ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, January 29, 2019

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን ከፍተኛ ባለሙያዎች ጋዜጣው መግለጫ ሰጡ።

ጉዳያችን / Gudayachn
ጥር 22/2011 ዓም (ጃንዋሪ 29/2019 ዓም)

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን  በአሜሪካና  አውሮፓ ካሉት ሶስት ስቱድዮዎች በተጨማሪ ኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ ስቱድዮ እንደሚያስመርቅ አክቲቪስት ታማኝ በየነ፣ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና  አበበ ገላው ዛሬ ጥር 21/2011 ዓም ዋሽንግተን ላይ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

በእዚሁ መግለጫ ላይም ጥር 22/2011 ዓም የጎፈንድ በቀጥታ ስርጭት በዋሽንግተን ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በኃላ ከ2 pm ጀምሮ እንደሚኖር እና የካቲት 9/2011 ዓም በአዲስ አበባ በሚገኘው የሚሊንየም አዳራሽ  የኢሳት 8ኛ ዓመት ልዩ መርሐግብር እንደሚኖር ተገልጧል።

በየካቲት 9/2011 ዓም ከሚደረገው የአዲስ አበባ  መርሃግብር ለመገኘት ወደ ሀገር ቤት ከሚያቀኑት ጋዜጠኞች ውስጥ ከዋሽንግተን አበበ ገላው ፣መሳይ መኮንን፣ ሲሳይ አጌና እና እንግዱ ወልዴ ሲሆኑ ወንድማገኝ ጋሹ ከለንደን  እና ዘላለም ኃይሉ  የሚገኙበት እንደሆነ በመግለጫው ላይ ተገልጧል።በሌላ በኩል ጋዜጠኛ ገሊላ እና መታሰቢያ በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ እንደሚገኙም  በመግለጫው  ላይ ተብራርቷል።
ሙሉ መግለጫውን ከስር ይመልከቱ።

ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

Monday, January 28, 2019

የታሪክ ምሑራን አንድ በሉን ETHIOPIAN JEWS TRIED TO SAVE EUROPEAN JEWS FROM HOLOCAUST

(የኢየሩሳሌም ፖስት ሙሉ ፅሁፍ ከአማርኛ ስር ያንብቡ)
የታሪክ ምሑራን  አንድ በሉን - ኢየሩሳሌም ፖስት የተሰኘው ዕድሜ ጠገብ የእስራኤል ጋዜጣ በዘመነ ሂትለር አይሁዶች በአውሮፓ እንዳይጨፈጨፉ በኢትዮጵያ የሚኖሩ አይሁዶች በጠየቁት መሰረት ነበር  የግሪክ ተወላጆች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ የተደረገው (ቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ በውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አጥንተው የወሰኑት ጉዳይ) ፈላሻዎች በጠየቁት መሰረት እንደሆነ የሚያትት ፅሁፍ በእዚህ ሳምንት ወጥቷል።ይህ ጉዳይ ተዛብቶ የቀረበ ይመስለኛል። ቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ እና መንግስታቸው በውጭ ፖሊሲው አውጥቶ አውርዶ የወሰነውን አይሁዶች ንጉሡን ጠየቁ የሚለው ጉዳይ  ትክክል ነው?
ቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ግርኮችን፣አርመኖችን  መጠግያ ሲሰጡ፣ አይሁድ ናችሁ ብለው የታሪክ ትርክት መኖሩን አላውቅም።በእድሜ ባንደርስበትም የግሪክ ሱቅ፣የአርመን ሱቅ ይባል እንደነበር ሰምተናል።ኢትዮጵያ ጥገኝነት ስትሰጥ ከአይሁድነታቸው  በተያያዘ ነው ወይ? ፈላሻዎችስ ማኅበራዊ ወይንም ፖለቲካዊ አደረጃጀት ያውም በ1940ዎቹ ገና የእስራኤል መንግስት ሳይመሰረት (እስራኤል በ1947 እ ኤ አ እንደመመስረቷ) ተደራጅተው አይህዶችን አምጡ የማለት የተደራጀ ድምፅ በንጉሡ ዘመን ነበራቸው ወይ? የታሪክ ምሁራን አንድ በሉን ኢትዮጵያ እንደመግስት የወሰነችው ውሳኔ ሁሉ የአይሁዳውያን ወይንም የፈላሻዎች ግፊት ነበር  እየተባለ ሊወሰድ ነው ማለት ነው?
ግሪክ ዋና ከተማ አቴንስ ውስጥ አቢሲንያ አደባባይ የሚባል አለ።ባለፈው ዓመት ወደዝያው በሄድኩበት ወቅት ይህ አደባባይ ግሪኮች  በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ማብቅያ ላይ አውሮፓ ረሀብ ላይ በነበረበት ወቅት አፄ ሃይለስላሴ ወደ አቴንስ ተጉዘው ረሀብ ላይ የነበረውን ሕዝብ ሰብስበው  ስጋ ወስደው ያበሉበት ቦታ ነው።የቦታውን ታሪክ እውነተኛነት ለማረጋገጥ በሱቆች የተከበበው እና መሃሉ ክብ አደባባይ ያለው ቦታ ሄጄ ባለሱቆቹን ለምን የአብሲንያ አደባባይ ተባለ? ብዬ ጠይቄ ነበር።ይህንኑ ታሪክ ነበር የደገሙልኝ። ይህ ማለት ግሪኮች ሲመጡ አይሁድነታቸው ተለይቶ ሳይሆን እንደሀገር የገባው ችግር ከመረዳት መሆኑን የሚያሳይይመስለኛል።ሆኖም ግን የታሪክ ምሁራን በበለጠ በጉዳዩ ላይ መፃፍ አለባችሁ። በታሪክ ግንባታ ኢትዮጵያ እንደሀገር በወጥነት የሰራችውን ሥራ ሌሎች እንደወሰኑት እና በሌሎች ተፅኖ የተሰራ ለማስመሰል የሚደረግ የታሪክ  ሽምያ ነገም እንዳየቀጥል ውስጣዊ አንድነታችንን የሚቃረን እንዳይሆን መጠንቀቅ ተገቢ ነው።ዛሬ ጋዜጣ ላይ የወጣ የነገ ፅሁፍ ማጣቀሻ ነው።ኢየሩሳሌም ፖስት ያወጣው ሙሉ ፅሁፍ ከእዚህ በታች ተለጥፏል።
===============
BY 
The Jerusalem post 
JANUARY 27, 2019



