ጉዳያችን - በጉዳያችን ሚድያ፣ኮምኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት የሚዘጋጅ ሲሆን ከ2003 ዓም ጀምሮ በድረ-ገፅ ላይ የነበረ በአሁኑ ጊዜ ከአንድ ሚልዮን በላይ ጎብኚዎች ያሉት ገፅ ነው። Gudayachn is prepared by Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant Organization. It has been online since 2011. Currently, Gudayachn is being visited by over One-million readers from all over the world.
ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages
Sunday, January 31, 2016
ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማ/ቅዱሳን ኦሮምኛ ወረብ EOTC Mahibere Kidusan Afan oromo : Galanni
ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
Thursday, January 28, 2016
ለትዕቢት እና ጎጣዊ ስሜት ሕመምተኞች አልቅሱ! (የጉዳያችን ልዩ ማስታወሻ)
foto: http://hearinghealthmatters.org/
የሰው ልጅ በኖረበት ዘመን ሁሉ ሁለት ነገሮች ቀንደኛ ፈተናዎቹ ናቸው።እነርሱም ትዕቢት እና ጎጠኝነት ናቸው።ትዕቢት ከእኔ በላይ ማን አለ? የሚል ስሜት እና ሌላውን ዝቅ አድርጎ የመመልከት አባዜ ሲሆን የጎጠኝነት ስሜት ደግሞ ''ሰው ሁሉ ለምን እኛ መንደር አልተወለደም'' መሰል የአስተሳሰብ ድህነት ነው።በሌላ በኩል ጎጠኘንት ከእራስ ወዳድነት አልፎ ሌላን መጥላት መለያው ያደርጋል።
የአንድ ሕዝብ እና የአንድ ግለሰብ ባህርያት የጋራ መገናኛ ድልድይ አላቸው።ሁለቱም መከራ ይሸከማሉ።ሁለቱም የሌሎችን የትቢት አንቡላ በላያቸው ላይ ሲራገፍ እንዳላዩ ሆነው ለተወሰነ ጊዜ ያልፋሉ።ሁለቱም የጎጣዊ ስሜት ውስጣቸውን እንደምስጥ ለቦረቦራቸው ሁሉ እያዘኑ አሁንም ለጥቂት ጊዜ ይታገሳሉ።
አንድ ግለሰብ ትዕቢትን እና ጎጥን መጠየፉ በእራሱ የትዕቢተኞች እና የጎጣዊ ስሜት አራማጆች ሰለባ እንዳይሆን ዋስትና አይሆነውም። ትዕቢት እና ጎጥን የማምለክ በሽታዎች ደግሞ የሚገለጡበት አንድ አይነተኛ መንገድ አለ።ይሄውም በንቀት ነው። ጎጠኞች በቅርብም ሆነ በሩቅ የሚያውቁትን ከመንደራቸው ውጭ የሆነውን ሁሉ በጣም ይንቃሉ።በአደባባይ ጎጠኛ እንዳልሆኑ ለመታየት ግን ይታትራሉ።ጎጠኞች ሁል ጊዜ ከበታቻቸው ሆኖ ለማየት የቀን እና የሌት ህልማቸው ነው።ከጎጣቸው ውጭ የሆነ ሰው ሰርቶ ቢያገኝ ይነዳቸዋል። ተምሮ መልካም ደረጃ ላይ ቢደርስ አይፈልጉም። ሆኖም ግን ይህንን እኩይ ስሜታቸውን ውጠው በጎ የመከሩ መስለው መቅረብ ደግሞ ይችሉበታል።አፋቸው ማር ነው።ከንፈራቸውን በየጊዜው ለሚያሳዝነውም ለማያሳዝነውም እሰው ፊት በመምጠጥ አዛኝ ቡቡ መምሰል ይችሉበታል። ዘወር ብለው ግን ከጎጣቸው ጋር ገጥመው ሰው ሁሉ የእነርሱ ጠላት ስለሚመስላቸው የተንኮል መረባቸውን ሲያደሩ ስትመለክቱ ትገረማላችሁ።
መፅሐፍ ''ትዕቢት ውድቀትን ይቀድማል'' እንደሚል ከጎጣቸው ውጭ የሆነ ሰው ምን ቢወዳጃቸው እና ሊዛመዳቸው ቢፈልግ ከእርሱ አንዳች ጥፋት እና ክፉ ቃል ቢያጡበት የእርሱ ጥፋት ይመስል ''እናቱ ለምን እኛ መንደር መጥታ አልወለድችውም'' መሰል ጥላቻ በተግባራቸው ውስጥ ሁሉ ታዩባቸዋላችሁ።ስለዚህ ከጎጣቸው ውቼ የሆነውን ሰው አሁንም ምኑንም ያክል ሊወዳጅ ቢፈልግ አንዳች ጥፋት ሳያገኙበት የጎጥ ህመማቸው ቀስፎ ስለሚይዛቸው ብቻ ያገሉታል፣ይርቁታል፣ ወይንም ግንኙነታቸው ከጎጣቸው እና የእኔ ከሚሉት ወይንም ከሚሏት ጋር ብቻ ያደርጋሉ። በእዚህ ጊዜ ግን የተገለለው ጎጠኞችን በበጎዎች አስገብቶ ማየት የለበትም። ሌሎች የሚያውቃቸው ደጋጎቹን እያሰበ እራሱን ማፅናናት የግድ ይለዋል። የጎጠኞች የንቀትን ልክ ስርዓት ለማስያዝ እልሁን መፈታተኑ አይቀርም። ሆኖም ደጋጎቹን ያየ እና መልካም እና በጎ ህሊና ያላቸው ሌሎቹን ያየባቸውን በጎ ዘመኖች ያስባል።ሁለት ፀጉር እና እድሜ ካላስተማራቸው ጋር መልሶ መጎጠጥ በእራሱ በሽታ መሆኑን መረዳት የግድ ይላል።
