በእዚህ ጽሑፍ ስር የሚከተሉትን ንዑስ ርዕሶች ያገኛሉ፡
- በአሁኑ ጊዜ ቤተክርስቲያኒቱን እና ምእመናንን የሚያምሷት እነማን ናቸው?
- እራሱን ''የሲኖዶስ አስፈጻሚ ኮሚቴ'' እያለ የሚጠራው ማን ነው?
- የቡድኑ ''ሶማትዮ ማኅበር'' እና ''ቀሲስ አየለ'' የሚለው አጀንዳው
- ''ቤተክርስቲያኑ እንዲዘጋ እንፈልጋለን'' የአማሳኝ ቡድኑ የእየሳምንቱ ፉከራ
- የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ምእመናን በአማሾች ሲታመሱ ያደረጉት ምንድን ነው?
- በአሁኑ ጊዜ የምእመናኑ አንድነት እና ሕብረት የበለጠ ጠንክሮ ወጥቷል።
መግቢያ
በጥንታዊቷ እና ቀደምት የክርስትና መገኛ ከሆኑት ሀገሮች ውስጥ በሆነችው ግሪክ የምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አቴንስ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን የዓመታት ችግር ፈቺ በሆነ መልክ ሪፖርት እንዲዘጋጅ ቋሚ ሲኖዶስ በወሰነው መሰረት የተቋቋመው እና ከቤተክሕነት፣ከኖርዲክ እና ግሪክ ሀገረስብከት እና ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን የተገኙበት ልዩ አጣሪ ኮሚቴ በግንቦት 2016 ዓም ለቅዱስ ሲኖዶስ ካቀረበው ሪፖርት መግቢያ ላይ የቀረበው ጽሑፍ በግሪክ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አመሰራረት ላይ ጥሩ ማብራርያ ይሰጣል። የሪፖርቱ መግቢያ እንዲህ ይነበባል፡
በጥንታዊቷ እና ቀደምት የክርስትና መገኛ ከሆኑት ሀገሮች ውስጥ በሆነችው ግሪክ የምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አቴንስ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን የዓመታት ችግር ፈቺ በሆነ መልክ ሪፖርት እንዲዘጋጅ ቋሚ ሲኖዶስ በወሰነው መሰረት የተቋቋመው እና ከቤተክሕነት፣ከኖርዲክ እና ግሪክ ሀገረስብከት እና ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን የተገኙበት ልዩ አጣሪ ኮሚቴ በግንቦት 2016 ዓም ለቅዱስ ሲኖዶስ ካቀረበው ሪፖርት መግቢያ ላይ የቀረበው ጽሑፍ በግሪክ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አመሰራረት ላይ ጥሩ ማብራርያ ይሰጣል። የሪፖርቱ መግቢያ እንዲህ ይነበባል፡
''በእአአ1996 ዓ/ም (1989) የግሪክ የሃይማኖት ተቋማት ሕጋዊ የዕውቅና ምዝገባ አስመልክቶ ባወጣው አዋጅና መመሪያ መሠረት “በአቴንስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን” ቃለ ዓዋዲው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ አንድ ውስጠ ደንብ በሕግ ባለሙያዎች ተዘጋጅቶና በሀገሪቱ መንግሥት ዐዋጅ ጸድቆ ለምዝገባ በመቅረቡ የአቴንስ ምክሐ ደናግል ቅድስት ኪዳነ ምኅረት ቤተ ክርስቲያን በሀገሪቱ የሃይማኖት ተቋማት ምዝገባ ዕውቅና አገኘች፤ ይኽ አሁን (ሶማቲዎ) እየተባለ የሚጠራው ነው፤ በወቅቱ የነበሩት የሰበካ ጉባኤ አባላትም ይኽንኑ ጉዳይ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ (ዶ/ር) አምስተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ አሳውቀዋል፡፡ ዕውቅናው ለቤተ ክርስቲኒቱ ተጨማሪ የሕግ ሰውነት የሰጣት ሲሆን እአአ ከ1994 ዓ/ም ጀምሮ ለነበረባቸው የሰነድ ተቀባይት ችግርም መፍትሔ መስጠቱ ሰበካ ጉባኤው በላከው ደብዳቤ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይኽ የሶማቲዎ (ማኅበር) የግብር መለያ ቁጥር (Tax No) 997874156 ሲሆን “AΙΘΙΟΠΙΚΗΣΟΡΘΟΔΟΞΗΣ ΕΚΚΛΗΣΙΑΣ ΤΗΣ ΑΘΗΝΑΣ” በሚል ንብረት ለማፍራት፣ ገንዘብ
ለማንቀሳቀስ፣ በግብርና ተያያዥ ክፍያዎች አፈጻጸም ዙሪያ ያሉ ችግሮችንም ለመፍታት ተችሏል፡፡በኋላም ብፁዕ አቡነ ገሪማ (ዶ/ር) ባጸደቁት የኮሚቴዎች ስም መንፈሳዊ አገልግሎቱ ቀጥሏል፡፡''
ይህ ሪፖርት ቅዱስ ሲኖዶስ ተቀባይነት ያገኘ እና ከቤተክሕነት ረዳት ፕሮፌሰር መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል፣ ከስዊድን ዶ/ር ቀሲስ አባተ፣ከፊንላንድ፣ሄልሲንኪ ከደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስትያን የሀገረስብከቱ ጸሐፊ መልዓከ አሚን ቀሲስ ለማ በሱፈቃድ፣ከሀገረስብከቱ የሕግ ክፍል ምክትል ሰብሳቢ አቶ ደምስ በግሪክ ያሉ ሁሉንም ወገኖች አነጋግረው በመጨረሻ ምክረ ሃሳብ አክለው ያዘጋጁት ልዩ ሪፖርት ነው። በእዚሁ ሪፖርት መሰረት ቅዱስ ሲኖዶስ በመጋቢት/2017 ዓም አቡነ ጢሞቲዎስ እና አቡነ ጴጥሮስ ያሉበት ልዩ ልዑክ ግሪክ ድረስ ልኮ የግሪክ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ጉዳይ ለማየት ተሞክሯል። ከብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት የአቴንስ ጉዞ ተከትሎ ቅዱስ ሲኖዶስ ክሕነታቸው ተይዞ የነበረው የአባ ወልደሚካኤልን ስልጣነ ክሕነት የመለሰ ሲሆን ለአቴንስ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን በሕገ ቤተክርስቲያን መሰረት አዲስ አስተዳዳሪ ሊቀስልጣናት አባ ኪሮስ ጸጋዬን መድቦ፣በአሁኑ ጊዜ ምእመናን የአዲሱን አስተዳዳሪ መምጣት በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።ይህ በአሁኑ ጊዜ ቤተክርስቲያኒቱ የምትገኝበት ተጨባጭ እውነት ነው።
በአሁኑ ጊዜ ቤተክርስቲያኒቱን እና ምእመናንን የሚያምሷት እነማን ናቸው?
በአሁኑ ጊዜ ቤተክርስቲያኒቱን እና ምእመናንን የሚያምሷት እነማን ናቸው?
ቅዱስ ሲኖዶስ ለቤተክርስቲያኒቱ በቂ ክትትል በማድረግ ተገቢውን ስራ ቢያከናውንም ከመጀመርያ ጀምሮ የቅዱስ ሲኖዶስን ሲኖዶሳዊ ውሳኔ ሲቃወሙ የነበሩ፣በኋላም በአጉራ ዘለል እና ፍጹም ኢትዮጵያዊም ሆነ ኦርቶዶክሳዊ ትብሃል ባልሆነ መንገድ ቤተክርስቲያኒቱን ለማመስ የሚሞክሩት እጅግ ጥቂት የሆኑ ግለሰቦች እነማን እና ምን እንደሚፈልጉ ለመግለጽ መጀመርያ ማንነታቸውን መግለጹ ያስፈልጋል።
አማሾቹ እነማን ናቸው?
- የመጀመርያው ቡድን ውስጥ ያሉት በጣት የሚቆጠሩት ለዓመታት የግሪክ አቴንስ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪነት ዘመን ማለት ቀድሞ አባ ዮሐንስ፣በኋላም የነበሩት ንቡረዕድ አባ ኃይለልዑል ገሪማ ቤተክርስቲያኒቱን ሲያስተዳድሩ በቤተክርሲቲያኒቱ ገንዘብ እንደ የግል ንብረት ሲጠቀሙ የነበሩ፣ወደ ሃገርቤት ከግሪክ ከቀረጥ ነጻ በቤተርክስቲያን ደብዳቤ ሲያስገቡ እና አብረዋቸው ሲሞዳሞዱ የነበሩ የቡድን አባላት የመጀመርያ ተጠቃሽ ናቸው ናቸው።ከእዚህ ቡድን አባላት ውስጥ በሕገወጥ መንገድ የቅስና እና የድቁና ማዕረግ ሳይገባቸው የተቀበሉ ያሉበት ነው። ይህ ቡድን አባላቱ በአሁኑ ጊዜ ከአራት የማይበልጡ ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ ሰላማዊ በመምሰል በምዕመኑ ውስጥ መለያየት የሚነዛ፣በአደባባይ እየተቅለሰለሰ ቤተክርስቲያንን ለማመስ ከሚሮጡ ጋር ከአስተባባሪነት እስከ በቀጥታ ሃሳብ በመስጠት በአጽራረ ቤተክርስቲያንነት የተሰለፈ ግለሰብ አለበት።ይሄው ግለሰብ በሀገርቤትም በንዋየ ቅድሳት መሸጫ ሱቅ ቀደም ብሎ በቅዱስ ዑርዔል ቤተክርስቲያን በሕገወጥ መልክ ሱቅ የነበረው እና በአሁኑ ጊዜ በሌላ ቦታ ሱቅ ያለው ሲሆን፣ ከግሪክ የሚመጡ እቃዎችን ከቀረጥ በነጻ በማስገባት ከፍተኛ ምዝበራ ላይ የተሰማራ ግለሰብ ነው።
- በሁለተኛው ቡድን ውስጥ የሚገኙት በጣት የሚቆጠሩ የአማሽ ቡድን አባላት በቀደመው የሰበካ አባላት የነበሩ፣የቤተክርስቲያኒቱን ንብረት በአግባቡ መያዝ አለመቻል ብቻ ሳይሆን፣እስካሁንም ሪፖርት እንዲያቀርቡ እና ንብረት እንዲያስረክቡ በቅርቡም ጭምር ተጠይቀው አሻፈረኝ ያሉ፣ከተለያዩ የስለት የወርቅ ስጦታዎች እስከ የቤተክርስቲያኒቱን ሚኒባስ አላስረክብም ብለው መኪናው በሕግ እንዲያስረክቡ ተደርገው ሌሎቹን በተመለከተ በምእመኑ በተቋቋመ አጣሪ ኮሚቴ ሪፖርት ቀርቦ ምላሽ ያልሰጡ፣ከሰንበት ትምሕርት ቤት ቲሸርት ሸጦ ገንዘቡን በአደባባይ ወደ ኪሱ የከተተ እና እስከ ሁለት ሺህ ኢሮ ከሰንበት ትምሕርት ቤት ንዋየ ቅዱሳን መሸጫ ሱቅ በድፍረት ጠፋብኝ ብሎ የተዘባበተ ግለሰብ ያለበት ቡድን ነው።
- በሦስተኛው ቡድን ውስጥ የሚገኙት አሁንም በጣት የሚቆጠር ቡድን ያለበት ቡድን ባንዳ እና ባዳ የሚባለው ቡድን ነው። በእዚህ ቡድን ውስጥ የሚገኙት ጸረ ኢትዮጵያ አቋም መመረዛቸው በስራቸው ያስመሰከሩ ናቸው። በእዚህ ውስጥ ለኢትዮጵያ ባዳ የሆኑ ነገር ግን ለቤተክርስቲያን የሚቆረቆሩ መስለው እኛኑ መስለው የሚያምሱ ናቸው። ዓላማቸው የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን ከግሪክ መንቀል፣ምእመኑን ማወክ፣ኢትዮጵያውያን በቤተክርስቲያናዊ እና ብሔራዊ ስሜታቸው እንዳይኮሩ ማድረግ እና የኢትዮጵያን ስም በግሪክ ማኅበረሰብ ዘንድ ማጠልሸት ነው።
በእዚህ ውስጥ በቅስና የሚገኙ፣በቀድሞ ሰበካ ውስጥ የነበሩ እና ከኋላ ሆነው በኢትዮጵያውያን ላይ የሚጎነጉኑ ''አካይስት'' አስተሳሰብ ያላቸው የበሉበትን የኢትዮጵያን ወጪት ሰባሪ አሳፋሪዎች ናቸው። ከእነርሱ ጋር አብረው ያሉት ባንዳዎች የቤተክርስቲያን ጉዳይን ለዘመኑ የጥፋት ስራ ለማዋል የቋመጡ ከባዳ ጋር አብረው ቆመንለታል ለሚሉት የረከሰ የባንዳ ተግባር በቤተክርስቲያን ስም ለውሰው ለመንቀሳቀስ የሚሞክሩ አሳፋሪዎች ያሉበት ነው። እዚህ ላይ በኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ስም ፌስ ቡክ ከፍቶ ላለፉት ስባት ዓመታት ያህል የቤተክርስቲያኒቱን ስም ሲያጠለሽ፣የአባቶችን ክብር ሲያዋርድ የኖረ እና እራሱን በመንፈሳዊ ማኅበር ውስጥ ሽጉጦ በአሁኑ ጊዜ ደግሞ አንዴ አዲስ አበባ ቤተክሕነት ሌላ ጊዜ አቴንስ ፖሊስጣብያ በር ላይ እየተንገዋለለ የዘረኛ መርዙን ሸሽጎ የባንዳነት ተግባሩን የሚሰራ ዲያቆን የተካተተበት ነው። ይህ ዲያቆን በተለይ ለዓመታት የግሪክ ጉዳይ እንዳይፈታ በአንድ የቤተክሕነት አባት አገላለጽ ሲናገር ''የእባብ መርዝ የሚተፋ'' ያሉት ግለሰብ በሀገረ ስብከቱና በግሪክ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መሃል ችግር እንዲፈጠር የሰርክ ጉባዔ ቀመስ በሆኑ ጥቅሶች ምእመኑን በፌስቡክ ሲያምስ የኖረ እና አሁንም እያመሰ የሚገኝ ግለሰብ ነው። - በአራተኛ ቡድን ውስጥ ያሉት ጥቂት ግለሰቦች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነትን ለመበረዝ የሚቅበዘበዙ ቡድን አባላት ናቸው። በእዚህ ስር ያሉት ከቤተክርስቲያኒቱ ዶግማና ቀኖና ውጪ በሆነ መልክ መሰረተ እመነቷን ለመበረዝ ምእመኑን ለመክፈል የሚሮጡ የሃይማኖት ቀሳጮች ናቸው።እነኝህ በቤተክርስቲያን ውስጥ ኦርቶዶክሳውያን የሚመስሉ ነገር ግን ቤተክርስቲያኒቱ እንድትጠላ በቀጥታ በማናቸው ቤተክርስቲያንን በሚያውኩ ተግባራት ውስጥ ይሰማራሉ።
ከላይ የተጠቀሱት አራት ቡድኖች ሲደመሩ ከ15 አይበልጡም።ቤተክርስቲያኒቱን የሚበጠብጡት በእዚህ ያህል ያሉ ቁጥር ያላቸው ናቸው። አራቱም ቡድኖች አዲስ የመጡ ስደተኞችን ለመያዝ በብዙ ጥረት የእኩይ ተግባራቸው ተባባሪ ለማድረግ ቢሞክሩም፣ ሁሉም የተንኮላቸው ተባባሪ ስላልሆኑ ዛሬም በጣት የሚቆጠሩ የቡድኑ አባላት ቀርተዋል።
እራሱን ''የሲኖዶስ አስፈጻሚ ኮሚቴ'' እያለ የሚጠራው ማን ነው?
በመጋቢት/2017 ዓም ወደ አቴንስ የመጣው የቅዱስ ሲኖዶስ ልዑክ ከተመለሰ በኋላ ከላይ በአራት የአስተሳሰብ እና የፍላጎት ውጥረት ውስጥ የገባው ወደ 15 የሚቆጠር ቡድን ከሃገረስብከቱ ሊቀጳጳስ ባገኘው አረንጓዴ መብራት እራሱን ''የሲኖዶስ አስፈፃሚ ኮሚቴ'' በማለት አንድ መቶ የማይሞላ ተከታይ ይዞ በፌስቡክ ተከሰተ። ቡድኑ የሰረቀው፣የባዳው እና የባንዳው እንዲሁም የሃይማኖት ቀሳጩ ቡድን በጋራ የተሰበሰበበት ቡድን ነው።
የቡድኑ ''ሶማትዮ ማኅበር'' እና ቀሲስ አየለ የሚለው አጀንዳው
በአቴንስ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ለማመስ የሚንቀሳቀሰው 15 ሰዎች የያዘው ስብስብ ከእውቀት ነጻ የሆነ ቤተክርስቲያኒቱ ቀድሞ ጀምሮ በግሪክ መንግስት የተመዘገበችበትን ''ማኅበር '' ወይንም ''ሶማትዮ '' የሚለውን ስም የቤተክርስቲያን መስደብያ ቋንቋ አድርጎታል። ቤተክርስቲያኒቱን እንደፈለጉ አድርጎ ለመዝረፍ እና ለማጥፋት አልመች ያለው ይሄው አደረጃጀት መሆኑን ስለሚያውቁ በከፍተኛ ጥላቻ የቤተርክስቲያኒቱን አደረጃጀት ማጥላላት ዋና ስራ አድርገው ይዘውታል።ቡድኑ በራሱ ''የብሪፍ ኬዝ'' ተንቀሳቃሽ የቤተክርስቲያን ስም የሚነገድበት ማኅተም ይዞ የሚዞር ሲሆን አደረጃጀቱም በእድር መልክ ''ኪኖኒታ'' በሚል አደረጃጀት የኖረ ነገር ግን አድራሻውን በቦርሳ ይዞ የሚዞር ነው።
ይህ የተለያየ ፍላጎት ያዘለው ቡድን ከሰሞኑ ይዞ የመጣው በግሪክ የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ከአስር ዓመት በፖሊጎኖ የምትገኘውን የኪዳነምሕረትን ቤተክርስቲያን ትተው የሄዱትና ከቅርብ ወራት ወዲህ ተመልሰው የመጡት ቀሲስ አየለን በአጀንዳነት ይዞ መጥቷል።ቀሲስ አየለ ወ/ጻድቅ በቅዱስ ሲኖዶስ በደብዳቤ ቁጥር 397/408/2018 ሐምሌ 23/2017 ዓም ባደረገው ስብሰባ መሰረት በየትኛውም የቤተክርስቲያን አስተዳደር እንዳይገቡ ያገደ ሲሆን በሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ የተሰጠ ማናቸውም ጊዜያዊ ደብዳቤ በሕገ ቤተክርቲያን አንቀጽ 28 መሰረት የተሻረ መሆኑን ደብዳቤ የተጻፈባቸው መሆኑ እየታወቀ ቡድኑ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በመጻረር ቀሲስ አየለን የብጥብጥ አጀንዳ ለማድረግ ሞከረ።
በእዚህ መሰረት ቀሲስ አየለ ከላይ ከተጠቀሰው ቡድን ጋር በመሆን እስካለፈው እሑድ ድረስ በተለያዩ ሳምንታት ለ6 እሑዶች ጊዜ የሰንበት ቅዳሴ እንዳይቀደስ ከማወክ አልፈው ምእመናን ላይ ፖሊስ በመጥራት ቤተክርስቲያኒቱ ዙርያ ያሉ ነዋሪዎች ጭምር እንዲታወኩ አድርገዋል።ይህንን ጉዳይ የተመለከተው ምእመን ከአንድ ሳምንት በፊት መክሮ ቀሲስ አየለ መቅደስ የሚገቡት አዲሱ አስተዳዳሪ ከመጡ በኋላ ጉዳዩ በካሕናት ጉባዔ ከታየ በኋላ ነው የሚለውን ሃሳብ ወደጎን በማድረግ ወደ መቅደስ እንዲገቡ በሚለው ጉዳይ ላይ ሃሳብ ከተሰጠ በኋላ ባለፈው ሳምንት እሑድ ወደ መቅደስ እንዲገቡ ሲጠየቁ ቀድሞም ምክሩ ከአማሽ ቡድኑ ጋር ስለነበረ የአማሽ ቡድኑ ባሳለፍነው እሑድ የካቲት 29፣2018 ዓም በቤተክርስቲያን ውስጥ ገብተው የሚከተሉትን ጸያፍ ተግባራት ፈጸሙ። ይሄውም፡
በእዚህ መሰረት ቀሲስ አየለ ከላይ ከተጠቀሰው ቡድን ጋር በመሆን እስካለፈው እሑድ ድረስ በተለያዩ ሳምንታት ለ6 እሑዶች ጊዜ የሰንበት ቅዳሴ እንዳይቀደስ ከማወክ አልፈው ምእመናን ላይ ፖሊስ በመጥራት ቤተክርስቲያኒቱ ዙርያ ያሉ ነዋሪዎች ጭምር እንዲታወኩ አድርገዋል።ይህንን ጉዳይ የተመለከተው ምእመን ከአንድ ሳምንት በፊት መክሮ ቀሲስ አየለ መቅደስ የሚገቡት አዲሱ አስተዳዳሪ ከመጡ በኋላ ጉዳዩ በካሕናት ጉባዔ ከታየ በኋላ ነው የሚለውን ሃሳብ ወደጎን በማድረግ ወደ መቅደስ እንዲገቡ በሚለው ጉዳይ ላይ ሃሳብ ከተሰጠ በኋላ ባለፈው ሳምንት እሑድ ወደ መቅደስ እንዲገቡ ሲጠየቁ ቀድሞም ምክሩ ከአማሽ ቡድኑ ጋር ስለነበረ የአማሽ ቡድኑ ባሳለፍነው እሑድ የካቲት 29፣2018 ዓም በቤተክርስቲያን ውስጥ ገብተው የሚከተሉትን ጸያፍ ተግባራት ፈጸሙ። ይሄውም፡
- ቤተክርስቲያን ውስጥ በካሕናት ላይ እጅግ አስነዋሪ ስድብ፣እና ለመደብደብ መገባበዝ፣
- በቤተክርስቲያን ወንበር ላይ ቆመው ፊሽካ እየነፉ የቡናቤት ስድቦች መሳደብ፣
- በፉጨት እና ከዘፈን ባልተናነሰ ድምፅ ማቅራራት፣
- የቤተክርስቲያንን ወንበር እየገለበጡ መዘባበት እና ሌሎች እጅግ ለአእምሮ የሚከብዱ ተግባራትን በቤተክርስቲያን ውስጥ ሲፈጸም ተስተውሏል።
''ቤተክርስቲያኑ እንዲዘጋ እንፈልጋለን'' የአማሳኝ ቡድኑ የእየሳምንቱ ፉከራ።
በአቴንስ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ከአርባ ዓመታት የቆየችበት ፖሊጎኖ የሚገኘው ቤተክርስቲያን ከአጠገቡ በሚገኘው በግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ስር የሚተዳደር በመሆኑ እና በአማሳኝ ቡድኑ የየሳምንቱ እጅግ ነውረኛ የሆነ የስድብ እና የረብሻ ተግባር የተነሳ የአካባቢው ነዋሪ እንዲታወክ ሆኗል። የረብሻው አንዱ ዓላማ የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን መበተን በመሆኑ የአማሳኝ ቡድኑ ቀንደኞች ''ቤተክርስቲያኒቱ እንድትዘጋ ነው የምንሰራው '' እያሉ በአደባባይ ሲናገሩ ብዙ ጊዜ ተሰምተዋል፣ በማኅበራዊ ሚድያም ይህብንኑ ያልተገራ ነውራቸውን ሲለጥፉ ይታያሉ። በእርግጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ከአቴንስ ከተማ ቅርብ ርቀት የሚገኝ ሌላ በገዳምነት የነበረ ይዞታ አላት። ይህ ግን በእየእሑዱ ለሚኖረው ቅዳሴ እርቀት አለው።ይህንኑም ገዳም ይሄው አማሳኝ ቡድን በርካታ ወረቀቶችን ወደ የግሪክ የሃይማኖት ሚኒስቴር በመላክ ገዳሙን ለማሳሸግ ሞክሯል።
