ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, December 31, 2014

ህወሃቶች በደደቢት ለአርቲስቶቹ የነገሯቸው እና ያልነገሯቸው ታሪኮች ሁሉ የሚያሳዩት አሁንም ህወሓት ስለመንደሩ እንጂ ለኢትዮጵያ አለመቆሙን ነው።(የጉዳያችን ዘገባ)


ፎቶ -በ1997 ዓም በአዲስ አበባ በአጋዚ ጦር የተገደሉ ኢትዮጵያውያን 

መንደርደርያ 

ኢትዮጵያ በታሪክ የእርስ በርስ ጦርነትን እንደ ትልቅ ታሪክ የምትዘክር ሀገር ሆና አታውቅም።እንደዚያ ቢሆን ኖሮማ ዘመነ መሳፍንት የብዙ የእርስ በርስ ጦርነቶች ባለ ታሪክ ነበር።ሆኖም ግን የወቅቱ የሀገራችን መሪ ግዜያዊ ድል ሲያገኝ  የእኔን ማሸነፍ የኢትዮጵያ ታሪክ አድርጉልኝ ሲል አልተሰማም።ጉዳዩ የእርስ በርስ ጦርነት ነዋ! በተቃራኒው ግን ኢትዮጵያ ለነፃነቷ እና ለአንድነቷ የሞቱላትን ከህወሓት በፊት የነበሩት የኢትዮጵያ መሪዎች ትልቅ ቦታ ሰጥተውት ኖረዋል።እነኝህ መሪዎች ከጣልያን ጋር የነበረውን ትንቅንቅ ዘከሩ እንጂ ለስልጣን የተደረጉ ውግያዎችን የኢትዮጵያ ትልቁ ታሪክ ነው ብለው አልተሟገቱም።ህወሓት ግን ያለፉትን ለኢትዮጵያ የሞቱትን እየነቀፈ እና እየወቀሰ ሲመቸው ደግሞ ለማደብዘዝ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ እየከፈተ ኢትዮጵያ የተፈጠረችው ደደቢት ላይ ነው መሰል ንግግር ሊያሰማን ይዳዳዋል።

ፖለቲከኞችን ማሳመን ያልቻለው ህወሓት ለአርቲስቶች ምን ነገራቸው? 

ሰሞኑን አርቲስቶችን አሳፍሮ ደደቢት ላይ የከረመው የወያኔ አመራር ቡድን 150 ሚልዮን ብር ወጪ(ለፀጥታ ጥበቃ፣ትራንስፖርት፣ለሁሉም አርቲስቶች የቀን አበል፣የምሽት እራት እና ዳንስ ወዘተ)  መውጣቱን የውስጥ አዋቂ ዘገባዎች ዘግበዋል።አርቲስቶቹም ድራማ ሲሰሩ ከርመዋል።ሰው ለሰው ድራማ በዋና አክተሩ ተወክሏል፣የህወሓት የዛሬ የአዲስ አበባ እና መቀሌ ህንፃ ባለቤቶች ሲደንሱ ታይተዋል።ለአርቲስቶቹ በእርስ በርስ ጦርነት ወቅት እንዴት ድልድይ እንደፈረሰ፣የቱ ጋር ትግራይን ለመገንጠል እንደተዶለተ፣የቱ ድንጋይ ላይ ተቀምጠው  ለሻብያ የምፅዋ ጦርነት የትግራይ ልጆች እንዲላኩ እንደተወሰነ፣የቱ ጋር ስለ ብሔር ብሔር በሚል ሽፋን የኢትዮጵያ ጉድ የሆኑትን ጉድ የብሔር ድርጅቶች ለመፈልፈል ህወሓት እንደዶለተች ተነገረ።

ለአርቲስቶቹ ከተናገሩት ውስጥ አቶ ስዩም መስፍን፣አቦይ ስብሐት እና ሳሞራ የኑስ እንዴት ኢህአፓን እና ኢድዮን እንዴት ከትግራይ እንዳስወጡ ተተረከ።አቦይ ስብሃትም በመሃል የሚያስቆማቸውን ሳል እየሳሉ ሲቀጥሉ እንዲህ አሉ ''የቀድሞዎቹ ተቃዋሚዎች ሁሉም የተሰገሰጉት የቀደመውን ስርዓት ለመመለስ የሚፈልጉ ነበሩ'' ካሉ በኃላ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ችግር የብሔር ችግር ነው ካሉ በኃላ የብሔር ችግርን ''የማይታረቅ ቅራኔ'' ሲሉ ስደመጡ ተሰብሳቢውን አስደንግጧል።

ቀጥሎ ከተናገሩት ውስጥ አቶ በረከት ነበሩ።አቶ በረከት አቦይን የወረፉበት ንግግር አቦይን ''ድራማቲክ'' አቀራረብ ያለው ሲሉ ተደምጠዋል። አቶ በረከት የገለጡበት መንገድ እንዲህ ይነበባል -''የአቦይ ስብሐት አይነት ድራማቲክ አቀራረቦች ስንሰማ ልንዋጥ እንችላለን።በታሪክም ልንጠፋ እንችላለን'' በማለት ነበር።የሁሉም ንግግሮች ያጠነጠኑት ትግራይ በሌላው ኢትዮጵያ ላይ የበላይ እንደሆነ ማብራራት ነበር።ደደቢት ላይ ህወሓት ባይመሰረት ኖሮ ኢትዮጵያ ትጠፋ እንደነበር ለመግለፅ መድከም ሌላው ለማስተላለፍ  የታሰበው መልዕክት ነበር።

ህወሓት የፖለቲካ ማሳመኛው ፍልስፍናው ሁሉ ተሟጦ የቀረው የደርግ ዘመንን ደጋግሞ ማንሳት ብቻ ሆኗል።አሁን ኢህአዴግን ፖሊሲህ ዘመን ያለፈበት በቂም፣በዘር እና በበቀል የታሸ ነው የሚለው ደግሞ ኢህአዲግ አዲስ አበባ ሲገባ ገና በእግራቸው መቆም ያልቻሉ ሕፃናት የነበሩ ወይንም ገና ያልተወለዱ ናቸው።ህወሓት የኢትዮጵያን ሕዝብ ዲሞክራሲ የነጠቀ፣በጠራራ ፀሐይ ድምፄ ተሰረቀ ያሉ ወጣቶችን በጥይት የቆላ፣ብሔር ከብሄር በማጋጨት ከእራሱ የወጡ አባሎቹ የመሰከሩበት፣አባላቱ በሙስና በሰበሰቡት ገንዘብ መሃል አዲስ አበባ እና መቀሌ ላይ ባለ ሰባት ፎቅ ሲገነቡ እፍረት የማይሰማቸው አባላት ያሉት ወንጀለኛ ድርጅት መሆኑን የሚሞግቱት አሁንም ወያኔ አራት ኪሎ ቤተ መንግስትን ሲቆጣጠር በእናታቸው እቅፍ ሆነው ጡት የሚጠቡቱ ናቸው። በመሆኑም ተከራክሮ የማያሳምነውን ትውልድ ሸሽቶ ስለፖለቲካ ቢናገሩ እናንተን አይመለከትም ለማለት የሚቀሉትን አርቲስቶችን መማፀኑ ካለተከራካሪ የእኔን ብቻ ስሙኝ ስልት መሆኑ ነው።

 ህወሓት ለአርቲስቶች ያልነገራቸው 

የህወሓት መሪዎች አርቲስቶቹን ፈረንጆቹ ''ዱላ እና ካሮት'' በሚሉት አስተያየት እያዩ እና አንዳንዴ ፈገግ መልሰው ኮስተር እያሉ በማሳቀቅ የተረኩት ሁሉ ዛሬ ላለችው ኢትዮጵያ እና ዓለማቀፋዊ ሁኔታ ፋይዳው ምንድነው? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው። የስብሰባው ዋና ዓላማ ህወሓት የተንጠለጠለበት የጎሳ ፖለቲካ እንዳይበጠስ በመስጋት የጎሳውን ታላቅነት የሰበከ መስሎ ብዙዎች አይናቸውን ተክለውባቸዋል ባለው አርቲስቶች በኩል ህዝብን ማስፈራራት፣ተስፋ ማስቆረጥ እና ''መጪውም ገዢዎችህ እኛ ነን።'' የሚል መልእክት ለሕዝቡ ማስተላለፍ ነው።''መጪው ምርጫንም ክደደቢት አንፃር ተመልከቱ እና እንዴት ነው በካርድ ስልጣን እንድለቅ የምታስቡት?'' የሚልም ቃና አለበት።

እዚህ ላይ ግን አምባገነኖች የራሳቸውን ታሪክ እራሳቸው ከሚተርኩት በዘለለ ነፃ የታሪክ ምሁራን የራሳቸውን ምርምር አድርገው ታሪክ እንዲፅፉ አይፈልጉም እና ተራክዎችም ሆነ ሰሚዎች እራሳቸው እንደሆኑ የመቃብር ጉዞ ይጀምራሉ።እዚህ ላይ ህወሃቶች ለአርቲስቶቹ ያልነገሯቸውን ማንሳት ተገቢ ነው።
 • አቦይ ስብሐት፣አቶ ስዩም እና አቶ በረከት ቢቢሲ ስላረጋገጠው ህወሓት ለትግራይ ሕዝብ በ 1977 ዓም እረሃብ የመጣውን የዕርዳታ እህል ሱዳን እየተወሰደ ይሸጥ እንደነበር እና የጦር መሳርያ ይገዛበት እንደነበር አልነገሩትም።
 • በደርግ ዘመን በአሶሳ የአማራ ተወላጅ ናችሁ ተብለው በአንድ ቤት ተከተው በእሳት ስለተቃተሉት ምንም አላሉም።
 • ኤርትራ ከኢትዮጵያ ትለይ ብለው እስከ ምፅዋ እና ከረን ድረስ የትግራይ ተወላጆች ደም እንዲገብሩ መላካቸውን አላነሱትም።
 • ህወሓት እስካሁን ድረስ በአሜሪካ የሽብር መዝገብ ላይ እንደሰፈረ መሆኑን ትንፍሽ አላሉም።
 • በህወሓት የተሳሳተ ፖሊሲ ሳብያ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሴት እህቶቻችንን ለአረብ ሀገር መከራ መዳረጋቸውን ያነሳ የለም።
 • በህወሓት ውሳኔ በሺህ የሚቆጠሩ ሕፃናት ለጉድፈቻነት መዳረጋቸው እና በለውጡ ህወሓት ብዙ ሚልዮን ዶላር ማትረፉን ትንፍሽ ያለ የለም።
 • ህወሓት ከተሞች በጎዳና ተዳዳሪዎች፣ወጣቶች ለጫት እና ለሽሻ፣የዩንቨርስቲ ምሩቃን የኮብል ስቶን ሥራ ሰራተኛ እንዲሆኑ የተደረጉት በዘመነ ህወሓት መሆኑን ለመናገር የደፈረ የለም።
 • በከተሞች የሚኖሩ ብዙ ሺዎች የገዛ ቤታቸው በግሬደር ሲፈርስ እና የጎዳና ተዳዳሪ የሆኑት በህወሓት ዘመን መሆኑን ህወሀቶች አላነሱትም።
 •  ገበሬው ለዘመናት ከኖረበት ቦታ በጎሳ እና በቋንቋ እየለዩ ለዘመናት ከኖረበት ቦታ የተፈናቀለው በዘመነ ህወሓት መሆኑን ያወሳ የለም።
 • አስራሶስት የህወሓት አመራሮች በስዊድን ዓለም አቀፍ የጦር ፍርድ ቤት በዓለም አቀፍ ወንጀለኛነት ከተከሰሱ ገና ቀናት እየተቆጠሩ መሆናቸውን ሊያስታውሱ አልፈለጉም። 
ከሁሉም የሚገርመው ህወሃቶች ከአርትስቶቹም ሆነ ከትግራይ ሕዝብ የደበቁት ትልቅ ጉዳይም አለ።የሀውዜን እልቂትን ጉዳይ።ይህንን እልቂት አቦይ ስብሐት አዲስ የማስቀየሻ ያሉትን ሃሳብ ይዘው ቀርበዋል።''በጉዳዩ ላይ የእስራኤል እጅ አለበት'' ነበር አቦይ ያሉት።መቸው ህወሃቶች ከገደሉ ወይም ከተኮሱ አልያም ከተናገሩ በኃላ ነው ማሰብ የሚጀምሩት።ለእዚህም ነው ነገሩን ከመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ጋር በማያይዝ ከአረብ ሃገራት ያተረፉ የመሰላቸውን የተናገሩት። ከህወሓት የለቀቁት የቀድሞ ከፍተኛ ባለስልጣናቱ ግን በሃውዜን እልቂት ላይ የህወሓት ቁልፍ ባለስልጣናት እጅ ሆን ተብሎ የተቀናበረ መሆኑን ያብራራል።አቶ ገብረ መድህን አርአያ፣አቶ ግደይ እና አቶ አብርሃም ያየህ በተለያየ ጊዜ በጉዳዩ ላይ ማብራርያ ሰጥተዋል።ከእዚህ በታች የአቶ ገብረ መድህን የቀድሞው የህወሓት መስራች እና የፋይናንስ ኃላፊ በሃውዜን እልቂት ህወሓት አቀናባሪ እንደነበር እና ምክንያቱንም ጭምር እንዲህ ያብራራሉ።

''“ወይ፡ ሀውዜንም የወያኔ ድራማ ነው።” በዚያን ጊዜ ሕወሀት በምትሰራው ስራ ምክንያት እጅግ በጣም ተጠልታ ነበር። ሰው አጣች። ምልምል ጠፋ። እናስ? ተንኮል አሰቡ። የዚያን ግዜ የትግራይ አስተዳዳሪ ለገሰ አስፋው ነው። ከዚያ ወያኔ ሀውዜን አንድ ክ/ጦር እያስገባች እያስወጣች ወያኔ ሀውዜን ስብሰባ ልታደርግ ነው የሚል ወሬ ለደርግ ደህንነት እንዲደርሰው አደረገች። ሀይሉ ሳንቲም (ሳነቲም ቅጽል ስሙ ነው) የሚባል የወያኔ የጦር ደህንነት፡ የወያኔ ጦር ሀውዜን ሊሰበሰብ ነው የሚለውን መረጃ ለለገሰ አደረሰ። እውነት እንዲመስልም፡ በገበያው ቀን የተወሰኑ ታጋዮች ባካባቢው ውር ውር ሲሉ እንዲታዩ ተደረገ። የሀውዜን ገበያ መቼም እጅግ የታወቀ ነበርና ከብዙ ቦታ ብዙ ሰዎች ለንግድ ይመጣሉ። በእለቱ ስድስተ የደርግ ሚጎች እየተመላለሱ በመስቀልያ ቅርጽ፡ ገበአውን ደበደቡት። ይሄ ሁሉ ሲደረግ ቪዲዮ ይነሳ ነበር። ነገሩ ለረጅም ግዜ የተቀነባበረ መሆኑ የሚታወቅባቸው ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው። ወደ አስራ ሁለት ፎቶ አንሺዎች ሱዳን ውስጥ ሄደው እንዲሰለጥኑ ተደርጓል። ገብሬ የዚያን ግዜ ቪዲዮ ካሜራ አያውቅም ነበር። እነ ተክለወይን አስፍሀ፡ እነ ሱራፌል ምህረተአብ፤ እነ እያሱ በርሄ ካሜራ ቀራጭነት ሱዳን ውስጥ ተምረው መጡ። ያ ሁሉ ድብደባ ሲደረግ ተራራ ላይ ቆመው እያንዳንዱን ሚግ ከሁሉም አቅያጫ ቪዲዮ ያነሱ ነበር። ይቀርጹ ነበር። በነጋታው ይሁን ማታውኑ ያ ሁሉ ፊልም ሱዳን ውስጥ በቲቪ ታየ። ገበያ ላይ የሞተው ሰው እንሰሳ፡ ህዝብ፡ ሽማግሌ ሕጻናት በቲቪ በደንብ ተቀርጿል።'' ብለዋል።

የምንስ ለቅሶ መልሶ መልሶ 

ባጠቃላይ ህወሓት በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ምንም አይነት አሻራ የለውም የሚል እምነት የለም።ሆኖም ግን መታሰብ ያለበት ጉዳይ ዛሬ ላይ በሞቱት አጥንት ላይ ተቀምጠው፣በሙስና በስብሰው፣ዲሞክራሲን በእግራቸው እረግጠው እና በርካታ ግድያ ፈፅመው የሞቱትን እያነሱ መመፃደቅ አሁንም በሞቱት ላይ መሳለቅም አያጣውም።ለሕወሃቶች የምመክራቸው ሴኮቱሬ ከደደቢት ያስተላልፍ የነበረውን ፕሮፓጋንዳ ዛሬ ላይ ደግመው ማንበብ ቢችሉ የሚል ነው።ካልረሱት ሴኮቱሬ በእየለቱ በሚተላለፈው የህወሓት ራድዮ የኢትዮጵያን ሕዝብ እንዲህ ይለው ነበር - ''ትግላችን የኢትዮጵያ ሕዝብ ካለምንም ገደብ የመፃፍ፣የመናገር እና ሃሳብን በነፃት የመግለፅ ነፃነትን ለማረጋገጥ ነው።ትግላችን ህዝቦች ካለ አንዳች ፍርሃት ሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርጉበትን በፈለጉት የሀገሪቱ ቦታዎች የመኖር መብታቸው እንዲረጋገጥ ነው'' ይል ነበር። ለእዚህ ነዋ ''ህገ መንግስቱ ይከበር'' ያሉትን ንፁሃን ወጣቶች እስር ቤት የምታማምቁት? ለእዚህ ነዋ ! ''ነፃነት ለፍትሃዊ ምርጫ'' ብለው የተሰለፉትን የሰማያዊ ፓርቲ እና የዘጠኙን ፓርቲዎች ጥሪ በድብደባ መባረራቸው እና መታሰራቸውን።ባጭሩ በደደቢት ህወሃቶች ለአርቲስቶቹ የነገሯቸው እና ያልነገሯቸው ታሪኮች ሁሉ የሚያሳዩት አሁንም ህወሓት ስለመንደሩ እንጂ ለኢትዮጵያ አለመቆሙን ነው።

ጉዳያችን ታህሳስ 23/2007 ዓም (ጃንዋሪ 1/2015)

Tuesday, December 30, 2014

ሰበር ዜና - ባለፈው ቅዳሜ ታህሳስ 18/2007 ዓም ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በየመን የባህር ዳርቻ በድጋሚ አደጋ ደርሶባቸዋል።ከጥቂት ሳምንታት በፊት የደረሰውን ተመሳሳይ አደጋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ''አደጋ አልደረሰም'' ነበር የሚል መግለጫ ዛሬ መስጠቱ ኢትዮጵያውያንን አስቆጥቷል።


አደጋውን አስመልክቶ ''የመን ታይምስ'' የለጠፈው ፎቶ 

ባለፈው ቅዳሜ ታህሳስ 18/2007 ዓም ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በየመን የባህር ዳርቻ አደጋ ደርሶባቸዋል።ከጥቂት ሳምንታት በፊት የደረሰውን ተመሳሳይ አደጋ ''ቢቢሲ'' እና ''አልጀዚራ'' ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ የዓለም የዜና አውታሮች ቢዘግቡትም  ዛሬ ማክሰኞ ታህሳስ 21/2007 ዓም  የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ''ምንም አደጋ አልደረሰም'' በሚል ድፍን ያለ አረፍተ ነገር በኢቢሲ ዜና ላይ በማስነበብ ክዶታል።

የእዚህ አይነቱ የደረሰውን አደጋ በአግባቡ ከማጣራት ይልቅ ''የሞተ የለም ውሸት ነው'' በሚል ዜና ብቻ የኢትዮጵያውያንን ሕይወት እንደ ዋዛ መታለፉ የብዙዎቻችንን ልብ ያደማ ጉዳይ ነው።ይህ በእንዲህ እያለ ነው ሌላ አደጋ አሁንም ከየመን የተሰማው።ይህንን የቅዳሜ ታህሳስ 18/2007 ዓም አደጋ ''የመን ታይምስ'' እንዲህ ዘግቦታል-

17 ETHIOPIANS DROWN OFF DHUBAB COAST IN TAIZ
source - Yemen Times 
SANA’A, Dec, 29—Upwards of 17 Ethiopian migrants and one Yemeni smuggler drowned when the boat transporting them capsized off the coast of Dhubab city in Taiz governorate on Saturday evening, according to Shuja Mahdi, chief officer of the National Coast Guard Operations Department. 