በጎጥ በሽታ የተለከፉ እራሳቸውን የደጎች መጨረሻ አድርገው ለመሳል ይሞክራሉ።ሆኖም ግን እንደ አይን ብሌን ከህሊናቸው ጋር የተሰፋው የዘር ቡቶቶ እያደናቀፈ ስለሚጥላቸው ደጋግመው ሊወዳጃቸው የቀረበውን በጥላቻ እሾህ አዕምሮውን እየጨቀጨቁ ሲወጉ ህሊና ቢስነታቸው ለእራሳቸውም አይታወቃቸውም። በመጀመርያ ህሊና ከጎጥ ይልቅ ሰው መሆን ማመንን ይጠይቃል።ህሊና በበሰበሰ አስተሳሰብ ከታጀለ የጎጥ ቂም እና ''እናቱ ለምን እኛ መንደር አልወለደችውም '' መሰል የተደናበረ አስተሳሰብ ወጥቶ ሰው የተባለ ፍጡርን በማየት ብቻ ማዘንን ይጠይቃል። ህሊና የእራስ ጎጥ ሁል ጊዜ ልክ ነውን ሳይሆን ማመዛዘን እና ግፍ መፍራትን ይፈልጋል።
ሌላው የጎጥ በሽተኞች አስገራሚ ባህሪ እድሜ የሚባል ትምህርት ቤት ፈፅሞ አያስተምራቸውም።እነርሱ እዚህ እድሜ ለመድረስ የተለያዩ በጎጥም በምንም የማይመስሏቸው ሰዎች ባደረጉላቸው በጎነት መሆኑን እረስተው ዛሬ ላይ ሆነው የጥላቻ መርዛቸውን ''የኛ አይደለም'' ባሉት ላይ ለመትከል እንደ ቀትር እባብ ሲቅለበለቡ መመልከት መጨረሻቸውን ለማየት ያስናፍቃል።
ባጭሩ ጎጥ አምላኪዎች የግለሰብም ሆነ የህዝብ ፀር ናቸው።ግፋቸው ለዘለዓለም ነዋሪ አይደለም።ለሕዝብ እና ለግለሰብ ያላቸው የንቀት ደረጃ በድቡሽት ላይ እንደተሰራ ቤት ሲፈርስ እራሳቸው የታሪክ ምስክር ይሆናሉ።በጥላቻ የገነቡት ከንቱ ስብዕና እራሳቸውን እንደምስጥ ቦርቡሮ ወና መቃብር ያደርጋቸዋል። አንዲት ቀን ከጎጣቸው ውጭ ለሆነ ሰው ለተባለ ግለሰብ በጎ ማድረግ ሳይሆን በትዕቢት መወጠር የተለማመደ ከንቱ እነሱነታቸው የሸረሪት ድር ማድርያ ይሆናል። እግዚአብሔር ለትዕቢተኞች እና ለጎጠኞች ጥብቅና ቆሞ አያውቅም።ትዕቢተኞች እና ጎጠኞች እርስ በርሳቸው ''አይዞህ፣አይዞሽ'' በመባባል የሰሩትን የግፍ ግፍ ለመሸፋፈን ይሞክሩ ይሆናል።ሊዛመዳቸው በቀረበው ሕዝብ እና ግለሰብ ላይ የሰሩትን ኃጢአት ለማጠብ የሚሆን ጠብታ ውሃ ግን ማመንጨት አይችሉም።እግዚአብሔር ለጎጠኞች እና ትዕቢተኞች የሚከፍለው የቁጣ የደሞዝ ቀን እንደ ንስር እየበረረ ይመጣል።
ጉዳያችን GUDAYACHN
ጥር 20/2008 ዓም (ጃንዋሪ 29/2016)
Tuesday, January 19, 2016
ኢህአዴግ/ህወሓት ለኢትዮጵያ ድንበር በሞቱት አባቶቻችን ደም ውስጥ እጁን ነከረ! በገንዘብ፣በጎጥ እና በደም ጥማት የሚንቀለቀል ልቦና የተሸከሙት የአራት ኪሎ ባለስልጣናት አፄ ቴዎድሮስ ከነገሱበት እስከ አፄ ዮሐንስ የተሰዉበትን መሬት ለሱዳን ለመሸጥ ተስማምተዋል።የሱዳን ትሪቡን ጋዜጣ ትርጉም ይዘናል።
ኢህአዴግ/ህወሓት ለኢትዮጵያ ድንበር በሞቱት አባቶቻችን ደም ውስጥ እጁን ነከረ! አፄ ቴዎድሮስ ከነገሱበት እስከ አፄ ዮሐንስ የተሰዉበትን መሬት ለሱዳን ለመሸጥ ተስማምቷል። ኢትዮጵያ የተዳከመች ሲመስላቸው ጠላቶቿ ስነሱባት መስማት አዲስ ነገር አይደለም። አዲስ ነገር የሚሆነው በቤተ መንግስቷ በኢትዮጵያ ስም መንግስት ነኝ የሚሉ ስብስቦች የኢትዮጵያን ጥቅም ከባዕዳን ጋር ሲዶልቱ፣ሲሸጡ እና ሲያስማሙ መመልከት ነው።በገንዘብ፣በጎጥ እና በደም ጥማት የሚንቀለቀል ልቦና የተሸከሙት የአራት ኪሎ ባለስልጣናት አፄ ቴዎድሮስ ከነገሱበት እስከ አፄ ዮሐንስ የተሰዉበትን መሬት ለሱዳን ለመሸጥ ተስማምተዋል።ይህ ሕሊናን የሚያደማ ብቻ ሳይሆን የመኖር እና ያለመኖር ህልውና ጉዳይ ነው።''ዳሩ ሲነካ መሃሉ ዳር ይሆናል'' የሚለው አባባል እዚህ ላይ ማሰቡ ተገቢ ነው።ይህ ሥራ በመንግሥትነት እራሳቸውን የሾሙ ስብስቦች ኢትዮጵያን የማፈራረስ ልክ የት ድረስ እንደሚሄድ ብቻ ሳይሆን የከሃዲነት ደረጃቸው እና ህዝብን የመናቃቸው መጠን ምን ያክል እንደሆነ ማሳያ ነው።
