ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Sunday, October 27, 2019

Analysis: Ja-War, Aljazeera, Bloodshed and Terror in Ethiopia




Jawar Mohamed
Photo = file


Jawar Mohammed’s latest religious war on Ethiopia kills at least 70 over the week and the radical Islamist activist also declared an election campaign with the backing of Aljazeera and other sponsors.
Analysis by Solomon Aregawi
October 27/2019
A deadly violence called by Jawar Mohamed and his rebels kills at least 70 this week. 55 of them are, according to a report by AFP, members of the Ethiopian Orthodox Church – killed by traditional weapons like machetes which Jawar Mohammed said his neighbors in Arsi province “would to kill Christians with if the Christians keep their heads up”. The young man is a well educated (at least for Ethiopian politics) and well funded politician holding a US passport like most terrorists with international religious agenda.
His latest target is Ethiopia’s evangelical leader Abiy Ahmed who recently won a Nobel Peace Prize and is trying his best to decolonize Ethiopia from radical tribal politics. Jawar who is a US citizen with alleged Yemeni family background can not legally operate or run for political office since he’s a foreigner. But his deep illegal political operation is knocking on the palace and that will determine his fate in Ethiopia later.
Background
In June 2013, Qatar who has an official state religion in Islam introduced its latest recruit for their religious and political mission in Ethiopia. A certain young man named Jawar Mohammed appeared on Qatar state owned and run Aljazeera. In a well orchestrated and rehearsed show with fellow Islamist activist Mohamed Ademo and non-believer Oromo Galasa Dilbo, Aljazeera’s actress in hijab (pretends to be a journalist) asked Jawar if he’s Oromo first or Ethiopia first. How would that kind of question pop up on the mind of a non-Ethiopian unless it was scripted?. Jawar answered he’s Oromo first and his fame skyrocketed.
In July 2013, a few weeks after the Aljazeera drama, Jawar defined what he meant by “Oromo first”. In an event organized by Muslims activists in Washington DC, Jawar said “Oromo means Muslim, Muslim means Oromo”. He continued ” touching Oromo is touching Muslim and touching Muslim is touching Oromo”,
“so non Oromo Muslims should also support the Oromo struggle” Jawar added, because practically it’s a ‘Muslim struggle” for political power in the name of Oromo. He continued “your Muslim relatives in Djibouti, Somalia, Gondar or even Axum will be proud of you”.
In that historic speech, Jawar also talked about how they would kill Christians with machetes in his home province Arsi. The machetes he mentioned in the speech were used to kill Christians and others in the 2018 Burayu massacres and this week’s violence in Arsi, Bale and Hararghe.
                                                     Jawar in June 2013 at an Aljazeera studio
Since 2013, Jawar Mohamed cruised to power on the back of Muslim majority east Ethiopia. He’s highly supported by rich men from east Ethiopia who donate in millions to his operations against the state of Ethiopia. The former Minnesota based activist repeatedly attacked Welega based Protestant Christian Oromo liberation front (OLF) leaders. With Jawar’s emergence, OLF is now dead and unimportant in Ethiopian politics. Jawar who is way younger that the half a century old rebel movement is more powerful and important than OLF in today’s Ethiopia. Hence, one of the areas Jawar does not reach is the Christian Welega province. Dawud Ibsa’s OLF is popular there and its supporters have established a rival TV network – repeatedly warned Jawar they’d kill him if he comes to Welega.
His popularity among the Muslim Oromo east is high. Most Oromo Muslim speakers have expressed their support – summed up by a recent Facebook post by an Ustaz who said “touching Jawar is touching Muslim”. They always remember what he said in that historic speech of 2013 – Jawar defiantly made clear his intentions to be the replica of medieval Ethiopia Emperor Immam Ahmed Gragn by invading ancient Christian lands of Gondar and Axum to form the Islamic kingdom of Ethiopia.
A bloody return
Jawar Mohammed’s swift return to Ethiopia after TPLF’s ouster was taken as a positive signal by many. He also gave false positives by traveling to the “Amhara” province and meeting with famous “Amhara” politicians like now foreign minister Gedu Andargachew and an Amhara rebel leader by the name Colonel Demeke Zewdu. Jawar did that making wrong calculations that the Christian majority areas in the north are politically and militarily weakened after 45 years of assault by successive Marxist-Leninist rulers in Mengistu Hailemariam and Meles Zenawi and long internal skirmishes. With that wrong calculation in mind, Jawar thought his peaceful capture of Ethiopia was imminent. But that turned out to be false immediately.
New leader Abiy Ahmed’s love with the Orthodox Church and diaspora returnees woke him up. Abiy Ahmed’s affair with these groups was also widely accepted by the nation as seen in pro-Abiy rallies in those days. Jawar and his hate camp hated that their calculations were wrong. So, they wanted to fire back. Even though, they have deadly animosity with Welega based Oromo rebels leader Dawud Ibsa, Jawar’s camp used Dawud Ibsa’s group return to Addis Ababa as a good propaganda bullet to fire back at prime minister Abiy Ahmed and the reunited Orthodox Church. It worked very well. A highly funded campaign rose millions of uninformed Oromo youth to come to Addis Ababa to “welcome OLF returnees” but in fact they were used in a staged drama scripted by “smart” Jawar. Their partners Aljazeera reported and made consecutive news shows about that drama.
On that fateful Saturday night, Jawar claimed dozens of Oromos were killed by hostile Addis Ababa youth but he had no evidence of the killings. Law enforcement did not question him either since it was a potential call for violence. His claim and call for violence on the 87 % Christian Addis Ababa resulted in the Burayu massacres of that weekend. Close to a hundred people were massacred in two days in the outskirts of the capital. Most of the victims were killed by machetes, Jawar Mohammed’s favorite weapon.
Jawar paced up his radical Islamist revolution against Ethiopia and the thriving prime minister Abiy Ahmed. But he avoided openly shooting at Abiy in fear of backlashes but has intensively attacked the inner circle of the prime minister until for the last 18 months. The lawlessness and the mysterious silence from the prime minister’s new regime helped him a lot in recruiting operatives from the prime minister’s ruling Oromo bloc, ODP. But lately, with growing frustrations from the larger public, the prime minister’s regime started acting to stop Jawar. Their weapon was Jawar’s US citizenship. According to Ethiopia’s Constitution, foreigners can not meddle in the country’s political affairs. But due to the ongoing lawlessness in the country, he was given a free ride by the regime for long.
Final shots
In just one week, reports of Jawar changing his citizenship came out followed by Abiy Ahmed’s direct warning at him. Jawar then called his rebels to save him after claiming assassination attempts. His call for violence resulted in the death of at least 70 in the last few days. Most of them were killed by Jawar’s favorite machetes. The bloodshed has continued despite the deployment of the army to violence hit areas like Bale, Arsi and Hararghe where mainly Christians were targeted by Jawar’s rebels. Specially, Jawar birth place Arsi is the center of violence against Christians.
Since Jawar Mohamed returned to Ethiopia last year, over 50 churches have been burnt and hundreds of Christians massacred, including the Sidama violence where Christians were brutally murdered, their bodies dismembered, their teeth extracted and burnt alive. Many accuse him of being behind these attacks by invoking his infamous threat of killing Christians by machetes in that 2013 speech to Muslims in the US.
His version of Islamist Aljazeera, OMN TV network has been the leading mouthpiece of extremist groups who campaign against the ancient Ethiopian Orthodox Tewahido Church. Jawar himself have been a key member of an outlawed group that declared a new separate Orthodox clergy to divide the Christian community along political lines.
Running out of cards?
Jawar Mohamed has a huge support among the Muslim majority east Oromiya region and southern parts of the country. He has “unknown” financial sources and donors who are funding his operations throughout the country. Abiy Ahmed’s divided government has failed to deal with Jawar in fear of Muslim backlash. Jawar is now ‘untouchable”. From his cell in the capital guarded by soldiers taking orders from a faction of ODP that supports Jawar, he has kept calling for more violence blackmailing the army deployed to stop his rebels from killing more people.
Now Jawar has decided to fully fight the war. He never built a carrier, so a return to the US would be a disaster. He has already touched the ball with his hand. Nobody, other than the uneducated Selecas who worship him, considers him a serious political expert. So, his last card is to do what he always feared – return his US citizenship and fight the war as long as he can. Jawar in the past repeatedly said he is ” a good pundit and a teacher not a politician” to avoid direct political involvement. But now he’s forced to swim naked in the water by himself.
Aljazeera’s long held religious agenda
Aljzeera and Jawar’s foreign buddies have been presenting him and his allies as political pundits on their networks drawing a distorted image of Ethiopia to the international community. These radical Islamist pundits usually attack Ethiopia’s Christian Emperors. Aljazeera airs and publishes fake stories it receives from the Jawar camp like “five million Oromos were massacred” in the 19th century by the Christian Emperor Menelik II who sent his Christian Shoa Oromo army to Muslim Arsi where Jawar is born. There were no five million deaths in a war between local tribes with traditional weapons. Aljazeera didn’t care to verify the numbers.
The Qatar state owned network also recently said “after 150 years, Oromos celebrated their religious festival in the capital”. Aljazeera again did not care to verify the number 150. It just took it from the Islamist proxies in the Oromo region. The Islamist news network was kicked out of the united states a few months after starting “Aljazeera America” for poor journalism and unprofessionalism. It started massive propaganda campaign directed to Ethiopia following the rise of Abiy Ahmed. It wants to topple Abiy Ahmed for his relationship to the UAE camp in addition to its old radical Islamist agenda against Ethiopia.
Aljazeera’s twisted report on the latest violence says “Jawar organized the protests that brought Abiy to power”. And the rest of the globalist media simply copy-pasted that with no verification. The Qatari network is no shy of its agenda on Ethiopia and even Eritrea but it has been given a free ride by most locals. It didn’t care to air a documentary on a mediocre pro-Jawar Muslim Oromo woman even long after she was removed from her post as the nation’s tourism minister.
With Jawar’s forced entrance to election politics, Aljazeera sits behind this hostile camp along with other sponsors to hit two birds by one stone. They intensify their religious agenda and unseat pro-UAE Abiy Ahmed if they can. So far they have succeeded with an ill regime led by Abiy Ahmed, a man too slow to catch up with the pace of Jawar and his terror network.

ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Tuesday, October 22, 2019

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ መደመርን ሃሳብ በመቀበል እና የኢህአዴግን ውህደት በመደገፍ በአዲስ አበባ እና በሌሎች ከተሞች መሬት አንቀጥቅጥ የድጋፍ ሰልፎች ያስፈልጋሉ።የኢትዮጵያ ሕዝብ የፅንፍ የጎሳ ፖለቲካ አራማጆችን በሃሳብ የሚረታበት፣ኢትዮጵያዊነትን የሚያገንበት ወርቃማ አጋጣሚ ነው (ጉዳያችን ሀሳብ)



ጉዳያችን /Gudayachn 
ጥቅምት 11/2012 ዓም (ኦክቶበር  22/2019 ዓም)

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ላለፈው አንድ ዓመት ተኩል በርካታ ለውጦች ታይተውበት፣ተስፋ ተሰንቆበት፣ስጋት ታጅቦበት እስከ ዛሬ ደርሷል።የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂ ትዕግስት፣መቻቻል፣መከባበር  እና ከፍተኛውን የዋጋ ንረት ችሎ የኖረበት መንገድ ሁሉ አገሪቱ በርካታ መሰናክል የማለፍ አቅም እንዳላት አስመስክሯል።

በኢትዮጵያዊነት እና በፅንፍ የጎሳ ፖለቲካ ስንገላታ የነበረው አወዛጋቢ የኢትዮጵያ  የፖለቲካ መስመር አሁን መልክ እየያዘ የመጣ ይመስላል።በመጀመርያ የነበረው የጎሳ ፖለቲካ ፅንፈኞች ተፅኖ አሁንም ድረስ በፖሊስ፣በአስተዳደር እና በከተሞች የቀበሌ እና ክፍለ ከትሞች አስተዳደር  ጭምር በመሰግሰግ ኢትዮጵያዊነት አገንግኖ እንዳይወጣ የተቻላቸውን እየፈፀሙ ይገኛሉ።ሌላው ቀርቶ በመስቀል ደመራ በዓል ሳይቀር የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የያዙ ኢትዮጵያውያን የደረሰባቸው እንግልት የእነኚህ የፅንፍ ፖለቲካ አራማጆች እጅ በፖሊስ እና የቢሮክራሲ መስመር ሁሉ ቦታ መያዝ ያመላከተ ጉዳይ ነበር።

መደመር የፖለቲካ መስመሩን እንዲቀይር ዕድል እንስጠው

የፅንፍ ፖለቲካ አራማጆች ቅጥ ያጣ ተግባር ባየለበት እና ሕዝብ ለመጨረሻው ፍልምያ መነሳት እንዳለበት ባመነበት ሰዓት  ነበር ባለፈው ቅዳሜ የጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ መደመር የተሰኘው መፅሐፍ በይፋ በሚሊንየም አዳራሽ የተመረቀው። መፅሐፉ  ኢትዮጵያዊነት የሚያገነግነው ብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ በሚገባ ሊያጎላው እና ኢትዮያውነትን ከፍ አድርጎ ለማሳየት  ሊጠቀምበት የሚገባ ብቻ ሳይሆን ከልብ መርምሮ መሰረተ ሃሳቡን ደግፎ መቆም ያለበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው። ይህ ብቻ አይደለም። ከመደመር በተጨማሪ የኢህአዴግ ውሕደትም የኢትዮጵያ ሕዝብ ደግፎት ሊቆም የሚገባው ሌላው መልካም አጋጣሚ ነው።ውሕደቱ የተከፋፈለ የጎሳ ፖለቲካ አራማጅ ኢትዮጵያን ወደተሻለ የፌድራል አስተዳደር የሚመራ መልካም ጎዳና ነው።ይህም ኢትዮጵያዊነትን የሚያገነግን ሌላው መልካም ፖለቲካ ነው።ነገር ግን ይህንን ደግፎ አለመቆም በራሱ ትልቅ የፖለቲካ ክሳራ ነው።ኢትዮጵያዊነትን የሚያገነግኑ የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆኑ ጠቅላላ ህዝቡ በአዲስ መንፈስ እነኝህን ሃሳቦች ከፍ አድርጎ መነሳት እጅግ እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ ነው።

 የፅንፍ ኃይሎች የኢህአዴግ ውህደት  እና የመደመር  ፖለቲካ ለምን አስደነገጣቸው?