    Ten Ethiopians survived the capsizing and were able to swim ashore, he said.  

Nick Stanton, a communications officer with the UN Refugee Agency (UNHCR) in Yemen, told the Yemen Times on Monday that as of now the UN has received reports that five Ethiopians had died in the incident. 

The Yemen Times contacted Birhane Meskal Kihisen, a member of the Diaspora Engagement Affairs Department at the Ethiopian Embassy, who claimed that his office had yet to receive any information regarding the incident.

Local fishermen were the first to be notified that the boat had capsized, according to Mahdi. They were radioed by the Yemeni smuggler who was aboard the ship. He called them to launch a rescue attempt. However, fishermen did not arrive in time, according to Mahdi. Those that survived swam ashore themselves. The fishermen later arrived at the coastline and helped transport the survivors to health clinics in Dhubab city.

Waters around the Gulf of Aden become hazardous between July and December, and so smugglers prefer to bring migrants into the country via the Dhubab and Al-Mokha coastlines located in Taiz governorate. 

Whatever the route taken, the trek across the water remains a perilous journey that a growing number of Africans seem to be willing to risk. A vessel carrying 70 migrants capsized in the Red Sea on Dec. 5, with anywhere between 18 to 21 dying in the incident according to the UNHCR.

According to the Interior Ministry, coast guards have arrested 18 smugglers in 2014. While the national coast guard is not tasked with rescuing illegal immigrants, officer Mahdi says he and his colleagues do what they can to help those in danger. 

The UNHCR reported that 65,000 migrants arrived on Yemen’s shores in 2013. Earlier this month, Zaid Alalaya, a public information officer with the UNHCR reported that 240 migrants had drowned in Yemen this year, more than in 2012 and 2013 combined. 

Stanton told the Yemen Times that Sept. 2014 had witnessed the largest number of African migrants coming to Yemen from the Horn of Africa, with more than 12,800 fleeing from Ethiopia, Somalia and other countries. A continued spike in human rights abuses and drought in southern Somalia were the main factors behind this increase, he said.

Saturday, December 27, 2014

How free and fair election on May, 2015, could run in Ethiopia? where as a prominent politician is pushing to leave his job that served for more than a quarter century just because of his out look, Prof. Merara Gudina. Who is who? ( ጉዳያችን GUDAYACHN Blog short note)

Prof.Merara Gudina
 • Pro.Merera began his college education at Addis Ababa University (AAU), but was imprisoned for seven years due to participating in protests against the dictatorship of Mengistu Haile Mariam. 
 • After his release, Merera went to Egypt to complete his education at the American University in Cairo.
 • Merera received his doctorate July 2002 from the Institute of Social Studies, at the Hague in the Netherlands. 
 •  He completed his thesis, "Ethiopia: competing ethnic nationalisms and the quest for democracy, 1960-2000".
 • As of 2009,Merera is an associate professor of political science at AAU. He participates in several scholarly conferences worldwide, including in the United States, concerning political and social developments of Ethiopia.
 • Yesterday Dec.26,2014,very sad news heard from Addis Ababa University.According toESAT(Ethiopian Satellite Television),at the result of  the direct political intervention of the ruling party on Addis Ababa University's academic right, Dr.Merara is obliged to leave his job where he served for more than a quarter century ( twenty-five years). 
How free and fair election on May, 2015, could run in Ethiopia? where  as a prominent politician is pushing to leave his job that served for more than a quarter century just because of his out look, Prof.Merara Gudina. 


ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG


TAHISAS 19/2007 EC (December 28/2014)

Friday, December 26, 2014

የስርዓቱ ቡድን መሪዎች እና ጀሌዎቻቸውን ፋሽሽታዊ ባህሪ የሚያሳይ ተግባር - በባህር ዳር የአንድ እንግሊዛዊን ድንገተኛ ሞት እየመረመርኩ ነው ያለው ወያኔ/ኢህአዲግ ''በታህሳስ 9/2007 ዓም የአምስት ሰዎችን ሞት እና የአንድ መነኮሳይትን ጨምሮ የሌሎች በርካታ ኢትዮጵያውያን ደም መፍሰስ ትክክል ነበር'' የሚል ሰልፍ እያዘጋጀ ነው።


ፎቶ -ታህሳስ 9/2007 ዓም የቤተ ክርስቲያን ይዞታን መንግስት ያክብር ብለው ከምዕመናን ጋር ከተሰለፉት ውስጥ በጥይት የተመቱ መነኮሳይት 

ወንበዴ መሪ በሆነበት ሀገር ፍትህ መቀለጃ ትሆናለች።ሕግ፣ስርዓት እና ምክንያታዊነትን ዜጎች ቢናፍቁም ህገወጦች ስልጣን ከተቆናጠጡ ዙርያቸውን በሀገር ውስጥ እና በባህር ማዶም ጭምር የሚኮለኩሏቸው ለሆዳቸው እና ለጥቅማቸው ብቻ የሚሰለፉቱን ነውና ብዙ ጆሮ የሚጠልዙ ነገሮችን መስማት ይለመዳል።

ታህሳስ 9/2007 ዓም በባህር ዳር ከተማ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን ይዞታነት የመስቀል ደመራ እና የጥምቀት በዓል የሚከበርበት ቦታ ለግል ባለ ሀብት የሚተላለፍ መሆኑ እና ከቀሪው ቦታ ላይ ደግሞ ተቆርጦ ለመንገድ ሥራ የሚውል መሆኑ እንደተሰማ የባህር ዳር ነዋሪ የእምነቱ ተከታይ በከፍተኛ ቁጣ ወጥቶ ተቃውሞውን መግለፁ ይታወሳል።

በወቅቱ የስርዓቱ ታማኝ ወታደራዊ ፖሊሶች በሰላማዊ ሰልፈኛው ላይ በወሰዱት ጨካኝ እና አረመኔያዊ ተግባር 5 ሰዎች ሲሞቱ አንድ ደካማ መነኮሳይት እና በርካቶች በዱላ እና በጥይት ጉዳት እንዲደርስባቸው ሆኗል።ጉዳዩን አስመልክቶ በዕለቱ በምሽቱ 2 ሰዓት  የስርዓቱ ልሳን በሆነው በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የተላለፈው ዜና ሰላማዊ ሰልፈኞቹን ''ከሽብርተኛ ወገኖች ጋር የወገኑ፣''ወዘተ የሚል አሳፋሪ ዜና ከመለቀቁም በላይ ምንም አይነት ይቅርታ ከመንግስት አለመጠየቁ እና ይልቁንም ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታት ቤተ ክህነት አንዳችም አይነት መግለጫም ሆነ አሁን በመንበሩ ላይ የተሰየሙት ፓትሪያርክ አቡነ ማትያስ አንዳችም የሚያፅናና ቃል ለምእመናን በቦታው ተገኝተው አለማስተላለፋቸው ይታወቃል።

የእዚህ አይነቱ አሳፋሪ ተግባር ምዕመናንን በእጅጉ አስቆጥቶ ሳለ ነው እንግዲህ ሌላ አሳፋሪ አረመኔያዊ ተግባር በሕዝቡ ላይ ሊፈፀም መሆኑ የተሰማው።በባህር ዳር የአንድ እንግሊዛዊን ድንገተኛ  ሞት እየመረመርኩ ነው ያለው ወያኔ/ኢህአዲግ ''በታህሳስ 9/2007 ዓም የአምስት ሰዎችን ሞት እና የአንድ መነኮሳይትን ጨምሮ የሌሎች በርካታ ኢትዮጵያውያን ደም መፍሰስ ትክክል ነበር'' የሚል ሰልፍ እያዘጋጀ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ዜናውን ''ነገረ ኢትዮጵያ'' በማኅበራዊ ድረ-ገፁ ለቆታል።ጉዳዩ ከፍፁም የለየለት ዘረኛ እና አረመኔያዊ ድርጊት ከመሆኑም በላይ  የስርዓቱ ቡድን መሪዎች እና ጀሌዎቻቸውን ፋሽሽታዊ ባህሪ በትክክል የሚያሳይ ነው።

የነገረ ኢትዮጵያን የዛሬ ታህሳስ 17/2007 ዓም ዜና ከእዚህ በታች ያንብቡት።

ገዥው ፓርቲ ባህርዳር ላይ የተደረገውን ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ የሚቃወም የድጋፍ ሰልፍ ሊጠራ ነው በሰልፉ የማይገኝ ቅጣት ይጠብቀዋል ተብሏል።


ገዥው ፓርቲ በአማራ ክልል አስተዳደር ባህር ዳር ከተማ የቤተ ክርስቲያን ንብረት የሆነውን የታቦት ማደሪያ ለመንገድና ለጥቃቅንና አነስተኛ ሱቆች መስሪያ እንዲነጠቅ ማዘዙን ተከትሎ በባህር ዳር ቀደም ሲል የተካሄደውን ህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ የሚቃወም የድጋፍ ሰልፍ ሊጠራ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡
መንግስት ታህሳስ 9/2007 ዓ.ም የተደረገውን ህዝባዊ ተቃውሞ የ‹‹ፀረ ሰላም ኃይሎች እጅ እንዳለበት›› በመግለጽ ‹‹ህገ-ወጥ ሰልፍ›› ማለቱ የሚታወስ ሲሆን ባህር ዳር ከተማ የሚገኙት የቀበሌ ካድሬዎች የተደረገውን ህዝባዊ ተቃውሞ የሚቃወም የድጋፍ ሰልፍ ለማድረግ እያስተባበሩ እንደሚገኙ ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ የቀበሌ ካድሬዎች በየ ቤቱ እየሄዱ የነዋሪዎችን ስም በመመዝገብ በሰልፉ የማይሳተፍ ሰው ቅጣት እንደሚጠብቀው እያስጠነቀቁ እንደሆነ ተገልጾአል፡፡ የድጋፍ ሰልፉ ታህሳስ 21 ወይንም 22 ቀን 2007 ዓ.ም ይደረጋል ተብሎ ይታሰባል፡፡ 

ምንጭ - ነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia
የታህሳስ 9ኙን ዕልቂት ፎቶ በከፊል ለማየት ይህንን ይጫኑ።

ጉዳያችን 
ታህሳስ 17/2007 ዓም 

Tuesday, December 23, 2014

Saturday, December 20, 2014

The killing of innocent Ethiopian Orthodox Tewahido church followers by TPLF government forces, November 19/2014 ( Look at massacres photos) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን ምዕመናን ላይ የተፈፀመ የጅምላ እልቂት (ፎቶዎች)


Friday November 19/2014 was a black day of Ethiopians. Ten thousands of Ethiopian Orthodox Tewahido church followers protested the TPLF government's illegal cut of the church's plot of land located at BahrDar town.

Bahrdar town is one of the most important centre to Ethiopian Orthodox church.It is surrounded by Ancient  Monasteries and their Islands. The Holy Monasteries are aged more than thousand years.

According to ESAT, Washington D.C based Ethiopian television report, the friday incidence was followed by  the death of 5 and many others wounded. The tension is still high.
International community must respond urgently against the barbaric act of TPLF on Ethiopian Orthodox church followers.
Look at some photos of TPLF police forces barbaric act on peace full protesters.

Wednesday, December 17, 2014

በአዲሱ የአውሮፓውያን 2015 ዓም ዓለም ለአዲስ የፖለቲካዊም ሆነ የምጣኔ ሀብታዊ የቅርፅ እና የይዘት ለውጥ እየተዘጋጀች ይመስላል (የጉዳያችን ጡመራ ምልከታ)ከፍልስጤም እስከ ኩባ 

ዛሬ ሮብ ታህሳስ 8/2007 ዓም አዲሱ የፈረንጆቹን ዓመት ሊገባ አስራ ሶስት ቀናት ብቻ ቀርተውታል።በእዚሁ ዕለት ግን ላለፈው ግማሽ ክ/ዘመን ያልተፈቱ የፖለቲካ ውጥረቶች አዲስ ቅርፅ እና ይዘት መያዛቸው ተነግሯል።ከእዚህ ውስጥ የመጀመርያው  የአሜሪካ እና የኩባ ግንኙነታቸውን ሊያድሱ መሆኑ ዛሬ መነገሩ ነው።ይህ ማለት አሜሪካ እና ኩባ ከ1954 ዓም ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ይኖራቸዋል ማለት ነው።

ሁለተኛው  በስዊድን የተጀመረው እና ለዓለማችን ትልቁ የፀጥታ ችግር የሆነውን የፍልስጤም  ግዛት በመንግስትነት የመታወቅ ጥያቄ ጉዳይ ነው።ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ፍፃሜ በኃላ የፍልስጤም ጉዳይ በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ ቢተላለፍበትም ተግባራዊ መሆን ያልቻለው የፍልስጤም የመንግስትነት የመታወቅ ጉዳይ ዛሬ የአውሮፓ ሕብረት ''በመርህ ደረጃ'' የፍልስጤምን  መንግስትነት ማወቁን በመግለፅ ድምፅ ሰጥቷበታል።የሩስያ የመገናኛ ብዙሃን ''ለይምሰል'' (symbolic) በማለት የጠሩት ይህ ውሳኔ ምን ያህል  በመካከለኛው ምሥራቅ የኃይል ሚዛን ላይ ተፅኖ እንደሚኖረው በሂደት የሚታይ ጉዳይ ይሆናል። 

በሌላ በኩል ይህ ዕውቅና የመስጠት ሂደት ከእስራኤል  የሚገጥመው የተግዳሮት ደረጃ የከፋ እንደሚሆን ይጠበቃል።ከእዚህ ጋር በተያያዘ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ለዘመናት አሸባሪ ያለውን ''ሐማስን'' ከአሸባሪነት መዝገብ መፋቁ ሌላው ከፍልስጤም ጉዳይ ጋር በተያያዘ ዛሬ የተደመጠ አዲስ ዜና ነው።እስራኤል በተለይ የሀማስ ከሽብርተኛ መዝገብ መነሳት ''መውጊያው ባንተ ይብሳል'' የሚል ቃና ያለው ንግግር ተናግራለች።''የሐማስ ችግር ከእስራኤል ይልቅ ለእራሱ ለአውሮፓ ይከፋል'' ነበር እስራኤል ያለችው።

የሩስያ ጉዳይ 

ሌላው ከላይ ከተጠቀሱት የዛሬው የሃገራት የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ለውጦች ጋር በቀጥታ ግንኙነት የሌለው የሚመስለው ግን የቀዝቃዛው ጦርነት መፋፋም አመላካች የሆነው እና በክረምያ ጉዳይ ሳብያ በሩስያ ላይ እቀባ ያወጀው የምዕራቡ ዓለም የሩስያ ገንዘብ ሩብል መውረዱን በመገናኛ ብዙሃኑ ደጋግሞ እየተናገረ ነው።የሩስያ ቲቪ (አር ቲ) በተቃራኒው የሩብል መውረድ ''የሩብልን ትክክለኛ ዋጋ አያሳይም።ጊዜያዊ 'ንዝረት' ነው'' እያለ ነው።ነገ ሐሙስ ታህሳስ 9/2007 ዓም  የሩስያው ፕሬዝዳንት ፑቲን  በጉዳዩ ላይ የቀጥታ ንግግር  ለህዝባቸው ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል ዛሬ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን ''ሩስያ ከዓለም ኢኮኖሚ እየተገለለች ነው።ይህም ለዓለም ሕግ ያለመገዛቷ ውጤት ነው'' ሲሉ ለፓርላማ ተሰብሳቢዎቻቸው ተናግረዋል።ሁኔታውን ለተመለከተ ግን ሩስያ ከምዕራቡ ገበያ በእቀባ ስምም ይሁን በሌላ መራቋ የበለጠ የማጠንከር ከእዚያም አልፎ ከደቡብ እስያ ሃገራት ጋር ልትመሰርት ካለችው የገበያ ቀጠና ጋር ከምዕራቡ ምጣኔ ሀብት ያላትን ትስስር እያላላ ወደ እስያ አድማሷን ያሰፋላት እንደሆነ እንጂ ትልቅ ንዝረት ይፈጥራል ተብሎ ማሰብ ይከብዳል።ይልቁንም ሩስያ ከምዕራቡ  ገበያ በተገለለች ቁጥር የእራሷን የንግድ ቀጠና ለመፍጠር እና ወደ ባልካን ሀገሮች መስፋፋቷ ልትቀጥል ትችላለች።ከእዚህ ሁሉ ጋር ግን የዓለማችን ትልቁን የመሬት የቆዳ ስፋት የያዘች ባለ 146,300,000  ሕዝብ (የአለምን 2.03%) የያዘች ሀገርን ማግለሉ እና ትንሿን ኩባ ማቅረቡ ውጤቱ  ምን እንደሚሆን ወደፊት የምናየው ነው።

