ጉዳያችን - በጉዳያችን ሚድያ፣ኮምኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት የሚዘጋጅ ሲሆን ከ2003 ዓም ጀምሮ በድረ-ገፅ ላይ የነበረ በአሁኑ ጊዜ ከአንድ ሚልዮን በላይ ጎብኚዎች ያሉት ገፅ ነው። Gudayachn is prepared by Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant Organization. It has been online since 2011. Currently, Gudayachn is being visited by over One-million readers from all over the world.
ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages
Saturday, December 31, 2022
የእነደብረጽዮን ወደ አዲስ አበባ መምጣት ለፖለቲካዊ እርቅ ወይንስ ለአገራዊ እርቅ?
Wednesday, December 28, 2022
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በታላቅ ግርማ ሞገስ በሰዓታት ውስጥ ከመቀሌ አሉላ አባነጋ አየር ማረፍያ ጀምሮ መቀሌን መቆጣጠር ይጀምራል!
በእዚህ ምጥን ጽሑፍ ስር ፡
- ምስጋና ለኢትዮጵያ ህዝብ ይገባዋል፣
- አድናቆት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አመራር ያስፈልጋል።
- የትግራይ፣አፋር እና አማራ ክልሎች በጋራ በየትኛውም ወገን ለሞቱ ወገኖች ለሦስት ቀናት የሃዘን ቀናት ቢያውጁ፣
- የኢትዮጵያ ሕዝብ ዐይኑን በጨው ሳይሆን በአጃክስ አጥቦ ለታየው የህወሃት አመራር እንዴት ዓይነት ንስሃ እንደሚገባ እየጠበቀ ነው።
ለእዚህ ምንም ዓይነት ማብራርያ አያስፈልገውም።የህወሃት አመራሮች ከግማሽ ሚልዮን በላይ ህዝብ አጫርሰው በከረቫት ብቅ ብለው መታየታቸው እና አለማፈራቸው የኢትዮጵያ ህዝብ የእየቤቱ መነጋገርያ ነው።አሁን ለራሳቸው ንስሃ ገብተው ዳግም ኢትዮጵያን ከልብ ይቅርታ ይጠይቃሉ ወይንስ በለመዱት አፋቸው ደልለው መልሰው ሃገር ያምሳሉ? የሁሉም ጥያቄ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ግን እየጠበቀ ነው።
Friday, December 23, 2022
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቅ ሰሞኑን በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እና ክርስቲያኖች ላይ የሃሰት ትርክት ላቀረቡ ትምህርታዊ ምላሽ ሰጡ። (ሙሉ የቪድዮውን ምላሽ ይመልከቱ)
Monday, December 19, 2022
ወቅታዊው የኢትዮጵያ ሁኔታ በተመለከተ ልናውቅቸው የሚገቡ አምስት ወሳኝ ዐበይት ጉዳዮች
========
ጉዳያችን=========
የጎሳ ጉዳይ በተመለከተ በምናስበው ደረጃ አይደለም።
የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ሲነሱ በተለይ አዕምሮ የሚረብሹ ጉዳዮች በዜና ሲነገሩ ብዙ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጥሩት የስሜት መዋዥቅ አና የተስፋ መቁረጥ ስሜት ቀላል አይደለም።በተለይ በአብዛኛው የፖለቲካ ጉዳዮችን ሳይሰሙ የኖሩ ወይንም በግማሽ ልብ አልፎ አልፎ የሚከታተሉ ኢትዮጵያውያን በድንገት የሚሰሟቸው ክፉ ዜናዎች መጪውን በከፋ ደረጃ እንዲያዩ ያደርጋቸዋል።ይህ ደግሞ ወደ ዲያስፖራው ማኅበረሰብ ሲመጣ አጅግ የከፋ ይሆናል።ዲያስፖራው በሚኖርበት ሀገር የተረጋጋ አካባቢያዊ ሁኔታዎች ከመኖራቸው አንፃር ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ክፉ ነገር ብቻ የሚናገሩ የውጭ ሚድያዎች አና እንደ አሸን የፈሉት የዩቱብ ገፆች ሁሉ የሚሉት በአዕምሮ ላይ የሚፈጥሩት ጠባሳ ቀላል አይደለም። የእዚህ ዓይነት ዜናዎች ተጠራቅመው ተስፋ የቆረጠ አና ስሜታዊ ውሳኔ የሚወስን ማኅበረሰብ የመፍጠሩ አደጋም ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ ነው።