Ethiopian Jews suffered under the Italian occupation but by 1943 they were able to reach out to the emperor to suggest hosting Jews fleeing Europe.

August 1943, the height of the Holocaust, Ethiopian Jewish leaders approached the Emperor of Ethiopia with a daring proposal. They asked Haile Selassie to help Jews in Europe flee to Ethiopia and assist Jewish refugees by hosting them in Ethiopian Jewish villages.

Three months after the Warsaw Ghetto Uprising and two months after all four of the Auschwitz crematoria were functioning, the Palestine Post, ancestor of today’s Jerusalem Post, published an article detailing Jewish immigration to Ethiopia. “Possibilities of Jewish immigration into Abyssinia were discussed by the Ethiopian Minister in London with Mr. Harry Goodman and Dr. Springer of Agudath Israel,” the August 8, 1943 article says. “A leading member of the Falasha (black Jewish) community expressed the desire to assist European Jewry and to welcome them in Falasha towns.” Falasha was the term used to describe Jews in Ethiopia at the time.

Discussions were ongoing in Addis Ababa where the emperor, who had returned to Ethiopia in May 1941 after it was liberated from Italian occupation with British help, was showing support for the plan. 1,500 Greek refugees, including Greek Jews, had arrived in Ethiopia in 1943, the article says. Emperor Selassie had stayed at the King David Hotel in Jerusalem in 1936 and was familiar with the Jewish minority in his country. Selassie also worked closely with Orde Wingate, the British officer who was a passionate Zionist and who led Gideon Force which helped defeat the Italians in Ethiopia. Ethiopian leaders and the Ethiopian Jewish community were therefore familiar with the local Jewish community and the plight of Jews worldwide at the time.
ETHIOPIAN JEWS TRIED TO SAVE EUROPEAN JEWS FROM HOLOCAUST

Ethiopian Jews suffered under the Italian occupation but by 1943 they were able to reach out to the emperor to suggest hosting Jews fleeing Europe. By that time it was too late for many of the Jews of Europe ensnared in the Nazi noose. The full story of the 1943 effort to convince Ethiopia to re-settle Jews fleeing Europe has not been researched and details about it remain unknown. For instance Harry Goodman, who is mentioned in the article, was a well known member of the Orthodox Agudath Israel World Organization. He published articles in the Jewish Weekly and broadcast messages to Jews in Nazi-occupied Europe. 

There is an M.R Springer mentioned in some records connected to the Czech Jewish community in the UK at the time. Italian dictator Benito Mussolini even briefly considered resettling Jews in Ethiopia in the 1930s during the Italian occupation. At the time there were estimated to be more than 50,000 Jews in Ethiopia, many of them living in villages near Gondar. 