ለእዚህም ይመልሳል ጅም ዮንግ ኪም የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት ዛሬ ''ለሲ ኤን ኤን'' ቴሌቭዥን  እንዳሉት ''የሩስያ ኢኮኖሚ ግዙፍ ኢኮኖሚ ነው በአለማችን ምጣኔ ሀብት ላይም ተፅኖ አለው'' በማለት በጉዳዩ አሳሳቢነት ላይ አፅንኦት የሰጡት።

የነገሮች መፍጠን ግን ዓለም በ2015 እ አውሮፓውያን አቆጣጠር ለሆነ ነገር እየተዘጋጀች ይመስላል።ለሆነ ነገር።ለምን?  የሚለውን አሁን መግለፅ አይቻል ይሆናል።ነገር ግን ለግማሽ ክ/ዘመን የቆዩ ጉዳዮች በውስጥ ድርድር አልቀው አዲስ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ይዘው ብቅ የሚሉት ከመጪው ዓመት የሀገራት ስልታዊ አካሄድ ጋር የትዛመደ እንደሚሆን መገመት ይቻላል።እርግጥ የፍልስጤም ጉዳይ የምዕራቡ ዓለም ከመካከለኛው ምስራቅ በተደጋጋሚ የሚነሳው የሽብርተኝነት ትንኮሳ አንዱ መነሻ የሚያደረገው የፍልስጤምን ጉዳይ በመሆኑ ጉዳዩን ለማስተንፈስ አይነተኛ መልስ መስጠት አስፈላጊነቱ ታምኖበት ይሆናል።ሆኖም ግን ጉዳዩ ከእስራኤል አንፃር የሚኖረው ምላሽ እና ከአሜሪካ ጋር ያላት የጠበቀ ግንኙነት ያለው ተፅኖ ገና አልተለካም።በተለይ በሐማስ አንፃር ያለው ጉዳይ ትልቅ የዓለማችን ትኩሳት መሆኑ አይቀርም።

ዓለም አቀፍ ሕግ  ከዓለም አቀፍ ተቋማት እጅ መውጣት 

በእዚህ ሁሉ መካከል የአፍሪካ እና የመካከለኛው ምስራቅ ስልታዊ ተፈላጊነት እና የተፈጥሮ ሀብት ያላቸው ሀገሮች የውስጥ ቅራኔዎቻቸውን ተከትሎ የዓለም አቀፉ የምጣኔ ሀብት ጦርነትም ሆነ ፖለቲካዊ ግፍያ ሳይነካካቸው ማለፍ አይችልም።ለእዚህ ደግሞ አንዱ ምክንያት የሚሆነው ዓለም አቀፍ ሕግ ቀስ በቀስ እንደ ተባበሩት መንግሥታት ካሉት ዓለም አቀፍ ተቋማት እጅ እየተንሸራተተ መምጣቱ ነው።ከ1982 ዓም ከሩስያው  ሚካኤል ጎርባቾቭ ''ግልፅነት ወይንም ግላስኖስ'' ፖሊስ ወዲህ በዓለም አቀፍ የፀጥታ ጉዳይ ላይ ከተባበሩት መንግሥታት ይልቅ ቀድማ አሜሪካ እና የጦር ሸሪኮቿ ''ናቶ'' በአለማችን ላይ የተነሱትን የፀጥታ ችግሮች  መፍትሄ ጉዳይ  ላይ መክረው ከጨረሱ በኃላ  ወደ  ተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክርቤት የሚወስዱበት አግባብ ተለምዷል።ለእዚህ ብዙ አብነቶችን መጥቀስ ይቻላል።የኔቶ ወረራ በኢራቅ (አንደኛ እና ሁለተኛው)፣በቀድሞዋ ዩጎዝላቭያ ላይ የኔቶ ጣልቃ መግባት ፣በአፍጋኒስታን ላይ እና በሊብያ ላይ የተደረጉት ዘመቻዎች ሁሉ ከተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውይይት ይልቅ የኔቶ ቁርጠኝነት ተጠብቆበታል።

ሆኖም ግን ሩስያ ዘግይታም ቢሆን የምዕራቡን ዓለም የተገዳደረችው ፕሬዝዳንት ፑቲን ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ስልጣን ከመጡ በኃላ ያውም በሶርያ ጉዳይ ላይ ሩስያ የፀጥታው ምክር ቤትን ውሳኔ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብቷ ውድቅ አድርጋ ''ሶርያ ሊብያ እንድትሆን አልፈቅድም'' ብለው ፕሬዝዳንት ፑቲን ከተናገሩ በኃላ ነበር።ፕሬዝዳንት ኦባማ ደጋግመው ፕሬዝዳንት ፑቲንን ለማግባባት ሞከሩ ፑቲን ይብሱን ''ከአልቃይዳ የባሱ አሸባሪ ሰው በላዎች'' ያሏቸውን የሶርያ ፅንፈኛ አማፅያንን ''የምዕራቡ ዓለም መደገፉ ምን ያህል ሰዋዊ አስተሳሰብ እንደራቀው ያሳያል'' ሲሉ በግልፅ ተናገሩ።የምዕራቡ ዓለም ሩስያን ማግለል ጀመረ።በቡድን ስምንት ጉባኤ ላይ ሩስያ ለመጀመርያ ጊዜ ወደኃላ ቀረች።በቅርቡ በተደረገው የቡድን 20 ስብሰባ ላይ እንደ አልጀዝራ ጋዜጠኛ አባባል ''ፑቲን ምሳ ሲበሉም እንዲገለሉ ተደረጉ'' ካለ በኃላ ጋዜጠኛው ''ግን ፑቲንን አጥብቀው የምፈልገው ማን ነው የምዕራቡ ዓለም ነው ወይስ? እና ያገለለው ማነው ፑቲን የምዕራቡን ዓለም አገለሉ ወይስ ምዕራባውያን ሩስያን አገለሉ?'' ብሎ ይጠይቃል።

ከሶርያ ጉዳይ በኃላ የሩስያ ዳግም ''ለአቅመ ልዕለ ኃያልነት'' ሰውነቷን እያሟሟቀች መሆኑን ምዕራቡ ዓለም አወቀ።ትንሽ ዘግይቶ ቅርቡ በዩክሬን ጉዳይ የክሬምያን ጉዳይ ሩስያ የያዘችበት አግባብ የምዕራቡን ዓለም የበለጠ አስደነገጠው።የኢኮኖሚ እቀባ ታወጀ፣የሩስያ የጋዝ ሽያጭ የሚያሳስባት ጀርመንም እያቅማማችም ቢሆን ገባችበት። ሩስያ ባንፃሩ ከአውሮፓ እና አሜሪካ ምንም አይነት የእርሻ ምርት ላለመግዛት ወሰነች።በተለይ ይህ ውሳኔዋ የአሳ ምርት እና የእርሻ ምርት ለሩስያ ያቀርቡ የነበሩ የአውሮፓ ሃገራት የገበያ ቀውስ መፈጠሩ አልቀረም ለአውሮፓዊው ግን አሳ እና አትክልት  አንፃራዊ በሆነ መልክም ቢሆን ከቀድሞው ረከስ ባለ ዋጋ መግዛት ቻለ።

አዲሱ የአውሮፓውያን 2015 ዓም

መጪው 2015 የዓለማችን ሃያላን የበለጠ የገበያ እና የፖለቲካ ፍትግያ ውስጥ የሚገቡበት፣የመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት የህዝብ ብዛት፣ሥራ አጥነት የፅንፈኛ ኃይሎች ወደ ስልጣን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መቅረብ እና ከነዳጅ ቀውስ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች ወደ በለጠ ቀውስ ሊያመሩ የሚችሉበት ዓመት ሊሆን እንደሚችል መገመት ይችላል።ለእዚህም ማሳያ የሚሆነው እነኚሁ የመካከለኛ ምስራቅ ሃገራት የመንግስት ስሪታቸው በፍፁም ፈላጭ ቆራጭነት ላይ የተመሰረተ የቤተሰብ ስልጣን ስለሆነ አሁን በስልጣን ላይ ያሉት በሆነ አጋጣሚ ከስልጣኑ ዘወር ሲሉ ቀውስ እና የጎሳ ግጭት መከተሉ የተለመደ ነው።ለእዚህ ምሳሌ የምትሆነን የጋዳፊዋ   ሊብያ ነች።የሊብያ የአሁኑ ጥያቄ የአንድነት እና የሰላም ጉዳይ ነው።የምዕራቡ ዓለም ደግሞ ጋዳፊ ከወረዱ በኃላ የሊብያን ጉዳይ ከዜና ርዕስነትም ጭምር አውጥቷቷል።

ተመሳሳይ ጉዳይ ለአፍሪካ ሀገራትም ሊገጥማቸው ይችላል።ሆኖም ግን የአፍሪካ ሃገራት ሙስናን ቀንሰው ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እና ጠንካራ የመንግስት ስርዓትን መመስረት ከቻሉ ከሁኔታዎች የሚጠቀሙበት ዕድል ቀላል አይደለም።ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ ስንመጣ ኢህአዲግ/ወያኔን የሚገዳደር ጠንካራ ተቃዋሚ ነጥሮ መውጣቱ የግድ አስፈላጊ የሚሆንበት ጊዜ ነው።ይህ ተቃዋሚም የኢትዮጵያን አንድነት ላይ የማያወላውል አቋም ያለው መሆኑ እና ከጎሳ ፖለቲካ የራቀ መሆኑ ነገ ከኢህአዲግ/ወያኔ በኃላ ለምትኖረው ኢትዮጵያ ብቸኛ ዋስትና ነው።ለሁሉም ግን 2015 የፈረንጆቹ ዓመት አጀማመሩ በአለማችን የፖለቲካም ሆነ የምጣኔ ሀብት ጉዳይ ላይ ብዙ የይዘትም ሆነ ይቅርፅ ለውጦች ይዞ እንደሚመጣ ከወዲሁ እየጠቆመ ነው። በአካባብያችንም ያላለቁ ብዙ አጀንዳዎች አሉ።የደቡብ ሱዳን ጉዳይ ከዑጋንዳ እና ኢትዮጵያ ጉዳይ ጋር መያያዙ፣የሱማልያ ጉዳይ፣ከኤርትራ ጋር ያለው ሁኔታ እና የግብፅ የፍላጎት ትኩረት ከፍተኛ መሆን የሚጠቀሱ ናቸው።

ጉዳያችን (ታህሳስ 7/2007 ዓም (ደሴምበር 17/2014)


Monday, December 15, 2014

ሰበር ዜና - በኢትዮጵያ የስዊድንን አምባሳደር ጨምሮ በ12 ስዊድናውያን ላይ የመግደል ሙከራ ተደረገኢሳት ራድዮ ዛሬ ታህሳስ 6/2007 ዓም  እንደዘገበው በግድያ ሙከራው ላይ የስዊድን የመገናኛ ብዙሃን በብዛት እየዘገቡበት መሆኑን ያብራራል።
እንደ ዘገባው  በኦሞ ስምጥ ሸለቆ ለሽርሽር የሄዱት በኢትዮጵያ የስዊድን አምባሳደርን ጨምሮ ሌሎች 12 ስዊድናውያን የነበሩ መሆኑን እና የተኩስ እሩምታ እንደወረደባቸው ይገልፃል።
አቶ ሞላ ይግዛው በስዊድን የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፎረም ምክትል ሊቀመንበር በጉዳዩ ላይ በሰጡት አስተያየት እንዲህ ብለዋል -

''አስራ ሁለት የስዊድን ዜጎች አምባሳደሩን ጨምሮ  ከሚሄዱት ውስጥ  አራት ሰዎች የጫነው መኪና ላይ  ስዊድናውያንን ለመግደል ያለመ እና ያነጣጠረ ተኩስ ነው የተከፈተው።ከእዚህ ጋር በጥያየዘ ባለፈው ጊዜ H&M የተሰኘው ድርጅትን ያጋለጠ አንድ ጋዜጠኛ በእዛ አካባቢ ወይም ደቡብ ኢትዮያ  የሚደረገውን ግፍ ለዓለም ማጋለጡ እና በዓለም የሌለ ዲክታተር መባሉ ይታወቃል።ከእዛ በፊት  አንድ ቀን የስዊድን የጦር ፍርድቤት ያቀረብነውን የወንጀል ክስ ተቀብሎ ክስ እንደሚመሰርት አስታውቆ ነበር።በመሆኑም ይህንን ያደረገው ወያኔ ነው ሌላ ሊሆን አይችልም'' ብለዋል።

ኢሳት  ራድዮ በመጨረሻ ላይ እንደገለፀው ጉዳዩን የስዊድን ጋዜጦች፣ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ሌሎች  የመገናኝ ብዙሃን ሽፋን ቢሰጡትም ኢህአዲግ ም ሆነ የሚቆጣጠራቸው ራድዮ እና መገናኛ ብዙሃን እስካሁን ምንም ያሉት ነገር እንደሌለ ይገልፃል።

ጉዳያችን
ታህሳስ 7/2007 ዓም (ደሴምበር 16/2014)

Friday, December 12, 2014

ኢትዮጵያን መውደድ ሕይወትን ከመስጠት ያነሰ እሳቤ እንደሌለው በተግባር ያሳዩት አንዳርጋቸው ፅጌ ዛሬ ታህሳስ 3 ከየመን ከተጠለፉ 172ኛ ቀናቸው ከ172 ቀናት በኃላስ ኢትዮጵያ የት ነች?ኢትዮጵያን መውደድ ሕይወትን  ከመስጠት ያነሰ እሳቤ እንደሌለው በተግባር ያሳዩት በዘመናችን የምንጠቅሳቸው ጀግና አንዳርጋቸው ፅጌ ዛሬ ታህሳስ 3 ከየመን ከተጠለፉ 142ኛ ቀናቸው።
ከ172 ቀናት በኃላስ ኢትዮጵያ የት ነች? በእነኝህ 172 ቀናት ውስጥ ምን ደረሰብን?

- ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እስር ቤት ገባ፣

- የዞን 9 ጦማርያን በእስር ቤት ግርፋት ተፈፀመባቸው፣

- ተማሪዎች በሙሉ ''የኢትዮጵያ ስጋት'' ተብለው በኢህአዲግ ሰነድ ላይ ሰፈሩ፣

- አሸባሪ የሚለው ቃል ''ተመንድጎ'' የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን አገልጋዮች እና ማኅበራትን ሁሉ የመፈረጃ ቃል ሆነ፣

- ከደርዘን በላይ ጋዜጠኞች ከሀገር ተሰደዱ፣ከተሰደዱት ውስጥ አንዱ ህይወቱ ኬንያ ላይ አለፈ፣

- አዲስ ጉዳይ መፅሔትን ጨምሮ ፍትህ እና ሌሎች ጋዜጦች ተዘጉ፣የቆዩ የግል ጋዜጦች ማንበብ ይሻላል ብሎ ህዝቡ የቆዩትን መግዛት ጀመረ፣

- በአዲስ አበባ ዙርያ እና አምቦ ላይ ከመሬት መቀራመት ጋር በተያያዘ በርካታ የኦሮምኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን በጥይት ተመቱ የቀሩት ለእስር ተጋዙ፣

- ኢትዮጵያዊ ትውልድ ያላት ሱዳናዊቷ ማርያም  ክርስቲያን በመሆኗ የሞት ፍርድ ሲፈረድባት መላው ዓለም ድምፁን ሲያሰማ የኢህአዲግ/ወያኔ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም ሆነ ስርዓቱ በገዛ ዜጋው ላይ የተወሰነውን ጉዳይ በዝምታ አለፈው።ማርያ ተፈታ ስትሄድ ጣልያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯን እስከ አይሮፕላን ጣብያ ድረስ ሄደው ተቀበሏት፣

- የኢትዮጵያ የከፍተኛ ተቋማት ፕሬዝዳንቶች ዋና ተግባራቸው ለኢህአዲግ መስራት እና ምርጫ እንዲመረጥ ማድረግ መሆኑ እና የምመዘኑትም ከእዚህ አንፃር ብቻ  እንደሆነ በሰነድ ተደግፎ ተነገራቸው፣

- ከ70 በላይ ኢትዮጵያውያን በቀይ ባህር ውስጥ መስጠማቸውን ዓለም በሃዘን እየተቀባበለ ዘገበው፣የአሜሪካ አምባሳደር በአዲስ አበባ የሃዘን መግለጫ ለኢትዮጵያ ላኩ፣ኢህአዲግ/ወያኔ እያጣራሁ ነው ብሎ ጉዳዩን ችላ አለው፣

- ኢትዮጵያ የብድር መጠኗ ተመነደገ ያም አልበቃ ተብሎ ኢትዮጵያን ለበለጠ ዕዳ የሚዳርግ ''ሶቨሪን ቦንድ'' ፍለጋ አውሮፓ ተዞረ፣

- ከሳውዲ ባለፈው ዓመት ተባረው የተመለሱ ወገኖቻችን እያዘኑ ተመልሰው ውደ ሳውዲ መሄዳቸውን አዲስ ጥናት አዲስ አበባ ላይ በCRDA  ተገለፀ፣

- አዲስ አበባ ላይ ግን 1 ሚልዮን የሚበልጥ ሕዝብ ውሃ እንደሌለው እራሳቸው አቶ ኃይለማርያም ለጋዜጠኞች በገለፁ በወራት ውስጥ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ተብሎ አሶሳ ላይ በ300 ሚልዮን ብር ድግስ ተበላ፣

- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዘክር (ወመዘክር) ጥንታዊ የኢትዮጵያ ታሪኮች ያሉባቸው በተለያዩ የአውሮፓ ቋንቋዎች የተፃፉ መፃህፍት፣ የነገስታት ደብዳቤዎች፣የጥናት ፅሁፎችን ቦታ ጠበበኝ ብሎ በኪሎ ሸጣቸው፣

172 ቀናት ውስጥ ኢትዮጵያ እንዲህ ከረመች።ለእዚህ ነው ኢትዮጵያን መውደድ ሕይወትን  ከመስጠት ያነሰ እሳቤ እንደሌለው በተግባር ያሳዩት በዘመናችን የምንጠቅሳቸው ጀግና አንዳርጋቸው ፅጌን የምናደንቀው።

ጉዳያችን
ታህሳስ 3/2007 ዓም (ደሴምበር 12/2014)

