ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, January 30, 2014

አሜሪካ በኢትዮጵያ ጉዳይ ተነቃቃች …ወይንስ ?(አጭር ማስታወሻ)



አሜሪካ ዘግይታም ቢሆን በኢህአዲግ ላይ የምታደርገውን ድጋፍ ቀስ በቀስ ለመሳብ እያሰበች ይመስላል።በሳምንቱ ውስጥ አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምትሰጠው እርዳታም ሆነ ድጋፍ የዜጎችን ከመሬታቸው መፈናቀል የሚያስከትል እንዳይሆን ቅድመ ሁኔታ እንዲኖረው መወሰኑ በተነገረ በቀናት ውስጥ የኢትዮጵያ መንግስት የሰብአዊ መብት ካላከበረ በቀር  ለፖሊስ እና ለጦር ኃይል ከአሜሪካ የሚሰጠው ድጋፍ በቅድመ ሁኔታ ስር እንዲሆን ወስኗል።

አሜሪካ  ይህንን ለማድረግ 23 አመታት ብትዘገይም ለዛሬው እርምጃ መጀመር ግን ምክንያቶቹ ከእዚህ በታች ከተዘረዘሩት የትኞቹ ይሆኑ?

1/ በድንገት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማሰብ ጀምራ?

2/ የቻይና በኢትዮጵያ መንሰራፋት ለአፍሪካም የተረፈ መሆኑ አስግቷት?

3/ ኢትዮጵያውያን በዋይት ሃውስ ደጃፍ ለአመታት ያደረጉት ሰልፍ በድንገት ትዝ ብሏት?

4/ የኢትዮጵያ ሕዝብ በኢህአዲግ አሰራር መማረሩን እና መቁረጡን ስላወቀች?

5/ የኢትዮጵያ ሁኔታ ወደባሰ መስመር የመሄዱ አዝማምያ ለአካባቢው አለመረጋጋት መዘዝ ስላለው የአካባቢ አረጋጊ ኃይል ላለማጣት?

6/ የድል አጥብያ አርበኛ ለመሆን?

መልሱ በሂደት የሚታይ ነው።

ላለፉት 23 አመታት ኢህአዲግ ሲታሰብ አሜሪካም አብራ ነበረች።ይህ ሀቅ ነው።ኢትዮጵያ የጎሳ ፖለቲካ ሲታወጅባት ጉዳዩ አደገኛ መሆኑን በትንሹ ለጎሳ ፖለቲከኛ መንግስት ስትናገር ብንሰማት ጥሩ ነበር። የሆነው ሆኖ የዛሬ የአሜሪካ መነቃቃት ደስ የሚል ነው።አሜሪካ ግን ተነቃቃች ማለት የሚቻለው ለኢትዮጵያ አንድነት፣የግዛት ሉአላዊነት እና የባህር በር ባለቤትነት የማያወላውል አቋም ስታሳይ ነው። ኢትዮጵያ ከፊቷ የሚጠብቁ ብዙ ጉዳዮች አሏት እና ዛሬ ማለት የሚቻለው አሜሪካ በርታ በይ ቀጥይ ገና ነሽ ይመስለኛል።

Monday, January 27, 2014

ሰማያዊ ፓርቲ ከመጪው አርብ ጀምሮ ነገረ ኢትዮጵያ የተሰኘ የድረ-ገፅ ጋዜጣ ሊጀምር ነው።



የጋዜጣውን መጀመር አስመልክቶ ዛሬ የሰማያዊ ፓርቲ በፌስ ቡክ ገፁ ላይ እንዲህ የሚል ፅሁፍ አስነብቧል-

''ሰማያዊ ፓርቲ በቅርቡ ነገረ ኢትዮጵያ የተሰኘች የህዝብ ልሳን የሆነች ጋዜጣ ለማሳተም ዝግጂት እያደረገ የነበረ ሲሆን ዝግጂቱን አጠናቆ ወደ ማተሚያ ቤት ከገባ በኋላ ግን ከፍተኛ የሆነ ስልታዊ ማደናቀፍ እየደረሰበት በመሆኑና ለጊዜው ማሳተም ባለመቻሉ ሰሞኑን በድረ-ገፅ መልቀቅ የምንጀምር መሆኑን እናስታውቃለን።
አርብ ይጠብቋት''


Sunday, January 26, 2014

የሱዳን መንግስት አስደማሚ ያላቸውን ለውጦች በፖለቲካ እና በምጣኔ ሀብት አንፃር እንደሚወስድ አስታወቀ።በ 48 ሰዓታት ውስጥ የለውጡን ዝርዝር የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር ሐሰን አልባሺር ለህዝባቸው የቀጥታ ንግግር በማድረግ እንደሚገልጡ እየተጠበቀ ነው።ባንፃሩ ኢትዮጵያ 'የጎሳ ፖለቲካ' አራማጅ መንግስቷ ለለውጥ ''ውሃ ቢወቅጡት... '' ሆኗል።


የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር ሐሰን አልባሺር

የሱዳን ታዋቂ ጋዜጣ 'ሱዳን ትሪቡን' የፕሬዝዳንቱ እረዳት እና የገዢው ፓርቲ -ብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር እብራሂም ጋንዶርን ጠቅሶ ካለፈው አመት ጀምሮ መንግስታቸው ሲያዘጋጀው የነበረውን ዝርዝር የለውጥ ይዘቶችን ፕሬዝዳንት ኦማር ሐሰን አልባሺር በ 48 ሰዓታት ውስጥ እንደሚገለፁ  ገልጧል።ጋዜጣው የሚገለፀው ለውጥ አስደማሚ እና ስር ነቀል ለውጦችንም ያካተተ ጥገናዊ ለውጦች መሆናቸውን ለማወቅ መቻሉን ያትታል።
ከለውጦቹ ውስጥ -

- ከሀገር ውስጥ ተቀናቃኝ ባላንጦች ጋር በአዲስ ህገመንግስት ያካተተ እርምጃን ጨምሮ የሰላም ስምምነት ላይ መድረስ፣ 

- ሃሳብን የመግለፅ መብት፣ነፃ ማኅበራት እና የፖለቲካ ድርጅቶች የመመስረት ሙሉ መብትን ማጎናፀፍ፣

- ከሀገሪቱ ሀብት የተገለሉትን ዜጎች የሀብት ተካፋይ እንዲሆኑ ማድረግ እና የፀረ-ድህነት መርሃግብሮችን በመላ ሀገሪቱ መተግበር፣ 

