Friday, September 11, 2020

ከዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንና ማኅበራት አንድነት ጉባኤ በኢትዮጵያ፣ በክርስቲያኖች ላይ ስለሚደርስ ተደጋጋሚ ጭፍጨፋ እና ኢፍትሃዊነት ላይ የተሰጠ መግለጫ


መግለጫው በአሁኑ ሰዓትም ክርስትያኖች በአሸባሪዎች ዛቻ እየደረሰባቸውና ቀጣዩንና መጪውን ጊዜ በመፍራት ላይ ስለሚገኙና አሸባሪዎች ለበለጠ ጥፋት እየተዘጋጁ ስለሆነ ለሚመለከታቸው አካላት ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ 

ዓለም አቀፍ የምእመናንና ማህበራት ጉባኤ በክርስትያኖች ላይ የደረሰውን ዘግናኝ ጭፍጨፋና ያስከተለውን ጉዳት ሲያጣራና ሲከታተል ቆይቷል። በጭፍጨፋው ምክንያት የተበተኑትን ወደቀያቸው ለመመለስ፤ የተጎዱትን ለመካስና አጥፊዎችን ለፍርድ ለማቅረብ የሚደረጉትን ጥረቶች ሲያግዝና ሲከታተልም ነበር። ነገር ግን እነዚህ ጥረቶች በሚገባው ፍጥነት ውጤት አለማምጣታቸው ብቻ ሳይሆን አሁንም ክርስትያኖች በአሸባሪዎች ዛቻ እየደረሰባቸው ስለሆነና አንዳንድ ሰዎች የደረሰውን የአሸባሪዎች ጭፍጨፋ በግልጽ ሲደግፉና የደረሰውን ዘግናኝ ጉዳት በተለያዩ ሚድያዎችና መንገዶች ሲያስተባብሉ ስለታዘበ ጉባኤው ይህን መግለጫ ለመስጠት ተገዷል። 

በመላው ዓለም ለመጀመርያ ጊዜ ክርስትና በሰላም እንበለ _ደም በፍቅር ተሰብኮ ሀገራዊ ኃይማኖት የሆነው በአፍሪካ ምድር በሀገረ ኢትዮጵያ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በብዙ መከራ ውስጥ ጸንታ ዘመናትን ተሻግራ ሀገር ሁናና ሀገር መስርታ የሌሎችን እምነትን አክብራና አስከብራ የሰው ልጅ በነጻነት በፍቅርና በመተሳሰብ እንዲኖር ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያደገችም ነው። 

ቤተክርስቲያኗ የተመሰረተችው በመስቀል ፍቅር፣ በክርስቶስ ደም ስለሆነ የሰው ልጅ በፍቅርና በሰላም ተከባብሮ እና ተሳስቦ እንዲኖር ምንጊዜም ታስተምራለች፤ የሰው ልጅ ሁሉ በእኩልነት እንዲኖርና ፍትህ እንዲሰፍን ትሰራለች። ይህንን የፍቅር ጥሪ በመቃወም እና ተከባብሮ እና ተሳስቦ የመኖር እሴትን በመጠየፍ ሰውን በአሰቃቂ ሁኔታ የሚገድሉ፤ ሴቶችን በኃይል የሚደፍሩ፤ ህጻናትን የሚገድሉ አብያተ ቤተክርስቲያናትን የሚያቃጥሉ ሰው ወጥቶ ወርዶ ያፈራውን ንብረት የሚዘርፉ የሚያወድሙ፤ በኃይል የግላቸውን እምነት ሌሎች ላይ በኃይል የሚጭኑ፣ ዓለም አቀፍ ትስስርና ትብብር ያላቸው አሸባሪዎች በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ ሀገራት በተለያየ ስሞች ይገኛሉ። ከእነዚህ መካከል ጎልተው የሚታወቁትን ለመጥቀስ ያህል አልቃይዳ፤ አይሲስ፤ አልሸባብ፤ ቦኮ ሀራም፤ ፉላኒ ኢስላሚክ ቡድንና ሌሎችም ይገኙበታል። 

እነዚህ ዓለም አቀፍ አሸባሪዎች በኢትዮጵያ ስማችውንና የሽብር ዘዴአቸውን ቀይረው በቅርብ ዓመታት ውስጥ ብዙ ክርስቲያኖችን በገጀራ ቀልተው፤ በቆንጨራ ቆራርጠው፤ በጦር ወግተው በጩቤ ዘክዝከው፤ በሜንጫ ተልትለው፤ በዱላ ቀጥቅጠው እና በደንጊያ ወግረው ገድለዋል። አስከሬናቸው በጎዳና ጎትተዋል። አስከሬናቸው በአራዊት እንዲበላ አድርገዋል ። ሽማግሌዎችን አርደዋል። ነፍሰጡሮችን አሰቃይተው ገድለዋል። ህጻናትን በወላጆቻቸው ፊት አርደዋል። ሴቶችን፥ በልጆቻቸው፣ በአባቶቻቸው እና በባሎቻቸው ፊት ደፍረዋል። ክርስትያኖች ለዘመናት የደከሙበት ቤት ንብረታቸውን፣ ዘርፈዋል። ቀሪውን ጋዝ እያርከፈከፉ አቃጥለዋል። ክርስትያኖችን በኃይል አስገድደው አስልመዋል። ቤተ ክርስቲያናትን አቃጥለዋል። ክርስትያኖች ከቤታቸውና ከቀዬአቸው ተፈናቅለው በመቃብር ቤቶች በልዩ ልዩ መንግሥታዊ ተቋማት እንዲሁም፣ በግለሰቦች ቤቶች ተጠልለዋል። ለአስከፊም ማኅበራዊ እና ሥነ ልቡናዊ ቀውሶች ተዳርገዋል። አሸባሪዎቹ ክርስትያኖችን የማጽዳት ዘመቻ ብለው በጀመሩት ጭፍጨፋ በኦሮምያ ክልል “ከክርስትያኖች የጠዳ ምድር” በማለት የለዩአቸው አካባቢያዎች አሉ። እነኝህ በክርስትያኖች የደረሱት የዘር ማጥፋት ወንጀሎች በጠንካራ መረጃና ማስረጃ በደንብ የተያዙ ስለሆነ አስፈለጊ ሲሆን ጉዳዩ ለሚመለከተው አካል ማቅረብ እንችላለን። 

አሸባሪዎቹ ባለፉት ጥቂት ጊዜያት የፈጸሟቸውን የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን ለአብነት ያህል በማሳያነት ለመጥቀስ፤ 

● ከሰኔ 22 ቀን ምሽት ጀምሮ እስከ ሰኔ 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ ባሉት ሦስት ተከታታይ ቀናት በኦሮምያ ክልል በተፈጸመ ጥቃት፥ 67 ምእመናን በግፍ እና በአሠቃቂ ኹኔታ ተገድለዋል፤ 38 ምእመናን ቋሚ(ከባድ)፣ 29 ምእመናን ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ኮኮሳ ሆጊሶ መድሃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ሙሉ ለሙሉ ተቃጥሏል።ከ 530 በላይ የክርስቲያኖች መኖርያ ቤቶች ከ200 በላይ ሆቴሎችና ከ6 በላይ ፋብሪካዎች ተቃጥለዋል;፤ ከ500 በላይ መኖርያ ቤቶችና ከ35 በላይ ሆቴሎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። በገጠር አካባቢ በማሣ ላይ ያሉ ሰብሎችም ወድመዋል። ባለሃብት የነበሩ ክርስትያኖች በአንድ ጀንበር ተመጽዋች ሆነዋል። ከ7000 በላይ ክርስትያኖች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው በመቃብርና በተለያዩ ቦታዎች ተሰባስበው የመላው ዓለምን ድጋፍ እየጠበቁ ይገኛል። እነዚህ ክርስትያኖች በተለያየ ደረጃ ለሚገለጽ ሥነ ልቦናዊ እና ሥነ አእምሯዊ ቀውስም ተዳርገዋል። የብዙዎች ቤተሰብ አባላት ተበትነዋል። አሸባሪዎቹ ሙሉ በሙሉ የቤተሰብ አባላትን፤ ሽማግዎችን፣ ህጻናት ሴቶችን ጭምር አርደዋል። ለምሳሌ በኦሮሚያ ክልል ዝዋይ አዳሚ ቱሉ በእነዚህ አሸባሪዎች አንድ ሙሉ ቤተሰብ (አባት፤ እናትና ሶስት ልጆች) እጅግ አሰቃቂ በሆነ መልኩ አርደዋቸዋል። በአርሲ ነገሌ ደግሞ ከመግደልም አልፈው ሬሳው እንኳን በክብር እንዳይቀበር ዘቅዝቀው የሰቀሉት አለ፡፡ 

● በጥቅምት 2012 ዓ;ም በኦሮምያ ክልል 31 አብያተ ክርስትያናት ተቃጥለዋል፤ 97 ክርስትያኖች በግፍ ተገድለዋል፤ ከ40 በላይ በውል የታወቁ የመንዲሳ (ምስራቅ ሐረርጌ)) ነዋሪዎች፣ ቤት ንብረታቸው ከተቃጠለ በኋላ ዓይናቸው እያየ ልጆቻቸው እንዳይታረዱ ሲሉ ተገደው ሰልመዋል። ከ17 በላይ የምእመናን ንብረት የሆኑ ሆቴሎች ተቃጥለዋል። ከ80 በላይ የክርስትያኖች መኖርያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል። የክርስትያኖች ንብረት የሆኑ መኪኖችና ባጃጆች ተቃጥለዋል። 

● በመጋቢት ወር 2011 እና በመስከረም 2012 በአማራ ክልል በኦሮምያ ዞን በአጣየ ብቻ 57 ክርስትያኖች በግፍ ተገድለዋል፤ 68 ክርስትያኖች ከባድ እና ቀላል የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል። የካራ ቆራ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ተቃጥሏል። 

● በኢትዮጵያ እነኝህን የአሸባሪ ጥቃት አድራሾች ከአልሸባብ ወይም ከቦኮ ሀራም በተግባር በዓላማና በሚፈጽሙት ሽብር ተመሳሳይ ሲሆኑ በሚከተሉት ጉዳዮች ይለያሉ። 

1) ሽብር የሚፈጽሙት በሀገር ወይም በክልል አልያም በአንድ አካባቢ የሚከሰትን ፖለቲካዊ ነውጥ ወይም ክስተት ጠብቀው ወይም ሽፋን አድርገወ ነው። ለምሳሌ ከሰኔ 22 ቀን ምሽት ጀምሮ እስከ ሰኔ 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ ባሉት ሦስት ተከታታይ ቀናት የደረሱት የአሸባሪዎች ጥቃት የታዋቂውን ክርስትያን አርቲስት የሃጫሉ ሁንዴሳን ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም. ምሽት በአዲስ አበባ ግድያ እና ግድያውን ተከትሎ የተከሰተውን አለመረጋጋት እንደሽፋን በመጠቀም የተፈጽመ ነው። ከላይ በሁለተኛ ደረጃ የተጠቀሰው የሽብር ጥቃት በጥቅምት 12፣ 2012 ዓ.ም. አንድ ፖለቲከኛ ያስተላለፈውን መግለጫ ተከትሎ በርካታ ወጣቶች ወደ ሰልፍ ወጥተው ቅሬታቸውን በመግለጽ ላይ በነበሩበት ወቅት ምሽት የየአካባቢው ነዋሪ ያልሆኑ ጸጉረ ልውጥ ሰዎች በየአካባቢው ተጠራርተው በመንቀሳቀስ በክርስትያኖች ላይ ጥቃት አድርሰዋል።