ከእዚህ በተጨማሪ የማለዳ ኪዳን በሚደረግባቸው ቀናት በማለዳ ቤተክርስቲያን በር ላይ እየቆሙ ካሕናትን መሳደብ እና መተናኮል የአማሽ ቡድኑ ተግባር ከሆነ ቆይቷል። ይህንንም ላለፉት ተከታታይ የእሑድ ሳምንታት ቅዳሴ እንዳይቀደስ በመረበሽ እና ቤተክርስቲያኑ ሲከፈት ደግሞ ካላይ እንደተጠቀሰው በጸያፍ ተግባር በመሳደብ እና ፊሽካ ጭምር በማጮህ ቤተክርስቲያንን በማወካቸው የዐቢይ ጾም ከገባ ጀምሮ አንድም እሑድ ቅዳሴ ማድረግ አልተቻለም። እዚህ ላይ ይህ የቤተክርስቲያን አማሽ ቡድን የህገረስብክቱ ሊቀ ጳጳስ ድጋፍ አለን በሚል ስለሚኩራሩ ''ምእመኑን ከቤተክርስቲያን እናስወጣለን '' የሚል ፉከራ ሲያሰሙ ለአፋቸው አያዳልጣቸውም።
የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ምእመናን በአማሾች ሲታመሱ ያደረጉት ምንድን ነው?
"እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።" (የሐዋርያት ሥራ 20:28) የሚለው ቃል ዛሬ በግሪክ በሚኖሩ ምእመናን ጆሮ ላይ የሚጮህ ድምፅ ነው። በግሪክ ምእመናን ለዓመታት አልቅሰዋል፣ገንዘባቸውን አውጥተው የገዙትን ገዳም ገዳም አድርጎ የሚባርክላቸው አባት አጥተው ተንከራተዋል፣ ለቤተክርስቲያን ያወጡት ገንዘብ በሌቦች ተወስዶ ከሌባ ጋር ሲተናነቁ ከሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በተጻፈ ደብዳቤ ለሰረቁት የእውቅና ደብዳቤ እየተሰጠ ባለፈው ዓመት ምእመኑን ሲያገለግሉ የኖሩት ካሕናት ስልጣነ ክሕነታቸው ''ከምእመን ያለፈ ስልጣን የሌለው ግለሰብ በጻፈልኝ ደብዳቤ መሰረት'' በሚል ለመያዝ ማስፈራርያ ተጽፏል። ቤተክርስቲያኒቱ ከግሪክ የሃይማኖት ሚኒስቴር ጋር የሚኖራት ግንኙነት በድብቅ እና የአማሹ ቡድን በሚሰሩት ደባ የታጀለ በመሆኑ በአሁኑ ጊዜ የቤተክርስቲያኒቱ ክብር በግሪክ ቢሮዎች ውስጥ ዝቅ ያለ እንዲሆን የራሱን አስተዋጽኦ አድርጓል። ሌላው ቀርቶ አሁን በፖሊጎኖ የምትገኘው የኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ከባለቤቷ የግሪክ ቤተክርስቲያን ጋር ያለው ግንኙነት ቤተክርስቲያኒቱን ለአማሹ ቡድን ለመስጠት በሚደረገው አድሏዊ ሕገወጥ ግንኙነት ምክንያት የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን ክብር ዝቅ የሚያደርግ ግንኙነት በመደረጉ ከፍተኛ ቅሬታ እንዲፈጠር ሆኗል።በእዚህም ሳብያ የግሪክ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪም በጉዳዩ ተማረው ቅሬታ አቅርበዋል።