- ሁሉም ዜጎች በዜግነታቸው ብቻ እኩል መብት እንዲኖራቸው ማድረግ የሚሉትን ነጥቦች እንደሚያካትት ይገልፃል።

ዝርዝሩ የለውጥ መርሃግብር ግን ፕሬዝዳንቱ በ 48 ሰዓታት ውስጥ እስኪገልፁ ድረስ ሱዳኖች ነቅተው እና ተግተው እየጠበቁ ነው።

ሃገሩን የሚወድ መንግስት ቅድምያ የሚሰጠው እርካሽ ለሆነ የመንደር የጎሳ ፖለቲካ ሳይሆን ለመላ ዜጎቹ ነው። ኢትዮጵያ ከሱዳን በባሱ ብዙ ውስብስብ ችግር ውስጥ (የጎሳ ፖለቲካ በሚያራምደው ኢህአዲግ/ወያኔ ሳብያ) መግባቷ ይታወቃል። ሆኖም ግን እንደ ሱዳን ከልብ የሆነ እርምጃ ለመውሰድ መነሳሳት ቀርቶ በብሄራዊው ቲቪ ህዝብን ከህዝብ ለማናከስ መርዘኛ የሆኑ ፊልሞችን 'ዶክመንተሪ' በሚል ስም እያሰራጨ መሆኑ ይታወሳል። ለእዚህም ማስረጃ የሚሆነው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የጥምቀት በዓል በምታከብርበት ዋዜማ የእስልምና እምነት ተከታዮችን በክርስቲያን ወንድሞቻቸው ላይ እንዲነሱ የሚቀሰቅስ ፊልም ሲያሳይ ማምሸቱን መጥቀስ ብቻ ይበቃል።ከሱዳን ጭንቅላት ያነሰ አስተሳሰብ የያዘ መንግስት እንዳለን መዘንጋት የለብንም።

የሱዳን መንግስት የሀገሩን ችግር ለመፍታት የተነሳሳበትን ሁኔታ ውስጥ ተገብተን የኢህአዲግ/ወያኔን መንግስት ስንመለከተው ፍፁም የበሰበሰ አስተሳሰብ ውስጥ የተዘፈቀ ምንም የተሻለ አስተሳሰብ ሊያመነጭ የማይችል ይልቁንም ኢትዮጵያን ወደባሰ መቀመቅ ውስጥ ለመክተት ቆርጦ የተነሳ ለመሆኑ የእየለት ተግባሩን ብቻ በመመልከት ማወቅ ይቻላል።ባንፃሩ ኢትዮጵያ 'የጎሳ ፖለቲካ' አራማጅ መንግስቷ ለለውጥ ''ውሃ ቢወቅጡት... '' ሆኗል።

የሱዳን ትሪቡን ዘገባ ቅጅ ከእዚህ በታች ይመልከቱ -

anuary 25, 2014 (KHARTOUM) – The Sudanese presidential assistant and deputy chairman of the ruling National Congress Party (NCP) for party affairs Ibrahim Ghandour disclosed today that President Omer Hassan al-Bashir will deliver a speech at a rally in the coming 48 hours to announce details of the reform document that his party has been working on since last year.

Ghandour said during a television interview on Saturday that his boss would unveil a new approach on all political, security and economic matters in the framework of a unified country.

Sudanese officials have for months been talking of an initiative being worked on by Bashir that would radically alter the political landscape and accommodate all parties and groups in the country.

The visiting United States former president Jimmy Carter told reporters after meeting with Bashir on Tuesday that the latter informed him of his intention to declare "important" political decisions in the coming days but offered no details.

Some aspects of the lengthy reform document prepared by the NCP was revealed by the al-Ayam newspaper and included

Reaching peace with internal rivals through dialogue that would also be incorporated in a new constitution;

Democratic transformation that would see the people enjoying freedom of association, freedom to form political parties and freedom of expression among others;

Launching a program for poverty reduction that would eliminate claims of marginalization;

Resolving the issue of the country’s identity and making citizenship the basis of all rights

The Doha-based Al-Jazeera television website reported that Bashir will offer a "surprise" in his announcement which caused a flurry of speculations that focused on whether the 70-years old leader will step down and hand over power to his newly appointed 1st Vice President Bakri Hassan Saleh.

Some observers predicted that Bashir would dissolve the parliament and form a national transitional government while a new constitution is being drafted.

But Ghandour dismissed all these projections as illogical saying they are a result of wild imagination given the upcoming 2015 elections and the NCP general convention scheduled later this year. He further said that the current government is a national one even if not all parties are represented.

"What I am reading is like fiction plays as the resignation of the president is out of question and the quitting of the president in this manner cannot be expected by any sane person as we are heading to elections. The president will not escape [from responsibility] in this fashion," Ghandour stressed.

"It was described as a surprise and it is really a programme presented by a respectable president hoping for reconciliation of his people," he added.

Bashir met on Wednesday with the son of the Democratic Unionist Party (DUP) leader Mohamed al-Hassan al-Mirghani and other party figures to lay out his vision for reform. He is expected to hold further meetings with other opposition parties on the same subject.

Ghandour also denied the existence of secret or even public dialogue with the Popular Congress Party (PCP) of Hassan al-Turabi as was reported recently though he expressed hope that channels of communications between the two sides can be established noting that they have no disagreements about application of Islamic Sharia’a law, free economy and Islamic proselytizing.

The PCP creation was a result of a split within the Islamists in the late 1990’s that saw Turabi, who masterminded the 1989 coup led by Bashir, moving to become the most vociferous critic of the government.

Despite numerous attempts by internal and external mediators to bring the two sides together they have remained irreconcilable foes.

The PCP political Secretary Kamal Omer said today that they reject the idea of forming a national government with participation of certain parties only insisting that no force should be excluded and particularly rebel groups that form the Sudan Revolutionary Front (SRF).

Omer said that the PCP political secretariat met on Saturday and affirmed the party’s relationship with the other opposition groups forming the National Consensus Forces (NCF) to resolve Sudan’s crises.