ይህ ማለት በኢትዮጵያ በፅንፍ ኃይሎች እና በሰሜኑ ህወሓት በጫረው ጦርነት ሳብያ እየጠፋ ያለው ሕይወት ቀላል ነው ወይንም በንፁሃን ላይ የደረሰው ሁሉ የሚቃለል ነው እእስከ አፋር አና አማራ ክልል ሁሉ የሆኑትና ዜጎች ላይ የደረሰው ሞት፣ስደት አና የንብረት መውደም አጅግ አሳዛኝ ነው።የሆነው ሁሉ ግን ዳግም እንዳይሆን አና የበለጠ ኢትዮጵያን አንዳይጎዳይ መጪውን ማስተካከል የሚጀመረው የዜጎችን የአዕምሮ ሁኔታ በሚገባ በመቃኘት አና የጠነከረ እንዲሆን በማድረግ ነው።
በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ የእርስበርስ የብሔር (ጎሳ) ግንኙነት በህዝብ ደረጃ የተበላሸ የሚመስላቸው፣አንዳንዱ ከወጣበት አካባቢ ውጭ ያለው ሁሉ አስጊ አድርጎ የማየት አደጋ አለ። ይህ ከበቂ መረጃ በራቀ መልኩ እራስን በአጥፊ ዩቱበሮች አና ሚድያዎች ልክ ወስኖ የመኖር የስህተት መንገድ ነው።ነባራዊ ሁኔታውን ለመረዳት ግን የኢትዮጵያ የጎሳ ግጭቶች ባህሪዎች የተለዩ አና ወደ ሕዝብ አንዳይመጡ የሚያደርጋቸው በርካታ ተፈጥሯዊ ጉዳዮች አሉ።ይህ ማለት አሁን ካለንበት ሁኔታ አንጂ ሕዝቡም ሆነ መንግስት በጋራ መሰረታዊ ለሆኑ የምጣኔ ሀብት አና ፖለቲካዊ ጉዳዮች መፍትሄ ካልሰጠን ለወደፊቱ ትውልድ የምናወርሰው አደጋ የለም ማለት ግን አይደለም።
ኢትዮጵያ የተለየች ሀገር የሚያደርጋት አና የጎሳዊ ጉዳዮች የሀገሪቱን ስር አንደማይነቅል በአርግጠኘትን መናገር የሚቻለው በሚከተሉት መሰረታዊ ነባራዊ ሁኔታዎች ነው።
ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው ሕዝብ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ቢያንስ ከሁለት ጎሳ የሚወለድ ነው።ነገር ግን ይህ የህብረተሰብ ክፍል አሁን ያለው የፖለቲካ አደረጃጀት አግልሎታል።ለመብቱ ሲነሳ ግን ኢትዮጵያዊነት ቦታውን ያስከብራል።
በኢትዮጵያ የጎሳ ግጭቶች ከመንግስት ባለስልጣናት የሚነሱ አልያም የፖለቲካ ድርጅቶች በቢሮ ቀምመው የሚሰሯቸው አንጂ ታሪካዊ የግጭት መሰረት ይዘው የሚመጡ አይደሉም።ይህንን ለማብራራት ብዙ ቦታ ስለሚወስድ አንዳለ አስቀምጠዋለሁ።እውነታው ግን ይሄው ነው።
በኢትዮጵያ የተደረጉ የእርስ በርስ ጦርነቶች ምን ያህል ጎሳን አየቀሰቀሱ ቢመጡም ኢትዮጵያ በቅኝ ተገዝታ ስለማታውቅ አና በማኅበረሰቡ ውስጥ የቆየ የመለያያ ሥራዎች አንደ የሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ስላልተተከሉ ሕዝብ በራሱ ማኅበራዊ መስተጋብር የሚያመክንበት የራሱ አሰራር አለው።ይህ አሰራር ደግሞ በማኅበራዊ ትስስር ብቻ ሳይሆን በታሪካዊ መንገዶች ሁሉ የተሰናሰለ ነው።
ከላይ ለተነሱት ነጥቦች ማስረጃ የሚሆነን የቅርቡን ከህወሓት ጋር የተደረገውን ጦርነት አና በወለጋ አየሆነ ያለውን መመልከት በቄ ነው።ህወሓት የትግራይን ሕዝብ የቀረው ኢትዮጵያዊ ሊያጠፋህ ነው የሚል የሐሰት ፕሮፓጋንዳ ሲነዛ ከሦስት አስር ዓመታት በላይ ሆኖታል።ይህንን ዘመቻውን በማድረግ የትግራይ ሕዝብ ሁሌ አየደነገጠ አንድኖር አና ህወሓት ከሌለ የማይኖር አድርጎ አንዲያስብ ብዙ ሰርቶበታል።ይህ ሁሉ ዘመቻ ፍፃሜ ለማድረስ ደግሞ መከላከያ ላይ የተቀናጀ ጥቃት በመፈፀም ከሃያ ዓመታት በላይ አብሮት የኖረውን ብቻ ሳይሆን ከሕዝቡ ጋር ተዋልዶ አና ተዛምዶ የኖረውን የትግራይ ማኅበረሰብ ለማቆራረጥ ሞከረ።ይህ ብቻ አይደለም።በአማራ አና አፋር ሕዝብ ላይ ሦስት ዙር ወረራ ሲያደርግ የትግራይን ሕዝብ ከአማራ አና ከአፋር አቆራርጦ የፍርሃት ስሜቱን በማናር አና ህወሓት ከሌለ ትግራይ አትኖርም የሚል ስሜትም ለመፍጠር በማለም ነበር አጅግ የሚዘገንኑ ግፎች በሰላማዊው የአማራ አና አፋር ሕዝብ ላይ አንዲፈፀም ያደረገው።የህወሓት ፍላጎት የጠላትነት ስሜት በማናር የትግራይ ሕዝብ ለህልውና በሚል ከህወሓት ጋር አብሮ ገደል አስቀመግባት ድረስ ለመያዝ ያለመ ነበር።ከአዚህ በተጨማሪ በመሃል ሀገር ከሚኖሩ በሚልዮን የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ላይ ሌላው ሕዝብ ይነሳል ይህም የትግራይ ሕዝብ ከህወሓት ጋር የበለጠ ያጣብቀዋል የሚል ከንቱ ስልት ይዞ ነበር የግፍ ስራውን ሲፈፅም የነበረው። ይህ የህወሓት ሕልም ግን አልሰራም።በመሃል ሀገር በሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ላይ ሕዝብ አንዳችም የተለየ መልክ አላሳየም።ህወሓት ወንድሙን ወሎ አና አፋር ላይ የገደለበት መሃል ሀገር የሚኖር ኢትዮጵያዊ ጎረቤቱ የትግራይ ተወላጅ ተጠይቂ አንዳልሆነ ጠንቅቆ ያውቃል።
