ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, July 28, 2016

ሰልፍ ከወጣህ መድረሻ ግብ ይዘህ ውጣ! ህወሓት የህዝብን የተነሳሳ የአንድነት ስሜት በሰልፍ ማቀዝቀዝ ለምዷልና።በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ሕዝብ በህወሓት የ25 ዓመታት አድሏዊ፣ጎጥ ላይ የተመሰረተ እና ኢትዮጵያን የሚከፋፍል አመራር ለመላቀቅ ሰዓታት እረዝመውበታል።በርካታ የማታለል ተግባራት የተፈፀመበት ሕዝብ እየመሩት ያሉት መሪዎች በመጀመርያ ደረጃ ጎጠኞች መሆናቸውን ተረድቷል፣ በመቀጠል ለኢትዮጵያ አንዳች የዜግነት ስሜት የማይታይባቸው ይልቁንም ከባዕዳን እኩል ለኢትዮጵያ ስጋት እንደሆኑ እና ለግል ብልፅግና ሌት ከቀን የሚደክሙ መሪዎች መሆናቸውን በሚገባ ተረድቷል።

ከመጪው እሁድ ጀምሮ  በጎንደር፣ባህርዳር፣ደሴ እና ሰሜን ሸዋ እንዲሁም በኦሮምያ ከተሞች ሰልፍ እንደሚደረጉ በማኅበራዊ ድረ-ገፆች እየተገለፀ ነው።በተለይ በጎንደር የሚደረገው ሰልፍ ከትናንት በስትያ አቶ በረከት እና የስርዓቱ ቁልፍ ሰዎች በተገኙበት የተደረገው ስብሰባ ካለ አንዳች ፍሬ የህዝቡን ቁጣ በጨመረ መልክ ከተጠናቀቀ በኃላ የጎንደር እና የአካባቢው ሕዝብ በመጪው እሁድ ሰልፉ ተፈቀደም አልተፈቀደም ሰልፉ እንደሚካሄድ ህዝቡ በቁጣ እየገለፀ ነው። በኦሮምያ ከተሞች ይህንን ሳምንት የመረረ ተቃውሞ ሲደረግ ነው የሰነበተው።

እዚህ ላይ መስመር ያለበት ጉዳይ ሰልፍ ማድረግ በራሱ ግብ አለመሆኑን ነው። ህወሓት የህዝብ ስሜት በከባዱ ሲነሳ አንዱ የማብረጃ መንገድ ያደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ነው። በሊብያ በአሸባሪው አይ ኤስ ኤስ በተገደሉት ወገኖቻችን ሳብያ የህወሓት ቸልተኝነት ያስቆጣው ሕዝብ በእራሱ ተነስቶ ሰልፍ ለማድረግ መቁረጡን ያወቀው ህወሓት የህዝብን ስሜት ያበረደው በሚቀጥለው ቀን ሰልፍ እንደሚደረግ በመፍቀድ ነበር። ሰው የቁጣው ስሜት ባየለበት ወቅት ስሜቱን በከፍተኛ ድምፅ ማውጣት ይፈልጋል።ይህ በእራሱ ችግር የለውም።ነገር ግን በአደባባይ በመውጣት በመጮህ እና ሰውነትን በላብ በመዝፈቅ ብቻ አምባገነኑ ስርዓት ይወገዳል ማለት አይደለም። ደግሞስ ያለውን ችግር አደባባይ መድገም ህወሓት ያላወቀውን እንዲያውቅ መረጃ ለመስጠት ነው? ህወሓት ማለት እኮ በሕዝብ እንባ ላይ እየተራመደ የሕፃናት እና የእርጉዞችን ሰቆቃ በጥይት ዝም እያስባለ በእየአውራ ጎዳናው አስከሬን ያስቆጠረ ስርዓት በሰላማዊ ሰልፍ ከስህተት ይማራል ተብሎ አይታሰብም።ይህ ማለት የተቃውሞ ሰልፍ አያስፈልግም እያልኩ አይደለም። ሰልፍ መድረሻ ግብ ይዞ ይነሳ ማለት ነው የፈልኩት።

በመጪው ዕሁድ የሚደረገው ሰልፍ በአደባባይ በመጮህ ስሜትን በመግለፅ ብቻ እርካታ አግኝቶ ወደ ቤት የሚገባበት ሳይሆን ነፃነት የሚታወጅበት ቀን መሆን አለበት።  ህወሓት በሰላማዊ የህዝብ ድምፅ የአገር ችግር እንደማይፈታ ባለፉት አመታት የታየ እውነታ ነው። ህወሓት በገዛበት የጭካኔ አገዛዝ ዘመኑ ሁሉ የደነገጠባቸው እና የስልጣን መንበሩን ያነቃነቁ የህዝብ እንቅስቃሴዎች የታዩት በኦሮምያ እና በጎንደር የተደረጉት ናቸው። ሁለቱም እንቅስቃሴዎች የሕወሀትን አምባገነናዊ እና ጎጥን  መሰረት ያደረጉ የአስተዳደር መዋቅሮቹ ተናግተዋል።ሁለቱም እንቅስቃሴዎች በአሁኑ ሰዓትም ያልተቆጣጠራቸው ከመሆናቸውም በላይ በመጪው ጊዜ ለማፈን ሌላ ስልት እያሰላሰለባቸው እንደሆነ ከእራሱ የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።

ስለሆነም በመጪው እሁድ የሚደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ምን መምሰል አለባቸው?

1/  ሕዝብ በአደባባይ የህወሃትን ስርዓት ለመጣል ቃል የሚገባበት  መሆን አለበት
የሃይማኖት አባቶች፣ሽማግሌዎች እና ታዋቂ ግለሰቦች በሰልፉ ላይ  የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰቆቃ መቆም እንዳለበት፣በዘር እና በጎሳ መከፋፈል የህወሓት መርዘኛ ፖለቲካ ኢትዮጵያን እንደ አገር የማያስቀጥል መሆኑን ማስረዳት እና ከህወሓት ጋር የሚተባበር ሁሉ የተወገዘ እንዲሆን የሚያውጁበት መሆን አለበት።

2/ ተቃውሞው የትግራይን ሕዝብ ኢላማ ያደርገ ሳይሆን ህወሓትን እና የጥቅም ተካፋዮችን ብቻ እና ብቻ ያለመ መሆኑን ማሳየት አለበት


ህወሓት 25 ዓመታት ሙሉ ላፈሰሰው ደም የትግራይ ሕዝብ እንደ ሕዝብ እንዲጠየቅ ለማድረግ እና በትግራይ ሕዝብ ላይ ተንጠላጥሎ ከቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በማጋጨት እና በማስበርገግ የስልጣን እድሜውን ማራዘም ይፈልጋል።ይህንን በተለይ ከ1997ዓም ምርጫ ጀምሮ አጠንክሮ ሲሰራበት የነበረ እና በሚቆጣጠራቸው የመገናኛ ብዙሃን በርካታ መርዛማ ፕሮግራሞችን ሲያስተላልፍ እንደነበር ሕዝብ ምስክር ነው።በእዚህም ሳብያ አንዳንድ የዋህ የትግርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ይህንኑ ሲያስተጋቡ ይታያሉ። የእዚህ አይነቱ ሰልፍ ላይ ህወሓት ሕዝብ ከህዝብ ለማጋጨት የሚሞክርባቸውን መንገዶች ሁሉ ቀድሞ ማክሸፍ ያስፈልጋል።ለምሳሌ ከሰልፉ አላማ ውጭ የሆኑ የትግራይ ህዝብን የሚያጥላሉ መፈክሮች የሚያሰሙ ካድሬዎች በሕዝቡ ውስጥ ከማሰማራት ጀምሮ የእርስ በርስ ግጭት እንዲነሳ እና  አንዱ ሕዝብ በሌላው ላይ መሳርያ የመዘዘ አስመስሎ ሊያቀርብ ይችላል።ስለሆነም ሰልፎቹ እነኝህን እና የመሳሰሉትን የህወሓት ተንኮሎች የሚያከሽፉ መሆን አለባቸው።


3/ የኢትዮጵያን ጦር ኃይል እና ፖሊስ ሰራዊት የህወሓት የጎጥ ፖለቲካ አስፈፃሚ መሆኑን እንዲያቆም የሚያስጠነቅቅ መሆን አለበት


በኢትዮጵያ ዘመናዊ የጦር ኃይል አደረጃጀት ታሪክ ባልታየ መልኩ ከአንድ አካባቢ የመጡ ሰዎች የጦር  ኃይሉ ከፍተኛ መኮንኖች የሆኑበት ጊዜ በህወሓት ዘመን ብቻ ነው።ይህ ማለት ግን ተራው ወታደር በሙሉ እንደ ከፈተኛ መኮንኖች በጎጥ ፅንፍ ብቻ የሚያስብ ነው ማለት አይደለም።እንደማንኛውም ኢትዮጵያውያዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ የሚያሳስበው የስርዓቱ  ጥቂት ቅምጥል ባለስልጣናት ዝርፍያ እና በትውልድ መንደራቸው የሚያስቡ ዘረኞች የስልጣን ጥማት ኢትዮጵያን ወደማትመለስበት  አደጋ እየመራት እንደሆነ ይረዳል።ይህ ሰልፍ ይህንን ሰራዊት ኃላፊነቱን እንዲወጣ የሚያሳስብ እና ይህንን ካላደረገ ግን ከህዝብ ፍርድ እንደማያመልጥ ግልፅ መልዕክት የሚያስተላልፍ መሆን አለበት።


ባጠቃላይ ከእንግዲህ ወዲህ በኢትዮጵያ የሚደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ከእዚህ በፊት ከሚደረጉት ሰልፎች የተለዩ እና የህወሓትን ባህሪ ከግንዛቤ መሆን አለባቸው።ሰልፍ ከወጣህ መድረሻ ግብ ይዘህ ውጣ! የህዝብን የተነሳሳ የአንድነት ስሜት ህወሓት በሰልፍ ማቀዝቀዝ ለምዷልና።

ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

ለእሩብ ክ/ዘመን ኢትዮጵያን ያመሰው የህወሓት ጎጥን መሰረት ያደረገ የፈድራል አስተዳደር መሬት ላይ ፈርሷል።ህወሓት እጅ ወረቀቱ ብቻ ቀርቷል።
መነሻ 

በ20ኛው ክ/ዘመን ውስጥ አለማችንንም እንዲሁም ኢትዮጵያን ያመሱት ሁለቱ ዋነኛ ርዕዮት ዓለሞች ውስጥ የካፒታሊስት እና የሶሻሊስት ርዕዮተ ዓለሞች ቀዳሚዎች ነበሩ። አውሮፓን መሻገር የጀመረው የኢንዱስትሪ አብዮት ካፒታሊዝምን፣ በአስራዘጠነኛው ክ/ዘመን መጨረሻ ላይ በጀርመን እና ፈረንሳይ እውቅና ያገኘውን እና በኃላም እኤአ 1917 ¨ሰራተኛው የተቆጣጠረው¨ የተባለው የቀድሞዋ የሶቪየት ሕብረት ¨የቦልሸቪክ¨ አብዮት እስከ እኤአ 1980ዎቹ መጨረሻ ድረስ መላው ዓለምን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተፅኖውን በማሳረፍ የብዙ አገሮችን ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ቅርፅ ለመቀየር ችሏል።