He stressed that contacts with the SRF are continuing describing it as important and fundamental for the next political transformation in the country. He said that the meeting also emphasized the need for a transitional period to rebuild the Sudanese state on a new basis and move the country from a state party to the nation state .

The NCF chairman Farouk Abu-Issa a separate statements said that they will not budge on their goal to topple the regime.

Abu-Issa said that a solution to the current crisis in the country is within reach as the NCP acknowledged its failure and is working on a roadmap that was previously set by the opposition to run the country under a transitional government.

He stressed that the NCP resorting to what he described as "under the table" deals will not work adding that they did not delegate anyone to negotiate on their behalf with the ruling party.

On the economic front Ghandour stressed that the government is keen not to see a repetition of the crisis which led to a shortage in fuel, cooking gas and bread pointing out that Sudan spends billions to provide basic commodities to the citizens.

He also said that the fluctuations in US dollar exchange rates happens for many reasons and that the black market traders follow statements by Sudanese officials to decide on prices adding that the central bank and finance ministry are working to bring back the exchange rate back to normal.

Last week traders in the black market said that 1 US dollar was selling for 8.20 pounds compared 8.00 in the beginning of the week. They also projected further drop in light of low forex supplies held by the central bank as well as growing fears over fighting in neighboring South Sudan and its potential for disrupting oil flow.

On the South Sudan crisis, Ghandour said that the government had refused to pour oil on the fire of war in the south. He instead affirmed Sudan’s support for the Intergovernmental Authority on Development (IGAD) initiative to resolve the crisis in the south and the legitimate government in Juba.

The Sudanese official expressed hope that interference of foreign countries in the ongoing fighting in reference to Uganda’s dispatching of troops to fight alongside South Sudan army (SPLA) against rebels led by former vice-president.
Source - Sudan Tribune http://www.sudantribune.com/spip.php?article49720   

Thursday, January 23, 2014

ሰበር ዜና - የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኞች የተኩስ አቁም ለማድረግ ከጥቂት ሰዓታት በፊት ተስማሙ (ጉዳያችን ጡመራ Gudayachn Blog)

Photo South Sudan News Agency -Negotiating teams in a past session, Addis Ababa, Ethiopia. Photo credit: Larco Lomayat


የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኞች የተኩስ አቁም ለማድረግ ከጥቂት ሰዓታት በፊት ተስማሙ።አዲስ አበባ ላይ በውይይት ላይ የነበሩት የደቡብ ሱዳን መንግስት እና አማጽው  የቀድሞው ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቸር ደጋፊዎች ባደረጉት ውግያ ከግማሽ ሚልዮን ያላነሰ ሕዝብ ተሰዷል።ይህ ከጥቂት ሰዓታት በፊት የተደረሰበት ስምምነት በ 24 ሰዓታት ውስጥ ተግባራዊ እንዲሆን ይጠይቃል።ስምምነቱ ምን ያህል እንደሚፀና ወደፊት የምናየው ይሆናል።
በደቡብ ሱዳን ጉዳይ የአካባቢው ሃገራት የተለያየ ጎራ መያዛቸውን ሰሞኑን የታዘብነው ጉዳይ ነው። ጉዳያችን ጡመራ ችግሩ በተፈጠረ ሰሞን የዩዌሪ ሙሴቨን እጃቸውን መንከር ቀድማ አትታ የነበረ መሆኑ ይታወሳል። ይህንን ሊንክ ከፍተው ያንብቡ።
ትናንት ምሽት ቁልፏን ከተማ ቦርን ተቆጣጠሩ።ኢትዮጵያና ዑጋንዳ በደቡብ ሱዳን አንፃር (ጉዳያችን አጭር ዘገባ ታህሳስ 10/2006 ዓም)http://gudayachn.blogspot.no/2013/12/102006.html

ስለ ዛሬው ስምምነት የደቡብ ሱዳን ዜና ወኪል የዘገበው አጭር ዜና ከእዚህ በታች ያንብቡ።በነገራችን ላይ የደቡብ ሱዳን ዜና አገልግሎት በጦርነቱ ወቅት የሚዘግበው ዘገባ በጣም አስገራሚ እና ሚዛናዊ ለመሆን የጣረ ነበር።

South Sudan Warring Factions Sign Ceasefire in Ethiopia

Addis Ababa, January 23, 2014 (SSNA) -- The government of South Sudan and rebels have signed “cessation of hostilities” accord in the Ethiopian capital, Addis Ababa.

The deal requires the two warring factions to stop the ongoing fighting. The agreement is expectd to take effect in 24 hours.

Taban Deng Gai, head of the rebels' team said he hopes the agreement will create peace in South Sudan.

"These two agreements are the ingredients to create an environment for achieving a total peace in my country", Gai told AFP.

Peace talks will resume on the 7th of February 2014, the South Sudan News Agency has learned.

More details soon…

source - http://www.southsudannewsagency.com/news/breaking-news/south-sudan-warring-factions

Gudayachn Blog

Tuesday, January 21, 2014

በኢትዮጵያ አብዮት በየካቲት ወር 1966 ዓም ከፈነዳ በመጪው የካቲት/2006 ዓም ሙሉ አርባ አመት ይሞላዋል (እነሆ የወደፊቱን ለማሰብያ ኦድዮ ክላሲካል ሙዚቃ)





በኢትዮጵያ አብዮት በየካቲት ወር 1966 ዓም ከፈነዳ እነሆ በመጪው የካቲት/2006 ዓም ሙሉ አርባ አመት ይሞላዋል።በእነኝህ አርባ አመታት ውስጥ የሶቭየት ህብረት ርዕዮት እና ወታደራዊ የአምባገነን ስርዓት ለ 17 አመታት መንግስታዊ የጎሳ ፖለቲካ ለ 23 አመታት አስተናግደናል።ዛሬ ላይ ሆነን ያለፈው አርባ አመትን ስንተነትነው ብንውል ብዙም የሚፈይድ ነገር አይኖረውም።በመጪው አመታት ግን እንዳለፉት አርባ አመታት መቀጠል አለብን ወይ? ትልቁ ጥያቄ ነው።ጥያቄው የሁላችንም ነው።

ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ፍልስፍናችን የት ነው? በዘርፉ የሰለጠኑ ምሁራን ብዙ ሊሉበት የሚገባ አጋጣሚ ላይ ነን።የት ነበርን? አሁን የት ላይ ነን? ወደፊትስ ወዴት እና እንዴት መሄድ አለብን? የአንድነት ኃይሎች ከበታኝ ኃይሎች ጋር ምን ያክል እርቀት መሄድ ይችላሉ? ኢትዮጵያዊነት የፖለቲካ ፍልስፍና ጠርቶ መውጣት የለበትም ወይ? ብዙ ጥያቄዎች አሉ።እነሆ የወደፊቱን ለማሰብያ (ኦድዮ) ክላሲካል ሙዚቃ። ኢትዮጵያችን ለዘላለም ትኑር!