በተመሳሳይ መንገድ በወለጋ የተፈፀመው በንፁሃን በአብዛኛው የአማራ ተወላጆች አና አንዲሁም የኦሮሞ ማኅበረሰብ ላይ የደረሰው የጅምላ ግድያ አቀናባሪው የፖለቲካ ድርጅቶች አንጂ ሕዝብ አንደህዝብ ተነስቶ የፈፀመው አይደለም።ለምሳሌ በወለጋ ለዓመታት የኖሩ የአማራም ሆነ የኦሮሞ ማኅበረሰብ ጎረቤቴ ተሰብስበው አንዲህ ዓይነት ግፍ ፈፀሙብኝ ያኛው መንደር ሰው በአዝህኛው መንደር ሕዝብ ላይ ይህንን አደረገ የሚል ክፉ ወሬ አልተሰማም። በፖለቲካ ድርጅቶች የተደራጁ የታጠቁ ኃይሎች አና የአነርሱ የሴል አካላት ከልዩ ኃይል ወይንም በመንግስት መዋቅር ውስጥ ተሸሽገው የፈፀሙት ወንጀል ነው በኢትዮጵያ አየታዬ ያለው።የፖለቲካ ድርጅቶች አና በመንግስት ውስጥ የተጠለሉ ወንጀለኞች መሆናቸውን ሕዝብ ስለሚያውቅ በጥቃቱ የሚሰደዱትን ስደተኞች ቦታ ቀይረው በሰፈሩበት ሁሉ የሚረዳቸው የአካባቢው ማኅበረሰብ ማለትም የኦሮሞም የአማርም ማኅበረሰብ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል።
ከላይ በትግራይም ሆነ በወለጋ ለሆኑት ሁሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደህዝብ ያለው ጥንቁቅነት፣የይቅርባይ መንፈስ ይዞ ነገ ላይ የሚያሻግር ሥራ ላይ ማትኮሩ አና አሁንም የፖለቲካ ድርጅቶች አና በመንግስት ውስጥ የተጠለሉ ወንጀለኞች የሚሰሩበትን ወንጀል ወደ ጎረቤቱ ሳያጋባ የመኖር ጥበቡን ማድነቅ አና ይህንን አጉልተን ማሳየት አስፈላጊ ነው።ከብዙ መጥፎ ነገሮች ውስጥ መልካም ነገሮችም አሉ አና ይህንን የኢትዮጵያን ሕዝብ መልካም ነገር አውጥተው የሚያሳዩ ሚድያዎች ስለሌሉ አና ክፉ ክፉው ብቻ ስለምነገረኝ አራሳችንን ሳናውቅ አንድንኖር አየተደረግን ነው።ባለው አጋጣሚ ግን ይህንን መልካም ጉዳይ አሁንም አጉልቶ አና ተጨባጭ ታሪኮችን ይዘው ሚድያዎች ሊመጡ ይገባል።ይህ ደግሞ አሁን ያለውን ትውልድ አንድነት ለማጠንከር ብሳይሆን ለመጪው ትውልድ አንዴት ይህንን ጊዜ አንዳለፍን ማሳያ ተጨባጭ ትምህርት ስለሚሆንም ጭምር ማለት ነው።
በአእምሯችን ላይ ሚድያዎችና የመንደር ወሬዎች የፈጠሩብንን ጥቃቅን ቀበሮዎች እንንቀላቸው።
ሕዝብ ዝምብሎ አይለያይም መጀመርያ አዕምሮ ላይ የመለያየት ጥቃቅን ቀበሮዎች በእየለቱ እንእንዲፈጠሩ ይደረጋል።ጥቃቅን ቀበሮዎቹ ሌላው ሕዝብ መጥፎ እንደሆነ የማሰብ፣እራስ ከተወለዱበት አና የመጡበት አካባቢ ውጭ ያለ አደገኛ አና አጥፊ ነው የሚል የሐሰት ትርክት በየአለቱ የምንሰማው የማኅበራዊ ሚድያ መጥፎ ጎርፎች የሚመጣ ነው።በማኅበራዊ ሚድያ ላይ የሚጣሉት አንዱን ጎሳ ከሌላው የሚያብጠለጥሉ አና የራስን ጎሳ የሚያሞካሹ ጥቅሶች፣ንግግሮች አና የምናከብራቸው ሰዎች የተሳሳተ የጥላቻ ሃሳቦች ሁሉ በጥቃቅን የጥላቻ ቀበሮዎች አእምሮአችንን ይበክሉታል። ይህ አጅግ አደገኛ ሁኔታ ነው።በአዚህ ዓይነት ስሜት ውስጥ ሰዎች የሚያውቁትን ጎረቤት ብቻ ሳይሆን የተለይ የጎሳ አባል ነው የሚሉትን የሚያውቁትን አና አብረው ለዘመናት የኖሩትን ዘመድ ሳይቀር ሳያውቁት ክፉ ስሜት አንድሰማቸው ያደርጋል። ስለሆነም ሰውን በሰውነቱ የማክበር አና የተሳሳተ ቢኖርም የሚታርም መሆኑን የማመን ስብእና ማዳበር ያስፈልጋል።ይህንን ለማድረግ ያማያስፈልጉ የውሸት ትርክቶችን አለመስማት፣ጆሮን ከመጥፎ ወሬ መጠበቅ አና የሰውነት ክብርን ጠብቆ መኖር ያስፈልጋል። ይህንን ለማድረግ ደግሞ በተለያየ ጊዜ ወደ አእምሮ የገባውን ጥቅቅን የጥላቻ ቀበሮ መንቀል ያስፈልጋል።
ኦሮሞ ሁሉ ወንድሜ ነው፣ትግራይ ሁሉ ኢትዮጵያዊ ወገኔ ነው፣አማራ ሁሉ ወገኔ ነው፣ሱማሌ ቤተሰብ ነው፣አፋር የአኔው ነው አያልን በአግባቡ አእምሮ የማከም ሥራ ያስፈልጋል። ይህንን በተገቢው መንገድ መስራት የሚገባቸው ሚድያዎች አሁንም፣ አሁንም ብዙ ይጠበቅባቸዋል።
ኢትዮጵያን የሚመራ መሪ በማጥላላት የኢትዮጵያን ርዕይ ለማጨለም መሞከር የተለመደው የባዕዳን ስልት በመሆኑ እንንቃ!