2) አልቃይዳ፤ አይሲስ አልሸባብ ውይም ቦኮ ሀራም ሽብር ፈጽመው ኃላፊነት ይወስዳሉ፤ በኢትዮጵያ የሚገኙ አሸባሪዎች ግን ኃላፊነት አይወስዱም። ማንነታቸውንም አይገልጹም። እንዲያውም በተለያየ መልኩ በሚያደራጇቸው በሚረዷቸውና በሚደግፏቸው ሰዎች አማካይነት ምንም ችግር እንደሌለ፤ የማንም ክርስትያን ዝንብ እንኳን እንዳልነተካው አጥብቀው በየሚድያው እየጮሁ ሽፋን ይሰጧቸዋል። ትክክለኛ ዑላማዎችና ሙስሊሞች አሸባሪዎችን ለማውገዝና ድርጊታቸውን ለመንቀፍ ሲሞክሩ ከአሸባሪዎቹና ከደጋፊዎቻቸው የተቃውሞ ዘመቻ ይደረግባቸዋል። የመንግስት ባለስልጣናትን አጥብቀው ይጎተጉታሉ። ጫና ይፈጥራሉ። አስፈለጊ መስሎ ሲታያቸው የክርስትያኖችን የድረሱልን ጩኸት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ በማድረግ እውነተኛው ሙስሊም ከእነርሱ ጋር እንዲሆን ይቀሰቅሳሉ፣ ጫናም ያደርጋሉ። መንግስት ክርስትያኖችን ዝም እንዲያሰኛቸው ጫና ይፈጥራሉ።

3) በስልጣን ላይ የሚገኛው የኢትዮጵያ መንግስት የክርስትያኖች መከራ እንዳይሰማ ጫና ይፈጥራል። አሸበሪዎች በነጻነት እየተንቀሳቀሱ ብቻ ሳይሆን አሁንም ክርስትያኖችን እያሳደዱ መንግስት ግን ጭራሽ ክርስትያኖችን (ድምጻችን ይሰማ) ያሉትን ያስራል። ዶዶላ በጥቅምት 2012 ዓ.ም. አሸባሪዎች ቀርተው ክርስትያኖች እስካሁን ድረስ ያለምንም ጥፋት እንደታሰሩ ነው። በጉዳዩ ላይ ማብራርያ እንዲሰጠው ሄውማን ራይትስ ወች ባላፈው መጋቢት ወር ቢጠይቅም ከኢትዮጵያ መንግስት አስካሁን መልስ አላገኘም።

4) በኢትዮጵያ አሸባሪዎች እንቅስቃሴና ሽብር እንዲሁም የክርስትያኖች የመከራ ህይወት በዓለም መድረክ ያልተነገረ፤ ሚድያው በቅጡ ያልዘገበው፤ በተዘጋ ቤት ውስጥ የሚነድ አደገኛ አሳት ነው። 

በአሁኑ ሰዓትም ክርስትያኖች በአሸባሪዎች ዛቻ እየደረሰባቸውና ቀጣዩንና መጪውን ጊዜ በመፍራት ላይ ይገኛሉ። አሸባሪዎች ለበለጠ ጥፋት እየተዘጋጁ ስለሆነ ለሚመለከታቸው አካላት የሚከተለውን ጥሪ አናደርጋለን። 

1) ተጎጂዎች በሃይማኖታቸው ምክንያት በደረሰባቸው የአሸባሪዎች ጥቃት የተነሣ፣ ቤተሰባቸውን አጥተዋል። ወጥተው ወርደው ያፈሩት ሀብት ንብረት በአንድ ጀንበር ወድሞባቸው በአሁኑ ወቅት በመቃብር ቤቶች፤ በቤተ ክርስቲያን አዳራሾች እና በግለሰቦች መኖሪያ ቤቶች ተሰብስበው ይገኛሉና የኢትዮጵያ መንግስት ለሞቱት ቤተሰቦችና ሀብት ንብረታቸውን ላጡ ዜጎቹ አስፈላጊውን ካሳ በመክፈል ወደ ነበሩበት ህይወት ሙሉ በሙሉ መመለስ አስቸጋሪ ቢሆንም አንኳ ከዚህ በኋላ በሕይወት የመኖር እና ሀብት የማፍራት ሰብአዊ እና ዜግነት መብታቸውን በማስከበር፣ የደኅንነት እና የኑሮ ዋስትና በአፋጣኝ ሊያረጋግጥላቸው ይገባል፡፡

2) የሽብር ጥቃቱን ያቀዱትን፣ የፈጸሙትን ያስተባበሩትንና የተባበሩትን ኀይሎች እንዲሁም፣ የተጣለባቸውን ሓላፊነት ወደ ጎን በማለት ጥቃቱን በዝምታ የተመለከቱትን አልፈወ ተርፈው የተባበሩትን በመንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉትን ሹማምንት እና የጸጥታ አካላት የኾኑ አጥፊዎችን፣ የኢትዮጵያ መንግስት ፥ በቁጥጥር ሥር በማዋል እና በሕግ ተጠያቂ በማድረግ ፍትሕ ርትዕ እስከ መጨረሻው እንዲሰፍን ማድረግ ይኖርበታል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ፥ ይህንን ኃላፊነቱን መወጣት በተለያየ ምክንያት ካልቻለ ጉዳዩን በዓለም አቀፍ ደረጃ ወደ ሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊ በሆኑ መንገዶች በማድረስ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የኢትዮጵያ መንግስት ሹማምንት እና ሌሎች አጥፊዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ በህግ እንዲጠየቁ ለማድረግ እንገደዳለን።

3) የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎችን ከአሸባሪዎች ጥቃት የመጠበቅ ግዴታና ኃላፊነት አለበት ። ስለሆነም ይህ ረጅም ርቀት ተሂዶበት ከፍተኛ ዝግጅት ሲደረግበት የቆየ የአሸባሪዎች አስነዋሪ ተግባር እንዴት ከመንግስት ደኅንነትና ጸጥታ አካላት ክትትልና እይታ ውጭ ሊሆን እንደቻለ ወይንም እነኝህ የጸጥታ አካላት መረጃው ከነበራቸው ለምን አሸባሪዎችን ማስቆምና ዜጎችን ከጥቃቱ መከላከል እንዳልቻሉ መንግስት ምርመራ አድርጎ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድና ውጤቱንም ለህዝብ ይፋ ማድረግ ይኖርበታል። ከዚህ ጋር በተየያዘ ይህ የአክራሪ እስልምና የሽብር ጥቃት በዓለም አቀፍ የጆንሳድ ወይም የዘር ማጥፋት ህግ መሰረት አንድን ድርጊት ጆንሳይድ ለማለት ማሞላት ያለበትን ዝርዝር ጉዳዮች ሙሉበሙሉ በሚባል መልኩ ያሟላ ስለሆነ የኢትዮጵያ መንግስት የደረሰውን ጥፋት በዘር ማጥፋት ወንጀል ሊመለከተው ይገባል።

4) በኢትዮጵያ የፌዴራል መንግሥት፣ በተለይም ደግሞ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሹማምንት በኦርቶዶክሳውያን ላይ የማሸማቀቅ፣ የማሳደድ፣ ከመንግስት የስልጣን መንበር ከማግለል ተግባራት እንዲታቀቡ። በስውርም ሆነ በግልጽ የተለያዩ ጫና በመፍጠር የመንግስት ስልጣንን ለማግኘት ወይም ያላቸውን ለማቆየት ኦርቶዶክሳውያን እምነታቸውን እንዲቀይሩ ለማድረግ የሚደረገው አስነዋሪ ተግባር በገለልተኛ አካላት እንዲጣራና የእርምት እርምጃ እንዲወሰድበት ይገባል። በአሁኑ ወቅት ያለውን የከፍተኛ ሹማምንት ስብጥርና የኦርቶዶክሳውያንን ውክልና መመልከት እየተደረገ ለቆየው ኦርቶዶክሳውያንን የማግለል አካሄድ አንድ ማስረጃ ነው። 

በፖሊተካ ጫና የተነሳ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውስጥ ተፈጥሮ የነበረው የአስተዳደር ልዩነት ተወግዶ አንድነቷን ጠብቃ ለልጆቿና ለሀገር የሚገባውን አገልግሎት እንድታበረክት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ያደረጉትን አስተዋጽዖ እኛ የቤተ ክርስቲያን ልጆች የማንረሳው በጎ ተግባር ነው። ነገር ግን ይህን የጠቅላይ ሚኒስትሩን በጎ ተግባር በተጻረረ መልኩ የቤተ ክርስቲያኗ አንድነት ተጠብቆ የሚገባውን አገልግሎት እንዳትሰጥ፤ አሁን የምናቀርበውን አይነት የፍትህ ጥያቄ እንዳታቀርብና መንግስትን ስለፍትህ እንዳትሞግት ይልቁንም የቤተ ክርስቲያኗ አንድነት እንዲጠፋና እንድትሸማቀቅ ከተቻለም ሙሉ በሙሉ እንድትዳከም በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሚገኙ አንዳንድ ሹማምንት ጠርዝ የለቀቀ የብሔር ፖለቲካ አራማጆች ጋር በግልጽና በስውር በመቀናጀት ቤተ ክርስትያኗ የማታውቀው ነገር ግን በራሷ በቤተ ክርስትያኗ ስም ሕገ ወጥ ክልላዊ መዋቅር ያቋቁማሉ። የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን የሆኑ ግለሰብ የቤተ ክርስቲያኗን መዋቅር የሚፈታተኑ እንቅስቃሴዎችን መምራታቸውና የቤተ ክርስትያኗን ክብር የሚያጎድፉ መግለጫዎችን በሚዲያዎቻቸው ላይ ጭምር ማሰራጨታቸውም አሁን ለተከሰቱት ችግሮች ቁልፍ ምክንያትና የማብረታቻ ግበዓት ሊሆን እንደሚችል ይታሰባል። እነዚህ አካላት አሁንም ድረስ ቤተ ክርስትያኗን ያሸማቅቃሉ፤ ያስፈራራሉ። የቤተ ክርስቲያኒቱ አሠራር ከሚፈቅደው ውጪ በየወረዳው ጽ/ቤቶችን ያቋቁማሉ፤ አህጉረ ስብከት የመደቧቸውን ኃላፊዎች በመሻርና በኃይል በማባረር የራሳቸውን ቡድን ይሾማሉ፡፡ የመንግሥት ሹማምንትም እነዚህን ሕገ ወጥ አካሄዶች ከማስቆም፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ከፍተኛ የሥልጣን ባለቤት ቅዱስ ሲኖዶስንም ከመስማት ይልቅ ይህን ድርጅት በመያዣነት በመያዝ ቤተ ክርስትያኗን በፈለጉት መልክ ለማሽከርከር ይሞክራሉ። እናም ይህን አስነዋሪ ተግባር የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥት፣ ባስቸኳይ እንዲያስቆም ጥሪ አናቀርባለን። 