የበለጠ ለማንበብ ሊንኩን ይክፈቱ

የኢትዮጵያ የተቃውሞ የፖለቲካ መድረክ ኢትዮጵያን በተመለከተ ግልፅ የፖለቲካ አቅጣጫ መያዝ የሚያስፈልግበት ደረጃ ላይ ደርሷል (ከጉዳያችን ጡመራ) 









Monday, January 13, 2014

''በ 21ኛው ክ/ዘመን ፕሮፓጋንዳ ሠርቶ፣ጥላቻ ዘርቶ ፖለቲካ እሰራለሁ በእዚህም እታመናለሁ የሚል ስብስብ ካለ ውጤታማ የሚሆን አይመስለኝም'' ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ለሕብር ራድዮ የሰጡት ቃለ-ምልልስ (ኦድዮ)



የብሔር መብት በተመለከተ ያላችሁ አስተያየት ምንድን ነው?


''የግለሰቦች መብት ከተከበረ የቡድን መብት ይከበራል።ባህሌ፣ቋንቋዬ፣እምነቴ  እኔ ውስጥ አለ። በቋንቋዬ መናገር የእኔ መብት ነው፣የሙያ ማኅበር መመስረት የእኔ መብት ነው።የእኔ መብት ያልሆነ የቡድን መብት አይኖርም።የግለሰብ መብት ከተከበረ የማይከበር የቡድን መብት የለም።የወለጋን ሕዝብ ለማስተዳደር ከጎጃም ማምጣት የለብንም።የፌድራል አስተዳደሮች የራሳቸውን ቋንቋ መምረጥ እንዳለባቸው የታወቀ ነው።ዛሬ የአንድ ሰፈር ሰው የሌላ ሰፈር ሰው የሚወክልበት ሁኔታ የለም።ይህንን ዘመን አልፈነዋል።

የአፄ ምንሊክን 100ኛ አመት መታሰቢያ በተመለከተ 


''አፄ ምንሊክ ለእዚህ ትውልድ አርአያ የሚሆኑ ብዙ ነገሮች አሉዋቸው።አፄ ምንሊክ መልካም መሪ አልነበሩም የሚሉ ካሉ መብታቸው ነው።እኛ እሳቸውን እየዘከርን ያለነው ለሀገር ግንባታ ባደረጉት መልካም ነገር ነው።ለአፍሪካ ሕዝብ ነፃነት ተምሳሌት በመሆናቸው እንዘክራቸዋለን።'ጡት ቆረጡ' እንደዚህ ነው እንደዛ ነው ብሎ በመናገር በ 21ኛው ክ/ዘመን ፕሮፓጋንዳ ሠርቶ፣ጥላቻ ዘርቶ ፖለቲካ እሰራለሁ በእዚህም እታመናለሁ የሚል ስብስብ ካለ ውጤታማ የሚሆን አይመስለኝም።'' ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ለሕብር የሰጡት ቃለ-ምልልስ




ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

Saturday, January 11, 2014

የአውሮፓውያን እና የእኛ የገና በዓል አከባበር ለምን ተለያየ? የእኛ ትክክል ለመሆኑ ማስረጃዎች (አጭር ማስታወሻ)


ዛሬ  እዚህ ኦስሎ ውስጥ በተገኘሁበት የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ የገና በዓል መታሰብያ ላይ አንዳንዶች ስለበዓሉ ቀን መለያየት ጥያቄ ሲያነሱ ነበር።ከእዚህ በታች ያለው ፅሁፍም መርሃግብሩ  ላይ ካነበብኩት እረዘም ያለ ፅሁፍ ጥቂቱን እና ስለበዓሉ የተመለከተውን ብቻ ነው።ፅሁፉ በተለያዩ ጋዜጦች እና ድህረ ገፆች ላይም  ወጥቷል።

ከጥንት ጀምሮ ሮማውያን እውነተኛ ፀሐይ የተወለደበት ቀን እያሉ ታኅሣሥ 16 ቀንን ያከሩ ነበር ምክንያቱም በሮማውያን ግዛት የረጅሙ የክረምት ወቅት አብቅቶ በመጀመሪያ ጊዜ የፀሐዩን ብርሃን የሚያዩት በዚህች ቀን ነው፡፡ ሮማውያን በተለምዶ ከዚያ ከሚያኮራምት የክረምት ወቅት በማለፍ ብርሃንና ሙቀትን ስለሚያገኙ ለተክሎቻቸው ልማት ለከብቶቻቸውም የፍንደቃ ወቅት ስለሆነ ለዚህ ብርሃን በየዓመቱ የምስጋና መስዋእትን በመያዝ ሁሉም ወደ ተራራ ጫፍ ላይ በመውጣት መስዋዕትን ያቀርቡ ነበር፡፡

 ክርስትና  እስከ አራተኛ ክፍለ ዘመን ድረስ በስደት ላይ ባልተረጋጋ ሕይወት ውስጥ ስለነበረ   በዓለም ላይ በሰፊው ያልታወቀበት ዘመን ስለነበር  አውሮፓውያን ስለ ጌታችን ልደት ብዙም ትኩረት አይሰጡም ነበር፡፡እንደሚታወቀው ከአራተኛው ክፍለ ዘመን በፊት ክርስትያኖች በሮማውያን ነገስታት ተሳደዋል፣ተገርፈዋል ለአውሬ ተሰጥተዋል።ቤተክርስቲያን እረፍት ያገኘችው በእሌኒ ንግስት ልጅ ንጉስ ቆስጠንጢኖስ ሲነግስ ነበር።