በኢትዮጵያም በ1933 ዓም ፋሽሽት ጣልያን ከኢትዮጵያ ከተባረረች በኃላ ኢትዮጵያ በቀጥታ የገባችው ለአመታት ከኢንዱስትሪው አብዮት ተለይታ እንደመኖሯ ለዘመናዊ ትምህርት፣ለኃይል ማመንጫ እና ለመንገድ ስራዎች ነበር።በ1950ዎቹ እና 60ዎቹ ወደ ባህር ማዶ ለትምህርት የሄዱ ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ከሰለጠኑት አገሮች የእድገት ደረጃ ጋር ሲያነፃፅሩ የኢትዮጵያ ሁኔታ ማነሱ ብቻ ሳይሆን የለውጥ አስፈላጊነቱ አንገብጋቢው የወቅቱ ጥያቄ ሆነ።ስለሆነም የባእዳኑ የርዕዮተ ዓለም ፍትግያ ኢትዮጵያን ለማሳደግ በሚል ብርቱ ምኞት ታጅቦ ወደ አገራችን ገባ። ወደ ኢትዮጵያ የመጣው የሶሻሊስት አስተሳሰብ በበቂ ሁኔታ ውይይት ተደርጎበት ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ሳይፈተሽ እና ሳይቃኝ በወቅቱ የውጭ አገራት መፃህፍትን ማንበባቸው እና ዘመናዊ ትምህርት መቅሰማቸው ብቻ ታሳቢ እየተደረገ በወጣቱ ኢትዮጵያዊ ዙርያ አገሪቱን ከ1933 ዓም ጀምሮ ሲመራ የነበረውን የዘውድ ስርዓት ማስወገድ የሚል  ብቸኛ ዓላማ እንዳነገበ  የጠራ የርዕዮተ ዓለም መንገድ ሳይኖረው ግብታዊው አብዮት የካቲት፣1966 ዓም ፈነዳ። 

በ1966 ዓም የፈነዳው አብዮት ከአገር ውጭ እና በአገር ውስጥ የነበረው ነባራዊ ሁኔታ እና ሂደት በሚገባ መጠናት ያለበት እና በለውጡ ሂደት ላይ የንጉሡ እና የቤተሰቡ ትክክለኛ ሃሳብ ሁሉ ወደፊት ታሪክ በባለሙያዎቹ በሚገባ ሲፈተሽ የምንረዳው ይሆናል።ንጉሡ ቀደም ብለው አራተኛ ክ/ጦር መኮንኖች ተሰብስበው እየዶለቱ መሆናቸውን እያውቁ ¨ተዉ አትንኩ እኛው ያሳደግናቸው ናቸው¨ ያሉበት ሁኔታ እና አልጋ ወራሽ አስፋ ወሰን ንጉሡ ስልጣናቸው እንዲገደብ እና አገሪቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ትተዳደር የሚል ሃሳብ አቅርበው ነበር የሚሉት በበቂ ማስረጃ መረጋገጥ ያለባቸው ታሪኮች ሁሉ ወደፊት ለትውልዱ መተላለፍ ያለበት የታሪክ ባለሙያዎች የቤት ስራዎች ናቸው።

የደርግ ፈድራሊዝም ?


ሰኔ 21፣1966 ዓም ጊዜያዊ ወታደራዊ ደርግ በሚል ስያሜ ስልጣን የያዘው አካል ለ17 አመታት ያህል ኢትዮጵያን አስተዳደረ።ይህ ስርዓት መሰረታዊ የፖለቲካ እና ምጣኔ ሀብት ለውጥ በኢትዮጵያ ላይ ከማምጣቱም በላይ በስልጣን አስተዳደር አዳዲስ አሰራሮችን በወረቀት ደረጃም ቢሆን ማምጣቱ አልቀረም።የገጠር መሬት ይዞታ ወደ ገበሬው የሚያዞረው የየካቲት 25፣1967 ዓም አዋጅ እና የሐምሌ 19፣1967 ዓም ትርፍ የከተማ ቤቶች ይዞታን የሕዝብ የሚያደርገው አዋጅ ከመሰረታዊ ለውጦች ውስጥ ተጠቃሾች ናቸው። 

ደርግ በብሄር ብሔረሰቦች ጉዳይ ከህወሓት የሚለየው ህወሓት በየዓመቱ በብሄር በሄረሰብ ስም ጭፈራ እና ድግስ ሲያሳምር፣ደርግ ግን የብሔር  ብሔረሰቦች ኢንስቲትዩት መስርቶ በኢትዮጵያ ያሉትን ብሔር ብሔረሰቦች ታሪክ፣ባህል እና ትስስር ያጠና ነበር።ይህ ብቻ አይደለም በኢትዮጵያ መኖራቸው በመሃል አገር ሕዝብ በብዛት የማይታወቁ በዳር አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ታሪክ፣ባህል እና ውርስ የሚያሳይ በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ የሆነ በጋዜጠኛ ብዙ ወንድም አገኘሁ የሚዘጋጅ እና በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ዘወትር ሐሙስ የሚተላለፍ ¨ ተጉአዥ ካሜራችን¨ የተሰኘ ፕሮግራም ያስተላልፍ ነበር።በአስተዳደር በኩልም ለኢትዮጵያ እንግዳ ከሆነው ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ለውጥ ባሻገር ደርግ ያመጣው አዲስ ነገር ¨የእራስ ገዝ¨ የሚል የአስተዳደር ዘይቤ ነበር። የእራስ ገዝ የተሰጣቸው የአስተዳደር ቦታዎች ከሚጠቀልላቸው ውስጥ ድሬዳዋ፣ጋምቤላ፣አሰብ እና ኤርትራ የሚጨምር ሲሆን በእነኝህ ቦታዎች ያሉት የተለዩ መብቶች ከጠቅላላው የደርግ መንግስት አስተዳደር ግዛቶች አንፃር የተለየ አይነተኛ እና እውነተኛ መብቶች ማግኘት ቢያስቸግርም በመርህ ደረጃ ግን የተቀመጡ መብቶች ነበሩ።ጃምሮው ግን የደርግ ፈድራሊዝም ጅማሮ ብለን ልናልፈው እንችላለን።

የህወሓት ጎጥን መሰረት ያደረገው ፌድራሊዝም ሞት 


ህወሓት በ1967 ዓም አፉን ያሟሸው ስለ ጎሳ ፖለቲካ በማውራት ነው።እዚህ ላይ ስለ ብሔር ብሔርሰብ መናገር እና ስለ ጎሳ ማውራት ይለያያል።ህወሓት ቋንቋን መሰረት ያደረገው ማንፈስቶው በ1967ዓም ሲያወጣ ወዳጅ እና የምታገልለት ያለው የትግርኛ ተናጋሪውን ኢትዮጵያዊ ሲሆን ¨ጠላት¨ብሎ የሚፈይደው ደግሞ በዋናነት የአማርኛ ተናጋረውን የአማራ አማርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን ነው።
ህዳር 29፣1987 በህወሓት አጠራር  ታሪካዊ፣በአብዛኛው ኢትዮጵያዊ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ መከፋፈል ቀን ተብሎ የሚታወቀው እና በአንቀፅ 29 ላይ ከተጠቀሰው የመገንጠል መብት ጨምሮ ኢትዮጵያን በቋንቋ  የሚከፋፍል የፈድራል አስተዳደር መታወጁ ኢትዮጵያ ቀደም ብላ የማታውቀው እንግዳ የሆነ አስተዳደር በህወሓት ተጣለባት። ይህ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ የሚኖረው አሉታዊ ተፅኖ አደገኛ መሆኑ ቢታወቅም አሜሪካንን ጨምሮ ሌሎች ተፅኖ ፈጣሪ መንግሥታት ከዳር ቆመው ከማየት ባለፈ ኢትዮጵያ በጎሳ ፖለቲካ ውስጥ ማለፍ ትልቅ ተሞክሮ እያሉ መመፃደቅ ጀመሩ።አንዳንድ ዓለም አቀፍ እና የአገር ውስጥ ምሁራን ግን ጎሳን መሰረት ያደረገው አስተዳደር ውሎ አድሮ ለኢትዮጵያ ትልቅ አደጋ እንደሚያስከትል እና እራሱ ህወሓትን ይዞት የሚሄድ ጎርፍ እንደሚሆን የትነበዩም ነበሩ። ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ ከውጭ የተጫነ አስተሳሰብ የሚያስከትለውን አደጋ እንደሚከተለው ይገልፀዋል።

¨ከአገዛዞች መቀየር በኋላ በየአገሮች በእነ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት አቀነባባሪነት የሚወጡትና ተግባራዊ የሚሆኑት ፖሊሲዎች በሙሉ የቴክኖክራቶች ጫወታዎች እንጂ በምድር ላይ የሚታየውን የህዝቦችን ችግር መፍታት እንዳልቻሉ ነው የምናየው። በታሪክ ውስጥም ቴክኖክራሲያዊ የኢኮኖሚ ሞዴል የአንድን አገር ህዝብ ችግር የፈታበት ቦታና ጊዜ የለም። ቴክኖክራቶች ስለቁጥር እንጂ ስለ ሰው ልጅና ስለስልጣኔ ብዙም ስለማይገባቸው ተግባራዊ የሚያደርጉት ፖሊሲ በሙሉ ችግሩን ውስብስብ ያደርገዋል እንጂ በፍጹም ሊፈታው አይችልም። በተጨማሪም የአገራችን የተወሳሰበ ችግር በአንድ ትልቅ ፕሮጀክትና ወይም ደግሞ እዚህና እዚያ በሚተከሉ ትናንሽ ፕሮጀክቶች ሊፈታ እንደማይችል መገንዘብ ያስፈልጋል። ኢኮኖሚያዊ ክንውን ከህብረ-ብሄር ግንባታ ጋር እስካልተያያዘ ድረስ ትርጉም ሊኖረው በፍጽም አይችልም። ስለሆነም ሰፊውን ህዝብ ያስቀደመና ለሁሉም የሚያመች ቆንጆ አገር ለመገንባት ከዚህ ከተክኖክራሲያዊ ሞዴል ባሻገር ማየትና ማለም ያስፈልጋል። በዚህ መልክ ብቻ ወደ ተፈለገው ዕውነተኛው ነፃነት ማምራት ይቻላል። የተከበረችና የምትፈራ አገርም  መገንባት ይቻላል.....አምባገነንነትን እቃወማለሁ፣ ነፃነትን አመጣለሁ ለሱም ጠበቃ የቆምኩ ነኝ የሚል ኃይል ሁሉ ዛሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተስፋፋው የተዛባ ስርዓትና ለብዙ ህዝቦችም ነጻነት ጠንቅ በሆነበት ሁኔታ ውስጥ እንዴት ዕውነተኛ ነፃነት ሊመጣ እንደሚችልና ተግባራዊም እንደሚሆን ማስረዳት ያስፈልጋል¨ ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ፣ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ፣ ጥር 14፣2014።