ችግሮችን ሁሉ የሀገር መሪ ላይ አስቀምጦ የሚፈለገውን ሀገር ማፍረስ የቀዝቃዛው ጦርነት አንዱ ስልት ነው።ይህ ስልት በወቅቱ የምስራቁ ጎራ ሊጠቀምበት አልቻለም።ምክንያቱም የምዕራብ ሀገሮች መሪዎች ተቀያያሪ ናቸው። በተወሰነ ጊዜ ምርጫ ማድረጋቸው መሪዎቻቸው በስልጣን አስካሉ ድረስ ላለው አጭር ጊዜ ኢላማ ቢደረጉም አዳዲስ ተመራጭ መሪዎች ከአዲስ ሃሳብ ጋር ስለሚመጡ የህዝቡንን ስሜት የመግዛት አቅማቸው ከፍ ያለ ሆኗል።በአዚሁ የቀዝቃዛው ጦርነት ጊዜ የምዕራቡ ዓለም ግን በምስራቁ ዓለም ለነበሩ መሪዎች ላይ በሚገባ ተጠቅሞበታል።በጊዜው የነበሩት የኢትዮጵያ መሪ ኮለኔል መንግስቱ ኃይለማርያም አንዱ ሰለባ ነበሩ።የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊ አና ምጣኔ ሃብታዊ ችግሮች ሁሉ ተጠያቂ ተደርገው አንዲቀርቡ የተደረጉት ኮሎኔል መንግስቱ ነበሩ።በአዚህም የኮሎኔል መንግስቱ መወገድ ብቻ የኢትዮጵያን ችግር ይፈታል የሚል ቂላቂል ሃሳብ ተጠቂ የሆነው ተራው ሕዝብ ብቻ ሳይሆን በኮሎኔል መንግስቱ ዙርያ የተሰበሰቡ ከፍተኛ ባለስልጣናት መሆናቸው የፕሮፓጋንዳው ኃይል ምን ያህል አንደሰራ አአላካች ነው።ለአዚህም ነው ግንቦት 13፣1983 ዓም ኮሎኔል መንግስቱ ከኢትዮጵያ መውጣታቸውን አስመልክቶ በወጣው የመንግስት መግለጫ ላይ ‘’የኮሎኔል መንግስት ከስልጣን መወገድ ለአገራችን ሰላም አስፈላጊ በመሆኑ’’ የሚል ዓረፍተ ነገር የተጨመረበት እና ለኢትዮጵያ ሕዝብ በራድዮ አና ቴሌቭዥን የተነበበው።በጊዜው መንግስቱ ኃይለማርያም ከአስፈሪ ሰው ጋር ብቻ ሳይሆን ከመጥፎ ነገር ጋር ሁሉ የተዛመደ ተደርጎ አንድሳል ተሰርቶ ነበር።
በቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ የስልጣን ማብቅያ ላይም የታየው ይሄው ነው።ንጉሱን የማጥላላት ዘመቻ ውስጥ ውስጡን በተቻለ መጠን በተለይ በወቅቱ በነበረው ወጣት ዙርያ ተሰርቷል።ኢትዮጵያን ወደዘመናዊ አስተዳደር ለማምጣት ከትምህርት አስቀ ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ድረስ ብዙ የሰሩት ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ላይ የተደረገው የማጥላላት ዘመቻ አስቀ ቤተሰባቸው ድረስ አንዲዘልቅ ከመሞከሩ የተነሳ የራሳቸው ልጆች ብቻ ሳይሆኑ በወቅቱ የነበሩት ባለስልጣናት ሳይቀሩ ከንጉሡ ጋር አብረው ለኢትዮጵያ መፍትሄ ለማምጣት አስከመዘናጋት አድርሷቸዋል።በወቅቱ ጥቂት ምሁራን ብቻ ችግሩን ከንጉሡ ጋር ብቻ ማያያዝ አና የአርሳቸው መወገድ ብቻውን የኢትዮጵያን መፍትሄ አንደማያመጣ ይልቁንም አርሳቸውን በቦታቸው በሀገር ክብርነት አስቀምጦ አስተዳደሩን በሕዝብ በተመረጠ መንግስት መቀየር አስፈላጊ መፍትሄ ነው ያሉት አንዴ ደራሲ አና ዲፕሎማት ሐዲስ አለማየሁ ያሉ ምሑራን ብጎተጉቱም የሰማቸው የለም።ይልቁንም የጥላቸው ዘመቻ ንጉሡ አፍሪካ ላይ የነበራቸውን የቅኝ ግዛት አንዳስጣሏቸው ያሰቡ ቅኝ ገዢ መንግሥታት ጭምር የተደገፈ ስለነበር አና ሕዝቡም ንጉሡ የሁሉ ችግር መነሻ ተደርገው ስለተነገሩት አና ይህንኑ በየዋህነት የተቀበሉ የጦር መኮንኖች ሳይቀሩ ንጉሱን በቭኦልስዋገን መኪና ከቤተመንግስት ወደ አራተኛ ክፍለጦር ይዞ መሄድ አንደትልቅ ጀብዱ ቆጠሩት።በወቅቱ የነበረው ወጣትም የኢትዮጵያ ችግር ሁሉ የሚወገድ መስሎት ጨፈረ።
ዛሬም ያለንበት ጊዜ ተመሳሳይ ነው።ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይን በኢትዮጵያ ላይ የጥቅም ፍላጎት ያላቸው ኃይላኑ መንግሥታት በመጀመርያ የስልጣን ዘመናቸው አካባቢ በጣም አሞገሷቸው።በማሞገስ ብቻ አልቆሙም የኖቤል ተሸላሚ መሆናቸውን አድንቀው ፃፉ።የኢትዮጵያ ሕዝብም ከፍተኛ ድጋፉን ገለፀ።በመቀጠል ችግሮች ሲፈጠሩ የችግሮቹ ሁሉ ምንጭ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ናቸው የሚል የሞኛሞኝ ሃሳብ በበታኝ ኃይሎች መስተጋባት ጀመረ።ይህንኑ ሃሳብ የሚቀምር አራሱን የቻለ ቡድን ከህወሓት አስቀ ኦነግ አና በአማራ ስም ከሚነግዱ አክራሪ ቡድኖች አስከ ባህር ማዶ የደህንነት ቡድኖች በአንድነት አየተገመደ ለፕሮፓጋንዳነት ዋለ።አዚህ ላይ ብዙ ሰበብ መስጠት ይቻል ይሆናል። በኢትዮጵያ የተፈፀሙት ግድያዎች፣ስደቶች አና የንብረት መውደም ምንም አንኩዋን አያንዳንዱን ጉዳይ በዝርዝር መመርመር ቢያስፈልግም መንግስትን አይመለከተውም አያልኩ አይደለም።ነገር ግን አያነሳሁ ያለሁት በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ችግሮች ሁሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ናቸው የሚል የጅላጅል ሃሳብ በአእምሯቸው ለምመላለስ አና ይህንኑ አንደመፍትሄ ለሚመስላቸው ዜጎች ቆም ብለው አንድያስቡ ደጋግሜ አየነገርኩ ነው።
