ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, January 2, 2014

እንቆቅልሽ! ይህ መንግስት ማን ነው?


  • መንግስታዊ ሽብርተኝነት እና የዘረኝነት መርዝ ለመርጨት ከህዝብ በቀረጥ መልክ የሰበሰበውን ገንዘብ በጀት መድቦ የሚንቀሳቀስ መንግስት ማን ነው?


  • በአፈ ታሪክ እያወራ ያልተቆረጠ  የጡት ሃውልት እየሰራ በሕዝብ ደም በሚሳለቁ ካድሬዎች የተሞላ መንግስት ማን ነው?


  • የክርስትና እና የእስልምናን ሃይማኖት ተከታዮች ለማጋጨት በሕዝብ ገንዘብ በሚተዳደር  በብሔራዊ ቴሌቭዥን ጣብያው ጦርነት የሚያስነሳ ፕሮግራም እንዲሰራ ያደረገ መንግስት ማን ነው?


  • በውጭ ሀገር የሚኖሩ ዜጎቹ ለልማት ሳይሆን እርስ በርስ በዘር እንዲናከሱ የዘረኝነት መርዝ  ለመርጨት የሚተጋ  ፓልቶክ ከፍቶ ገንዘብ የሚያፈስ መንግስት ማን ነው?


  • የሀገሩን የፖለቲካ ፓርቲዎች በዘር እና በቋንቋ ብቻ እንዲደራጁ ያስገደደ እና የሚያበረታታ መንግስት ማን ነው?


  • ስለ ሕዝብ ህብረት እና አንድነት የሚቆሙ የፖለቲካ ድርጅቶችን ብቻ ሳይሆን ዘፋኝንም ካለ ወንጀሉ ''ሰው በመኪና ገጨህ'' ብሎ እስር ቤት ያንገላታ እና በገዛ ሀገሩ የሚያሳድድ ስለ ፍቅር ላስተምር ሲል ውሉን እንዲሰረዝ የሚያዝ መንግስት ማን ነው?


  • ለፋሽሽት መሪ ግራዝያኒ  ሃውልት መሰራት አይገባውም ብለው ሰልፍ የወጡ ዜጎቹን በእስር እና በዱላ ቁም ስቅል ያሳየ መንግስት ማን ነው?


  • በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎቹ በሳውዲ አረብያ የዜግነት መብታቸው ተገፎ፣ሴቶቹ ተደፍረው፣ተገለው በየጎዳናው አስከሬናቸው ሲጎተት እያየ አንዳች የተቃውሞ ድምፅ በሳውዲ አረብያ ላይ መግለጫ ያላወጣ ይልቁንም ለሳውዲ አረብያ መንግስት ከ 300 በላይ ፕሮጀክት ድርጊቱ በተፈፀመ ሰሞን የሸለመ መንግስት ማን ነው?


  • ''ወገኖቻችን በሳውድ አረብያ አለቁ'' ብለው ለተቃውሞ በሳውዲ ኢምባሲ በር ላይ ሰልፍ ሊያደርጉ የነበሩ ዜጎችን በፖሊስ ኃይል የበተነ፣የደበደበ እና ያሰረ መንግስት ማን ነው?


  • በሙስና የተጨማለቀ አንዳንዶቹ ሲያዙ አልጋቸው ስር በሺ የሚቆጠር ዶላር፣ኢሮ እና ብር የተገኘባቸው ባለስልጣናት ያሉት መንግስት ማን ነው?


  • በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣት የነገ ተስፋ ሊሆኑ የሚችሉ ሴቶችን ወደ አረብ ሀገር ፣ሌሎች በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሕፃናትን ወደ አውሮፓ እና አሜሪካ በመላክ የውጭ ምንዛሪ የሚሰብስብ ጨካኝ መንግስት ማን ነው?

  • በሺ የሚቆጠሩ ገበሬዎችን ከመሬታቸው እያፈናቀለ ለውጭ ባለሀብቶች በነፃ ከመስጠት ባልተናነሰ ገንዘብ የሀገሩን መሬት እና ወንዝ የሚሸጥ በእዚህም የሚመፃደቅ መንግስት ማን ነው?


  • አባቶቹ የሞቱለትን ድንበር አፍርሶ ለሱዳን መንግስት በሺ የሚቆጠር መሬት በመስጠት በአባቶቹ አጥንት የሚቀልድ መንግስት ማን ነው?
እንቆቅልሽ! ይህ መንግስት ማን ነው?
ታህሳስ 24/2006 ዓም
ጉዳያችን ጡመራ 

No comments:

በኢትዮጵያ የእገታ ወንጀል ተሳታፊ አራት አካላት ናቸው። ለችግሩ የመፍትሄ አካላት ሁለት ናቸው።ሁለቱ አካላት ምን ይስሩ?

======= ጉዳያችን ======= በኢትዮጵያ ዜጎችን እያገቱ ገንዘብ የሚቀበሉ ወንጀለኞች ከተራ ወንጀለኝነት አልፎ በታጣቂ ቡድኖች የገንዘብ ማግኛነት መዋል ብቻ ሳይሆን ዜጎችን የማሸበርያ ፋሺሽታዊ ተግባር ሆኗል። እገታ የ...