Source; - The Jerusalem Post

ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

Sunday, January 27, 2019

ኢትዮ-ሳውዲ ቢልዮነር ሼህ አላሙዲን ዛሬ ከእስር መፈታታቸው ተሰምቷል።

ጉዳያችን ዜና  /Gudayachn News 

ኢትዮ ሳውዲ ቢልዮነር ዶ/ር ሼህ አላሙዲን ከአንድ ዓመት በላይ ከታሰሩበት ከሳውዲ እስር ቤት መፈታታቸው ተሰምቷል።ዝርዝሩ ገና አልታወቀም።አላሙዲን ከመታሰራቸው በፊት የነበረችው ኢትዮጵያ በበርካታ ፖለቲካዊ ለውጥ ተለውጣ ትጠብቃቸዋለች።እራሳቸውን ከለውጡ ጋር አዛምደው እንደሚሄዱ የብዙ ኢትዮጵያውያን ተስፋ ነው። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አላሙዲን እንዲፈቱ ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸው ይታወቃል።
Ethio Saudi billionaire Mohammed Al amoudi (PhD) has just released from Saudi prison.
More development is coming.
ዶ/ር ሼህ አላሙዲን Mohammed Al amoudi (PhD) 
ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Monday, January 21, 2019

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአውሮፓ አህጉረ ስብከት ከስኖዶሳዊ አንድነት በፊት የነበሩ ችግሮች እየተቀረፉ ነው።(ጉዳያችን ዜና)

  • ለረጅም ጊዜ የቆየው  የጣልያን ሀገረ ስብከት ችግር አዲስ በተሾሙት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሕርያቆስ ብርቱ ጥረት በቅርቡ ተፈትቷል፣
  • የግሪክ ጉዳይ እልባት ለማግኘት ሂደት ላይ ነው፣
  • በጀርመን ያሉ አብያተ ክርስትያናትም የአንድነት ሀገረ ስብከት አዋቅረዋል።
በአቡነ ሕርያቆስ የደቡባዊ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የተመራው ስብሰባ ሮም፣ኢጣልያ ሲካሄድ 

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሀገራዊ የፖለቲካ ለውጡን ተከትሎ በቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች የረጅም ጊዜ ፀሎት  እና በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ ብርቱ ክትትል እና ጥረት ለሃያ ሰባት ዓመታት  የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተዳደራዊ አንድነት ከከፈለ በኃላ በቅርቡ ሲኖዶሳዊ አንድነቱ ተፈጥሮ ቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደራዊ አንድነቷን ለማስጠበቅ መቻሏ ይታወቃል።

በእዚሁም መሰረት ከስኖዶሳዊ አንድነቱ በኃላ የመጀመርያውና በቤተ ክርስቲያኒቱ ታሪክ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጳጳሳት ጉባኤ የተደረገበት የሲኖዶስ ጉባኤ ባለፈው ጥቅምት ወር 2011 ዓም አዲስ አበባ ቤተ ክህነት መደረጉ ይታወሳል።የሲኖዶስ ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜ ስለሚደረግ ቀጣዩ ስብሰባ በመጪው ግንቦት ወር (ለርክበ ካህናት) እንደሚደረግ ይታወቃል።
በአቡነ ሕርያቆስ የተመራው  ከሮሙ ጉባኤ ተሳታፊ አባቶች በከፊል 

የጥቅምቱ የሲኖዶስ ጉባኤ ካከናወናቸው ተግባራት ውስጥ የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አህጉረ ስብከት ድልድል ሲሆን በእዚህም መሰረት ለአውሮፓ ደቡባዊ ክፍል ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባልና የኦስሎ፣ኖርዌይ መካነ ቅዱሳን ወአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የበላይ ጠባቂ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የኖርዲክ ሀገሮች እና ሰሜን አውሮፓ ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ የጀርመን እና አካባቢው ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የእንግሊዝ ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ በመሆን መመደባቸው ይታወሳል።

የደቡባዊ አውሮፓ ማለትም ኢጣልያ፣ፈረንሳይ፣ግሪክ፣ቱርክና ቤልጅየም  ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሕርያቆስ በአጭር ጊዜ ከሁሉም ሀገረ ስብከት ካህናት እና ምእመናን ጋር በአካል እና በስልክ በመገናኘት ወደ ሥራ የገቡ ሲሆን፣ለዓመታት የቆየ ችግር የነበረባቸው የኢጣልያ እና የግሪክ ሀገረ ስብከት ችግሮችን ለመፍታት በአካል በመገኘት ቀናት የፈጀ ውይይት እና የቆዩ ቁርሾዎችን ለመፍታት ባደረጉት ጥረት በኢጣልያ የነበረው ችግር ካህናቱን በመሸምገል እና ሀገረ ስብከቱ ለዓመታት የነበረበትን መዋቅራዊ አሰራር ወደ አንድ እና ወጥ መልክ እንዲይዝ ለማድረግ ችለዋል። 