Thursday, December 11, 2014

ሰበር ዜና -ባለፈው ዓመት ከሳውዲ አረብያ ከተባረሩት ከአንድ መቶ ሰባ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን 50% (ከ 85ሺህ በላይ የሚሆኑት) ተመልሰው ሳውዲ አረብያ መግባታቸውን አዲስ አበባ ላይ ዛሬ በወጣ አዲስ የዳሰሳ ጥናት ተገለፀ (የጉዳያችን አጭር ጥንቅር)


ፎቶ - የሰማያዊ ፓርቲ  የጠራው በሳውዲ መንግስት በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን ግፍ በመቃወም ሰልፍ የወጡ ወጣቶች በኢህአዲግ/ወያኔ ''ፌድራል ፖሊሶች ሲደበደቡ እና ወደ እስር ሲጋዙ  

ኢትዮጵያ ውስጥ የኑሮ መክበድ፣የነፃነት ማጣት እና የስርዓቱን ማዋከብ፣እስር እና ግድያ እየሸሹ የሚሄዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከእለት ወደ እለት እየጨመረ ነው።ሰሞኑን በየመን የባህር ዳርቻ በቀይ ባሕር ውስጥ ከሰባ በላይ ኢትዮጵያውያን መስመጣቸው ይታወቃል።

ዛሬ የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማኅበር  (CRDA) በሳውዲ ተመላሾች አሁን ያሉበት ጉዳይ ላይ የሚወያይ አውደ ጥናት አዲስ አበባ ላይ የቀረበ አንድ ጥናት ባለፈው ዓመት ወደ ኢትዮጵያ ከተባረሩት ከአንድ መቶ ሰባ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን 50% (ከ 85ሺህ በላይ የሚሆኑት) ተመልሰው ሳውዲ አረብያ መግባታቸውን ይገልፃል።ቪኦኤ የአሜሪካ ራድዮ የአማርኛው አገልግሎት ዘጋቢ ከአዲስ አበባ አውደ ጥናቱን አስመልክቶ ባቀረበው ዘገባ   የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማኅበር  (CRDA) የስትራቴጂክ ቡድን መሪ እና በድርጅቱ ልዩ አማካሪ አቶ ክፍለ ማርያም ገ/ወልድን ባነጋገረበት ወቅት ''ሀቁን እንነጋገር ከተባለ ግማሾቹ ተመልሰው ሄደዋል'' ብለዋል።

በአውደ ጥናቱ ላይ የተገኙ የስደት ተመላሾች ውስጥ ለቪኦኤ ሃሳቧን የሰጠች ወጣት ''ከችግር የተነሳ ነው።እዚህ ሆኘ እራሴን ከማጠፋ ሄጄ ልሙት ከማለት ነው'' ብላለች።ለወገኖቻችን በአራቱም ማዕዘን መውጣት የሀገራችን አጠቃላይ የፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ጉዳዮች ከዋና ምክንያትነት አያመልጡም።የችግሩ ዋና መንስኤ እየተተወ ስደቱን ብቻ ብናወጋው መፍትሄ አይሆንም።

የተመላሾቹንም ሆነ የአዲሱን ትውልድ በሀገሩ ተመክቶ እና ተማምኖ እንዲኖር  አልተደረገም።ይልቁንም የኢህአዲግ አባል ካልሆነ  እና ከካድሬዎች እግር ስር ካለወደቀ መኖር አይችልም።በሥራ ዓለም ያለው ባለሙያንም ብንመለከት የነፃነት ማጣቱ እና ሃሳቡን እና ችሎታውን ለሀገሩ ማበርከት አልቻለም።መሃንዲሱ፣የህክምና ዶክተሩ እና የአይሮፕላን አብራሪው በሀገሩ ተስፋ እንዲቆርጥ ተደረገ።ሁሉ ሃገሩን ጥሎ ለመሄድ አኮበኮበ የቀረው ቆርጦ ከኢህአዴግ/ወያኔ ጋር ተጋፈጠ።ለእዚህ አብነት የሚሆኑን የሰማያዊ ፓርቲ እና የዘጠኙ አጋሮቻቸው ድርጊት ተጠቃሽ ነው።

የኢትዮጵያ ጉዳይ በእንዲህ አይነት ሁኔታ እንደሀገር የመቀጠላችን አደጋ በራሱ በግልፅ ይታያል።ጥቂቶች በሙስና እና በጎሳቸው ብቻ በሀብት ሲናጥጡ ሌላው ዜጋ ሃገሩን በረሃ ለበረሃ እየተንከራተተ ሲወጣ አይኖርም።አንድ ቀን እዝያው ሀገር ውስጥ ሁኔታዎች ከቁጥጥር ውጭ የመውጣታቸው አደጋ አይኖርም ማለት አይቻልም።የወገኖቻችን  ሀገር ጥለው የመሄድ ጉዳይ የሚያመለክተው ይህንን ነው።ቁጥር ደግሞ ከሁሉ በላይ የሀገራችንን የፖለቲካ መድረክ መቀየር እንዳለበት አመላካች ነው።''ከሰማንያ ሺህ በላይ የሚሆኑ ወደ ሀገር ቤት የተመለሱ ወገኖቻችን ተመልሰው መከራ ወደ አዩባት ሳውዲ ተመለሱ'' የሚለው ዘገባ በእራሱ መጪውን አመላካች ነው።እናት ልጇ ተመልሳ እቤት ከገባች በኃላ ተመልሳ ስትሰደድ እንዴት ታዝን? ምን ያልደረሰብን አለ? ሱዳን ባቅሟ ኢትዮጵያውያንን አባረረች ስንባል፣የመን ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መንገዶቿን ሞሉ ሲባል፣ጅቡቲ ኢትዮጵያንን ስታስር፣ እራሳችንን መጠየቅ ያሉብን ሶስት ጥያቄዎች አሉ እነሱም -
ኢትዮጵያ ክብሯ እና ማንነቷ አልተዋረደም ወይ?  
ያለውን አስከፊ ሁኔታ ለመቀየር የፖለቲካው ችግር አለመስተካከል ዋነኛው ምክንያት አይደለም ወይ? እና 
ለእዚህም ተጠያቂዎች የእያንዳንዳችን ለስርዓቱ መቀየር የአቅማችንን አለማድረግ አይደለም ወይ? የሚሉ ጥያቄዎች።
በመሆኑም ሰቆቃ ስንሰማ የምንኖርበት ዘመን እንዲቆም፣ኢትዮጵያ የጎሳ ፖለቲካ አራማጅ፣በሙስና የተነከረው እና ክብሯን እና ማንነቷን ከሚመጥናት በታች የሆነ አስተሳስብ ያለው ኢህአዲግ/ወያኔ የበለጠ ሀገራችንን መቀመቅ ሳይከት የእያንዳንዳችንን ኃላፊነት እንወጣ።በዝምታችን ኢትዮጵያን ከሚገድሉ ጋር አንተባበር።

ከእዚህ በታች ያለው ማያያዣ የጀርመን ድምፅ ራድዮ ከጥቂት ወራት በፊት ከሳውዲ የተባረሩ ወገኖቻችን ተመልሰው ወደ ሳውዲ የመመለሳቸውን ሁኔታ አስመልክቶ በድምፅ  ያቀረበው ዘገባ ነው።

http://radio-download.dw.de/Events/dwelle/dira/mp3/amh/1FC0F3BD_2_dwdownload.mp3  

ጉዳያችን 
ታህሳስ 3/2007 (ዴሴምበር 12/2014 ዓም)


Tuesday, December 9, 2014

አሳዛኙ ብሔራዊ ውርደታችን፣ኢትዮጵያ መንግስት አላት ወይ? የአሜሪካ አምባሳደር ለኢትዮጵያ መንግስት በቀይ ባህር ለሞቱት ኢትዮጵያውያን የሃዘን መግለጫ ላኩ።ኢህአዲግ/ወያኔ እስካሁን አንዳች አልተነፈሰም።Statement by Patricia Haslach, U.S. Ambassador to Ethiopia

Patricia Haslach, U.S. Ambassador to Ethiopia

በያዝነው ሳምንት መጀመርያ ላይ ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች በየመን የባህር ዳርቻ፣ በቀይ ባህር ውስጥ ከሰባ በላይ  የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መስመጣቸው መሰማቱ ይታወቃል።ጉዳዩ በሀገር ቤት እና  በመላው ዓለም በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ሃዘን አስከትሏል።

ከእዚህ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያውያንን ልብ ያደማው ጉዳይ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን ቢቢሲን ጨምሮ በርካታ የዜና አውታሮች የተቀባበሉትን ጉዳይ ላይ አንዳች የሃዘን መግለጫ አለማሰማቱ ነው።በትናንሽ አደጋ ለሞቱ ለሌላ ሀገር ዜጎች የሃዘን መግለጫ በማውጣት እና በመላክ የሚታወቀው ኢህአዲግ/ወያኔ  ለኢትዮጵያውያን ሞት አንዳች አልመተንፈሱ ሌላው የብሔራዊ ውርደታችን መገለጫ ነው።በሳውዲ ጉዳይ መንግስት እንደሌለን አውቀን ነበር።ዘንድሮም በቀይ ባህሩ አደጋ አረጋገጥን።በፌስቡክ ገፃቸው የእየእለቱን ውሎ የሚለጥፉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ሰሞኑን  ከ300 ሚልዮን ብር በላይ ወጣበት ስለተባለው በአሶሳ ስለነበረው  ብሔር ብሄርሰቦች በዓል ማውሳታቸው ስለ አደጋው ግን አንዳች አለማለታቸው እና መስርያበታቸውም ሆነ የሀገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ዝምታ ኢትዮጵያ መንግስት አላት ወይ? ብለው ብዙዎች እንዲጠይቁ ማስገደዱ አልቀረም። 

ከእዚህ በታች በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ ከሰባ በላይ ለሚሆኑት በቀይ ባህር ሕይወታቸው ላለፈው ኢትዮጵያውያን ያወጣውን የሃዘን መግለጫ ይመልከቱ እንዲህ ይነበባል- 

''ትናንት በየመን የባህር ዳርቻ ቀይ ባህር ውስጥ በሰጠመችው ጀልባ ሕይወታቸው ባለፈው ኢትዮጵያውያን የተሰማኝን ትልቅ ሃዘን ለኢትዮጵያ መንግስት እና ለሟቾች ቤተሰብ እገልፃለሁ።ልባችን ከሟቾች ቤተሰቦች እና ወዳጆች ጋር ሁሉ ነው'' በኢትዮያ የአሜሪካ አምባሳደር ወ/ሮ ፓትሪሽያ ሃስላች 

Source - US EMBASSY ADDIS ABABA

''I would like to offer my condolences to the government of Ethiopia and the families of the many victims, including Ethiopian citizens, who drowned in the tragic sinking of a boat off the coast of Yemen in the Red Sea yesterday. Our thoughts are with the families and friends of those who died.'' Patricia Haslach, U.S. Ambassador to Ethiopia

ከእዚህ በታች ያለው ቢቢሲ አደጋውን አስመልክቶ የዘገበው ነው።

Yemen migrant boat carrying Ethiopians sinks killing 70

Source -  BBC 

A boat carrying African migrants has sunk off Yemen's western coast, killing 70 people, Yemeni officials say.

The boat, carrying mostly Ethiopian migrants, sank off Yemen's al-Makha port due to strong winds and rough waves, security officials said.

Tens of thousands attempt to cross the Red Sea into Yemen every year, often in rickety, overcrowded vessels. Hundreds have died making the journey.

Yemen is viewed by many migrants as a gateway to the Middle East or Europe.

The latest sinking occurred on Saturday, with reports of the incident emerging on Sunday.

The Red Sea crossing between the Horn of Africa and Yemen is one of the world's major migration routes, BBC Arab affairs editor Alan Johnston says.

Migrants dream of finding jobs and better lives in rich places like Saudi Arabia - but they are in the hands of unscrupulous people smugglers and, too often, never reach the Yemeni shore, our correspondent adds.

In October, the UN refugee agency said that more than 200 people had died at sea in 2014 while attempting to reach Yemen.

"There have been frequent reports of mistreatment, abuse, rape and torture, and the increasingly cruel measures being adopted by smuggling rings seem to account for the increase in deaths at sea," the UN said at the time.


Saturday, December 6, 2014

አሁንስ ሰዎቹ ጫካ የነበሩም አልመስልህ አለኝ።ጫካ የነበረ እኮ ከአራዊቱም ከእፅዋቱም ሕግ ይማራልሕግ ሕግ ሕግ!!! ቅንጣት ታክል ሕግ የማያከብሩ ለማክበርም ፍላጎት የሌላቸው ሰዎች ተሰብስበው መንግስት መሆናቸው እየቆየ ይብሱን የሚያንገበግብ ጉዳይ እየሆነ ነው።የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢህአዴግ/ወያኔዎች የዛሬ 20 ዓመት አፀደቅነው ያሉትን ሕግ እየጠቀሰ ሲሞግታቸው እና ሕግ አክብሩ ሲላቸው ዓመታትን አስቆጠረ።በሕግ ስልጣን ባትይዙም በሕግ ስልጣን  ለሕዝብ አስረክቡ ቢባሉም አልሰሙም።ከሽግግሩ ጊዜ ጀምሮ ብዙዎች ብዙ ሊመክሩ ሞክረዋል። በ''ዞን 9'' ጦማርያን፣በፖለቲከኞቹ አንዱዓለም አራጌ፣በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ቀደም ብሎም በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ዳኛ ብርቱካን ደሜቅሳ እና ሌሎችም ስማቸውን ያልተጠቀሰው ሁሉ ሕግ የማክበርን 'ሀሁ' ለማስተማር ቢጥሩም ሰሚ አጡ።ሁሉም ስለ የሕግ የበላይነት ተናግረዋል፣ፅፈዋል።ሰሚ የለም።ይብሱኑ ከአመት ዓመት ትዕቢት ቤቷን እየሰራች በልቦናቸው ላይ እንደ ሸረሪት ድር እያደራች የሚናገሩት እሬት እሬት የሚል የሚሰሩት የውድቀታቸውን ጥልቀት የሚያሳይ ሆነ።

ሕግን ከመከራ  

ሰሞኑን በያዝነው በኅዳር ወር መጨረሻ ''የሕገ መንግስቱ ሰነድ የፀደቀበት'' እያሉ በሚወተውቱን ሰሞን የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 30 ''የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት'' በሚለው ርዕስ ስር ቁጥር 1 ስር ''ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሣሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ፣ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና፣ አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው'' የሚለውን መሰረት አድርገው ሃሳባቸውን በሰላማዊ መንገድ ሊገልጡ የተነሱትን የሰማያዊ ፓርቲን ጨምሮ 'የዘጠኙ ጥምረት' በመባል የሚታወቁት ዛሬ ህዳር 27/2007 ዓም ሰልፍ መውጣታቸው እና ከፍተኛ ድብደባ እና እስር እንደተፈፀመባቸው ይታወቃል።ፓርቲዎቹለሰልፉ  ያነሳሳቸው ዋናው ጉዳይ ሕግ የማያውቀውን ግን የህገ መንግስቱን  ሃያኛ  ዓመት ''ልደት'' ለማክበር ሽር ጉድ እያልኩ ነው የሚለውን ስርዓት ሕግ ለማስተማር ነበር።መማር አንድ ከማስተዋል አልያም ከመከራ ነው እና ኢህአዲግ/ወያኔ ከማስተዋል ሕግ እንደማይማር በተግባር አሳይቷል።ከመከራ ግን እንደሚማር ለማወቅ ግን ነቢይ መሆን አይጠይቅም።  


ሕግ ካላወቅህ ለምን እንደመለስከውም አትናገርም
 


ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ሐሙስ ህዳር 25/2007 ዓም ወደ አውሮፓ የነበረው ጉዞ እገዳ ምክንያት እስካሁን አልታወቀም።
ዛሬ ቅዳሜ ህዳር 27/2007 ዓም  በሸገር ''ታድያስ አዲስ'' ፕሮግራም ላይም የቴዲ ጉዞ ለምን እንደታገደ አለመታወቁን ተወስቷል።
ተመልከቱ! አንድ ኢትዮጵያዊ ያውም በሕዝብ የሚታወቅ ከያኒ አየር መንገድ ደርሶ ''ተመለስ መውጣት አትችልም'' ሲባል ለምን እንደሆነ አይነገረውም።''ለምን?'' ብሎ መጠየቅም አይችልም።ሕዝብም  አንድ ታዋቂ የኪነት ሰው ለምን ከሀገር መውጣት አትችልም እንደተባለ የማወቅ መብት የለውም።ምን ሕዝቡ ብቻ ጉዳዩ ስለ ኪነት ሰው ቢሆንም ጋዜጠኞችም ስለጉዳዩ መጠየቅ አይችሉም።ተመልከቱ! የትዕቢትን መጠን።ተመልከቱ የመጥገብን ልክ።ሌላው ቢቀር የአንድ አየር መንገድ ኢሚግሬሽን ሰራተኛ ሊሰጠው ከሚገባው አገልግሎት አንፃር ትንሹ አንድን ተገልጋይ እንደ ሰው ቆጥሮ ''እንዳትሄድ የተደረገው በእዚህ ምክንያት ነው'' ብሎ መናገር የአገልግሎት አሰጣጡ የሚጠይቀው ትንሹ የደንበኛ የማስተናገድ ክህሎት ነው።ለእዚህም ግን ትዕቢታቸው 'ስቅ ስቅ' እያለች ወጣጠረቻቸው።''ወደ ቤት ሂድ'' አሉት።ሃገሩ የግላቸው ነዋ! ሕግ አይገዛቸውም።ጥቂቶች ተጠራርተው በአንድ ወቅት ግንባራቸውን ለሞት በሰጡ ኢትዮጵያውያን አጥንት ተረማምደው ስልጣን ይዘዋላ! ማን ይናገራቸው? ሕዝብ ሕግ ምን እንደሆነ የሚያስተምርበት ቀን እሩቅ አይሆንም።


አዲስ ዘመን እና የፀጥታው መስርያ ቤት 

ሰሞኑን ''ዋዜማ'' የተሰኘው የድረ-ገፅ ራድዮ ነፍሱን ይማረውና በቅርቡ ለረጅም አመታት በስደት በኖረባት ስዊድን  ሀገር ህይወቱ ያለፈው  የታዋቂው ገጣሚ በብዕር ስሙ ገሞራው ከዛሬ 40 ዓመት በፊት በንጉሡ ዘመን ደርሶበት የነበረውን እንዲህ ይገልፀዋል።
''ገሞራው በ1966 ዓም በወቅቱ የኢትዮጵያ የፀጥታ መስርያ ቤት በመባል የሚታወቀው የደህንነት መስርያቤት በርካታ የድርሰት ፅሁፎቹ ይወሰዱበታል።ገሞራው ዝም አላለም አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ለፀጥታ መስርያ ቤቱ ፃፈ።የደብዳቤው ይዘት ፅሁፎቹ በመስርያ ቤቱ መወሰዱን እና በፍጥነት ይመለስለት ዘንድ ይጠይቃል።አዲስ ዘመን ጋዜጣ በወቅቱ የንጉሡ ተቃዋሚ እና በተማሪዎች እንቅስቃሴ ንቁ ተሳታፊ የነበረው ገሞራው የወቅቱን የደህንነት መስርያቤት ወቅሶ ለፃፈው ደብዳቤ በሚዛናዊነት አትሞ አወጣው።''