ከላይ የተጠቀሰው የዶ/ር ፈቃዱ በቀለ ፅሁፍ ላለፉት 40 አመታት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ያለፈበትን ውጣ ውረድ የሚያመለክት ነው። ቀደም ብሎ በሶሻሊዝም ስም ቀጥሎ በዓለም ባንክ አይዞህ ባይነት የጎሳ ፖለቲካ የተፈራረቀባት ኢትዮጵያ የእራሷን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ አስተዳደር ሲፈራረቅባት ይሄው አሁን ላለንበት የህውሃት የጥፋት ድግስ ደረጃ አድርሶናል።ህወሓት ይህንን ያደረገው ሕዝቡን ከፋፍሎ ለመግዛት ካለው እቅድ መሆኑ የታወቀ ነው።ዶ/ር ወንድወሰን ተሾመ በቪየና ዩኒቨርሲቲ የአንትሮፓሎጂ ትምህርት ክፍል ተመራማሪ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2008 ዓም በዓለም አቀፉ ሰብአዊ ሳይንስ የምርምር መፅሄት ላይ የኢትዮጵያን የኢህአዴግ/ህወሃት የጎሳ ፖለቲካ በሚገልፅ ያወጡት የጥናት ፅሁፍ ገፅ 11 ላይ እንዲህ የሚል ይገኝበታል።
” የጎሳ ፈድራሊዝም የህወሃት ‘ከፋፍለህ ግዛ’ ፖሊሲ ሲሆን የተዋቀረበት ዋናው ምክንያትም ስርዓቱ የራሱን ስልጣን ለማስጠበቅ ነው።ሁኔታው ግን አገሪቱን እንዳትከፋፈል ያሰጋል” ያላል። (ጉዳያችን፣ጥር፣2015)።
”…ethnic federalism is the ”divide and rule” policy of the TPLF designed to strength its own position and it might lead the country in to disintegration” International Journal of Human Sciences (2008, 11p). 
ህወሓት ህዳር 29፣1987 ዓም የጎሳ ፈድራሊዝም ሲታወጅ (ቀድሞ የታወጀ ቢሆንም ለይስሙላ ቢደረግም ) አንድ ምንነቱን በአግባቡ ያልተረዱ ተሳታፊ ጋቢያቸውን መሬት ሲጥሉ እና ሲዘሉ ያሳይ እንጂ በወቅቱ አደጋው የታያቸው ሁሉ ይህ ጋቢ ጥሎ መዝለል ነገ ሕዝብ ከህዝብ አጋጭቶ ኢትዮጵያን አደጋ ላይ እንዳይጥል ስጋት ያደረባቸው ብዙ ኢትዮጵያውያን ነበሩ።የተፈራው አልቀረም ላለፉት 24 አመታት ኢትዮጵያ ውስጥ አንዱ ጎሳ ከሌላው መጋጨት እና መጋደል የተለመደ የኢትዮጵያ ዜና መሆን ጀመረ።በኢትዮጵያ የህወሓት የጎሳ ፈድራሊዝም በፈጠረው አለመረጋጋት እና የህዝብ መፈናቀል ሳብያ የተሰደደው፣የሞተው እና ንብረቱን ያጣው ኢትዮጵያ ቁጥር እጅግ ከፍተኛ ነው።ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ህወሓት የሌላውን ሕዝብ የእርስ በርስ ግጭት በስርዓቱ ሳብያ ይፈጠር እንጂ አደጋው ለስልጣኑ የሚያሰጋው አልመሰለውም ነበር። ይልቁንም ህወሓት ሕዝብ ሲጋጭ እርሱ አስታራቂ እየሆነ የመኖር ሕልም እንጂ እሳቱ ዞሮ የስልጣን ምህዋሩን ያናጋዋል ብሎ አስቦ አያውቅም።የሆነው ግን ቀድሞ የተፈራው እና የተተነበየው ሆነ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ህወሓት የጎሳ ፖለቲካውን እያወደሰ ነፍጠኛ ያለውን እየገፋ የሚኖር አድርጎ ቢያስብም ሕዝብ ግን የጎሳ ፖለቲካውን በአራሱ እያፈረሰ ህወሃትን በመቃወም በተፃራሪ መንገድ ቆመ።ህወሀትም ሲመፃደቅበት የነበረው ጎሳን መሰረት ያደረው ፈድራሊዝም በያዝነው ዓመት በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍል የህወሃትን የጎሳ ፖለቲካ በእራሱ ማፍረስ ጀምሯል።እስካሁን የኦሮምያ፣የአማራ፣የጋምቤላ እና የሱማሌ ክልል ጎሳን መሰረት ያደረገ ፈድራሊዝም ሙሉ በሙሉ በመሬት ላይ የፈረሰ ሲሆን ህወሓት እነኝህን ቦታዎች በወታደር ኃይል ለመምራት እየሞከረ ሲሆን  ይህ አካሄድ ስርዓቱን ወደ ፍፁም ፋሽሽታዊ ስርዓትነት ለመቀየሩ ብዙዎች ይስማማሉ።በእዚህ ዓመት ብቻ ህወሓት የጎሳ ፖለቲካን ለማስፈን  ከአንድ ሺህ በላይ ኢትዮጵያንን በጥይት መግደሉ ምን ያህል ለስልጣኑ እንደሚንገበግብ እና የጎሳ ፈድራሊዝም የሚለው የስልጣን ማቆያ መሳርያ ብቻ መሆኑን  ያመላከተ ክስተት ሆኗል።
ዛሬ ላይ የህወሓት የጎሳ ፖለቲካ ኢትዮጵያን ለ25 ዓመታት ያመሰው የጎሳ ፖለቲካ መሬት ላይ ሙሉ በሙሉ ፈርሷል።የቀረው የህወሓት የእጅ ቦርሳ ላይ የሚገኝ ወረቀት እና በሚቆጣጠረው የቴሌቭዥን ጣቢያ ላይ ብቻ ቀርቷል።ህወሓት ይህንን ሊክድ ይሞክራል።እውነታውን ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ እየተመከተ ነው።አሁን ያለንበት ጊዜ የህወሓት አገር አጥፊ የጎጥ ፖለቲካን ሕዝብ አልቀበልም ብሎ ተአስቶ ያፈረሰበት ጊዜ ነው።አሁን ኦህዴድ ቢሮ የለም፣ዛሬ ብአዴን አብዛኛው አባሉ ከህዝብ ጎን ቆሟል።ጋምቤላ በህውሃት ወታደሮች በደረሰው እልቂት የአንድ ቡድን ተገዢ መሆን በቃኝ ብሏል። ለእሩብ ክ/ዘመን ኢትዮጵያን ያመሰው የህወሓት ጎጥን መሰረት ያደረገ ፌድሬሽን መሬት ላይ ፈርሷል።ህወሓት እጅ ወረቀቱ ብቻ ቀርቷል።

ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

Saturday, July 23, 2016

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ እና ጄኔራል ኃይሌ መለስ የጎንደርን እንቅስቃሴ አስመልክተው ያወጡት መግለጫ

ጄኔራል ኃይሌ መለስ

ጄኔራል ኃይሌ መለስ የጎንደር  ሕዝብን  መግለጫ 

ምንጭ = ሳተናው  
የጎንደር ህዝብ ወንድሙን አሳልፎ የመስጠት ባህል የለውም። እኔ ከወረታ እስከ ባህርዳር በተደረገው ጦርነት በ1983ዓ.ም ሰባት ጊዜ ሰባት ቦታ ላይ ቆስዬ አዲስ አበባ ሄጀ ልታከም የሚል አጋጣሚ ሊኖረኝ ይችል ነበር፤ነበረኝም።ሂዶ መታከም እችል ነበር ያኔ ደርግ ጨርሶ አልፈረሰም ነበርና። ግን የነገሩን ማለቅ ስለተረዳሁት በቀጥታ በታንኳ ተሻግሬ ዘጌ አርፌ እንደገና ሌላ ታንኳ ይዤ እብናት ነው የገባሁት። እብናት ገብቼም ህዝቡ ትጥቁን እንዳይፈታ መጥቸልሃለሁ ትጥቅህን አትፍታ ነው ያልኩት ህዝቤን እና ብዙ ሽምቅ ተዋጊዎችን አደራጅቼ እየተዋጋሁ ለ5 ዓመታት ያክል ስዋጋ ቆይቻለሁ።
በዚያን ሰዓት በኔ በግል በደረሰብኝ ችግር፤ ቤተሰቦቼ ላይ በደረሰ ሰቆቃ፤ ወያኔ እኔን አሳልፈው እንዲሰጡ እንዲሁም አብረው በሚታገሉ ወገኖቸም ዘንድ የደረሰው ግፍ ይሄ ነው ተብሎ ሊገለፅ የሚችል አይደለም። ይሄ ሁሉ ችግር እያለብኝ ግን እጄን ለጠላቴ ለወያኔ አንስቼ ልሰጥ ፈፅሞ አልዳዳኝም። ወጣሁ ቆርጨው በአዲስ አበባ አቋርጨ ቀጥታ በኬንያ ነው የወጣሁት! ከኬኒያ እንደገና ሱዳን ገብቼ ነው ውጊያ የጀመርኩት። ያገሬ ህዝብ ጎንደር እኔን አሳልፈህ እንዳልሰጠህ እንዲያውም የኔን ሞት እንደሞትክ ሁሉ የጀግናው ወንድማችንና ልጃችን የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ህይወትም ማትረፍ መቻል አለብህ እና አምኖ አድነኝ ብሎሃል፤ወንድምህ ነው አድነው፤ ተዋደቅለት። ሌላም ልጨምር! የምችለው ነገር ብኖር ሁሉም ሸዋ፣ወሎና ጎጃም እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይሄ ሁሉ ግፍና ሰቆቃ በአማራው ላይ የሚሆነው ኢትዮጵያን ለማፍረስ ስለሆነ አማራው ብቻ ሳይሆን መነሳት ያለበት መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ተነስተህ ይሄ ያገር ጠንቅ የሆነውን ወያኔ ንቀል፤ጊዜው አሁን ነው ተጀምሯል፤ከአሁን በኋላ ይሄ ነገር መክሸፍ የለበትም።
ከዚህ በፊት ብዙ አጋጣሚዎች አምልጠውናል፤ይሄ ግን ሊያመልጠን አይገባም። በድጋሜ ይሄንን የመሰለው ወርቃማ ጊዜ ሊያመልጠን አይገባም እና ተነስ የኢትዮጵያ ህዝብ። ይህ የመጨረሻ ጥሪዬ ነው የማቀርብልህ። በተለይ በተለይ የደቡብ ጎንደር ህዝብ ባለፈው ጊዜ ብዙ እንዳስቸገርኩህ አውቃለሁ።አሁን የማስቸግርህ ለመጨረሻ ጊዜ ነው፤ተነስ! ተነስ! ተነስ! ይህንንም ደግሞ ላንተው መዳን ሲባል ነው፤አንተ ህይወትህ እንዲቀጥል ነው የምለምንህ። እና እስከዛሬ እንዳላሳፈርከኝ ሁሉ ዛሬም እንደማታሳፍረኝ ፅኑ ዕምነቴ ነው።

በመጨረሻም የጎንደር ህዝብ ማድረግ የሚገባህን ተጋድሎ ሁሉ ማድረግ አለብህ። በምንም ታዓምር ወያኔን አሳፍረኸዋል፤ አሁንም ደግመህ ደጋግመህ አሳፍረው።ሌላውም ህዝብ ይሄንን የጎንደርን ህዝብ ማገዝ መቻል አለብህ። በምንም ተዓምር ወያኔ ሁልጊዜ አሸናፊ እየሆነ መውጣት የለበትም፤ይሄ የመጨረሻው መሆን አለበት። እያታለለ አንድ ጊዜ ኦሮሞውን፣ ሌላ ጊዜ አማራውን፣ሌላ ሰሞን ደሞ አኙዋኩን እንዲሁም ሱማሌውን እየደበደበና እርስበርስ እያባላ የሚነግድበት ካርድ ለመጨረሻ ጊዜ ማቃጠልና ማስቆም አለብህ።