5) የኢትዮጵያ ኃይማኖቶች ተቋማት ጉባኤ በሃይማኖታቸው ምክንያት ብቻ ሰዎች ሲገደሉ ሀብት ንብረታቸው ሲወድምባቸው የአምልኮት ቦታዎች ሲቃጠሉና ሲደፈሩ “የእውነት አፈላላጊ” ኮሚቴዎችን አቋቁሞ ትክክለኝ መረጃዎችን ለህዝብ ማቅረብ ይጠበቅበታል.። ስለሆነም ከላይ የተጠቀሱትን የአሸባሪዎች ጥቃትን በተመለከተ በግልጽ ሊያወግዝና መግለጫ ሊያወጣ ይገባል። ይህ የአሸባሪዎች ጥቃት ሆነ እነ አልሸባብ አልቃይዳና ሌሎች ተመሳሳይ አሸባሪዎች የሚያደርጉት ጥቃት እውነተኛ ሙስሊሞችንና እስልምናን አይወክልም። የእነዚህ ነውረኛ አሸባሪዎች ጥፋት አሁን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለይ ይበርታ እንጅ ሁላችንም በአንድነት ካላስቆምነው ሁሉንም የእምነት ተቋማት ማዳረሱ በፍጹም አይቀርም። ስለሆነም የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት በእምነት ተቋማት መካከል ውይይቶች ከታች ከህብረተሰቡ ጀምሮ እየተደረገ ለዘመናት በመተሳሰብ በፍቅር የኖርንበት እሴት እንዲጠበቅና አሸባሪዎችና ነውረኞች በህዝቡ ዘንድ አንዳይደበቁ የበኩሉን ኃላፊነት መወጣት ይኖርበታል።

6) በዚሁ አጋጣሚ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጀምሮ በየደረጃው ያሉ የቤተ ክርስቲያናችን መዋቅራት የቤተ ክርስቲያኒቱን ሐዋርያዊ ተልእኮ ለማሳካት፣ አስተዳደራዊ ሥራዎችን ለማዘመንና ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር በመሆን የምእመናንን ደኅንነት ለመጠበቅ የሚያደርጓቸውን ጥረቶች ለመደገፍ ምንጊዜም ዝግጁና ቁርጠኛ መሆናችንን ለመጠቆም እንወዳለን፡፡ 

እግዚአብሔር አምላክ ለሞቱት መንግስተ ሰማያትን፣ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን፣ ጉድትና ንብረት ለወደመባቸው ብርታትና ጥንካሬን ይስጥልን። 


እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና መላው ዓለምን ይባርክ። ሕዝቡንም በቸርነት ይጠብቅልን። 

ዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንና ማህበራት አንድነት ጉባኤ 

ጳጉሜ 12012 

ኢሜል፡ office@eotcadvocacy.org 


Tuesday, September 8, 2020

እነኝህ ሶስቱ እጅግ ወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ፈጣን ውሳኔ፣አረዳድ እና ዕይታ ይሻሉ።

ጉዳያችን ማሳሰቢያ!
የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ከስሜት በፀዳ ነገር ግን የቆረጠ እና የጠራ መስመር እንዲይዝ ማድረግ ተገቢ ነው።በመሆኑም በቂ መረጃዎችን ማድረስ እና ጉዳዮች መያዝ ያለባቸውን መንገድ መጠቆም አስፈላጊ ነው።

ፈጣን ውሰኔ፣አረዳድ እና ዕይታ የሚሹት ጉዳዮች 
 
1) ውጪ ጉዳይ ያሉ የፅንፈኞቹ መረብ (ውሳኔ የሚፈልግ)
2) የሕወሃትን ምርጫ ለማየት ሄዱ ስለተባሉ ጋዜጠኞች፣እና የውጭ ሀገር ዜጎች በተመለከተ (ውሳኔ የሚፈልግ) 
3) ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ (ዕይታ እና አረዳድ የሚፈልግ )
=======================
 1) ውጪ ጉዳይ ያሉ የፅንፈኞቹ መረብ (ውሳኔ የሚፈልግ)
==========================
ከለውጡ ሂደት ጀምሮ በኢትዮጵያ ያሉ መስርያቤቶች የአሰራር እና የመዋቅር ለውጥ እያደረጉ እንደሆነ ተነግሯል።አንዳንዶቹ መስርያቤቶች ጋር ጥሩ እየሄደ ነው ሲባል አንዳንዶቹ ጋር የሚቀረው ሂደት እንዳለው ይነገራል።ለውጥ የሚለው አካሄድን በመጠቀም አብረው ተሳፍረው ከሚያበላሹት ውስጥ ዋነኞቹ የፅንፍ ኃይሎች ናቸው።የፅንፍ ኃይሎች እንደ አሜባ እንዲወሯቸው ከተደረጉት የመንግስት መስርያቤቶች ውስጥ በተለይ ከአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ወደ ውጭ ጉዳይ ከመምጣታቸው በፊት ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ ያሉ ክፍሎች እና በውጭ ሀገር ያሉ ኤምባሲዎች ናቸው።

በእነኝህ የስራ ቦታዎች ውስጥ ኢትዮጵያን እንደሀገር የሚጠሉ ሰዎች የተሰገሰጉባቸው የስራ መደቦች እና ኤምባሲዎች መብዛታቸውን የዲያስፖራው ማኅበርሰብም ሆነ ተግባራቸው በግልጥ እያሳየ ነው።ይህ ጉዳይ አደገኛ ጉዳይ ነው።የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መስርያ ቤትም ሆነ ኤምባሲዎቹ የሀገር ስስ ከሆኑ አካሎች ውስጥ የሚመደብ እና ከፍተኛ የሰው ኃይል ብቃት፣ሃገርን መውደድ እና ከምንም ዓይነት የሙስና አሰራር የፀዳ ስብዕና ይጠይቃል።የኤምባሲ ሠራተኛም ሆነ አምባሳደር ኤምባሲው ማለት የሀገሩ ምድር በመሆኗ የሚመጣውን ማናቸውም ጉዳይ እስከሞት ተጋፍጦ የሀገሩን ክብር የማስከበር የሞራል ልዕልና ሊኖረው ይገባል።የአሜሪካ ኤምባሲ በኢራን ተማሪዎች በታገተ ጊዜ የአሜሪካ ዲፕሎማቶች ያሳዩት የአሜሪካዊ ሃገራዊ ፍቅር እስካሁን ድረስ ይጠቀሳል።

በኢትዮጵያ ላለፉት ሰላሳ ዓመታት የሚደነቁ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞችም ሆኑ አምባሳደሮች ጥቂት እንዲሆኑ ያደረገው የካድሬ አመላመል እና ጎሳን መሰረት ያደረገ አመዳደብ እና ዕድገት መኖሩ ነው።አሁን ደግሞ ሁኔታው ወደ አደገኛ መስመር እየሄደ ፅንፈኛ የኦነግ ሸኔ አቀንቃኞች እና አድናቂዎች የሚጠሏትን ኢትዮጵያን የሚወክሉ መስለው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥም ሆነ በቅን የሚያገለግሉ ኢትዮጵያዊነታቸው የሚያከብሩትን ሲያሸማቅቁ እና ተገቢ ስራቸውን እንዳይሰሩ ሲያደርጉ እየታዩ ነው።ስለሆነም  ፀረ-ኢትዮጵያ የሆነው የፅንፈኞች መረብ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከኤምባሲዎች በሙሉ መበጣጠስ አለበት።

2) የህወሓትን ምርጫ ለማየት ሄዱ ስለተባሉ ጋዜጠኞች፣እና የውጭ ሀገር ዜጎች በተመለከተ (ውሳኔ የሚፈልግ) 

የህወሓትን ምርጫ ለመታዘብ ወደ መቀሌ ሊሄዱ ሲሉ ከቦሌ አየር መንገድ ትናንት የውጭ ሀገር ጋዜጠኞች እና የዓለም አቀፍ ድርጅት ሰራተኞች መያዛቸው ተሰምቷል።ይህንን ያደረጉ የውጭ ሀገር ጋዜጠኞች የሀገሪቱ ሕግ አውጪ አካል የፌድሬሽን ምክር ቤት ቅዳሜ ነሐሴ 30/2012 ዓም በህወሓት የሚደረገው ምርጫ ህገ ወጥ ምርጫ መሆኑን ለመጨረሻ ጊዜ ያሳለፈው ውሳኔ እያወቁ ወደ መቀሌ ለመሄድ መሞከራቸው ከታወቀ ወንጀል ብቻ ሳይሆን የሚሰሩበትን የዜና አገልግሎትን ብቻ ሳይሆን የሚሰሩበትን ድርጅት ሕጋዊ አሰራር ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው።ሙከራው በአንድ ሀገር የውስጥ ጉዳይ የመግባት ጉዳይም ነው።ስለሆነም ይህ ጉዳይ ተጣርቶ ከፈቃድ መሰረዝ እስከ ወደ ሀገር እንዳይገቡ የሚያግድ ውሳኔ ከመንግስት ይጠበቃል።የድርጊቱ ሂደት በውስጥ ጉዳይ የመግባት እና የሀገሪቱን ሕግ አለማክበር የሚታይበት ግልፅ አካሄድ ነው።

3) ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ (ዕይታ እና አረዳድ የሚፈልግ )

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይን በተመለከተ በማኅበራዊ ሚድያ አልፎ አልፎ የሚታዩ ነቀፋዎች እየተመለከትን ነው።በእርግጥ ከእዚህ በፊትም ጨዋነት ከጎደለው እስከ በሆነ ባልሆነው የጥላቻ ፅሁፎች በየማኅበራዊ ሚድያው የሚለጥፉ አሉ።አንድ ሰው የተሰማውን ጨዋነት በተላበሰ መንገድ ሃሳቡን መግለጥ መብቱ ነው።ነገር ግን ኢትዮጵያን እንወዳለን ለምንለው ነው ይህንን መልዕክት ማስተላለፍ የምፈልገው።ኢትዮጵያን የሚጠሉ የአክራሪ ፅንፍ ኃይሎች እና የጎሳ ፖለቲካ ለማራመድ የሚፈልጉ  የሌላው ገመድ ጎታቾች ጧት ማታ ጠቅላይ  ዓቢይን ሲያጥላሉ ቢውሉ ኢትዮጵያን ማለታቸው  እንዳልተመቻቸው መረዳት እንዴት ያቅተናል?

 ሁሉም ሊያውቀው የሚገባው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይን የምናደንቀው ኢትዮጵያን በማለታቸው ነው።የፓርላማ ንግግራቸውን ከአርባ ጊዜ በላይ ኢትዮጵያ! በሚል ንግግር ካጀቡበት ቀን ጀምሮ እስከአሁን ድረስ ያሳዩትን የኢትዮጵያዊነት ሂደት ማበረታታት ኢትዮጵያን ከምንል ሁሉ ይጠበቃል።የጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አስተዳደር ያልተቆጣጠራቸው የመንግስት የስራ ቦታዎች አሉ ወይ? አንዱን ሲነካው ሌላው ይተረተራል በሚል ያቆዩት ጉዳይ አለ ወይ? አጠቃላይ ማዕቀፉ እና አካሄዳቸው ኢትዮጵያዊ ነው ወይ? ብሎ ነገሮችን በሚገባ መመርመር ኢትዮጵያን ከሚለው ሁሉ ይጠበቃል። 

ሌላው የሕዝብ ትኩረት ለመሳብም ሆነ አዲስ የትሕትና መንገድ ለማሳየት እራሳቸውን ከሊስትሮ እስከ ትራፊክ እየሆኑ የሚያሳዩትን አንዳንዶች ''አታለለን''ወዘተ እያሉ ከፅንፍ ኃይሎች ጋር አብረው በማኅበራዊ ሚድያ ላይ ሲፅፉ እያየን ነው።ቢያንስ ይህንን የትህትና መስመራቸውን ማድነቅ ኢትዮጵያዊ መስመራቸውን ማገዝ ነገር ግን የሕግ፣የኢትዮጵያን ማኅበራዊ መሰረት እና ታሪካዊ ዳራ ባላናገ መልኩ ሀገሪቱ እንድትሄድ አቅጣጫ ማስቀመጥ እንጂ ኢትዮጵያን ያለ ሰው ከማበረታታት ይልቅ የነቀፋ ሃሳብ መሰንዘር ትክክል አይደለም።

ዛሬም ሆነ ነገ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይን የምናበረታታቸው የበለጠ ለኢትዮጵያ እንዲሰሩ ነው እንጂ የስሜታዊነት ጉዳይ አይደለም።በእርግጥ ከፅንፍ እና ከጎሳ ስሜታቸው አንፃር ጧት ማታ የሚነቅፉት የቆሙበት መሰመር ስለሆነ እና ዓቢይ የእነርሱን ፀረ-ኢትዮጵያዊ መንገድ እንዳለተቀበላቸው ስላወቁ መሆኑን ማወቁ ቀላል ነው።ባጭሩ ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያን ያለ ማንንም ሰው አብረነው ልንቆም ይገባል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ደግሞ ከኢትዮጵያዊነት መስመር ያልወጡ ኢትዮጵያን በእዚሁ መስመር ለማስገባት እየጣሩ ያሉ ሰው ናቸው።
 
መልካም አዲስ ዓመት!

