ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, August 27, 2014

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር፣ የግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እና የአማራ ዲሞክራሲ ኃይሎች ንቅናቄ የውህደት ስምምነትን በተመለከተ -የዜናው ይዘት፣ የውህደቱ ደረጃ ፣ውህደቱ በምን ያህል ፍጥነት እንደሚጠናቀቅ እና የውህደቱ ዜና በኢትዮጵያውያን እና በውጭ ኃይላት ዘንድ የሚኖረው ትርጉም (የጉዳያችን ጡመራ አጭር ጥንቅር)


ዜናው 

ነሐሴ 19/2006 ዓም ምሽት የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን (ኢሳት) በሰበር ዜናነት የሚከተለውን ዜና አሰማ -
''በስልጣን ላይ ያለውን የኢህአዲግ መንግስት በተለያየ መንገድ ሲታገሉ የነበሩ ድርጅቶች ወደ ውህደት የሚያደርሳቸውን ስምምነት ተፈራረሙ።ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር፣ የግንቦት7 የፍትህ፣የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እንዲሁም የአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ ናቸው።ድርጅቶቹ በጋራ ባወጡት መግለጫ ትግላቸውን በአንድነት አቀናጅተው እንደሚንቀሳቀሱ አስታውቀዋል” ይላል። 
ድርጅቶቹ ያወጡት መግለጫ ይህንን በመጫን ይመልከቱ።
ከእዚህ ጋር ተያይዞ ሰሞኑን የወጡ ዘገባዎች የውህደቱን ደረጃ እና በምን ያህል ፍጥነት እንደሚከናወን የሚገልጡ ናቸው።

የውህደቱ ደረጃ 

ነሐሴ 20/2006 ዓም የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ምክትል ሊቀመንበር አቶ አበበ ቦጋለ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሊቀመንበር አቶ መዓዛ ጌጡ የውህደቱን ደረጃ አስመልክተው ለኢሳት ራድዮ በሰጡት መግለጫ የውህደቱ ደረጃ -
1/ ድርጅቶቹ ሙሉ በሙሉ ተዋህደው የቀድሞ ድርጅቶች ከስመው ሶስቱም አንድ ድርጅት እና በአንድ አመራር ስር እንደሚሆኑ፣
2/ አቶ አበበ የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ምክትል ሊቀመንበር ቃል በቃል እንዳስቀመጡት ''ዋናው ዓላማ ብሔራዊ የሆነ ነፃ አውጪ ኃይል መፍጠር'' መሆኑን መግለፃቸውን እና 
3/ የሶስቱም ድርጅቶች ሰራዊት በአንድ ዕዝ ስር እንደሚገቡ ገልፀዋል። 

ውህደቱ በምን ያህል ፍጥነት እንደሚጠናቀቅ

የብዙዎች ጥያቄ የሆነው ውህደቱ በምን ያህል ፍጥነት የከናወናል? የሚለው ነው።ለእዚህ ጥያቄ የኢሳቱ ጋዜጠኛ አቶ መሳይ ለአቶ አበበ ቦጋለ የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ምክትል ሊቀመንበር ''ምናልባት የውህደቱን ጊዜ በጊዜ ማስቀመጥ ይቻላል?'' በሚል ላቀረበው ጥያቄ አቶ አበበ እንዲህ መልሰዋል -
''.....ይህ ውህደት በዓላማ እና በራዕይ ተመሳሳይ በሆኑ ድርጅቶች መካከል የተደረገ ነው.........አሁን ሂደታችንን በተመለከተ የውህደት ኮሚቴ ተመስርቷል ውህደቱን በወራት ምናልባት ቢዘገይ እሰከመጪው ጥቅምት 30 እንደ ኤውሮፓውያን አቆጣጠር ይጠነቀቃል ብለን እናስባለን.....ውህደታችን በጉልበት፣በገንዘብ እና በንብረት የተሻለ አቅም ይፈጥራል።በሂደትም ከሌሎች ድርጅቶች እንደ ትግራይ የነፃነት ድርጅት ጋር በጥምረትም ሆነ በትብብር የምንሰራበት ሁኔታ ይኖራል'' ብለዋል።

የውህደቱ ዜና በኢትዮጵያውያን እና በውጭ ኃይላት ዘንድ የሚኖረው ትርጉም 

የውህደቱ ዜና በኢትዮጵያውያን ዘንድ ትልቅ መደመምን ፈጥሯል።በርካታ ተቃዋሚ ድርጅቶች በአንድነት መዋሃድ ሲሳናቸው ለዓመታት የሰማ ሕዝብ የሰሞኑ ዜና በትልቅ ብስራትነት ቢመለከት ቢያንሰው እንጂ አይበዛበትም።ይህ ጉዳይ ግን በውጭ ኃይላት ዘንድ የሚኖረው ትርጉም እንደሚለያይ መገመት ብዙም አስቸጋሪ አይደለም።በኢትዮጵያ ላይ ስልታዊ ጥቅም ያላቸው ኃይሎች ካላቸው ጥቅም አንፃር ለውህደቱ የሚሰጡት ትርጉም የተለያየ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው።
አንድ ነገር ግን ከወዲሁ ማለት ይቻላል።በተለይ የውጭ ኃይሎችን በተመለከተ።ይሄውም ሁሉም የውጭ ኃይሎች ባላቸው መረጃ የሚያረጋግጡት ጉዳይ አሁን በስልጣን ላይ ያለው ኢህአዲግ/ወይኔ የህዝብ ድጋፍ የራቀው ብቻ ሳይሆን እርስ በርሱም በሙስና፣በርዕዮት ዓለም ቀውስ እና በስልጣን ሽምያ ችግር ውስጥ መሆኑን እና ወደውድቀት እያመራ ያለ መሆኑን ነው።
በሃያላኑ አንፃር ግን ጉዳዩ ከእዚህም እንደሚዘል ይታሰባል።የሄውም የለውጥ ተዋናይ የሆኑት ድርጅቶች  በኢትዮጵያ የሚያመጡት ለውጥ የሃያላኑን ጥቅም በአፍሪካ ደረጃም የሚጎዳ እንዳይሆን ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ቀንድ እና የመካከለኛው ምስራቅ አካባቢ  ካንዣበበባቸው የፅንፈኛ እስልምና ኃይሎች ነፃ መሆኑን ማረጋገጥ ላይ ትኩረት መስጠታቸው አይቀርም።
በመሆኑም ውህደት የፈጠሩት ኃይሎች በዓለም ዓቀፉ የዲፕሎማሲ መድረክ ላይ ተሰሚነትን የማግኘቱን ሂደት የውጭ ኃይሎችን ጥቅም  በማያስደነብር መልኩ ግን ደግሞ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና ዘለቄታዊ ጥቅም ባስከበረ አቀራረብ ዓለም አቀፉን ማሕበረሰብ የማማለል እና ኢትዮጵያ ውስጥ ላሉት ፖለቲካዊ ችግሮች በአማራጭ ኃይልነት ቶሎ እራሳቸውን ማቅረብ አለባቸው።ይህ እንግዲህ በሀገር በት ከሚኖረው ዋናው ትግል ጎን ለጎን የሚካሄድ ይሆናል ማለት ነው።

