oct 2013
We are ready for Nigeria, we are very ready. We learned a lesson from the mistakes we made last time, says Ethiopia's Teshome


In matching blue jerseys and red shorts, Ethiopia's footballers confidently criss-cross their home pitch, launching the ball back and forth.
The players press on under the blistering morning sun for over two hours. At this crucial stage in the 2014 World Cup Africa zone qualifiers, the team knows that every minute of training counts.

"We have tried to prepare them physically as well as mentally in the first week and now we are doing our tactical work and we will continue in the coming few days to combine the two," said Ethiopian 'Waliya Antelopes' coach Sewnet Bishaw, as his team waged a practice match behind him.

Ethiopia are preparing to face Nigeria on Sunday in their toughest qualifying match yet.

Though the odds are stacked against Ethiopia – Nigeria rank 36th in the world, according to international football governing body Fifa, while Ethiopia clocks in at 93 - the 'Waliyas' maintain an unflinching resolve to win.

Having beaten 2010 World Cup hosts South Africa to land at the top of their group, it is the closest the Horn of Africa nation has come to reaching the finals.

Ethiopia know the next match will be far from easy. On top of their impressive global ranking, Nigeria have more international experience and boasts several players from top European leagues.

But the 'Waliyas' refuse to let that spook them.


Having played Nigeria last January at the Africa Cup of Nations, Ethiopia are familiar with the strength of Nigeria's 'Super Eagles', who won the game 2-0 before moving on to win the lift the trophy in South Africa.

"We are ready for this match, we are very ready. We learned a lesson from the mistakes we made last time," said midfielder Menyahil Teshome.

Coach Sewnet said despite Ethiopia's defeat, the Nigerian squad is not a better team and the 'Waliyas' maintained their strength until the last 10 minutes of the game.

"If you look seriously at that match, Nigeria were not a better team than us. Up to the (end) we were performing good. But in the last 10 minutes they used their experience, so they got two penalties," he said.

"I think we will have a better game in the coming match against Nigeria," Sewnet said.

But he admits training has been set back by the absence of the team's four professional players, including star striker Saladin Said, who are expected early this week.

Ethiopia – a country better known for their renowned runners than their footballers – have amazed supporters by making it this far in the qualifiers.

Menyahil said his team, regarded as underdogs among powerful African national football teams like Ghana and Ivory Coast, is bolstered by a strong sense of nationalism and a refusal to be intimidated.

"Our strength is our team spirit," he said, sweating after training at Addis Ababa's national stadium, which is lined with posters of the late Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi.

"We have nothing to fear. Until now, we've been supported by our people," added Menyahil, who was fielded illegally in a match against Botswana, costing the team three points.

Though preventing Nigeria from scoring away goals is crucial if Ethiopia want to proceed, coach Sewnet said the team is focused on both defending and attacking, and is not prioritising one over the other.

And while he insists he is focusing on winning each match individually, instead of pressuring his team to reach Brazil, he does not scoff at the idea of making it to the World Cup.

"Why not? I don't know Brazil, so I want to see it," he joked.

The return match is scheduled for Calabar in south-east Nigeria on November 16 and the aggregate winners qualify for the World Cup.

Monday, October 7, 2013

Ethiopia got new chinese language speaker president./ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሆኑ


ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ 

ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሆኑ።ዶ/ር ሙላቱ የቻይና እና የአሜሪካ ዩንቨርስቲ ምሩቅ ሲሆኑ የቻይና ቋንቋ አቀላጥፈው እንደሚናገሩ  በምክርቤቱ ውስጥ ተነግሯል።ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በኢህአዲግ አባላት የተሞላው የተወካዮች ምክርቤት ዛሬ መስከረም 27/2006 ዓም  ባቀረበው ብቸኛ እጩ ዶ/ር ሙላቱ ተሾመን በጭብጨባ ከማፀደቁም በላይ  ብቸኛ ተቃዋሚ አቶ ግርማ ድጋፋቸውን ሲሰጡ አሳይቷል።ዶ/ር ሙላቱ በተለያዩ ሀገሮች በአምባሳደርነት ያገለገሉ እና በአሁኑ ወቅት በቱርክ የኢትዮጵያ አምባሳደር ነበሩ።

Ethiopia got new chines language speaker president.
Dr.Mulatu Teshome, china University graduate has elected as president of Ethiopia.Today October 7/2013 Ethiopian parliament which is almost fully filled by  EPRDF members, could present one candidate for the post and vote in favour.