ይሄንን መሰሪ ቡድን ማጥፋትና ነፃነትህን ማገኘት መቻል አለብህ።
ጀኔራል ሃይሌ መለስ።

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ  መግለጫ 

ምንጭ - ዘሐበሻ 

ሐምሌ 15, 2008 ኖርዌይ !!
ዴሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጲያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ከተቋቋመበትመሰረታዊ ዓላማዎች አንዱና ዋነኛው በሃገራችን ኢትዮጵያ ያለውን ፍትሃዊና የአንድ ዘር የበላይነት አገዛዝ  የሰፈነበትን አምባገነን ሥርዓት በማውገዝ እንዲሁም በመታገል  ዴሞክራሲያዊ ኢትዮጵያን  ማለትም  የዜጎችን እኩልነትየተረጋገጠባት፣ ሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠባት  የዜጎች ሰብዓዊናዲሞክራሲያዊ መብቶች የተከበረባትና የተረጋገጠባት   የሕግ የበላይነትየሰፈነባት፣ እንዲሁም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በኩል አይን የሚታይባትዴሞክራሲያዊት ኢትዮጲያን ለመገንባት የሚደረገውን ህዝባዊ ትግል መደገፍናብሎም በአጋርነት መቆም ነው፡፡
እኛ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት አባላት የወያኔ መንግስትበመላው አገሪቱ ዜጎችን በማናለብኝነት ከትውልድ ቦታቸውና ከመኖሪያአካባቢያቸው ማፈናቀልም ሆነ ይዞታቸውን በጠመንጃ አፈሙዝ መንጠቅ አንድንአገር አስተዳድራለሁ ያለን መንግስት ለሕዝብ ያለውን ንቀት ያሳያል። ወያኔ ስልጣንበጠመንጃ ከያዘ ጀምሮ በመላው አማራ በጉራ ፈርዳ  በጋምቤላ  በኦሮሚያ ክልል በማስትር ፕላን ሰበብ፣ እንዲሁም አዲስ አበባዜጎችን የመኖሪያ ቤታቸውን ከሀና ማርያም፣አቃቂ ቃሊቲ፣ላፍቶ ክፍለ ከተማና ሌሎችም አካባቢዎች ህዝብን ከይዞታቸው ማፈናቀል አሁንደግም በጎንደር ወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄን በጠመንጃ አፈሙዝ ለማፈን የሚደረገውን ትግል በማናለብኘነትና በአምባገነንነትየተወሰደና ሕገ ወጥ እርምጃ ነው 
በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል በጎንደር ከተማ  ከወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄን ተንተርሶ  በሰላማዊና በሰለጠነ መንገድ  ላለፉት  ሃያአምስት ዓመታት  የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ  ቀደም ሲል በቤጌምድር በኋላም በሰሜን ጎንደር በአማራነቱ ተከብሮ የኖረ ሕዝብ ስለሆነ ወደትግራይ ክልል መካለሉን በመቃወም ጥያቄዉን በአግባቡ ያቀረበ ቢሆንም ይህን በሰላማዊ መንገድ ላቀረበዉ ጥያቄ አንባገነኑ የወያኔጉጀሌ ቡድን የሕዝቡን ጥያቄ በሃይል ለማፈን የኮሚቴ አባላቱን ማሰርና ማፈን የቀጠለ ሲሆን ኮረኔል ደመቀ ዘዉዴ ለማሰር የሞከረዉንሙከራ ተንተርሶ ሕዝብዊ ማዕበል/ቁጣ ተነስቷል። የሕዝብን ጥያቄ በሃይል ለማፈን እንደማይቻል ትላንት በኦሮሚያ የታየዉን ሕዝባዊአመጽ ዛሬ በታሪካዊቷ ጎንደር ተደግሟል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ላለፉት25 ዓመታት በአሸባሪውና በፋሽስቱ ወያኔ ቁጥጥር ሥር ከወድቀበትጌዘ አስቶ የፍዳ ዓመታትን እያሳለፈ ሲሆን በእነዚህ ረጅም  የመከራ ዓመታት አንድም ቀን ወያኔን ከመታገል የተቆጠበበት ጊዜ ግን አልነበረም:: ወያኔ የማህበረሰቡን እሴትበቁጥጥር ስር ለማስገባት በአካሄደው አረመኔያዊ ድርጊት አሉ የሚባሉትን ማህበራዊ  እሴቶቻችንን  በሙሉ  ተራ  በተራ  ያፈራረሳቸዉና በራሱ  አሻንጉልቶች በመተካት ፀረ ማህበረሰብ ዘመቻውን በሰፊው ገፍቶበታል። ይህ አንባገነን ሥርዓት  ኢትዮጵያ እንደሃገር ሕዝቧምእንደ ሕዝብ ቀድሞ  በነበረዉ  ሃገራዊ  ትስስር እንዳይቀጥል  ለእኩይ ዓላማዉ ሲል ብቻ  የሃገሪቷን ሕዝቦች  በዘርና በቋንቋ በመከፋፈልየሃገሪቷን ሕዝቦችን ሲያጣላና  እርስ በርሳቸዉ እንዳይተማመኑ በከፍተኛ ጥንቃቄ የሰራና በሃገሪቷ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ማህበረሰቦችወይም ብሄረሰቦች  ከራሳቸው ዘር ውጭ ሌላውን ማመን የማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ እየገቡ ለመሆናቸው በቅርቡ እየተፈፀሙ ያለውድርጊት ከበቂ በላይ ማስረጃ ነው። በጋራ ሁላችንም በሰውነታችን ብቻ ልንቀበላቸው የሚገቡ፣ ዘርን፤ ቋንቋንና ባህልን ተሻግረውሊያስተሳስሩን የሚገቡ ጉዳዮቻችንን እያፈራረሳቸዉ ይገኛል።
የወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት በህዝብ ያልተወከለ አገሪቱን  የግዛት አንድነት ያላስጠበቀ፤ የሃገሪቷን አኩሪ የነፃነትና  የአንድነትን ታሪክ ገድልየካደና የናደ  እኩይ ቡድን ስለሆነ ይህ ቡድን ከህዝብ ጫንቃ ላይ ማስወገዱ አማራጭ የሌለዉ ወቅታዊና ሃገራዊ ግዴታ መሆኑንዲሞክራሲያዊ ለዉጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ሰጪ ድርጅት በጽኑ ያምናል።  በወልቃይት  ጠገዴ መሪዎች ላይ  ይህ አንባገነን  ታጣቂዎችንከትግራይ ወደ ጎንደር በመላክ የኮሚቴ አባል የሆኑትን ኮለኔል ደመቀንና ሌሎችንም ለማፈን እንዲሁም ላለፉት ዓመታቶች  በወልቃይትጠገዴ ማንነት ጥያቄ  አቅራቢዎች ላይ የጦር ሀይል፤ ደህንነትና ፖሊሶችን በማዝመት ጥያቄዉን ለማኮላሸት ቢሞክርም የወልቃይትጠገዴና ጠለምት ሕዝብ ጥያቄዉን እንዲያቀርቡለት የመረጣቸዉ የኮሚቴዉ አባላቶች ለሚደርስባቸዉ ወከባና  እንግልት ሳይበገሩየተጣለባቸውን አደራ ያለማወላወል በመጠበቅ ባካሄዱት አኩሪ የትግል ገድል ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ ታሪኩን በወርቅ ቀለም ፅፏል።ዘረኛው  ወያኔንና ተባባሪዎቹ የማይገባቸውና  እስከ ዛሬ ያልተረዱት የሕዝብ ፍላጎት ብሎም ቁጣንውን አሻፈረኝ አልገዛም ብሎ ማመጽወቅቱ ጠብቆ የሚመጣ ክስተት ነው። የወያኔ መንግስት ይሄንን ሕዝባዊ መነቃቃት ለማጥፈት በሌሎችም ላይ እንደሚያደርገው ሁሉየተለያዮ ዘዴዎችን በመጠቀም ያላሰለሰ የሞት ሽረት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል።አሁንም በተግባር እየፈፀመ ነው።
ዴሞክራሲያዊ ውጥ በኢትዮጲያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አምባገነኑ ህውሃት(ኢህአዴግበሰላማዊና በንፁሃን ዜጐች ላይ የወሰደውንኃላፊነት የጐደለው እርምጃ አጥብቀን እያወገዝን የኢትዮጵያ ሕዝብ ልዩነቱን ወደ ጐን በመተው ይህንን ዘረኛ  አምባገነን ስርዓትለማስወገድ ከመቸውም ጊዜ በላይ ተባብሮ እንዲነሳ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። እንዲሁም በሰላማዊ መንገድ ድምጻቸውን ሊያሰሙበወጡ ዜጎች ላይ የወሰደውን አረመኔያዊ እርምጃ በጥብቅ እያወገዘን የጎንደር ሕዝብ እያደረገ ያለውን ፍትሃዊ ትግል ሙሉ በሙሉእንደግፋለን።ለተጀመረው የነጻነት ትግል ዴሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጲያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አጋርነቱን ይገልጻል።

ወያኔ በማስወገድ የሃገራችንን አንድነትና ዳር ድንበር እናስከብር!!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!!
የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ !!!!ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Wednesday, July 20, 2016

ዘረኛው ማን ነው? ሊመለከቱት የሚገባ አዲስ ጥናታዊ ፊልም

Source = ESAT (Ethiopian Satellite Television)
http://video.ethsat.com/?p=26054ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Monday, July 18, 2016

¨በሰላም ባስ¨ የቃጠሎ ነበልባል ውስጥ ዋልድባን አየሁት (ጉዳያችን ማስታወሻ)


የዋልድባ መነኮሳት 

ኢትዮጵያችን የተጎዳችው በጭፍን የጎጥ ፖለቲካ ብቻ አይደለም።ሚዛናዊ አስተሳሰብ ደብዛው መጥፋቱም ብቻ አይደለም። እንደ ሰው የማሰብ ተፈጥሯዊ ክህሎት ነው። እንደ ሰው ማሰብ የአምሳያው ሰው ሞት፣ስደት፣ነፃነት ማጣት እና ድህነት ሁሉ የእኔ ችግር ነው ብሎ ከማሰብ ይጀምራል። የማኅበራዊ ሚድያው ፈጣን መረጃ ከመስጠት አልፎ ሰዎች ስለ ክስተቶች ምን እንደሚያስቡ ሃሳባቸውን በቀላሉ ለማካፈል ዕድል ፈጥሯል።በእዚህም ሳብያ የብዙዎች የአስተሳሰብ ጥግ ከየት ተነስቶ የት ላይ እየደረሰ መሆኑን ለማወቅ ሙሉ በሙሉ በቂ ባይባልም ጥሩ መረጃ ግን ይሰጣል።

ከአራት አመታት በፊት በሰሜን ጎንደር ከነበረው ትልቅ የአገራችን አነጋጋሪ ጉዳይ ውስጥ አንዱ የህወሓት የዋልድባ ገዳምን ይዞታ የሆነ መሬት አብያተ ክርስቲያናትን እና የቅዱሳንን መቃብር እየፈነቀለ ስኳር ሸንኮራ አገዳ ለመትከል መወሰነኑን የመናገሩ ጉዳይ ነበር።በወቅቱ የገዳሙ መነኮሳት በማያውቁት የከተማ ሕይወት የገዳሙ አባቶችን የተማፅኖ ደብዳቤ ይዘው አቶ መለስ ቢሮ አዲስ አበባ ድረስ መጥተው ሲጠይቁ ሃይማኖታዊ ከበሬታው ቢቀር ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በማይገልፀው መልኩ በስልክ እንደተሰደቡ በሃዘን በወቅቱ ለአሜሪካ ራድዮ አማርኛው ክፍል መግለፃቸው ይታወቃል።በወቅቱ ገዳማውያኑ ስለ ዋልድባ የገለፁበት ቃላት ''ቦታው የቃል ኪዳን ቦታ ነው ገዳሙ ሀጥያት የማይሻገርበት ፣ዘር የማይዘራባት፣እህል የማይበላባት ቦታ ነው''  ( ጉዳያችን፣2014የሚል ነበር። በጎንደር ከተማ እና በውጭ አገራት የተለያዩ የተቃውሞ ሰልፍ ቢደረግም በአቶ አባይ የሚመራው ፕሮጀክት እንዲህ ከ70 ቢልዮን ብር በላይ ውጦ ዝም ሊል በወቅቱ በእየመድረኩ ላይ በትዕቢት የተወጠረ ንግግር ማድረግ ልማዱ አድርጎት ነበር። ሌላው አስገራሚው ጉዳይ ዋልድባ ለምን ይታረሳል? በርካታ የአገራችን መሬቶች መች ተነኩና ነው ዋልድባ ይታረስ የተባለው? ሲባል የህወሓት እና እራሳቸውን የትግራይ ጎሳ ጠበቃ አድርገው የሾሙ ወገኖች ¨የዋልድባን ጉዳይ የምትቃወሙት ትግራይ እንዳትለማ ነው¨ የሚል ትግራይ የእነርሱ ብቻ ትመስል ባጠለቁት የጎጥ ፖለቲካ ጥብቆ ልክ ሲናገሩ ታዝበናቸዋል። ይህ አባባል ደግሞ ሃይማኖተኛ ነን እያሉ እራሳቸውን በሚጠሩት ብቻ ሳይሆን የሃይማኖት አባቶች ሁሉ ጉዳዩን ለማድበስበስ ቢያንስ እንደ ሰው መቃወም የሚገባቸውን ግልፅ ጉዳይ ለስርዓቱ በማደር እንዳላዩ አልፈውታል።ይህ ሁሉ ሆኖ ግን አቶ መለስም በሞት ወደ ማይቀረው ሳጥን ገቡ፣ የስኳር ፕሮጀክትም ጥቂት የህወሓት ሰዎችን ኪስ አደልቦ አንድም ሳይራመድ ባለበት እየረገጠ ይሄው አለ።የሰላም ባስ ባለቤቶች በወቅቱ በዋልድባ ጉዳይ የተናገሩት ለጆሮ የሚጠልዝ እና ሃይማኖት የእዚህን ያህል በጎጠኝነት ተቀይራለች እንዴ? የሚያስብሉ ንግግሮች ከብዙ ትዝብት ላይ ጥሏቸዋል።ችግሩ ዛሬም ድረስ እውነትን ከመጋፈጥ ይልቅ ከአርባ ዓመት በፊት በቆሙበት የጎጥ ጭቃ ውስጥ እየዳከሩ ሌላውን ኢትዮጵያዊ ሊለውሱ የመዳከራቸው ድፍረት ነው።