ጉዳያችን 
ነሐሴ 22/2006 ዓም (ኦገስት 28/2014)





የእዚህ ትውልድ የሰላማዊ ትግል ገድል በሚገባ የተገለፀበት ሊመለከቱት የሚገባ አዲስ ልዩ ጥናታዊ ፊልም።የፊልሙ ርዕስ- ‹‹የፀረ ሽብር ህጉ ሰለባዎች ››በፍኖተ ነፃነት ዝግጅት ክፍል የተዘጋጀ

''በጥፍሩም በጥርሱም ለስልጣኑ የሚተጋን መንግስት በሁሉን አቀፍ ትግል መጣል አለብን ብለው ጠብ መንጃ ቢያነሱ ክፋቱ ምን ላይ እንደሆነ አልታይህም እያለኝ ነው፡፡ ለምን በጠብ መንጃ ፍልሚያ ስልጣን መያዝ እንዳለብኝ በግሌ ባይገባኝም አሁን ግን የኢህአዴግ ዓይነት መንግሰት ከደርግ እንዴት እንደሚሻል ማሰብ እያቃተኝ ነው፡፡ የሰላማዊ ትግል ሰራዊት እንዴት እንገንባ ለሚለው ጥያቄ አፋጣኝ ምለሽ ካልሰጠን በስተቀር መንግሰት በግልፅ እየደገፈ ያለው በጠብ መንጃ ሊገዳደሩ የፈለጉት ነው፡፡ በሰላም ያልነውን ሰላም እየነሳን ይገኛል፡፡ መንግሰት ሆይ ሰላም እንድትሆን ሰላም ሰላም ለምንል ዜጎች ሰላም ሰጠን የምር የቀረበ ጥያቄ ነው'' ብቸኛው ተቃዋሚ የፓርላማ አባል የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ ሰሞኑን በጡመራ ገፃቸው ላይ ከፃፉት የተወሰደ


ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

Monday, August 25, 2014

''የአፄ ኃይለ ስላሴ ውርስ ጠንካራ እና ሕጋዊ እንደሆነ ቀጥሏል'' የቻይናው ሲሲቲቪ በቅርቡ ከለቀቀው ፊልም ግርጌ ከተፃፈው ማስታወሻ። የቻይናው ሲሲቲቪ ''የአፍሪካ ገፅታ'' በተሰኘው ፕሮግራሙ ''ኃይለ ስላሴ የዘመናዊት ኢትዮጵያ መስራች አባት'' (Haile Selassie: The pillar of Ethiopia) በሚል ርዕስ ስር የሰራው አስደናቂ ጥናታዊ ፊልም ለዘመናችን ባለስልጣናትም ሆነ ትውልድ አስተማሪ ነው።Faces Of Africa - Haile Selassie: The pillar of Ethiopia, part 1 & 2 CCTV (ቪድዮውን ይመልከቱ)

ማንኛውም መሪ መቶ በመቶ ትክክል ሊሰራ አይችልም ግን ከ 80 በመቶ በላይ መልካም ሥራ ቢሰራ የቀረው ''ስህተት'' የተባለውም ለሀገሩ ካለው ፍቅር የሰራው ከሆነ ይህ መሪ ታላቅ ነው።
አፄ ኃይለ ስላሴ ከስልጣን ከወረዱ በመጪው መስከረም 2/2007 ዓም ሙሉ አርባ ዓመት ይሞላቸዋል።ዛሬም ግን ታሪክ እየጎለጎለ የሚነግረን ለኢትዮጵያ ታላቅ ሥራ የሰሩ መሪ መሆናቸውን ነው።
የምዕራቡ ዓለም መገናኛ ብዙሃን ብዙ ብለዋል።እንደ ''ታይም'' አይነት መፅሄቶች''የመቶ ዓመቱ ታላቅ ተፅኖ ፈጣሪ'' ብለው አወድሰዋቸዋል።ለነገሩ የታሪካችን አካል የሆኑ መሪን ማንነት የባዕዳን መገናኛ ብዙሃን እና ፀሐፍያን ሲመሰክሩልን ብቻ የምናምን ሲያብጠለጥሉ ደግሞ ዝቅ የማድረግ አባዜ ሊጠናወተን አይገባም።አፄ ኃይለሰላሴን በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ዘመናዊ ታሪክ ላይ ያላቸውን አሻራ የዘገቡልን በሁሉም ርዕዮተ ዓለም ውስጥ ያሉ ሃገራት መሆናቸው ጉዳዩ ምን ያህል ተአማኒ መሆኑን አመላካች ነው።ለምሳሌ የዛሬውን የታሪክ ዘገባ የቀረበው  የቻይናው ታዋቂው  ቴሌቭዥን ''ሲሲ ቲቪ'' ነው።ቪድዮውን ይመልከቱት።

Haile Selassie I (1892 -1975)
ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

Sunday, August 17, 2014

Thursday, August 14, 2014

Monday, August 11, 2014

ከኢህአዲግ/ወያኔ መላቀቅ ማለት ከድንቁርና ነፃ መውጣት ነው!



