የቡክናፋሶ ፕሬዝዳንት ካምፓዌሪ እና የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ
ቢቢሲ ዓለም አቀፍ አገልግሎት ራድዮም አሁንም በዛሬው ዕለት ዘገባው ''የቡኪናፋሶውን ጉዳይ ብዙ ከሳሃራ በታች ያሉ ሃገራት መንግሥታት በአንክሮ እየተከታተሉት ነው።ብዙ የአፍሪካ ሀገር መሪዎች ለእረጅም ጊዜ በስልጣን የቆዩ ናቸው የዩጋንዳው ሙሰቬኒ እና የሩዋንዳው ካጋሜ እና ሌሎችም በስልጣን ላይ ለእረጅም ጊዜ የቆዩ ፓርቲዎች አሉ'' ብሏል።
የቡኪናፋሶው አመፅ ''የጥቁር አብዮት'' (Black Spring) የሚል ስም ተሰጥቶታል።ሕዝብ ምላሽ ካላገኘ አብዮትን ብቸኛ አማራጭ አድርጎ መነሳቱ የተረዳ ነገር ነው። ሕዝብ ሲነሳ ግን ፓርላማውን፣ሆቴሉን በእሳት እያነደደ መሆኑ አሳዛኝ ነው።አምስቱ ስርዓተ ማኅበራት ተብለው ከሚጠቀሱት ውስጥ የባርያው ስርዓተ ማኅበር አንዱ የሚገለፅበት የአመፅ መንገድ የአሰሪው መጠቀምያ የሆኑትን የመገልገያ መሣርያዎች ለምሳሌ ማረሻውን እና የመሳሰሉትን መሰባበር ነው።ሕብረተሰብ እያደገ ሲመጣ ይላል የሕብረተሰብ እድገት ትረካ አመፆች የመገልገያ መሳርያዎችን ማጥፋት ቀረ።ምክንያት ከድል በኃላ ለህብረተሰቡ ጥቅም እንደሚውሉ የሰው ልጅ ተገነዘበ።እውነት ነው ዛሬ በሩቅ ምስራቂቱ ሀገር ጃፓን የፋብሪካ ሰራተኞች ዓመፃቸው ብልሃት በተሞላበት ሀገራቸውን እና ንብረታቸውን በማያወድም መልክ መከወን የጀመሩት።
አብዮት የለውጥ ብቸኛ አምራጭ ሆኖ የመምጣቱ እውነታ አምባገነኖች በስልጣን መኖርን የሞት እና የሕይወት ጉዳይ እስካደረጉት ድረስ አይቀርም።ነገር ግን አብዮት ሁሉ የነበረ ህንፃን እና ፓርላማ በእሳት ማንደድ አለበት ማለት አይደለም።ማቃጠል ጀብዱ ሊሆን አይችልም።ተቃዋሚ የመምራት አቅሙ የሚፈተነው እዚህ ላይ ነው።አብዮት መሪ፣መነሻ እና ግብ የተቀመጠለት ሲሆን ህንፃ አያነድም።እንደፈለገ አድርገህ ህንፃውን አንድደህም ቢሆን አብዮቱን አምጣው የሚል ተቃዋሚ እንደማይኖር ሁሉ ቀድመው ያልመሩትን በኃላ ሊገቱትም ሆነ ሊመሩት ይቸግራል።
ባጭሩ ሕዝብ እምቢተኝነት አጠንክሮ እንዲሄድ ሲነገር ንብረትን ማውደም፣የህዝብም ሆነ የግለሰብ ንብረትን ሕዝብ እራሱ እንዲጠብቅ አብሮ ማስተማር ተገቢ ነው።አዎን! ዋጋ የማያስከፍል አብዮት የለም።ግን የአፍሪካ አብዮት በዝቅተኛ ወጪ እና በአስተዋይ ምሁራን የማይመራበት ምክንያት ምንድነው? የቡኪናፋሶን የዛሬው የፓርላማ መቃጠል አስታከን ስንናገር መቃጠሉ ሳይሆን ግቡ ለውጡ እና እምቢተኝነቱ መሆኑን ማሳየት ተገቢ ነው።መቃጠሉ ያሳዝናል።አምባገነንነትን መቃወም ያስመሰግናል።የምዕራቡ ሚድያ አገላለፅ ለአፍሪካ ውስጠ ወይራ ሆኖብኛልና ነው ይህንን ማለቴ።
አሜሪካ የዛሬው የቢኪናፋሶው አመፅ ሊነሳ ቀናት ሲቀሩት የቡኪናፋሶን አምባገነን መሪ እንዴት እንደምታሞካሽ ከእዚህ በታች ባለው ቪድዮ ይመልከቱ እና የአቶ ኃይለማርያም እና የልዑካናቸው ባለፈው ወር በፕሬዝዳንት ኦባማ የተሞካሹበትን አግባብ ያስታውሱ።
''ቡኪናፋሶ ለአካባቢው ሰላምና ፀጥታ ትልቅ አስተዋፅኦ እያደረገች ነው'' የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ዛሬ የት እንደገቡ ያልታወቁትን የቡኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ከስልሳ ቀናት በፊት ዋሽግተን ድረስ ጠርተው ሲያሞካሹ (የሶስት ደቂቃ ቪድዮ)
ቪድዮ - የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ዩትዩብ
Video Source - US State Department youtube
ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG