ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, October 31, 2017

ለኦስሎ፣ኖርዌይ የቤተ ክርስቲያን ጨረታ በተጨመሩት ጥቂት ቀናት ምዕመናን ተጠቅመው የቤተ ክርስቲያንን አቅም ማጠናከር እንዲቀጥሉ ተጠየቁ።

በኦስሎ፣ኖርዌይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስት ተዋህዶ ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የህንፃ ጨረታ ምዕመናን በተራዘሙት ጥቂት ቀናት በመጠቀም የቤተ ክርስቲያንን አቅም እንዲያጠናክሩ ተጠየቁ።ይህንን የጠየቀው የቤተክርስያኒቱ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ጋር በጥምረት የሚሰራው የህንፃ ኮሚቴ ነው። ጨረታው የተራዘመበትን ምክንያት ኮሚቴው ማምሻውን በቫይበር ግሩፕ ለሚከታተሉት ምዕመናን በኢሜል ያስታወቀ ሲሆን የጎፈንዱ አካውንትም (የጎፈንዱን አካውንት ለመክፈት ይህንን ይጫኑ)  እስከ ጨረታው መጀመርያ ቀን ድረስ እንደሚቆይ ለማወቅ ተችሏል። የህንፃ ኮሚቴው ማምሻውን የላከው ኢሜል ከእዚህ በታች የሚከተለው ነው።


ሰብሕዎ ለአምላክነ (መዝሙር) ያድምጡት 




ጉዳያችን GUDAYACHN

 www.gudayachn.com

Saturday, October 28, 2017

ኦስሎ ኖርዌይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የምትጫረተው ጥንታዊ ቤተ ክርስቲያን ሀገር ቤት ያሉት ገዳማት የነገ ጥሪት ነው







  • ነገ የቤተ ክርስቲያን አንድነት ተመልሶ አባቶቻችን በአንድነት ቤተ ክርስቲያንን ሲያስተዳድሩ የቤተ ክርስቲያናችን እያንዳንዱ በውጭ ያፈራቸው ሀብት በማዕከል ይተዳደራል።
  • ሁሉ ነገር በድረ ገፅ አይፃፍም።የመገንዘብ አቅማችንን ተጠቅመን ጉዳዩን እንረዳው። 
  • በተለይ በአሜሪካ እና ሌላው ዓለም ያላችሁ እየተለመናችሁ ያላችሁት ለማክዶናልድ ከምታወጡት 20 እና 30 ዶላር ነው።
  • በእዚህ ቤተ ክርስቲያን ግዥ ሳቢያ ቤተ ክርስቲያን በውጭ ማዕከሏ የምታደርገው ሐዋርያዊ ጉዞ ያድጋል፣ የኢትዮጵያ ተሰሚነት ይጨምራል።
  • በሁሉም መልክ ተፅኖ ፈጣሪነት ያሳድጋል።ይህ እንግዲህ ከመንፈሳዊው ጥቅም በዋናነት እንዳለ ሆኖ ማለት ነው። 
  • እኛም ማሰብ ያለብን የነገዋን ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚሰራ ስልታዊ ሥራ ላይ ነው። 
  • ከስልታዊ ስራዎች ውስጥ አንዱ በውጭ ሃገራት እንደዚህ ቁልፍ የሆኑ ቦታዎች እና ታሪካዊ አብያተ ክርስቲያናትን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ንብረት እንዲሆን መስራት ነው። 
  • ቤተ ክርስቲያን የከፈተችው ጎፈንድ ሊንክ ከእዚህ በታች ተያይዟል። አነሰ የሚባል የለም።የእኔ የሻይ ምን ሊሰራ ነው ማለት ግን ከብዛት ለውጥ እንደሚያመጣ አለማሰብ ነው።



ኦስሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለሃያማኖት ቤተ ክርስቲያን ከሶስት ቀናት በኃላ በኦስሎ ለሽያጭ የቀረበ በ1900 ዓም እ ኤ አ የተመሰረተ ቤተ ክርስቲያን ለመጫረት በዝግጅት ላይ ነች።የቤተ ክርስቲያኒቱ ምዕመናን በግላቸው ከመበደር አንስቶ ባላቸው አቅም እየተረባረቡ ነው።የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ይህንን ቤተ ክርስቲያን በጨረታ ማሸነፍ ማለት ብዙ ነገር ማለት ነው።

በመጀመርያ ደረጃ አሁን ላለው ምእመን በእርጋታ አምልኮት የምፈፅምበት እና አሁን በአብነት ትምህርት ላይ ያሉትን ጨምሮ የበለጠ ልጆችን ማፍራት የመቻሉ ጉዳይ አንዱ እና የቅርብ ጥቅሙ ነው። ክዚህ ባለፈ ግን በሰሜን አውሮፓ ወደፊት ቤተ ክርስቲያን ለምታደርገው ሐዋርያዊ አገልግሎት ቁልፍ ሥራ ነው።አሁን እዚህ ሀገር ተወልደው የሀገሩን ባህል እና ልማድ ሁሉ ጠንቅቀው የሚያውቁ ልጆች የቤተ ክርስቲያኒቱን ትምህርት ከአባቶቻቸው እግር ስር መማራቸው ነገ ለሐዋርያዊ አገልግሎት እንዲነሱ እና ለአውሮፓ የተረፈ ሥራ ለመስራት እንደሚችሉ ምንም ጥርጥር የለውም።አውሮፓ በሃይማኖት የሚያድነው የሚፈልግበት ሰዓት ነው። የእዚህ ትውልድ ሥራ ነገ ህፃናቱ አድገው ለሚሰርቱ ሥራ ቁልፍ የሆነውን ህንፃ አዘጋጅቶ መጠበቅ ነው።
በሌላ በኩል አንዳንድ ምእመናን ይህ ቤተ ክርስቲያን ሀገር ቤት ላሉት ገዳማት የሚፈይደው ነገር እንደሌለ ይገምታሉ።ይህ ፈፅሞ አላዋቂነት ነው።ነገ የቤተ ክርስቲያን አንድነት ተመልሶ አባቶቻችን በአንድነት ቤተ ክርስቲያንን ሲያስተዳድሩ የቤተ ክርስቲያናችን እያንዳንዱ በውጭ ያፈራቸው ሀብት በማዕከል ይተዳደራል።ያን ጊዜ አሁን የገዛነው ህንፃ ዋጋው ይጨምራል።ቤተ ክርስቲያን በውጭ ማዕከሏ የምታደርገው ሐዋርያዊ ጉዞ ያድጋል፣ የኢትዮጵያ ተሰሚነት ይጨምራል።በሁሉም መልክ ተፅኖ ፈጣሪነት ያሳድጋል።ይህ እንግዲህ ከመንፈሳዊው ጥቅም በዋናነት እንዳለ ሆኖ ማለት ነው። 

አባቶቻችን በኢየሩሳሌም ገዳማትን ያላቸውን ጥሪት እየያዙ ስገዙልን እና ለትውልድ ሲያስተላልፉ የኖሩት ለመጪው ትውልድ ነው። እኛም ማሰብ ያለብን የነገዋን ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚሰራ ስልታዊ ሥራ ላይ ነው። ከስልታዊ ስራዎች ውስጥ አንዱ በውጭ ሃገራት እንደዚህ ቁልፍ የሆኑ ቦታዎች እና ታሪካዊ አብያተ ክርስቲያናትን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ንብረት እንዲሆን መስራት ነው። 
የኦስሎ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የመጫረት አቅሟ ከፍ እንዲል በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንዲያግዙ እና ትኩረት እንዲሰጡት ይህ በአሜሪካ እና ሌላው ዓለም እንዳለው ያለ ጉዳይ አይደለም ቁልፍ የቤተ ክርስቲያኗ ጉዳይ ነው።

ሁሉ ነገር በድረ ገፅ አይፃፍም።የመገንዘብ አቅማችንን ተጠቅመን ጉዳዩን እንረዳው። በተለይ በአሜሪካ እና ሌላው ዓለም ያላችሁ እየተለመናችሁ ያላችሁት ለማክዶናልድ ከምታወጡት 20 እና 30 ዶላር ነው።ሁላችሁም የእኔ ትንሽ ነው ሳትሉ ማድረግ ከቻላችሁ የቤተ ክርስቲያን የመወዳደሯ አቅም ከፍ ይላል። በአጥብያችሁ ብዙ ቀዳዳ ይኖር ይሆናል።ለሀገር ቤት ገዳሞቻችን ሁሉም እኩል የመርዳት አቅም የላቸውም። የኦስሎው በተለየ መልክ ተመልከቱት።አሁን ለጨረታ የተለያዩ አካሎች የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ለመፎካከር እየመጡ ነው። ጉዳዩን ትኩረት ሰጥታችሁ አሁን ባሉት ሶስት ቀናት ውስጥ የአቅማቹን ብታደርጉ ለውጥ እናመጣለን። ቤተ ክርስቲያን የከፈተችው ጎፈንድ ሊንክ ከእዚህ በታች ተያይዟል። አነሰ የሚባል የለም።የእኔ የሻይ ምን ሊሰራ ነው ማለት ግን ከብዛት ለውጥ እንደሚያመጣ አለማሰብ ነው።ይህንን ጨረታ አስመልክቶ ይህ የመጨረሻ ፅሁፍ ነው።መቼም በድረ ገፅ የማይፃፉ ብዙ ነገሮች አሉ (ይህ ማለት ለቤተ ክርስቲያን ያለው ጥቅም አንፃር ከእዚህ ሀገር ሕግ አንፃር   ቤተክርስቲያኒቱን ለመፎካከር እየመጡ ያሉትን ማለት ነው) እና እባካችሁ ለቤተ ክርስቲያናችሁ ስልታዊ ሥራ ስሩ ይህንን ጨረታ አግዙ ከማለት ሌላ ምን አይነት ንግግር መናገር ይቻላል። እግዚአብሔር ምስጢሩን ይግለጥልን  እንጂ።
የጎፈንድ አካውንቱ ሊንክ http://www.eotcnor.no/በመላው-ዓለም-ለምትኖሩ-ኢትዮጵያውያን-አ/

የቤተ ክርስቲያኒቱ ድረ-ገፅ http://www.eotcnor.no

ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Wednesday, October 25, 2017

Vi vil gjerne kjøpe Gamlebyen menighetshus



I Faderens,Sønnens og Helligåndens navn Amen

Vi har i flere år satset på å skaffe oss passende bygg til gudstjenester, søndagsskole, veiledning, leksehjelp, fest, samlinger, døp, møter og seminarer. Denne uken (uke 42) har vi fått en sjelden mulighet til å kjøpe Gamlebyen menighetshus, som er satt ut til salgs. Ansvarlige i vår menighet har vært på visning, og anser lokalene I Gamlebyen menighetshus som egnet for vår kirke.

Vi vil gjerne kjøpe Gamlebyen menighetshus. I den forbindelse setter vi nå i gang denne innsamlingskampanjen. Vi ber om deg eller dere som får denne e-posten om hjelp. All hjelp mottas med takknemlighet og ydmykhet.

Bankkontonr.: 15034581883
BIC: DNBANOKKXXX
Elektronic IBAN: NO2115034581883
IBAN for use in print: NO21 1503 4581 883
Kontakt: 99479730/91139611

Med vennlig hilsen!

Biskop Hiryakos
Leder for den etiopiske ortodokse kirken i Norge St.Gabriel og Abune Teklehaymanot kirke
Assistant Biskop for etiopiske ortodokse kirker i Europa


ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Monday, October 23, 2017

ከሰሜን አውሮፓ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጥሪ!


አሁን ለቤተ ክርስቲያናችን ህንፃ ኮሚቴ በደረሰው ኢሜይል እና ስልክ መሰረት ቀድመው ከነበሩት በተጨማሪ ሌሎች ተጫራቾች በመምጣታቸው እና እነርሱም ቤተ ክርስቲያኑን በእራሳቸው መሀንዲስ ለማስመርመር እስከ መጪው ማክሰኞ ድረስ ጊዜ ስለጠየቁ ጨረታው በአንድ ሳምንት ተገፍቷል:: ስለሆነም እባካችሁ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ንብረት ለማድረግ ለምናውቃቸው ሁሉ ነግረን በተሻለ አቅም እንድንቀርብ እንትጋ::እስካሁን ለለገሳችሁ እግዚአብሔር ዋጋችሁን አያስቀርባችሁ።



በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቁስ አሐዱ አምላክ አሜን።
በመላው ዓለም ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ ጥሪ! 

ይህንን በመደገፍዎ ኢትዮጵያ ሃይማኖትን ፣ቅርስን እና ታሪክን በአውሮፓ ምድር እንድትተክል በመርዳት እራስዎን የሂደቱ አካል አደረጉ ማለት ነው። 
++++++++++++++++++++++++++++++
በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ በ1900 ዓም የተገነባ እና ጥንታዊ ይዘቱን ሳይለቅ በ1990ዎቹ በሚገባ የታደሰ በ730 ካሬ ላይ የሰፈረ ህንፃ ቤተ ክርስቲያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ለመግዛት ከፍተኛ ርብርብ ላይ ነች።ጨረታው በ72 ሰዓታት ውስጥ ይደረጋል።ለጨረታው የሕንፃ ኮሚቴ ካለው ገንዘብ እና የባንክ ብድር በተጨማሪ የተወሰነ ገንዘብ ያስፈልገዋል።ቅርሱ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ባለፈ ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ አንደምታ አለው። ስለሆነም በመላው ዓለም የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ይህንን ለጥቂት ሰዓታት የተከፈተ ጎ ፈንድ አካውንት የአቅማችሁን በመስጠት ከበረከቱ ተካፈሉ። ይህንን በመደገፍዎ ኢትዮጵያ ሃይማኖትን ፣ቅርስን እና ታሪክን በአውሮፓ ምድር እንድትተክል በመርዳት እራስዎን የሂደቱ አካል አደረጉ ማለት ነው።

በኖርዌይ ኦስሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅዱስ ገብርኤል አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ህንፃ አሰሪ ኮሚቴ 
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ከበረከቱ ለመሳተፍም ሆነ የታሪኩ አካል ለመሆን ከስር የተለጠፈውን ተጭነው በ''ጎፈንድ'' አካውንት አስተዋፅኦ ያድርጉ።
እስካሁን ለለገሳችሁ እግዚአብሔር ዋጋችሁን አያስቀርባችሁ። ከእዚህ በታች ያለውን ሊንክ ተጭነው የበኩልዎን ትንሽ ነው ሳይሉ ይለግሱ።






ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Sunday, October 22, 2017

በኦሮምያ ቡኖ በደሌ የዓማራ እና ትግራይ ተወላጆች መታረዳቸው ዛሬ ተሰምቷል። ከእዚህ ሁሉ ጀርባ 'አስረሰሽ ምች' ባዮች እነማን ናቸው?


  • ዜናዎቹ  (ፎክስ ኒውስ፣ዋሽንግተን ፖስት እና አሶሼትድ ፕሬስ ምን አሉ?)
  • በግጭቶቹ  ሳቢያ 'አስረሰሽ ምች' ባዮች እና 
  • መፍትሄዎቹ 
ጉዳያችን / Gudayachn
ጥቅምት 13/ 2010 ዓም  ( ኦክቶበር  22/ 2017)

የጉዳዩ መነሻ 

በኢትዮጵያ ላለፉት 26 ዓመታት የተደገሰው እና የተፈተለው የጎሳ ፖለቲካ ወደ ከረፋ ደረጃ እየደረሰ ነው።ከእነ ክርፋቱ አብረውት ታቅፈው እሹሩሩ የሚሉት ከባህር ማዶም ሆነ ከአራት ኪሎ እንዲሁም ከአዳማ ከተሞች ንፁሃን ላይ እልቂት እያወጁ ነው።በዛሬው እለት ብቻ በርካታ ቁጥር ያለው ሕዝብ ዐማራ፣ትግራይ እንዲሁም መጤ  ነህ በሚል ብቻ በአሰቃቂ  አገዳደል ተገድሏል።የቀረው በሽሽት ወደ እምነት ቦታዎች እና ጫካ ሸሽቷል።

1ኛ/ ዜናዎቹ  (ፎክስ ኒውስ፣ዋሽንግተን ፖስት፣ ኢኤንኤን እና አሶሼትድ ፕሬስ ምን አሉ?)

የዛሬውን ዜና  ፎክስ ኒውስ ዜና እንዲህ ይነበባል  ''በኢትዮጵያ በቀጠለው ፀረ መንግስት ተቃውሞ በኦሮምያ ክልል 11 ሰው ተገደለ ሁኔታው ወደ ብሔር ግጭት እያመራ ነው'' ሲለው ዋሽንግተን ፖስት ትናንት ምሽት ላይ " የአሜሪካ ወዳጅ ሀገር ኢትዮያ የጎሳ ፖለቲካ ያሰጋታል።ድብቁ የእሩቅ ገጠራማ ቦታዎች ጦርነት በመቶዎች የሚቆጠሩ ገድሎ መቶ ሺዎችን አሰድዷል'' በማለት ገልጧል።
አሶሼትድ ፕሬስም በዛሬው ዘገባው በበኩሉ 11 ሰዎች በኦሮምያ ክልል መገደላቸውን ከገለጠ በኃላ የኦሮምያ ክልል መንግስት ቃል አቀባይ በኦሮምያ ቡኖ በደሌ 8 የኦሮሞ ተወላጆች እና 3 የአማራ ተወላጆች መገደላቸውን የኦሮምያ ክልል ቃል አቀባይ አቶ አዲሱ አረጋ በፌስ ቡክ ገፃቸው ላይ ለጥፈው መነበቡን ይገልጣል። 

አሶሼትድ ፕሬስ በመቀጠል እንዲህ ይላል '' 100 ሚልዮን ሕዝብ ያለባት ሀገር ላይ የጎሳ ፖለቲካ መሰረት ያደረገ ፖለቲካ መንግስት በማራመዱ በሶሻል ሚድያ ሳይቀር መንግስት በከፍተኛ ሁኔታ እየተወቀሰ ነው'' (''Reports of the latest killings in the Oromia region came amid widespread social media accusations against the government for running an ethnic- based administration on this east African nation of more than 100 million people.'' Associated Press)
አፍቃሪ ህወሓት እንደሆነ የሚታማው ኢኤንኤን የስፖርት ፕሮግራም አቁሞ ዛሬ በሰበር ዜናው ባልተለመደ መልኩ  ''መጤዎች በሚል ዓማራ ናችሁ እየተባልን እየተገደልን ነው ፣ ሕዝብ በእየጫካ እየተበተነ ነው አንገታቸው እየተቆረጠ ተጥሏል'' የሚል መልዕክት በቴሌቭዥን ሰበር ዜናነት አሰምቷል።ለመሆኑ ከእዚህ ሁሉ ጀርባ የፖለቲካ ትርፈኞች እንደሆኑ እያሰቡ 'አስረሽ ምቺው' የሚሉት እነማን ናቸው?
  
2ኛ/ በግጭቶቹ  ሳቢያ 'አስረሰሽ ምች' ባዮች 
       
'አስረሽ ምቺው' ባይ ቁጥር አንድ 

በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ባለንበት ሰዓት ሁለት ኃይሎች በኢትዮጵያውያን ህብረት እና ፍቅር ስጋት ላይ ወድቀዋል።ይህ በግልጥ መታወቅ ያለበት ነው።ይህንን ጉዳይ ተደባብቀን እና አለባብሰን ማለፍ መፍትሄ አይሆንም።እነኝህ በኢትዮጵያውያን ህብረት ስጋት ያደረባቸው ኃይሎች የመጀመርያዎቹ በውጭ በፅንፈኛ የኦሮሞ ብሔር አቀንቃኝነት የሚታወቁት ናቸው።እነኝህ ክፍሎች ሰሞኑን የተነሳው በኦሮምያ የተነሳው ህወሓት ከስልጣን ይውረድ ጥያቄ እኛ ያልወጠወጥነው ነው በሚል ስሜት እኛ ይህንን አመፅ  አናውቀውም አላስተባበርንም በሚል ከእዚህ በፊት የቀናት የስራ ማቆም አድማ ይጠሩ የነበሩ የዛሬው የጠነከረ የህዝብ ህብረት ግን እንዳስከፋቸው በግልጥ ሳያፍሩ ከባህር ማዶ ሆነው ተናግረዋል። ሌላው ቀርቶ ከኦሮምያ ክልል ወደ ጣና የዘመቱ ወዶ ዘማቾችን ጉዳይ የምንተፍረት ያህል '' ወዶ ዘማቾቹ በአካባቢ ጥበቃ ላይ  ለመስራት ነው ሌላ መልዕክት አይደለም '' የሚሉ ቃላት በጃዋር  ፌስ ቡክ ገፅ ላይ እስከመፃፍ ተደርሷል።

በጎሳ በቆሰለች ሀገር ውስጥ ከኦሮምኛ ተናጋሪ ወጣቶች የዐማራ ወንድሞቻቸውን ለመርዳት ጣና ድረስ መሄዳቸው በምን መልኩ ነው የአካባቢ ጥበቃ እንጂ የፖለቲካ አንድነት አይደለም የሚያስብለው? ይህ ለአንድ በፖለቲካ ሳይንስ ትምህርት ላለፈ ቀርቶ ለማንም ተራ ሰው በጎሳ ግጭት ለተወጠረች ሀገር ፖለቲካዊ መልክቱ እና አንድነቱ መገለጫ እንደሆነ ግልጥ ነው። የሚንሶታው ሰው ግን የአካባቢ ጥበቃ ጋር አያያዘው። በእርግጥ ከእዛ በማስከተል ''ፍቅር በፍቅር ሆነ'' የሚሉ መልክቶች ከገፁ ላይ አንብበናል። 

የህዝብ አንድነት የሚፈጠርበት ቀዳዳ ሁሉ ለማስፋት ለምናፍቅ ሕዝብ ግን አብሮ የኖረ ሕዝብ ያገናኘው የአካባቢ እንክብካቤ ነው ብሎ መፃፍ  በጦር የመውጋት ያህል ያማል።ይህ ማለት የህዝብ አንድነት የሚያሰጋቸው እና እነርሱ አመፁን ለመምራትም ዕድል የማይሰጣቸው ብቻ ሳይሆን በቅራኔዎች እና ያለፉ ታሪኮችን በማውራት በሚፈጠር ግጭት የፖለቲካ ኃይል የማሰባሰብ ዕድል እንዳላቸው የሚያስቡ የዛሬው እልቂት ሲፈፀም ቁጥር አንድ ተደሳቾች ናቸው። እነርሱ ማን ናቸው? ለሚለው ጥያቄ በውጭ ሀገር በፅንፈኝነት በኦሮሞ ስም የሚንቀሳቀሱ ብቻ ሳይሆኑ እራሳቸውን አዳማ እና ናዝሬት ላይ ተቀምጠው በንፁሃን ደም የፖለቲካ ቁማር የሚጫወቱ ናቸው።

'አስረሽ ምችው' ባይ ቁጥር ሁለት 

በቁጥር ሁለት የእዚህ አይነቱ ግጭት  በማራገብ ብቻ ሳይሆን ከ26 ዓመት በፊት የጎሳ ፖለቲካው ውጤት ምን እንደሚያመጣ የሚያውቀው እና ላለፉት 26 ዓመታት በተለይ በዐማራነት እየተመረጠ ሕዝብ ሲገደል፣ መሬታቸው እየተነጠቀ ሲባረሩ በፓርላማ የተጠየቁት አቶ መለስ ጨምሮ ሕግ እና ስርዓት ከማስከበር ይልቅ  ከጉርዳ ፈርዳ ሕዝብ ተሰደደ፣ ተገደለ ለምን? ተብሎ ሲጠየቁ አቶ መለስ ለፓርላማ በሰጡት መልስ '' ጉርዳ ፈርዳ ምስራቅ ጎጃም ስለመሰለ ነው፣ዛፍ እየቆረጡ ስላስቸገሩ ነው'' የሚል እንደ ነበር የምናስታውሰው ነው። ህወሓት በመንግሥትነት ተቀምጦ አባላቱ የመከላከያ እና ደህንነት ቁልፍ ቦታ ይዘው ሕዝብ በጎሳ እንዲያልቅ ሲደረግ ምንም የሕግ ማስከበር ሥራ አለመስራታቸው ብቻ ወንጀለኛ ያደርጋቸዋል።
  
 ከላይ ቁጥር አንድ እና ሁለት ላይ የተጠቀሱት አስረሽ ምችው ባዮች ተመጋጋቢዎች ናቸው።ሁለቱም የጎሳ ፖለቲካ አራማጆች ናቸው። ሁለቱም ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች ጋር በማንኛውም መንገድ ለጥቅማቸው ይደራደራሉ። ሁለቱም ኢትዮጵያዊ እሴቶች መጥፋት ላይ ይስማማሉ።ሁለቱም ለስልጣን ካልበቁ ኢትዮጵያ ''ብትንትኗ''  ይውጣ ባዮች ናቸው። ሁለቱም በሙስና በቀጥታም  በተዘዋዋሪ መንገድ ኢትዮጵያን  መዝብረዋል።ስለሆነም እርስ በርስ ይመጋገባሉ።

መፍትሄዎቹ  

ከመፍትሄው ውስጥ ቀዳሚው ነጥብ ይህ የጎሳ ግጭት በሁለቱ ተመጋጋቢ ክፍሎች  እንዳይዛመት ማድረግ ነው።በመቀጠል በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በጎሳ መለያየት ስልጣኑን ለማቆየት የሚሞክረውን ህወሓትም ሆነ ወደ ስልጣን መወጣጫው መንገድ በጎሳ ግጭት እና ህዝብን ከህዝብ በመለየት ነው ብሎ የሚያምነው መንተላጠያውንም ኦህዴድ ስር አድርጎ የመሸገው ክፍልን አምርሮ መቃወም እና እስከመጨረሻ ድረስ መታገል የግድ መሆኑን መረዳት ይገባል። 

እነኝህ ከላይ የተጠቀሱት ሁለት ክፍሎችን ታግሎ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ወደ ጤናማ መስመር ለማምጣት የሚፈልጉ ኃይሎች ደግሞ ሁለቱም ከላይ የተጠቀሱት ክፍሎች ውስጥም መኖራቸውን መረዳት እና እነርሱንም  አበረታቶ ወደ ኢትዮጵያ የፍቅር ማዕድ ማምጣት እና በሁለቱ ክፍሎች ውስጥ ያለውን የጥፋት ደዌ እንዲታገሉ ማብቃት ሌላው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው። ለምሳሌ በህወሓት ውስጥ የሚገኙ የጦር ሰራዊቱ አባላት ህወሓት የሚሰራውን ሸፍጥ የሚያውቁ ለለውጥ እንዲነሱ እና የህዝብ አደራ እንዳለባቸው ማስታወስ እና ለለውጥ ማገዝ እንዲሁም በኦህዴድ ውስጥ የተሰገሰጉ እና ከባህር ማዶ ሆነው ፀረ ኢትዮጵያዊ ዘመቻ ላይ የተጠመዱትን መሰረታዊ ባህሪ እና ማንነት የሚያውቁ ነገር ግን በኦህዴድም ውስጥ ሆነ በባህር ማዶው ፅንፈኛ ፀረ ኢትዮጵያዊነት ኃይል ዙርያ ያሉትን አሁንም ከማያዋጣ ብቻ ሳይሆን የባዕዳን እንዲሁም አንዳንድ ፅንፈኛ የመካከለኛ ምስራቅ ሀገሮች ተንኮል ያለበት መሆኑን እንዲገነዘቡ እና ለጋራ ሀገር እኩል መብት እንዲቆሙ በፍቅር መቀበል ያስፈልጋል።

ባጠቃላይ በኢትዮጵያ እየሆነ ያለው የፖለቲካ መልክ ውስብስብ እየሆነ መምጣቱ ቀድሞውንም የተገመተ ነው።አሁን እየሆነ ያለውም እንዳይሆን ስደቀምበት ከነበረው የተለየ አይደለም።ይህ ማለት ግን ቀላል ጉዳይ ነው ማለት አይደለም። የብዙ ስም ያሉ ዝምተኞች ወደ መሃል እየመጡ ሕዝብ ሊያስተምሩ፣ልያነቁ እና ሊሰሩ የሚገባቸው ቁልፍ የህብረት እና የፍቅር ተግባራት ላይ የበለጠ መትጋት ያስፈልጋል።ምንም መገራገጭ ቢገጥም በሕዝብ ደም የፖለቲካ ቁማር የሚጫወቱት ለፍርድ መቅረባቸው አይቀርም። ሕዝብ እነማን ምን እየሰሩ እንዴት እንዳጋደሉትም ፈልፍሎ ማወቁ አይቀርም። ስለሆነም ለማይቀር ፍርድ በሕዝብ ደም ከመታጠብ እራስን ማቀብ እና ለጋራ ህልውና መስራቱ የወቅቱ ጥያቄ ነው።በተለይ በከተሞች የሚኖረው ሕዝብ የበለጠ እልቂት እንዳይፈጠር ቀድሞ በእነማን ላይ መነሳት እንዳለበት ማወቅ እና መነሳት አለበት።በከተሞች የሚደረጉ የትግል መርሆዎቹ ለገጠሩ እንደ ማገር የሚሆኑ የጋራ ሃሳቦች ስለምፈልቁ ገጠሩን ማስደመሙ እና የተንኮለኞች ሰለባ እንዳይሆን ብርታት ይሆነዋል። 


ጉዳያችን GUDAYACHN 
www.gudayachn.com

Wednesday, October 18, 2017

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በኖርዌይ በቋሚነት ለመትከል እና ሰሜን አውሮፓን በቤተክርስቲያኒቱ እምነት ለማጥመቅ በመላው ዓለም ያሉ ኢትዮጵያውያንን ትጣራለች

ህንፃ ቤተ ክርስቲያኑ በቀይ ቀለም የሚታየውን ቦታ ሁሉ ይሸፍናል።

ጉዳዩ ምንድነው?

የኢትዮጵያውያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን በተመለከተ በኖርዌይ በእዚህ ሳምንት ለየት ያለ በጎ ጉዳይ ተከስቷል። ይሄውም በኦስሎ ከተማ ውስጥ ከከተማው እምብርት በቅርብ እርቀት ላይ የሚገኝ ካቴድራል ለሽያጭ ቀርቧል።ማስታወቂያው የወጣው ባሳለፍነው ሳምንት ውስጥ ነበር።ቀደም ብሎ  በኦስሎ የምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅዱስ ገብርኤል፣አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ላለፉት ሁለት ዓመታት በአዲስ መልክ የቤተ ክርስቲያን ህንፃ ኮሚቴ አሁን ቤተ ክርስቲያን በኪራይ ከምትገለገልበት ህንፃ የእራሷ ህንፃ እንዲኖራት እየሰራ ባለበት ጊዜ ነው ያለፈው ሳምንት በኖርዌይ የቅርብ ታሪክ ያልተሰማ የቤተ ክርስቲያን ሽያጭ ዜና የተሰማው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ኦስሎ ላይ ይህንን ህንፃ ገዛች ማለት ምን ማለት ነው?

አንዳንዶች ኢትዮጵያውያን በውጭ ሃገራት አብያተ ክርስትያናትን መግዛታቸው ለዘላለም ውጭ የሚቀሩ አድርገው ስለሚቆጥሩ የሚመስላቸው ስለሆነ ነው ብለው ያስባሉ።ጉዳዩ ግን ይህ ማለት አይደለም።በየትኛውም የዓለም ጫፍ የሚኖር የቤተ ክርስቲያን ግዥ ነገ ቤተ ክርስቲያናችን በአንድነት እና በህብረት የምትኖርበት ጊዜ በመላው ዓለም ባሏት ንብረቶቿ ከክርስቶስ ወንጌል በተጨማሪ እንደ ሀገር ያለን ተፅኖ ያድጋል። ይህ በኦስሎ ለሽያጭ የቀረበው ህንፃ በከተማው እምብርት ካለው ቅርበት አንፃር ለመጪው ትውልድም ሆነ አሁን ያለው ትውልድ ከሃይማኖት የራቀውን የሰሜን አውሮፓ ህዝብን በሃይማኖትም ሆነ በባህላችን በቀላሉ ለመድረስ የሚያስችለን፣ የኢትዮጵያን ስም ከፍ የሚያደርግ እና እዚህ ላይ ለመጥቀስ ጊዜ እና ቦታ የማይበቃቸው በርካታ ጥቅሞች አሉት።

ከ 700 ካሬ በላይ ስፋት ያለው ቤተ ክርስቲያን የምድር ክፍሎች እና ደረጃውን የጠበቀ አዳራሽ አለው 

አሁን የጨረታው ሂደት ምን ላይ ይገኛል?

የቤተክርስትያኒቱ የህንፃ ኮሚቴ የጨረታውን ማስታወቂያ ከሰማ ጀምሮ በርካታ ስራዎች ለመስራት ሞክሯል። በእጁ ያለውን የተቀማጭ ገንዘብ ጋር በተጨማሪ ከባንክ ብድር ለማግኘት፣ ከምእመናን ጋር ተከታታይ ስብስብሰባ ባለፈው እሁድ እና ዛሬ ምሽት በቤተ ክርስቲያን ከማካሄዱ በላይ በመጪው እሁድም ተመሳሳይ ምክክር ያደርጋል።

ጨረታው መቼ ነው?

ጨረታው የሚደረገው በመጪው ሳምንት ውስጥ ነው።

አሁን ያለው ችግር ምንድነው?

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ህንፃውን እንዳትገዛ እንቅፋት የሆነባት ከጨረታው መነሻ ገንዘብ  ማለትም 16 ሚልዮን የኖርዌይ ገንዘብ (2.5 ሚልዮን የአሜሪካ ዶላር ገደማ ) ውስጥ በብድር እና ቤተ ክርስቲያን ካላት ተቀማጭ ተደምሮ በጨረታው በበቂ መንገድ ተወዳድሮ የቤተ ክርስቲያን ንብረት ለማድረግ ጨረታው ከሚጠይቀው ገንዘብ 45% ገደማ የሚሆነውን ለማሟላት በኖርዌይም ሆነ በአውሮፓ እና አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ኖርዌይ ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የእራሷ ህንፃ መኖር ምን ማለት እንደሆነ  ተገንዝበው እግዚአብሔር ባመለከታቸው መልክ አስፈላጊውን ርብርብ እንዲያደርጉ ተማፅኖ ቀርቧል።



ይህ ጉዳይ የማይመለከተው እና የሚመለከተው አለ?

ይህ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ በየትኛውም እምነት ያለ ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያ ቅርስ ለመጪው ትውልድ መኖር አለበት ዛሬ ቤተ ክርስቲያናችን በሃይማኖት ያልተለያዩ በአስተዳደር ጉዳይ ብቻ በተለያዩ አባቶች ስር ብትሆንም ቤተ ክርስቲያን አንድ ስትሆን የሁላችን ሀብት ነው ብሎ አርቆ የማሰብ አዕምሮ የተሰጠው እና ንብረቱ መቸም ቢሆን መቼ የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ ንብረት መሆኑን የሚያምን አርቆ አሳቢ ሁሉ ቅሌን ጨርቄን ሳይል ሊረባረብበት የሚገባ ጉዳይ ነው።

ስለሆነም ትልቅ የኢትዮጵያዊነት ህብረት በመላው ኖርዌይ፣አውሮፓ እና መላው ዓለም የምንኖር ኢትዮጵያውያን የምናሳይበት አንዱ መገለጫችን ነው። በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ መድሃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን የአይሁድ ምኩራብ ሆኖ ያገለገለ ነበር።ቤተ ክርስቲያኑ ለሽያጭ ሲቀርብ ጥንታዊ የሆነ ቤተ ክርስቲያን ካልገዛው በዘመናዊ መልኩ ነን የሚሉ ቤተ ክርስቲያኖች እንዳይገዙት ግብፆችም ሆኑ አይሁዶቹ ኢትዮጵያ እንድትገዛው ድጋፍ አድርገዋል። ይህም ለሰው ልጅ ቅርስ ሁሉ ከመጨነቅ የመነጨ ነበር።ቤተ ክርስቲያኑ በ1990ዎቹ መጀመርያ አጋማሽ እንደተገዛ ሲኤንኤን ሳይቀር ´´ዎርልድ ሪፖርት´´በተሰኘ ፕሮግራሙ ላይ ልዩ ዘገባ ሰርቶ እንደነበር የእዚህ ፅሁፍ ፀሐፊ ያስታውሳል። አሁንም ይህ በአውሮፓ የሉተር ማዕከል በሆነች ሀገር ዋና ከተማ ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የእራሷ ህንፃ መያዝ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ከገባን ምንም አይነት ልዩነት ኢትዮጵያውያን ለቤተ ክርስቲያኑ እንዳይረባረቡ ሊያግዳቸው አይችልም።
የቤተ ክርስቲያኑ አንድኛው ክንፍ የሚገኘው መስኮት 

በኖርዌይ፣አውሮፓ፣አሜሪካ እና በመላው ዓለም ያሉ ምእመናን ባሉት ጥቂት ቀናት (ከመጪው ሳምንት መጨረሻ በፊት  ምን ያድርጉ?

ጉዳዩን በትክክል ከተገነዘብነው ይህ ጉዳይ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞችን ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነታቸው የሚኮሩ እና የኢትዮጵያ ወዳጆች የሆኑት ሁሉ ሊረባረቡበት የሚገባ ጉዳይ ነው። አንድ ኢትዮጵያዊ ተቋም (የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን) ኦስሎ እምብርት ላይ ይህንን የሚያህል ህንፃ ገዛች ማለት ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ የልጆቻችን ሀብት እና መኩርያ ነው።ከእዚህ በተጨማሪ ቋሚ ኤግዚብሽን በመክፈት የኢትዮጵያን የቱሪስት መዳረሻ ማስተዋወቂያ አንድ ሁነኛ ማዕከላችን መሆኑን መገንዘብ ይገባል። ስለሆነም ምእመናን የጉዳዩን ክብደት በሚገባ ከተገነዘቡ በኃላ በሚከተሉት መንገዶች በፍጥነት ማገዝ ይችላሉ።

1/  የህንፃ ኮሚቴውን በብድር ሂደቶች ወይንም ለእዚህ ተግባር የሚያግዙ ድርጅቶች ካሉ በቀጥታ በባለቤትነት እንዲያግዙ በመርዳት፣መረጃ በመስጠት፣ወዘተ 

