የተከበራችሁ የጉዳያችን ተከታታዮች፣ከእዚህ ደብዳቤ በተጨማሪ የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ምርጫ በተመለከተ ከሁለቱ ከተሞች ተፅዕኖ ፈጣሪነት አንፃር የተለያዩ ሃሳቦች ከተለያዩ ሰዎች እንደሚሰጡ ጉዳያችን ተገንዝባለች።ከእነኝህም ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል።እነርሱም -
1) የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተሞች ምርጫ ከሀገራዊ የተለየ ማድረጉ የሌሎቹ ውጤት ከታወቀ በኃላ የሁለቱን ከተሞች ብዙም አስፈላጊ እንዳይሆን ያደርገዋል፣
2) የለም፣የሁለቱ ከተሞች ምርጫ ውጤት የሌላውን ይወስናል፣
3) የሁለቱ ከተሞች ምርጫ ከሀገራዊው መለየቱ ሌላው ጋር የመረጡ መልሰው አዲስ አበባ እና ድረዳዋም መጥተው እንዲመርጡ ዕድል ይሰጣል።ይህም ለፅንፍ ኃይሎች የማጭበርበር በር ይከፍታል።
4) የሁለቱን ከተሞች ምርጫ መለየት ለፅንፍ ኃይሎች ዕድል ስለሚሰጥ ለሁከት በር ይከፍታል፣ወዘተ የሚሉ ሃሳቦች ይነሳሉ።
በመሆኑም የምርጫ ቦርድ ለእነኝህ ጉዳዮች በቂ ምላሽ ከወዲሁ በመስጠት ጉዳዩን ማጥራቱ ሃገራዊ ጥቅም አለውም።
ከእዚህ በላይ ያለው ጉዳያችን ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሰማችው ነጥቦች ናቸው እንጂ የእናት ፓርቲ ደብዳቤ ጋር ግንኙነት የለውም።
===========
ከእዚህ በታች የእናት ፓርቲ ለምርጫ ቦርድ የፃፈው ሙሉ ደብዳቤ ነው።
No comments:
Post a Comment