Thursday, September 3, 2020

የነሐሴ 28/2012 ዓም ጆሮ  ጠገብ ያልሆኑ ዜናዎች በአስር ደቂቃዎች ውስጥ ብቻ

የነሐሴ 28/2012 ዓም የጉዳያችን ጆሮ ጠገብ ያልሆኑ ዜናዎች በአስር ደቂቃዎች ውስጥ ብቻ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ሩስያ፣ የማር ገበያ፣የሉተር የተሐድሶ ኢላማ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በሚሉ ርዕሶች ቀርበዋል

Wednesday, September 2, 2020

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የሚሰጡትን እርዳታ የያዙበት ምሥጢር

ጉዳያችን 9ኛ ዓመቷ በያዝነው ነሐሴ/2012 ዓም ሞልቷታል።ከዛሬ ጀምሮ በዩቱብ ጠቃሚ የሆኑ ኢትዮጵያን የሚመለከቱ ጉዳዮች፣ማኅበራዊ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ አጫጭር የቪድዮ መልዕክቶች ይቀርባሉ።
የዛሬው ርዕስ አሜሪካ እና የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የሚሰጡትን እርዳታ የያዙበት ምሥጢር  የሚል ነው። ይከታተሉ፣ዩቱቡን ሰብስክራይብ ያድርጉ ለሌሎች ያካፍሉ።

ቪድዮውን ለማየት ሊንኩን ይክፈቱ 

Saturday, August 29, 2020

የትምህርት ሚኒስቴር ላለፉት 27 ዓመታት በተሳሳተ ሥርዓተ ትምህርት ኢትዮጵያን እንደከፋፈለ ዳግም እንዲከፋፍል ሊፈቀድለት አይገባም።

የትምህርት ሚኒስቴር ዋና መስርያ ቤት በቀዳማዊ አፄ ሃይለስላሴ ዘመን (1950ዎቹ መጨረሻ) አዲስ አበባ ልዩ ስሙ አራት ኪሎ ግንባታ ላይ ሳለ 

ኢትዮጵያ የኅብረብሔር ሀገር ነች።በዘመናት ሂደት ህዝቧ ከሰሜን ደቡብ፣ከምዕራብ እስከ ምስራቅ በንግድ፣በጦርነት፣በስደት፣በተፈጥሮ አደጋ እና በሌሎች ምክንያቶችም እየተንቀሳቀሱ እርስ በርስ ተዛምደዋል፣ተዋልደዋል።ይህ በታሪካችን የነበረ ዕውነታ ነው።በምሳሌነት የዝዋይ ደሴት ነዋሪዎችን ብንመለከት ከላይ የተጠቀሰው የህዝብ የአኗኗር ታሪክ አንዱ ማሳያ ነው።በዘጠነኛው ክ/ዘመን የተነሳችው እና አያሌ አብያተ ክርስቲያናትን ያቃጠለችው ዮዲት ጉዲትን ሸሽተው ታቦተ ፅዮንን ይዘው የተሰደዱት ካህናት እና አብሯቸው ከተለያየ የኢትዮጵያ ክፍል የመጣው ሕዝብ በዝዋይ ደሴት ሰፍሮ ነበር።ታቦተ ፅዮን ስትመለስም ከመላው ኢትዮጵያ የመጣው ሕዝብ ግማሹ ስመለስ ሌላው እስካሁን ዝዋይ ደሴት ቀርቷል።በእዚህም መሰረት በዝዋይ ደሴት ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል የተውጣጡ ቃላት በአንድነት የፈጠሩት ዘዬ የተሰኘ መግባብያ ፈጥረው ይኖራሉ።በመሆኑም የዘዬ ሰዎች ዛሬም ሲናገሩ ከጉራግኛ፣ከአማርኛ፣ከትግርኛ እና ከሌሎችም የተቀየጡ ቃላት መስማት የተለመደ ነው።

ኢትዮጵያ እንዲህ ነች።እርስ በርሷ የተጋመደች፣የተዛመደች እና የተጣመረች ነች።ይህ ሁኔታ የአንዱ ስልጣኔ የተለየ፣የሌላው ዝቅ ያለ ብሎ መውሰድ የሚቻልበት ሁኔታ የለም።በእያንዳንዱ የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ያለፈው የህዝቡ ታሪክ የራሱ የሆነ በዘመናችን የሚጠራው የዲሞክራሲም እንበለው የመንግስት ስርዓት ወይንም የአካባቢ አስተዳደር ዘይቤ አለው።ለሺህ ዓመታት የነበረው የነገሥታቱ የንግስና ስርዓትም ሆነ የኦሮሞ ገዳ ስርዓት፣ፍትሐ ነገሥትም ሆነ ሕገ መንግስታዊ ስርዓት ሁሉም በኢትዮጵያ ምድር ያለፉ ናቸው እና በሚገባ መጠናት፣በቂ ምርምር ማድረግ እና መመርመር ይፈልጋሉ።

ይህንን የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ በግብታዊነት የተወሰነ ውሳኔ በሚመስል መልክ የትምህርት ሚኒስቴር የገዳ ስርዓት በአዲስ አበባ እና በኦሮምያ ክልል ከ2013 ዓም የትምህርት ዘመን ጀምሮ እንዲሰጥ መወሰኑን ነሐሴ 23/2012 ዓም የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በምሽት ዜና እወጃው ላይ  ማስታወቁን ለማወቅ ተችሏል። 

ይህ ውሳኔ ግን በራሱ ብዙ ጥያቄዎችን ያስነሳል።በመጀመርያ ደረጃ የገዳ ስርዓት የኢትዮጵያ ተማሪዎች መማር የለባቸውም የሚል ተቃውሞ በደረቁ ያነሳ የለም።በእዚህ ፅሁፍም ላይ ይህ አይደለም የሚንፀባረቀው። የትምህርት ሚኒስቴር የወሰነበት ሂደት እና አፈፃፀሙ ግን በራሱ ብዙ ጥያቄ ያጭራል።የትምህርት ሚኒስቴር በመላ ሀገሪቱ ውስጥ የሚሰጡ ትምህርቶችን ወጥነት ባለው መልክ እንዲሰጡ የማድረግ ግዴታ አለበት።በአንድ ሀገር ውስጥ ሁለት እና ሶስት አይነት ትምህርት እየሰጠ ትውልድ የሚነጣጥል ተግባር መስራት በራሱ ወንጀል ነው።እዚህ ላይ አንድ መርሳት የሌለብን ጉዳይ የገዳ ስርዓት ታሪክ በኢትዮጵያ ሁሉም ትምህርት ቤቶች እና ዩንቨርስቲዎች በዘመነ ደርግም ሆነ በቀዳማዊ አፄ ሃይለስላሴ ዘመን  በታሪክ ትምህርት ውስጥ  ራሱን በቻለ ምዕራፍ ተሰጥቶት ተማሪዎች ይማሩት ነበር።ይህ አሁን ያልነበረ የሚመስላቸው ካሉ ተሳስተዋል።ኢህአዴግ ስለ ገዳ ማውራት የጀመረ የሚመስላቸው አይጠፉም።ደርግ በኢትዮያ የብሔር ብሔረሰቦች ኢንስቲትዩት ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ አስጠንቶታል። ሆኖም ግን ደርግም ሆነ በአፄ ኃይለ ስላሴ ዘመን በታሪክ ትምህርት ውስጥ ገብቶ ተማሪዎች እንዲማሩት የተደረገው ሀገር በሚከፋፍል አንዱ የእናት ልጅ ሌላው እንጀራ ልጅ በሚመስል እና በሚነጣጥል መልኩ አልነበረም። በወቅቱ ትምህርቱ ትምህርቱ የሚሰጠው  የኢትዮጵያ ታሪክ ትምህርት የሚማሩ ኢትዮጵያውያን ከአክሱም እስከ ሞያሌ፣ከጅጅጋ እስከ ጎንደር በታሪክ ትምህርት ውስጥ የሌላውን የኢትዮጵያ ታሪክ ሲማሩ ራሱን በቻለ ምዕራፍ የገዳ ስርዓትን  በዝርዝር በሚያስረዳ መልኩ ከሌላው የኢትዮጵያ ታሪክ ጋር በአንድነት ነበር። 

የሰሞኑ የትምህርት ሚኒስቴር በተናጥል አስተምራለሁ ያለው ትምህርት ግን የገዳ ስርዓት የሚባል ትምህርት ለብቻው ለአዲስ አበባ እና ለኦሮምያ ክልል እሰጣለሁ የሚል ነው። እዚህ ላይ ጥያቄው የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር እንዲህ እየነጠለ የእየብሄረሰቡን ትምህርት በትምህርት ካሪኩለም ውስጥ በማስገባት እና ለየብቻው እየሰጠ ይዘልቀዋል? ወይንስ ለገዳ ስርዓት ብቻ ነው የተፈቀደው? ለምንስ ነው የኢትዮጵያ የተለያዩ የዲሞክራሲ ባህሎች በአንድነት ተሰብስበው በእዚሁ ስር የገዳ ስርዓትም ገብቶ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንዲማሩ የማይደረገው? ኢትዮጵያ ለዘመናት የተዳደረችበት ለዓለም አቀፍ ሕግም ያበረከተችው ፍትሐ ነገስት የሚባል ስርዓት እንዳላት የትምህርት ሚኒስቴር አልሰማም? ከገዳ ስርዓት ጋር ለምንድነው ኢትዮጵያውያን የማይማሩት? መማር አይጎዳም።ተማሪዎች ዛሬ የሀገራቸውን የነበረ እና የዳበረ የማሕበራዊ እሴቶች ታሪክ ማወቃቸው ነገ የተሻለውን አውጣጥተው ዘመኑን በዋጀ መልኩ ለሀገራቸው አዲስ ሃሳብ እንዲያፈልቁ ይረዳል።

የትምህርት ሚኒስቴር ዋና መስርያ ቤት አዲስ አበባ (አራት ኪሎ) 