የዋልድባ ጉዳይ የህወሓትን የጎጥ ፖለቲካ የሚጋሩ ሁሉ ማንነት በሚገባ የተፈተሸበት ነው።እንደ ሰው የሚያስቡ ሳይሆን የጎጥ ስብስባቸው ለክቶ እና ሰፍሮ በሚሰጣቸው የጎጥ መለክያ ብቻ ለማሰብ እራሳቸውን እና ስብእናቸውን ለመሸጣቸው ማሳያ ነው። ማንም ሰው የፈለገውን ስብስብ የመደገፍ መልኩ የተጠበቀ ነው።ነገር ግን የተሰበሰበበት ስብስብ ስህተት ሲሰራ ስህተት ነው።ትክክል ሲሆን በእዚህ በዚህ ምክንያት ትክክል ነው ብሎ መናገር ጤነኛ አስተሳሰብ ነበር። የህወሓት የጎጥ ስብስቦች ግን ድርጅታቸው ገዳማትን ሲወር ትክክል ነው። ገዳማውያኑን በጎጥ እየከፈለ አንዱን የእንጀራ ልጅ ሌላውን  የአገር አባት ሲያደርግ ልክ ነው።በዋልድባ ዙርያ ያሉ አብያተ ክርስቲያናትን እየነቀለ፣የቅዱሳንን አፅም እየፈነቀለ ሲጥል ሁሉ በእነርሱ አባባል ለትግራይ ነው እና ተዉ! ሲሉን ከረሙ።በአሶሳ፣ጉርዳፈርዳ፣ቡራዩ፣ እና ሌሎች በርካታ ቦታዎች ሰዎች በትውልድ ቦታቸው እየተጠራ ሲባረሩ እና ንብረታቸው ሲዘረፍ በህወሓት በጎ ፍቃድ ነው ነው እና  አንዳች ሳይተነፍሱ ይልቁንም የሚናገሩትን ሲያስሩ እና ሲገድሉ ሰነበቱ። ይልቁንም አቶ መለስ ሰዎች ለምን ይፈናቀላሉ? ተብለው ሲጠየቁ ¨ጉርዳፈርዳ ምስራቅ ጎጃም መስሏል¨ በሚል የጎጥ ንግግራቸውን በጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ ተቀምጠው የኢትዮጵያ ምክር ቤት  በሚሉት ፊት በቴሌቭዥን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በቀጥታ በሚተላለፍ ንግግራቸው ላይ ተናገሩ። ከእዚህ በላይ መታወር ከየት ይመጣል?

ከ20 አመታት ባላነሰ በጎንደር ላይ ሲሽከረከር የነበረው የሰላም አውቶቡስ ጎንደር ከተማ ላይ በእሳት ጋይቷል።ግን ጥያቄው ለምን ለዓመታት ያልሆነው አሁን ሆነ? ነው።ጉዳዩን በአንክሮ ስንመለከተው የነገው የህወሓት ዕጣ አመላካች ነው።በአውቶብሱ ነበልባል ውስጥ በሚገባ መመልከት የቻለ ሰው ዋልድባን ይመለከትበታል።ከአራት ዓመታት በፊት የዋልድባ መነኮሳት እንባ በጉንጫቸው እየወረደ ከሰሜን ጎንደር ተነስተው አዲስ አበባ የአቶ መለስን ቢሮ እና የአቡነ ጳውሎስን ልዩ ፅህፈት ቤት ደጅ ሲጠኑ እና የሚያናግራቸው አጥተው መንግስት የሚባለው አካል እና ቤተ ክህነት ይህንን ያህል የስምንተኛው ሺህ ትንቢት መፈፀምያ መሆናቸውን ተመልክተው ሞታቸውን የተመኙባትን ደቂቃ ያጤንበታል። በእሳቱ ነበልባል ውስጥ  በጎንደር ዋልድባን አስመልክተው የተደረጉ የህዝብ ስብሰባዎች ላይ እንባቸውን እየዘሩ የተናገሩ አዛውንት እና እናቶች ድምፅ ይሰማል።በእሳቱ ነበልባል ውስጥ በእግራቸው ከጎንደር ተነስተው  እስከ ዋልድባ እያለቀሱ የሄዱ የጎንደር  ወጣት ወንዶች እና ሴቶች ሰቆቃ ይታያል።በእሳቱ ውስጥ የህወሓት ¨ነፍሰ በላ¨ ገራፊዎች የዋልድባ አባቶችን ልብስ አስወልቀው እያዋረዱ እና እየሰደቡ የገረፉበት እና የመነኮሳቱ ገላ ከሰንበር አልፎ ደም ያፈሰሱበት መሬት እና ጨለማ ቤት ይታያል።በእሳቱ ነበልባል ውስጥ የህወሓት ገዳዮች ዋልድባን ደም ባፈሰሰና  በረከሰ እግራቸው ገብተው ያመሱበት እና ለዓመታት ከገዳማቸው ወጥተው የማያውቁ መነኮሳት ወደ ሱዳን እና ኤርትራ ሌት በቁር ቀን በሐሩር እየተንከራተቱ መሰደዳቸው ይታየናል።በሰላም ባስ እሳት ነበልባል ውስጥ እነኛ ሮጠው ያልጠገቡ ኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ታዳጊ ሕፃናት በአጋዚ የጥይት አረር የመፈጀታቸው ግፍ እና የወላጆቻቸው እሪታ ይታየናል።

ባጠቃላይ ከአራት ዓመታት በፊት የህወሓት እብሪተኛ መሪዎቹ ደረታቸውን ነፍተው፣አንገታቸውን አቅንተው ዋልድባን እንደሚያርሱ ሲነግሩን አልቅሰናል። የእነርሱን ንግግር ተከትሎ የህወሓት መንደርተኛ አስተሳሰብ አራማጆች ጎጠኛ ድርጅታቸው ወደ ፋሽሽትነት እየተቀየረ መሆኑን ስንነግራቸው፣ እናምነዋለን የሚሉት ሃይማኖትም ሳይገዛቸው ቀላብቸውን አጥተው ፎክረዋል።ይህ ብቻ አይደለም የእዚህ አይነት እብሪት ዞሮ ዞሮ ለወገናችን የትግራይ ሕዝብ እንደሚተርፍ እና ችግሩን መቀልበስ አስቸጋሪ እንደሆነ እያለሳለስንም እያከረርንም ስንመክራቸው ስቀውብናል። ዛሬ ላይ የሰላም ባስ ሲቃጠል ከድንጋጤ ባለፈ መጪው ጊዜ በትንሹ እንደ እነርሱ አገላለጥ ¨በወጋገን¨ እየታያቸው ነው። የሚያሳዝነው ግን አሁንም ለሌላ እልቂት በኦሮምያ እንደፈፀሙት በጎንደርም ለመፈፀም ሳንጃቸውን ስለው ጎንደር ላይ እየከተሙ ነው።

ባጠቃላይ የህወሓት ወደ ፋሽሽት ድርጅትነት መቀየር ለትግራይ ሕዝብ ግልፅ ሊሆንለት ይገባል።የሰሞኑ በጎንደር ሕዝብ ላይ የሚፎከረው ¨አማራ ገዳይ¨ ፉከራ  የመጨረሻው መጀመርያ እንደሚሆን ማንም አይጠራጠርም።መታወቅ ያለበት ገበሬ ካልቆረጠ በሰኔ እና ሐምሌ መሣርያውን ይዞ ከቤቱ አይወጣም።ይህ ወቅት የእርሻ ወቅት ነው።ከቆረጠ ግን እንዲህ እንዳሁኑ ይነሳል።የተከበረውን የትግራይ ሕዝብ ከሌላው ሕዝብ ጋር  በማጋጨት የሚጠቀም የሚመስለው ህወሓት በመጨርሻ ችግሩ ሲጠና ቀድሞ የሚነሳበት የትግራይ ሕዝብ ለመሆኑ ባይተራጠር ጥሩ ነበር። የአሁኑ የጎንደር እንቅስቃሴ ከመነሻው ጀምሮ ፍትሃዊ እና እውነት እንደሆነ  ህሊናውን ለመሸፈን ያልፈለገ እና እራሱን ከእብሪት ለማራቅ የሚፈልግ የህወሓት አቀንቃኝ ሁሉ ያውቀዋል።የወልቃይት ኮሚቴ አባላትን ኮ/ል ደመቀን ጨምሮ አቶ ሃይለማርያም አሁኑኑ ላናግርህ እፈልጋለሁ ወደ አዲስ አበባ ና! ቢሏቸው በቀጥታ የሚመጡ ህዝቡ ውስጥ የሚኖሩ ሰላማዊ ሰዎች ናቸው። ለአማራ ካልል የፀጥታ ኃይል ሳይናገሩ እንደ ጅብ በሌሊት የመጡት የአባይ ወልዱ ቅልቦች ናቸው። ጧት እንዲመጡ ስነግራቸው በሩን የሰበሩት አሁንም እነኝሁ ቅልቦች ናቸው።የነገሩ መነሻ ከሰው አይመስልም።ህወሓት መውጫ እንዲያጥረው ነገሩን የሰራውም የሰው ሥራ አይመስልም።የዋልድባን ሰቆቃ በሰላም ባስ የቃጠሎ ነበልባል ውስጥ የሚታይ ብዙ ነገር አለ። ለህወሓት የጎጥ ፖለቲካ ኢትዮጵያን በዘር ሊለበልቡ የተነሱ ሁሉ የሰላም ባስ ከሃያ አመታት በላይ እንደፈለገ ሲሄድ የነበረው አውቶብስ ለምን ዛሬ አቃተው? ብለው መጠየቅ እና የዋልድባን ሰቆቃ በእሳቱ ነበልባል ውስጥ ማየት ካልቻሉ የዕይታ ችግር ያለው ከእነርሱ እንጂ ከእሳቱ ነበልባል አይደለም። 

ጉዳያች Gudayachn
www gudayachn com 

Tuesday, July 12, 2016

ጎንደር ኮ/ል ደመቀ ከበባውን ሰብረው ከሕዝቡ ጋር ተቀላቅለው እራሳቸውን እየተከላከሉ ነው


ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ 

¨ጎንደር ጦርነት አለ!" ጋዜጠኛ ተፈራ አስማረ 1984 ዓም ¨

ህወሓት ከ25 ዓመታት በፊት ሶስተኛ አብዮታዊ ሰራዊትን ሽሬ እንዳስላሴ ላይ ካጠቃ በኃላ ከፍተኛ ተቃውሞ የገጠመው ጎንደር ላይ ነበር።ጎንደር ከተማ እና ደብረ ታቦር ከተማን ልክ በአምቦ እንደሆነው ሁሉ ሁለት ጊዜ ገብቶ በሕዝቡ ተባሮ ወጥቷል።በእዚሁ ሳብያም በርካታ ወጣቶች በግፍ ተገድለዋል፣በግዞት ወደ እስር ቤት ተግዘዋል የቀሩት ለስደት ተዳርገዋል።ለህወሓት የጎንደር ጉዳይ ሲነሳ ልቡ የሚመታው ካለነገር አይደለም።የህዝቡን የስነ ልቦና ደረጃ እና ቁርጠኝነት ላይ በቂ ልምድ አለው። ለእዚህም ነው በ1984 ዓም ጋዜጠኛ ተፈራ አስማረ በወቅቱ በሚታተመው የግል ጋዜጣው ላይ በፊት ገፁ ላይ ¨ ጎንደር ጦርነት አለ!¨ በሚል ርዕስ ባወጣው ዜና አማካይነት ህወሓት በከባድ ወንጀል ከሶት የነበረው። በወቅቱ ተፈራ ¨ጦርነት ለመኖሩ የቪድዮ ማስረጃም አለኝ ¨ ማለቱ እና ህወሓት ግን ከዜና ሁሉ አጥብቆ የሚፈራው ዜና ¨ጎንደር ጦርነት አለ¨ የሚለው መሆኑ የታወቀው ከ24 አመታት በፊት ነበር።