አቶ ኃይለማርያም በድንበሩ አካባቢ የሚያርሱ ገበሬ ኢትዮጵያውያንን የህዝብ ተወካይ ነኝ ባሉ ምክር ቤት ስም ''ሽፍቶች'' እያሉ የተሳደቡትን ስድብ የሱዳኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እብራሂም ጋንዱር ለአልጀዝራ በሰጡት መግለጫ ላይም ደግመውታል።ኢትዮጵያውያንን እርሳቸው ብቻ ሳይሆኑ በስልጣን ላይ የተቀመጠው የኢትዮጵያ መንግስትም እንደሚገልላቸው ሲገልጡ ''ኢትዮጵያ እና ሱዳን በሱዳን ግዛት ላይ የሰፈሩትን ሽፍቶች (gangs) በመግታት የድንበር ማካለሉን ሥራ በአንድነት እየሰሩ ነው'' ነበር ያሉት።አሁን የንግግር እና የወሬ ጊዜ አይደለም።ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል በሙሉ መለየት አለበት።ኢትዮጵያን ከሸጡ ጋር ነህ ወይንስ አይደለህም? ጥያቄው ይህ ነው።ኢትዮጵያን የከዳ በሙሉ ተገቢውን ቅጣት ማግኘት አለበት።
ኢህአዴግ/ህወሓት ለኢትዮጵያ ድንበር በሞቱት አባቶቻችን ደም ውስጥ እጁን ነክሯል።የኢትዮጵያ የቀደሙት መሪዎች ማናቸውም የኢትዮጵያን ድንበር ጉዳይ ላይ ሲደራደሩ አልታዩም።አፄ ዮሐንስ ከደርቡሽ ጋር ተዋግተው መተማ ላይ አንገታቸው የተቀላው ለአገራቸው ክብር ነው።አፄ ቴዎድሮስ መቅደላ ላይ እራሳቸውን የገደሉት ለኢትዮጵያ ክብር ነው።ዛሬ ሚልዮኖች ያፈሰሱትን ደም እረግጦ የኢትዮጵያን መሬት ለባዕዳን አሳልፎ ለመስጠት የተነሳው የህወሓት ቡድን የሕዝብ ፍርድ ያስፈልገዋል።
ወቅቱ እያንዳንዱ ሰው ለድንበሩ ዘብ የሚቆምበት ጊዜ ነው።ባዕዳን ዳር ድንበሩን ሲፈልጉ ከመሃል በጎሳ እንድንቧደን እና እንድንጋጭ በማድረግ ጭምር ነው።ለእዚህም የሚረዳቸው የአራት ኪሎ መንግስት አለ።ሱዳን የኢትዮጵያን መሬት ስትወስድ ብቻዋን አትሆንም ኢትዮጵያን ለዘመናት ለማዳከም የሚማስኑ የአረብ ሊግ አባላት እና የሩቅ መሰሪዎችንም ይዘው ነው።ጉዳዩ የተቀናበረ ነው።ለኢትዮጵያውያን ቀዳሚውን ሥራ ለመግለፅ የሚያጠቃልለው ሁነኛ አባባል ''ጠላትማ ምን ጊዜም ጠላት ነው።አስቀድሞ መምታት አሾክሿኪውን ነው'' የሚለው ነው።ቀዳሚው ጠላት እኛነታችንን የሸጠን ለ24 ዓመታት በኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ የተንሰራፋው ስርዓት ነው።ቅድምያ ስልጣኑን መልቀቅ ያለበት ህወሓት ነው።የሱዳኑ ጉዳይ 'እዳው ገብስ ነው'።
ወቅቱ እያንዳንዱ ሰው ለድንበሩ ዘብ የሚቆምበት ጊዜ ነው።ባዕዳን ዳር ድንበሩን ሲፈልጉ ከመሃል በጎሳ እንድንቧደን እና እንድንጋጭ በማድረግ ጭምር ነው።ለእዚህም የሚረዳቸው የአራት ኪሎ መንግስት አለ።ሱዳን የኢትዮጵያን መሬት ስትወስድ ብቻዋን አትሆንም ኢትዮጵያን ለዘመናት ለማዳከም የሚማስኑ የአረብ ሊግ አባላት እና የሩቅ መሰሪዎችንም ይዘው ነው።ጉዳዩ የተቀናበረ ነው።ለኢትዮጵያውያን ቀዳሚውን ሥራ ለመግለፅ የሚያጠቃልለው ሁነኛ አባባል ''ጠላትማ ምን ጊዜም ጠላት ነው።አስቀድሞ መምታት አሾክሿኪውን ነው'' የሚለው ነው።ቀዳሚው ጠላት እኛነታችንን የሸጠን ለ24 ዓመታት በኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ የተንሰራፋው ስርዓት ነው።ቅድምያ ስልጣኑን መልቀቅ ያለበት ህወሓት ነው።የሱዳኑ ጉዳይ 'እዳው ገብስ ነው'።
ከእዚህ በታች የሱዳን ትሪቡን ጋዜጣ እኤአ ጥር 17/2016 ዓም ድንበሩ በእዚህ ዓመት እንደሚሰጥ የገለጠበትን ዘገባ ትርጉም ያንብቡ።(ትርጉም ጉዳያችን)
