ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, April 27, 2020

እናመሰግናለን! እንልመድ።ጉዳያችን አራት የኢትዮጵያ ሰዎችን ዛሬ ልታመሰግን ትወዳለች።

የኛ ማኅበረሰብ አንዱ ችግር መልካም ላደረገ እናመሰግናለን ከማለት ይልቅ ትንሽ ስህተት ለማግኘት ብዙ የሚደክም  መሆኑ ነው።ይህ ደግሞ ከቤተሰብም የማመስገን ባሕል አለመውረስም ጭምር ነው።እቤት ውስጥ ሲመሰጋገኑ እያዩ አለማደግ በራሱ ይዞ የመጣው ችግር አለ።አባት ልጁን ካመሰገነ የበለጠ እንዳይሰራ አኮራዋለሁ ብሎ ያስባል፣እናትም ልጇን ማድነቅ እና መመስገን ያዘናጋዋል ብላ ታስባለች።ይህ ሁሉ ወደ ባሕላችን እየገባ ነው። የማኅበራዊ ሚድያውም ከባሕላችን ውጪ አይደለም።የኛው ነፀብራቅ ነው።እስኪ ማመስገን እንልመድ።
የሚለፉትን ማመስገን ጤናማነት ነው።

ከእዚህ በታች የምትመለከቷቸውን እንደናሙና ነው ያቀረብኩት።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ሊመሰገኑ ይገባል



በእዚህ በኮሮና ወረርሽኝ ዘመን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ ነገ ስንት አስከሬን ይቆጠር ይሆን? ነገ ከቀውስ ኢትዮጵያን እንዴት ማውጣት ይቻላል? እያሉ ሌት ከቀን መጨነቅ ምን ማለት እንደሆነ ካልገባን ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይን እንዴት ማመስገን እንችላለን? በእርሱ ቦታ ስንት ጉዳዮች እንቅልፍ አሳጥተው እንዲሰራ እያደረጉት መሆኑን ካልገመትን እንዴት ማመስገን እንችላለን።ይህንን ካላሰብን ነው ጥቃቅን ነገር እየፈለግን ባልተጨነቀ እና ግዴለሽ አዕምሮ ውስጥ ሆነን የፈለግነውን እየፃፍን አሉታዊ ነገር ስናደምቅ የምንውለው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የጎደለባትን በየአገሩ እየደወሉ መጠየቅ፣የአገር ውስጥ የዕለት ከዕለት ጉዳይ መከታተል፣በየክልሎች ያለው ጉራማይሌ የስልጣን ጥማት እና የፅንፍ ኃይሎች ተንኮል ሁሉ ጋር መሟገት ምን ያህል እረፍት ነሺ ሥራ መሆኑ ካልገባን ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማመስገን አንችልም።

ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት ወሳኝ ጊዜ ላይ ኮሮና ሲከሰት የነበረ ዕቅድ በሙሉ ሰርዞ ወይንም አቆይቶ አዲስ የአደጋ ጊዜ ዕቅድ አውጥቶ መምራት ምን ያህል አቅም የሚጠይቅ ሥራ መሆኑ ካልገባን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩን የማናመሰግነው።ስለሆነም ጠቅላይ ሚኒስትሩን እናመሰግናለን።

የጤና ጥበቃ ሚንስትሯ  ዶ/ር ሊያ ታደሰ ሊመሰገኑ ይገባል


በኮሮና ዘመን የጤና ሚኒስትር መሆን ምን ማለት እንደሆነ የሚሰማን የታመሙ ሰዎች ቁጥር ለመንገር ወደ ሚድያ ላይ መውጣት እና ሕዝቡን ማርዳት ምን ያህል አስጨናቂ ጉዳይ እንደሆነ ሲገባን ነው።ነገ ምን ያህል አስከሬን እንደሚያመጣ ያልታወቀ በሽታ ጉዳይ በሴት ስሜት ቀን ከሌሊት በማሰብ እና የመምራቱ ኃላፊነትም እራስ ላይ መውደቅ ምን ማለት እንደሆነ ከተረዳን ብቻ ነው።

የኮሮና ወረርሽኝ የተያዙ ቁጥር፣የዳኑ እና ያገግሙ ሁኔታ ሌሊቱን ሪፖርቱን እየጠበቁ ማደር አንዳንዴም ሌሊት ተነስቶ ሪፖርት መፃፍ ከቤተሰብ ኃላፊነት ጋር ምን ማለት እንደሆነ ሲገባን ነው የጤና ሚኒስትሯን የምናመሰግነው።ስራው የሞራል ጥንካሬ፣ትጋት እና የአደጋ ጊዜ የአስተዳደር ብቃት ሁሉ ይጠይቃል።ስለሆነም የጤና ሚኒስትሯን እናመሰግናለን።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ  አቶ ተወልደ  ሊመሰገኑ ይገባል