በመሆኑም ትምህርት ሚኒስቴር የገዳ ትምህርትን ለብቻው ለአንዱ ክልል እሰጣለሁ ከማለት ይልቅ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በአንድ ማዕድ የገዳ ስርዓትን ጨምሮ ሌሎች የኢትዮጵያ እሴቶች ለምሳሌ ፍትሐ ነገስት፣የኮንሶ ባህላዊ እሴቶች፣የአክሱም ጥንታዊ ስርዓቶች፣የሐረር እና የጅማ የንግድ ባህሎች ሁሉ ያካተተ ስርዓተ ትምህርት ቀርፆ ሁሉንም ኢትዮጵያን እንዲያስተምር ሕዝብ ግፊት ሊያደርግበት ይገባል። የትምህርት ሚኒስቴር ላለፉት 27 ዓመታት በተሳሳተ እና በከፋፋይ የትምህርት ፖሊሲ ኢትዮጵያን እንደከፋፈለ ዳግም እንዲከፋፍል ሊፈቀድለት አይገባም።የትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠውን ርዕይ፣ተልዕኮ እና እሴቶች ብሎ ላስቀመጣቸው ገዢ ሃሳቦች ተገዢ እንዲሆን ደግመን ልንነግረው ይገባል።

ከእዚህ በታች የትምህርት ሚኒስቴር ርዕይ፣ተልዕኮ እና እሴቶችን እንመልከት እና አሁን እየነጠለ እና እየከፋፈለ ለመስጠት የምሞክረው ትምህርት ምን ያህል ከራሱ ጋር እንደሚጣላ መመልከቱ በቂ ነው። ፍትሃዊ የትምህርት አሰጣጥ ማለት የሁሉንም ያቀፈ ትምህርት ለሁሉም ኢትዮጵያዊ መስጠት እንጂ እየነጠሉ ብሔሮች የራሳቸውን ታሪክ ብቻ እንዲያጠኑ መወሰን አይደለም።ትምህርት ድንበር የለውም።በትምህርት የአሜሪካንን ታሪክ እያጠናን የአክሱምን የመንግስት ስሪት ወይንም የጎንደርን የቤተ መንግስት ስርዓት ለጅማ እንዳያውቅ ማድረግ ወይንም የአባ ጅፋርን የቤተ መንግስት ስርዓት እና የገዳ ስርዓትን ለወሎ እና ለጎጃም ተማሪ እንዳያውቅ ማድረግ በርሱ የትምህርትን መሰረታዊ መርህ የሚፃረር ተግባር ነው።

የትምህርት ሚኒስቴር  የተቀመጠለት ርዕይ

ብቁ ዜጋ የሚያፈራ፣ ጥራትና ፍትሃዊነት ያረጋገጠ የትምህርትና ስልጠና ስርአት በቀጣይነት መገንባት ነው!

የትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠው ተልእኮ

የትምህርት ዘርፉን የማስፈጸም አቅም በመገንባት፣ የብቃት መለኪያዎችን በማውጣትና በማስጠበቅ፣ ደረጃውን የጠበቀ ትምህርትን በማስፋፋት፣ እንዲሁም ተግባሮቻችንን በህዝብ ግንኙነት ስራ በማገዝ ጥራት ያለው ውጤታማና ፍትሃዊ የትምህርትና ስልጠና ስርአትን ማረጋገጥ ነው፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር እሴቶች

- ውጤታማነት
- ጥራት
- ፍትሃዊነት
 -አሳታፊነት
 - አርአያነት
 -የአላማ ጽናት
 - ልቆ መገኝት

================////===========================

Thursday, August 27, 2020

''እንዴት አንድ ሰው ፈጣሪዬ ብሎ በሚጠራው ፈጣሪው የተፈጠረ ብሎ የሚያምነውን ሰው በዕምነት ስላልመሰለው ብቻ በፈጣሪው ሥም ያርዳል?'' - አቶ ዓለማየሁ ብርሃኑ ከባሌ እና ከአርሲ ጉብኝታቸው ባለፈው ሳምንት እንደተመለሱ ለጉዳያችን የተሰማቸውን ፅፈዋል።ሙሉውን ያንብቡ።

አቶ ዓለማየሁ ብርሃኑ

እኔ ባደግሁበት አካባቢ በልጅነት አዕምሮአችን እየሰማን ያደግነው አባቶቻችን ነገ ለሚያደርጉት ነገር ሲቀጣጠሩ በጠዋት ለመገናኘት የቀጠሮ ሠዓት የሚያደርጉት "ጠዋት አላህ ወአክበር ሲል" እንነሳ ይባባሉ ነበር፡፡ ከዚህም ባሻገር እንደዛሬው ሰዓት ባልነበረበት በዚያ ዘመን ጠዋት ክርስቲያን አባቶቻችን ወደ ቤተ ክርስቲናቸው ለመሄድም የመስጊዱን አዛን ቀስቅሶ እንደሚያበረታታ 'በጎ ቀስቃሽ' ይጠቀሙበት ነበር።ምክንያቱም አንዱ የአንዱን እምነት አክብሮ የሚኖርበት የፍቅር ዘመን ስለነበር፡፡
ታዲያ! በዚህና በሌሎችም ምክንያቶች ከእስልምና እምነት ተከታይ አብሮ አደግ ጓደኞቻችን ትርጓሜውን ስንጠይቅ 'ኣላህ ታላቅ ነው' ማለት እንደሆነ ይነግሩን ነበር፡፡ ይህ ቃል እንግዲህ ለጨዋዎቹ የእስልምና አማኞች ክብር ያለው ቃል እንደሆነ ከትርጓሜው መረዳት ይቻላል፤ ለክርስቲያኑም ከላይ እንደጠቀስኩት ይህ ቃል በጎ ቃል ሆኖ ኖሯል፡፡ዛሬም ኢትዮጵያውያን ተከባብረው በሚኖሩበት ቦታ ሁሉ ከመስጊድም ሆነ ከአብያተ ክርስቲያናት የሚወጡ የማንቂያ ድምፆች እንደተከበሩ አሉ ይህ ቃል ግን ዛሬ በምሥራቅ ኦሮሚያ ላሉ ክርስቲያኖች የሰቀቀን ቃል ሆኗል። ክርስቲያኖችን በአደባባይ የሚገድሉ በእስልምና ስም የሚንቀሳቀሱ እና የንፁሃንን ደም የሚያፈሱ ይህንኑ ''አላህ ወአክበር'' የሚሉትን ቃላት እየተጠቀሙ ነው።
በሰኔ 23 እና 24/2012 ዓም በአምስቱ የኦሮሚያ ዞኖች በአካባቢው በሚገኙ የዕምነቱ ተከታይ ነን በሚሉ የመንግስት ባለሥልጣናትና ፖሊሶች ድጋፍ በተደረገው ክርስቲያኖችን የማጥፋት ዘመቻ ላይ ይህ ቃል እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ በሰፊው በሥራ ላይ ውሏል። ግን ለበጎ ተግባር ሳይሆን አብሮ የኖረን ህዝብ ንብረት ለማውደምና ለመስረቅ በተለይም ደግሞ ዕምነት የሌለው ሰው እንኳን ያደርገዋል ተብሎ የማይገመት አሰቃቂ ግድያን በወንድም ላይ ለመፈፀም ነው፡፡ እኔም በባሌና አርሲ የደረሰውን ጉዳት ለማየት ባለፈው ሳምንት ከሄደው ቡድን ጋር ተጉዤ ነበርና ከተጎጂዎቹ በአካል ተገኝተን በሰማነው መሠረት ሰው በህይወቱ እያለ እጅ ሲቆርጡ ዓይን ሲያወጡ፣ አጋርፋ ላይ የአእምሮ ዝግመት ያለበትን ወጣት ጭንቅላቱን ቀጥቅጠው በማጅራቱ ሲያርዱትና መሰል አስነዋሪ ተግባራትን ሲፈፅሙ ሁሉ "አላህ ወአክበር" እያሉ እንደነበር ከጉዳቱ የተረፉት ሃዘን በተሞላ አንደበት ተርከውልናል ፡፡
ይህ ነገር አዲስ አይደለም ሠዎች በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ከክርስቲያኑ ሃጫሉ ሞት ጋር ያያይዙታል። ነገር ግን ይኼ ታቅዶ የተሰራ ዛሬ ብቻ ሳይሆን ከአስር ዓመት በፊትም በጅማ ዙርያ በሻሻ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያንም በተመሳሳይ እልቂት ሲፈፀም ይሄው ቃል እየተጠራ ነበር።በቅርቡ በጥቅምት/2012 ዓም ተመሳሳይ ድርጊት በተፈፀመበት እና ከ80 በላይ ንፁሃን ሕይወት በጠፋበት እልቂት ወቅትም ይሄው ቃላት የተደጋገመ መፈክር ሆኗል፡፡ የድሮ አልቃሽ አባቷ ሞቶባት በዓመቱ ባሏ ለሞተባት ሴት ስታላቅስ "ያምናን ቀን አማሁት ላፌ ለከት የለው፤ መጣ የዘንድሮው እጅ እግር የሌለው፡፡" አለች አሉ፡፡ እኛም ታዲያ 'ከካቻምናም አምና ከአምናውም ዘንድሮ፤ እያስጠላኝ መጣ የዚች ዓለም ኑሮ' እንድንል በክርስቲያንነታችን እየተገፋን ነው፡፡ እንዴት አንድ ሰው ፈጣሪዬ ብሎ በሚጠራው ፈጣሪው የተፈጠረ ብሎ የሚያምነውን ሰው በዕምነት ስላልመሰለው ብቻ በፈጣሪው ሥም ያርዳል? እንዲህ ዓይነት የዕምነት አስተምህሮ አለ ብሎ መቀበል በዕውነቱ ይከብዳል። በተለይ ጠላትህን ውደድ በሚል አስተምህሮ ለተገራው ከአዕምሮ በላይ ነው፤ ግን ደግሞ እየሆነ ያለው ዕውነታ ይህ ነው፡፡
እዚህ ላይ ታዲያ የኔ ጥያቄ በተለይ ለዕውነተኞቹ የእስልምና አማኞች በርዕሱ ላይ እንደጠቀስኩት 'አላሁ አክበር' ትርጉሙ ተለወጠ እንዴ? የሚል ነው፡፡ እኔ ይወክሏችኋል ብዬ ባላምንም እናንተም በምታመልኩበት አምላካችሁ ሥም ነውና እየተገደልን ያለነው ለምን ዝም አላችሁ? አምናችሁበት በውስጣችሁ ደስ እያላችሁ? ወይንስ ከናንተው ወገን ያለሃፍረት 'እዚህም ቤት እሳት አለ' በሚል ዓይነት ማስፈራሪያ የምናስጮኸው አናጣም ብለው ሊያስፈራሩን የሚሹት ሠዎች እናንተም ላይ የሚያሳድሩት ስውር ደባ ይኖራቸው ይሆን? በእርግጥ ኃይማኖትን የተረዱ ጥቂት ዕውነተኛ ኡስታዞችና ህሊናቸውን ለዕውነት አስገዝተው ስለዕውነት ድርጊቱን በማውገዝ በፊት ለፊት በግላቸው ያወገዙትን ዋጋ ማሳጣት አልፈልግም፡፡ በሌላም በኩል በሱማሌ ክልል ደርሦ በነበረው ጥቃት በይፋ ድርጊቱን በማውገዝና ይቅርታ በመጠየቅ በጋራ ለማቋቋም ጥረት ያደረጉትን የክልሉን ፕሬዝዳንት ሙስጠፌንና የሶማሌ ሙስሊም የሃገር ሽማግሌዎች ዓይነት ሠዎች ባሉበት ሃገር ከዚህ ትምህርት መውሰድ ሲገባ ዛሬም 'አምላክ ታላቅ ነው' እያሉ አምላክ የፈጠረውን በማረድ ለማባረር መሞከር መጨረሻው ላያምር ይችላልና ቆም ብለን ብናስብበት ጥሩ ነው፡