ስለዚህ  ክርስትና በአግባቡ በሕዝቡ ውስጥ እስኪሰርፅ እና የመንግስት ሃይማኖት እስኪሆን ድረስ ሁሉ የፀሐይ አምላክ እንደማንኛውም ሮማዊ በአባቶቻቸው የወረሱትን አምልኮ ነውና መስዋዕትን ይሰዉለት ነበር፡፡ ከ  320ዓም በኃላ  ለመጀመሪያ ጊዜ በተለያዩ ቦታዎች የሚኖሩ ክርስትያኖች የጌታችን ልደት በታኅሣሥ 29 ማክበር ጀመሩ፡፡

በ354 ዓ.ም. ግን ሮማዊው ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊብሮስ ክርስቲያኖች ‹‹ሳትሩን›› እየተባለ በሚጠራው የፀሐይ አምላክ ፈንታ መንፈሳዊ የፍትህ ፀሐይ ክርስቶስ የተወለደበት የደስታና የነፃነት አብሳሪ ልደት በዲሴምበር 25 (ታኅሳስ 16) ቀን እንዲከበር ለዓለም ሁሉ አዋጅ አስተላለፋ፡፡ በወቅቱ ብዙ የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት የሊብሮስ አዋጅ አልተዋጠላቸውም ነበር፡፡

 ከዚህ በኋላ አብዛኛዎቹ አብያተ ክርስቲያናት ታኅሣሥ 25 (እ አ አቆጣጠር) እንደ ጌታ ልደት ቀን ተቀበሉ፡፡  የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ግን እስከ ዛሬ ታኅሣሥ 29 የጌታን ልደት ብላ ታከብራለች፡፡ ይህ እለት በመፅሐፍ ቅዱስ እንደተጠቀሰው መጥምቁ ዮሐንስ ጌታችንን በስድስት ወራት ይቀድመዋል(መጥምቁ ዮሐንስ  ልደት ሰኔ 30 ነው) እመቤታችን በመጋቢት 29 በቅዱስ ገብርኤል ብስራት እግዚአብሔር ወልድ ከሥጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በተዋህዶ ሰው ሆኖ ካለ አባት በመንፈስ ቅዱስ ግብር ተፀነሰ።ከ 9 ወር ከ 5 ቀን በኃላ በታህሳስ 29 ተወለደ። ታህሳስ 29 ቀን ትክክለኛ የክርስቶስ የልደት ቀን ነው።አጉስጦስ ቄሳር ሕዝቡን ለቆጠራ በሰበሰበበት ወር ከቆጠራ ሲመለሱ በከብቶች ግርግም እመቤታችን ጌታችንን እንደወለደችውቅዱስ መፅሐፍ ይነግረናል።
////////////////////////////////።።።።።።።።።።።።።።/////////////////////።።።።።።።።።።።።////////////////////።።።።።።።።።///////

Wednesday, January 8, 2014

በቴዲ አፍሮ ላይ የተከፈተው ዘመቻ በኢትዮጵያዊነት ላይ የተቃጣው ሰይፍ አካል ነው ዛሬም ሌላ በፀረ-ኢትዮጵያዊነት መልክ አዲስ ዘመቻ ከፍተዋል።''CUT CHRISTIANS NECK BY MENCHA'' NEW TERRORIST MOVEMENT TARGETED ETHIOPIAN CHRISTIANS.


''CUT CHRISTIANS NECK BY MENCHA'' NEW TERRORIST MOVEMENT TARGETED ETHIOPIAN CHRISTIANS has already started its act on opening social media campaign against popular Ethiopian musician Tewodros Ksahun. What will you call such non-human act other than Terrorism.Terrorists must get their lesson very soon!!

''በሜንጫ የክርስቲያኖችን አንገት እንቁረጥ'' በሚል እራሳቸውን የሚጠሩ ቡድኖች  ቴዲ አፍሮ አፄ ምንሊክን በተመለከተ ያልሰጠውን መግለጫ አዛብተው አቅርበው የማኅበራዊ ድህረ ገፆች ዘመቻ ከፍተውበት  እንደነበር ይታወቃል።በ እዚሁ እኩይ ተግባር ላይም ኦህዴድ እና የገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች ተባብረውበት ''የፍቅር ዘመቻ'' የተሰኘው ኮንሰርቱ እንዲሰረዝ መደረጉ አሁንም በ ልዩ ልዩ ድህረ-ገፆች ሲገለፅ መሰንበቱ ይታወቃል።

''በሜንጫ የክርስቲያኖችን አንገት እንቁረጥ'' የተሰኘው ይህ ቡድን ዛሬም ቴዲ ኢትዮጵያን በአለም አቀፍ ደረጃ የሚያስጠራበትን በኮካኮላ ካምፓኒ የተዘጋጀውን መርሃ ግብር ላይ እንዳይሳተፍ ለማድረግ አዲስ ዘመቻ ከፍተዋል። ይህንን ዘመቻ አለመጀመራቸውን ማስተባበያ በአንዳንድ ድህረ-ገፆች ላይ ቢገልፁም አሁንም የሚደርሱት ዘገባዎች ግን የኢትዮጵያ ስም በብራዚል አደባባይ መጠራቱ በእጅጉ እንዳመማቸው የሚያመላክት ነው።

ይህ ተግባር የቴዲ ጉዳይ ብቻ አይደለም ዘመቻው በኢትዮጵያዊነት ላይ የተቃጣ ሰይፍ አካል ነው።ቴዲ የፈለገውን ሃሳብ የመግለፅ ሙሉ መብት አለው።ቴዲ ባልተናገረው ጉዳይ ቢዘመትበትም መታየት ያለበት ግን ማንም ሰው ማንኛውንም ድርጊት ቅዱስ ወይንም እርኩስ የማለት መብቱ ሊከበር የመገባቱ ሃሳብን የመግለፅ ሙሉ መብት ጉዳይ ነው።ማንም አንገትህን በሜንጫ ልቁረጥ ባይ ተነስቶ የአንድን ግለሰብ መብት እንዲጋፋ ዕድል ልንሰጠው አይገባም።