አስገራሚው የአዲስ ዘመን ጋዜጣ የአንድ ተበዳይን ደብዳቤ ማተምን  ዛሬ ቢሆን  አዲስ ዘመን ጋዜጣ  ያደርገዋል ወይ? ብለን ጠይቀን ምን ያህል ወደኃላ እንደሄድን ማሰብ ሳንጨርስ ራድዮኑ የወቅቱ የፀጥታ መስርያቤት ''ስማቸውን ገሞራው ብለው ለጠሩት ግለሰብ'' ብሎ የመስርያቤቱን ሕግ አክባሪነት፣ የተወሰዱት ፅሁፎች በመስርያ ቤቱ ውስጥ እንደሚገኙ እና እየተመረመሩ መሆናቸውን እና መስርያ ቤቱ ከሌሎች በሕግ ከተመሰረቱ መስርያ ቤቶች አለመለየቱን የሚገልፅ ሰፋ ያለ ምላሽ መፃፉን እና ፅሁፉን አሁንም አዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳተመው ያብራራል።

ይህ ከአርባ ዓመታት በፊት የነበርንበት ዛሬ የኃልዮሽ ጉዞ ስናጤን የደህንነት መስርያ ቤት ለአንድ ግለሰብ ምላሽ ሊሰጥ ቀርቶ በንቀት ዜጋውን ቁልቁል የሚያይ የማን አለብኝ ባዮች መጠራቀምያ መሆኑ ነው አሳዛኝነቱ።ሕግ ማረፍያ አጣች።ኢትዮጵያውያን ፍትህ አጡ።ለቅሶ በየቦታው ተሰማ።ጥቂቶች በሕግ ላይ የሚረማመዱ ልዩ የዜግነት መብት ያላቸው ሆኑ።ለእዚህም ነው  ሰዎቹ ጫካ የነበሩም አልመስልህ አለኝ።ጫካ የነበረ እኮ ከአራዊቱም ከእፅዋቱም ሕግ ይማራል የሚያስብለኝ።

ጉዳያችን
ህዳር 28/2007 ዓም (ደሴምበር 7/2014)

''እውነትን እስከያዝን እና በርካቶች ከእኛ ጋር እስከቆሙ ድረስ በእርግጠኝነት አድርባዩን ግንብ ደርምሰን አደባባዩ እንደርሳለን፡፡'' በጌታቸው ሺፈራው ከሰማያዊ ፓርቲ ልሳን 'ነገረ ኢትዮጵያ' ፌስ ቡክ የተገኘ

የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት ከህዳር 27/2007 ዓም ሰልፍ በፊት 

በእርግጠኝነት አደባባዩ ጋ እንደርሳለን!
በጌታቸው ሺፈራው
ትናንት ለሰላማዊ ሰልፉ ዝግጅት ሙሉ ሌሊቱን ነው ስንሰራ ያደርነው፡፡ በተለይ ጋዜጠኛ በላይ ማናዬና ሳሙኤል አበበ ሌሊቱን ሲለቀቁ ቢሮው ይበልጡን ሞቅ ደመቅ ብሎ አመሸ፡፡ ቢሮ ውስጥ የነበሩት ወጣቶች እስከ አፍንጫቸው አውተማቲክ መሳሪያ የታጠቁ የገዥው ፓርቲ ደህንነትና ፖሊሶች ቢሮውን እንደከበቡት ረስተው ስራቸው ላይ ተጠምደዋል፡፡ ደህንነት ይሁን ፖሊስ ከምንም አይቆጥሩትም፡፡ አቤል፣ ብርሃኑ፣ ወይንሸት፣ እያስፔድ፣ ምኞት፣ በላይ፣ ሜሮን፣ ኃይለማሪያም፣ ሳሙኤል፣ እየሩስ፣ ወሮታው፣ ይልቃል...... ፖሊስ፣ ደህንነት፣ መሳሪያ ቅብጥርጥስ ብሎ የማያስፈራቸው ፍጥረቶች ናቸው፡፡
በሌላ በኩል ከሰማያዊ ፅ/ቤት ውጭ ሰላማዊ ሰልፉን ለመጀመር ሌሎች ደፋር ወጣቶች ተሰማርተዋል፡፡ ቆራጡ ጌታነህ ባልቻ አንዱን ክፍን ይመራዋል፡፡ እየደወሉ አንዳንድ ነገሮችን ይጠይቁናል፡፡ እነሱም እንዲሁ በትንንሽ ሜትሮች ፖሊስና ደህንነት የሚበገርባት አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ አይመስሉም፡፡ ኢህአዴግ አፍነዋለሁ በሚለው ሰላማዊ ሰልፍ ማሰቃያው ማዕከላዊ እስር ቤት ጀርባ ሳይቀር ሌሊቱን ወረቀት እየተለጠፈ እንደሆነ ሲሰሙ የራሳቸውን ቆራጥነት ረስተው ሌሎቹን ያሞካሻሉ፡፡ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በፓልቶክና በመሳሰሉት ድጋፋቸውን ሲሰጡ ሲሰሙ ስራቸውን በደስታ ነበር የሚሰሩት፡፡ የሁሉም ትኩረት በተቻለው ሰላማዊ መንገድ ሁሉ መስቀል አደባባይ መድረስ ነው፡፡ ለዛም ጊዜው የረዘመባቸው ይመስላል፡፡ ደግሞ በበርካታ ስራዎች ተጠምደዋል፡፡
ወጣቶቹ ጠዋት ተነስተው ሌሎች አካባቢዎች የሚገኙት ጓዶቻቸው ምን ደረጃ ላይ እንደደረሱ፣ መቼ እንደሚጀመር ለማወቅ ቋምጠዋል፡፡ እስከዛው ደግሞ ፌደራልና ደህንነቶች የቆሙበት ድረስ እየሄዱ ፎቶ ግራፍ እያነሱ ያመጣሉ፡፡ የደህንነቶችን ስራ በማህበራዊ ሚዲያዎቸ ያጋልጣሉ፡፡ ብዙዎቹ ምግብ አልቀመሱም፡፡ የእነሱ ትኩረት ወደ መስቀል አደባባይ ማቅናት፣ ከዛም ለኢትዮጵያውያን መብት መጮህ ነው!
እናም ያ ጊዜ ደረሰ፡፡ የተወሰኑ ሰዎች ቢሮ መቅረት ነበረባቸው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞም አብዮት አደባባይ ላይ ሰልፍ ለመውጣት (ያውም የአዳር ሰልፍ) ሲሞከር ከስርዓቱ የሚመጣው ምላሽ ምን ሊሆን እንደሚችል ለወጣቶቹ ግልጽ ነው፡፡ ስርዓቱ ሊደባደብ፣ ሊያስር፣ ከዚህም ሲያልፍ ሊገድል እንደሚችል ያውቃሉ፡፡ ግን ፍርሃትን አላሰቡትም፡፡ እንዲያውም ‹‹ኑ ራሳችን ነጻ በማውጣት አገራችን ነጻ እናውጣ›› የሚሉት ወጣቶቹ ራሳቸውን ከፍርሃት ነጻ አውጥተዋል፡፡ እነሱ የሚታገሉት ሌሎች ከፍርሃታቸው ነጻ ይወጡ ዘንድ ነው፡፡ እናም ፍርሃትን አላሰቡትም፡፡ እነሱ ያሰቡት መስቀል አደባባይ ስለመድረስ ብቻ ነው፡፡ ከዛ ውጭ ያለው መስዋዕትነት የትግሉ አካል ነው፡፡ ስለሆነም ‹‹እኔ ብሄድ ይሻላል፡፡ እንትና ይቀር›› የሚሉት በዙ፡፡ ቢሮ መቅረትን የሚፈልግ ሰው የለም፡፡
እናም ያ ጊዜ ደረሰ፡፡ አመራሮቹ ደግሞ የሚቀያየሩትን ነገሮች ጋር አብረው ለመሄድ በተደጋጋሚ ‹‹ኦረንቴሽን›› ይሰጣሉ፡፡ በተለይ በተለያዩ የአብዮት አደባባይ አካባቢ የነበሩት የሰልፉ አስተባባሪዎች መንቀሳቀስ ሲጀምሩ ሰማያዊ ጽ/ቤት የነበሩት ወጣቶች ይበልጡን ተቁነጠነጡ፡፡ ምክንያቱም የሚያስመልሱት መብትን ነው፡፡ የሚያስመልሱት ታሪካዊ አደባባይንም ነው፡፡ ደግሞም ሌላ ቦታ ሰልፉን የጀመሩት ጓደኞቻቸው ከፖሊስና ደህንነት ጋር እየተጋፈጡ ነው፡፡ ቆይቶ ግን የእነሱም የተጋድሎ ተራ ደረሰ፡፡
ከአቧሬ በኩል መንገድ ተዘግቶ በርካታ ፖሊሶች ተደርድረዋል፡፡ በካሳንችስ በኩልም እንዲሁ፡፡ ደህንነቶች (ጆሮ ጠቢዎች) ቢሮው በር ድረስ ተኮልኩለዋል፡፡ እንግዲህ እነዚህ ወጣቶች አብዮት አደባባይ ለመድረስ ይህን ሁሉ አጥር ጥሰው ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡ እነ ብርሃኑ፣ እያስፔድ፣ አቤል፣ ወይኒ፣ እየሩስ፣.......በግንባር ቀደምነት ድምጻቸውን እያሰሙ የፌደራል ፖሊስና ደህንነቶችን ለመጣስ በሚያስችል ፍጥነት ስለ ነጻነት እየጮኹ ወደ አደባባዩ ከነፉ፡፡ ግን እውነትን ስለያዙ እንጅ የእነሱ ቁጥር በየ ቦታው ከተኮለኮለው ደህንነትና መንገድ ዳር ከተዘረገፈው ፌደራል በእጅጉ የሚያንስ ነበር፡፡ እናም እንደራሴ ላይ ስርዓቱን ለመከላከል ቆርጦ ከተነሳ ፀረ ዴሞክራሲያዊ ግንብ ጋር መላተም ነበረባቸው፡፡ ከእውቀት ይልቅ በጥላቻ የተገነባ ግንብ፡፡ ለለውጥ የቆረጡ እንጅ አድርባይነት የማይታይባቸው ወጣቶች በደቂቃዎች በምክንያት አሳምነው የማያልፉት በጥላቻ የጠጠረ አድር ባይ ግንብ፡፡
ስርዓቱ ግንብ ለሰላማዊ ታጋዮች፣ ለህዝብ ጥቅም የቆሙት ላይ ጥላቻ ያለው እንደሆነ ሁሉ አቤል፣ ወሮታው፣ ይልቃል፣ በላይ፣ ጣይቱዎቹ...ለአድርባይነት፣ ለኢ -ዴሞክራሲያዊነት የጠለቀ ጥላቻ ይዘዋል፡፡ ፖሊስና ደህንነት ከስርዓቱ እንደወገነ ሁሉ እነሱ ስለ እውነት ከኢትዮጵያውያን ጋር ወግነዋል፡፡ እናም ሁለት የተለያዩ (ተቃራኒ) ግንቦች ፊት ለፊት ተፋጠጡ፡፡ ስለ እውነት፣ ህግን መሰረት አድርገው መብት የሚጠይቁት ወጣቶች ስርዓቱን የከለለው ግንብ አልፈው መንጎድን መርጠዋል፡፡ ስርዓቱን ለመመከት የተበገረው ግንብ ደግሞ ከእውነት ይልቅ መሳሪያና ቆመጥ ይዟል፡፡ በተለያዩ ቋንቋዎች ተነጋገሩ፡፡ ወጣቶቹ በሰላማዊ መንገድና በህግ ፖሊስና ደህንነት በኃይል!
በአድርባይነት የቆመው ፖሊስና መከላከያ እስከ አፍንጫው የታጠቀውን ስርዓት በባዶ እጃቸው ነጻነታቸውን እንዲያከብር የሚጠይቁትን ወጣቶች ደበደበ፡፡ አቤል ኤፍሬም፣ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት፣ ንግስት ወንዲፍራው፣ ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ በላይ ማናዬ፣ ኃይለማሪያም.....ሁሉም በጭካኔ ተደበደቡ፡፡ ድምጽ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን መብታቸው እንዲከበር እጁን ብቻ ወደላይ አንስቶ ‹‹ነጻነት!›› ያለው አቤል በቅልብ ፌደራሎች ተቀጥቅጦ ራሱን ስቶ ወደቀ፣ ንግስት ወንዲፍራውና ሌሎችም በተመሳሳይ፡፡ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት በጭካኔ ተደበደበ፣ ሌሎቹም እንደዚሁ፡፡
ግን ሁለቱም የሚገባቸውን አድርገዋል፡፡ ፌደራል ፖሊስና ደህንነት ስልጣናቸውን እንጅ ምክንያት፣ ህግ ተብሎ በማይገባቸው ባለስልጣናት ‹‹ደብድብ!›› ተብሎ የተሰጠውን ‹‹ስራ አከናወነ››፡፡ ህገ ወጥ አቅሙን በህጋዊያን ላይ ተጠቀመ፡፡ ለፖሊስና ደህንነት ይህ አድርባይነት ማደሪያው ነው፡፡ ስለ ነጻነት የቆሙት ደግሞ መጀመሪየም ስርዓቱ እንደሚያስደበድብ ያውቁታል፡፡ እናም ስለእውነት ሲሉ ያለ መሳሪያ መሳሪያ ያነገበው ጋር ተፋጠው ተደበደቡ፡፡ ይህም ለነገው ትግላቸው እርሾ እንደሆነ ያውቁታል፡፡ ፌደራል ፖሊስ ወጣቶቹን ሲደበድብ ራሱን ይደበድባል፡፡ ቢያንስ ይህ ቁስል ዛሬ ባይሰማው ነገ ይጠዘጥዘዋል፡፡ ያመረቅዛልም፡፡ በተለያዩ ጊዜያት እንዳየሁት የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች ስለ መብታቸውን ሊያስከብሩ ሰልፍ ወጥተው ሲደበደቡ ይዘምራሉ፡፡ የዛሬው ዱላ በእጅጉ በርትቶባቸው ራሳቸውን ቢስቱም ቁስሉ ግን ሊሰማቸው አይችልም፡፡ እያንዳንዷ ቁስል፣ ስቃይ፣ መስዋዕትነት ለነጻነት ትግሉ ስንቅ ነች፡፡ እናም የአድር ባዩ ፖሊስና ደህንነት ቆመጥ ለጊዜው እንጅ እንደማይሰማቸው እርግጠኛ ነኝ፡፡
ዛሬ እነዚህ ቆራጥ ወጣቶች ከጎኔ የሉም፡፡ ለዘገባ እንደምወጣ ስነግረው ‹‹አይሆንም እኔ ነኝ የምወጣው!›› ብሎኝ ምንችክ ያለው በላይ ማናዬን አውቀዋለሁ፡፡ ፖሊስ ከሚያሳርፍበት አጥንት የሚሰብር በትር ይልቅ ቅንጣት እውነት ስትዛባ ያመዋል፡፡ አቤል፣ ብርሃኑ፣ ይልቃል፣ ወሮታው፣ ሳሙኤል... ጣይቱዎቹን አውቃቸዋለሁ፡፡ እውነት ስትዛባ ያንገበግባቸዋል፡፡
ጓደኞቼ ወደ አደባባዩ ሲያቀኑ እንደሚደበደቡ አውቃለሁ፡፡ ከእነሱ ጋር አንድ አይነት ጥያቄ አንግቦ መደብደብ ለጊዜው ካልሆነ በስተቀር አያምምና እኔም ለመሄድ ቋምጬ ነበር፡፡ ግን ቢሮ ሰው መቅረት ነበረበትና ቀርቻለሁ፡፡ ግን ደግሞ ቢሮ ሆኖ እንደቆሰሉ መስማት እንዴት ያማል? ስለ እውነት ጠይቆ መስዋዕትነት መክፈል እንዴት ክብር ነው? ወጣቶቹ እንደትናንትው አብረውኝ ቢሮ ውስጥ ባያድሩም እምነታቸው ግን አብሮኝ ነው፡፡ ከእምነት ወዲያ ምን አለ?
ጓደኞቹ አብዮት አደባባይ (መስቀል አደባባይ) ለመድረስ አማትረው ለጊዜው ጉዟቸው መንገድ ላይ ተገትቷል፡፡ በጭካኔ ተደብድበዋል፣ ቆስለዋል፡፡ ይህ ስለሆነ ግን አሁንም ወደ አደባባዩ ከማማተር አይቆጠቡም፡፡ ራሳቸውን ነጻ ቢያወጡም ሌሎች ነጻ እንዲወጡ ከተለሙት አላማቸው የሚያቆማቸው የለም፡፡ ዛሬ እንደራሴ ላይ ቢቆሙ፣ ነገ ካሳንቺስ ድረስ እንደርሳለን፡፡ አካላዊ ቁስሉ ሳይበግረን ከነገ ወዲያ....እንዲያ እያልን ደግሞ ወደታለመው አደባባይ እናቀናለን፡፡ በእርግጠኝነት የአድርባዩ ጎራ እየሳሳ፣ ስለ እውነት የቆሙት የሚጠነክሩበት ጊዜ ሩቅ አይደለም፡፡ እውነትን እስከያዝን እና በርካቶች ከእኛ ጋር እስከቆሙ ድረስ በእርግጠኝነት አድርባዩን ግንብ ደርምሰን አደባባዩ እንደርሳለን፡፡Wednesday, December 3, 2014

''ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች!'' ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት (የጉዳያችን ማስታወሻ)


እናት አርበኞች 

''ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች'' ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ሰሞኑን ፓርቲው እና ዘጠኙ አጋር ፓርቲዎች በጋራ በጠሩት በመጪው ቅዳሜ እና ዕሁድ (ህዳር 26 እና 27/2007 ዓም) በአዲስ አበባ የተጠራውን የ 24 ሰዓት የተቃውሞ ሰልፍ አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተናገሩት ንግግር ነው። 