አዎን! ጧት ማታ ዓቢይ! ዓቢይ! የሚል ንግግሮች በአያንዳንዱ የኢትዮጵያ ችግሮች ላይ የሚነገሩት ሆን ተብሎ አና የተለመደ የስነልቦና ዘመቻ መሆኑን ልብ ማለት ይገባል።ለምሳሌ የህወሃቱ ጌታቸው ረዳ አና በኢትዮጵያ ጥቅም ላይ የቆሙ ከባአዳን ድርጎ የምላክላቸው ዩቱበሮች ስንት ጊዜ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ስም አንደሚጠሩ ቁጠሩት።ይህ በአጋጣሚ የሚመስለው ካለ ተሞኝቷል።በስነ ልቦና አማካሪዎች የተጠና አና ችግሩን በዋናነት የጥፋት አጀንዳቸውን ለማስፈፀም አላስቻለኝም ያሉትን መሪ ስም ደጋግሞ በጥላቻ በመጥራት ከህዝብ መነጠል አና ሕዝብ የችግሩ ሁሉ ምንጭ መሪው ነው ብሎ አንድያምን አና በርሱ ላይ አንድነሳ ለማድረግ የሚሞከር ሙከራ ነው።በቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ላይ አና በኮ/ል መንግስቱ ላይ የተፈፀመው ይሄው ነው።የኢትዮጵያ ችግር መውጫ ሌላ መንገድ ምሑራኑ አንዳይፈልጉ በጭፍን ፕሮፓጋንዳ የኢትዮጵያ ችግር የሚወገደው ንጉሡ አና ኮለኔሉ ሲወገዱ ነው የሚለውን የጅል ሃሳብ አብረው አቅደው ሲያስፈፅሙ የነበሩትን ባለስላጣናት ሁሉ አታለሉበት።አንድ ሀገር ምንም ልምድ የሌላው መሪ ይዛ ችግር ለመፍታት ከምትሞክር በአንድሳምንትም ቢሆን በመምራት ልምድ ያለው መሪ የችግሮችን አፈታት አና መጪውን የመረዳት አቅም አለው።
ስለሆነም ዛሬም ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ላይ የሚከፈቱ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻዎች ግብ ሕዝብ የችግሩ ብቸኛ መፍትሄ የአርሱ አለመኖር አንድመስል አና በኃላ ኢትዮጵያውያን መሪ በድንገት አጥተው በሚያደርጉት ሹክቻ የባአዳን አራት ለማድረግ የታሪካዊ ጠላቶቿ ዋና ግብ ነው።ልብ ያለው ልብ ይበል።መሪ ሲሳሳት ባለበት ለማረም አና ሲወርድም በሥርዓት አና በሕግ ይህም በምትፈልገው ጊዜ መጥቶ የሚያማክርበት አመቺ ሁኔታ ተፈጥሮ አንጂ በማጥላላት አና በመገፍጠር ኢትዮጵያን አናጠፋ ይሆናል አንጂ ያለፈውን ስህተቶች አያርምም።አዚህ ላይ መሪዎች የማይወቀሱ፣የማይቀሰሱ ናቸው የሚል መልአክት አያስተላለፍቁ አይደለም።ለአዚህ ሕዝቡም ምድያዎችም መሞገት አለባቸው።ነገር ግን ለሀገር ያላቸውን የመሪነት ሚና አና የሰብአዊ መብታቸውን በሚያጥላላ ደረጃ መሄድ ከራስ አልፎ መጪውን ትውልድ መበከል ነው።መሪዎችን ኢላማ አድርጎ የችግሮች ሁሉ ምክንያትም መፍትሄም አድርጎ ማቅረብ ግን ታሪካዊ ስህተት ነው።
ማክበር የሚገባንን የያዝነውን የፖለቲካ አቅጣጫ ምሕዋር አለመልቀቅ
መንግስት አንዴት ይመሰረታል? የሚለው ጥያቄ ሁሌ ሊያቀራክሬን አይገባም።መንግስት ወደ ቤተመንግስት የሚገባው ወደፊትም መቀጠል ያለበት መንገድ ለጊዜው አንድ መሆኑን በትክክል ማመን ይገባል።ችግር በተፈጠረ ቁጥር ትንንሽ ዘውድ መድፋት የሚፈልግ ሁሉ አንዴ በክላሽ ሌላ ጊዜ የራስን ስም ለማግነን በመዋተት የኢትዮጵያን ሕዝብ መከራ የሚያሳዩት ስልጣን ከምርጫ ውጪ ሊገኝ ይችላል በሚል ነው።የያዝነው የፖለቲካ አቅጣጫ አና ምሕዋሩ ስልጣን በምርጫ የሚለው ነው።ይህንን ማዳበር አና ወደ የበለጠ ጥራት ያለው የምርጫ ሂደት ለማሳደግ ሁልጊዜም መስራት ይገባል።ለአዚህ ደግሞ የሚድያው፣የሕግ አውጪው አና ሕግ አስፈፃሚው አንዲሁም የሁሉም ዜጋ ጥረት ይጠይቃል።ስለሆነም ህዝብም አቅጩን መንገር ያለበት ከምርጫ ውጪ የስልጣን መንገድ የለም ነው።ያለው መንግስት ያልተስማማው በመጪው ምርጫ ላይ ለመስራት ይነሳ።ከአዚህ በተለየ ሌላው መንገድ ዝግ በምሆኑን ደጋግሞ መንገር አና ማሳየት በራሱ የብዙ ሰላም ምንጭ ነው።