ሰሞኑን የኢህአዲግ/ወያኔ የኮምንኬሽን ሚኒስትር ዴታ የነበሩት አሁን በስደት የሚገኙት አቶ ኤርምያስ ለገሰ የሰጡትን መግለጫ  በኢሳት ቴሌቭዥን እየተከታተልኩ ነበር።አቶ ኤርምያስ ከተናገሩት ውስጥ የኢህአዲግ/ወያኔ አመራሮችም ሆኑ ቡድኑ ባጠቃላይ የተማሩ ኢትዮጵያውያንን ለምን እንደሚያሳድድ ያስረዱበት መንገድ ሚዛን የሚደፋ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።አቶ ኤርምያስ ኢህአዲግ/ወያኔ በመመርያው ውስጥ የተማሩ አባላት ከ 1% እንዳይበልጡ ለምን እንደሚደረግ እና ባጠቃላይ ድርጅቱ የተማሩ ኢትዮጵያውያንን የሚጠላበትን መሰረታዊ ምክንያት ሲያስረዱ እንዲህ ነበር ያሉት (ቃል በቃል ባይሆንም ሃሳቡን እንዲህ ይገለፃል) -
  ''ማየት ያለብን ድርጅቱን የሚመሩት ሰዎች አነሳስን ነው።እነኝህ ሰዎች ገና የ 16 እና 17 ዓመት ልጆች ሆነው ከግብርና ተነስተው (ግብርና የተከበረ ሙያ መሆኑን ሳንዘነጋ) ወደ ውግያ ገቡ።ዋናውን የወጣትነት ጊዜ ማለትም እውቀት የሚቀሰምበት እና የህዝቡን ማህበራውም ሆነ ቤተሰባዊ ሕይወት በማወቅያቸው ጊዜ ሁሉ ለአስራ ምናምን ዓመት የሚያውቁት መተኮስ ነው።አሸንፈው ቤተመንግስት ሲገቡ የመማርያ ጊዜ አልፏል።እኛ ያለፍንበትን የቤተሰብ ሕይወት እና ምክንያታዊነት ላይ የተመሰረተውን የዕውቀት መገብየት ዘመን አያውቁትም።ትምህርት ቤት አያውቁም፣ማህበራዊ ኑሮ አያውቁም።በመሆኑም  የተማረ ሰው አዲስ ሃሳብ ይዞ ከመጣ ይገለብጠናል ብለው ይሰጋሉ።'' ነበር ያለው።ሚዛን የሚደፋ አገላለፅ ነው። 
ይህንን የአቶ ኤርምያስ አባባል በሰማሁበት ሰሞን ዛሬ ደግሞ ''የአዲስ ጉዳይ'' መፅሄት ባለቤት እና ሶስት አዘጋጆች የመሰደዳቸው ዜና ተሰማ።የጋዜጠኞች መሰደድ እና የግል ሕትመት ውጤቶች መዘጋት በዘመነ ኢህአዲግ/ወያኔ የተለመደ ዜና መሆኑ ይታወቃል። ነገር ግን የሕትመት ውጤቶችን መዝጋት ከፖለቲካዊ አንደምታው በዘለለ የኢህአዲግ/ወያኔ ትውልዱን አደንቁሮ የመግዛት እቅዱ አካል መሆኑን ልብ ማለት ተገቢ ነው።

1/ ''ትምህርት በአብዮታዊ ዲሞክራሲ መጠመቅ ብቻ ነው'' ኢህአዲግ/ወያኔ 

ዕውቀትን በመግደል ኢህአዲግ/ወያኔን የሚተካከለው የለም።የተማረው ክፍል ከአብዮታዊ ዲሞክራሲው ጫማ ስር ተንበርክኮ የምልኮሰኮስ እንዲሆን ለማድረግ ሃያ ሶስት ዓመታት ሙሉ ስታትር ተስተውሏል።እዚህ ላይ የዩንቨርስቲ ቁጥር መጨመር ግን በጥራት የወረዱ መሆናቸውን ብቻ ሳይሆን የትምህርት ደረጃው ባጠቃላይ ከሳሃራ በታች ካሉት ሀገሮች ጋርም መወዳደር የማይችል ደረጃ የደረሰው በዘመነ ኢህአዲግ/ወያኔ ነው።
 የዩንቨርስቲ ቁጥር ጨመርኩ ባለበት አፉ  የትምህርት ጥራትን መግደሉን እራሱ ኢህአዲግ/ወያኔም  በተለያየ መድረክ አረጋግጧታል።
እንደ 'እስስት' የሚቀያየረው የትምህርት ፖሊሲ በአንድ ሀገር የምንኖር መሆናችን ግራ እስኪገባን ድረስ አንዴ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እስከ 10ኛ ሆነ።ሌላ ጊዜ የለም እስከ 12ኛ ክፍል አደረግነው። መልሰው ደግሞ የሶሻል ትምህርት 30% ሆነ፣ወዘተ እየተባለ በበቂ ጥናት ላይ ያልተመሰረተ የተደናገሩ ዓመታት ሰለባ የሆነው ይሄው ትውልድ ነው።
መምህራን ግራ ተጋብተው ''በአብዮታዊ ዲሞርክራሲ ማደናገርያ ተጠመቁ'' ተብለው በተማሪ ካድሬ እንዲመሩ እና እንዲሸማቀቁ የተደረጉት ብቻ ሳይሆን እነኝሁ ትውልድ ቀራጮች እንባ አውጥተው ሲያለቅሱ የታዩት አሁንም በኢህአዲግ/ወያኔ ዘመን ነው።

2/ ''ጫት ቤት እና ሺሻ ቤት ይስፋፋ! መፃህፍት ቤት እና የሚነበቡ የሕትመት ውጤቶችን  ዝጋ!''

ወደ ኃላ ሄደን በ1983 ዓም አዲስ አበባ ስንት የጫት ቤቶች እና ሺሻ ቤቶች ነበሩ? ብለን ብንጠይቅ መልሱ ግልፅ ነው።ባለፉት 23 ዓመታት ውስጥ ከዜሮ ከሚባል ደረጃ ዛሬ የእየደጃፋችን እና የትምህርት ቤቶች መዳረሻዎች ሁሉ በጫት መቃምያ እና በሺሻ ቤቶች እንደተሞሉ እንረዳለን።ለእዚህ ማሳያ የሚሆነን ከዛሬ 23 ዓመታት በፊት በአዲስ አበባ በሚኖሩ ሱቆች ላይ  ''የጫት መሸጫ ሱቅ'' ብሎ መለጠፍ አስነዋሪ እና በህብረተሰቡ ዘንድተቀባይነቱ ብቻ ሳይሆን አሳፋሪም  ነበር።
በኢህአዲግ/ወያኔ ዘመን የተስፋፋው የጫት ገበያ

ብዙም አልቆየ ኢህአዲግ/ወያኔ ስልጣን በያዘ በወራት ውስጥ ''የበለጩ ጫት፣የባህር ዳር ጫት'' እና ሌሎችም ማስታወቂያዎች ተኮለኮሉ።ዩንቨርስቲዎች፣የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ወዘተ በጫት ተጥለቀለቁ።ኢህአዲግ/ወያኔ እና ካድሬዎቹ ዋና አቀባባይ እና አሰራጮች ሆኑ።የጫት ሱሱ ከፍተኛ የኢህአዲግ/ወያኔ ባለስልጣናትን ሁሉ በሱስ ተጠምዷል እና አዲሱ ትውልድንም ለማደንዘዝ እንደ አንድ መሳርያ ተጠቀመበት።
የጫት እና ሺሻ ቤቶችን በየመንደሩ ያስፋፋው ኢህአዲግ/ወያኔ በጎን በኩል ደግሞ ወጣቱ በማንበብ እራሱን በእውቀት እንዳያበለፅግ የሰራቸው ሁለት ተጨማሪ ወንጀሎች አሉ።የመጀመርያው ከተሞች መፃህፍት ቤት እንዳይኖራቸው ምንም ባለማድረግ ሲሆን ሁለተኛው የነፃ የህትመት ውጤቶችን ማፈን ነበር

 2.1 ''መፃህፍት ቤት ዝጋ ጫት እና ሺሻ ቤት ክፈት!''

