ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Friday, January 3, 2014

''አጠቃቀስኩ !'' ዛሬ ታህሳስ 25/2006 ዓም የኢቲቪ ''ዶክመንተሪ'' የተጠቀመበት ቃልዛሬ ታህሳስ 25/2006 ዓም  ምሽት ኢቲቪ አባ ዱላን አቅርቦ ኦነግ  በበደኖ ለፈጃቸው ንፁሃን ዜጎች ተጠያቂ መሆኑን ጠረንጴዛ ለመደብደብ በቀረ ዛቻ ሲያሰሙ አሳየ።
ቀጥሎም  ለኢሳት ከሀገር ቤት መግለጫ የሚሰጡ ተቃዋሚዎችን እና ባለስልጣናትን ያስፈራራበት ቃል በጣም አስቂኝ ብቻ ሳይሆን የአራዳ ልጆች በእድሜ የገፉ አዛውንት ፊት የማይናገሩትን ቃል በመጠቀም እንዲህ ገለፀው- '' በሀገር ቤት የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች የተቃዋሚዎችን አጀንዳ ባጠቃቀስኩ ማራመድ ብዙ እርቀት የማይወስድ ነውና…..'' ቀጠለ ንግግሩ።

አሁን ያ'ራዳ' ልጆች ''አጠቃቀስኩ'' የሚለውን ቃል ከእድሜ እኩዮቻቸው ጋር እንጂ ትልቅ ሰው ፊት አይናገሩትም።ኢቲቪ ግን ሚልዮን ኢትዮጵያውያንን ''አጠቃቀስኩ'' ሲላቸው አንገቱን ሰበርም አላደረገ። ኢቲቪ ኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ብቻ ነው እንዴ ደፋርነቱ?

የሆነው ሆኖ ለኢሳት መግለጫ የሰጡ አቦይ ስብሐት፣አምባሳደሮች፣የፖሊስ ኮሚሽነሮች የክልል መንግስት ባለስልጣናት እነኝህ ሁሉ አጠቃቀሱ ማለት ነው? ወይ ማጠቃቀስ? በሀገር ቤት ነፃ ሚድያ የተነፈገ ሕዝብ እንደ ኢቲቪ  አባባል በሳተላይት ዲሽ አጠቃቅሶም ቢሆን ነፃ ሚድያ ከነፃ ምድሮች መመልከት የለበትም? አቦይ ስብሐት ስንቴ በኢሳት እንደልባቸው ሲያጠቃቅሱ ዝም ብላችሁ? ዛሬ አታጠቃቅሱ ምናምን ማለት ምንድነው?

ኢሳት ግን አርማው ዛሬ ምሽቱን በኢቲቪ እንዲታይ ተደረገ። የኢትዮጵያ ህዝብም የኢሳትን አርማ እና ጋዜጠኞች ተመልክቶ እናቶች ደረታቸውን እየመቱ ''እናቴ ኢሳት! እናቴ ኢሳት! ልጄ ሳውድ አረብያ ውስጥ ስትቸገር የነገርከኝ፣ አጎቴ ከጉርዳ ፈርዳ መፈናቀሉን ያሳወከኝ፣እህቴ ጅጅጋ መገፋቷን ያሳየሄኝ፣የጋሼ ቤት ቡራዩ ላይ በግሬደር መፍረሱን የገለፅክልኝ -----እናቴ ኢሳት አንድ ቀን ጥቁር አንበሳ አጠገብ ካለው የኢቲቪ ህንፃ ሆነህ የምታስተላልፈውን መርሃ ግብር እናያለን።'' ሲሉ

ሌላው ቤት ደግሞ የኢሳት አርማ ኢቲቪ ላይ ብቅ ሲል ትንሹ ማሙሽ አውራ ጣቱን እያሳየ ''እማዬ ኢሳት በኢቲቪ!'' ብሎ ስጮህ ከሌላ ክፍል ተሰብስቦ ቡና ይጠጣ የነበረው ቤተሰብ እየሮጠ ሲመጣ ኢቲቪ '' አጠቃቀስኩ'' ሲል ቤተሰቡ ሲስቅ ነበር ትዕይንቱ።ባጭሩ  የዛሬው ምሽት የኢቲቪ አጠቃቀስኩ የገና ስጦታ ሆኖ አመሸ።ቃሉ (አጠቃቀስኩ) ግን የአዘጋጁን የመንግስት አካል ስነ-ምግባር እና የሞራል ደረጃ አሳይታኛለች።አይ አጠቃቀስኩ።እንዴት በሳል ቃል የሚጠቀሙ ጋዜጠኞች አሉን እባካችሁ?

ጉዳያችን
ታህሳስ 25/2006 ዓም
ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...