Sunday, October 6, 2013

የሰሞኑ የአቶ ኃይለማርያም ጋዜጣዊ መግለጫ የመንግስትን የአሰራር ድክመት ያመላክታል።


አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ  
ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በአዲሱ የስልጣን እርከን ላይ ሆነው በርከት ላሉ ጋዜጠኞች መግለጫ ሲሰጡ የመስከርም 24/2006 ዓም የመጀመርያቸው ነው።በእዚህ ቃለመጠይቅ ላይ የተለያዩ ጉዳዮች ተነስተዋል።የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሾች ግን በደንብ ለሚያጤነው ሰው መንግስት አዲስ አይነት አሰራሮች እና ሃሳቦች አሁንም አለማስተዋወቁን እና  በአዲሱ 2006 ዓም የህዝቡ አንገብጋቢ ጉዳዮች እንዳሉ እንደሚቀጥሉ ይገነዘባል።ቃለ ምልልሱ አንገብጋቢ ከሆኑ የህዝብ ጥያቄዎች ውስጥ ፈፅሞ ያልተመለከታቸው  ለምሳሌ-የኑሮ ውድነቱ እየናረ መምጣት፣የስራ አጥ ወጣቶች ችግር ለመቅረፍ መንግስት ስለሚወስደው አፋጣኝ እርምጃዎች፣የትምህርት ጥራት ጉዳይ እና የኢትዮጵያ የውጭ ብድር ከጊዜ ወደ ጊዜ የመናሩ ጉዳይ አልተነሳም። በቃለመጠይቁ ውስጥ ከተነሱት ጉዳዮች ውስጥ የሚከተሉት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ምላሾች ወዴት እየሄድን እና የት ላይ እንዳለን የሚያመላክት ነው።

1/ የውሃ እጥረትን በተመለከተ 


የአቶ ሃይለማርያም ምላሽ '' በአዲስ አበባ እስከ 90% የሚሸፍን የውሃ አቅም አለ።ችግሩ ስርጭት ላይ ነው።'' በሚል ነው ያለፉት።
እዚህ ላይ  እንደተባለው ስርጭት ችግር ከሆነ ችግሩ የመንግስት የሰው ኃይል፣የገንዘብ እና የተክኖሎጂ አጠቃቀም ችግር ያመላክታል ማለት ነው።ይህም የጠቅላይ ሚኒስትሩን መንግስት አሰራር የሚያሳይ ከመሆን አያልፍም።

2/ ሙስናን በተመለከተ 

ሙስናን በተመለከተ አቶ ሃይለማርያም የመለሱት ምላሽ እጅግ አስገራሚ ሆኖብኛል። በመጀመርያ ምላሻቸው እንዲህ አሉ-
'' የሙስናው ጉዳይ መጀመርያ ከነበረው እየተወሳሰበ ነው የመጣው አንዱ ክር ስመዘዝ ሌላው እየተነካ ነው ያለው።ቀድሞ ካሰብነው በላይ ትንሽ ውስብስብ ነው የሆነው'' ካሉ በኃላ አንድ የገረመኝን ንግግር አከሉ ''በእኛ (በኢህአዲግ ማለታቸው ነው) እምነት ከእዚህ በፊት ትንሽ ያጠፋ(የሰረቀ) ካለ ከአሁን በኃላ ከተወ ችግር የለውም ዋናው ነገር ከአሁን በኃላ ነው'' የመልሱ መጨረሻ።
ይህ ማለት ከእዚህ በፊት የሰረቁ፣የዘረፉ ሁሉ አሁን ይህንን ተግባር ትተው ቀድሞ የሰረቁትን በመብላት ላይ ብቻ ከተወሰኑ እና እንደ አቶ ሃይለማርያም አገላለፅ ''ዋናው ነገር ከአሁን በኃላ ነው።'' እና መስጋት የለባቸውም ነው።ይህ እስካሁን ድረስ ሙስናን አስመልክተው ከተሰጡት መግለጫዎች ውስጥ ያውም በጠቅላይ ሚኒስትር ደረጃ  ሲቀርብ በአለማችን ላይ የመጀመርያው ሳይሆን አይቀርም።