ከሶስት ሚልዮን በላይ ሕዝብ ያላት አዲስ አበባ የጫት ቤት እና ሺሻ ቤቶች ተስፋፉባት እንጂ መፃህፍት ቤት እንዲኖራት ኢህአዲግ/ወያኔ አልፈቀደላትም።በ 1997 ዓም በነበረው ሃገራዊ ምርጫ ቅንጅት ለአዲስ አበባ አቅርቦት የነበረው የምርጫ መቀስቀሻ ነጥቦች ውስጥ አንዱ ''በአዲስ አበባ ውስጥ በእያንዳንዱ ክፍለ ከተማ ውስጥ ቢያንስ አንድ መፃህፍት ቤት መክፈት'' የሚል የነበረ መሆኑን የእዚህ ፅሁፍ አቅራቢ ያስታውሳል።ለሀገር ማሰብ ትውልድን በእውቀት ማነፅ እና የማንበብ ባህልን በማዳበር ይጀመራልና ቅንጅት ከየት እንደሚጀመር ያሳየበት ጥበብ የተሞላበት የስራ ዕቅድ ነበር ያቀረበው።
ኢህአዲግ/ወያኔ ስልጣን ከያዘ ወዲህ አዲስ አበባ አንድ ደረጃውን የጠበቀ መፃህፍት ቤት አላየችም።በግል ባንድ ጊዜ ከሁለት እና ሶስት መቶ ሰው በላይ የማያስተናግዱ መፃህፍት ቤቶች በስተቀር ከተማዋ መፃህፍት ቤቶች የሏትም። ማንበብ የማይወዱት ባለሥልጣኖቻችን የኢትዮጵያን ከተሞችም በጨለማ ውስጥ ከትተው ዓመታትን አሳለፉ።እስካሁን ባሉ መረጃዎች አዲስ አበባ ከሶስት ሚልዮን በላይ ነዋሪ ቢኖራትም አሁንም ድረስ በመፃሕፍት ብዛቱም ሆነ በትልቅነቱ የሚጠቀሰው ለሕዝብ ክፍት የሆነው መፃህፍት ቤት ከአርባ ዓመታት በፊት በብላቴ ጌታ ሕሩይ ወ/ሥላሴ የተሰራው ''ብሔራዊ ቤተ መዘክር (ወመዘክር)'' ተብሎ የሚጠራው እና ባህል ሚኒስቴር አጠገብ የሚገኘው ብቻ ነው።እዚህ ላይ የዩንቨርስቲዎች ወይንም የድርጅቶች መፃህፍት ቤቶች ለሁሉም ሕዝብ ክፍት ስላልሆኑ የህዝብ መፃህፍት ቤት ተብለው እንደማይወሰዱ ለማሳሰብ እወዳለሁ።
አብዛኛው ወጣት ሥራ አጥ ሆኖ ከቤት  የሚውልባቸው ከተሞች የመፃህፍት ቤቶች ቢስፋፋላቸው በርካታ ጥቅም እንደሚኖራቸው ሳይታለም የተፈታ ነው።የመጀመርያው ጥቅም ጊዜን ከአልባሌ ቦታ ጠብቆ ማሳለፍ ሲሆን ሁለተኛው አዲስ የስራ መስክ ለመፍጠር ከፍተኛ የስነልቦና ልዕልና የመቀዳጀቱ ፋይዳ ነው።ኢህአዲግ/ወያኔ ግን በተቃራኒው ለወጣቱ የደገሰለት የጫት እና ሺሻ ቤቶችን በእጥፍ ማስፋፋት ነው። 

2.3 ''የሕትመት ውጤቶችን ዝጋ! አደንቁረህ ግዛ!''

ኢህአዲግ/ወያኔ መፃህፍት ቤቶችን ብቻ አይደለም ያቆረቆዘው።ላለፉት ሃያ ሶስት ዓመታት እየተከታተለ ሲያጠፋ የኖረው ለትውልዱ ጭላንጭል የዕውቀት ብርሃን የሚፈነጥቁ የነበሩትን የግል የህትመት ውጤቶችን ነው።ትውልድ የማንበብ እና የማወቅ መብቱ የተዘጋው በጣት የሚቆጠሩ የነፃው ፕሬስ ውጤቶችን ነው።ቀደም ብሎ ኢህአዲግ/ወያኔ የግል ፕሬሶችን ሲወቅስ የነበረው 'የጋዜጠኛ ሙያ የላቸውም፣ተቃዋሚዎች ናቸው' ወዘተ እያለ ነበር።ሆኖም ግን ይህንን አባባል ገደል የሚከቱ በፖለቲካ ትንታኔ ምጥቀትም ሆነ በምርምር ላይ በተመሰረቱ ጥናታዊ ፅሁፎችን በማተም ዝናን ያተረፉትን እንደ ''አዲስ ነገር ጋዜጣ'' እና  ''የአዲስ ጉዳይ'' መፅሄትን ለህትመት እንዳይበቁ የጭካኔ በትሩን አሳረፈባቸው። ኢህአዲግ/ወያኔ ትውልዱን አደንቁሮ የመግዛት ደረጃውን ለመረዳት ሃገራችንን ከአሜሪካ እና አውሮፓ ህትመቶች ጋር እያወዳደርኩ አይደለም።ነፃነቷን ካገኘች ገና ግማሽ ክ/ዘመን ካስቆጠረችው  ከኬንያ ጋር ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ሁኔታ ማመላከት ብቻ  የኢህአዴግ/ወያኔ  ''አደንቁረህ ግዛ!'' ፖሊሲምን ያህል አስከፊ እንደሆነ በግልፅ ያሳየናል።
ኢህአዲግ/ወያኔ እግር በእግር እየተከታተለ የህዝቡን የዕውቀት እና የማንበብ ባህል የሚገድልበት የግል ህትመት ውጤቶች ከሰማንያ ሶስት ሚልዮን በላይ ለሆነ ሕዝብ በአንድ ሳምንት ውስጥ የሚያሰራጩት የሕትመት ብዛት 20 ሺህ የማይሞላ ሲሆን በሕዝብ ብዛቷ ከኢትዮጵያ ከግማሽ በታች የሆነችው ኬንያ በእየቀኑ ብቻ ''ዴይሊ ኔሽን'' የተሰኘው ጋዜጣ ብቻ ከሩብ ሚልዮን በላይ ለሆነ ሕዝብ አዳርሳ ታድራለች።ይህንን ወደ አንድ ሳምንት ስንቀይረው በኬንያ ብቻ ወደ 1.4 ሚልዮን የሚሆን ሕዝብ የሕትመት ውጤቶች በአንድ ሳምንት ውስጥ ይደርሱታል ማለት ነው።ይህ እንግዲህ በድረ-ገፅ የሚያነበውን አይጨምርም።
ኢህአዲግ/ወያኔ የማንበብ እና የማወቅ መብታችንን ማፈኑ ብቻ አይደለም ትውልዱ የማንበብ ባህሉ እንዲሞት በተለዋጭ ግን የጫት እና የሺሻ ሱሰኛ እንዲሆን ተገዷል።ይህ ታሪካዊ፣አድሏዊ እና ዘረኛ ወንጀል ነው።ምክንያቱም ይህ ተግባር በሁሉም የኢትዮጵያ ወጣት ላይ አልተደረገማ! ጫት እንዳይሸጥባቸው ሀሽሽ እንዳይዘወተርባቸው በቂ ቁጥጥር የሚያደርግ ክልል አለና! ''አደንቁሮ መግዛት'' ማለት ይህ ነው።ከኢህአዲግ/ወያኔ መላቀቅ ማለት ከድንቁርና ነፃ መውጣት ማለት ነው።ይህ ደግሞ በትውልዱ ላይ የወደቀ ኃላፊነት ነው።ዕውቀት ወይስ ድንቁርና? ለትውልዱ የቀረቡ ሁለት ብቸኛ አማራጮች።