¨ገበያችን ጎንደር ነው አታጣሉን¨ የትግራይ ገበሬ 1980 ዓም


ህወሓት ኃላፊነት በማይሰማቸው፣ቤተሰባዊ መሰረት የሌላቸው እና ለሀብት ንብረት በሚስገበገቡ መሪዎች መመራቱ ክፉኛ ጎድቶታል።በትጥቅ ትግሉ ወቅት የህወሓት ካድሬዎች በህወሓት አመራሮች ከሚሰጣቸው መመርያ ውስጥ አንዱ እና ዋነኛው  የአማራውን ሕዝብ ነፍጠኛ የሚል ታቤላ ለጥፎ የትግራይን ሕዝብ ከአማራ ማሕበረሰብ ጋር ለማጣላት ብዙ ደክሟል።በሽሬ የተገኘ አንድ የህወሓት ካድሬ የትግራይ ገበሬ ሰብስቦ የለመደውን የአማራ ሕዝብ የሚያጥላላ ንግግር ሲያደርግ አንድ ገበሬ ይነሱ እና ¨ አንተ የተላክበትን አራግፈህ ትሄዳለህ ለእኛ ትግራዮች ግን ቅዳሜ ገበያችን ደባርቅ ጎንደር ነው አታጣላን¨ አሉት። ተመሳሳይ ንግግር ለአቶ ታምራት ላይኔ መነገሩን በወቅቱ በክርክሮቹ ወቅት የነበሩ በተለያዩ መፅሄቶች ላይ ስያወሱት የነበረ ጉዳይ ነው። ዛሬም ህወሓት አፉ እንዳመጣ በመናገር ለስልጣን መጠበቅያው በህብረት ለዘመናት የኖረውን የአማራ እና የትግራይ ማሕበረሰብ ለማጣላት የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም።ስለሆነም ይህንን እኩይ ተግባር ለማክሸፍ የትግራይ ሕዝብ ለመጪው ዘመን ሲል ከፍትህ ጋር መቆም እና ህወሃትን ከቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር መቃወም የቀረበለት ብቸኛ መንገድ ነው።

ጎንደር ጦርነት አለ


ሐምሌ 4 ለ 5/2008 ዓም ከለሊቱ 10 ሰዓት የወልቃይት ጉዳይ ከሚከታተሉት የኮሚቴ አባላት አንዱ ኮ/ል ደመቀ ዘውዴ ቤታቸው ይቆረቆራል። ፊታቸውን ጭንብል ያጠለቁ የፌድራል ፖሊስ መሆናቸውን የሚናገሩ እና እውነታው ግን ከትግራይ በሚስጥር ወደ ጎንደር የተላኩ ግለሰቦች ነበሩ።ኮ/ል ደመቀ ከመንግስት ከመጡ ሲነጋ እንደሚያናግራቸው እና አሁን ግን ሌሊት ስለሆነ  ከበሩ ላይ እንዲሄዱ ይነግራቸዋል። ሆኖም የህወሓት ታጣቂዎች ፈቃደኛ አልነበሩም። በመቀጠል  ታጣቂዎቹ በኃይል ለመግባት ሲሞክሩ ተኩስ ይከፈታል።ሁለቱ ታጣቂዎች ይወድቃሉ።ይህ ዜና ለጎንደር ብሎም እስከ አርማጮ ድረስ ይሰማል። የጎንደር ሕዝብ ኮ/ል ደመቀን አናስነካም ብሎ የከበቡትን ፈድራሎች መልሶ ይከባል።ቀኑን ሙሉ እስከ ቀትር በኃላ ድረስ ይታኮሳል።የህወሓት ንብረት ናቸው ያላቸውን የሰላም ባስ አውቶብስ፣ኮ/ል ደመቀን ወደ ትግራይ ለመውሰድ የመጣው መኪና እና ሌላ የፖሊስ መኪና ጨምሮ ይቃጠላል።የጎንደር ዩንቨርስቲ ተማሪ፣ ከአርማጮ የመጡ ታጣቂዎች በስድስት አውቶብስ እና የከተማው ነዋሪ ከሌሎች የገጠር ቀበሌዎች ጭምር ወደ ጎንደር ከተማ ይገባሉ። ከምሽቱ በፊት ኮ/ል ደመቀን ለማባባል የህወሓት ሰዎች የገዛ ዘመዶቹን አግባብተው እጁን እንዲሰጥ ይልካሉ። የተላኩት የኮለኔሉ ዘመዶች ግን ኮ/ል ደመቀን እንዳገኙ ያገኙትን መሳርያ ይዘው አፈሙዛቸውን ወደ ህወሓት ነፍሰ ገዳዮች አዞሩ። የዕለቱ ጀንበር ሳትጠልቅ ኮ/ል ደመቀ ከሕዝቡ ጋር ሆኖ ከበባውን ሰብሮ አመለጠ።በአሁኑ ሰዓት ከሕዝቡ ጋር ሆኖ ከህወሓት ታጣቂዎች ጋር ሆኖ  እየተዋጋ መሆኑን ኢሳት በምሽቱ የራድዮ ዘገባ ከስፍራው ያናገራቸውን የአይን እማኞች ቃል  አስደምጧል።

ባጠቃላይ ከ24 አመታት በፊት ህወሓት የፈራው እና ጋዜጠኛ ተፈራ አስማረን መቀጣጫ ያደረገበት ¨ ጎንደር ጦርነት አለ¨ የሚለው ዜና ገዝፎ እና አድጎ በሩ ላይ መጥቷል።ህወሓት አገሩን ሁሉ እየገዛ ትግራይን ከሌላው ኢትዮጵያ ለመለየት ባለው ሕልም  ምክንያት የትግራይን ሕዝብ ለማስደነበር እና ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ለመለየት የሚያደርገው ጥረት  መልሶ እራሱኑ እንደሚፈጀው ቢረዳ ጥሩ ነበር።የአባይ ወልዱ እና ወዳጆቻቸው የአስተሳሰብ ችሎታ ጥግ  ከአፍ እስከ አፍንጫ ድረስ ባይሆን እና የዛሬን ሳይሆን አሻግረው መጪው ትውልድ ሕልውናው እንዳየበጠበጥ ማሰብ ቢጀምሩ ጥሩ ነበር።አሁን እንደሚታየው ግን ፈፅሞ ለአቅመ መጪውን ማሰብ ደረጃ እንዳልበቁ እና ጎንደርን በደም ለመንከር ተጨማሪ ሰራዊት እያስገቡ መሆኑ ተሰምቷል። የጎንደር እና አርማጮ ህዝብም እራሱን የመከላከል ሥራ ሴቶች ከበርበሬ እስከ ክላሽ ይዘው የወጡበት ፍልምያ መሆኑን እየገለፁ ነው። እስከ ሰኔ 30 ድረስ መንግስት ምላሽ እንዲሰጠው የጠየቀው የወልቃይት ግፉአን ማኅበርም ባወጣው መግለጫ የህወሓት እብሪት አደብ እንዲገዛ ሁሉም ኢትዮጵያዊ  እንዲነሳ ጥሪ አቅርቧል። 


ጉዳያችን GUDAYACHN 
www.gudayachn.com

Monday, July 11, 2016

ኢሳት አገራዊ ኃላፊነት የመወጣት አቅሙን ያስመሰከረባቸው ሁለቱ ዜናዎች


የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን ከተመሰረተ በኃላ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ተፅኖ ፈጣሪ ለመሆን ሶስት ዓመታት አልፈጀበትም።አሁን ላይ ኢሳት ከተመሰረተ ገና ስድስተኛ ዓመቱ ቢሆንም በመላው ዓለም ከተበተኑት ኢትዮጵያውያን እና አገር ቤት ከሚገኘው ሕዝብ በተጨማሪ በኢትዮጵያ የሚገኙ የልዩ ልዩ አገራት ዲፕሎማሲ ማሕበረሰብ እና የኢትዮጵያን ጉዳይ ለበጎም ሆነ በጎ ላልሆነ ስልታዊ ፍላጎት የሚከታተሉ ባዕዳን ኃይሎች ዘንድ ሁሉ ዕለት ከዕለት በሚፈልጉት ቋንቋ እየተረገሙ የሚከታተሉት የዜና ምንጭ ሆኗል። ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮችም በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ በብቸኛ የዜና ምንጭነት የሚጠቅሱት ኢሳት የሆነበት ጊዜ መኖሩ በእራሱ የድርጅቱን ተአማኒነት እያደገ የመሄዱን እውነታ የሚያመላክት አንዱ ማሳያ ነው። (የዋሽግተኑ ተቃውሞ ኢሳትን በዓለም ዓቀፍ ስመጥር የዜና አውታሮች ዝናው ገንኖ እንዲወጣ አደረገ 

ኢሳት ባለፉት አርባ አመታት ውስጥ  በኢትዮጵያ የማዕከላዊ መንግስት ተቃዋሚነት ተሰልፈው የነበሩ የዜና አውታሮች አንፃር ስንመዝነው በበርካታ መስፈርቶች ገንቢ እና ሚዛናዊ ዘገባዎቹ የተሻለ እና ለወደፊቱ የኢትዮጵያ የሚድያ አገልግሎት የእራሱን በጎ አሻራ ትቶ የሚሄድ  ለመሆኑ የሚያመላክቱ በርካታ ነጥቦች እናገኛለን። ባለፉት አርባ አመታት ውስጥ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሕይወት ውስጥ ተፅኖ ለመፍጠር የሞከሩ አንድ ሁለት ተብለው ሊጠቀሱ የሚችሉ ከባህር ማዶ ወይንም ከጎረቤት አገራት መሰረታቸውን ያደረጉ የራድዮ ጣብያዎች ነበሩ።

በ1960ዎቹ መጨረሻ በአጭር ሞገድ ራድዮ ይተላለፉ የነበሩት የኢድዩ፣ህወሓት፣ሻብያ  እና ሱማልያ ራድዮ ጣብያዎች እና በኃላም በ1970ዎቹ መጨረሻ እና 80ዎቹ መጀመርያ እስከ 1981 ዓም በኮ/ል መንግስቱ ሃይለማርያም ላይ በግንቦት 8 እስከተደረገው መፈንቅለ መንግስት ድረስ የቆየው የኢትዮጵያ አንድነት ድምፅ የተሰኘው በአጭር ሞገድ የሚተላልፈው የራድዮ ጣብያ ሁሉ ሙሉ በሙሉ በተቃዋሚ ሚድያነት የሚታወቁት ራድዮ ጣብያዎች ሙሉ በሙሉ በስልጣን ላይ የነበረውን መንግስት ማጥላላት ላይ የተመሰረቱ ቃላት እና ፕሮፓጋንዳ ይዘት ያላቸው ዝግጅቶች ላይ ብቻ ያተኮሩ ነበሩ።

ኢሳት ባለፉት አርባ አመታት ውስጥ ከታዩት በውጭ አገራት መሰረታቸውን ካደረጉ ኢትዮጵያዊ የመገናኛ ብዙሃን የሚለይበት የተለየ ባህሪ ይታይበታል ሲባል የሚከተሉትን ነጥቦች ታሳቢ በማድረግ ነው።ይሄውም - 