3/ ቴሌን በተመለከተ 

የስልክ መስመር መቆራረጥ እና ጥራትን በተመለከተ የችግሩ መንስኤ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም የሰጡት ምክንያት ''ከጠበቅነው በላይ የተጠቃሚው ቁጥር በመጨመሩ ነው'' የሚል የሚል ነበር።
ይህ መልስ ግን አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሰጠው ምላሽ ሊሆን አይገባም። ምክንያቱም የተጠቃሚ ቁጥር እንደጎርፍ የሚመጣ አይደለም።እንበል እንደጎርፍ ጥያቄ ቢመጣ ሲሆን ቀድሞ መስርያቤቱ በአጭር ጊዜ እና በመካከለኛ ጊዜ ውስጥ ሊቀርቡ የሚችሉ የደንበኞችን ጥያቄ ቀድሞ በገበያ ጥናት ክፍሉ አጥንቶ ከወዲሁ ተገቢውን ዝግጅት ማድረግ ያለበት ማን ነው? ድርጅቱ ወይንም መንግስት አይደለም ወይ? አሁንም እንበል እና የደንበኝነቱ ጥያቄ ስለመጣ ብቻ በሌለ የመስመር አቅም መሰጠት አለበት እንዴ? የቁጥር እድገቱ እንዲጨምር ሲባል ብቻ በሌለ የመስመር አቅም የሌላው እየታወከ መሰጠት አለበት ወይንስ ተጨማሪ አቅም ተገንብቶ አቅምን ያገናዘበ ደንበኛ ማፍራት ይገባ ነበር? እንደእውነቱ ከሆነ የእዚህ አይነት መልስ ምን ያህል ስራዎች ምክንያታዊ እና ሳይንሳዊ በሆነ መልክ እየተሰሩ ለመሆናቸው አመላካች ነው።

4/ የኤርትራን ጉዳይ በተመለከተ 


ሰሞኑን ከመንግስት የሚሰጡት በተለይ የኤርትራን ጉዳይ የተመለከቱ መግለጫዎች የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ያከበረ ገፅታ የላቸውም።ከእዚህ በፊት በፕሬዝዳንት ደረጃ ያሉት አቶ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ''ኤርትራ ድረስ ሄጄ እርቅ እፈጥራለሁ'' አሉን።ቀደም በለው አቶ ኃይለማርያም አስመራ እንደሚሄዱ እና ችግር እንደሌለባቸው አስረዱን።በእዝህኛው ቃለመጠይቃቸው ላይ ደግሞ ''ኳሱ ኤርትራ እጅ ነች'' አሉን። በዲፕሎማሲያዊ ንግግር ''ኳሱ እገሌ ጋር ነው'' ማለት ምን ማለት ነው? ይህ ማለት ምላሹን መስጠት ያለበት ብቻ ሳይሆን ''ተፅኖ የመፍጠር '' አቅሙ (የኃይል ሚዛኑ) ያለው እዚያ ነው።የሚል ትርጉም ይይዛል።ይህ ምን ለማለት ተፈልጎ ነው?

