የብሔር መብት በተመለከተ ያላችሁ አስተያየት ምንድን ነው?
''የግለሰቦች መብት ከተከበረ የቡድን መብት ይከበራል።ባህሌ፣ቋንቋዬ፣እምነቴ እኔ ውስጥ አለ። በቋንቋዬ መናገር የእኔ መብት ነው፣የሙያ ማኅበር መመስረት የእኔ መብት ነው።የእኔ መብት ያልሆነ የቡድን መብት አይኖርም።የግለሰብ መብት ከተከበረ የማይከበር የቡድን መብት የለም።የወለጋን ሕዝብ ለማስተዳደር ከጎጃም ማምጣት የለብንም።የፌድራል አስተዳደሮች የራሳቸውን ቋንቋ መምረጥ እንዳለባቸው የታወቀ ነው።ዛሬ የአንድ ሰፈር ሰው የሌላ ሰፈር ሰው የሚወክልበት ሁኔታ የለም።ይህንን ዘመን አልፈነዋል።
የአፄ ምንሊክን 100ኛ አመት መታሰቢያ በተመለከተ
''አፄ ምንሊክ ለእዚህ ትውልድ አርአያ የሚሆኑ ብዙ ነገሮች አሉዋቸው።አፄ ምንሊክ መልካም መሪ አልነበሩም የሚሉ ካሉ መብታቸው ነው።እኛ እሳቸውን እየዘከርን ያለነው ለሀገር ግንባታ ባደረጉት መልካም ነገር ነው።ለአፍሪካ ሕዝብ ነፃነት ተምሳሌት በመሆናቸው እንዘክራቸዋለን።'ጡት ቆረጡ' እንደዚህ ነው እንደዛ ነው ብሎ በመናገር በ 21ኛው ክ/ዘመን ፕሮፓጋንዳ ሠርቶ፣ጥላቻ ዘርቶ ፖለቲካ እሰራለሁ በእዚህም እታመናለሁ የሚል ስብስብ ካለ ውጤታማ የሚሆን አይመስለኝም።'' ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ለሕብር የሰጡት ቃለ-ምልልስ
ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
No comments:
Post a Comment