በእዚህም መሰረት ጥር 3 እና 4/2011 ዓም ሮም ላይ ከኢጣልያ፣ፈረንሳይ፣ግሪክ፣ቱርክና ቤልጅየም በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት በመጡ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ተወካዮች የሀገረ ስብከቱን ጠቅላላ ሰባካ ጉባዔ ስብሰባ የተደረገ ሲሆን በስብሰባው ላይ በበርካታ የሀገረ ስብከት አገልግሎት ሂደት እና አሰራር ላይ ከመነጋገሩም በላይ የአስተዳደር ጉባኤ መርጧል፣የክፍለ አህጉረ ስብከቱን መዋጮ መጀመር ላይ ወስኗል እንዲሁም የ2011 ዓም የአገልግሎት ትኩረት አቅጣጫ ላይ ለመወሰን ችሏል። ቀደም ብሎ በኢጣልያ ለረጅም ጊዜ የቆየ እና ምዕመናንን  በከፍተኛ ሁኔታ ሲያውክ የነበረው በሁለት አጥብያዎች መካከል የነበረው አለመግባባት በአቡነ ሕርያቆስ አባታዊ ምክር እና ልመናም ጭምር ጉዳዩ በይቅርታ መፈታቱ ምዕመናንን ያስደሰተ ተግባር ሆኖ አልፏል።

ቀደም ብሎ በታህሳስ /2011 ዓም እንዲሁ በግሪክ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን የጎበኙት የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ እና የስካንድንቭያ እና ሰሜን አውሮፓ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ በአቴንስ ከተማ የሚገኙ አጥብያ ቤተክርስቲያናት ያሉባቸው ችግሮች ዙርያ ከተወያዩ እና አባታዊ ምክር፣ግሳፄ እና ትምህርት ከሰጡ በኃላ፣እዚያው የሚፈቱትን ጉዳዮች ውሳኔ ከሰጡባቸው በኃላ  ሲኖዶሳዊ ውሳኔ የሚሹ ጉዳዮችን ወደዝያው እንደተመሩ ከምዕመናን የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ።በግሪክም ሆነ በኢጣልያ ብፁዓን አባቶች የቤተ ክርስቲያንን ችግር ለመፍታት በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ሁሉ የኢትዮጵያ ቆንስላ እና ኤምባሲ ኢትዮጵያን እንደመወከላቸው እና ቆንስላ እና አምባሳደሯ  አባቶችን ከመቀበል እና ችግሩን እንዲፈታ በማገዝ በኩል በጎ ተግባር እየፈፀሙ እንደሆነ መሰማቱ ሌላው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ የሆኑት አሻራዎች ላይ ሁሉ አለኝታነቱን የማሳየቱ ጅማሮ ተደርጎ ሊቆጠር ይችላል።

በተመሳሳይ መንገድ በብፅዕ አቡነ ዲዮናስዮስ የሚመራው የጀርመን እና አካባቢው ሀገረ ስብከት የምሥረታ ጠቅላላ ጉባኤውን በፍራንክፈርት ከተማ በሚገኘው በምስካዬ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ታህሳስ 6 ቀን 2011 ዓ.ም. ማካሄዱን ለማወቅ ተችሏል። ይህ ጀርመንን፣ ስዊዘርላንድን፣ ኦስትሪያን እና ሆላንድን የሚያጠቃልለው ሀገረ ስብከት በቁጥር ከ 30 በላይ የሚሆኑ አጥቢያዎችን የሚያስተዳድር ሲሆን ለዚህ ጉባኤ ከአብዛኛዎቹ አጥቢያዎች የመጡ የአድባራት አስተዳዳሪዎች እንዲሁም የሰበካ ጉባኤ፣ የካህናት እና የሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮች በአጠቃላይ ከ 90 በላይ ተሳታፊዎች ተገኝተውበታል። 
በጀርመን ሀገረ ስብከት ጉባኤው በአቡነ ድዮናስዮስ እየተመራ ሲካሄድ።

ባጠቃላይ በአውሮፓ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አህጉረ ስብከት ከስኖዶሳዊ አንድነት ወዲህ ሁለት ቦታ የነበሩትን ሀገረ ስብከቶች በአንድ በማካተት እና አስተዳደራዊ አካል እንደገና በአንድነት በማዋቀሩ ሥራ ላይ አመርቂ ሥራ እየተሰራ ነው።በአስተዳደራዊ አንድነት ሂደት ላይ ከመዋቅር በዘለለ ተግባራዊ አንድነት እና ምዕመናንን በአንድነት የማገለገል ተግባር ከእዚህ በፊት ክፍተት የሚያሳዩ ደንቦችን በማሻሻል እና በማረቅ ለበለጠ አገልግሎት መትጋት አሁንም ከሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላት ይጠበቃል። ዛሬ ዓለም በተለይ አውሮፓ ከእምነት በራቀ አሳዛኝ ሕይወት ውስጥ ይገኛል።የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ይህንን ተስፋ የጠፋበት አህጉር እንዴት ልትደርሰው ትችላለች?እነቅዱስ ጳውሎስ አውሮፓን የሰበኩት እንደዛሬው ኢንተርኔት ሳይኖር በእግራቸው እየሄዱ ነበር።ዛሬም ቤተ ክርስቲያን መንገዷ ረጅም መሆኑን ከአሁኑ ማወቅ አለባት።ለእዚህም በርካታ ውስጣዊ ስራዎች ይጠበቁባታል።የመጀመርያው ተግባር ቤተ ክርስቲያኒቱን ከሙስና በፀዳ መልክ የሰው፣የገንዘብ እና የንብረት ሐብቷን በቶሎ ማደራጀት ነው። ጊዜ የለም።



ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

Sunday, January 13, 2019

የጥምቀት በዓል በእዚህ ሳምንት መጨረሻ በመላዋ ኢትዮጵያ እና በባሕር ማዶ ይከበራል።በዓሉ የብሔራዊ አንድነታችን እና መተሳሰባችን አንዱ መገለጫ ነው።

  • ኦስሎ፣ኖርዌይም የበዓሉ ታዳሚ ነች። 
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን  በአደባባይ ከሚከበሩት በዓላት ውስጥ ጥምቀት አንዱ እና ዋናው ነው። ዘንድሮ የሚከበረው የጥምቀት በዓል በያዝነው ሳምንት ከዓርብ ጥር 10/2011 ዓም (ጃንዋሪ 18/2019 ዓም) ከቀትር በኃላ ጀምሮ ታቦታት ወደ ጥምቀተ ባሕሩ ወጥተው  በመላዋ ኢትዮጵያ እና በባሕር ማዶ በሚገኙ ኢትዮጵያን ዘንድ ይከበራል።በዓሉ የብሔራዊ አንድነታችን እና መተሳሰባችን አንዱ መገለጫ ነው።

በዓሉ በኦስሎ፣ኖርዌይ የኢትዮጵያ ኦ/ተ/መካነ ቅዱሳን ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያንም በድምቀት ይከበራል።በበዓሉ ላይም የደቡብ አውሮፓ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የሚገኙ ሲሆን መምህር ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ ከኢትዮጵያ  በስብከተ ወንጌል ያገለግላሉ።

ጥምቀት አዲስ አበባ ቪድዮ (ከዩቱብ ፋይል)

ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

Friday, January 11, 2019

የህወሓት የጎሳ ጥብቆና የጠባብነት ቀለበት ወራሾች

ጉዳያችን / Gudayachn
ጥር 3/2011 ዓም (ጃንዋሪ 11/2019 ዓም)



ኢትዮጵያን ትልቅ ሀገር ለማድረግ ከህወሓት በፊት የነበሩት መሪዎች የራሳቸውን አሻራ እያስቀመጡ ሄደዋል። ለኢትዮጵያ ጥብቆ ያሰፋ እና የጠበበ ቀለበት ውስጥ ያስገባት ህወሓት ለመሆኑ ክርክር የሚያነሳ የለም።ዛሬ ላይ ቆመን ልናነሳ የሚገባን ጥያቄ የአሁኑ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ህወሓት በሰፋለት ጥብቆ እና ቀለበት ውስጥ ነች ወይንስ አይደለችም? የሚለው ነው።


ህወሓት ለኢትዮጵያ ያሰፋው ጥብቆ እና ቀለበት

ታሕሳስ 7/1953 ዓም  መንግስቱ ንዋይ እና ገርማሜ ንዋይ የመሩት የመፈንቅለ መንግስት እንቅስቃሴ ላይ እኩለ ቀን ሲሆን በኢትዮጵያ ራድዮ ሲታወጅ እንዲህ የሚል ቃል ተነበበ።
''...አሁን በቅርብ ጊዜ ነፃ የወጡት የአፍሪካ አገሮች ከቀን ወደ ቀን በኢኮኖሚ፣በትምህርትና በኑሮ መሻሻል ፈጣን እድገት አድርገው ኢትዮጵያን አልፈዋት ሄደዋል።'' ካለ በኃላ የራድዮ መልዕክቱ ሲደመድም '' የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ አንድነትህ ከብረት የጠነከረ ይሁን! የዛሬዋ ዕለት ለኢትዮጵያ አዲስ ጎህ መቅደዱን ለመላው ዓለም የምታበስር ናት!'' ይላል።

ይህ የራድዮ መልዕክት በኢትዮጵያ ራድዮ ከተላለፈ ሃምሳ ስምንት ዓመታት አለፉ።ጥያቄው ግን አሁንም አለ።ለነፃነታቸው የቆምንላቸው የአፍሪካ ሀገሮች በእጅ አዙር ቅኝ ግዛት የወደቁበት ደረጃ ቢለያይም ቢያንስ በነፍስወከፍ ገቢ ትተውን የሄዱት የአፍሪካ ሀገሮች ቁጥር ቀላል አይደለም።በድህነት እና ኃላ ቀርነት ሀገራችን የኖረችበት ዋናው ምክንያት የፖለቲካው ጉዳይ አለመስተካከል መሆኑ የታወቀ ነው።ኢትዮጵያ ግን በብዙ ውጣ ውረድ አልፋም ቢሆን በሀገርነት ኖራ እዚህ ደርሳለች።ሆኖም ግን ኢትዮጵያ በቀደሙ ዘመናት ከገጠማት ፈተና ሁሉ የከፋው በህወሓት የተሰፋላት የጎሳ ጥብቆ እና የጠባብነት  ቀለበት ውስጥ ሀገሪቱ የገባችበት መከራ ነው።ጥብቆው ስለ ጎሳህ ብቻ እንድትዘምር እና በጠበበ ቀለበት ውስጥ እየኖርክ ሰለ ትልቅ ኢትዮጵያ እንዳታስብ የሚከለክል እኩይ መመርያ አለው።