ይህ ንግግር አሁን ላለው ትውልድም ሆነ በኢትዮጵያዊነቱ ለሚያምነው ሁሉ ከሰማይ የገዘፈ፣ ሲያስቡት በትንሿ አእምሯችን ልንሸከመው የሚከብድ ግን ከእውነትም በላይ የሆነ እውነት ነው።

ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ካቆሟት ነገሮች ውስጥ አንዱ ለዘመናት የኖረው ሕግ ነው።ዓለም እንደ ዛሬው ስለ ሕግ ብዙ ሳይናገር በቤተ መንግስቱ እና በሕዝቡ መካከል የሚያገናኙ ሕጎች ነበሩ።የተበደለ ፍትህ የሚያገኝበት፣አቤት የሚልበት ቦታ ነበረው።በዳኝነት የተቀመጠውም ህሊናውን እና አምላኩን የሚፈራበት መመዘኛ ነበረው።ፍፁምነት በእራሱ ከሰው ልጅ ባይጠበቅም እንደ ማህበረሰብ፣እንደ ሕዝብ እና እንደ መንግስት ኢትዮጵያ እና ህዝቧ ለሺህ ዓመታት ሲዳኝ የኖረው ከፈረንሳይ ሀገር በመጣ ወይንም ከእንግሊዝ በመጣ ሕግ አይደለም። ሃይማኖታዊ መሰረቱን በያዘ፣ህሊናን እና ህዝብን ታሳቢ ያደረገ ሕግ እና ፍርድ ለዘመናት አኑረውናል።

ይህንን ሕግ እና በነፃነት የመኖር ፀጋን አባቶቻችን በነፃ አላገኙትም።ወጥተው እና ወርደው ደምተው እና ቆስለው ያቆዩት እኛነታችን ነው።ለእዚህ ነው ዛሬ ላይ ሆነን ለነገ ለማስተካከልም ሆነ የምናወራው ስለ ምን ዓይነቷ ኢትዮጵያ እንደሆነ ለማስታወስ ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት ሀገር መሆኗን ለአፍታም አለመርሳቱ ተገቢ የሚያደርገው።ብዙ የተደከመባት ብቻ አይደለም ብዙ ታላልቅ ሰዎች የተሰዉላት ሀገር ነች።ኢንጅነር ይልቃል ያስታወሱን እኔም በአምሮዬ ሲመላለስ የከረመው አረፍተነገር ይህ ነው።

ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች


ኢትዮጵያ ንግስት ሳባ በሴት አቅሟ በረሃ ለበረሃ ተንከራታ ኢየሩሳሌም ድረስ ሄዳ  ታቦተ ፅዮንን ያመጣችላት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።

ኢትዮጵያ ንጉስ ካሌብ እስከ የመን የሀገሩን ስም ይዞ ሄዶ በባርነት የተያዙትን ናግራውያንን ነፃ ያወጣባት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።

ኢትዮጵያ የመሐመድ ቤተሰቦች ተሰደው በክብር ተቀብላ መጠለያ ሰጥታ እስልምና ሃይማኖትን ለዛሬ አማኝ የሰው ልጆች በሙሉ ከመጥፋቱ በፊት የታደገች ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።

ኢትዮጵያ በዘመነ ዮዲት (ጉዲት) ለአርባ ዓመት የመከራ ዶፍ ሲወርድባት ከመከራው ጋር የነደዱ፣በእሳት የተቃጠሉ፣በጦር የተወጉ ለሀገራቸው እና ለህዝባቸው ክብር በሰይፍ የተቀሉ ጀግኖች የሞቱባት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።

ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያ ክብር ፣ለሌሎች ነፃነት እና ለእምነታቸው ፅናት የተጉ  እነ አፄ ዳዊት፣ነገስታቷ ግብፅ ያሉ ህዝቦች ተጨቆኑ ብለው በሱዳን በረሃ ተንከራተው የግብፅን ሕዝብ ከመከራ የታደጉ ሲመለሱም  የክርስቶስን መስቀል ይዘው የተመለሱ በመንገዳቸው መከራ ህመምን ታቅፈው ሀገራቸው ድንበር ላይ የሞቱባት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።

ኢትዮጵያ ባዕዳን እንግሊዞች ሀገራችውን እና ወገናቸውን በከዱ ባንዳዎች እየተመሩ ሲመጡ እጅ አልሰጥም፣ኢትዮጵያን መሳቅያ አላደርግም ብለው የገዛ ሽጉጣቸውን ጠጥተው የሞቱባት አፄ ቴዎድሮስ የተሰዉላት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።

ኢትዮጵያ ራስ አሉላ ''ፈረሴ የቀይ ባህርን ውሃ ሳይጠጣ አይመለስም'' ብለው በባህረ ነጋሽ በረሃዎች ተንከራተው የሀገራቸውን ክብር ያስጠበቁ የተሰዉላት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።
ኢትዮጵያ አፍሪካን  በጠረንጴዛ ዙርያ ተሰብስበው ለመቀራመት ከተስማሙ በኃላ ሊወራት የመጣውን ጣልያንን ለመዋጋት ለወራት በእግራቸው እስከ አድዋ ድረስ ተጉዘው መስዋዕት የተቀበሉባት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።

ኢትዮጵያ ኢጣልያ ዳግም በ1928 ዓም ሲወራት ከሊቅ እስከ ደቂቅ በረሃ ለበርሃ ተንከራተው ከውስጥ አርበኛ እስከ ዓለም አቀፍ ሙግት ገብተው፣ከጳጳሳቷ እስከ ሕፃን ሰማዕት የሆኑባት፣በአዲስ አበባ በየካቲት 12 ቀን ብቻ ከአስር ሺህ በላይ የንፁሃን ደም በአካፋ እና በዶማ ጭምር የፈሰሰባት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።

ኢትዮጵያ እነ ሞገስ አስገዶም እና አብርሃም ደቦጭ በአርበኝነታቸው ተይዘው ጥፍራቸው እየተነቀለ ተሰቃይተው የሞቱላት ሀገር ነች ኢትዮጵያ።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች። 

ኢትዮጵያ በሮም ጣልያን አደባባይ ጎራዴ መዘው የጣልያንን ፋሽትትን የቀሉ በመጨረሻም ለሞት ሰማዕት የሆነላት ዘርአይ ድረስን ያበቀለች ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።

ኢትዮጵያ ከጣልያን እስር ቤት አምልጦ በገዛ የጣልያን በረሃ ሸፍቶ ፋሽትን ያርበደበደ በመጨረሻም በድል የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ እያውለበለበ ሮም የገባ እና ከአዲሱ የጣልያን ፕሬዝዳንት የገዛ የእጅ ሰዓታቸውን አውልቀው የሸለሙት ጀግና አብዲሳ አጋን ያፈራች ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።
  
ኢትዮጵያ የተሻለ አስተዳደር ያስፈልጋታል።ብለው እራሳቸውን የሰጡ ጀግና የጦር ኃይል አባላት እነ ጀኔራል መንግስቱ ንዋይ እና ገርማሜ ንዋይ በስቅላት አንገታቸውን ለገመድ የሰጡላት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።

ኢትዮጵያ አሁንም የተሻለ አስተዳደር ያስፈልጋታል፣''ሕዝባዊ መንግስት አሁኑኑ!'' ያሉ በሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶች ለሞት እራሳቸውን የሰጡባት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።

ኢትዮጵያ የዚያድባሬ ሱማልያ ''ቁርስ ድሬዳዋ፣ምሳ አዲስ አበባ'' ብላ በምትፎክርበት ወቅት ከሶስት መቶ ሺህ በላይ ወዶ ዘማች ባጭር ጊዜ ለኢትዮጵያ እሞትላታለሁ ብለው የተሰለፉላት እና ሺዎች በፈንጅ ላይ እየተራመዱ ሞተው ሀገራቸውን ለክብር ያበቁ ዜጎች የወለደች ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።

ኢትዮጵያ አንድነቷ አይናጋም፣አትቆራረስም፣በጎሳ እና በዘር አትከፋፈልም ብለው ሰማዕት የሆኑላት እንደ ምፅዋ በነበረው የእርስ በርስ ውግያ ሳንጃ በሳንጃ እየተሞሻለቁ ከአፈር የተደባለቁላት ሀገር ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።

ኢትዮጵያ አሁንም ከአምባገነናዊ አገዛዝ ትላቀቅ ብለው ተነስተው በመጨረሻ ሰንደቅ አላማዋን ተጠቅልለው በመከላከያ ሚኒስትር ቢሮ ውስጥ የተሰዉላት እነ ጀነራል መርድን፣በሰሜን እኔ ብ/ጄነራል ደምሴ ቡልቱን፣ኮለኔል ታሪኩን ያፈራች መሬት ነች።ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች።

አዎን ! ዛሬ በጎሳ እና በከፋፋይ አገዛዝ እጅ ወድቃ ብትቆስልም ኢትዮጵያ ብዙ ደም የፈሰሰላት፣ብዙዎች የደከሙላት ወደፊትም የሚደክሙላት ሀገር ነች።ዛሬ ኢትዮጵያን ስናስብ ይህንን ሁሉ ድካም እና እንደጎርፍ የፈሰሰው ደም ሊታወሰን ይገባል።

ይህንን ሁሉ ነው የኢንጅነር ይልቃል ንግግር ያስታወሰኝ።ይህንን ስናስብ ነው በሀገራችን ምን ያህል እንደቀለድን ሀገራችንን ለአልባሌ እዚህ ግባ ለማይባል ዘረኛ ቡድን ሰጥተን ግማሾቻችን ለስደት የቀረነው ለህሊና እስረኝነት መዳረጋችን የሚያንገበግበው።

አዎ እያወራን ያለነው ስለ ኢትዮጵያ ብዙ ስለተደከመላት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች ስለተሰዉላት ሀገር ነው።አዎን!! ኢትዮጵያ ብዙ የተደከመባት እና ብዙ ትላልቅ ሰዎች የተሰዉባት ሀገር ነች! ይህ ትውልድ የሀገሩን ክብር ማስመለስ ያለበት ወሳኝ ጊዜ ላይ ነው።ሁሉ እንጀራ ጋጋሪ አይሆንም።ሁሉም ወጥ አይሰራም።ባለን በችሎታችን ለሀገራችን ካልሰራን ከሞቱት አንሰናል።ብዙዎች የደከሙላት እና የሞቱላት ሀገር ላይ ቸል የማለት መብት የለንም።

ጉዳያችን 
ህዳር 24/2007 ዓም (ደሴምበር 3/2014) 

Wednesday, November 26, 2014

የግሪክን ብሔራዊ ህልውና የተፈታተነ ''ሶቨሪን ቦንድ'' ለኢትዮጵያ እንዴት ይሰራል?ኢትዮጵያ ከእዚህ በፊት ከመንግሥታት፣አህጉራዊ ወይም ዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ተቋማት ብድር ወስዳለች።አሁን ያለባት የብድር መጠን ከ20 ቢልዮን ዶላር ወይንም ከ400 ቢልዮን ብር በላይ መሆኑ ይታወቃል።ወደ ''ሶቨሪን ቦንድ'' እንድትገባ በዝግ ምክርቤት ወሰነ የተባለው የብድር አይነት ግን ኢትዮጵያ ከግል አበዳሪዎች ሁሉ በደላሎች ብድር እየፈለገች እንድትበደር የሚያደርግ፣በሙስና ለተሰነገ ሀገር ፈፅሞ የማይመከር ነው።ለመሆኑ የሶቨርን ቦንድ ምን ማለት ነው? ''ኢንቨስቶፕድያ እንዲህ ይገልፀዋል።

''ሶቨሪን ቦንድ'' ማለት በመንግሥታት  በውጭ ምንዛሪ የሚቀርብ የብድር ዋስትና ሲሆን የውጭ ምንዛሪው በጠንካራ አለም አቀፍ ገንዘብ (ሃርድ ከረንሲ) የተደገፈ ነገር ግን ለቦንድ ያዥው የበለጠ አደጋ ያለው '' ይላል 

''DEFINITION OF 'SOVEREIGN BOND'
A debt security issued by a national government within a given country and denominated in a foreign currency. The foreign currency used will most likely be a hard currency, and may represent significantly more risk to the bondholder.'' www.Investopedia.com

ምዕራባውያን እና ሶቨርን ቦንድ 

ብድሩን የምዕራብ ሃገራት ፍላጎት የታዳጊ ሀገሮች ወደገበያው መግባት ነው። ምክንያቱም አበዳሪ ሁል ጊዜ ተበዳሪ  ማግኘት ስራው ነው።ይህ ማለት ተበዳሪ በአዋጭም ይሁን በማያዋጣ መንገድ ላይ ቢሆን ለአበዳሪ ጉዳዩ አይደለም። አበዳሪ ገንዘቤ ባይመለስ በምን ሌላ አስገዳጅ ነገር ውስጥ አስገብቼ ያልታሰበ ሲሳይ ይገኛል? ነው ጥያቄው።ለእዚህ ነው የ''ፋይናንሻል ታይምስ'' ጨምሮ የኢትዮጵያን ወደ እዚህ ብድር መምጣት አሰማምሮ የፃፈው።ኢትዮጵያ ወደ ቻይና ተጠጋች የሚለውን ስጋት ለማራቅ ''በሶቨሪን ቦንድ'' መያዙ ለወደፊት 'ስልታዊ ጥቅም' አለውና።በሌላ በኩል ይህ ብድር የሉላዊነት (ግሎባላይዜሽን) ማስፈፀምያ አንዱ ስልት ነው።

ግሪክን ያየህ ተቀጣ

 ግሪክ ባለፉት ሁለት ዓመታት የምጣኔ ሃብቷ ያን ያህል ያሽቆለቆለው ብቻ ሳይሆን የአውሮፓ ሃገራት ስር በተለይ ጀርመን ስር እንድትንበረከክ የተደረገው በእዚሁ ''ሶቨርን ቦንድ'' አማካይነት ነው።የሀገሪቱ ህዝብም አደባባይ ወጥቶ የገዛ መንግስቱን የተቃወመው በእናንተ ሙስና ምክንያት ሀገሪቱ ከማትችለው ብድር ውስጥ አስገባችሁ በሚል ነበር።ይህንን ለመረዳት ''የሶቨሪን ብድር ቀውስ የዘመናዊዋ ግሪክ አሳዛኝ ሁኔታ''  ''The Sovereign Debt Crisis: A Modern Greek Tragedy'' በሚል ርዕስ የወጣውን ''የሴንት ሉዊስ ባንክ'' ፅሁፍ ያንብቡት።


ሉዓላዊነታችን አደጋ ላይ የመውደቅ እድል አለው 

በኢትዮጵያ ላይ የረጅም ጊዜ ስልታዊ ፍላጎት ያላቸው ሀገሮች በግለሰብ ወይንም በኩባንያ ስም ከአውሮፓ ወይንም ከአሜሪካ ብቅ ቢሉስ? ለምሣሌ የገንዘብ ችግር የሌለባቸው እንደ ሳውዲ አረብያ ያሉ ሀገሮች ገንዘባቸውን በባንክ ከማስቀመጥ በእደዚህ አይነት ብድር ለድሃ ሃገራት  ቢሰጡ ያተርፋሉ።ኢትዮጵያ ላይ በብዛት ብድር ሰጥተው መልሰው የነገር መቆስቆሻ ሊያደርጉት እና እስከ ጦርነት የሚያደርስ ብሎም በሉዓላዊነታችን  ላይ የሚጋረጥ አደጋ ሊያጋጥም ይችላል።በእንደዚህ አይነት መንገድ የሚነሱ ግጭቶች ደግሞ ወደ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሲደርስ ምንም አይነት የዲፕሎማሲ ድጋፍ የማያስገኝ ስለሆነ አበዳሪዎች በዓለም መድረክ የመሰማት እድላቸው ከፍተኛ ነው። ለእዚሁም ምክንያቱ ኩባንያዎቹ በተለያየ ጥቅም ከብዙ ሃገራት ጋር የጀርባ ንግግር ስላላቸው እና ዓለም አቀፍ ማህበረሰብም ብድሩን መክፈል አለባት የሚሉ ቃላትን እንጂ ሌሎች ሁኔታዎችን የምያገናዝብበት ዕድል ፈፅሞ አይፈጥርለትም።በመሆኑም ሕጋዊ በሚመስል መንገድ ሀገር ለአደጋ ያጋልጣል ማለት ነው።

ባጭሩ የሶቨሪን ብድር በአለማችን የገንዘብ ስርዓት ውስጥ ያለ ቢሆንም እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሃገራት ግን የሚገቡበት አግባብ የራሱ የተገደበ መስመር መያዝ ይገባው ነበር። ይህ የተገደበ መስመር ማለት-

 1/ ስለ ብድሩ ምንነት፣አስፈላጊነት እና የመክፈል አቅም በዝርዝር በስሙ ለሚበደሩት የኢትዮጵያ ሕዝብ በግልፅ መነገር ነበረበት፣
2/ ህዝቡ በጉዳዩ ላይ መወያየት ነበረበት፣
3/ ሙስናው ቅጥ ባጣበት ሀገር እዴት ሊሰራ እንደሚችል መጤን ነበረበት፣
4/ብድሩ ለየትኛው ፕሮጀክት እና  ምን ያህል እንደሚወሰድ ለሕዝብ መታወቅ ነበረበት፣
5/ መንግስት የሚበደረውን የገንዘብ መጠን በሕግ ገድቦ ማስቀመጥ ነበረበት። ለምሳሌ ገንዘብ ባነሰው ቁጥር በደላላ አበዳሪ እየፈለገ የሚበደር ከሆነ መጨረሻው የት ሊሆን ነው?
6/ ኢትዮጵያ ብድሩን ተበድራ ለመክፈል የምታስበው ከየት እና ምንን ታሳቢ አድርጎ ነው? የሚለው  በግልፅ ለሕዝቡ መቅረብ ነበረበት።

እነኝህ ሁሉ ባልተደረጉበት ሁኔታ ኢትዮጵያን አፏን ለጉመው፣የመገናኛ ብዙሃንን ዘግተው፣የግል ጋዜጦችን አሽገው፣ፓርላማውን በዝግ ስብሰባ አስፈራርተው በእኛ እና በልጆቻችን ስም የመበደር መብት እንዴት ያለ ሕዝብን የመናቅ ደረጃ ነው? በትክክል ከላይ ከተባለው አንፃር ስንመለክተው አደጋ ላይ ነን።ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ በተድበሰበሰ መንገድ የሚሰራው ሥራ ''ምን ያህል ኢትዮጵያዊ አስተሳሰብ የያዙ ሰዎች አመራር ላይ አሉ?'' ብሎ የመጠየቂያው ጊዜ ነው።

በመጨረሻም ኢትዮጵያ ከእራሷ ሀብት አፍርታ፣ወደውጭ የሚላክ ምርት ጨምራ የውጭ ምንዛሪ አግኝታ የመኖር አቅሟን ላለፉት 23 ዓመታትም መፍጠር አለመቻሏ አመላካች አንዱ መንገድ ይህ አሁን በቅርብ ቀናት ውስጥ አውሮፓ ላይ  ''ልንበደር ነው አድገናል'' የሚለው መግለጫ በኢህአዲግ/ወያኔ ባለስልጣናት ሊሰጥ መሆኑ ነው።የእድገታችን መገለጫ መበደር እንዴት ሊሆን ይችላል? ፖለቲካዊ ዝናን ለማግኘት የተገቡባቸው ትልልቅ ፕሮጀክቶች ወሳኝ ግን ጠቃሚ የነበሩትን እንደ በምግብ እራስን መቻል፣ወዘተ ፕሮጀክቶች ችላ እንዲባሉ አላደረገም ወይ? ይህ የተሳሳተ የፖሊሲ ውሳኔ ዛሬ ዋጋ እያስከፈለን አይደለም ወይ?  ነገሩን በአንክሮ ለተከታተለው ሰው አሳዛኝ ነው።ጥያቄው ግን አይቆምም የግሪክን ብሔራዊ ህልውና የተፈታተነ ''ሶቨሪን ቦንድ'' ለኢትዮጵያ እንዴት ይሰራል?