ሱዳን እና ኢትዮጵያ የድንበር ማካለል ስራቸውን በእዚህ ዓመት ያጠናቅቃሉ
ጥር 17/2016 (ካርቱም)
በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል የድንበር ማካለሉን ሥራ ኃላፊነት የወሰደው የቴክኒክ ኮሚቴ በመሬት ላይ ድንበሩን የማካለሉን ሥራ በእዚህ ዓመት እንደሚያጠናቅቅ ገልጧል።ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በኃላ ቆሞ የነበረው የድንበር ማካለሉ ሥራ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም እና የሱዳኑ ፕሬዝዳንት አልበሽር ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው በሰጡት መመርያ መሰረት ስራውን በህዳር ወር 2014 ዓም ቀጥሏል።የቴክኒክ ኮሚቴው ሰብሳቢ አብደላ አል-ሳዲግ ለሱዳን ሚድያ ሴንተር (SMC) እንደገለጡት ኮሚቴው እዚህ ግባ የሚባል ምንም ችግር በስራው አልገጠመውም ነበር።
አብደላ አል-ሳዲግ አክለው እንደገለጡት በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል ያለው የሚካለለው የድንበር ርዝመት 725ኪሜ በሁለቱ አገሮች መካከል ያሉ ገበሬዎች በባለቤትነት ግጭት የተፈጠረበት አል-ፋሻጋ አካባቢ እና ደቡብ ምስራቅ ግዛት ገዳረፍን ያጠቃልላል።
አል-ፋሻጋ 250 ስኩኤር ኪሎ ሜትር እና 600 ሺህ ጋሻ ለም መሬት ይዟል።ከእዚህ በተጨማሪ ቦታው በወንዝ የበለፀገ ሲሆን አትባራ፣ሰቲት እና ባስላም የተባሉ ወንዞች ይገኙበታል።ባሳለፍነው ቅዳሜ እና ዕሁድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢብራህም ጋንዱር መቀመጫውን ኩአታር ላደረገው አልጀዚራ ቴሌቭዥን እንደገለፁት ''ኢትዮጵያ እና ሱዳን በሱዳን ግዛት ላይ የሰፈሩትን ሽፍቶች (gangs) በመግታት የድንበር ማካለሉን ሥራ በአንድነት እየሰሩ ነው'' ከማለታቸውም በላይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በመቀጠል አፅንኦት ሰጥተው እንደተናገሩት ''አል-ፋሻጋ የሱዳን ግዛት ነው።የሱዳን መንግስት የኢትዮጵያ ገበሬዎች እንዲያርሱት ፈቃድ የሰጠውም በሁለቱ አገራት መካከል ባለው ትብብር ሳብያ ነው።ኢትዮጵያም አልፋሻጋ የሱዳን ግዛት መሆኑን አምናለች'' ብለዋል።
ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋንዱር በሁለቱ አገራት መካከል በፕሬዝዳንት ደረጃ በድንበሩ ጉዳይ ውይይት መደረጉን ጠቁመው ውይይቱ በሱዳን ጋዳርፍ እና ብሉ ናይል ግዛት እና በኢትዮጵያ በአማራ ክልል ደረጃም መደረጉን ገልጠዋል።በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል የተሰመረው በእንግሊዝ እና ጣልያን ቅኝ ግዛት ወቅት በ1908 ዓም ነው።ሁለቱ መንግሥታት ድንበሩን እንደገና በማካለል የአካባቢው ሕዝብ መጥቀሙ ላይ ተስማምተዋል።ሆኖም ግን የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ገዢውን ፓርቲ የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን አሳልፎ በመስጠቱ ይከሱታል።
====የሱዳን ትሪቡን ጋዜጣ ትርጉም መጨረሻ===
====የሱዳን ትሪቡን ጋዜጣ ትርጉም መጨረሻ===
Sudan, Ethiopia to complete border demarcation this year
January 17, 2016 (KHARTOUM) - The technical committee tasked with redrawing the border between Sudan and Ethiopia said it would complete its work on the ground during this year.