ይህ ኢትዮጵያዊ ሁሉ እንዲገባበት የተሰፋለት የጎሳ ጥብቆ እና  የጠባብነት ቀለበት አሁን ባለው የኢትዮጵያ የለውጥ ፖለቲካ ላይም የራሱን ጥላ አጥልቷል። ለውጡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ፣ አቶ ለማ እና አቶ አንዳርጋቸው ቡድን እውን ሲሆን በመጀመርያ ግብግብ የገጠመው ህወሓት ለኢትዮጵያ ያሰፋውን የጎሳ ጥብቆ እና የጠባብነት  ቀለበት የመስበር እንቅስቃሴ ላይ ነው። ይህንኑ ጉዳይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መጋቢት 24/2010 ዓም የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን መንበር ሲረከቡ ባደረጉት ንግግር ጥብቆው እና ቀለበቱ ላይ ያነጣጠረ ሰፊዋን ኢትዮጵያ ደግሞ በመደመር የስሌት ቀመር  ህወሓት ለኢትዮጵያ ያሰፋውን የጎሳ ጥብቆ እና  የጠባብነት ቀለበት በአደባባይ እርቃኑን አስቀሩት።

ከመጋቢት 24/20110 ዓም የጠቅላይ ሚኒስትር  ዓብይ ንግግር በኃላ ሚልዮኖች ኢትዮጵያውያንን ከጎናቸው አሰለፈ።ከገጠር እስከ ከተማ ሕዝብ ደስታውን የገለጠበት ነጥብ የህወሓት የጭቆና ሰንሰለት መበጠሱ ብቻ አይደለም።የህወሓት የጎሳ ጥብቆና የጠባብነት ቀለበት መበጠሱ ነው ከሁሉም በላይ ህዝብን ያስደሰተው።እውነታው ይህ ነው።ሆኖም ግን የጎሳ ጥብቆውና የጠባብነት ቀለበት በቀላሉ የማይነቀል የሃያ ሰባት ዓመት ትክል መሆኑን ያወቁት የለውጥ ኃይሉ መሪዎች ጥብቆውን እና ቀለበቱን በአንድ ጊዜ ከመቅደድ እና ከመስበር ይልቅ በሂደት በማስተማር እና እራሳቸውን  በአንድ ጊዜ ጥብቆውን አውልቀው ከመቅደድ የታቀቡበት ምክንያት መሬት ላይ ያለውን የጥብቆ እና የቀለበት ትክል በሂደት ለመንቀል ነው።

የጥብቆው እና የቀለበቱ ወራሾች የለውጡ ረባሾች

የህወሓት የጎሳ ጥብቆ እና የጠባብነት ቀለበት ለውጡ ከመጣ በኃላም ሊጠፋ ያልቻለበት ዋናው ምክንያት የህወሓት ወራሾች የጎሳ ጥብቆውን እና  የጠባብነት ቀለበቱን ይዘው ኢትዮጵያን ወደ አደገኛ መንገድ እየመሯት ነው።ጥብቆውና ቀለበቱ የሕዝብ ፍላጎት አይደለም። ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታትም ሆነ ባሳለፍናቸው ጥቂት የለውጥ ወራት ውስጥ ሁሉ የጎሳ ጥብቆው እና የጠባብነት ቀለበቱ ኢትዮጵያን እንደሀገር ከማቆርቆዝ ባለፈ የብዙ ዜጎች ሕይወት በጥብቆው እና ቀለበቱ አፍቃሪዎች  እረግፏል። አስገራሚው ጉዳይ የጎሳ ጥብቆውና የጠባብነቱ ቀለበትን ከህወሓት የወረሱት ቡድኖች በዓማራ፣በኦሮሞ፣በትግራይ እና በሌሎች ስም እየማሉና እየተገዘቱ እንዲሁም ለመንደራቸው ዘብ የቆሙ መሆናቸውን በማወጅ የህወሓት ውላጆች መሆናቸውን እያስመሰከሩ ይገኛሉ።በኢትዮጵያ ውስጥ አንዳች ችግር ሲፈጠር የእነርሱን መንደር ካልነካ ላይጮሁ፣ የመንደራቸው ልጅ ከተነካ ግን  የጎሳ ጥብቆ እና የጠባብነት ቀለበታቸውን ይዘው በመውጣት ፍጅት ያውጃሉ።