5/ አክራሪነትን በተመለከተ 

አክራሪነትን በተመለከተ አቶ ሃይለማርያም ትንሽ ተኮስ ባለ ስሜት ነበር የገለፁት። ''ቀይ መስመሩን ማለፍ አይቻልም'' በሚል ቃል የታጀበ  ነበር።ቀይ መስመሩ የሃይማኖት ነፃነትን መጠየቅ? ወይንስ የራስን እምነት አክብሮ መያዝ? ቀይ መስመር ታለፈ የሚባለው ምን ሲታለፍ ነው?
በተለይ በአክራሪነት ዙርያ ያነሱት ነጥብ ላይ ስለምድራዊ እና ሰማያዊ ሕይወት ልዩነት ካብራሩ በኃላ ''ከሃይማኖት ተቅዋማት ውስጥ አክራሪዎች እራሳቸውን እንዲለዩ እኔ በግሌ አሳስባለሁ'' ብለዋል። እዚህ ላይ ግን ''እዝያም ቤት እሳት አለ'' የሚለውን አባባል የዘነጉት ይመስላል።ኢትዮጵያ በታሪክ ሕዝቡን ባልመሰሉት ግን ከባህር ማዶ በመጡ ክርስቲያን  ነን ባሉ  ''ጀሃድስቶች''  አሳር ያየች ምድር መሆኗን የረሷት ይመስላል።የአቶ ሃይለማርያም ቀዩ መስመር የቱ ነው?


አበቃሁ

ጌታቸው
ኦስሎ


Thursday, October 3, 2013

ሸገሮች መልካም ልደት! ሊባሉ ይገባል



ሸገር ራድዮ ስርጭት የጀመረበት ስድስተኛ አመቱን እያከበረ ነው።የሸገር የመጀመርያ ስርጭት የተጀመረው መስከረም 23/2000 ዓም ነው።
ሸገር -
- ማኅበራዊ ችግሮች የሚቀረፉበትን መንገድ በማመላከት፣
- ወቅታዊ መረጃዎችን በመስጠት እና
- የተዋጣለት ሀገርኛ ዘይቤ የተላበሱ መዝናኛ ፕሮግራሞቹን ለሕዝብ በማድረስ የቀዳሚነቱን ስፍራ እንደያዘ ብዙዎች የሚያወሱለት ነው።
ሸገር -
 - ለአዲሱ ትውልድ ጠንክሮ የመስራት ውጤትን አበክሮ በመንገር፣
 - ኢንዱስትሪያዊ ሰላም እንዲሰፍን ቀድሞ መረጃዎችን ለሚመለከታቸው ሁሉ በመስጠት፣
 - ያለፈውን በእርጋታ የመመልከት እና መጪውን ተስፋ በማመላከት በኩል ሸገር የተዋጣለት ነው።

ይህ ብቻ አይደለም ሸገር ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር! ብሎ መርሃግብሩን የሚጀምር እና የሚጨርስ ብቸኛ ሀገርቤትኛ የመገናኛ ብዙሃንም ነው።

ድምፀ መረዋዋ መዓዛ ብሩ የተዋጣለት የጋዜጠኝነትን ሙያ፣ስነ-ምግባር እና ኃላፊነት ያሳየች የሸገር 102.1 ራድዮ መስራች ነች።

ሸገሮች መልካም ልደት ሊባሉ ይገባል።
የሸገር ድህረ-ገፅ የፊት ገፅ ለመክፈት ይህንን ይጫኑ  - http://www.shegerfm.com

በኢትዮጵያ የእገታ ወንጀል ተሳታፊ አራት አካላት ናቸው። ለችግሩ የመፍትሄ አካላት ሁለት ናቸው።ሁለቱ አካላት ምን ይስሩ?

======= ጉዳያችን ======= በኢትዮጵያ ዜጎችን እያገቱ ገንዘብ የሚቀበሉ ወንጀለኞች ከተራ ወንጀለኝነት አልፎ በታጣቂ ቡድኖች የገንዘብ ማግኛነት መዋል ብቻ ሳይሆን ዜጎችን የማሸበርያ ፋሺሽታዊ ተግባር ሆኗል። እገታ የ...