ጉዳያችን 

ነሐሴ 6/2006 ዓም (ኦገስት 12፣2014)



   

Letter to the British Prime Minister, David Cameron


David Cameron, Prime Minister of UK


August 11, 2014

Rt Hon David Cameron MP,
Prime Minister
London

Dear Prime Minister:

We are writing this letter to express our deep dismay at the manner in which the British Government has handled the brazen abduction, and extradition of Andargachew Tsege, a British citizen.Global alliance for the rights of Ethiopians

Mr. Tsege, was carrying a UK passport and travelling from Dubai to Asmara. He was in transit at Sana’a International Airport when he was abducted by Yemeni security forces on June 23, 2014. His illegal detention and subsequent extradition to Ethiopia in clear contravention of the Vienna Protocol was completely ignored by British authorities.

Mr. Tsege was held incommunicado and his whereabouts unknown to his family for more than a week. On July 3, 2014 the Foreign Office informed his family in London that the Yemeni Ambassador to the UK has confirmed Mr. Tsege’s extradition to Ethiopia where he was sentenced to death in absentia in 2009 and 2012 on politically motivated trumped up charges.

We have received reports of Mr. Tsege’s mistreatment and abuse. These unconfirmed reports compounded by the fact that neither Mr. Tsege’s family nor British Embassy officials have been allowed any contact with Mr. Tsege have left us to fear the worst. We believe beyond a shadow of a doubt that he is imprisoned in one of the dungeons of the Ethiopian regime for a crime that was never committed. The politically motivated charges that the regime in Ethiopia fabricates against its perceived enemies has been consistently reported and condemned by respected international rights groups.

The International Bill of Human Rights, comprising: the Universal Declaration of Human Rights (UDHR), the International Covenant on Economic, Social and Cultural Rights (ICESCR), and the International Covenant on Civil and Political Rights (ICCPR) with its Optional Protocol, provide a line of legislation that clearly establishes a rule against rendition.

The timid response to the illegal abduction carried out by the regime in Ethiopia and the reluctance on the part of the UK government to stand up for the rights of its own citizen against illegal and unacceptable treatment is truly appalling. The reluctance of the British government to stand against the violation of numerous international laws gives the perception of complicity on the part of the British government. The reason for this is because we have not seen any determined effort on the part of your government to do everything in its power to help right this flagrant violation of international law.

The illegal abduction of a British national by Yemeni security forces must be rectified. The British government must publicly denounce the criminal act and demand the regime in Ethiopia to immediately and unconditionally release Mr. Tsege and return him to his home and family in London.

We thank you for your attention to this urgent matter.

Sincerely,

Meron Ahadu,
Spokesperson,

Global Alliance for the Rights of Ethiopians

c.c. Mr. Nick Clegg, Deputy Prime Minister
Mr. Phillip Hammond, Foreign Secretary

source -  ECADF 

Thursday, August 7, 2014

ሰበር ወቅታዊ ፖለቲካዊ ሁኔታዎች - ኢህአዲግ እና ተቃዋሚዎች ወሳኝ ነጥብ ላይ መሆናቸውን አውቀውት ይሆን? የግብፁ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የደህንነት ኃላፊ ዋሽግተን ገቡ፣የመካከለኛው ምሥራቅ ትኩሳት ተቀስቀሰ፣ሩስያ ከመቸውም በበለጠ ደረጃ እየተፈራች ነው።(የጉዳያችን አጭር ማስታወሻ)

ማስታወሻ- ይህ ፅሑፍ ከሶስት ወር በፊት ሚያዝያ 16/2006 ዓም (April/2014) በእዚሁ ጡመራ ገፅ ላይ የወጣ እና ዛሬ እንደገና የተለቀቀ ነው።''የኢትዮጵያን ጉዳይ በተመለከተ ጊዜ የለም ''ይላል።
ካርታ ከ ቢቢሲ ሰኔ 2005 ዓም ከለቀቀው ዜና የተገኘ 