- A road leading to Ethiopia-Sudan border (Photo Jamminglobal.com)
In November 2014, Ethiopia’s Prime Minister Hailemariam Desalegn and Sudan’s President Omer al-Bashir instructed their foreign ministers to set up a date for resuming borders demarcation after it had stopped following the death of Ethiopia’s former Prime Minister, Meles Zenawi.
The head of the technical committee Abdalla al-Sadig told the semi-official Sudan Media Center (SMC) that the border demarcation between Sudan and Ethiopia doesn’t face any problems.
He pointed out that the length of the border with Ethiopia is about 725 km, saying the process of demarcation is proceeding properly.
Farmers from two sides of the border between Sudan and Ethiopia used to dispute the ownership of land in the Al-Fashaga area located in the south-eastern part of Sudan’s eastern state of Gedaref.
Al-Fashaga covers an area of about 250 square kilometers and it has about 600.000 acres of fertile lands. Also there are river systems flowing across the area including Atbara, Setait and Baslam rivers.
On Saturday, Sudan’s foreign minister Ibrahim Ghandour told the Qatar-based Aljazeera TV that Sudan and Ethiopia are working together to curb the activities of Ethiopian gangs inside Sudanese territory.
He stressed that Al-Fashaga is a Sudanese territory, saying the government allowed Ethiopia farmers to cultivate its land as part of the cooperation between the two countries.
“However, Ethiopia is committed and acknowledges that [Al-Fashaga] is a Sudanese territory,” he said.
Ghandour pointed to joint meetings between the two countries at the level of the presidency to discuss borders issues.
Sudan’s Gadarif and Blue Nile states border Ethiopia’s Amhara region. The borders between Sudan and Ethiopia were drawn by the British and Italian colonisers in 1908.
The two governments have agreed in the past to redraw the borders, and to promote joint projects between people from both sides for the benefit of local population.