ጉዳያችን
ህዳር 18/2007 ዓም (ኖቬምበር 27/2014)

ቅኝ ግዛት እና ሕዝቡን ቢራ እንዲጠጣ ማበረታታ ምን እና ምን ነበሩ? ዳቦ ሳንጠግብ እና የምናነበውን ጋዜጣ ሁሉ ዘግተው አዕምሯችንን እያደነዘዙ የቢራ ፋብሪካ መደርደር ምን ይባላል?
በባዕዳን በቅኝ ግዛት ተይዘው የነበሩ ሀገሮች ሁለት ዋና ዋና ሀብታቸውን አጥተዋል።( በነገራችን ላይ በባዕዳን ቅኝ ግዛት የተያዙቱኑ ነው ያልኩት እንጂ ፕሬዝዳንት መሆን ያማረው ሁሉ ቅኝ ግዛት ነበርኩ እያለ የእራሱን እና የህዝቡን ክብር ገደል የሚጨምረውን አይመለከትም።)
እነኝ በቅኝ ግዛት የተያዙ ሃገራት ካጡት ሀብት መካከል የመጀምርያው ምጣኔ ሀብታቸው የባዕዳን ገዢዎቻቸውን ምጣኔ ሀብት እንዲያገለግል ተደርጎ መዋቀሩ  ሲሆን ሌላው የነበራቸውን ከቀደሙት የወረሱት ባህል እና የአኗኗር ዘይቤ ነው።ሃገራቱ እንዲያመርቱ የተደረጉትም ሆነ ወደውጭ የሚልኩት ምርት የገዢዎቻቸውን የጥሬ ዕቃ ፍላጎት ብቻ ላይ እንዲያተኩር ተደረገ።ዛሬ እነ ኬንያ፣ታንዛንያ እና ዑጋንዳን ብንመለከት ሃገራቱ ለንግድ የሚሆኑ የእርሻ ምርታቸው በወቅቱ እንግሊዝ ትፈልገው ከነበረው ምርት ጋር ብቻ እንዲቆራኝ የተደረገ ነው።

በአንፃሩ ደግሞ አውሮፓውያን በእነርሱ ክህሎት ብቻ የሚሰራውን ምርት ቅኝ ተገዢዎች እንዲቀበሉት አደረጉ።አፍሪካውያን ቡና ከመጠጣት ቢራ እንዲጠጡ እና እንዲለማመዱ ተደረጉ።እንድያውም አንዳንድ ቦታ ቢራ ለመጠጣት ያልደረሱ ታዳጊዎች ሁሉ በሰሩት ሥራ ልክ የሚከፈላቸው ቢራ የነበረበት ወቅት ነበር።የቢራ መጠጥ ከቅኝ ግዛት በኃላም በሰፊው ተለመደ።ብርጭቆ ተጋጨ።በዓል የሚከበረው በቢራ እና በቢራ ብቻ ሆነ። ዛሬ በዑጋንዳ እና በታንዛንያ ቢራ የሚጠጣውን ያክል ቡና አይጠጣም።በአውሮፓ ደግሞ ቡና የሚጠጣውን ያክል ቢራ አይጠጣም።አፍሪካውያን የሚጠጡበት ቢራ በትንሹ ግማሽ ሊትር የሚይዝ ነው።አውሮፓውያን ቡና የሚጠጡበት ስኒ የሻይ ብርጭቆ ያክላል።ቡናው ለንቃት ወደ አውሮፓ ይላካል።

የመንገድ እና ሌሎች የመሰረተ ልማት አውታሮች ዝርጋታ የቅኝ ገዢዎች የሰሩት አሁንም የሀገራቸውን ምጣኔ ሃብት እንዲገነባ ነው።ለምሳሌ የወደብ ቦታዎች የሚመረጡት የሀገራቱን አንጡራ ሀብት በተገቢ መልክ ለማውጣት ከማመቸቱ አንፃር እንጂ ለሕዝብ ከሚሰጠው ጥቅም አንፃር አይደለም።በምዕራብ አፍሪካ እና በምስራቅ አፍሪካ በቅኝ ገዥዎች የተሰሩትን ወደቦች መመልከት ይቻላል።

ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ካልተገዙ ጥቂት ሃገራት አንዷ ነች።ኢትዮጵያውያንን ቡና አትጠጡ ቢራ ብቻ ጠጡ ብሎ ያስገደዳቸው ቅኝ ገዢ አልነበረባቸውም።እድሜ በደማቸው ሀገራቸውን አስከብረው ለኖሩት አባቶቻችን እና እናቶቻችን።እኛ እንደ ብዙ የአፍሪካ ሃገራት ዋና ከተማችንን የቅኝ ገዢዎች አልመረጡልንም። አለመምረጥ ብቻ አይደለም የከተሞቻችን ህንፃዎች እና መንገዶች በአብዛኛው የተሰሩት በእራሳችን መሀንዲሶች ነው።የአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃቤት ፕላን ሲቀርብ አንድ ፈረንሳዊ መሃንዲስ ባለ ብዙ ፎቅ እንዲሆን አድርጎ አቅርቦ ነበር።በኃላ ግን ኢትዮጵያዊው መሃንዲስ (ስማቸውን አላስታውስም) ወደ ንጉሡ ቀርበው ''ይህንን ያህል ፎቅ ብዙ ሕዝብ በእየለቱ በሚወጣበት እና በሚገባበት ህንፃ ላይ አይሆንም።ይህ ማለት ከሀገሩ ሊፍት እንድናስገባ ሊያደርገን ነው።ከእዝያ ይልቅ ወደጎን ነው መለጠጥ ያለበት'' ብለው ባቀረቡት ሃሳብ መሰረት ማዘጋጃ ቤቱ ወደጎን እንዲሰፋ ተደረገ።በእዚህም ብዙ ሕዝብ ለጉዳዩ በቀላሉ ለመውጣት እና ለመግባት ቻለ።ቅኝ ገዢዎች መሰረተ ልማቱን እንዴት ለሀገራቸው ኢንዱስትሪዎች መጋቢ እንዲሆን አድርገው እንደሚቀርፁ የሚያመላክት አንዱ ማሳያ ነው የማዘጋጃ ቤቱ ህንፃ ጉዳይ።
ቅኝ ግዛት መዘዙ ብዙ ነው።ጉዳቱ የሚታወቀው ትውልድ በተቀያየረ ቁጥር ነው።

ዛሬ ግን ያልገባኝ ጉዳይ በኢትዮጵያ የቢራ ፋብሪካ እንደ አሸን መፍላት ነው።በምግብ እራሷን ያልቻለች ሃገር ለምንድነው የእህል ቀበኛ የቢራ ፋብሪካዎች እንዲበዙላት የተደረገው? ብዙ ተመጣጣኝ ምግብ ማቀናበርያ በምትፈልግ ሀገር ውስጥ ለምን ለቢራ ፋብሪካ በሚልዮን የሚቆጠር ገንዘብ እንዲወጣ ይደረጋል? በኑሮ ውድነት በሚንገላታ ሕዝብ መካከል አማላይ የሆኑ የቢራ ማስታወቅያዎች ምን ይሰሩለታል? ቢራ ከሀገር ይጥፋ አይባልም።ሰው እንደ ምርጫው እና ፍላጎቱ ሊጎነጭ ይችላል።ግን እንደ ፖሊሲ ትኩረት ተሰጥቶት ሊደከምበት አይገባም።የኢህአዲግ የንግድ ድርጅቶች ሳይቀሩ የቢራ ምርት ላይ በከፍተኛ ትኩረት ሲሰሩ ይታያል።የቢራ ፋብሪካ መመስረት ብቻ ሳይሆን የማስፋፋት ሥራ በጣም እየተሰራበት ነው።በቅርቡ ወደ ገበያ ሊመጣ ነው የተባለው የራያ ቢራን ጨምሮ 8 የቢራ ፋብሪካዎች አሉ።እነርሱም አዲስ ቢራ፣በደሌ ቢራ፣ሐረር ቢራ፣ዳሸን ቢራ፣ሜታ  ቢራ፣ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ፣ባቲ ቢራ  እና በቅርቡ ሥራ የሚጀምረው ራያ ቢራ ናቸው።በኢትዮጵያ ያሉት የቢራ ፋብሪካዎች የማስፋፋቱ ሥራ ላይ የተጠመዱት የስርዓቱ የኢኮኖሚ መዋቅሮች ብቻ ሳይሆኑ በቦርድ መሪነት ለምሳሌ የራያ ቢራ ፋብሪካን ብንወስድ የኢህአዲግ/ወያኔ የሰራዊቱ አዛዦች ይገኙበታል።ዛሬ ሕዳር 17/2007 ዓም የወጣው ጋዜጣ የራያ ቢራ ፋብሪካ መከፈትን አስመልክቶ ባወጣው ዜና ላይ እንዲህ የሚል ይገኝበታል።

''አክሲዮን ማኅበሩን በቦርድ ሊቀመንበርነት እየመሩ ያሉት አቶ ኃይሌ አስግዴ ሲሆኑ፣ ምክትላቸው ደግሞ ሌተና ጄኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳዔ ናቸው፡፡ ሁለቱም አመራሮች በራያ ቢራ አመራር ውስጥ ያሉ ሲሆን፣ ሌተና ጄኔራል ፃድቃን የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ኃይሌ ደግሞ የቦርድ አባል መሆናቸው ይታወቃል'' ሪፖርተር ጋዜጣ 

ባጠቃላይ ይህንን ማለት ይቻላል። ፋብሪካዎቹ የስራ ዕድል ይፈጥራሉ።ግን የቢራ ፋብሪካዎች እንደ አሸን መፍላት እህልም ሆነ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ከሚገመተው በላይ ይበላሉ።ፋብሪካ ይኑረን። ግን አዋጪ እና ሌሎች አንገብጋቢ ፋብሪካዎች ለምን አይበልጡብንም? ነው ጥያቄው። ደግሞስ  ቅኝ ገዢዎች ከብዙ ጥቅማቸው አንፃር አደረጉት።እኛ ቅኝ ያልተገዛነውስ? ኢህአዲግ/ወያኔ በወሎ እና በጎንደር ብቻ አዳዲስ የቢራ ፋብሪካዎችን ከፍቷል።አንድ ቢራ ለመጥመቅ ከፍተኛ የምግብ እህል ፍጆታ እና ብዙ ሺህ የተጣራ ንፁህ ውሃ እንደሚፈልግ ይታወቃል።ቅኝ ገዢዎች አፍሪካውያን ቢራ እየጠጡ እንዲናውዙ ማድረግ አንዱ የተሳካላቸው  ስራ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው።የኛ ገዢዎች በየመንደሩ የቢራ ፋብሪካ በሚልዮን የሚቆጠር ገንዘብ እያወጡ የሚከፍቱልን ለምንድን ነው? ዳቦ ሳንጠግብ እና የምናነበውን ጋዜጣ ሁሉ ዘግተው አዕምሯችንን እያደነዘዙ የቢራ ፋብሪካ መደርደር ምን ይባላል? ከየት የተማሯት ''ጥበብ'' ነች?  ለናሙናነት 

ጉዳያችን
ህዳር 18/2007 ዓም (መጋቢት 4/2006 ዓም ወጥቶ የነበረ)

Sunday, November 23, 2014

''ጥቁሩ ቅዳሜ'' በመባል የሚታወቀው ደርግ ስልሳ የካቢኔ ሚኒስትር አባላት ሲቪል እና ወታደራዊ ባለስልጣናትን የረሸነበት ህዳር 14 1967 ዓም ዛሬ ህዳር 14/2007 ዓም 40 ዓመት ሞላው (ስም ዝርዝራቸውን ከቪድዮው ይመልከቱ)

ደርግ ባለሥልጣናቱን በህዳር ወር ላይ ከመረሸኑ በፊት ሰኔ 21/1966 ዓም አፄ ኃይለ ስላሴን ደርግ ስልጣን እንዲለቁ ሲጠይቃቸው የተናገሩት የመጨረሻ ቃል -

''በጠቅላላው የተናገራችሁትን ሰምተናል።የ ኢትዮጵያ ንጉሰ  ነገስት ስንሆን ስም ብቻ አይደለም።ህዝብንም ሀገርንም በሰላም ጊዜ የሚሰራበትን ጥፋትም ሲመጣ የሚመከትበትን በማሰናዳት መሆኑን ይህ በ ጦር ሰራዊታችን ውስጥ የታወቀ ሳይሆን ይቀራል ብለን አንጠረጥርም። ቢሆንም በየጊዜው የሚለዋወጠው ነገር ለሀገር የሚጠቅም ነገር እስካለበት የሀገርን ጥቅም በሌላ ለመለወጥ አይቻልምና ይህን ያነበባችሁትን ሰምተናል በእዚሁ ማቆም ነው።'' ብለዋል።ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

የታወቀ የጀርመን የፊልም ኩባንያ ከ20 ሚ. ብር በላይ በሆነ ወጪ “ዘ ኢትዮጵያን” የተሰኘ በኢትዮጵያ ላይ የሚያተኩር ፊልም ሊሰራ ነው።ፊልሙ በአገሪቱ ባህልና የአየር ፀባይ ተማርኮ በኢትዮጵያ በቀረ ጀርመናዊ እውነተኛ ታሪክ ላይ ያጠነጥናል፡፡ታዋቂ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች ይሳተፉበታል።

ፎቶ - ሳያት ደምሴ (ይህንኑ ፊልም አስመልክቶ ኢትዮ-ሲኒማ ሪቪው ድረ-ገፅ ላይ ከወጣው ፖስተር የተወሰደ)

ሳያት በኢትዮጵያ ፊልም ታሪክ ከፍተኛ ተከፋይ ትሆናለች  
ፊልሙን የሚቀርፀው የጀርመን የቴሌቪዥን ጣቢያ ነው
የታወቀ የጀርመን የፊልም ኩባንያ ከ20 ሚ. ብር በላይ በሆነ ወጪ “ዘ ኢትዮጵያን” የተሰኘ በኢትዮጵያ ላይ የሚያተኩር ፊልም ሊሰራ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ዕውቋ ድምፃዊና ተዋናይት ሳያት ደምሴ ከታዋቂ የጀርመን ተዋናይ ጋር በፊልሙ ላይ በመሪነት ትተውናለች፡፡ ሳያት ደምሴ በኢትዮጵያ ፊልም ታሪክ ከፍተኛው ክፍያ እንደሚከፈላት የፊልሙ ዝግጅት አስተባባሪ ዮሐንስ ፈለቀ ለአዲስ አድማስ ገልጿል፡፡ በጀርመናዊው ደራሲ ሄንሪክ ሄዲንት የአጫጭር ልቦለዶች መድበል ውስጥ የተካተተው “The Ethiopian” የተሰኘው ታሪክ ወደ ፊልም እንደሚቀየር የታወቀ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በአገሪቱ ባህልና የአየር ፀባይ ተማርኮ እዚሁ በቀረ ጀርመናዊ እውነተኛ ታሪክ ላይ ያጠነጥናል ተብሏል፡፡
በፊልሙ ላይ ከሳያት ደምሴ በተጨማሪ አንጋፋዋ አርቲስት ሃና ተረፈና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ተዋንያን እንዲሁም ሶስት ታዋቂ ጀርመናዊ ተዋንያን ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡ “ሳያት ብቻ ሳትሆን ሌሎችም ኢትዮጵያውያን ተዋንያን ከፍተኛ ክፍያ ያገኛሉ” ብሏል - አስተባባሪው፡፡ የፊልሙ ዳይሬክተር ታዋቂው ጀርመናዊ ፈርዲናንድ ለኢራች ሲሆን ፊልሙን በመቅረፅ ዕውቁ የጀርመን ቴሌቪዥን ጣቢያ “ሙቪ ዘ አርት ኦፍ ኢንተርቴይንመንት”፣ በፕሮዱዩሰርነት ደግሞ “ኮንስትሬይን ፊልም ፕሮዳክሽን” እንደሚሳተፉ አስተባባሪው ገልጿል፡፡ 

ኢትዮጵያ የተሟላ መሰረተ ልማት (ኢንተርኔት፣ ደረጃውን የጠበቀ ሆቱል፣ የቀረፃ ቦታና ሌሎች) የሏትም በሚል ፊልሙ በኬንያ ሊሰራ እንደነበር የጠቆመው አስተባባሪው “እንዴት የኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ያተኮረ ፊልም ኬኒያ ውስጥ ይሰራል” የሚል ከፍተኛ ሙግት ከተካሄደ በኋላ በኢትዮጵያ እንዲሰራ መወሰኑን ገልጿል፡፡ የፊልሙ ቀረፃ ከመጪው ሳምንት ጀምሮ በአዲስ አበባ፣ በድሬደዋና በሃረር እንደሚከናወን አስተባባሪው አክሎ ገልጿል፡፡ 
ምንጭ - ኢትዮ ሲኒማ ሪቪው ድረ ገፅ 
         - አዲስ አድማስ ጋዜጣ  ኅዳር 13/2007 ዓም (22 November, 2014) ዕትም 
 •  

Thursday, November 20, 2014

የሃና ጉዳይ የፖለቲካው ብልሹነት ውጤት ነው።የፖለቲካው ብልሹነት ሌሎች ብዙ ሃናዎች እንዲደፈሩ መንገድ ያመቻቻል። እንዴት? (የጉዳያችን አጭር ማስታወሻ)


መንደርደርያ 
ከጥቂት ቀናት በፊት በአዲስ አበባ የ17 ዓመት ወጣት በአውሬ ለበስ ወጣቶች ተደፍራ ሕይወቷ ማለፉ መሰማቱ የብዙዎቻችንን ልብ ያደማ ጉዳይ ነበር።ጉዳዩ የአውሬለበስ ግለሰቦች ተግባር መሆኑ ባያከራክርም።ማህበረሰባችን እና የምድሪቱ ሰው ሰራሽ ሕግ በደንብ ልፈተሹ ይገባል።ግለሰቦች በያሉበት ሊብከነከኑ ይችላሉ።ሆኖም ግን እንደ አንድ ሕብረተሰብ ለመንቀሳቀስ እና ለማኅበራዊ ቀውሶች መፍትሄ ለመስጠት ነፃነት የተሞላበት አካባቢ የግድ ይላል።በታፈነ ሕብረተሰብ ውስጥ አፋኙ ስርዓት  ለችግሩ እራሱን ተጠያቂ ሳያደርግ።እንደ ጵላጦስ ''ከደሙ ንፁህ ነኝ'' ማለት አይችልም። ለምን?