በሃያ አንደኛው ክ/ዘመን ላይ ሆነው ''የክርስቲያኖችን አንገት በሜንጫ እንቆርጣለን'' ብለው የተናገሩ እና በጉዳዩ ላይ መስማማታቸውን የገለፁ ሁሉ በይፋ ይቅርታ ካልጠየቁ በሚኖሩበት ሀገር ለፍርድ የማይቀርቡበት ምንም ምክንያት ሊኖር አይችልም።ለእዚህም የሲቪል ማኅበራት ለሚመለከታቸው አካላት የጉዳዩን አደገኛነት የመግለፅ ግዴታ አለባቸው።

ለእያንዳንዱ የሀገራችን ችግር በተናጥል በመፍታት ለውጥ ማምጣት ባይቻልም ችግር መፍትሄን ይወልዳል እና ኢትዮጵያውያን ከመቸውም ጊዜ በላይ በ እዚህ በሉላዊነት (globalaization) ዘመን ለሚነሱ የጋራ ሃገራዊ ጉዳዮች አንድ ድምፅ የሚያሰሙበትን የበየነ-መረብ (internet) ዘመቻዎች እና የመረጃ መለዋወጫ መስመሮቻቸውን ማጠናከር እንደሚጠበቅባቸው አመላካች ነው። በመሆኑም በኅብረተሰባችን ውስጥ ታዋቂነት ያተረፉ አክትቪስቶች ሳይውሉ ሳያድሩ አፋጣኝ ንቅናቄ ማድረግ ''በሜንጫ አንገት እንቁረጥ'' ቡድን አባላት  አሁን ላነሱት ፀረ-ኢትዮጵያ ዘመቻ ብቻ ሳይሆን ወደፊት ለሚነሱ ሌሎች እኩይ ተግባራት ሁሉ ወሳኝ የሆኑ ምላሾች መስጠት ላይ ማተኮር ይገባቸዋል።

ጉዳያችን ታህሳስ 30/2006 ዓም

የኢቲቪ የልደት በዓል መርሃግብሩ ላይ የተሻሻሉ እና ያልተሻሻሉ መልኮቹ


ኢቲቪ በትናንትናው የገና በዓል ላይ ከእዚህ በፊት በተሻለ አቀራረብ ቀርቧል።የዛሬ አመት ካቀረበው ደረጃውን ካልጠበቀ መርሃግብር የዘንድሮው የተሻለ በዓል አስመስሎታል።በሌላ በኩል ደግሞ የሚቀሩት መርሃግብሮችም መኖራቸውን ሳንረሳ ነው።በመሆኑም የተሻሻለ አቀራረብ እና ያልተሻሻሉ አቀራረቦች ወይንም መርሃግብሮች በሚሉት ላይ እንዲህ ልበል-

የተሻሻሉ አቀራረቦች 

1/ መርሃ ግብሮቹን የቴሌቭዥን ጣቢያው በእራሱ ከመያዝ ለማስታወቅያ ድርጅቶች ዕድል ሰጥቷል።የሰራዊት ፍቅሬ እና ሸዋፈራሁ ማስታወቅያ ድርጅቶች ተሳትፈዋል፣

2/ በመርሃግብራቸው ላይ በቃለ መጠይቅ ያቀረቧቸው እንግዶች ብዙ ስብጥር ባይታይባቸውም ጠንክሮ ስለመስራት አውርተዋል።እዚህ ላይ በአጭር መንገድ ሃብታም  እና ጄኔራል የሆኑ ሰዎች ሲደነቁ እውነታውን ያንፀባርቃል የሚል እምነት እንደሌለኝ ይመዝገብልኝ።ዝርዝሩን ለማውራት ጊዜ የለኝም፣

3/ የሰራዊት ፍቅሬ እና ሸዋፈራሁ ማስታወቂያ ድርጅቶችን ጨምሮ ለፌስቱላ ሆስፒታል ስጦታዎች ሲበረከቱ ታይቷል፣

4/ ኢትዮጵያዊነት በጋሽ ውብሸት ወርቃለማሁ ሲነገር እና ሲተረክ አምሮበታል፣

5/ የሸገሮቹ ''የእኛ'' የራድዮ ተውኔት እና በ''አቤት'' እና ''እቴጌ'' ዜማቸው የሚታወቁት አምስቱ ወጣቶች ስለሀገር እና የሴት ልጅ አቅም ላይ  የተናገሩት አስተማሪ ነበር፣

6/ የገና ጫወታ ከዘመናዊው ዳንስ ጋር ያለው ልዩነት ለማሳየት እና ባህልን ማክበር ተገቢነት ላይ ያተኮረ ትንሽ ትይንት በመጠኑ ለማሳየት ተሞክሯል እና የመሳሰሉት ሲሆኑ።

ያልተሻሻሉ  አቀራረቦች 


1/ የበዓሉን ሃይማኖታዊ ገፅታ የሚያንፀባርቅ መርሃግብር አልታየም።ልደቱ የክርስቶስ መሆኑ ተረሳ እንዴ? የጌታን ልደት ለሁለት ሺህ አመት ያከበረች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ስለበዓሉ መርሃ ግብር እንዲኖራት ለሕዝቡ እንድትናገር ዕድል መስጠት ይገባ ነበር፣

2/ በጣም አስቂኝ የዘንድሮ ኢቲቪ አቀራረብ በመሃል ላይ የፈረንጆቹን የገና ክላሲካል የምታሰማ ሙዚቃ ከፍቶ በረዶ ሲንጠባጠብ እና ብልጭልጭ የገና ኮተት የሚያሳይ ምስል ብልጭ ያደርግ ነበር።ይህ በኢቲቪ 3 ላይም ደጋግማ የታየች የባዕድ ቡትቶ ነገር ነች።እኛ ሀገር እኮ በገና በረዶ የለም።አሁን በረዶ ሲንጠባጠብ እና የአውሮፓ የገና ክላሲካል በእየመርሃ ግብሩ መሃል ማስገባት ለምን አስፈለገ? የገና በዓል የሚገልፅ ሀገርኛ ዜማ ጠፋ ማለት ነው?