የኢህአዴግ የውህደት  ጉዳይ ድርጅቱ በሙሉ ድምፅ በሐዋሳ በወሰነው መሰረት መቀጠሉ የሱማሌ ክልልን ጨምሮ አፋር፣ጋምቤላ እና ቤንሻንጉል ክልሎች በከፍተኛ ጉጉት እየጠበቁት ነው።ህወሓት የተቃውሞ መግለጫ ብታወጣም፣የትግራይ ኤሊቶች እና የንግዱ ማኅበረሰብ ይህንን ውህደት እንደሚደግፈው መገመት ይቻላል።ምክንያቱም የትግራ ኤሊቶች እና ነጋዴዎች በሁሉም የአገሪቱ ክፍል ተዘዋውረው ለመስራትም ሆነ በአዲስ አበባ እና ሌሎች ቦታዎች ያላቸውን የንግድ ሥራ ለመስራት የኢሕአዴግ ውህደት ሰላማዊ ሁኔታ ከሕዝቡ ጋር እንደሚፈጥሩ  ስለሚያውቁ ሰላማዊ ሽግግሩን በውህደት ቢያልቅ እና ትግራይም ህዝቡ እንደፈለገ የመዘዋወር መብቱ እንዲጠበቅ ይፈልጋሉ። ይህ ማለት ህወሓት ያወጣችው መግለጫ  በራሱ ሕዝቡን የተቃረነ መሆኑን ለማወቅ ይቻላል።ስለሆነም በትግራይ ያለው አማራጭ አንዱ ህወሓት በራሷ ላይ ለውጥ አድርጋ ወደ ለውጡ ጎራ መግባት ወይንም  በተቃዋሚዎች መቀየር አልያም የመጨረሻው አማራጭ የውሕደቱ ሂደት ደግፎ መቆም ነው።

ይህ በእንዲህ እያለ የፅንፍ ኃይሎች የኢህአዴግን ውህደት የፈሩበት ዋና መንገድ ኦደፓ ውስጥ ላለፉት ዓመታት  የተሰገሰጉ የፅንፍ ፖለቲካ አራማጆች በሙሉ ዋና መንጠላጠያቸውን የጎሳ ፖለቲካ  በሁለት መንገድ እንደሚያጡ እና ከስራ ውጪ እንደሚሆኑ ስለተረዱት  ነው።አንዱ መንገድ ኦዴፓ ወደ ውህደቱ ሲመጣ በሁሉም ክልል የመንቀሳቀስ ዕድል ሲኖረው ሌሎች የቀድሞ የኢህአዴግ አጋሮችም በኦሮምያ በሁሉም ክልል የመንቀሳቀስ መብታቸው ይከበራል። ይህ ማለት ፅንፈኞቹ የግድ ከጉረኖ እየወጡ በአደባባይ የፖለቲካ አቅማቸው ብቻ ሳይሆን የአስተሳሰባቸው ጥግ የሚጋለጥበት  ስለሆነ ነው።

 የፅንፍ ፖለቲካ አራማጆች ትልቁ ድንጋጤ የዶ/ር ዓቢይ የመደመር ፅንሰ ሃሳብ ነው ።መደመር ሕብረ ብሔራዊ ጉዳይ ስለሆነ የጎሳ ፖለቲካን አፈርድሜ የምያበላው ብቻ ሳይሆን የሃሳብ ድውይ አድርጎ በሕዝብ ፊት የሚያንተባትበው አደገኛ ጉዳይ እንደሆነ አውቀውታል። ስለሆነም አጥብቀው ይፈሩታል።
''በመደመር እና በአብዮታዊ ዲሞክራሲ መሃል ብዙም ልዩነት አይታየኝም'' አለ ሃጅ ጃዋር ለኤልቲቪ ቴሌቭዥን የመደመር መፅሐፍ በሚመረቅበት ቀን በሰጠው ቃለ መጠይቅ።በመቀጠልም መፅሐፉን ለማራከስ አሉኝ ያላቸውን ቃላት ሁሉ ለመጠቀም ሞከረ። ይህ በራሱ አስገራሚ ብቻ ሳይሆን አስቂኝም ጉዳይ ነው።ጃዋር ሊነግረን የፈለገው በቀኝ ኃይሎች እና በግራ ኃይሎች መሃል ልዩነት የለም የማለት ያህል ነው። ቀጠለናም አብዮታዊ ዲሞክራሲ አሳሳችው መሰል ''አብዮታዊ ዲሞክራሲን  በሙሉ ማጥላላትም ትክክል አይደለም'' አለ።እውነተኛ ወዳጅ የችግር ጊዜ አይደል የሚገኘው።አብዮታዊ ዲሞክራሲ ሊቀበር አንድ ሐሙስ ሲቀረው  ጃዋር ሊደርስላት ስንገዳገድ ይታያል።

የአብዮታዊ ዲሞክራሲ መንገዳገድ ያሳስበው፣የመደመር ሕብረ ብሔራዊ ፈድራሊዝም ያሰጋው እና የኢህአዴግ ውህደት ያስደነገጠው የፅንፍ ፖለቲካ አራማጅ ኃይል ተደናግጧል ። መደናገጡ ደግሞ ያለ የሌለ ኃይሉን አንቀሳቅሶ የኢትዮያን ሕዝብ ለመረበሽ  ሰሞኑን በአዲስ አበባ ዙርያ የቄሮ ነን ያሉ ሕዝቡን እዚህ እና እዚያ እንዲረብሹ በማድረግ የለውጡን ሂደት  ለመረበሽ ሞክረዋል።ይህንን እኩይ ስራቸውን ሊገፉበት ይችላሉ። ህዝቡ ግን ከመደመር እና የኢህአዴግ ውህደት ከመደገፍ ጎን  በመቆም የጥፋት ኃይሎች በማያሻማ መንገድ የማስጠንቀቂያ ደወል ማሰማት እና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ  መልካም ሀሳቦች እና ኢትዮጵያዊነት አገንግኖ እንዲወጣ የማገዝ ታሪካዊ ኃላፊነት አለበት።በእዚህ ሰልፍ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሶስት መልዕክት ማስተላለፍ ይችላል። እነርሱም -
1ኛ) የብሔር ፖለቲካ እንደሚያጫርሰው ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን ወደ መጨረሻ የውድቀት ገደል የሚገፋ ስለሆነ ፈፅሞ እንደማይቀበለው  ለጥፋት ኃይሎችም ሆነ ለዓለም ዓቀፉ ማኅበርሰብ ግልጥ መልዕክት ያስተላልፋል።

2ኛ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ በሙሉ መተማመን የመደመር ሃሳባቸውን እንዲያራምዱ እና አብሯቸው እንደሚቆም በግልጥ ያሳያል።እርሳቸውን ተፃረው የጎሳ ፖለቲካ ለማስፈን የሚፈልጉ ኃይሎችን ያስጠነቅቃል፣

3ኛ) የህዝቡን አንድነት መልሶ የሚያረጋግጥበት መልካም አጋጣሚ ይሆናል።

ስለሆነም አክትቪስቶች፣ቅን ዜጎች እና በውጭ የምትኖሩ ሁሉ ከሰሞኑ የደመቀ የድጋፍ ሰልፍ የኢህአዴግን ውሕደት በመደገፍ እና የመደመር ፅንሰ ሃሳብን በመደገፍ  ምድር አንቀጥቅጥ  ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ትርጉሙ ትልቅ መሆኑን ልትረዱት ይገባል።ለማስታወስ ያህል፣የሰኔ 15ቱ ሰልፍ በፊት ቀደም ብሎ አንድ ሳምንት በአዲሱ የለውጥ ኃይል ላይ የዛቻ እና የማደናቀፍ ሙከራ አዘል መግለጫ ሲወጣ ጉዳያችን ምሽቱን መፍትሄው በአዲስ አበባ ታላቅ ሰልፍ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁማ የመወያያ ርዕስ ሆኖ ብዙዎች አሳድገውት በአንድ ሳምንት ውስጥ ሰልፉ መቀናበሩ ይታወሳል። እዚህ ላይ ጉዳያችን ይህንን አደረገች ለማለት ሳይሆን ሃሳብ ሲሰጥ ብዙዎች ካመኑበት ወዲያው የሃሳቡ አራማጆች የመሆናቸው መልካም ሂደት ለመጠቆም ነው። ይህ ሰልፍ አሁንም ለኢትዮጵያ እጅግ አስፈላጊ እና የለውጡን ምህዋር በኢትዮጵያዊነት ፍቅር እንዲፀና የራሱ ታሪካዊ ሚና ያለው መሆኑን መዘንገት አያስፈልግም።