እንደኔ ግን እነኚህ ሠዎች ለክርስትና ብቻ ሳይሆን ሳያምኑበት የሚያምኑበት አስመስለው ዓላማቸውን ማራመጃ ላደረጉት ለእስልምናም ውሎ አድሮ አደጋነታቸው አይቀሬ ነው፡፡ ስለዚህ ሁሉም በጋራ ሊያወግዘው የሚገባ ሃይማኖት ተኮር እኩይ ተግባር ነው፡፡ ይህ ሲባል የሚያቅራቸው የመንግስት ሹማምንትም ለዕውነታው ዕውቅና ሰጥተውና ይፋ ይቅርታ ጠይቀው ለመፍትሔው አብሮ መስራት ይሻላል እንጂ የሐይማኖት አይደለምና ዕውነትን አትናገሩ ብሎ ሚዲያዎችን ለማገት መጣሩ ለማንም አይጠቅምም፡፡ ቤተክርስቲያን በተለይ ባለፉት ሁለት ዓመታት 'ለምጣዱ ሲባል…' በሚለው ሃገራዊ ብሂል መሠረት ብዙ መከራዎችን ዋጥ አድርጋ መታገሷን ታሪክ ይመዘግበዋል፡፡ አሁንም ይልቅ የደህንነት ሥጋት ያለባቸውን የዴራ ወረዳ ክርስቲኖች ቤት ንብረታቸው መውደሙ እየታወቀ ከተጠለሉበት ቤተ ክርስቲን ያለምንም ዝግጅት እንዲወጡ የሚያስገድዱ የወረዳ ሹማምንት ዕውነት ለመንግስት ጥሩ ሥም እየሰሩ ነው? ወይስ ያላለቀ ተልዕኮ ያላቸው ሠዎች ዛሬም ይኖሩ ይሆን? አሁንም የኦሮምያ ክልል ይህንን ፈትሾ ለዜጎች የደህንነት ዋስትና የመስጠት ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል፡፡
አምላክ እንደአባቶቻችን በፍቅር የምንኖርበትን ጊዜ ያምጣልን፡፡
ዓለማየሁ ብርሃኑ ነኝ

Monday, August 24, 2020

Why do the majority of Ethiopians support the visionary and talented PM Abiy Ahmed of Ethiopia?

Abiy Ahmed the winner of 2019 Nobel Peace Prize

================
In Ethiopia, extremists under the cover of Oromo ethnicity, killed over 200 people only within only three days following the famous musician Hachalu Hundessa assassinated on June 29,2020.The massive killing innocents was followed by destroying their properties and business centers. In Oromia region cities and rural areas like Shashemene,Arsi, Bale and Harar were typically targeted areas.Most of the victims were also being killed only because of their religion of christianity.The massive killing acts of innocent civilians were motivated by extremists social mediators residing in Europe (including Norway),Canada and USA. The social media motivators who need to load their non-humanity and savage ideas and acts on Ethiopian people are also accusing Abiy by demonstrations in Europe,USA and Canada streets.These are the people who opposed the legal action that the Abiy government is taking now. Their fear is that if law and regulations are approved in Ethiopia, their extreme plan will not be functional.

Contrary to extremists, the majority of Ethiopians including the Oromo region at home and abroad support all necessary actions that Abiy is taking now. Law and regulations are a key factor for any country's peace and stability.Here the paradox we should know is that Abiy himself is from Oromo ethnic.However extremists are calling themselves ‘’Oromo’’ more than the PM. The situation is a little bit 'funny'.Because even if the main objective of the extremists is to run extremism, they still attempt to use the cover of Oromo ethnicity.Ethnicity issues are not considered as a major issue to be leader in Ethiopia.However, the stand for humanity and respecting the legal framework matters a lot.

Europe and US policy makers and Governments must understand well the real cause and situation in Ethiopia.In Ethiopia, currently almost all regions including the Ethiopian-Somali region, Amhara, Gambella and Afar are so peaceful and busy doing their day to day development activities. The only problem is in extremists' temporary field, some parts of the Oromia region.

Therefore, the international community must stand with Abiy and his government. Because the horn of Africa peace and stability could be assured only through the modern and visionary leader of Abiy. It should be clear also the International community is not only expected to support Abiy's government, it is also very vital condemning extremists running hidden agenda within Oromo ethnicity.

Last but not least, we need to notice that Abiy is not only the hope of Ethiopia stability but he is also the right person to serve as a key bridge for the future political,Economic and Social relations between Africa and the rest of the world. So it is unquestionable, majority of Ethiopians will continue to support Prime minister Abiy Ahmed (Phd) administration. Yes! there are a number of challenges that his government is facing. Poverty, the past regime ethnocentric policy and corruption are the major one.These are also huge problems to other parts of the world.It is not unique only for Ethiopia. The difference is that Ethiopia is in huge transition process to tackle the problems.Now! the pre-most issue to Ethiopia and the Abiy's government is to control the extremists' move in any form both violently and spreading fake news on social media.The government is becoming successful to control illegal acts of the extremists.Therefore it is not vague why Ethiopians continue to support Abiy. They have a very good reason to do so.He is taking key measures to assure law and order in the country. It is quite clear that peace and stability are the key important issues of any government. Particularly, Ethiopia's peace and stability is the guarantee for the horn of Africa and the Middle East.

Getachew Bekele
Editor, Gudayachn


ጉዳያችን ሚድያ፣ኮሚኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት 

Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant
Gudayachn Multimedia, Kommunikasjon og Konsultent 

Saturday, August 22, 2020

በውጪ ሀገር የሚኖሩ የዝምተኞች እና የዳር ተመልካች ኢትዮጵያውያን መብዛት አገርን ዋጋ እያስከፈለ ነው።ሁኔታው የፅንፍ ኃይሎች በተሳሳተ መንገዳቸው እንዲቀጥሉ 'ዕድል' ሰጥቷቸዋል።


>> በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እውነታውን ለሚኖሩበት ሀገሮች ሚድያዎች በመግለጥ እና በመፃፍ  ከምን ጊዜውም በላይ ሊተጉ ይገባል።
>> የኢትዮጵያ ኤምባሲ ማኅበረሰብም ሆነ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ለውጪ መንግሥታት በውጪ ሀገር ሆነው የፅንፍ ፖለቲካ የሚያራምዱ ኃይሎች እኩይ ተግባር ማጋለጥ አለበት። 

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1992 እስከ 1995 ዓም የቦስንያ ጦርነት ተብሎ የሚታወቀው የመካከለኛው አውሮፓ እልቂት ከ25 ሺህ እስከ 30 ሺህ ንፁሃን ሕይወት ተቀጥፎበታል።እልቂቱ የታጀበበት አንዱ አሳዛኝ ክስተት ደግሞ ከፍተኛ የሐሰት ፕሮፓጋንዳ ቀድሞ እየተነዛ እውነቱን ለመሸፈን የተደረገው አሳዛኝ ጥረት ነው።

በኢትዮጵያ በኦሮሞ ስም የሚነግዱ የፅንፈኛ ኃይሎች በአሁኑ ጊዜ እየፈፀሙ ያለው ወንጀልም በአውሮፓ ከተፈፀመው ወንጀል ጋር ተመሳሳይ ነው።ይሄውም በውጪ የሚኖሩ በኦሮሞ ስም የፅንፍ ኃይሎች በሚያደርጉት ቅስቀሳ ሳቢያ በሀገር ውስጥ የንፁሃን መገደል ምክንያት መሆናቸውን ለመሸፈን በማኅበራዊ ሚድያ እና በሰልፍ ቀድመው በመጮህ እውነታውን ለመሸፈን መሞከር አሁን የያዙት አንዱ ስልት ነው።

የፅንፍ ኃይሉ አሁን በኦሮምያ ባለው የስልጣን ተዋረድ ውስጥም ተሸሽጎ የፅንፍ ኃይሉ በንፁሃን ላይ ያደረሰውን የግድያ እና የንብረት ማውደም ተግባር ለመሽፋፈን የተደረገው ጥረት በግልጥ ታይቷል።ይህንንም ክፍተት በመጠቀም በውጪ ያለው የፅንፍ ኃይል በኢትዮጵያ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በመሸፈን የኦሮሞ ማኅበረሰብን እንደ ማኅበረሰብ ለማጥቃት የሚደረግ ተግባር እንዳለ በማስመሰል በሰልፍ፣የተለያዩ ፅሁፎችን በውጪ ሀገር ለሚገኙ ጋዜጦች እና ድረ ገፆች በመፃፍ እና ለፓርላማ አባላት በቀጥታ ትውተር በመፃፍ ሁሉ የተሳሳተ መረጃ እንዲደርስ ለማድረግ ጥረት አድርገዋል።

ይህ በእንዲህ እያለ በውጪ የሚኖሩ በከፍተኛ የሙያ እና የአቅም ደረጃ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የዳር ተመልካች መሆናቸው እና ዝምታቸው በኦሮሞ ስም ለሚነግዱ የፅንፍ ኃይሎች በተሳሳተ መንገዳቸው እንዲቀጥሉ 'ዕድል' ሰጥቷቸዋል።በእርግጥ የፅንፍ ኃይሎችን የተሳሳተ ትርክት እና የሐሰት ዜናዎች ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለማጋለጥ ከሰላማዊ ሰልፍ እስከ የተለያዩ ጋዜጦች ላይ በመፃፍ ለኢትዮጵያ ድምፅ የሆኑ መኖራቸው ይታወቃል።ሆኖም ግን በውጭ ሀገሮች ከሚኖረው ከፍተኛ አቅም ያለው ኢትዮጵያዊ አንፃር የዝምተኞች እና ዳር ተመልካቾች መብዛት ኢትዮጵያን ዋጋ እያስከፈላት ነው።

የፅንፍ ኃይሎች በኢትዮጵያ ላለው የንፁሃን እልቂት ተጠያቂ እና ምክንያት መሆናቸውን በመሸፈን ያደረጉት መጮህ የአሜሪካን ምክር ቤት አባላትን እስከ ማሳሳት ደርሷል።በእርግጥ የአሜሪካ ምክር ቤት እውነተኛው መረጃ ሳይገባው ቀርቶ ነው ለማለት አይቻልም።የምክር ቤት አባላቱ ከ200 በላይ የሚሆኑ ንፁሃን በግፍ የተገደሉበት አንዱ መነሻ በአሜሪካ ጭምር የሚኖሩ የፅንፍ ኃይሎች ቅስቀሳ መሆኑን ያውቃሉ።ሆኖም ግን ስለ ንፁሃኑ መገደል አንዳች አልተነፈሱም።ይህ ሁኔታም በራሱ የምክር ቤት አባላቱ የሌላ የአሜሪካ የውጪ ፖሊሲ ማስፈፀምያነት የሰሞኑን የኢትዮጵያ ሁኔታ ለመጠቀም የሞከሩ ይመስላል።የምክር ቤቱ አባላት የኢትዮጵያን የአንድነት ጉዳይ ከዲሞክራሲ እና ከሰብዓዊ መብት መርሆዎች አንፃር ብቻ እየተነተኑ ለማቅረብ ከሞከሩ በራሱ አደጋ ነው። 