የምጣኔ ሀብት አድገት ለማምጣት የሚደርገው ጥረትን ወደ መስዋአትነት ደረጃ ማስመንደግ
ሀገር የሚያፈርሰው የፖለቲካ ስርዓት መፈረካከስ ብቻ አይደለም።የምጣኔ ሃብቱ አለመስተካከል አና ቀጣይነት አና ተከታታይ ትውልድን የሚያሳትፍ የአድገት ሂደት ላይ አለመገኘት በራሱ ሀገር ያፈርሳል።በድህነት ውስጥ የሚዳክር ተከታታይ ትውልድ ለባአዳን ባርነት የመሰጠቱ አደጋ የበዛ ነው።ቀጣይነት አና ተከታታይ አድገት ሲኖር የትውልዱ ተስፋ ይለመልማል።በሀገሩ ላይ ያለው ተስፋም ከፍ ያለ ስለሚሆን ለበለጠ ፈጠራ ይነሳሳል።በመሆኑም የምጣኔ ሀብት አድገት ለማምጣት የሚደረገው ጥረት የህልውናችን አንዱ አካል መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል።ህልውና መሆኑን ከተረዳን የህልውና ጉዳይ በተራ ጥረት አና ያዝ ለቀቅ በሚደረግ ሥራ ለውጥ ማምጣት አይቻልም ማለት ነው።
ለማጠቃለል፣ኢትዮጵያን ውጤታማ ወደሆነ የእድገት ደረጃ ለማሸጋገር በትክክል የሚቻልበት መስመር ላይ ሆነን በተሳሳቱ አስተሳሰቦች እና ተስፋ መቁረጥ ወደኃላ የመሄድ ምንም ዓይነት ችግር አንዳይገጥም ሁሉም ከተለመደው አና በመንጋ ከሚሄድ እሳቤ መውጣት አስፈላጊ ነው።የመንግስት ስርዓት ትክክለኛውን መስመር አንዳይለቅ ጋዜጠኞች ተግተው መስራት አለባቸው።ይሄውም ችግሮችን ነቅሶ ከመፍትሔ መፈለግ ጋር ለሕዝብ ማድረስ ይገባል።ህዝብም አንደህዝብ በጋራ በውስጡ ልከፋፍሉት የሚሞክሩትን የሚመለሰውን በፍቅር አና በማስተማር፣የማይመለሰውን ደግሞ በሕግ በማረቅ ስራዎች መስራት ያስፈልጋል።ለእዚህም የተለያዩ ማኅበራዊ አደረጃጀቶች፣የህዝብ ንቅናቄዎች እና ግለሰብ ምሑራን ከላይ የተጠቀሱትን አምስት ጉዳዮች ላይ በጋራ መግባባት አና ግንዛቤ አንድኖር ቢሰራ ብዙ ነገሮች ይቀላሉ።ኢትዮጵያም በሚፈለገው መልክ ከምትፈልገው ደረጃ ለመድረስ አጅግ የተቃና ጎዳና ይሆንላታል።
Friday, December 16, 2022
ብልጽግና የኢትዮጵያ የነገ ተስፋ የሆኑ ልጆቿን የሚከፋፍል አጀንዳ በአዲስ አበባ እያራመደ ነው።አስገራሚው ነገር የፓርቲው የሌሎች ክልል አባላት ይህንን ሃገር በታኝ አጀንዳውን ለማስቆም ምንም ጥረት ሲያደርጉ አለመታየታቸው ነው።
- ድርጊቱ ምንም ዓይነት የጎሳ ፖለቲካ ቅብ ለመቀባት ቢሞከር የድርጊቱ ዋና ግብ የኢትዮጵያን መጪ ትውልድ መከፋፈል እና ኢትዮጵያን ማዳከምን መድረሻው ያደረገ የመርዝ ብልቃጥ ነው።
- በምድር ላይ ያለ ማንም መንግስት የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማውን የሚገዳደር የአንድ ክልል ሰንደቅ ዓላማ እና መዝሙር ተማሪዎቹ እየዘመሩ እርስበርሳቸው እንዲከፋፈሉ ሲያደርግ ተሰምቶ አያውቅም።
በመጀመርያ ከከንቲባ አዳነች ጀምሮ ምክትል ከንቲባው አቶ ዣንጥራር እና የአዲስ አበባ ክልል አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ ከንቲባዋ ሕዝብ ሲያወያዩ የተናገሩት አቶ ዣንጥራር በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ታኅሳስ 6/2015 ዓም የተናገሩት እና ታኅሳስ 7/2015 ዓም አቶ ሳምሶን መለሰ ደግሞ በፋና ቴሌቭዥን ቀርበው ሲናገሩ ጉዳዩን የአዲስ አበባ ህዝብ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ኦሮምኛ የሆኑ ኢትዮጵያውያን በቋንቋቸው እንዳይማሩ ከመፈለጉ አስመስሎ ለማቅረብ ብዙ ሲጋጋጡ ማየት እራሱን የቻለ ድራማ ነው። ይህ በራሱ የተቀመጡበትን የሕዝብ ወንበር ክብር አለመስጠት ነው። አቶ ሳምሶን ፋና ቴሌቭዥን ላይ ጋዜጠኛ ዳዊት መስፍን ደጋግሞ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ላይ አይደለም ጥያቄው እያለው መልሶ ወ/ሮ አዳነች እና አቶ ዣንጥራር ሲሉት የነበረውን ስለአፍ መፍቻ ቋንቋ ለማስረዳት በመሞከር ዋናውን ጥያቄ ለማለፍ የሞከረው ሙከራ አስቂኝ ነበር።ጋዜጠኛ ዳዊት ግን አልለቀቀውም ደጋግሞ ወደ ዋናዋ ጥያቄ ''በአዲስ አበባ የኦሮምያ ዓርማ እና የክልል መዝሙር ከብሔራዊ መዝሙር ጋር እንዲዘመር የሚያዝ የሕግ አግባብ አለ ወይ?'' በማለት ጠየቀ።
Wednesday, December 14, 2022
ከኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን አዋልድ መጻሕፍት ውስጥ ተአምረ ማርያምን የሚያንቋሽሽ ንግግርን ጨምሮ ቤተክርስቲያኒቱ የማታመልከውን ታመልካለች እያሉ በአደባባይ ቤተክርስቲያኒቱን የዘለፉ ሁሉ በሕግ የሚጠየቁበት አግባብ መኖሩን ከፍተኛ የሕግ ባለሙያዎች ማብራርያ ሰጥተዋል።(ሙሉ ቪድዮውን ይመልከቱ)
Monday, December 12, 2022
ህወሓት ቀርጾ የሰጠውን የኦሮምያ ክልል ዓርማ እና ደርሶ የሰጠውን መዝሙር ከልሉ ውጭ በአዲስ አበባም ካልዘመርኩ ማለት የጽንፈኝነት የመጨረሻው ጥግ ነው።የአዲስ አበባ ህዝብ ኢትዮጵያውያን በፈቃዳቸው ኦሮምኛ አይማሩ አላለም።ይህንን በሃሰት የሚያራግቡ አመራሮች ቆም ብለው ማሰብ አለባቸው።
- አዲስ አበባ ከኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ጎን የአፍሪካ ሕብረት ሰንደቅ ዓላማ ብትሰቅል ይመጥናታል።
- አሁን በአዲስ አበባ የኦሮምያ ሰንደቅ ዓላማ እና የክልሉን መዝሙር በተመለከተ ያሉት አራት እውነታዎች
- የኦሮምያ ክልል ህዝብ በጊዜ መንቃት አለበት።
- መንግስት ማድረግ የሚገባው
- በእዚህ ጊዜ አጀንዳው የተነሳበት ምክንያት በኦሮምያት ክልል ውስጥ በጽንፈኛው የኦነግ ሸኔ የቀረውን የክልሉን የኦሮምኛ ተናጋሪ አንዱን የኦህዴድ ሌላውን የሸዋ ኦሮሞ እያለ እየከፋፈለ ስለሆነ በእዚህ ሳብያ በተነሳው የክልሉ የውስጥ ውጥረት እንደ ማብረጃ ተደርጎ ተወስዷል።
- በእዚሁ የመከፋፈል አጀንዳ ላይ የጋራ የክልሉ አጀንዳ በመፍጠር የውስጥ አንድነት ያመጣል በሚል ይህ የባንዲራ ጉዳይ ተፈልጓል።
- በኦሮምያ ክልል እና በአዲስ አበባ አስተዳደር ውስጥ እና በአዲስ አበባ ዙርያ ጋር በተቀናጀ የተፈጸሙ ዘግናኝ የሙስና ዘራፊዎች በሰሞኑ የመንግስት እንቅስቃሴ ሊመቱ እንደሆነ ስላወቁ ይህንን የባንዲራ አጀንዳ ማንሳት እና ክልሉ እንዳይረጋጋ እና ቀጥሎም መንግስትን ማዋከብ ተፈልጓል።
- በእዚህ ሁሉ እንቅስቃሴ ላይ ከውስጥ ሆነው በአዲስ አበባ አስተዳደር ውስጥ በክፍተኛ አመራር ላይ ያሉ ከጽንፈኞቹ ጋር የሚሰሩ አሉ።እነኝህ ከሁሉም ገለልተኛ መስለው ሁሉንም እየወቀሱ ግን የጽንፍ ኃይሉን የሚደግፉት አጀንዳውን በይበልጥ ከመንግስት ወገን ሆነው በማራገብ ነው።
- አሁን በትምሕርትቤቶች ውስጥ ህጻናቱን ኦሮሞ የሆነ እና ያልሆነ የሚል ክፍፍል ለመፍጣር በንጹሃን አዕምሮ ላይ ወንጀል መስራት ተጀምሯል።ይህንን የኦሮሞ ህዝብ በስሙ የሚደረገውን ንግድ ሊቃወመው ይገባል።
- የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የጸናችው በእነ ጀነራል ጃጋማ ኬሎ፣ ኮሎኔል አብዲሳ አጋ እና በሌሎች ሚልዮኖች የኦሮሞ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ነው።ዛሬ ከህወሃት የተሰጣቸውን ዓርማ እና መዝሙር ይዘው አዲስ አበባ ላይ ህዝብ ለመከፋፈል የሚነሱ የጽንፍ ኃይሎችን መቃወም ከኦሮምኛ ተናጋሪው ኢትዮጵያዊ ይጠበቃል።
- ፌድራል መንግስት ላይ ተቀምጠው እንደኦሮምያ ክልል አስተዳደር ኢትዮጵያን ለማስተዳደር የሚሞክሩትን በጊዜ አደብ ማስገዛት አለበት።እነኝህ ናቸው የአዲስ አበባ ህዝብ ጥላቻ ስላለበት ነው የሚል የተሳሳቱ ቃላትን በመግለጫዎቻቸው ላይ እየሰነቀሩ ጉዳዩን ሌላ ቅርጽ እንዲይዝ የሚያደርጉት። የአዲስ አበባ ህዝብም ሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ ኢትዮጵያዊ የሆነ የማንም ክልል ቋንቋ ማንም በፍላጎቱ አይማር የሚል ቅሬታ የለውም።
- አዲስ አበባ በተለየ መልኩ የሁሉም ክልል መኖርያ መሆኗን የኦሮምያ ክልል የጽንፍ ኃይሎች እንዲያውቁ ለመጨረሻ ጊዜ ማሳወቅ ብቻ ሳይሆን ህገመንግስቱ በሚያዘው መሰረት አዲስ አበባን መብቷን ሊያከብርላት ይገባል።አዲስ አበባ ከኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ጎን የአፍሪካ ሕብረት ሰንደቅ ዓላማ ብትሰቅል ይመጥናታል።
- በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች በአዲስ አበባም የሰንደቅ ዓላማ አሰቃቀል ሥነ ስርዓት በተለይ በትምህርት ቤቶች በሚገባ እንዲተገበር ልዩ የቁጥጥር ሥርዓት ማውጣት አለበት። ዛሬ በአዲስ አበባ ከእዚህ በፊት የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ይሰቅሉ የነበሩ ሁሉ ከጭቅጭቅ በሚል ያልሰቀሉ መኖራቸው ተሰምቷል። ይህ የመንግስት የመኖር እና አለመኖር መገለጫ አንዱ ማሳያ ነው። በሃገሪቱ ዋና ከተማ የሃገሩ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማን በአግባቡ ማሰቀል ያልቻለ መንግስት ማለት ትርጉሙ ብዙ ነው።
Thursday, December 8, 2022
ክቡር ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ ትናንት በጽሑፍ ዛሬ ደግሞ በቀጥታ ንግግር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያስተላለፉት መልዕክት ፍጹም ኢትዮጵያዊ እና ታሪካዊ መልዕክት የያዘ ነው።በአጽንኦት ማዳመጥ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ፋንታ ነው።
- ከሃሰተኛ ዩቱበር ተንታኞች እራስን ለመጠበቅ ከምንጩ አድምጦ በተሰጠን አዕምሮ ተጠቅመን ማገናዘብ፣ ጤናማ አስተሳሰብ ነው።
- የዛሬውን የንግግራቸው እና የትናንቱን የጽሑፍ መልዕክት፣ ሁለቱንም በቪድዮ እና ኦድዮ ከስር ያገኛሉ።
Tuesday, December 6, 2022
ኢትዮጵያ የጎሳ ፖለቲካን መርዝነት የተረዳ መሪ አላት ወይ? እንደርሱ ችግሩን የተረዱ የመንግስት ባለስልጣናትስ አሉ ወይ? መልሱ አዎን! ነው። መሪዎቿ ከሁሉ በፊት የሰው ህይወት ለመታደግ መንቀሳቀስ አልነበረባቸውም ወይ? አሁንም መልሱ አዎን! ነበረባቸው ነው።ኢትዮጵያውያን! ወቅታዊውን ችግር በቅንጥብጣቢ ጊዜያዊ መፍትሔ አንፈታውም።
ለውስጣዊ የጸጥታ ችግሮቻችን መፍትሔነት ሦስቱ መፈታት ያለባቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች።
ከእዚህ በተለየ ግን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከኦነግ ጋር አንድ አድርገው የሚያዩ ሰዎች ሁሌ የሚረሱት ጉዳይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢህአዴግ ስር ሆነው ከኦነግ ጋር የነበረውን የአይጥና ድመት መሳደድ፣በኋላም ይሄው ቡድን በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ከናይሮቢ ድረስ ሰው ልኮ ግድያ መሞከሩን እና ወለጋ ላይም የጠቅላይ ሚኒስትሩን ህይወት ለመቅጠፍ ተደጋጋሚ ሙከራ ማድረጉን ይረሱታል።ምክንያታዊ ዕሳቤዎች መልካም ናቸው።አሁን በወለጋ ባለው በሰሞኑ ጉዳይ በኦነግ ሸኔ በኩል በዋናነት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፋኖን እንዳዘመቱ ነው ቅስቀሳ የተያዘው።ሌላው ቀርቶ የጨፌ ኦሮምያ ምክርቤት አባላት ሳይቀሩ በትናንትናው ዕለት በመንግስት ላይ እየዘመቱ የሸኔን ቀጥተኛ አቋም ያንጸባረቁ ለእዚህ ሁሉ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩን የኦሮሞ ጠላት አድርገው ነው ያቀርቧቸው።
=================
በኢትዮጵያ የእገታ ወንጀል ተሳታፊ አራት አካላት ናቸው። ለችግሩ የመፍትሄ አካላት ሁለት ናቸው።ሁለቱ አካላት ምን ይስሩ?
======= ጉዳያችን ======= በኢትዮጵያ ዜጎችን እያገቱ ገንዘብ የሚቀበሉ ወንጀለኞች ከተራ ወንጀለኝነት አልፎ በታጣቂ ቡድኖች የገንዘብ ማግኛነት መዋል ብቻ ሳይሆን ዜጎችን የማሸበርያ ፋሺሽታዊ ተግባር ሆኗል። እገታ የ...
-
የቅዱስ ላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ጉዳያችን/ Gudayachn ሰኔ 2/2011 ዓም (ሰኔ 8/2019 ዓም) ግንቦት 29/2011 ዓም ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል በለቀቀው ዜና እንዲህ ይነበባል: - ...
-
Foto source:- Royal Norwegian Embassy in Addis Ababa, Ethiopia http://www.norway.org.et/News_and_events/press_releases/New-Norwegia...
-
በ ካርታ ጫወጣ ጎበዝ አደለሁም። ግን ጆከር የተባለች ካርታ መኖሯን አውቃለሁ።ጆከር ካርታ በ ሁሉም ቦታ ስለምትገባ በ ካርታ ጫወታ ጆከር የደረሰው ሰው የማሸነፍ እድል ስላለው ፊቱ በ ፈገግታ ይሞላል። የ አትዮጵ...