However, the Ethiopian opposition accuses the ruling party of abandoning Ethiopian territory to Sudan.
www.gudayachn.com
ጥር 10/2008 ዓም (ጃኗሪ 19/2016)
Wednesday, January 13, 2016
በኢቲቪ መድረክ ላይ በውሃ አስተዳደር የዲግሪ ተመራቂዋ ወጣት ለቅሶ፣ነፃነት! ወይንም ሞት! ይላል (የጉዳያችን ማስታወሻ)
፣
ከክብር ወርደናል።ሕዝብ እንደ ሕዝብ ተገፍቷል።ጥቂት በጎጥ የተጠራሩ ምንደኞች ኢትዮጵያን ለእሩብ ክ/ዘመን አምሰዋታል።በፍቅር ይኖር የነበረ ብሄረሰብ በቢላዋ እንዲተራረድ አደረጉት።አንዱ ላንዱ ይፀልዩ የነበሩ እምነቶች በጥርጥር እንዲተያዩ እና በአንድነት ኢትዮጵያ ስለምትባል አገር እንዳይናገሩ ታፈኑ።ጥንታዊቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን ስለ አገር ጉዳይ በአዋጅ ወደ አምላክ መቼ መፀለይ እንዳለባት ለመንገር የሚቃጡ ቅምጥሎች በቤተ መንግስት ሆነው ሊመሯት ፈለጉ።
መኖር ያስጠላው ሕዝብ፣የመኖር ትርጉሙ የጠፋበት ሕዝብ፣ግፍን ከምሽት እስከ ንጋት መመልከት የመረረው ሕዝብ፣ጥቂት በጎጥ እና በጥቅም የተጠራሩ የትውልድ ነቀርሳዎች ከህዝብ በዘረፉት ገንዘብ ሲቀማጠሉ መመልከት የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመቼውም ጊዜ በባሰ ሰልችቶታል።
የተራቡ ልጆቹን በአግባቡ መመገብ ያልቻለ አባወራ፣የልጆቿን መራብ እና መጠማት እየተመለከተች መግቢያ ያጣች እናት ዛሬ ከምን ጊዜውም በላይ ለለውጥ ብትነሳ ሲያንስባት እንጂ አይበዛባትም።
የወጣቷ መከራ የጎጠኛው ስርዓት የአድልዎ ውጤት
መማር በእራሱ በጎጥ ካባ ካልተሸፈነ ለውጤት የማያበቃ መሆኑን ለማየት ባሳለፍነው ገና ለእይታ የበቃውን የአንዲት የአዲስ አበባ ወጣትን ታሪክ ማንሳቱ በእራሱ ይበቃል።የወጣቷ ታሪክ መጀመርያ በሸገር ላይ ከተላለፈ በኃላ የአፍቃሪ ሕወሃቱ እና የኢትዮ-ቻናል ጋዜጣ አዘጋጅ ሳምሶን በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ያለፈው የገና ዝግጅት ላይ ወጣቷን በአካል ይዞ ብቅ አለ።እንደ ሳምሶን አገላለጥ ልጅቱ ጠንካራ ሰራተኛ በመሆኗ ነው ያቀረባት። በእርግጥ ወጣቷ ጠንካራ ሰራተኛ ነች። ሆኖም ከጠንካራ ሰራተኛነቷ ባለፈ ግን የኢትዮጵያ የተማረ ወጣት እንዴት በዘረኛ እና አፋኝ ስርዓት ውስጥ ትምህርቱን ቢማርም ለምንም አይነት ውጤት እንደማይበቃ የሚያመላክት ነው።
ወጣቷ ከመቀሌ ዩንቨርሲቲ በውሃ አስተዳደር ተመርቃለች።ሆኖም ግን ጊዜው ወጣቱ በሙያው እና በተማረው ትምህርት ሥራ የሚያገኝበት አይደለም እና ሥራ አጥታ ለአመታት ተቀመጠች።ይታያችሁ ስንት ወንዞች እና የከርሰ ምድር ውሃ ባለባት አገር አንዲት በውሃ አስተዳደር የተመረቀች ያውም ወጣት ሴት ሥራ አጥታ ተቀመጠች።የጎጥ እና የጥቅም ተጋሪዎች ግን ገና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሳሉ በሀብት ይንበሸበሻሉ።ይህች ወጣት ግን በውሃ ምህንድስና ትመረቅ እንጂ የውሃ ማማ በተባለችው የኢትዮጵያ ምድር በሺህ እንደሚቆጠሩት የእድሜ አቻዎቿ ሥራ ማግኘት አልቻለችም።ይልቁንም በልጆች ምሳ መያዣ ላስቲክ ውስጥ አድርጋ መርካቶ በቀን ሥራ ለሚተዳደሩ ሰራተኞች መሸጥ ጀመረች።''ምሳ ሰዓት ላይ አንድ የምሳ ስህን ከአንድ የላስቲክ ውሃ ጋር አድርጋ እያደለች ትሄድ እና ከቀትር በኃላ ተመልሳ ትሰበስበዋለች'' ይላል አንድ ለሸገር ራድዮ ቃሉን የሰጠ ወጣት።