መደመር በዜማ 


ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Saturday, October 19, 2019

በኖርዌይ የኖቤል ሽልማት ዙርያ አዲስ ዜና - በኦስሎ፣ኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ''በኢትዮጵያውያን የጋራ መድረክ በኖርዌይ'' አሰባሳቢነት የጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ የኖቤል ሽልማት ዙርያ ከአቀባበል እስከመስተንግዶ ባለው ዝግጅት ዙርያ ተወያዩ (Gudayachn Exclusive)


በስብሰባው ላይ ከተሳተፉ የኦስሎ ኖርዌይ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን በከፊል 

ጉዳያችን / Gudayachn 
ጥቅምት 8/2012 ዓም (ኦክቶበር 19/2019 ዓም)

የኢትዮጵያ ስም እንዲልቅ  

የቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ያደረጉትን ንግግር በሙሉ የያዘ መፅሐፍ በተለያዩ ጥራዞች ''ፍሬ ከናፍር'' በሚል ስም ይታወቃል።መፅሐፉ ንጉሡ በእያንዳንዱ በዓል፣የውጭ እንግዳ ሲቀበሉ እና በእራት ግብዣ ላይ ሁሉ ያደርጉት ንግግር በሚገባ በቀን፣በወር እና በዓመት ተለይቶ የተፃፈ መፅሐፍ ነው።መፅሐፉን በገበያ ላይ ባያገኙት በእርግጠኝነት አዲስ አበባ ከኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ዋና መስርያ ቤት ጀርባ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቤተ መዘክር (ወመዘክር) መፅሐፍት ቤት ጎራ ብሉ አያጡትም።በእዚህ መፅሐፍ ላይ በእያንዳንዱ ዓመት  ኢጣልያ ከኢትዮጵያ ከተባረረች ጊዜ ጀምሮ እስከ 1960ዎቹ ድረስ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ወደ ውጪ አገር ለትምህርት ሲሄዱ በቅድምያ ንጉሰ ነገሥቱን ቤተ መንግስት ሄደው አግኝተው መሰናበት እና ምክር ለመቀበል ሲሄዱ ለተማሪዎቹ ያደረጉት ንግግር የመፅሐፉ አንዱ አካል ነው።በእዚህ ጊዜ ንጉሡ የሚያደርጉት ንግግር ላይ ለትምህርት የሚሄዱ ተማሪዎችን የሚሉት አንድ የተለመደ ዓረፍተ ነገር አለ። ይሄውም የወጣቶቹ ወደ ውጪ መሄድ የኢትዮጵያ ስም እንዲልቅ መሆኑን ንጉሡ ደጋግመው የሚጠቀሙበት አነጋገር ነው። ወጣቶቹ በውጭ አገር በሚቆዩበት ጊዜ ሁሉ እና በኃላ መስራት ያለባቸው ሁሉ የኢትዮጵያ ስም እንዲልቅ መሆኑን አበክረው የተናገሩበት ንግግር በተደጋጋሚ ይገኛል።የንጉሡ ምክርም ይሄው የኢትዮጵያ ስም እንዲልቅ በሚል ዓረፍተ ነገር የተሞላ ነው።ዛሬ በኦስሎ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ያደርጉት ስብሰባም የሚያስታውሰው የኢትዮጵያ ስም እንዲልቅ በሚል ሃሳብ ዙርያ ነው።

የኢትዮጵያ ስም እንዲልቅ - በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የዛሬው የኦስሎ ስብሰባ  

ዛሬ ጥቅምት 8/2012 ዓም  የኢትዮጵያውያን የጋራ መድረክ በኖርዌይ በጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ የተገኙ ኢትዮጵያውያን ታሕሳስ 10/2019 ዓም እኤአ ኦስሎ፣ኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ በተገኙበት የሚሰጠው የኖቤል ሽልማት መርሐግብር ላይ የኢትዮጵያውያን ሚና ምን መሆን አለበት በሚል ሃሳብ ዙርያ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ላይ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ በኖርዌይ (ኢትዮጵያ ኮሚኒቲ) ሰብሳቢ አቶ ፍቅሩ፣ከኤርትራ ማኅበረሰብ እና ሌሎች ኢትዮጵያውያን የተገኙ ሲሆን በመርሐግብሩ መጀመርያ ላይ አቶ ጌታቸው በቀለ የኢትዮጵያውያን የጋራ መድረክ ሰብሳቢ የኖቤል ሽልማቱ ከኢትዮጵያን አልፎ አፍሪካውያን የፈጠረው ልዩ ስሜት ከደቡብ አፍሪካ እስከ ምዕራብ አፍሪካ ያሉ የመገናኛ ብዙኃን በርካታ ዘገባዎች እያቀረቡ መሆኑን፣ ኢትዮጵያ የሚለው ስም ከኖቤል ሽልማቱ  በፊት በጉግል ፍለጋ የነበረው ቁጥር በአማካይ ወደ ሰላሳ አራት ሚልዮን የነበረ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ  ባለፈው ሳምንት የኖቤል ሽልማት አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጠ በኃላ ቁጥሩ በአስር እጥፍ አድጎ ወደ ሶስት መቶ አርባ ሚልዮን  ማሻቀቡ ኢትዮጵያን በምን ያህል ደረጃ በመላው ዓለም በበጎ ጎኑ እንዳስጠራት ለማወቅ እንደሚቻል ገልጧል። 

በመቀጠል የኖቤል ሽልማት ምንነት እና በኖርዌይ የምንኖር ኢትዮጵያውያን የሚጠበቁብን ስራዎች በተመለከተ ማብራርያ የሰጡት  አቶ ለማ  ናቸው። አቶ ለማ በንግግራቸው መግቢያ ላይ ሽልማቱ የፈጠረው ደስታ ታላቅ መሆኑን አውስተው፣ይህንን ታላቅ ዕድል በሚገባ በመጠቀም የኢትዮጵያን ስም ከፍ ማድረግ እንደሚቻል አብራርተዋል።በተጨማሪም የሽልማቱ ምክንያት ከኤርትራ ጋር በተፈጠረው ሰላም ብቻ ሳይሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ  በአገር ውስጥ በሰሩት መልካም ተግባር መሆኑን ካብራሩ በኃላ የኖቤል ሽልማት የሚሰጠው ድርጅት ኖቤል ኢንስቲትዩት እንደሚባል እና  የተሸላሚዎችን ታሪክ በመላው ዓለም የማስተዋወቅ ሥራ በመስራት የሕዝብ ግንኙነት ሥራ የሚሰራው  ''ኖቤል ሴንተር'' የሚሰኝ  መሆኑን አብራርተዋል።