ይህ በእንዲህ እያለ ግን በመጨረሻ መሰመር ያለበት ጉዳይ በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ለውጪ መንግሥታት የማስረዳት ታሪካዊ ኃላፊነት ከምንግዜውም በላይ በእነርሱ ላይ መውደቁን ሊረዱት ይገባል።ለእዚህም ያስተማረቻቸውን ሀገር ሳይመሰክሩላት በዝምታ ድባብ የሚኖሩ የዳር ተመልካች ኢትዮጵያውያን የታሪክ ተወቃሽ እንዳይሆኑ ከምንጊዜውም በላይ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት መነሳት ይገባቸዋል።በእዚህም መሰረት የፅንፍ ኃይሎችን ተግባር እና በውጪ በሀገር ቤት በንፁሃን ላይ የእልቂት ተግባር እንዲፈፀም የሚቀሰቅሱትን ሁሉ ከተግባራቸው እንዲታቀቡ እውነታውን በእየሃገራቱ ለሚገኙ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች፣የድረ ገፅ እና የህትመት ጋዜጦች፣የፓርላማ አባላት እና ፖሊሲ አውጪዎች ሁሉ የማስረዳቱን ኃላፊነት መወጣት አለባቸው።ከእዚህ በተጨማሪ የማኅበራዊ ድረ-ገፆቻቸውን በመጠቀም ለቀሪው ዓለም እውነታውን ለማሳወቅ መድከም ይገባቸዋል።

ከእዚህ በታች እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ነሐሴ 21/2020 ዓም የአሜሪካ ምክር ቤት አባላት በኢትዮጵያ በፅንፍ ኃይሎች የሚፈፀመውን የጥፋት ተግባር ባላገናዘበ መልኩ በኢትዮጵያ ባለው የውስጥ ጉዳይ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በስልሳ ቀናት ሪፖርት እንዲያቀርብ የጠየቁበት ደብዳቤ ነው።የብዙ ኢትዮጵያውያን ዝምታ እና የዳር ተመልካችነት እንዲህ ኢትዮጵያን እንደሚያስጠቃ መረዳት ይገባል።


===========================//////=====================

Friday, August 21, 2020

GERD is meant to connect millions to power grid. Scholars’ in Norway present papers on GERD


The Ethiopian herald News Paper
August 20 , 2020
BY STAFF REPORTER
Addis Ababa
**************************
(EPA)
ADDIS ABABA - Over sixty-million rural people who have no access to electricity are counting down the days to the first energy generation of the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD).
Ethiopian Common Forum in Norway held a discussion and paper presentation on GERD last Saturday in cooperation with the GERD Support Group in Norway.
In his keynote speech, Ethiopian Ambassador to Sweden and other Nordic countries Diriba Kuma said this in a forum envisaged to inform the Norwegian government, officials, journalists, and the Ethiopian community in Norway.
Diriba underscored that Abay (the Nile) touches 70 percent of the livelihood of the population of Ethiopia and represents 2/3 of Ethiopia’s surface water potential, while over 70 percent of energy generation potential is in this river.
Indicating that 25 million people of Ethiopia are living under the poverty line, and 65 million people of Ethiopia have no access to electricity, he said: “Our citizens are waiting for the completion of the dam.” The government of Ethiopia has taken practical steps to negotiate and discuss all important matters since the inception of the project as these are the way out of the dispute, he said, adding that the GERD has no significant impact on the flow of Nile to downstream countries.
He also expressed a strong belief that under the auspicious of South African President Cyril Ramaphosa’s leadership the three countries would resolve the outstanding issues. Elaborating on the rationale of the forum, Dr. Mulugeta Bereded Zelelew, one of the paper presenters, said Egypt’s attempt to internationalize the GERD project with massive media coverage has been with full of bias and misleading information.
Group of GERD support Team in Norway did analysis into the media coverage, and decided to lay bare Egyptian fabrications with scientific evidence, he added. In his paper, entitled:GERD Project and its Significance for Ethiopia and the Region, he refuted Egyptian claim which is presenting Ethiopia as it has abundant rainfall arguing that the rainfall in Ethiopia is erratic and rushes to the rivers due to the nature of the topography. Hence, there is little time for the water to infiltrate into the soil and remain as residual moisture for sufficient time. It is to be noted that the major rivers of Ethiopia are trans-boundary.
Under normal rainfall year, as much as 5 – 10 million or more Ethiopians are chronically food insecure, he said, adding that 80-85% of the total volume occurs during the major rainy season and water storages are necessary to prolong water availability. Concerning the view that GERD is “an existential threat” to downstream countries of the Nile, he said: “Historical records thought us that Egypt and Sudan which have high storage capacity per capita have more resilience to drought management.”
In severe multi-year droughts, a basinwide drought management plan is required to optimize the competing water uses in the three countries and the three countries should take a shared responsibility to mitigate drought, according to him.
For his part, Dr. Admasu Gebeyehu, Professor of Practice in Water Resources Engineering,indicated that the great majority, 92.4 percent, of the share of energy supply is waste and biomass. He said the share of oil and hydropower is 5.7 percent and 1.6 percent respectively.
The bulk of energy source, 98 percent, in Norway is electricity production from a renewable energy source, he said, noting that Norway is in a unique position in the global perspective while Ethiopia is also in the same position in an African perspective with regard to hydropower potential.
The difference between Ethiopia and Norway is, Norway has gone a lot in the production of energy while Ethiopia has started going through the same path, he added.He also put the contribution of Ethiopia to Nile which stands at 77 BCM or 86 percent of the waters of the Nile.
However, his analyses have proven that Ethiopia’s water storage is insignificant as compared to Sudan and Egypt. Egypt has the Aswan High Dam with a storage capacity of 149.5 BCM while a series of dams in Sudan have boosted the Sudanese storage capacity.
Senior Ugandan Water Engineer Dr. Emmanuel Jjunju (PhD) also presented his work titled: ‘Victoria And Albert Nile Countries’interests On Nile Water Resources’. Jjunju touched up on issues ranging from colonial agreements to the recent basin-wide document, the Cooperative Framework Agreement (CFA).
He said almost all Nile Basin countries are at low level in human development with an exception of Egypt. If you want to take all these countries to the level of Egypt, for instance, it requires the countries lot of work. And it cannot come by without energy.
As electricity is a very big driver of development, be it education, telecom or what have you, countries ought to do a lot in this regard.
Mentioning that hydropower is the most feasible and affordable source of energy to the countries such as Uganda, Burundi and Kenya, he said most of the hydro potential of Uganda, 6,950 MW, is within the Nile basin.
He added that his country, Uganda, go to expensive alternative sources of energy that cost 0.16-0.20 USD cents/ Kh which is not really affordable. The benefits of GERD to downstream countries was discussed thoroughly with the presentations of scientific evidence, it was learnt.
================////============

Thursday, August 13, 2020

Nordmenn er invitert til Webinar-presentasjon og diskusjoner om Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD) / Norwegians are invited to Webinar presentation and discussions on the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD)


Gudayachn Report

August 14,2020

Senior Hydrologists and water resource Engineers webinar presentation and discussions on creating awareness about the Great Ethiopian Renaissance Dam (GERD) on the Blue Nile River to be held on Saturday, August 15,2020 between 11 am to 1 pm. 


Ethiopian Common Forum in Norway is a coordinator of a webinar presentation and discussion.The meeting will be attended by Ethiopian Ambassador for Nordic countries, His Excellency Ambassador Diriba Kuma, and Norwegian professionals from different  offices including Norwegian  Ministry of Foreign Affairs.


Here below, you will find the webinar link.You are invited to attend the meeting.

Date and time: Aug 15, 2020 11:00 AM Oslo

Topic: special discussion of creating awareness about the Great Ethiopian Renaissance Dam (GERD) on the Blue Nile River

Please click the link below to join the webinar:

https://us02web.zoom.us/j/82883949861


Monday, August 10, 2020

አዲስ የተመሰረተው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕብረት (International Orthodox Tewahedo Alliance - IOTA) በሰሞኑ በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ላይ የደረሰውን ጭፍጨፋ የአካል እና የስነልቡና ጉዳት እንዲሁም የንብረት መውደም የሚያወግዝ መግለጫ አወጣ።የመግለጫውን ሙሉ ይዘት ይዘናል


አዲስ የተመሰረተው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕብረት (International Orthodox Tewahedo Alliance - IOTA) በሰሞኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ላይ የደረሰውን ጭፍጨፋ  የአካል እና የስነልቡና ጉዳት እንዲሁም የንብረት መውደም አስመልክቶ ጠንካራ መግለጫ አውጥቷል።በኢትዮጵያ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በሕጋዊ መንገድ በመንቀሳቀስ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖችን መብት፣ደህንነት እና መልካም ዕሴቶች ላይ ለመስራት በቅርቡ የተመሰረተው እና በአሜሪካን ሀገር ሕጋዊ ምዝገባውን ያጠናቀቀው  ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕብረት (International Orthodox Tewahedo Alliance - IOTA) በዋናነት በችግርም ሆነ በመልካም ጊዜ  የቤተ ክርስቲያኒቱ ድምፅ በውጪ ሀገር ባለው ማኅበረሰብ በሚገባ አለመደመጡን ከግንዛቤ በማስገባት የተመሰረተ ለመሆኑ ድረ-ገፁ በዋናነት በእንግሊዝኛ የተዘጋጀ መሆኑን በመመልከት ለመረዳት ይቻላል።


ድርጅቱ በድረገፁ ላይ እንደሚያስነብበው ዋና ተልዕኮው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናንን ሁለንተናዊ ተደማጭነት ማጉላት መሆኑን ሲገልጥ እንዲህ አስቀምጦታል ‘’Our mission is to empower the Ethiopian Orthodox Tewahedo believers and communities’’ በሌላ በኩል ድርጅቱ ርዕዩን አስመልክቶ የገለጠበት ዓረፍተ ነገር ደግሞ ‘’ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እና ተከታይ ምእመናኖቿ ካለምንም ጥቃት እና መሸማቀቅ ዕምነታቸውን የሚገልጡባት ዓለም መፍጠር’’  ‘’To create a better world where Ethiopian Orthodox Tewahedo Churches and believers can be self-sustained to freely practice their faith without intimidation and persecution’’ የሚል ነው። 


ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕብረት (International Orthodox Tewahedo Alliance - IOTA) ሰሞኑን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን እና ንብረታቸው ላይ የደረሰውን ጥቃት አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ፣የድርጅቱን ድረ-ገፅ ማስፈንጠርያ (ሊንክ) እና ኢ-ሜይል ከእዚህ በታች ያገኛሉ -

Press Release – International Orthodox Tewahedo Alliance (IOTA) 

On June 29 and 30, following the assassination of renowned artist Hachalu Hundessa, violent protests took place across Ethiopia. These acts of terror occurred in selected cities and towns across ten provincial zones (Eastern and Western Arsi, Eastern and Western Hararge, Eastern Showa, Southwestern Showa, Jima, Balle, Harar and Metu, and two federally administered cities: Addis Ababa and Dire Dawa. Within the two days of violence, 239 lives, mostly civilians and Orthodox Christians are known to have been killed. According to government authorities, approximately 328 houses, mostly of ethnic minorities and Orthodox Christians, 44 hotels, 6 factories and 14 government buildings have been burned down or destroyed. The International Orthodox Tewahedo Alliance (IOTA) strongly condemns the killing of innocent citizens and destruction of their properties throughout the Oromia administrative region in Ethiopia. 