ጥብቆውን የቀደደ እና ቀለበቱን የሰበረ ዋንጫውን ይወስዳል

የኢትዮጵያ ሕዝብ በህወሓት የጎጥ ጥብቆ እና የጠባብነት ቀለበት ውስጥ የገቡ የፖለቲካ ቡድኖች ላይ የሚነሳበት ቀን እሩቅ አይደለም።አንዳንዶች ይህ ውሸት ይመስላቸዋል።ጉዳዩ ግን የጊዜ ጉዳይ ነው።እስካሁንም ያልተነሳበት ስለ ሁለት ምክንያት ነው።አንዱ፣ የሲቪክ ድርጅቶች እና አክትቪስቶች ኢትዮጵያዊነትን በሚገባ አለማንቀሳቀሳቸው እና ብሔራዊ ፀረ የጎሳ ጥብቆ እና የጠባብነት ቀለበት ንቅናቄ ባለመደረጉ ሲሆን ሁለተኛው ህወሓት የዘራው የእርስ በርስ የጎሳ ጥርጣሬ እንዲፈጠር ከህወሓት ባላነሰ መልክ ውላጅ ወራሾቹ የዘሩት ዘር ነው።

በመጪዋ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ አረፋ ኩፍ ያሉቱ የጎሳ ጥብቆ እና የጠባብነት  ቀለበት አራማጆች ቦታቸው እየጠበበ እንደሚመጣ ለመረዳት ብዙ ምርምር አይጠይቅም።የጥብቆው እና የጠባብነት ቀለበት አራማጆች ትግራይ የሚኖረውን ሕዝብ ዓማራ ጠላትህ ነው፣ኦሮሞ ደመኛህ ነው ይሉታል፣ዓማራው ውስጥ ያሉት የጎሳ ጥብቆው እና የጠባብነት ቀለበት ወራሾች ዓማራ ታራራውን እና ወንዙን ሳይቀር ዓማራ የሚል ቀለም እንቀባው ቀረሽ ቅራኔ እየፈጠሩ ሕዝቡን  የማገት ያህል ሌላ የፖለቲካ አስተሳሰብ እንዳይኖረው ቢያስብም እንደማይፈቀድለት ለመንገር ሲዳዳቸው ይታያሉ። በኦሮምያም ያሉት የጥብቆው ወራሾች ከስደት የመጡት የፖለቲካ ድርጅቶቻቸው የጥብቆው እና የጠባብነት ቀለበቱን ይዘው በሕዝቡ ላይ ለመንዛት እየተንገታገቱ ነው።ይህ ሁሉ የጎጥ እና የጠባብነት ወራሽ ደግሞ የለውጥ ሂደቱን ለማወክ በጎሳቸው ስም እየተገዘቱ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ለመዘወር የሚያደርጉት ከንቱ ሙከራ ሁሉ በሕዝብ ንቅናቄ ፈፅሞ እንደሚከሽፍ ፈፅሞ አያንጠራጥርም።

መጪዋ ኢትዮጵያ  ህወሓት የሰፋላትን የጎጥ ጥብቆ ቀዳዳ ትጥላለች።የጠባብነት ቀለበት ሰብራ ትጥላለች።የህወሓት የጎሳ ጥብቆ ለብሰው ኢትዮጵያን  በመንደራቸው ልክ ለማጣበቅ የሚፈልጉ እና በጠባብ ቀለበት ውስጥ ለማስገባት እና ኢትዮጵያን ወደየማያባራ የእርስ በርስ ግጭት ለመምራት የተዘጋጁ ኃይሎች በቀጥታ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር የሚፋጠጡበት ወቅት ደርሷል። የጎሳውን ጥብቆ ተርትሮ እና የጠባብነት ቀለበቱን ሰብሮ በኢትዮጵያዊ ሰገነት ላይ የቆመ ደግሞ ከኢትዮጵያ ሕዝብ የክብር ዋንጫውን ይቀበላል።ይህ ማለት የጥብቆው እና የጠበብነት ቀለበት ወራሾች መንገጫገጭ አይፈጥሩም ማለት አይደለም።መንገጫገጩ የህዝብ ሕይወት ይቀጥፋል።ሲሆን ጥብቆውና እና ቀለበቱን ጥለው ወደ ሰፊው ሃገራዊ ሜዳ ቢመጡ የበለጠ ባማረ ነበር።የጥቅም፣የስልጣን እና የመተዳደርያ ጉዳይ ከሆነ ግን ጥብቆውን እና ቀለበቱን እንደያዙ ሕዝብ ይደርስባቸዋል።