ሩስያ ከመቸውም በበለጠ ደረጃ እየተፈራች ነው

የዓለማችን ዓለም አቀፋውም ሆነ አካባቢያዊ ሁኔታዎች በፍጥነት እየተቀየሩ ነው።የዩክሬኑ ጉዳይ ከመሻሻል ይልቅ ከቀን ቀን እየተባባሰ መጥቷል።ሩስያ ከክሬምያ ህዝበ ውሳኔ በኃላ የምዕራባውያን ቁጣ ወደ ጎን በማለት ዩክሬን ያሉ አፍቃሪ-ሩስያውያንን ሁኔታ በአንክሮ እየተከታተለች ነው።ዛሬ ዩክሬን  በአፍቃሪ-ሩስያውያን ላይ በወሰደችው እርምጃ ከአምስት ያላነሱ መገደለቸው ሩስያን በእጅጉ ከማስቆጣቱም በላይ በዩክሬን ድንበር ላይ የጦር ልምምድ እያደረገች መሆኗ ተገልጧል።የሩስያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም በድጋሚ (ዛሬ) ለዩክሬን ማስጠንቀቅያ ሰጥተዋል።ሌላው አስገራሚ ጉዳይ ደግሞ ትናንት ቢቢሲ በድረ-ገፁ እንደገለፀው 'የእንግሊዝ አየር ኃይል የሩስያ አየር ኃይል የእንግሊዝን የአየር ክልል ለመጣስ ሲሞክር ተደረሰበት የሚል ዜና መልቀቁ ሲሆን ጉዳዩ ወደ መጎናተል ተሽጋገረ እንዴ? ለማለት ያስገድዳል።

የግብፁ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የደህንነት ኃላፊ ዋሽግተን ገቡ

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከግብፅ አብዮት ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ ከፍተኛ የተባለ የግብፅ ባለስልጣናት ወደ ዋሽግተን ለምክክር ተጉዘዋል።ባለስልጣናቱ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ናቢል ፋህሚ እና የደህንነት መስርያቤቱ ኃላፊ ሜጀር ጄነራል ሞሐመድ ኤል ቶሃሚ ሲሆኑ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ጋር ዝግ ውይይት እንዳላቸው ''አህራም ኦን ላይን'' በድረ-ገፁ ገልጧል።አሜሪካ ባለፈው ሐምሌ ወር ለግብፅ ትሰጥ የነበረውን የወታደራዊ እርዳታ እንደገና እንደምትገመግም መግለጧ ይታወቃል።የሁለቱ ባለስልጣናት ጉብኝት ዋና አላማ አሜሪካን ለግብፅ ለመስጠት ተዘጋጅታ የነበሩና ያዘገየቻቸውን ታንኮች፣ሚሳኤሎች፣ተዋጊ አይሮፕላኖች እና ሄሊኮፕተሮች እና በተጨማሪም 260 ሚልዮን ዶላር የጥሬ ገንዘብ ዕርዳታ እንድትለቅ ለማግባባት ጭምር እንደሚሆን ድረ-ገፁ ገልጧል።ከእዚህ በተለየ ድረ-ገፁ አይግለፀው እንጂ የግብፅ የወቅቱ ቁጥር አንድ አጀንዳ በኢትዮጵያ እየተሰራ ያለው የአባይ ግድብ ጉዳይ እንደሚነሳ መገመት ይቻላል።

የመካከለኛው ምሥራቅ ትኩሳት ተቀስቀሰ

በሌላ በኩል ለዘመናት የአፍካ ቀንድ ሃገራትን እና ግብፅ ከአሜሪካን እና እስራኤል ጋር የሚኖራቸውን የግንኙነት መስመር የሚያዋልለው የመካከለኛው ምስራቅ ትኩሳት የመጨመር አዝማምያ እንደሚኖር የሚያመላክት አዲስ ክስተት መታየት ጀምሯል።ይሄውም የፍልስጤም ሁለቱ ባላንጣ ቡድኖች ማለትም በምዕራቡ በሚደገፈው የፍልስጤም ራስ ገዝ መንግስት እና በነውጥ የሚያምነው 'በሐማስ' መካከል ለእረጅም ጊዜ ሲደረግ የነበረው ውይይት ሰምሮ የመስማማታቸው ዜና ነው። አሜሪካ እና እስራኤል ከሐማስ ጋር የሚደረግ ማናቸውም ስምምነት እንደማይደግፉ በግልፅ አሳውቀዋል።እስራኤል በተለይ ከፍልስጤም ራስ ገዝ መንግስት ጋር የነበረውን ውይይት ለማቆም መገደዷን ገልፃለች። ይህ ማለት የመካከለኛው ምስራቅ የኃይል አሰላለፍ እንደገና አጃቢ ስልታዊ ሃገራትን ይዞ መቀስቀሱን ያመላክታል።የኃያላን ሃገራትም ትኩረት በአዲስ መልክ ከመሳቡ ባለፈ ትናንሽ የሚባሉ ሀገራትንም ስቦ ማስገባቱ አይቀርም።

ኢህአዲግ እና ተቃዋሚዎች ወሳኝ ነጥብ ላይ መሆናቸውን አውቀውት ይሆን?

ከላይ የተገለፁት የሩስያ የልዕለ ኃይልነት ስሜት መነቃቃት እና የመካከለኛው ምስራቅ ፖለቲካ መጋጋል የግብፅን ስልታዊነት አስፈላጊነት መጨመሩ እና ኢትዮጵያ ደግሞ ከግብፅ በበለጠ በአባይ ጉዳይም ሆነ በአፍሪካ ቀንድ ባላት የህዝብ ብዛት እና ወሳኝ ስልታዊ አቀማመጥ አስፈላጊነቷ መጨመሩ የማይቀር ብቻ ሳይሆን የምዕራባውያንን ትኩረት መሳቧ ሃቅ ነው። ይህ ማለት በኢትዮጵያ የሚነሳ ማናቸውም ተፅኖ ፈጣሪ የመደመጥ ኃይሉ ቀላል አይሆንም ማለት ነው። የአካባቢው ትኩሳት በመካከለኛው እና በሩስያ ጉዳይ ብቻ አይሳብም የደቡብ ሱዳን እና የሱማልያው ጉዳይ ገና  አቅጣጫቸው በአግባቡ ያልለየላቸው መሆኑ እና ኢትዮጵያ አሁንም ወሳኝ መሆኗን ማሰብ ይገባል።እዚህ ላይ የኤርትራ ዕድልም እራሱ የሚታየው የአዲስ አበባ ፊት እየታየ መሆኑ እውነታው ነው።እነኝህ ሁሉ ሁኔታዎች የኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ መረጋጋት እና ወሳኝ ደረጃ ላይ መድረስ እንዳለበት ለማመን ሊቅ መሆን አይጠይቅም።