  • ኢሳት ከቀደሙት ሚድያዎች በሙሉ በተለየ መልኩ በስልጣን ላይ ያለውን ስርዓት መንግስት ብሎ የሚጠራ እና ለሁሉም አካላት  የመገናኛ ብዙሃንነቱን ያንፀባርቀ ነው፣
  • ኢሳት በስልጣን ላይ ካለው ስርዓት ባለስልጣናት አቦይ ስብሐት እስከ የፅንፍ ፖለቲካ አራማጅ ተቃዋሚዎች ለሁሉም ሃሳባቸውን የመግለፅ ዕድል ለመስጠት ሞክሯል፣
  • ኢሳት በፕሮፓጋንዳ ላይ ከተመሰረተ ዝግጅት ባለፈ የኪነ ጥበብ ዝግጅት፣ የመዝናኛ መርሃ ግብር፣ ሰብአዊ መብት ላይ ያተኮሩ ቃለ መጠይቆች እና ኢትዮጵያውያን በውጭ አገራት የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶች ለምሳሌ በአረብ አገራት የተመለከቱ መርሃ ግብሮችን በማቅረብ ከቀደሙት የተለየ ይዞታ ሁሉ የተለየ ያደርገዋል።

ኢሳት አገራዊ ኃላፊነት የመወጣት አቅሙን ያስመሰከረባቸው ሁለቱ ዜናዎች

ከላይ እንደመነሻ ኢሳት ባለፉት አርባ አመታት ከውጭ አገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚተላልፉ መገናኛ ብዙሃኖች ያለውን ልዩነት ከገለጥኩ በመቀጠል የፅሁፉ መነሻ ወደሆነው የኢሳት አገራዊ ኃላፊነት ታይቶባቸዋል ወደምላቸው ሶስቱ ዜናዎች ልግባ። አሁን ባለንበት የ21ኛው ክ/ዘመን ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ኃላፊነት እጅግ ኃላፊነት ያለበት ትልቅ እና ቁልፍ ሥራ ነው። ለእዚህም ማሳያው የቴክኖሎጂ ብቃት እና ጥራት የዘመኑ መገናኛ ብዙሃን በእያንዳንዱ የገጠርም ሆነ የከተማ ነዋሪ ቤት የመድረስ አቅም መጨመር የመገናኛ ብዙሃን ተፅኖ የመፍጠር አቅም ምን ያህል ከፍ እንዳለ አመላካች ነው።ኢሳት ባለው ግልፅ እና ስውር የመረጃ ምንጮች ከአገር ቤት እና ሌሎች አገራት የሚያገኛቸውን ዜናዎች በኢትዮጵያ ላይ እንደ አገር የሚፈጥሩትን አሉታዊ ተፅኖ ሳያጤን ለአየር እንደማያበቃ እና አንድ ኃላፊነት የሚሰማው መንግስት ከሚወስደው የኃላፊነት ስሜት ባልተናነሰ መልኩ የሚያደርገው ጥንቃቄ ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ትልቅ ኩራት ነው። ለአብነት ሁለት ዜናዎችን እንመልከት።

የአቶ መለስ ዜናዊ ሞት 

አቶ መለስ ዜናዊ በብራስልስ ከእዚህ ዓለም መሞታቸውን ቀድሞ ያወቀ ኢሳት ነበር።ኢሳት ዜናውን በሰማበት እና የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ለሕዝብ በገለጠበት ጊዜያት መካከል ከሰላሳ ቀናት ያላነሰ ልዩነት ነበር።ሆኖም ግን ኢሳት የአቶ መለስ ዜናዊን እረፍት እንደሰማ ለአየር አላዋለውም።በየትኛውም አገር ቢሆን በስልጣን ላይ ያለ አገር መሪ ሲሞት በአገሪቱ የዕለት ተዕለት ተግባራትም ሆነ የፀጥታ ጉዳይ ላይ የሚፈጥረው የኃይል ክፍተት እንደሚኖር የታወቀ ነው።ይህ ደግሞ ይዞ የሚመጣው እና የሚያስከትለው ቀውስ ለመገመት በቀላሉ አይቻልም።በተለይ በባዕዳን ዘንድ ሁኔታውን አገሪቱን ለማጥቅያ ምቹ ጊዜ የመጠቀም ሁኔታ የመፈጠር እድሉ ሁሉ ቀላል አይደለም።በመሆኑም ኢሳት በአቶ መለስ ዜናዊ እረፍት ዜና ላይ በቅድምያ ወደ እውነት የቀረቡ ዜናዎች እየወጡ መሆናቸውን በመቀጠል ለተከታታይ ቀናት በስልጣን ላይ ላለው ስርዓት እስከ ቀጣዩ ሰኞ ቀን ድረስ ሁኔታውን እንዲያሳውቅ ይህንን ካላደረገ ደግሞ ኢሳት ባለው ኃላፊነት ጉዳዩን ለሕዝብ ግልጥ እንደሚያደርግ በማሳወቅ እና በመጨረሻም ዜናውን ለሕዝብ ይፋ በማድረግ የአንድ መገናኛ ብዙሃን ኃላፊነትን ተወጥቷል። እዚህ ላይ ኢሳት ኢትዮጵያዊ ኃላፊነት የማይሰማው ቢሆን ኖሮ ዜናውን እንዳገኘ እና እንዳረጋገጠ  ወዲያውኑ ለፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በተጠቀመበት ነበር።

የ2008 ዓም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቅያ ፈተና መሰረቅን በተመለከተ 

በሐምሌ 3፣2008 ዓም የተጀመረው የሁለተኛ ደረጃ መልቀቅያ ፈተና መሰረቅን በተመለከተ ኢሳት መረጃውን ከማግኘቱም በላይ የተወሰኑ ፈተናዎች ሙሉ ጥያቄ እጁ እንደገባ ገልጧል።ሆኖም ግን ቀደም ባለው ወር ውስጥ ድጋሚ ፈተናው ከመሰረቁ በፊት የፈተና ውጤቱን እንዳሰራጩት ፈተናውን ለሕዝብ አልለቀቀም።ኃላፊነት በተሰማው መንገድ የፈተናው አዘጋጅ የትምህርት ሚኒስቴር ጉዳዩን ትኩረት ሰጥቶ እንዲመለከት እና መሰረቅ አለመሰረቁን እንዲያረጋግጥ ከመጠየቅ ባለፈ ፈተናውን ከኢትዮጵያዊ ኃላፊነት ውጭ ለአየር አለማብቃቱ ኢሳት በእውነትም በመጪው ጊዜያት ኢትዮጵያ እንደ አገር ለሚገጥሟት ችግሮች ሁሉ ኃላፊነት በተሰማው መልኩ የሚሰራ ለመሆኑ ሌላው ማረጋገጫ ሆኖ አልፏል።

ባጠቃላይ የመገናኛ ብዙሃን በአንድ አገር ፖለቲካው፣ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ሕይወት ላይ የሚኖረው ተፅኖ በተለይ አሁን በምንኖርበት ዘመን ከፍተኛ ነው። በአሁኗ ኢትዮጵያ በየትኛውም የዓለም ጫፍ እና በአገር ቤት የሚኖረው ሕዝብ የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያ ነክ ዜናዎችን በማመን የሚሰማው የመረጃ ምንጭ ኢሳት ነው። አሁን በስልጣን ላይ የሚገኙ በለስልጣናት ምሽት ላይ በራቸውን ዘግተው የሚከታተሉት ኢሳት ለመሆኑ በርካታ መረጃዎች ወጥተዋል።በመግብያው ላይ እንደተገለጠውም ከዓለም አቀፍ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ እስከ ገጠር በጀነሬተር መብራት እስከሚያገኘው የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢሳት ላይ ከፍተኛ እምነት አላቸው። ኢሳትም ኃላፊነት በተሰማው መልኩ መስራቱ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ኩራት ብቻ ሳይሆን ከነፃነት በኃላ ኢትዮጵያ የሚኖራት የመገናኛ ብዙሃን ብቃት በችግር ጊዜ ተፈትኖ ያለፈ እና ስሜታዊነትን ባራቀ መልኩ የሚሰራ ለመሆኑ ሌላው ማረጋገጫ ነው። እናመሰግናለን ኢሳት!


ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

Saturday, July 9, 2016

ሰበር ዜና - በደቡብ ሱዳን ቤተ መንግስት በታንክ የታገዘ ውግያ ተካሄደ


ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር፣ ምክትላቸው ርክ ማቻር እና ሌላው ምክትል ጀምስ ዋኒ  ከግጭቱ በኃላ በጋራ መግለጫ ሲሰጡ (ፎቶ ሱዳን ትሪቡን)


በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ የሚገኘው  ቤተ መንግስት የፕሬዝዳንት ሳልቫኪር እና ምክትላቸው ሪክ ማቻር ልዩ ጥበቃ አባላት መዋጋታቸው ተሰምቷል። ከአንድ መቶ በላይ ወታደሮች የተሳተፉበት ነው የተባለው ይህ ግጭት  በታንክ የታገዘ እንደነበር የሱዳን ትሪቡን ጋዜጣ  ዓርብ፣ሐምሌ 2/ 2008 ዓም ዘግቧል። የአርብ ዕለቱ ግጭት ሲደረግ በቤተ መንግስት ውስጥ ሁለቱ የቀድሞ ባላንጣ መሪዎች ቀደም ብሎ ሐሙስ እለት በነበረው የፕሬዝዳንት ኪር ሶስት ወታደሮች ግድያ  ጉዳይ ላይ ሶስቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ማለትም ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር፣ ምክትላቸው ሪክ ማቻር እና ሌላው ምክትል ጀምስ ዋኒ ውይይት ላይ እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል።ከግጭቱ በኃላ ሶስቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ ሲሆን በመግለጫቸውም ህዝቡ እንዲረጋጋ ተማፅነዋል።

 ከሁለቱ ግጭቶች  በኃላ ጉዳዩን የሚያጣራ አጣሪ ኮሚቴ አርብ ሐምሌ 2/ 2008 ዓም መመስረቱ እና የኮሚቴው መሪ የአገሪቱ የአገር ውስጥ ሚኒስትር ሌ/ጀነራል አልፍሬድ ላዶ ጎሬ መሆናቸውን ዋሽንግተን የሚገኘው የደቡብ ሱዳን ኤምባሲ መግለጫ ማሳወቁን የሱዳን ትሪቡን ዜና አክሎ ገልጧል።  

በሌላ በኩል የደቡብ ሱዳን ዜና አገልግሎት ድረ-ገፅ ምንም አይነት መረጃ ያልሰጠ ሲሆን ድረ-ገፁ በጦርነቱ ወቅት ከነበረበተ የተሻለ መረጃ ምንጭነት በአሁኑ ወቅት የታፈነ በሚመስል መልኩ የቆዩ ዜናዎች ብቻ በገፁ ላይ መታየታቸው ደቡብ ሱዳን በባሰ ውጥረት ውስጥ መሆኗ ሌላው አመላካች ነጥብ መሆኑን ለማወቅ ይቻላል።

የደቡብ ሱዳን የፀጥታ ሁኔታ ለህወሓት ትልቅ የእራስ ምታት የሆነበት እና የስርዓቱ ተቀናቃኞች ትጥቅ እና ስንቅ ማቀባበያ እንዳይሆን የሚል ስጋት አለበት።በደቡብ ሱዳን ጉዳይ እጃቸውን ያስገቡ የአካባቢው አገራት መብዛት እና የደቡብ ሱዳን የፀጥታ ጉዳይ የአሜሪካን፣አውሮፓ ህብረት እና ኖርዌይን የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ኃይሎችን የሳበ መሆኑ የደቡብ ሱዳን የፀጥታ ሁኔታ ያለውን ተፅኖ ፈጣሪነት መረዳት ይቻላል። 

የዜናው ምንጭ - ሱዳን ትሪቡን ሐምሌ 2፣ 2008 ዓም

ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Saturday, July 2, 2016

የሃይማኖት አባቶች በአዲስ አበባ በፈረሱት ቤቶች ዙርያ ዝም ሊሉ አይገባም። (የጉዳያችን አጭር ማስታወሻ)