ከስብሰባው ተሳታፊዎች በከፊል 

ከእዚህ በተጨማሪ አቶ ለማ በሶስቱ ቀናት የሚኖሩትን መርሃግብሮች በተመለከተ የሚኖሩ ክንውኖችን ከመርሐግብሩ አንፃር ሲያብራሩ፣ ታህሳስ  9/2019 ዓም ጋዜጣዊ መግለጫ ኦስሎ ላይ እንደሚሰጥ፣ በቀጣዩ ቀን ታህሳስ 10/2019 ዓም  ሽልማቱ የሚሰጥበት ቀን ሲሆን በእዚሁ እለት ምሽት ላይ በሁሉም የኖቤል ሽልማቶች ላይ እንደሚደረገው በርካታ የኖርዌይ ድርጅቶች በሕብረት  የሚያዘጋጁት በብዙ ሺህ የሚቆጠር የኖርወያውያን፣የውጭ ዜጎች እና ኢትዮጵያውያን የሚሳተፉበት የጧፍ ማብራት ሰላማዊ ሰልፍ ከማዕከላዊ ኦስሎ በተለምዶ ''ነብሩ'' ተብሎ ከሚጠራው ቦታ እስከ ግራንድ ሆቴል ድረስ እንደሚኖር እና ግራንድ ሆቴል ሰገነት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ከኖርዌይ ንጉሳውያን ቤተሰብ ጋር ብቅ ብለው  ለተሰላፊዎች የክብር ሰላምታ እንደሚሰጡ ገልጠዋል። በቀጣዩ ቀን ከእዚህ በፊት የተሸለሙ መሪዎች እንደሚያደርጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ  ከኖርዌይ ባለስልጣናት ጋር ኦፊሻል ውይይት የሚያደርጉበት ቀን ሊሆን እንደሚችል ይህ ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሚኖራቸው መርሐግብር ጋር አብሮ የሚሄድ መሆኑን ገልጠዋል። ከእዚህ በተጨማሪ የኖቤል ሽልማት እንደተደረገ ዓመቱን ሙሉ ልዩ ኤግዚቢሽን ለሕዝብ ክፍት እንደሚሆን ገልጠው በመጨረሻም አቶ ለማ የአቀባበሉ ስነ ስርዓት ሁሉን በእኩልነት ያሳተፈ እንዲሆን፣ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ያለበት፣ሰንደቅ ዓላማ በተመለከተ ኦፊሻል መንገድ መጠቀም እና የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በማዕከልነት ማስተባበሩ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል። 

በመቀጠል የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሰብሳቢ አቶ ፍቅሩ ይህንን ስብሰባ ያዘጋጀው የኢትዮጵያውያን የጋራ መድረክን  አመስግነው፣የኖቤል ሽልማቱ የተሰጠበት ቀን ኮሚኒቲው ምሽቱን ጥሪ አድርጎ ደስታውን በአንድነት መግለጡን  እና በዕለቱ ከኖርዌይ ቴሌቭዥን ዘጋቢዎች መገኘታቸውን ገልጠዋል።ከእዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ኮምኒቲ  የኖቤል ሽልማት ዝግጅት በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ለማግኘት ጥረት ማድረጉን እና ኤምባሲውም በራሱ መረጃ እየጠበቀ መሆኑን እንደገለጠ አስታውቀዋል።ከእዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የምንም እና ማንም የፖለቲካ ድርጅት አቀንቃኝ አለመሆኑን አፅንኦ ሰጥተው አሁንም ከሁሉም ስብስቦች ጋር  ለመገናኘት እየሞከረ መሆኑን ገልጠዋል።

ስብሰባው በተከታይ በኢትዮጵያውያን የጋራ መድረክ ሰብሳቢ አቶ ጌታቸው በቀለ አወያይነት ተሰብሳቢዎቹ በኖቤል ሽልማቱ ስነ ስርዓት ሰሞን በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሚና እና የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በማገዝ ሊሰሩ የሚገባቸው ስራዎች ዙርያ  ተሰብሳቢዎቹ ሃሳብ ሰጥተዋል። ከተሳታፊዎች ከተሰጡት ሃሳቦች ውስጥ -

'' እኔ በሕይወቴ ያላየሁት ጉዳይ ነው ያየሁት'' አሉ አንድ እናት ስለ ኖቤል ሽልማቱ ሲናገሩ በመቀጠል '' ዜናው ሲነገር ነጮቹ ድንገት መጥተው  ከበቡኝ እየሳሙ 'ግራቱለረ' የምስራች! አሉኝ።ቀኑን ሙሉ ስሳም የዋልኩት፣ልጄ ድንገት ደውሎ 'ግራቱለሬ' ማሚ ብሎ ደስታው ሲቃ እየተናነቀው አናገረኝ።ትምህርት ቤቱ ተማሪው ሁሉ ከቦት ደስታውን እየገለጡለት እንደሆነ  ነገረኝ።ይህ ብቻ አይደለም።የትምህርት ቤቱ የክፍል ልጆች ጋር ተሰብስበው በዓል አደረጉ።ይህ ጉዳይ በልጆቻችን ላይ የፈጠረው የሞራል ልዕልና  በቃላት የምገልጠው አይደለም።እባካችሁ ልጆቻችን የኢትዮጵያን መከራ ስናወራ ሲሰሙ ነው ያደጉት። ቢያንስ ደስታ እስኪ የሚሰሙበት ጊዜ እንዲሆን ይህንን የኖቤል ሽልማት አስመልክቶ አንድ አይነት  ትልቅ ዝግጅት ማዘጋጀት አለብን።ይህንን ዝግጅት ላይ ለመገኘት የኖርዌይ ተወላጆች ሁሉ እየጠየቁ ነው እና ይህ ጉዳይ  ሊታሰብበት ይገባል'' ብለዋል።

ሌላ እናት ቀጠሉ '' የሽልማቱ ቀን በርካታ ቴክስት ከኖርዌይ ተወላጆች ደረሰኝ።ብዙዎቹ የጉዲፈቻ ኢትዮጵያውያንን ያሳደጉ ናቸው። ሁሉም የሚያሳድጉዋቸው ልጆች ይህንን ደስታ የሚያሳዩበት አንድ አይነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን የሚገናኙበት  የጋራ ደስታ መግለጫ በዓል እንዲዘጋጅ እና በእዚህ ዝግጅት ላይ እንደሚገኙ ቃል ገብተዋል። ስለሆነም እባካችሁ ከእኛ ይልቅ ልጆቻችን የሚኮሩበት እና በአገራቸው የሚኮሩበት መልካም ዕድል እንፍጠር'' ብለዋል።


ስብሰባው በመቀጠል ከኤርትራ ማኅበረሰብ የመጡ አቶ ንጉሡ አስተያየት የሰጡ ሲሆን በአስተያየታቸው ''እኔ አሁን ኤርትራ ቀድሞ የኢትዮጵያ ክፍለ አገር የመጣሁ የዓቢይ ወጤት ደጋፊ ነኝ።አብረናችሁ ነን።ኢትዮጵያ እና ኤርትራ አንድ ሕዝብ ነን በእዚህ  ዝግጅት ላይም አብረናችሁ ነን'' ብለዋል።

በመጨረሻም  ስብሰባው ከመጠናቃቁ በፊትበሚከተሉት ነጥቦች ላይ የጋራ መግባባት ተደርሶበት  ስብሰባው ተፈፅሟል። እነኝህ በጋራ መግባባት የተደረሰባቸው ነጥቦች -

  • የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ቀድም ብሎም እንደገለጠው ከኖቤል ሽልማቱ ጋር በተያያዘ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ወደ ኦስሎ ሲመጡ ለሚኖረው የክብር አቀባበል፣እስከ የሚመለሱበት ጊዜ ያለው ዝግጅት ዙርያ የሚያስተባብር አንድ ግብረ ኃይል  በኢትዮጵያ ኮሚኒቲ እንዲመሰረት እና ወደ ሥራ እንዲገባ፣ይህ ኮሚቴ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን፣
  • የኢትዮጵያ ኤምባሲ (ስዊድን ፣ስቶኮልም የሚገኘው) ከኢትዮጵያ ኮሚንቲ ጋር አብሮ እንዲሰራ እና ዝግጅቱ ውበት ያለው እንዲሆን መስራት እንዲጀመር፣
  • ኢትዮጵያን ባላቸው የግልም ሆነ የቡድን ግንኙነት (ኔትዎርክ) የኖቤል ሽልማቱ ለኢትዮጵያ ትልቅ ስም የሚሰጥ ብቻ ሳይሆን በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን  ይህንን ታሪካዊ እና አገራዊ ፋይዳ ያለው ዝግጅት በኢትዮጵያዊ ጨዋነት  እና በባለቤትነት እንዲያስተናግዱ እና  አስፈላጊውን ጥሪ ከኮምንቲ እንዲጠብቁ፣
  • አንድ ልዩ የደስታ መግለጫ መርሃግብር ሁሉንም ኢትዮጵያውያን፣አፍሪቃውያን እና የኖርዌይ ተወላጆች የሚያሳትፍ ዝግጅት እንዲኖር  በእዚህ ዝግጅት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ የሚገኙበት ሁኔታ እንዲመቻች ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይም  ኢትዮጵያውያንን የሚያገኙበት መልካም አጋጣሚ እንዲፈጠር የሚሉት ዋና ዋና ነጥቦች ነበሩ።
በመጨረሻም የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በተሰጡት ሃሳቦች ዙርያ አስተያየት ከሰጠ በኃላ በስብሰባው መደሰቱን እና በርካታ ጠቃሚ ግብዓቶች  መገኘታቸው እና አሁንም በዝግጅቱ ማማር ዙርያ ሁሉም ኢትዮጵያውያን አብረው እንዲሰሩ እና በተቀናጀ መልክ  ለመስራት እና የኢትዮጵያን ስም ከፍ ለማድረግ ለመስራት ጥሪ አቅርቦ የዕለቱ ስብሰባ ተፈፅሟል። 


ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

የ“መደመር” መፅሐፍ ምርቃት ስነ ስርዓት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ያደረጉት ታሪካዊ ንግግር

ጉዳያችን / Gudayachn

ጥቅምት 8/2012 ዓም (ኦክቶበር 19/2019 ዓም)
=======================
Today's Historical speech of Ethiopian prime minister Abiy Ahmed (PhD) on the launch of his new book ''MEDEMER". The 280-page book examines and outlines the economic, political and foreign policy directions of Ethiopia. 
Source = EBC


ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com

Friday, October 18, 2019

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ የኖቤል ሽልማቱ የኢትዮጵያን ስዕል በመላው ዓለም ቀይሮታል። አፍሪካ ስትፈልገው የነበረው መሪ ይህ ነው።የደቡብ አፍሪካ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን Africa should celebrate Abiy Ahmed for winning the Nobel Peace Prize:

ጉዳያችን / Gudayachn
አፍሪካ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ የኖቤል ሽልማት  እጅግ መደሰት አለባት።አፍሪካ ስትፈልገው የነበረው መሪ ነው።ኢትዮጵያውያን ምንም ዓይነት ፖለቲካ ተከተሉ፣ ከየትኛውም ጎሳ መጡ በእዚህ ሽልማት መደሰት አለባቸው።ይህ የኢትዮጵያ ብቻ ሽልማት አይደለም።ይህ ለአፍሪካም የተሰጠ ነው።የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኖቤል ሽልማቱ የኢትዮጵያን ስዕል በመላው ዓለም ቀይሮታል። የደቡብ አፍሪካ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን 
Africa should be proud. This is the leader that we Africans are looking for.
Source =SABC


ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com

Monday, October 14, 2019

ቆይታ ከሙሐዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ጋር ክፍል 1

ማን ምን አለ?
ኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን (ኢሳት)
ጥቅምት/2012 ዓም 


ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com

Friday, October 11, 2019

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ የኖቤል ሽልማት ማግኘታቸው ለአፍሪካ ያለውን አንደምታ ዋናው የደቡብ አፍሪቃው ብሮድካስት ቴሌቭዥን በሚገባ ተንትኖታል (ቪድዮ)

በቅድምያ ጉዳያችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ከመላው ዓለም የኖቤል ሰላም  የ2019 ዓም እኤአ አሸናፊ በመሆናቸው ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ለመላው ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያው ወዳጆች በሙሉ እንኳን ደስ አለን! ለማለት ትወዳለች።

Source = SABC (South African Broadcasting Corporation)


ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Wednesday, October 9, 2019

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለውን ጥፋት በተመለከተ በኦስሎ፣ኖርዌይ ቅዳሜ ታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባ ተጠርቷል።

ጉዳያችን / Gudayachn 
መስከረም 28/2012 ዓም (ኦክቶበር 9/2019 ዓም)
+++++++++++++++++++ 
በጉባኤው ላይ መሳተፍ በርቀት ከመቆጨት ያለፈ አንድ እርምጃ ነው።
  • በኦስሎ የሚገኙ ሁለቱም አጥብያዎች ካህናት እና ምእመናን በአንድነት በስብሰባው ላይ ይሳተፋሉ።
  • ከኦስሎ ውጪ  ለሚገኙ አጥብያዎች  ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በሙሉ እንዲያውቁት መልዕክት ደርሷል።
  • ከኦስሎ ውጪ የሚመጡ ተሳታፊዎች ይኖራሉ።
በመጪው ቅዳሜ ጥቅምት 1/2012 ዓም (ኦክቶበር 12/2019 ዓም)  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የሰሜን አውሮፓ አህጉረ ስብከት የኦስሎ፣ኖርዌይ መካነ ቅዱሳን ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለ ኃያማኖት ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ሰበካ ጉባኤ አስተባባሪነት  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለውን ጥፋት በተመለከተ ሕዝባዊ ስብሰባ ተጠርቷል። በተመሳሳይ መልኩ በሀገር ቤት ከሃምሳ ከተሞች በላይ እና በባህር ማዶ በአሜሪካ እና አውሮፓ ተመሳሳይ ጥሪዎች በሰላማዊ ሰልፍ መተላለፋቸው ይታወቃል።


በኦስሎ፣ኖርዌይ በመጪው ቅዳሜ የሚደረገው ሕዝባዊ ስብሰባ ሊቃነ ጳጳሳት፣ካህናት እና በርካታ ምእመናን እንዲሁም ከቤተ ክርስቲያኒቱ ተከታዮች ውጪ በኢትዮጵያዊነታቸው የሚገኙ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።ቅዱስ ሲኖዶስ በድንገተኛ ስብሰባው ላይም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተከታይ ያልሆኑ ሁሉ አጋርነታቸውን እንዲገልጡ ባሳሰበው መሰረት በእዚህ ጉባኤ ላይም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በእዚሁ ዓውድ የሚታይ ነው።

በመጨረሻም በኦስሎ የሚደረገው ስብሰባ በሌሎች አካባቢዎች ከሚደረጉ ሰልፎች በተለየ ምእመናን በአንድነት ስብሰባዎችን በማዘጋጀት መምከር ሌላው አማራጭ በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚደርሰውን ፈተና የመቃወምያ መንገድነት በር የሚከፍት መልካም ሃሳብ እንደሚሆን ይታመናል።

አንዲት ናት ቤተክርስቲያን አንዲት ናት (በማኅበረ ቅዱሳን የመዝሙር ልዑክ የተዘጋጀ አዲስ መዝሙር)


ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

Tuesday, October 8, 2019

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሰባት ነጥቦች ዙርያ መግለጫ አወጣ (የመግለጫው ሙሉ ቃል በድምፅ እና በጽሁፍ)

መስከረም 27/2012 ዓም (ኦክቶበር 8/2019 ዓም) 
መግለጫው በጽሁፍ  ከኦድዮ ስር ያገኙታል።
ምንጭ - ዘ-ሐበሻ
የመግለጫው ፅሁፍ



ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Friday, October 4, 2019

ሰበር ዜና - የአዲስ አበባ ነዋሪ በዕጣ ደርሶት የነበረው 23 ሺህ ኮንደሚንየም በመጪው ሰኞ ተነጥቆ ''ለባለተረኞች'' በኦፊሴል በሚሌንየም አዳራሽ ሊታደሉ ነው (Gudayachn Exclusive)

ጉዳያችን GUDAYACHN 

መስከረም 24/2012 ዓም  (ኦክቶበር 5/2019 ዓም)