ሌላው ቀርቶ ቅዱስ ሲኖዶስ የአቴንስ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ እንዲሆኑ የመደባቸው አባት ሊቀስልጣናት አባ ኪሮስ ፀጋዬ ወደ ግሪክ መጥተው አገልግሎት እንዲጀምሩ ለማድረግ የሚደረግ የድጋፍ እንቅስቃሴ ከሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስም ሆነ ከሀገረስብከቱ አንጻር የሚታይ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ አይታይም።ጉዳዩ የቤተክርስቲያን መሆኑ ቀርቶ የአማሽ ቡድኑ ጋር በሚደረጉ ሕገወጥ እና ቤተክርስቲያንን ማዕከል ያላደረገ ግንኙነት የህገር እና የቤተክርስቲያን ክብር ጉዳይ መሆኑ ቀርቶ ተራ የእልህ እና የሴራ ትብተባ ውስጥ እንዲገባ ሲሞከር ይታያል። ይህ ልብ የሚሰብር በግሪክ የምትገኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰቆቃ ድምፅ ነው።ጉዳዩን ቅዱስ ሲኖዶስ በአንክሮ እና በአፋጣይ ማየት ያለበት ጉዳይ ነው።የምንናገረው ስለየግል ጉዳይ አይደለም ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለተሰቀለበት፣ስለተገረፈበት እና ስለሞተበት የምእመናን ጉዳይ ነው። ስለሆነም ማንንም ሳያፍሩ እና ሳይፈሩ እውነቱን መናገር ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው።
በአሁኑ ጊዜ የምእመናኑ አንድነት እና ሕብረት የበለጠ ጠንክሮ ወጥቷል።
''ክርስቲያን እና ሚስማር ሲመቱት ይጠብቃል።'' እንዲሉ፣ በግሪክ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምእመናን ቤተክርስቲያናቸው ላይ የሚሰነዘሩትን የአማሳኞች ጥቃት ለመመከት ብቻ ሳይሆን ቤተክርስቲያኒቱ ወደ ግማሽ ክ/ዘመን ያህል ከአንድ ሰንበት ትምሕርት ቤት ባልበለጠ አነስተኛ ቤተክርስቲያን የመቆየቷ ቁጭት ጨምሮ እና በአጠቃላይ ወደየተሻለ አገልግሎት ለማሸጋገር ከመቼውም ጊዜ በላይ ቆርጦ የተነሳበት ጊዜ አሁን ነው። እንደ አንድ ምእመን አገላለጥ ''ኪዳነ ምሕረት የቤተክርስቲያኒቱ የቆዩትም፣ድንገት ደራሾችም፣ባዳውም ሆነ ባንዳው ተለይቶ ጠልሏል።የጠለለ ነገር እዳው ገብስ ነው።'' እንዳሉት ምእመናን በግሪክ የምትገኘውን ቤተክርስቲያን ከአጽራረ ቤተክርስቲያን እና ከአማሽ ቡድን ለመገላገል የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሷል።ለእዚህም ሁሉም የድርሻውን ለመወጣት ከመቼውም ጊዜ በላይ ተነስቷል። የአማሽ ቡድኑ የአማንያኑን የትሕትና መንገድ ሁሉ ከበጎ ከመመልከት ይልቅ በተሳሳተ መንገድ መመልከታቸው የስሌት ችግር ካልሆነ በቀር ሌላ ሊሆን አይችልም። ስሌት ክፉ ነው።ቤተክርስቲያን ከሕይወት በላይ ነች። የእዚህን ምእመን ኃይማኖታዊ መነሳሳት ቅዱስ ሲኖዶስ የጎደለውን በመሙላት፣የሃገረ ስብከት ችግርን በመፍታት እና ለቤተክርስቲያኒቱ የተመደቡትን አባት በፍጥነት ወደ ግሪክ የሚመጡበትን ማናቸውንም መንገድ በመጠቀም እና በማሳካት አስፈላጊው ሁሉ እንዲከናወን በግሪክ የሚኖሩ ምእመናን ጥያቄ ነው።
======================////===========
======================////===========
No comments:
Post a Comment