አቶ ተወልደን የማውቃቸው (እርሳቸው ላያውቁኝ ይችላሉ) ከሃያ ሶስት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ የገበያ ክፍል ውስጥ ባልሳሳት የዲፓርትመንት ክፍል ኃላፊ ሆነው ነው።እኔ አየር መንገድ ውስጥ ያለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞች አገልግሎት ላይ ሲመጡ እና ስናገለግላቸው አውቃቸዋለሁ።አገልግሎቱ እስኪያልቅ ድረስ ካውንተሩ ላይ ትንሽ ቆም ብለው የሚያወሩን የበሰሉ ንግግሮች አሁንም ድረስ አስታውሳለሁ።ትልቅ ዲስፕሊን ያላቸው፣ትሑት እና በወቅቱ ለእኛ ተራ የባንኩ ሰራተኞች ሳይቀር አክብሮት ያላቸው ናቸው።

እሳቸውን በሚያውቁ ሰዎችም እንደምረዳው ለእምነት እና ለሞራል ዋጋ የሚሰጡ፣ዕምነት የግል ቢሆንም አንዳንዶቻችን በእርሳቸው ቦታ ያለ ሰው ብዙ ጉዞ፣ግብዣ የሚያስተናገድ ሰው አይችልም የምንለውን በእምነታቸው  በፈቃድ እንጂ የማይገደዱበት ''የፅጌ ፆም'' በመባል የሚታወቀውን የክርስቶስን የስደት ወራት ፆም ሳይቀር የሚፆሙ፣በበርካታ ስብሰባዎች ላይ እና ዓለም አቀፍ ጉዞዎች ውስጥ ይህ የግል ዕምነታቸው የማይጣረስባቸው ግለሰብ ናቸው። ይህንን ስብዕና በሥራ ሂደት በተሰሩ የስራዎች ሂደት እያስታከኩ  ያላደረጉትን እንዳደረጉ አድርጎ ማብጠልጠት ግለሰብን ብቻ ሳይሆን አገር ይጎዳል።

በእርግጥ በአመራር ወቅት ኃይለኛ ናቸው የሚሉ ይኖራሉ።ይህንን አንድ ጊዜ ተጠይቀው የመለሱት ሚዛን ይደፋል። ''የአየር መንገድ ሥራ እንደ ወታደር ሥራ ነው። ትንሽ ካዛነፍክ ብዙ ነገር ይበላሻል ስለሆነም በሥራ አመራር ላይ ጠጠር የምለው ለእዚህ ነው።ይህም ሆኖ ግን በውሳኔ ላይ በቡድን ነው የምንወስነው።ብዙ ክርክሮች ተደርገው ነው ውሳኔዎች የሚሰጡት'' ነበር ያሉት።ይህንን አባባላቸውን በሸገር ራድዮ ምናልባት አንድ ዓመት ባልሆነው ጊዜ ውስጥ ተላልፏል።

እኝህ ሰው አሁን በቀውስ ላይ ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥራ አስኪያጅ ናቸው።በብዙ ፈተና ላይ የሚገኘው አየር መንገድ በእዚህ ጊዜ ከሌላው ዓለም አየር መንገዶች በተለየ በካርጎ ንግዱ እንዲጠነክር እየሰሩ ነው።በቀውስ ውስጥ አየር መንገድ መምራት ምን ማለት እንደሆነ ካልገባን አናመሰግናቸውም።ስራው አየር መንገዱን ከቀውስ አስተዳደር አውጥቶ ወደ ነበረበት የመመለስ ትልቅ ሥራ ነው።ስለሆነም አቶ ተወልደን እናመሰግናቸዋለን።

ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ የውሃ፣መስኖ እና ኢነርጂ ሚንስትርን እናመሰግናቸዋለን


በኢትዮጵያ በውሃ ቴክኖሎጂ እና ተያያዥ ሙያዎች አሉ ከተባሉ ምሁራን ውስጥ ናቸው።በዓባይ ግድብ ዙርያ ብዙ ምክረ ሃሳቦች ከመስጠት አልፈው የአካባቢው ከውሃ ጋር በተያያዘ ያለውን ጅኦፖለቲካ ጉዳይ ላይ ልምድ አላቸው።ኢትዮጵያ ከግብፅ እና ሱዳን ጋር ባደረገችው ድርድር ሚናቸው ቀላል አይደለም።የፖሊሲ አውጪዎች እንዴት ማሰብ እንዳለባቸው ቅርፅ የመስጠት ሚና እንዳላቸው ይነገራል።ከሁሉም በላይ በጠንካራ የኢትዮጵያዊነት ስሜት በግድቡ ዙርያ የሚያሳዩት ቁርጥ ሃሳብ ያስመሰግናቸዋል።''ግድቡ የእኔ ነው!'' የሚለው አባባላቸው ዛሬም ብዙዎች ጆሮ ላይ ይጮሃል።