በአዲስ አበባ ዙርያ ከዓመታት በፊት ለልማት ተነስተው የነበሩ እና በምትኩ ለእርሻም ሆነ ለመኖርያ ቦታ ተሰጥቷቸው  የነበሩ የኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ቀድሞ ከተሰጣቸው ምትክ ካሳ በተጨማሪ በሚመጣው ሰኞ በሚሊንየም አዳራሽ በሚደረግ ስነ ስርዓት የኮንደምንየም እደላ ሊደረግ መሆኑን ከአዲስ አበባ ተሰምቷል።

መረጃውን በተመለከተ ጉዳያችን ለማጣራት እንደሞከረችው ከእዚህ በፊት ካሳ ተሰጥቷቸው  የነበሩት ብዛት ሶስት ሺህ ሲሆኑ የተቀሩት 20 ሺህ የሚሆኑት በውሸት የተፈናቀሉ ነበሩ በሚል ስም ከተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች ውስጥ ተመርጠው የሚመጡ እና ካለምንም ዕጣ እና ክፍያ የሚሰጣቸው መሆኑ ተሰምቷል።በሌላ በኩል ለእነኝህ አካላት የሚሰጠው የኮንደምንየም እደላ ልዩ የብድር አገልግሎት ይመቻችላቸዋል የሚል መረጃ አለ።የተረጋገጠው ጉዳይ ግን የአዲስ አበባ ሕዝብ በዜግነት መብቱ ተመዝግቦ እና ዕጣ አውጥቶ ኮንደሚንየም  እየጠበቀ ቢሆንም  ከ23 ሺህ የማያንሱ ኮንደሚንየም ቤቶች በሙሉ ከላይ ለተጠቀሱት አካላት የሚሰጥ መሆኑ ነው።

በኮንደሚንየም አሰጣጡ ኢ-ፍትሃዊ አካሄድ ደግሞ ቀድሞ ካሳ ለተሰጣቸው ድጋሚ ኮንደሚንየም ሲሰጥ፣በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ሁለቴ እና ሶስቴ እየተሰጠ ሲሆን ለምሳሌ በቤተሰብ ውስጥ ለቤተሰቡ ሶስት መኝታ ክፍል ከተሰጠ በኃላ በቤተሰቡ ውስጥ ላሉ ከአስራ ስምንት ዓመት በላይ የሆኑ ልጆች ላሏቸው ለልጆቹ ለብቻቸው ሌላ የኮንደሚኒየም ቤቶች እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል።

ይህ በእንዲህ እያለ ዛሬ በአዲስ አበባ የእረቻ በዓል ዋዜማ በሚል በመስቀል አደባባይ የኦሮምያ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ  ''የኦሮሞ ሕዝብ የተሰበረው እዚህ ነው፣የነፍጠኛ ስርዓትን ዛሬ ሰበርነው፣የኦሮምያ ሕዝብ ደስ ይበልህ'' የሚል አደገኛ የዘር ቀስቃሽ ንግግር (ምናልባትም የሁቱ እና ቱትሲ ግጭት የመሰለ  ንግግር) መናገሩ ከፍተኛ ውጥረት ኢትዮጵያ ውስጥ ፈጥሯል።

የአቶ ሽመልስ ንግግር የኦዴፓ ድብቅ እና ከፋፋይ ዓላማ በግልጥ ያሳየበት ብቻ ሳይሆን ኦዴፓ ከፅንፍ ኃይሎች ጋር አፍ ለአፍ ገጥሞ እየሰራ መሆኑ ግልጥ ማሳያ ሆኗል።ሌላው የንግግራቸው ማሳያ አሁን ለውጡ ሙሉ በሙሉ ሐዲዱን እየለቀቀ መሆኑን ማሳያ ተደርጎ መወሰድ ይችላል።

ለኢትዮጵያ ነፃነት ከታገሉ የኢትዮጵያ ነፍጠኛ  አርበኞች መካከል ፋሺሽት ጣልያን ኢትዮጵያን በወረረበት  ወቅት 1928 ዓም አዲስ አበባ 
Determined Ethiopian young patriot NEFTEGNA at the beginning of the second world war, when Italy invaded Ethiopia in 1935.



ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com

Wednesday, October 2, 2019

ከ2 ሚልዮን ምዕመናን በላይ የተገኙበት የዛሬው የግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም ንግሥ በዓል ላይ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ያስተላለፉት ሙሉ መልዕክት (ቪድዮ)

መስከረም 21፣2011 ዓም  ግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም ገዳም ቀጥታ ስርጭት 


ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

የኦሮሞ ድርጅቶች ተፈራረሙ ወይንስ ተፈራሩ? (የጉዳያችን ምልከታ)

 Bildergebnis für oromo patriots 
ታላቁ የኢትዮጵያ አርበኛ ጀነራል ጃጋማኬሎ

ጉዳያችን/Gudayachn
መስከረም 21/2011 ዓም (ኦክቶበር 2/2019ዓም)

=========================
ትናንት ማክሰኞ መስከረም 20/2011 ዓም ወደ 14 የሚጠጉ ድርጅቶች በጋራ ለመስራት መፈራረማቸውን ለአምስተኛ ጊዜ በመፈራረም አሳይተዋል።የፊርማው ድባብ በራሱ የሚነግረን ነገር ግን የተለየ ነው።
ለመሆኑ የተፈራረሙት ማን ከማን ጋር ነው ብለን ብንጠይቅ መልሱ ቀላል ነው።ለሃያ ሰባት ዓመታት ኦህደድ የኦነግ ድርጅቶችን ሸኮና እየሰበረ አላስገባ ካላቸው ኃይል ጋር ነው።ይህ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራው የኦህዴድ (የአሁኑ ኦዴፓ) የኦነጎችን ፕሮፋይል ደካማና ጠንካራ ጎን ሲያጠና ነው የኖረው።በእርግጥ የኦነግ አንጃዎች እና ኦዴፓ በአንድ ነገር ላይ ይስማማሉ።ይሄውም ኢትዮጵያዊ ቅኝትን ማጥፋት፣የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ተሰሚነት ማደብዘዝ፣ያለፈውን ታሪክ በአዲስ የእረቻዊ የታሪክ ትርክት መፃፍ እና ሌሎች ላይ አብረው የሚያልሙት ጉዳይ ነው። ይህ ግን ሁሉም ኦዴፓ ውስጥ ያለ ሃሳብ አይደለም።ሃሳቡ ቢኖርም እንደማያዋጣ ጠንቅቀው የሚያውቁ ብዙ ናቸው።ስለሆነም ግቡ ላይ ቢስማሙም አካሄድ ስልት ላይ ግን ይለያያሉ።

በአካሄድ ከሚለያዩት ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ይጠቀሳሉ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልችት ያላቸው ጉዳይ አሁንም የኦነግ እንደአንዳንዶች አባባል የማይጠራ የበግ ሽንፍላ የማጠብ ያህል ማለቂያ የሌለው ያረጁ እና የጃጁ ጥያቄዎች እራሱ ኦነግ ቤተ መንግስት ቢገባም ያማይመልሳቸው ጥያቄዎች ናቸው።እነኝህ ጥያቄዎች የ21ኛው ክ/ዘመንን የማይመጥኑ ብቻ ሳይሆኑ ያለፈው እና የድሮው ስራቶችንም ያማይመጥን ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ አይነት ጥያቄ ያለው ግን ግቡ እና ዓላማው ኢትዮጵያዊነትን በፅንፍ የእስልምና ሃሳብ የመተካት ነው። ከኦነግ አንጃዎች ውስጥ ብዙዎቹ የኦኤምኤን ባለቤት ሃጅ ጀዋርን ጨምሮ የሚያገናኛቸው ይሄው ኢትዮጵያን ወደ ፅንፍ የእስልምና አብዮት መምራት ነው።ሁሉም ለኦሮሞ ሕዝብ እንደ ሰብዓዊ ጋሻ ከመጠቀም ያለፈ ቅንጣት ታህል አይፈልጉትም። ቢፈልጉት ኖሮ ሀገር ቤት ከገቡም በኃላ በኦሮሞ ስም እንደ አሜባ እየተራቡ ባልተከፋፈሉ ነበር።