2/ እግዚአብሔር ፀጋውን የሰጣቸው እነርሱ እና እግዚአብሔር በሚያውቀው እራሱ ከሰጣቸው ላይ በቀጥታ ገንዘብ በመለገስ  እና 

3/ ከእዚህ ሁሉ በፊት ደግሞ እግዚአብሔር ፈቃዱ እንዲሆን ጊዜ እና ሰዓት ሰጥተው በመፀለይ ናቸው።

ከእዚህ በታች የቤተ ክርስቲያኒቱ ህንፃ ኮሚቴ የባንክ ሂሳብ ቁጥር እና ፔይ ፓል ማያያዣ ከፍተው መመልከት ይችላሉ። በሊንኩ ላይ ከባንክ ሂሳብ ቁጥር በተጨማሪ የኮሚቴ አባላት ሙሉ ስም እና አድራሻ ስለተያያዘ ማናቸውንም ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።ስልኮቹ በሙሉ የሞባይል ስልኮች ሲሆኑ የኖርዌይ መግቢያ ኮድ ከፊት 0047 ማስገባት አይዘንጉ። የህንፃ ኮሚቴ በተመለከተ አስፈላጊ መረጃ ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ : -
ይህንን ሊንክ ይጫኑ - http://www.eotcnor.no/የሕንፃ-ኮሚቴ/ያግኙን/ 


የአቡነ ሕርያቆስ መልዕክት 


ጉዳያችን GUDAYACHN


 www.gudayachn.com

Tuesday, October 17, 2017

Do not stand with the dying regime of Ethiopia. Stand with the future politics of the land - unity and democracy.


Photo = OAKLAND INSTITUTE

ጉዳያችን /Gudayachn (www.gudayachn.com)
October 17,2017
Oslo, Norway

Ethiopia needs the special focus of an international community.  Free zone of terrorism, peace, and stability of the Horn of Africa, all have the direct and indirect link to the political, economic and social turmoil of Ethiopia. Currently, regarding Ethiopia, the sole choice that puts on international community´s table is to support and respect Ethiopia´s unity and hard way of travel to democracy. The current ethnocentric based regime led by TPLF (Tigray Peoples Liberation Front) is disintegrating by itself. In another way, it is dying the natural death of the dictators. In fact, the struggle of the people against TPLF brutal rule and its annex teams has already continued with a new and challenging full chapter. Its annex poppets organizations arranged themselves under the name of Amhara and Oromo ethnics of the country. For the last seven days only the speaker of the house, Aba Dulla and senior advisor and policy maker, since TPLF came to power, Mr. Bereket Semeon has left their office with unknown reasons.

 The internal and external political environment of Ethiopia is boiling in a real way. In this week, Ten thousand participated protests are going on in all part of the country including around the capital Addis Ababa. The regime is continuing to create new clashes among different ethnic groups. It is well believed by ordinary Ethiopians that the recent clashes between Ethiopian-Somali and Oromo ethnics were masterminded and secretly supported by TPLF top officials. Addis Ababa´s based opposition group called MEDREK had already disclosed as the regime was the main organizer to the mentioned clash which resulted for over one-hundred thousand Oromo ethnics displaced from Jijiga and other Ethiopian Somali regions to the high land area of Harare town.

There are some attempts that the international community is trying to challenge the regime to respect human rights condition. Human Rights Watch annual reports of 2015 and 2016 are typical examples of the challenges. In addition to that the US government is also mobilizing new initiative to impose on Ethiopian current government through H.Res 128 . However, the regime was ready to present its neck for the sake of its political power. US was told that if H.Res 128 will pass by the US Congress, TPLF is ready to cease all its cooperations with the international activities against terrorism in the horn of Africa. Therefore the legislation delays for some days but still active to be passed. It was quite clear any Government in our globe could not be allowed to put some precondition for the safety of its own people to protect from any form of terrorism. Protecting terrorism should not be presented for negotiation in terms of human rights issue. Because to respect human rights is nothing but an obligation of any government. However such normal way of thought is not applicable when we come to TPLF. It is just attempting to replace the life of the people with the extent of its political power for another dictatorial year.

To wind up the note, I think, the following four points should be taken into consideration by the international community and friends of Ethiopia and Ethiopians in all over the world. These are: - One, the TPLF regime is dying so fast both by its natural death after controlling an overall power of the nation for the quarter century and the struggle of the people. Two, the anti-terrorism struggle within the Horn of Africa will not be functional without the presence of democratic government in Ethiopia. The reason for that is terrorism could be protected mainly by the goodwill active participation of the entire people, not only by an act of few dictators within a non-functional government. Three, change is coming soon in Ethiopia. The important question is if the coming change could not assure the unity of the country, new clash and instability could have erupted and ugly form of a new chapter of the horn of Africa could be started. Four, it must be so clear that even if the current TPLF regime is trying to retain power through the assistance of the west, the situation will go from bad to worse. Therefore it is so crucial to the international community and friends of Ethiopia and Ethiopians to stand on the side of the people plus assist in all possible ways to keep the unity of the nation and transformation from a quarter century ethnocentric regime of TPLF to democratic one. Do not stand with the dying regime of Ethiopia. Stand with the future politics of Ethiopia. The future of Ethiopia is nothing but united and democratic political system.


ጉዳያችን GUDAYACHN  (www.gudayachn.com)
You can get the writer Getachew Bekele with an e-mail = getachewb221@gmail.com 

በኢትዮጵያ የእገታ ወንጀል ተሳታፊ አራት አካላት ናቸው። ለችግሩ የመፍትሄ አካላት ሁለት ናቸው።ሁለቱ አካላት ምን ይስሩ?

======= ጉዳያችን ======= በኢትዮጵያ ዜጎችን እያገቱ ገንዘብ የሚቀበሉ ወንጀለኞች ከተራ ወንጀለኝነት አልፎ በታጣቂ ቡድኖች የገንዘብ ማግኛነት መዋል ብቻ ሳይሆን ዜጎችን የማሸበርያ ፋሺሽታዊ ተግባር ሆኗል። እገታ የ...