ቤታቸው ፈርሶ ሜዳ ላይ የተበተኑ ኢትዮጵያውያን አዲስ አበባ ላፍቶ ሰኔ/ 2008 ዓም 
  • ለእዚህ ያህል ሕዝብ ላለቀሰበት፣ለሞተበት እና ለተሰደደበት ጉዳይ የሃይማኖት አባት ስሜቱ ተነክቶ ጉዳዬ ብሎ መግለጫ አለመስጠት፣ሄዶ አለማፅናናት፣ በዳዮችን በግልፅ አለመውቀስ ትልቅ የሞራል ውድቀታችን አንዱ ማሳያ ነው።


በአዲስ አበባ ከገርጂ እስከ ቡራዩ በሺህ የሚቆጠሩ ቤቶች በስርዓቱ ፈርሰዋል።በተለይ ሰሞኑን ከላፍቶ ቀርሳ ኮንቶማ ከ30 ሺህ ሕዝብ በላይ ቤት እየፈረሰ ነው።በእዚህ ሂደት ሁለት ቀሳውስት ጨምሮ አብያተ ክርስትያናት የመፍረስ ዕጣ ተፈርዶባቸው ምናልባት ሰዓታት እየጠበቁ ነው አልያም ፈርሰዋል።የኢሳት ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ከስፍራው ያነጋገራቸው አዛውንት አናግሮ የገለፁለትን በፌስ ቡክ ገፁ አርብ ሰኔ 24/ 2008 ዓም እንደሚከተለው ገልፆታል 

´´ ከላፍቶ ቀርሳ ኮንቶማ አንድ አባት አናግሬ መጨረሴ ነው። ስሜት ይረብሻል። እውነት በመዲናችን፡ በአፍሪካ መናገሻ፡ በአዲስ አበባ እንዲህ ዓይነት ግፍ ሲፈጸም መስማት ያማል። አባት እንደሚሉት የ3 ቀናት አራስ እቤቷ እንዳለች ላይዋ ላይ ቤት አፍርሰው ህይወቷ አልፏል። ሁለት ቄሶች በፖሊስ ጥይት ተገድለዋል። 2 ህጻናት በግርግር በአከባቢው በሚገኝ ወንዝ ገብተው ሞተዋል። በርካታ ወጣቶች በድብደባ ብዛት አቅላቸውን ስተው ህክምና ተነፍገው በፖሊስ ጣቢያ ስቃይ ላይ ናቸው።´´


አዲስ አበባ የሚታተመው አዲስ አድማስ በቅዳሜ ሰኔ 25/2008 ዓም ´´20 ሺ ቤቶች በሚፈርሱበት ክ/ከተማ የሰዎች ህይወት አልፏል´´ በሚል ርዕስ ባወጣው ዘገባ ላይም የድርጊቱን ግፍ በትትክክል የሚያሳይ ነው።ባጠቃላይ ጉዳዩ ፀሐይ የሞቀው ዜና ነው። ሕዝብ እያለቀሰ ነው።መሬቱን እየተነጠቀ ንብረቱን ሳያወጣ በላዩ ላይ ቤቱ ሲፈርስ እሪ! እያለ ነው።ይህንን ግፍ ለመቃወም የሃይማኖት አባቶች ሚና ቀላል አይደለም።በእዚህ የጭንቅ ሰዓት ሕዝብ የሃይማኖት አባቶቹን ሲመለከት ይፅናናል።የሃይማኖት አባቶች በቦታው ላይ በመገኘት የሚከተሉትን ተግባራት መስራት ይችላሉ።

1/ በቦታው ተገኝቶ በፈረሱት ቦታዎች ሕዝቡን በሃይማኖት ሳይለዩ ማፅናናት፣

2/ ተግባሩን መኮነን ይህም በቃል እና በፅሁፍ ለሚመለክተው ባለስልጣናት መግለፅ ይህንንም ለሚድያ መግለፅ እና 

3/ ሜዳ ላይ ለተበተኑት አፋጣኝ እርዳታ እንዲደርስ የአዲስ አበባ የሃይማኖት አባቶችን ማስተባበር እና ማድረስ የሚሉት ቀዳሚ ናቸው።

ባጠቃላይ እነኝህ ተግባራት እጅግ በጣም አስፈላጊ እና ወሳኝ ተግባሮች ናቸው።ይህንን ማድረግ ከስርዓቱ ግልምጫ ያስከትል ይሆናል። ሆኖም ግን ሕዝብ የማዳን ሥራ ነው እና ሌላ ምንም አይነት አማራጭ መንገድ የለውም።ከሁሉም የሚገርመው ቤተ ክርስቲያን እንደሚፈርስ እየተነገረ እና ሁለት ቄሶች መሞታቸው እየታወቀ ዝም መባሉ ነው። የዝምታው ጥግ የት ነው? ድሃ ተበደለ ፍርድ ጎደለ ብሎ መጮህ የማን ሥራ ነው? ዛሬ ያልጮህንለት ሕዝብ ነገ ሰው በላው ስርዓት ወደ እራሳችን ሲመጣ (ይህ አይቀርምና) የትኛው ሕዝብ ከእኛ ጋር ይቆማል? ብሎ ማሰብ ተገቢ ነው እና ጊዜ ሊሰጠው አይገባም።ለእዚህ ያህል ሕዝብ ላለቀሰበት፣ለሞተበት እና ለተሰደደበት ጉዳይ የሃይማኖት አባት ስሜቱ ተነክቶ ጉዳዬ ብሎ መግለጫ አለመስጠት፣ሄዶ አለማፅናናት፣ በዳዮችን በግልፅ አለመውቀስ ትልቅ የሞራል ውድቀታችን አንዱ ማሳያ ነው።

ጉዳያችን GUDAYACHN

 www.gudayachn.com

Friday, July 1, 2016

የሃይማኖት አባቶች ብታውቁበት ሀብታሙም የንስሐ ልጃችሁ ነበር (የጉዳያችን አጭር ማስታወሻ)

ሀብታሙ አያሌው 
  • የሃይማኖት አባቶች  ዛሬ ሀብታሙን ልጄ አደለም አላውቀውም ብለው መካዳቸው እንደ ጴጥሮስ መክዳት ያለ ግን  ዶሮ እስኪጮህ  ድረስ ብቻ  የሚቆይ መሆኑን አላውቁትም 
ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ተመልሶ መምጣቱ እና እውነተኛ ፍርድ የሚሰጥበት ጊዜ ከመምጣቱ በፊት በዓለም ላይ ምን አይነት ምልክት እንደሚታይ ያሳወቀበት የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 24 እና 25 አንዱ ነው። በእነኝህ የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ውስጥ ሐሰተኛ ነቢያት እንደሚነሱ ከተቻላቸው የተመረጡትን ሁሉ እንደሚያስቱ ይገልፃል።
በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 25 ቁጥር 41 ላይ እንዲህ ይላል : - 
«ጌታ ሆይ፥ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህስ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ? እንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህ? ወይስ ታርዘህ አይተን መቼ አለበስንህ? ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ አይተን መቼ ወደ አንተ መጣን?» ይሉታል። እርሱምመልሶ በሕይወት ዘመናቸው ከእነርሱ ለሚያንሱት ያደረጉትን መልካም የቸርነትና ትህትናሥራ እንደዋጋ ቆጥሮላቸው «እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት» ማቴ 25፣41

የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሀብታሙ ፣በህወሓት እስር ቤት የማቀቀው ሀብታሙ፣ በአንድ ወቅት አቶ መለስ በብሩህ አእምሮው ያደነቁት እና እንደሚፈሩት ያሳበቀባቸው ሀብታሙ፣ የዛሬውን የአልጋ ላይ ተኝቶ በህመም የሚሰቃየው ሀብታሙን ተገብተን ከላይ የተፃፈውን ጥቅስ እንመልከተው።

የሃይማኖት አባቶች ልጆቻቸውን በዘር በአካባቢ ትውልድ፣ቤተ መንግስት ያለውን ሰው ፊት እየተመለከቱ በሽተኛ የሚጠይቁ መሆን አለበት? የሃይማኖት አባቶችን አድር ባይነት በየዘርፉ ጠግበነዋል። ይህንን አድርባይነት በዝምታ ሽንገላ እግዚአብሔርን መደለል ከተቻለ ጥሩ ነው።ኢየሱስ ክርስቶስ ለሀብታሙ ያደረጋችሁት ለእኔም አደረጋችሁት የለናል።ለሃይማኖት የፓርቲ እና የአመለካከት መለክያ እንደ መስፈርት ከተቀመጠ ይህንን ዓለም ማን ሊዳኛት ነው? 

አድር ባይነትን በእጃቸው በያዙት መስቀል ሸፍነው ጌቶቻቸው አይዟችሁ እንዲሏቸው እና ሃቀኛ መስለው በመታየት የሃይማኖት አባቶች ዛሬ ሀብታሙን ገፍተውታል። ሀብታሙን ሄዶ ሆስፒታል መጠየቅም ሆነ ሕክምና ይፈቀደለት ብሎ መጠየቅ ከጮማው እና ከቀይ ወይን ብሎም ከምሽት ውስኪ ያጎድላል እና ማንም የሃይማኖት አባት ተብዬ ለሀብታሙ የሚጮሁትን ሁሉ አይሰሙም።ሀብታሙም የንስሐ ልጄ አይደለም ማለት ለጊዜው ከባለ ጊዜዎች ሙገሳ እና የጀግና መዳልያ ያሰጣልና የሃይማኖት አባቶች አይናቸውን ሳያሹ አላውቀውም ለማለት እየዳዳቸው ነው።

አሁን ያለንበት ዘመን መስሎ አዳሪ፣ለጥቅም እና ለይሉኝታ የገዛ ልጁን የሚገፋ የሃይማኖት አባት የሞላበት ነው።ከመንግስት ጋር የሚያጣላ የመሰለው ልጁ ነገ አገር ቤት ያለው ጥቅም ያሳንሳል አለፍ ሲል በዘመኑ ገዢዎች ፊት ያስነሳል እና ሀብታሙን መራቅ ብቸኛ አማራጭ ነው።ይህ ግን የሃብታሙን ክብር አይነካውም።ይልቁንም በእግዚአብሔር ዘንድ የበለጠ ክብር በሰው ዘንድም ሞገስን ከአምላኩ ይቀበልበታል።ለአመታት በጨበጡት መስቀል ለሕዝብ አንዳች ነገር ያልሰሩ የገበታ ላይ ወሬ አድማቂዎች የሃይማኖት አባት ተብዬዎች ግን አድር ባይነታቸው እንዳየለባቸው ፀሐይ ትጨልምባቸዋለች። ቢያውቁበትማ ኖሮ  ሀብታሙን መጠየቅ ሕክምና ይፈቀድለት ማለት ከማቴዎስ ወንጌል የክርስቶስ ቃል ጋር መስማማት መሆኑን በተረዱት እና በተጠቀሙበት ነበር።የእነርሱ መንደር ልጅ ያልሆነው ሀብታሙ ግን ዛሬ የእነርሱ ልጅ አይደለም።በሚስጥር የሚገናኙት  ከአራት ኪሎ ጌቶቻቸው ጋር ነው።በእነርሱ ቤት ይህንን ዓለም አያውቅም። የሃይማኖት አባቶች  ዛሬ ሀብታሙን ልጄ አደለም አላውቀውም ብለው መካዳቸው እንደ ጴጥሮስ መክዳት ያለ ግን  ዶሮ እስኪጮህ  ድረስ ብቻ መሆኑን አላውቁትም።ዶሮ ይጮሃል! አይዘገይም ማን ለወያኔ አድሮ ማንን እንዳሳደደ፣ማን ለሕዝብ ቆሞ ኢትዮጵያን እንዳላቆሰለ የሚለይበት ቀን አይዘገይም።


ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

ለፕሮፌሰር መራር፣ልደቱ፣ጀዋርና ኢንጅነር ይልቃል ዘፈን ይህችን ዜማ እንምረጥላቸው።

በቅድምያ ስለ አራቱም የመግቢያ ማስታወሻና ወቅታዊ ሁኔታቸው። አራቱም ከመስከረም በኋላ መንግስት የለም ብለው ኢትዮጵያን ለእርስ በርስ ጦርነት ሊነክሯት ሞክረዋል።ዝርዝሩን፣ከእነማን ጋር መክረው እንደነበር፣ለኢትዮጵያ ደግሰው...