ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር፣ ምክትላቸው ርክ ማቻር እና ሌላው ምክትል ጀምስ ዋኒ ከግጭቱ በኃላ በጋራ መግለጫ ሲሰጡ (ፎቶ ሱዳን ትሪቡን)
በደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ የሚገኘው ቤተ መንግስት የፕሬዝዳንት ሳልቫኪር እና ምክትላቸው ሪክ ማቻር ልዩ ጥበቃ አባላት መዋጋታቸው ተሰምቷል። ከአንድ መቶ በላይ ወታደሮች የተሳተፉበት ነው የተባለው ይህ ግጭት በታንክ የታገዘ እንደነበር የሱዳን ትሪቡን ጋዜጣ ዓርብ፣ሐምሌ 2/ 2008 ዓም ዘግቧል። የአርብ ዕለቱ ግጭት ሲደረግ በቤተ መንግስት ውስጥ ሁለቱ የቀድሞ ባላንጣ መሪዎች ቀደም ብሎ ሐሙስ እለት በነበረው የፕሬዝዳንት ኪር ሶስት ወታደሮች ግድያ ጉዳይ ላይ ሶስቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ማለትም ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር፣ ምክትላቸው ሪክ ማቻር እና ሌላው ምክትል ጀምስ ዋኒ ውይይት ላይ እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል።ከግጭቱ በኃላ ሶስቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ ሲሆን በመግለጫቸውም ህዝቡ እንዲረጋጋ ተማፅነዋል።
ከሁለቱ ግጭቶች በኃላ ጉዳዩን የሚያጣራ አጣሪ ኮሚቴ አርብ ሐምሌ 2/ 2008 ዓም መመስረቱ እና የኮሚቴው መሪ የአገሪቱ የአገር ውስጥ ሚኒስትር ሌ/ጀነራል አልፍሬድ ላዶ ጎሬ መሆናቸውን ዋሽንግተን የሚገኘው የደቡብ ሱዳን ኤምባሲ መግለጫ ማሳወቁን የሱዳን ትሪቡን ዜና አክሎ ገልጧል።
በሌላ በኩል የደቡብ ሱዳን ዜና አገልግሎት ድረ-ገፅ ምንም አይነት መረጃ ያልሰጠ ሲሆን ድረ-ገፁ በጦርነቱ ወቅት ከነበረበተ የተሻለ መረጃ ምንጭነት በአሁኑ ወቅት የታፈነ በሚመስል መልኩ የቆዩ ዜናዎች ብቻ በገፁ ላይ መታየታቸው ደቡብ ሱዳን በባሰ ውጥረት ውስጥ መሆኗ ሌላው አመላካች ነጥብ መሆኑን ለማወቅ ይቻላል።
የደቡብ ሱዳን የፀጥታ ሁኔታ ለህወሓት ትልቅ የእራስ ምታት የሆነበት እና የስርዓቱ ተቀናቃኞች ትጥቅ እና ስንቅ ማቀባበያ እንዳይሆን የሚል ስጋት አለበት።በደቡብ ሱዳን ጉዳይ እጃቸውን ያስገቡ የአካባቢው አገራት መብዛት እና የደቡብ ሱዳን የፀጥታ ጉዳይ የአሜሪካን፣አውሮፓ ህብረት እና ኖርዌይን የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ኃይሎችን የሳበ መሆኑ የደቡብ ሱዳን የፀጥታ ሁኔታ ያለውን ተፅኖ ፈጣሪነት መረዳት ይቻላል።
የዜናው ምንጭ - ሱዳን ትሪቡን ሐምሌ 2፣ 2008 ዓም
ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com
No comments:
Post a Comment