የትናንቱ የኦሮሞ ድርጅቶች ተፈራረሙ ዜና ተፈራሩ በሚለው ቢቀየር የተሻለ ነበር።የፊርማው ስነስርዓት ሲደረግ ጀዋር ጮክ እያለ ለማንበብ እየቸገረው ድምፁን እየቆራረጠ በኦሮምኛ ሲያነብ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳቃቸው መጥቶ አይናቸውን ከወዲያ ወዲህ ይወስዱ ነበር። አሁን መሰረታዊው ጥያቄ ፅንፈኛው ክፍል ዓቢይን ለመምታት በፊርማ ሊያዘናጋ እየሞከረ ነው ወይንስ ዓቢይ የፅንፈኛውን አካል ጋር ተስማማ? የሚለው ነው። ይህ ጥያቄ በደንብ መመለስ ያለበት ነው።የፊርማው ስነ ስርዓት የመፈራራት ውጤት ነው።ግቡም ጊዜ መግዣ ነው።ፅንፈኛው አካል ዓቢይ ከስልጣን መውረድ እንዳለበት ያልማል።በቀላሉ ሊያደርጉ እንደማይችሉ ደግሞ ገብቷቸዋል።ዓቢይ የምንፈልገው አይደለም።የኢትዮጵያን ለውጥ ከቱንስያ ከፍ ማድረግ ነበረብን።አሁን ቆጨን እና ሌሎችም ሲሉ የነበሩ ዛሬ ፊርማ ያሉት አንድ ዓቢይ ሊያስረን ነው ብለው ስለፈሩ።ግልጥ እርምጃ የኦዴፓ ሰዎች መውሰድ ስለጀመሩ።ይህም በቀጥታ ማፈንን የጨመረ በመሆኑ ጉዳዩ ሳይከፋ የተለመደው ፊርማ ማንጋጋት መፍትሄ ነው ብለው ስላሰቡ ነው።

''ሀሎ ዓብይ ፊርማ ስነ ስርዓቱ አንተ ባለህበት መሆን አለበት'' አቶ ለማ ወደ ዓቢይ ደውለው።
''እባክህ ስራዬን ልስራበት።ከፈለጉ ወደ አስመራ መልሳቸው አርባ ዓመት ከገማ አስተሳሰብ ጋር አታነካካኝ።ካመንቅበት እንደሚሆን አድርገው'' ዓቢይ 
'' ግዴለህም እንደመንግስት ስንሆን መታገስ አለብን።ይህንን ብቻ ዓቢይ የአንተ መገኘት በጣም አስፈላጊ ነው።ሰጥቶ መቀበል አርገውታል።አንተን በአደባባይ ማሳየት እንደ ሾው ነው።ሆነም አልሆነም ምን ያህል እንደታገስን የሚያስረዳ ነው የሚሆነው።እረቻ ላይ ነገር ከተበላሸ ብዙ መዘዝ አለው።እሺ በለኝ።'' አቶ ለማ።

ዓቢይ ወደ አዳራሽ ሲገባ የምንሊክ ግብር የመሰለ ከአክትቪስት እስከ ጋዜጠኛ ተሰብስቧል።ዓቢይ የውሸት ዕቃ ዕቃ የሚጫወት ነው የመሰለው።ኦነግ ምን ሲሰራ እንደነበር ሪፖርቱ አለው።ከህወሓት ጋር እነማን ምን እንደተባባሉ ቃል በቃል ሰምቶታል።ይህ ፊርማ ዓቢይ ከጀዋር ጋር ተሰለፈ ለመባል የገበያ ዋጋ እንዳለው ያውቃል።ለማን ማስቀየም አልፈለገም።ሁሉንም ከኢረቻ በኃላ ይደርሳል።ስለሆነም ስልችት እያለው እና ሳቁ እየመጣ ተፈራረመ።እንደ ኦህዴድ -ኦዴፓ ሆኖ ፈረመ።ፈርሞ ሲወጣ ዘወር ዘወር ብሎ አየ እና ''ነጋቲ'' ብቻ ብሎ ወጣ። ፊርማ ሳይሆን መፈራራት።የእውነት ሳይሆን ዓቢይን በማዘናጋት ለመምታት እና ስልጣን ለመቆጣጠር የስልት ፊርማ መሆኑ ገብቶታል።የለማ የዋህነት እና ፅንፈኛውም የእኛው ነው ነገሮችን ማረቅ አለብን የሚለው አባባል የቆየ  ግን የማይሰራ መሆኑ ገብቶታል።ስለሆነም ቀጣዩ እርምጃ እና ሂደት ላይ ብቻ ነው ዓቢይ እያሰበ የወጣው።የኦነግን ፋይል ደህንነት መስርያቤት እያለ ሲያነበው ነው የኖረው።ወደ ሰውነት ማደግ ያልቻሉ የጫጩ አስተሳሰቦች እንዳሉበት ያውቃል።ስለሆነም ወደ ቀጣዩ ሂደት ላይ ማትኮር እንዳለበት ገብቶታል።

ለማጠቃለል ፍጥጫው  በፊርማው ባሰበት እንጂ አልተሻሻለም።የሚሻሻል ቢሆን ኖሮ ከአምስት ወር በላይ ፈጀብን እያሉ መናገር አይሳፈልገውም ነበር።በትክክል ከታሰበ የፈጀባቸው አምስት ወር አይደለም አርባ ዓመት ነው።ከአርባ ዓመት በኃላም ስለ አንድ ኦሮሞ እያወሩ አስራ አራት ሆነው ተቀመጡ እንጂ አንዳች አልፈየዱም።ከአርባ ዓመት በኃላ ከአስመራ ሀገር ውስጥ ገብተው ጥይት አንጣጡ ባንክ ዘረፉ እንጂ አንዳች ፋይዳ ለኦሮሞ ሕዝብ አላመጡም።ኦሮሞ ይነሳል! ኢትዮጵያዊነቱን በደሙ ያስከብራል።ያን ጊዜ ለፅንፍ አውሬ ሊሰጡት ያሰፈሰፉ ሁሉ እውነተኛ ፍርዳቸውን ያገኛሉ።የወለጋ ሕዝብ የደረሰበትን እና አሁን እየደረሰበት ያለውን ይመስክር።በሰላም አርሶ መብላት እና ነግዶ ማትረፍ ሕልም የሆነበት በኦነግ እና ውላጆቹ አስተሳሰብ የተነሳ ነው።ከኦነግ ያረጀ አስተሳሰብ ጋር እሄዳለሁ የሚል ማንኛውም ኃይል ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይም ሆኑ የኦዴፓ ለኦነግ አሸርጋጆች ሁሉ የሚፋረዳቸው የኦሮሞ ሕዝብ ነው።ይህ ዕውነት አይዘገይም። ባጭሩ የኦሮሞ ድርጅቶች ተፈራረሙ ከማለት ተፈራሩ ማለቱ የተሻለ ነው።ጀግኖቹ እነ ጀነራል ጃጋማኬሎ ደምተው ባቆዩት ሀገር ፅንፈኛ አይፈነጭባትም።ጉዳዩ እየጠራ መጥቷል።ኢትዮጵያዊነት ያነገቡ ከምር የሚነሱበት የደውል ድምፅ ከፍ ብሎ እየተሰማ ነው።

 
ጉዳያችን GUDAYACHN 
www.gudayachn.com

ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።