These destructions are generally characterized as protests and spontaneous responses to the death of the artist; however, the coordination level of the destruction indicates a premeditated and well-orchestrated execution by an organized group that seeks to target Orthodox Christians. These organized groups have taken hold of some elements of the government to promote these persecutions and deny justice. Some high-level government officials are downplaying and denying these genocidal crimes. Without credible and transparent investigation of these crimes, the country is on the brink of an unimaginable genocide. 

IOTA denounces the authorities’ abdication of their sacred duty to protect and defend the defenseless, the hateful rhetoric and incitement of ethnic and religious violence by the media, political activists and organizations. We support the current measures the federal government is taking to combat such actions and hope that there will be a transparent and fair trial for the accused. 

We call on the Ethiopian government to protect and defend innocent citizens, rehabilitate those displaced from their homes and those affected by these heinous and gruesome acts of terror and bringing the perpetrators to justice. Finally, we call on the international community to pay close attention to these recurring violent and targeted crimes against Orthodox Christians and ethnic minorities, and support the protection of justice for innocent victims. 

Respectfully,

Office of IOTA 

+++++++++++++++++++++

የድርጅቱ ድረ-ገፅ = https://iotaethio.org/

ኢ-ሜይል = office@iotaethio.org Saturday, August 8, 2020

የኦሮምያ ክልል ባለስልጣን በዓለም ዓቀፍ ወንጀል መጠየቅ አለባቸው -በኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ላይ በአሰበ ተፈሪ ፣መኢሶ እና የአሰቦት የደረሰው ጭፍጨፋ (ቪድዮ)

-  እንጨት ሸጠው ያሳደጉ እናቷን ልትረዳ በባህር በኩል አረብ ሀገር ደርሳ ያፈራችውን ንብረት እንዴት እንዳወደሙት፣

- እራሱን ለማዳን ወደ ፖሊስ ጣብያ ሸሽቶ ሲሄድ ፖሊሶቹ እራሳቸው የገደሉት፣

- ባለቤቱ እና የአምስት ዓመት ልጁ ፊት የታረደው አባት፣ልጁ አሁን የአዕምሮ ህመምተኛ ሆኗል፣
- አስከሬን አነሳህ ተብሎ አሁንም ፖሊስ እየፈለገው ያለ ክርስቲያን 
- ቤተክርስቲያን ስረዳ የነበረ ለፍልሰታ በየዓመቱ ለሚያስቀሱ ሁሉ ንፍሮ የሚያድለው ምዕመን ታርዷል።


Thursday, August 6, 2020

የአቶ ሽመልስ አብዲሳ ዓይኞች የታረዱ ክርስቲያኖችን አንገት አሁንም ማየት አልቻሉም።ዛሬም በቃለ መጠይቃቸው ስለ ላም እና ጊደር ተረት እየተረቱ እና በ150 ዓመት የውሸት ትርክት ድክመታቸውን ሊሸፍኑ ይሞክራሉ።

አቶ ሽመልስ አብዲሳ 

የሰው ልጅ አንገት በካራ ተቀነጠሰ፣እርጉዝ በስለት ሆዷ ተቀደደ እየተባሉ የአስተዳደር ድክመታቸውን  በላም እና ጊደር ተረት ለመሸፈን ይሞክራሉ።በያዝነው ሳምንት አጋማሽ በኦቢኤን ቴሌቭዥን ቀርበው መግለጫ የሰጡት የኦሮምያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በቃለ መጠየቃቸው ላይ አሁንም በጎሳ ፖለቲካ የኦሮሞ ህዝብን ስሜት በመኮርኮር ቅጥ የለሽ የክልል አስተዳደር ሥርዓታቸውን ሊሸፋፍኑ እየሞከሩ ነው።በእዚሁ ቃለ መጠየቅ ላይ እስካሁን ምን ሰሩ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ከአንድ ዓመት በፊት በኮሚቴ የተሰራውን ከሱማሌ ክልል የተፈናቀሉትን መመለስ ከጠቀሱ በኃላ በድፍኑ በርካታ ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል በማለት አልፈውታል።በእርግጥ በክልሉ ውስጥ የተፈጠረው የሰላም እጦት ከክልሉ አልፎ ለኢትዮጵያም አደገኛ ሁኔታ መጋረጡን በራሱ እንደ አንድ የኦሮሞ መኩርያ ነጥብ አድርገው ሊያጎሉትም ሞክረዋል።
በኦሮምያ የተነሳው የፀጥታ ችግር ምክንያቶቹ እንደርሳቸው አገላለጥ ላለፉት ክ/ዘመናት ኦሮምያን የበዘበዙ ናቸው ካሉ በኃላ ችግሩ 'ድንበሩን እንዲያልፍ' ያደረጉት አሁንም ለ150 ዓመታት የተበተቡት ናቸው ብለዋል።በመቀጠል የኦሮሞ ሕዝብ ስልጣኑን አግኝቷል፣ባገኘው ስልጣን መጠቀም አለበት ብለዋል።ላለፉት 150 ዓመታት ኦሮሞ የተሸነፈው ከውስጣችን ተላላኪ ፈረስ ስላለ ነው ብለዋል።በመቀጠልም ላሚቷ፣ጊደሯም፣ወተቷም፣አሬራውም አሁን በእጃችን ነው ሲሉ በእዚሁ ቃለ መጠየቃቸው ላይ ተደምጠዋል። 

አቶ ሽመልስ በእዚህ ቃለ መጠየቃቸው  ትውልድ ከማቀራረብ ይልቅ የሚያራርቅ ጉዳይ ላይ ማተኮራቸው አሳፋሪ የመንግስት ባለስልጣን ያደርጋቸዋል።ኢትዮጵያ ላለፉት 150 ዓመታት ውስጥ የነበረችበትን የፊውዳል፣የፊውዶ-ቡርዣ እና የደርግ ዘመን (የሶሻሊስት ርዕዮት) አስተዳደር ሁሉ በአንድ ከረጢት ውስጥ ከትተው የኦሮሞ ሕዝብ ለ150 ዓመታት ሲበዘበዝ ነበር የሚለው ትርክታቸው ፈፅሞ ውሸት ነው።ይህ ተራ የስሜት መኮርኮር ሙከራ ከመሆን አያልፍም።

በእዚህም አቶ ሽመልስ ምን ያህል የታሪክ ዕውቀታቸው ብዙ የሚቀረው መሆኑን ያሳያል። እዚህ ላይ አፄ ሃይለስላሴም ሆኑ ኮለኔል መንግስቱ እነማን እንደሆኑ አለማወቃቸውን ያሳብቅባቸዋል።ከ150 ዓመቱ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን የመሩት እነርሱ ናቸው።ሁለቱም ደግሞ ከኦሮሞ ቤተሰብ የሚወለዱ ናቸው።አቶ ሽመልስ በምናብ የፈጠሩት ብዝበዛ ተራ የብሔር ስሜት ኮርኩረው ነገሮችን ለማድበስበስ ነው የሞከሩበት መንገድ ከመሆን አሁንም አያልፍም።ላለፉት 150 ዓመታት ለምሳሌ በፊውዳል ስርዓት ውስጥ ጭሰኛ ወሎ ውስጥ እንደነበረ ሁሉ ወለጋም ውስጥ ነበር።የወለጋው ባላባት ከወለጋ የወጡ ደጃዝማች እና ፊታውራሪዎች እንደሁኑ ሁሉ በወሎ እና ጎንደርም ተመሳሳይ ነበሩ።በ1967 ዓም የካቲት 25 የወጣው መሬት ላራሹ አዋጅ ደግሞ ይህንን የፊውዳል ስርዓት ስያንኮታኩት ወለጋ ያለው ገበሬም መሬት እንደተመራ ሁሉ ለጎንደሩም ተመርቷል።ኦሮሞ በተለየ የተበዘበዘበት የቱ ጋር ነው? 

የድምፃዊ ሃጫሉ ግድያ ተከትሎ በአርሲ፣ሐረር፣ባሌ፣ዝዋይ እና ሻሸመኔ በንፁሃን ላይ በደረሰው አሰቃቂ ግድያ እና የንብረት ዘረፋ የክልሉ የፀጥታ አጠባበቅ፣የልዩ ኃይል ከፅንፈኞች ጋር መተባበሩን በምስክርነት የሚያነሱ ተጠቂዎች እየተናገሩ፣ሰው በአደባባይ በስለት መታረዱ እርጉዝ ሴት በስለት መገደሏ ባጠቃላይ ከ200 ያላነሱ ኢትዮጵያውያን በተለይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት  ተከታዮችን እንዳጠቃ እያወቁ ዛሬም የሰለቸ የ150 ዓመት ትርክት ውስጥ ለማብራራት መሞከራቸው የሚመሩትን ሕዝብ አለማወቃቸውን ያመለክታል።

የአቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮምያ አመራር በክልሉ የሚያስተዳድረውን ሕዝብ እኩል የማስተዳደር እና በአንድ ዓይን የማየት ከፍተኛ ችግር እንዳለበት በክልሉ የሚኖሩ አሁን ድረስ የሚያማርሩት ጉዳይ ነው።በእዚህም ሳቢያ በርካቶች መጤ እየተባሉ እንደ ሁለተኛ ዜጋ የሚኖሩባት ክልል የሆነችው የኦሮምያ ክልል በአሁኑ ጊዜ ኢንቨስተሩ እየለቀቀ ወደ ሐዋሳ፣ባህርዳር እና ደብረብርሃን እየሸሸ እና ከፍተኛ የካፒታል ሽሽት እየታየ አቶ ሽመልስ ግን ብዙ ፕሮጀክት ገንብተናል እያሉ ነው።

የአቶ ሽመልስ ሌላው የአስተዳደር ድክመታቸው ማሳያ ደግሞ ሰሞኑን በአርሲ፣ሐረር፣ባሌ፣ዝዋይ እና ሻሸመኔ በንፁሃን ላይ በደረሰው አሰቃቂ ግድያ እና የንብረት ማቃጠል እና ዘረፋ ተከትሎ ለደረሰው ጥፋት የሃዘን መግለጫም ሆነ በቦታው ሄደው ያላፅናኑት አቶ ሽመልስ ከሰብዓዊነት ስሜት በራቀ መልኩ ለችግሩ መቀረፍ ያደረጉት የጎላ እንቅስቃሴ አለመታየቱ ብዙዎችን ግራ አጋብቷል።ባድምፃዊ ሃጫሉ ሞት ተከትሎ እንባቸው እየወረደ መግለጫ የሰጡት አቶ ሽመልስ የ200 ሰው ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ ማለቁ እንዴት  አልተሰማቸውም? ይህንን ያህል ንፁሃን ሕይወት ከጠፋ ገና በአንድ ወር ውስጥ የሰጡት መግለጫ ላይ የተበላሸ እና በአድሎ እና በፅንፈኞች የተበላሸውን አስተዳደራቸውን ለመሸፈን ያልሰሩትን እንደሰሩ ማቅረባቸው እና አሁንም ሕዝብ ከህዝብ የሚለያያ የውሸት የታሪክ ትርክት በመተረክ ለመሸፈን መሞከር ከተጠያቂነት ለማምለጥ የሚደረግ ሙከራ ከመሆን አያልፍም።

=================/////================


በሌሎች ሚድያዎች ያልተዘገቡ የጉዳያችን ዜናዎች በዩቱብ ይከታተሉ።

ዜናዎቹ በእየእለቱ እንዲደርሳችሁ ሊንኩን ከፍተው ሰብስክራይብ ያድርጉ   https://www.youtube.com/channel/UC5-Q4rqKJcqt17I0hTS4Nwg