በኢትዮጵያ ኢህአዲግ የህዝቡን ስሜት እና የፖለቲካ ሳይንስ ተከትሎ ለለውጥ አለመዘጋጀቱ እና የጎሳ ፖለቲካውን ከሚገባው በላይ መወጠሩ ኢትዮጵያ አስፈሪ ሁኔታ እንዳይፈጠር ያሰጋል።ይህንን ስጋት ማስወገድ ማለት ደግሞ በመካከለኛው ምስራቅ ላይ ሚና የምትጫወተውን ግብፅን ብቻ ሳይሆን የቀይ ባህርንም የመቆጣጠር ዕድል መሆኑን ወዳጅም ጠላትም የሚረዳው ጉዳይ ነው።ጠላት ከመቼውም በበለጠ ሁኔታ ኢትዮጵያን በጎሳ ለማተራመስ ሲሰራ ወዳጅ ደግሞ የኢትዮጵያን ታሪካዊ የፖለቲካም ሆነ ወታደራዊ የበላይነቷን እንድትይዝ ይሰራል።ከእዚህ በተለየ ደግሞ  ባእዳን ጥቅማቸውን በማንኛውም መንገድ ከሚያስከብርላቸው ጋር ለመስራት ይተጋሉ።ጥያቄው ለኢትዮጵያ የተሻለ ዕድል የሚፈጥረውን መንገድ መርጦ የሚሄድ መንግስት አላት ወይ? የሚል እና ተቃዋሚው ኃይልስ ምን እየሰራ ነው? የሚሉ ወሳኝ ጥያቄዎች ናቸው።

 ለኢትዮጵያ ያሏት እድሎች ሁለት ናቸው።አንድኛው-ኢህአዲግ እራሱ ለለውጥ ማዘጋጀት እና ኢትዮጵያ ያላትን መልካም ዓለም አቀፋዊና አካባቢያዊ ዕድል እንድትጠቀም ''360 ዲግሪ የዞረ'' የፖሊሲ ለውጥ ማሳየት እና ቅድምያ ለሃገር ቢሰጥ ያለንበትን ታሪካዊ ዕድል ለመጠቀም መቻል ነው።ካለፉት የኢህአዲግ ተግባራት ተነስተን ይህ ለብዙዎቻችን ሕልም ነው።ኢህአዲግ ለሀገር ቅድምያ ባለመስጠት ዝናን ያተረፈ ነው።ይህ ካልሆነ ግን ጉዳዩ ያለው ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር ነው ማለት ነው። የኢትዮጵያ የተቃውሞ ኃይላት እራሳቸውን በፍጥነት የሚያስተባብሩበት ጊዜ ነገ ሳይሆን ዛሬ መሆኑን መረዳት ይቻላል።ተቃዋሚ ኃይሎች ልዩ የሆነ ህብረት እና አዲስ አቀራረብ ይዘው ከሰሞኑ መገኘት እና ለልዕለ ሃያላኑንም ሆነ የኢትዮጵያ ጉዳይ ለሚያሳስበን ዜጎች ሁሉ ከጊዜያዊ ሕብረት ይልቅ ፍፁም የሆነ አንድነት እና የለውጥ ስልት ሊያሳዩን ይገባቸዋል።ዓለም አቀፋውም ሆነ አካባቢያዊ ፖለቲካዊ ሁኔታ የሚያመላክተው ይህንኑ ነው።ጊዜ ያለ አይመስልም።

ጉዳያችን
ሚያዝያ 16/2006 ዓም 

Monday, August 4, 2014

''U.S. has failed to hold the leaders of Ethiopia accountable for its abusive governance. America's silence in the face of egregious human rights violations and brutal oppression is perceived by Ethiopians as favoring the autocratic regime.'' Los Angeles Times Aug.3,2014

Aug.3,2014
When Secretary of State John F. Kerry traveled to Ethiopia last year, he met a young blogger named Natnael Feleke. When he returned a few months ago, Kerry found that Feleke, along with five other bloggers and three journalists, had been arrested — the latest in a long line of journalists the Ethiopian government has detained on the claim that they were trying to incite terrorism. Although Kerry addressed the arrests with officials he met, and President Obama has spoken forcefully on the importance of good governance in Africa, preoccupation with immediate security priorities — in particular counter-terrorism — trumps the fine words.

It is our hope that President Obama will use the summit of African leaders he is hosting this week to launch a new chapter in U.S.-African relationships — one in which support for good governance will guide U.S. policy, in deed as well as in word. If not, the result is likely to be more of the very violence and instability that counter-terrorism is supposed to curb.

In our country of Ethiopia, the government maintains a stranglehold on freedom of expression. Journalists or activists who question the ruling party or its actions face arbitrary arrests and repression. After his April visit, when Kerry made the long overdue comment that it was important for anti-terrorist mechanisms to avoid curbing the free exchange of ideas, Ethiopian democracy activists around the world were thrilled.

Yet at the same time, we know that words, even from a U.S. secretary of State, will not be sufficient to counter years of repression and disregard for human rights. The Ethiopian ruling regime — like many others in Africa — has ignored criticism from abroad; indeed, Feleke's and the other journalists' arrests came just days before Kerry's visit to Ethiopia.

Shortly after his election in 2009, Obama delivered a speech in Accra, Ghana, sketching the elements of his policy toward Africa, which involved focusing on "good governance," "the rule of law" and "civic participation."

Ethiopia, though projected by Washington as well as Addis Ababa as an important U.S. ally, violates these principles at every turn. The regime's draconian Charities and Societies Proclamation Act in essence criminalizes civil society. Under the terms of its 2009 anti-terrorism law, security forces can enter any home and seize any person or belonging. Presumed sympathy to anyone suspected of "terrorism," which is very broadly defined, is punishable by death. It was under this law that Natnael Feleke was arrested.

In spite of Ethiopia's well-documented record of oppression and corruption, it has become the biggest recipient of U.S. foreign aid in sub-Saharan Africa, receiving more than $6 billion since 2011. And to date, the U.S. has failed to hold the leaders of Ethiopia accountable for its abusive governance. America's silence in the face of egregious human rights violations and brutal oppression is perceived by Ethiopians as favoring the autocratic regime.

Such oppression, combined with systematic state corruption, have resulted in a narrow, monopolistic form of governance. Ethiopia's much-touted economic growth has mainly benefited kleptocrats, while reducing standards of living for many. In rural Ethiopia, the government has opened vast tracts of land to foreign investors from Saudi Arabia, India and China, and has also allotted enormous tracts to government-owned sugar plantations — whose returns enrich regime insiders. Large dams have flooded indigenous lands, and are creating renewed conflict over land and water resources. Such tactics are not a recipe for stability — quite the reverse.

Yet, U.S. officials seem oblivious to how the Ethiopian regime exploits its role as a key ally in America's war on terrorism to crush dissent and silence journalists and human rights activists.