የውሃ መሃንዲሷ ወጣት የስርዓቱ አቀንቃኝ እንደሆነ የሚነገርለት የኢትዮ ቻናል ሳምሶን በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ፊት በተሰበሰበው ሕዝብ መሃል ሲያቆማት ወጣቷ እንባዋ ይወርድ ነበር።ወደ መሬት አቀርቅራ ታለቅሳለች።ሳምሶን ስለስራዋ ታታሪነት ይናገራል።እርሷ ግን ማልቀሷን አላቆመችም።በእርግጥ ለወጣቷ የተለያዩ ድርጅቶች እና ግለሰቦች የገንዘብ አስተዋፅኦ አድርገዋል።የህ በእራሱ በጎ ተግባር ቢባልም የወጣቷ ውክልና ግን የኢትዮጵያን ወጣቶች በሙሉ ነው።ተምረው እንዳልተማሩ የተገፉት፣በጎጥ ማጥለያ እንዲገፉ ሆነው ከስራ ዓለም የተባረሩ እና የሚሰሩት ሥራ የባርነት ቀንበር ሆኖባቸው ለሚገኙት ሁሉ ወጣቷ በመድረኩ ላይ እንባዋን አፈሰሰች።
የእዚች ወጣት ሁኔታ ሥራ በማጣቷ አማራጭ ሥራ ሰራች እፁብ እፁብ በማለት የሚታለፍ አይደለም። ይልቁንም በእርሷ ማሳያነት ኢትዮጵያን ጠርንፎ የያዘው የህወሓት የጎጥ መርዝ ነቅሎ መጣል ብቸኛ አማራጭ እንደሆነ የሚያሳይ አንዱ እና አይነተኛው ማሳያ ነው።ሃያ ዓመት ያልዘለላቸው የጎጡ አባል በመሆናቸው ብቻ እና የሙሰኛ ባለስልጣናት ወገን ሰልሆኑ ቪላ ቤት እና መኪና በሚሰጥበት አገር በብዙ መከራ እና ጥረት የውሃ አስተዳደር በዲግሪ ደረጃ ያጠናችው ወጣት የሥራ ዕድል አጥታ ኢቲቪ በተቆራረጠ ጆንያ በተሰራ ማዕድ ቤት ውስጥ የምትሸጠውን እንጀራ እና ወጥ ስትሰራ ያሳየናል።የወጣቷ ጥረትም ሆነ የንግድ ፈጠራዋ የሚደነቅ ነው።በጎጥ የምትተዳደር አገር ውስጥ ሆና ተምራ እንዳልተማረች አገሯን ለማገልገል ሳትችል መቅረቷ ግን የምንም ውጤት ሳይሆን አገራችን በጎጥ ባርነት ውስጥ በመተብተቧ ሳብያ የመጣ ነው።ይህ ችግር ደግሞ ካለ ነፃነት አይጠራም።የወጣቷ የመድረክ ላይ ለቅሶም ሌላ አይደለም።እነ ሳምሶም እና መሰሎቹ ''የእኔ'' የሚሉት ጎጠኛው ስርዓት አፈና ነው።እንዳትናገር እነ ሳምሶን ቆመዋል።እንዳትተወው ብሶቱ ይገፋል።
ጉዳያችን Gudayachn
www.gudayachn.com
ጥር 4/2008 ዓም (ጃንዋሪ 14/2016)
Sunday, January 10, 2016
ሁላችንም ነፃ ካልወጣን ማንም ነፃ ሊሆን አይችልም (የቪድዮ መልዕክት)
ምንጭ:- ሶሊዳሪቲ እንቅስቃሴ ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ (Solidarity Movment for New Ethiopia)
ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
Monday, January 4, 2016
ሰበር ዜና - በሳውዲ አረብያ እና በኢራን መሃከል ውጥረቱ ተባብሷል፣የዲፕሎማቲክ ግንኙነት እና በረራ ቆሟል።ሱዳን ከሳውዲ ጎን መሰለፏ እየተነገረ ነው (የጉዳያችን አጭር ጥንቅር)
በሳውዲ አረብያ እና በኢራን መሃከል ያለው ውጥረት ጨምሯል።የዲፕሎማሲ ግንኙነት አቁመዋል።
ሱዳን እና ባህሬን ከሳውዲ ጎን ቆመዋል።ጉዳዩ ከየመኑ ሁኔታ ጋር ተያይዞ የአካባቢውን አገራት ሊያነካካ ይችል ይሆን? የሚል ጥያቄ አስነስቷል።ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ የማነካካቱ ጉዳይ ለብዙዎች ጥያቄ አይደለም።ነገር ግን ጥያቄው በምን ያህል ደረጃ የሚለው ነው።ኢራን የሚገኘው የሳውዲ ኢምባሲ ጥቃት ደርሶበታል።ይህንን ተከትሎ የሁለቱ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ቆሟል።