3/ በዋዜማውም ሆነ በዕለቱ ምሽት ላይ ዜና አንባቢው በአውሮፓ ሱፍ ከሚታይ የሀገር ባህል ልብሱን ቢለብስ ባማረበት ነበር።በእዚህ አቀራረብ ኢሳቶች ይምጡብኝ።ዜና አንባቢው በሀገር ባህል ልብስ ቂቅ ብሎ ነው የታየው።መቼም ኢቲቪን የተመለከቱ የውጭ ሀገር ዜጎች በዜና አንባቢዎቹ አለባበስ ከሀገር ቤቱ እኩል ሳያፍሩበት አይቀሩም፣

4/ የአመት በዓል መርሃግብሮችን ባብዛኛው ወጣቶች እና ታዳጊ ወጣቶች የመመልከታቸውን ያክል ታዋቂ ምሁራን እና በምርምር እንዲሁም በትምህርቱ ዘርፍ ዝናን ያተረፉ ሰዎች ከታሪካቸው ተሞክሮ ጋር ቢቀርቡ አስተማሪ በሆነ ነበር።ሁል ጊዜ የኪነት ሰዎች ብቻ መድረኩን ሊሞሉት አይገባም ባይ ነኝ።ኪነት አንዱ አስፈላጊ ዘርፍ ቢሆንም ሁሉም ሰው የኪነት ሰው ሆኖ ሀገር አያድግም።ምሁራኑን እንደ ቅቤ ጣል ቢደረጉ ጥሩ ነበር።

አበቃሁ

ጉዳያችን ታህሳስ 30/2006 ዓም 

Monday, January 6, 2014

መልካም የልደት በዓል!

ፎቶ - ከሰማያዊ ፓርቲ ፌስ ቡክ የ 2006 ዓም 'መልካም ገና' ምኞት ፖስተር https://www.facebook.com/photo.php?fbid=642998099071612&set=a.566241026747320.1073741826.566236800081076&type=1&theater



Saturday, January 4, 2014

''የኢትዮጵያ የተቃውሞ የፖለቲካ መድረክ ኢትዮጵያን በተመለከተ ግልፅ የፖለቲካ አቅጣጫ መያዝ የሚያስፈልግበት ደረጃ ላይ ደርሷል'' በሚል ርዕስ አዲስ መጣጥፍ ከጉዳያችን ጡመራ(GUDAYACHN BLOG) በቅርብ ቀን ይጠብቁ

''የኢትዮጵያ የተቃውሞ የፖለቲካ መድረክ ኢትዮጵያን በተመለከተ ግልፅ የፖለቲካ አቅጣጫ መያዝ የሚያስፈልግበት ደረጃ ላይ ደርሷል''  በሚል ርዕስ አዲስ መጣጥፍ ከጉዳያችን ጡመራ (GUDAYACHN BLOG) በቅርብ ቀን ይጠብቁ

///////////////////////////.……...////////////////////////////.…………..///////////////////.…………...//////////////////.…….///////

ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG 



Friday, January 3, 2014

''አጠቃቀስኩ !'' ዛሬ ታህሳስ 25/2006 ዓም የኢቲቪ ''ዶክመንተሪ'' የተጠቀመበት ቃል



ዛሬ ታህሳስ 25/2006 ዓም  ምሽት ኢቲቪ አባ ዱላን አቅርቦ ኦነግ  በበደኖ ለፈጃቸው ንፁሃን ዜጎች ተጠያቂ መሆኑን ጠረንጴዛ ለመደብደብ በቀረ ዛቻ ሲያሰሙ አሳየ።
ቀጥሎም  ለኢሳት ከሀገር ቤት መግለጫ የሚሰጡ ተቃዋሚዎችን እና ባለስልጣናትን ያስፈራራበት ቃል በጣም አስቂኝ ብቻ ሳይሆን የአራዳ ልጆች በእድሜ የገፉ አዛውንት ፊት የማይናገሩትን ቃል በመጠቀም እንዲህ ገለፀው- '' በሀገር ቤት የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች የተቃዋሚዎችን አጀንዳ ባጠቃቀስኩ ማራመድ ብዙ እርቀት የማይወስድ ነውና…..'' ቀጠለ ንግግሩ።

አሁን ያ'ራዳ' ልጆች ''አጠቃቀስኩ'' የሚለውን ቃል ከእድሜ እኩዮቻቸው ጋር እንጂ ትልቅ ሰው ፊት አይናገሩትም።ኢቲቪ ግን ሚልዮን ኢትዮጵያውያንን ''አጠቃቀስኩ'' ሲላቸው አንገቱን ሰበርም አላደረገ። ኢቲቪ ኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ብቻ ነው እንዴ ደፋርነቱ?

የሆነው ሆኖ ለኢሳት መግለጫ የሰጡ አቦይ ስብሐት፣አምባሳደሮች፣የፖሊስ ኮሚሽነሮች የክልል መንግስት ባለስልጣናት እነኝህ ሁሉ አጠቃቀሱ ማለት ነው? ወይ ማጠቃቀስ? በሀገር ቤት ነፃ ሚድያ የተነፈገ ሕዝብ እንደ ኢቲቪ  አባባል በሳተላይት ዲሽ አጠቃቅሶም ቢሆን ነፃ ሚድያ ከነፃ ምድሮች መመልከት የለበትም? አቦይ ስብሐት ስንቴ በኢሳት እንደልባቸው ሲያጠቃቅሱ ዝም ብላችሁ? ዛሬ አታጠቃቅሱ ምናምን ማለት ምንድነው?