Awareness of oppression in Ethiopia is growing. Sen. Patrick J. Leahy (D-Vt.) has been urging various administrations to reconsider support of the regime since the 2005 elections, when hundreds of peaceful protesters were killed. And in June 2013, Rep. Christopher H. Smith (R-N.J.) held a hearing called "The Future of Democracy and Human Rights" in Ethiopia.

We welcome this sort of pressure from the international community and specifically from the United States, and we believe that over the long term it can help bring about democratic change. President Obama, who is much admired in Ethiopia, should review U.S. policy and take a clear stand; his words must then be reinforced by the actions of his government.

Meron Ahadu and Lulit Mesfin are Ethiopian American democracy and human rights advocates.

Source - Los Angeles Times Aug.3,2014

Saturday, August 2, 2014

በመጪው ሰኞ ሐምሌ 28/2006 (ኦገስት 4/2014) ዓም ዋሽግተን ዲ ሲ ምናልባትም በኢትዮጵያውያን ዘንድ በታሪክ ያልታየ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ታስተናግዳለች። የኢህአዲግ/ወያኔ አስተዳደር ለእዚህ ጉባኤ የሚመጥን ውክልና ይዟል ወይ? የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ


በመጪው ሰኞ ሐምሌ 28/2006 (ኦገስት 4/2014) ዓም ዋሽግተን ዲ ሲ ምናልባትም በኢትዮጵያውያን ዘንድ  በታሪክ ያልታየ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ታስተናግዳለች።

የኦባማ አስተዳደር እ አ አቆጣጠር ከነሐሴ 4 እስከ 6/2014 ዓም በዋሽግተን ዲሲ ''የአሜሪካ - አፍሪካ መሪዎች ጉባኤ'' ጠርቷል።ጉባኤው ከሃምሳ በላይ የአፍካ መሪዎች እና ተወካዮች የሚገኙበት እና በአሜሪካ ታሪክ የመጀመርያው ግዙፉ የአፍሪካ እና የአሜሪካ የጋራ ጉባኤ መሆኑ ተነግሮለታል።ስብሰባው ባለፈው ዓመት ፕሬዝዳንት ኦባማ ወደ አፍሪካ ባደረጉት ጉብኝት ወቅት የተነሱ የአፍሪካ እና የአሜሪካ ግንኙነቶች ላይ የሚያተኩር መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።እንደ ዋይት ሃውስ መግለጫ መሰረት የጉባኤው መሪ ቃል ''በመጪው ትውልድ ላይ መስራት'' (Investing in the Next Generation)  የሚል መሆኑን ይጠቅሳል።

ስለጉባኤው ይህንን ያህል ካልን የኢትዮጵያ የኢህአዲግ/ወያኔ አስተዳደር ለእዚህ ጉባኤ የሚመጥን ውክልና ይዟል ወይ? ብለን መጠየቅ አለብን።መልሱ አይመጥንም የሚል ይሆናል።ለእዚህ ቀላል ማስረጃዎችን መጥቀስ ይቻላል። ለምሳሌ ከጉባኤው መሪ ቃል ''በመጪው ትውልድ ላይ እንስራ'' የሚለውን ብቻ ብንመለከት ኢህአዲግ/ወያኔ የመጪውን ትውልድ በማሳደድ እና ፍላጎቱን በኃይል በመጨፍለቅ የታወቀ እንጂ መጪውን ትውልድ ለአፍታም ቢሆን ሲያዳምጥ አልተስተዋለም።እዚህ ላይ መጪው ትውልድ ብዬ የምጠራው አሁን ያለውን ወጣት ትውልድን ነው።ነገ ሀገር ተረካቢው እርሱ ነዋ!  

ለአብነት ያህል ኢህአዲግ/ወይኔ በያዝነው ዓመት ብቻ የመጪው ትውልድ አካላትን ያጠቃበት እኩይ ተግባራት ብንመለከት ምን ያህል ለጉባኤው አለመመጠኑ እና ከጉባኤው መሪ ቃል ጋር ተግባሩ እንደተጣላ እንረዳለን።ከታሰሩ አንድ መቶኛ ቀናቸውን የያዙት  የዞን 9 ጦማርያን ለእስር የተዳረጉት፣በርካታ ወጣት ጋዜጠኞች ወደ ወህኒ የተወረወሩት ምንም አይነት ወንጀል ተገኝቶባቸው ሳይሆን ሃሳባቸውን በነፃ ለመግለፅ ስለሞከሩ ከሁሉም በተሻለ ደግሞ መጪውን አማትረው በመመልከት ለሀገራቸው ይበጃል ያሉትን ሃሳብ በመሰንዘራቸው ብቻ ነው። ይህን ያደረገ መንግስት ተወካዮች ናቸው እንግዲህ ''አይናቸውን በጨው አጥበው'' በስብሰባው ላይ ለመሳተፍ የሚዘጋጁት።

ሁለተኛ አብነት ልጥቀስ በያዝነው ዓመት አሜሪካ የዓለማችን ''የአዲሱ ትውልድ አዲስ ሃሳብ አመንጪዎች እና መሪዎች'' ብላ ባዘጋጀችው ጉባኤ ላይ የሰማያዊ ፓርቲ መሪ ኢንጅነር ይልቃል አንዱ ተመራጭ እና ተጋባዥ እንደነበሩ ይታወቃል።ኢህአዲግ/ወያኔ ግን ምን ነበር ምላሹ? ኢንጅነር ይልቃል የጉዞ ሰነዳቸውን አዘጋጅተው  አየር መንገድ እስኪቀርቡ ድረስ ጠብቆ ከፓስፖርታቸው አንዱን ገፅ ቀዶ እንዳይሄዱ ከለከላቸው።የመጪው ትውልድን እግር በእግር እየተከታተለ የማምከን እኩይ ስራውን ቀጠለበት። ይህንን ትዕዛዝ የሰጡት ባለስልጣናት ናቸው እንግዲህ በመጪው ሰኞ ምንም እንዳላደረጉ ሁሉ ከአፍካ መሪዎች ጋር አብረው ዋንጫ ሊያነሱ የተዘጋጁት።ይህ ለአሜሪካም ሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ውርደት ነው።ለእዚህም ነው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከየቦታው ተጠራርቶ በአይነቱ ግዙፍ የተባለ ሰልፍ ለማድረግ በመጪው ሰኞ ዋሽግተን ዲሲ ላይ የሚከትመው።ሰኞ መንግዶች ሁሉ ስቴት ዲፓርትመንት አጠገብ ወደሚገኘው ወደ ብሔራዊ የሳይንስ አካዳሚ ያመራሉ።

የሰልፉን ማስታወቂያ ከእዚህ በታች ይመልከቱ -

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሃራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሐራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)