ዛሬ ሰኞ ታህሳስ 25/2008 ዓም ደግሞ በሁለቱ አገራት መሃከል የነበረው የአየር በረራ መቆሙ ተሰምቷል።ብዙውን ጊዜ የአየር በረራ በሁለት አገራት መሃከል የሚቆመው በተለይ ከዲፕሎማቲክ መቆም ቀጥሎ ሲከተል መጪው ወታደራዊ ግጭት ሲሆን ማየት በአለማችን በርካታ የግጭት ሂደቶች የተለመደ ሁኔታ ነው።ሲ ኤን ኤን ዛሬ ታህሳስ 25/2008 ዓም የሳውዲውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአገራቸው እና በኢራን መሃከል ያለው የበረራ አገልግሎት ብቻ ሳይሆን የቆመው ዜጎቻቸውም ፈፅሞ አንዳቸው ወደ አንዳቸው አገር እንዳይሄድ እቀባ መጣሉን ገልፀዋል።ለጉዳዩ በፍጥነት መባባስ አንዱ ምክንያት የተባለው የኢራን ሰልፈኞች የሳውዲን ኤምባሲ ማጥቃታቸው ነው። የኢራን ወጣት ደግሞ ኤምባሲ መውረር ከቀደሙት አባቶቹ የወረሰው ልማድ ሆኖ ዘመናትን ተሻግሯል።ከእዚህ በፊት በቀቃዛው ጦርነት ወቅት ቴራን የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ መወረሩ ይታወሳል።
ኢራን ባብዛኛው የሺአ እስልምና ተከታይ ሲበዛባት ሳውዲአረብያ የሱኒ ሙስሊም ተከታዮች ይበዙባታል።ዩናይትድ አረብ ኢምረት፣ባህሬን እና ሱዳን ከሳውዲ አረብያ ጎን እንደቆሙ የታወቀ ሲሆን።ሁኔታው የመካከለኛው ምሥራቅን ባጠቃላይ ሊያበጣብጥ ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት አለ።በሌላ በኩል የቀድሞው የእንግሊዝ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚስተር ጃክ ስትሮው ለሲኤንኤን ቀርበው ሲናገሩ ግጭቱ ለአይ ኤስ ኤስ ሽብርተኛ ቡድን መስፋፋት ምክንያት እንዳይሆን የሚል ስጋታቸውን ገልጠዋል።
በመጨረሻም የኢራን እና የሳውዲ ግጭት የመካከለኛውን ምስራቅ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ቀንድም የራሱ የሆነ አንድ አይነት ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ጥላ ይዞ እንደሚመጣ ለማወቅ ይቻላል።ኤርትራ የመንን በአየር ለሚደበድበው የሳውዲ ቡድን ድጋፍ መስጠቷ ይታወሳል።የሳውዲ እና የኢራን ውጥረት ለሌሎች የነዳጅ ሻጭ አገሮች ደግሞ ሰርግና ምላሽ ነው።ምክንያቱም የነዳጅ ዋጋ ከአሁኑ የዋጋ መጨመር ማሳየት ጀምሯል።በነገራችን ላይ የሁለቱ አገሮች የቃላት ጦርነት ከአሁኑ እየተሟሟቀ ነው።የሳውዲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዛሬ ሰኞ ሲ ኤን ኤን ቀርበው ቆጣ ባለ እና በአረብኛ ቃና በተቃኘ እንግሊዝኛ ''ኢራን የሳውዲን ኃይል ንቃው ከሆነ በጣም ተሳስታለች'' ሲሉ ታይተዋል።
ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com
ታህሳስ 26/2008 ዓም (December 5/2016)
Subscribe to:
Posts (Atom)
የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።
የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...
-
የቅዱስ ላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ጉዳያችን/ Gudayachn ሰኔ 2/2011 ዓም (ሰኔ 8/2019 ዓም) ግንቦት 29/2011 ዓም ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል በለቀቀው ዜና እንዲህ ይነበባል: - ...
-
Foto source:- Royal Norwegian Embassy in Addis Ababa, Ethiopia http://www.norway.org.et/News_and_events/press_releases/New-Norwegia...
-
በ ካርታ ጫወጣ ጎበዝ አደለሁም። ግን ጆከር የተባለች ካርታ መኖሯን አውቃለሁ።ጆከር ካርታ በ ሁሉም ቦታ ስለምትገባ በ ካርታ ጫወታ ጆከር የደረሰው ሰው የማሸነፍ እድል ስላለው ፊቱ በ ፈገግታ ይሞላል። የ አትዮጵ...