ኢሳት ግን አርማው ዛሬ ምሽቱን በኢቲቪ እንዲታይ ተደረገ። የኢትዮጵያ ህዝብም የኢሳትን አርማ እና ጋዜጠኞች ተመልክቶ እናቶች ደረታቸውን እየመቱ ''እናቴ ኢሳት! እናቴ ኢሳት! ልጄ ሳውድ አረብያ ውስጥ ስትቸገር የነገርከኝ፣ አጎቴ ከጉርዳ ፈርዳ መፈናቀሉን ያሳወከኝ፣እህቴ ጅጅጋ መገፋቷን ያሳየሄኝ፣የጋሼ ቤት ቡራዩ ላይ በግሬደር መፍረሱን የገለፅክልኝ -----እናቴ ኢሳት አንድ ቀን ጥቁር አንበሳ አጠገብ ካለው የኢቲቪ ህንፃ ሆነህ የምታስተላልፈውን መርሃ ግብር እናያለን።'' ሲሉ

ሌላው ቤት ደግሞ የኢሳት አርማ ኢቲቪ ላይ ብቅ ሲል ትንሹ ማሙሽ አውራ ጣቱን እያሳየ ''እማዬ ኢሳት በኢቲቪ!'' ብሎ ስጮህ ከሌላ ክፍል ተሰብስቦ ቡና ይጠጣ የነበረው ቤተሰብ እየሮጠ ሲመጣ ኢቲቪ '' አጠቃቀስኩ'' ሲል ቤተሰቡ ሲስቅ ነበር ትዕይንቱ።ባጭሩ  የዛሬው ምሽት የኢቲቪ አጠቃቀስኩ የገና ስጦታ ሆኖ አመሸ።ቃሉ (አጠቃቀስኩ) ግን የአዘጋጁን የመንግስት አካል ስነ-ምግባር እና የሞራል ደረጃ አሳይታኛለች።አይ አጠቃቀስኩ።እንዴት በሳል ቃል የሚጠቀሙ ጋዜጠኞች አሉን እባካችሁ?

ጉዳያችን
ታህሳስ 25/2006 ዓም
ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

Thursday, January 2, 2014

እንቆቅልሽ! ይህ መንግስት ማን ነው?


  • መንግስታዊ ሽብርተኝነት እና የዘረኝነት መርዝ ለመርጨት ከህዝብ በቀረጥ መልክ የሰበሰበውን ገንዘብ በጀት መድቦ የሚንቀሳቀስ መንግስት ማን ነው?


  • በአፈ ታሪክ እያወራ ያልተቆረጠ  የጡት ሃውልት እየሰራ በሕዝብ ደም በሚሳለቁ ካድሬዎች የተሞላ መንግስት ማን ነው?


  • የክርስትና እና የእስልምናን ሃይማኖት ተከታዮች ለማጋጨት በሕዝብ ገንዘብ በሚተዳደር  በብሔራዊ ቴሌቭዥን ጣብያው ጦርነት የሚያስነሳ ፕሮግራም እንዲሰራ ያደረገ መንግስት ማን ነው?


  • በውጭ ሀገር የሚኖሩ ዜጎቹ ለልማት ሳይሆን እርስ በርስ በዘር እንዲናከሱ የዘረኝነት መርዝ  ለመርጨት የሚተጋ  ፓልቶክ ከፍቶ ገንዘብ የሚያፈስ መንግስት ማን ነው?


  • የሀገሩን የፖለቲካ ፓርቲዎች በዘር እና በቋንቋ ብቻ እንዲደራጁ ያስገደደ እና የሚያበረታታ መንግስት ማን ነው?


  • ስለ ሕዝብ ህብረት እና አንድነት የሚቆሙ የፖለቲካ ድርጅቶችን ብቻ ሳይሆን ዘፋኝንም ካለ ወንጀሉ ''ሰው በመኪና ገጨህ'' ብሎ እስር ቤት ያንገላታ እና በገዛ ሀገሩ የሚያሳድድ ስለ ፍቅር ላስተምር ሲል ውሉን እንዲሰረዝ የሚያዝ መንግስት ማን ነው?


  • ለፋሽሽት መሪ ግራዝያኒ  ሃውልት መሰራት አይገባውም ብለው ሰልፍ የወጡ ዜጎቹን በእስር እና በዱላ ቁም ስቅል ያሳየ መንግስት ማን ነው?


  • በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎቹ በሳውዲ አረብያ የዜግነት መብታቸው ተገፎ፣ሴቶቹ ተደፍረው፣ተገለው በየጎዳናው አስከሬናቸው ሲጎተት እያየ አንዳች የተቃውሞ ድምፅ በሳውዲ አረብያ ላይ መግለጫ ያላወጣ ይልቁንም ለሳውዲ አረብያ መንግስት ከ 300 በላይ ፕሮጀክት ድርጊቱ በተፈፀመ ሰሞን የሸለመ መንግስት ማን ነው?


  • ''ወገኖቻችን በሳውድ አረብያ አለቁ'' ብለው ለተቃውሞ በሳውዲ ኢምባሲ በር ላይ ሰልፍ ሊያደርጉ የነበሩ ዜጎችን በፖሊስ ኃይል የበተነ፣የደበደበ እና ያሰረ መንግስት ማን ነው?


  • በሙስና የተጨማለቀ አንዳንዶቹ ሲያዙ አልጋቸው ስር በሺ የሚቆጠር ዶላር፣ኢሮ እና ብር የተገኘባቸው ባለስልጣናት ያሉት መንግስት ማን ነው?


  • በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣት የነገ ተስፋ ሊሆኑ የሚችሉ ሴቶችን ወደ አረብ ሀገር ፣ሌሎች በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሕፃናትን ወደ አውሮፓ እና አሜሪካ በመላክ የውጭ ምንዛሪ የሚሰብስብ ጨካኝ መንግስት ማን ነው?

  • በሺ የሚቆጠሩ ገበሬዎችን ከመሬታቸው እያፈናቀለ ለውጭ ባለሀብቶች በነፃ ከመስጠት ባልተናነሰ ገንዘብ የሀገሩን መሬት እና ወንዝ የሚሸጥ በእዚህም የሚመፃደቅ መንግስት ማን ነው?


  • አባቶቹ የሞቱለትን ድንበር አፍርሶ ለሱዳን መንግስት በሺ የሚቆጠር መሬት በመስጠት በአባቶቹ አጥንት የሚቀልድ መንግስት ማን ነው?
እንቆቅልሽ! ይህ መንግስት ማን ነው?
ታህሳስ 24/2006 ዓም
ጉዳያችን ጡመራ 

የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ቃለ መጠይቅ ብዙ ጠቃሚ በሆኑ የጥበብ ቃላት የተሞሉ ናቸው ይመልከቷቸው (ቪድዮ)

ክፍል አንድ


ምንጭ - ኢ ቢ ኤስ ቲቪ እና ድሬ ዩትዩብ

ክፍል ሁለት
ምንጭ - ኢ ቢ ኤስ ቲቪ እና ድሬ ዩትዩብ

ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።