ለማጠቃለል ጥብቆውን መቅደድ እና ቀለበቱን መስበር የወቅቱ ጥያቄ ነው።የለውጡ ሐዋርያዎችም በድፍረት የመቅደዱን እና የመስበሩን ተግባር በዓላማ ደረጃ እንዳስቀመጡ ሁሉ ተግባሩን መጀመር ግን አለባቸው።የጎሳ ጥብቆ እና የጠባብነት ቀለበት ኢትዮጵያን እንደ ግመል ሽንት ወደኃላ የሚጎትታት ክፉ የዘመን ነቀርሳ ነው።ሰሆነም ሰዎቹን ትተን ሀሳባቸው ካልመከነ ኢትዮጵያ አደጋ ላይ ነች።ምንም አይነት ስም ቢሰጠው፣ ሃያ ሰባት ዓመት የተተከለ የጎሳ ጥብቆ እና የጠባብነት ቀለበት የህወሓት ስሪት መርዝ ነው።ኢትዮጵያ ትቀጥላለች።ጥብቆውን የሚቀድላት፣ ቀለበቱን የሚሰብርላትን እየጠበቀች ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ፣አቶ ለማ እና አቶ አንዳርጋቸው እና የለውጡ ኃይል በአንድነት ጥብቆውን የማውለቅ እና ቀለበቱን የመስበር ሥራ በይፋ ጀምሯል።የጥብቆው እና የቀለበቱ ወራሾች ግን በተቃዋሚ ስም ከህወሓት ያልተናነሰ የጎሳ ፖለቲካ እና የጠባብነት ቀለበታቸውን በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በአዲስ መልክ ለመጫን የሚሞክሩ ሁሉ ሀሳባቸው መና ካልሆነ አሁንም አደጋ ላይ ነን።የለውጡ ኃይል ጥብቆውን መቅደድ፣ቀለበቱን መስበር ኢትዮጵያዊነትን ማንገስ መሆኑን በግልጥ በጅማሮው አሳይቶናል።አቀዳደዱን እና አሰባበሩን ግን በጥንቃቄ ለማድረግ ቅዳጁም ሆነ ስባሪው የኢትዮጵያን ሕዝብ እግር እንዳይወጋ እየተጠነቀቀ እንዳለ ይገባናል።የሁሉም አካል እገዛ ግን ያስፈልጋል።የጎሳ ጥብቆውን የቀዳደደ እና የጠባብነት ቀለበቱን የሰበረ የዋንጫው ባለቤት ነው።የዋንጫው ሸላሚ ደግሞ ሕዝብ እና ሀገር ነው።

ጉዳያችን / Gudayachn 
www.gudayachn.com


































































ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com


Sunday, January 6, 2019

ከደብረብርሃን እስከ አንኮበር ያለው መንገድ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ተጀመረ።

ጉዳያችን/ Gudayachn
ታኅሳስ 28/2011 ዓም (ጃንዋሪ 6/2011 ዓም)
================
ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት የነበረው አገዛዝ ግልጥ የሆነ ብሔራዊ ጭቆና በልማት ስራዎች ላይ ሲያሳርፍ ታይቷል።ከደብረ ብርሃን አዲስ አበባ ያለውን የአስፋልት መንገድ ለመስራት ከአስር ዓመት በላይ  ያውም መንገዱ ከተቆፋፈረ በኃላ ፕሮጀክቱ ሲጎተት እንደነበር የአደባባይ ምስጢር ነው።ይህ ሕዝብ የሚያወራው እና 'ፀሐይ የሞቀው' በደል ነው።ስለቱሪዝም በሚወራባት ሀገር በርካታ ቅርሶች ያላት አንኮበር ከተማን ከደብረ ብርሃን ለማገናኘት አንድም ሥራ ሳይሰራ መኖሩ ብዙዎችን ብዙ አስብሏል።የቀደሙት ገዢዎቻችን በቢልዮን የሚቆጠር ዶላር ሕፃን ልጅ እንደፈረፈረው ደረቅ ዳቦ ሲጫወቱበት ሕዝብ በአቧራ መንገድ እየሄደ ለአይን ትራኮማ በሽታ ይዳረግ ነበር። በሀገራዊ ሀብት እኩል ተጠቃሚነት የሚለው አነጋገር ለቅንጡ የቀደሙት  የህወሓት ገዢዎች በቀላሉ አይገባቸውም።የተገፋው ሕዝብ ግን ያውቀዋል።
የደብረ ብርሃን አንኮበር መንገድ በአቧራ ተሸፍኖም በርካታ ቱሪስቶች አስቸጋሪውን መንገድ እየሄዱ ቦታውን ለመጎብኘት ጥረት አድርገዋል።አሁን በዶ/ር አብይ ዘመን የመንገዱ ሥራ መጀመሩን የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን አሳይቷል። ቪድዮውን ከስር ይመልከቱ።
ቪድዮ = ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ታኅሳስ 28/2011 ዓም 


ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com

ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።