በሀገራችን እያንዳንዱ የማኅበራዊ ለውጦች፣አደጋዎች እና ቀውሶችን እያጠና በወቅቱ  በማኅበራዊ ተቋማት አማካይነት እርማት እንዲወሰድ የመገናኛ ብዙሃንም ሆኑ የፖለቲካ አመራሩን የሚዘውረው (ኢህአዲግ/ወያኔ ) አንዳች ነገር አያደርጉም።እነኝህን ተቋማት በማፍረስ ላይ ግን ኢህአዲግ/ወያኔ ቀዳሚ ነው።የሃና ጉዳይ ምን ያህል የፖለቲካ አመራሩ የማኅበራዊ ደህንነት እና የፀጥታ ዋስትና ያለመስጠቱ አይነተኛ አመላካች ነው? ይህንን በምሳሌ እንረዳ-

ምሳሌ - 1/ 

ኢኮኖሚያችን ፖሊሲው፣አቅጣጫው እና ግቡ መጠናት ያለበት ገለልተኛ በሆኑ ምሁራን ነበር።ለምሳሌ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማኅበር ከአስር አመታት በፊት ጥሩ እንቅስቃሴ ያደርግ የነበረ መሆኑ ይታወቃል።ዛሬ እንቅስቃሴው የት ነው? አመታዊ ሪፖርቱን የሀገር ውስጥ የዜና አውታሮች ያሰማሉ? ዛሬ የኢህአዲግ/ወያኔን ሪፖርት ብቻ ነጋ ጠባ ሕዝብ እንዲሰማ ለምን ተገደደ? የሲቪል ተቋማትን የማፈን ተግባር አካል አይደለም?

ምሳሌ 2/ 

የኢትዮጵያ ሴት የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር በርካታ ስራዎችን የሰራ ነበር።በአዲሱ የመንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አዋጅ ስንት ሚልዮን ብር ነው ፍርድ ቤት አግዶበት አቅሙን ያሽመደመደው? በሌላው ሀገር በአፍሪካም ቢሆን የእዚህ አይነት ሲቪል ተቋማት ሪፖርቶች ፓርላማ ድረስ ቀርበው ጥናታቸውን የማቅረብ፣ሕጎች እንዲስተካከሉ የማሳየት እና የማማከር ሥራ ይሰራሉ።ይሄው ድርጅት በሴት እህቶቻችን ላይ የሚደርሰውን የመደፈር አደጋ ለማጋለጥ ብቻ ሳይሆን ብሔራዊ ንቅናቄ ለመፍጠር የጣረ ነበር።
ኢህአዲግ/ወያኔ እርሱ ያልጠረበው እንጨት እንጨት አይደለምና ገንዘቡን በፍርድ ቤት አገደው።ዛሬ ባለስልጣናቱም ሳይቀር የአዞ እንባ ያፈሳሉ።አሰራሩ እነ ሃና ሲደፈሩ ይጮሃል ሌሎች ብዙ ሃናዎች እንዲደፈሩ ግን መንገድ ያመቻቻል።

ባጠቃላይ 

ኢትዮጵያ ውስጥ የማኅበራዊ ቀውስን ቀድመው አጥንተው ተገቢው እርምጃ ሕዝብ እንዲወስድ የሚያደርጉ ድርጅቶች በኢህአዲግ/ወያኔ ተመትተዋል።የእዚህ አይነት ድርጅቶች ቢኖሩ ኖሮ የህዝቡን ማህበራዊ ቀውስ ደረጃ በጥናት እያሳዩ ባስደነገጡን እና ሕዝብ በመረጃ ተመስርቶ ወደ መፍትሄው እንዲሄድ በገፉት ነበር።ይህ ብቻ ሳይሆን በስልጣን ወንበር ላይ የተፈናጠጡትንም መንገድ ባሳዩዋቸው ነበር።ግን አልሆነም።ከእዚህ በከፋ ደረጃ ሕዝብ የሚሰማቸውን የሃይማኖት ተቋማት ሳይቀር በፖለቲካ አጅሎ የሃይማኖታዊ ችግሮችን ብቻ ሳይሆን ማኅበራዊ ጣጣዎችን እንዳይፈቱ ያደረጋቸው አሁንም ፖለቲካውን የሚዘውረው ኢህአዲግ/ወያኔ ነው።

በመቶ ሺህ የሚቆጠር የጎዳና ተዳዳሪ በኢትዮጵያ ከተሞች የተርመሰመሰው ባለፉት 23 አመታት ነው።ሴቶች እህቶቻችን የመደፈራቸው ዜና የሳምንት ክስተት የሆነው ባለፉት 23 አመታት ነው።ጫት መቃምያ በት በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት በር ላይ የተከፈተው ባለፉት 23 አመታት ነው።የሽሻ ቤቶች ትልልቅ ሕንፃዎችን ሁሉ መዳረሻቸው ያደርጉት ባለፉት 23 አመታት ነው።ባጭሩ የማኅበራዊ ቀውሱ መነሻ በስልጣን ላይ የተፈናጠጠው የኢህአዲግ/ወያኔ የአፈና ውጤት ነው።የፖለቲካ አመራሩ እና ፖሊሲው ማኅበራዊ ቀውሱን አፋጥኖታል።መጨረሻው የት እንደሆነ አይታወቅም።

ጉዳያችን 
ህዳር 11/2007 ዓም  (ኖቬምበር 20/2014)

Tuesday, November 18, 2014

ኬንያ፣ቡክናፋሶ እና አዲስ አበባ በእዚህ ሳምንት (ከሶስት ደቂቃ ያነሰ አጭር የቪድዮ ዜና ጋር)

 ኬንያ 

ኬንያ አንዲት ወጣት ሚኒስከርት በመልበሷ በወንዶች የደረሰባት ጥቃት በመቃወም ትናንት ሰኞ  በሺህ የሚቆጠሩ የናይሮቢ ሴቶች፣ተማሪዎች ሰልፍ ወጡ። ሕግ ይስተካከል! አዲስ አበባ ላይ በአውሬ ለበስ  ወንዶች ጥቃት የደረሰባት ሃና ሕይወቷ አልፎ የአዲስ አበባ ወጣት ሕጉ ይሻሻል ብሎ አይጮህም።ነገ በእኔ ነው።

ቡክናፋሶ

የሃያ ሰባት ዓመት አምባገነንነት ለሌላ ተጨማሪ  ዓመታት በስልጣን ላይ ለመቀመጥ ፓርላማው ሕጉን እንዲቀይር ያደረጉት ፕሬዝንዳንትን በሁለት ቀን አብዮት አስወግዶ ዛሬ ወታደራዊ አመራርን በሲቪል አስተዳደር ቀየረ።ሀገሪቱ  በመጪው ዓመት የአሁኑ ጊዚያዊ ፕሬዝዳንት የማይሳተፉበት አዲስ ምርጫ ታደርጋለች።ጊዝያዊ ፕሬዝዳንት ዛሬ ቃለ መሃላ ፈፀሙ።

አዲስ አበባ

በመጪው እሁድ አዲስ አበባ ላይ ከአርባ ሺህ ሕዝብ የማይንስ የሚሳተፍበት ታላቁ እሩጫ መነሻ እና መድረሻውን ጃን ሜዳ አድርጎ ይደረጋል።ገበታው በያይነቱ ነው።ከኬንያው የባሰ ጥቃት እህቶቻችን ላይ ተፈፅሟል።ከቡኪናፋሶ የከፋ በጎሳ ላይ የተመሰረተ አምባገነንነት በኢትዮጵያ አናት ላይ እየጨፈረ ነው።አንድ እንቁላል 3 ብር ከ 50 ሳንቲም በሚሸጥባት አዲስ አበባ አፍ ለጉሞ መሮጥ በራሱ ጤነኝነት አይመስለኝም።ኬንያ እና ቡክናፋሶ ጥለውን ሄዱ። ከእዚህ በታች ያለውን 3 ደቂቃ የማይሞላ ዜና ይመልከቱ።ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

Monday, November 17, 2014

የአንድ ወቅት የኮሜዲያን ልመነህ ቀልድ ለእዚህ ትውልድ ጥቂት ትምህርት ሳይኖራት አይቀርም። ፅሁፎቻችን፣የድረ-ገፅ ዘመቻዎችን እና ንግግሮቻችን ሕዝብ የሚያቀራርብ እንጂ የሚለያይ እንዳይሆኑ እንጠንቀቅ።(የጉዳያችን ማስታወሻ)

ኮሜድያን ልመነህ ታደሰ 

ልመነህ እና አጭር ኮሜዲው 
ኮመዲያን ልመነህ ታደሰ በአንድ ወቅት የኮሜዲ ሥራ ሲወሳ ቀዳሚ ስሙ የሚጠቀስ አርቲስት ነበር።ዛሬ ላለበት ሁኔታ አርቲስቶቻችን የሚያደርጉትን አንዳንድ ጥረቶች እያሞገስኩ (ድጋፎቹ በበቂ ደረጃ ናቸው ወይ? ለሚለው ጥያቄ መረጃ ባይኖረኝም) ይች በልጅነቴ የቀለዳት ቀልድን ማውሳት ፈለኩ።

 አጭር ኮሜዲ ድራማ - 
ሰውዬው ጎረቤቱን ሊከስ ፈለገ እና የሰፈሩን አንድ ወጣት ወደ ቤቱ ጠራው።ወጣቱን የፈለገበት ምክንያት የክስ ወረቀት እንዲፅፍለት ነበር።በመጀመርያ ያደረሰበትን በደል በቃል ነገረው፣ተረከለት በመጨረሻ ወጣቱ እንዲህ አለ ''ገባኝ እኔ ይህንን በደል በጥሩ ኪነ ጥበባዊ ፅሁፍ ከሽኘ ማመልከቻውን እስክፅፍልህ ግማሽ ሰዓት ስጠኝ'' ብሎ መፃፍ ጀመረ። ከግማሽ ሰዓት በኃላ ወጣቱ ለከሳሹ የፃፈውን ይዞ መጣ ለከሳሽም አነበበለት።

ወጣቱ ፅሁፉን ለከሳሹ ሲያነብለት ከሳሽ እንባው እየወረደ ነበር።በመጨረሻ ከሳሽ ማልቀሱን ማቆም አልቻለም።ወጣቱ ማመልከቻ ፀሐፊ ግራ ገባው።ቅድም ወደ ቤቱ ሲመጣ እንዲህ አልሆነም ነበር።አሁን የእርሱን ፅሁፍ ሲመለከት ይህን ያህል ማልቀሱ ግራ አጋባው።
ወጣቱ ጠየቀ - ''ምን ነካህ? ቅድም ጎረቤትህ ያደረሰብህን በደል ስትነግረኝ፣ያንን ሁሉ ታሪክ ስትተርክልኝ አላለቀስክም። አሁን የእኔን ፅሁፍ ስትሰማ ግን ማልቀስ ጀመርክ ጥላቻህም ባሰበት።ምንድነው ነገሩ?'' 

ከሳሽ መለሰ '' እኔ አሁን አንተ የፃፍከውን በደል ፈፅሞ አላውቀውም ነበር።እኔ በተራ ቃላት የማውቀውን በደል አንተ በከባድ ቃላት እና በስነ-ፅሁፍ ስታቀርበው የማላውቀውን በደል ስትነግረኝ ምንም እንኩአን አንተ ያልካቸው በደሎች ባይኖሩም ቢሆንስ ብዬ ጥላቻዬ ጨመረ።በጣም ነው የማመሰግንህ ያላደረገብኝን እና ያልተፈፀመብኝን ሁሉ ጨምረህ በስነ-ፅሁፍ አስውበህ በማቅረብህ።ቀድሞ በቀላሉ እናደድ የነበረውን ውብ በሆነ የፅሁፍ ችሎታህ የባሰ እንዳለቅስ ስላደረከኝ''

ወጣቱ ፀሐፊ ደነገጠ ማስታረቅ፣ሰላም ማውራት ሲገባው የባሰ ቤንዚን እየጨመረ መሆኑን ቆይቶ አወቀ።አንድነት ከመስበክ ይልቅ በደልን በኪነ-ጥበባዊ ፅሁፍ ከሽኖ ጎረበታሞቹን የባሰ ማጣላቱን አወቀ።የኮሜዲው መጨረሻ።

ወደ ዋናው ነጥብ ልምጣ  
በደል አለ።ማንም አይክደውም የበደሉን መጠን ለመለካት በደሉ የደረሰበትን ሰው ሆኖ መገኘት የግድ አይጠይቅም።ሰው መሆን በቂ ነው።ያለፈው የግማሽ ክ/ዘመን ታሪካችንን ብቻ ብንመለከት ደርግ በመላዋ ኢትዮጵያ ላይ ባደረሰው በደል ሁሉም የተነገረው ከተለያየ የስልጣን ፍላጎቶች አንፃር ነው።

በሰሜን ኤርትራ ለሚኖረው ሻብያ ''አንተ የተበደልከው ኤርትራዊ ስለሆንክ ነው'' አለው።
ህወሓት ለትግራይ ሕዝብ '' አንተ ትግራይ በመወለድህ ነው'' አለው።
ወለጋ ላይ ኦነግ ''አንተ ኦሮሞ በመሆንህ ነው'' አለው።
ይህ ሁሉ ሲሆን ግን በደርግ ስርዓት ውስጥ የደህንነት ሚኒስትር ሆነው የሚሰሩት የትግራይ ተወላጅ ነበሩ።እራሳቸው ኮ/ል መንግስቱ የኦሮሞ ተወላጅ ነበሩ።የኮ/ል መንግስቱ የቅርብ አማካሪ የኤርትራ ተወላጅ ነበሩ።እንደ ዘር የተነሱት ጉዳዮች ከአምባገነናዊ ባህሪ እና ከስልጣን ሽምያው ጋር ሲነፃፀሩ የትዬለሌ ነበሩ።መሰረታዊ ችግሮቹ ግን የሕግ የበላይነት አለመከበር እና ሕዝባዊ መሰረት ያለው የእያንዳንዱን ግለሰብ ተሳትፎ ያላገኘ የመንግስት ስርዓት እንጂ የጎሳ ጥያቄዎች አይደሉም።ይህ ማለት የብሔር ጭቆና የለም።ፈፅሞም አልነበረም አሁንም የለም ለማለት አይዳዳኝም። ነገር ግን የችግሮች ሁሉ መፍትሄዎች ወደ ብሔር ፖለቲካ ማራገብ ከወሰድነው ወይንም በይሉኝታ እየተያዝን አንዱን ወገን እናስደስት በሚል ተነሳሽነት ብቻ ጎሳን ካራገብን የማንወጣበት አዘቅት ውስጥ እንዳንገባ ያስፈራል።

የጎሳ ፖለቲካ የችግራችን ሁሉ ምንጭም መፍትሄም አይደለም  
እዚህ ላይ አሁን ያለንበትን የስርዓቱን የጎሳ ፖለቲካ ችግር እና በአንድ ጎሳ የመጠቅለል አባዜ መቃወም እና አጠቃላይ 'የኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግር የጎሳ ፖለቲካ ነው' ብሎ የመደምደም የመሃይም አስተሳሰብ መዳረሻው የት እንደሆነ አይታወቅም።የተለያዩ የፖለቲካ ቡድኖች ወደ ስልጣን መወጣጫ እስከመራቸው ድረስ የጎሳ ፖለቲካን ማራገብ እንደ አንድ ስልት ሲጠቀሙበት ይታያል።ይህ በአለማችን የተነሱ ጨካኝ አምባገነኖች የተከተሉት እኩይ መንገድ ነው።አሁን በስልጣን ላይ ያለው ህወሓት እየተከተለው ያለው ይህንኑ መንገድ ነው።ስልጣን ከያዘ ከ23 ዓመት በኃላም ስሙን ''የትግራይ ነፃ አውጪ'' የሚል ነው። በእርሱ መንገድ በመሄድ ስኬት አይገኝም።የተቀናቃኝን ተቃራኒ በመያዝ ግን ስኬት አለ።ጎሳ ለሚያራግበው ህወሓት ሌላ ጎሳን ማራገብ መቃወም ሳይሆን መመሳሰልን ያስከትላል። የሀገራችን ገበሬ ምን ያህል ፊደል ቆጠርኩ ከሚለው መሻሉን እናስብፅሁፎቻችን፣የድረ-ገፅ ዘመቻዎችን እና ንግግሮቻችን ሕዝብ የሚያቀራርብ እንጂ የሚለያይ እንዳይሆን እንጠንቀቅ

ጉዳያችን
ህዳር 8/2007 ዓም (ኖቬምበር17/2014)

ኢትዮጵያ በዘመናዊ ታሪኳ ታላቅ ተልዕኮ የሚኖረው ሀገራዊ የምምክር ኮሚሽን በተመለከተ ምን ያህል እናውቃለን?

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ኮሚሽን አማካሪ ኮሚቴ አባላትን ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል ባካተተ መልኩ አዋቅሯል። በእዚህ ጽሑፍ ስር የሚከተሉት ነጥቦች ምላሽ ያገኛሉ፡  ኮሚሽኑ እንዴት ተመሰረተ?  የኮሚሽኑ 11 ኮሚሽነሮች እንዴት ተመ...