እኚህ ሰው በዓባይ ግድብ ድርድር ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሂደቱን በማጥናት ብዙ ሌሊቶች ካለእንቅልፍ እንዳሳለፉ መገመት ቀላል ነው።ምሁርነት ማኅበራዊ ሚድያ ላይ ተቀምጦ መሪዎችን ከመስደብ እና ከመተቸት ያላለፈ ሥራ በሚሰራበት ዘመን ዶ/ር ኢንጅነር ስለሺን አለማመስገን አይቻልም።ስለሆነም እናመሰግናቸዋለን።

ባጠቃላይ በርካቶች ያላመሰገንናቸው የህዝብ አገልጋዮች አሉ።ከላይ የተጠቀሱት ግንባር ቀደም ከሆኑት ውስጥ ተነሱ እንጂ ብዙዎች ሊመሰገኑ የሚገባቸው አሉ።ማመስገን መልመድ ጤናማነት ነው።ለመንቀፍ ብቻ መሮጥ ደግሞ የመታመም ምክንያት ነው።ባለማመስገናችን መልካም የሰሩትን እናጣለን።በማመስገናችን ለበለጠ ሥራ እናተጋቸዋለን።

ጉዳያችን ሚድያ፣ኮሚኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት 
Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant
ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Sunday, April 26, 2020

የሰንበት በረከት - ዘወትር ዕሁድ በየሳምንቱ በአውሮፓ ያሉ ምዕመናን በሙሉ በአውሮፓ ሰዓት አቆጣጠር ከ17 (5pm) እስከ 19 (7pm) ሰዓት ከቤታቸው ሆነው በቀጥታ እየተያዩ በአንድ ጉባኤ የሚታደሙበት ጉባኤ መረጃ እና የትንሣኤ መዝሙር


- በዛሬው መርሃግብር መጋቢ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ትምህርት ይሰጣል።

በዘመነ ኮሮና ወረርሽኝ ብዙ ምዕመናን ያጡት አንዱ ጉዳይ በአንድ ጉባኤ ተሰብስቦ የእግዚአብሔርን ቃል መማር ነው።በአውሮፓ ግን ቀላል መንገድ አለ።ዘወትር ዕሁድ ከቤትዎ ሆነው ከቤተሰብዎ ጋር ወይንም ብቻዎን የሚማሩበት በአውሮፓ ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ምዕመናን በአንድ ጉባኤ የሚታደሙበት የትምህርት፣የመዝሙር የአገልግሎት ጉባኤ ከተጀመረ ሳምንታት ሆነውታል።

በጉባኤው ላይ ከየትኛውም የዓለም ክፍል መሳተፍ የሚችሉ ሲሆን በአውሮፓ የሚኖሩ በተለይ ባያመልጣቸው ይመከራሉ። በጉባኤው ላይ ከአገር ቤት እና ከልዩ ልዩ የዓለማችን ክፍሎች አገልጋዮች እየገቡ ትምህርት ሰጥተዋል፣ዝማሬ አሰምተዋል። በቅርቡ ዘማሪ ይልማ ኃይሉን ጨምሮ መምህር ብርሃኑ አድማስ እና ሌሎች አባቶች አገልግለዋል።በዛሬው ጉባኤ ደግሞ መጋቢ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ይገኛሉ።

ወደ ጉባኤው በዩቱብ እና ሪንግ ሴንትራል በመግባት በቀጥታ መከታተል  ይችላሉ።
ዩቱብ ሊንክ

ዝርዝሩን ከስር ካለው ፖስተር ላይ ይመለከቱ።ከፖስተሩ ስር የትንሣኤ መዝሙር ይመልከቱ።


የዲያቆን ፍሬዘር  ደሳለኝ መዝሙር 


ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Friday, April 24, 2020

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን አስረኛ ዓመቱን እያከበረ ነው።የኢሳት ቦርድ አስረኛ ዓመቱን ምክንያት በማስመልከት መግለጫ አውጥቷል።ሙሉ መግለጫውን ያንብቡ።



የዛሬ አሥር  ዓመት በሶስት የዓለማችን ታላላቅ ከተሞች ቢሮዎች ከፍቶ ስራውን የጀመረው ኢሳት፣በኢትዮያ የሚድያ ታሪክ ውስጥ በመላው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በማስተባበር፣በጉዳዮች ላይ የጋራ ግንዛቤ እንዲወስዱ በማድረግ እና ትክክለኛ መረጃ በመስጠት እና መረጃውም በውጭ እና በአገር ውስጥ እስከ ትንሿ የገጠር መንደር ድረስ በራድዮ እና በሳተላይት በመድረስ ታላቅ ገድል የፈፀመው ኢሳት አስረኛ ዓመቱን እያከበረ ነው።ከእዚህ በታች የኢሳትን አስረኛ ዓመት በማስመለከት የኢሳት ቦርድ ያወጣው መግለጫ ይመልከቱ።
====================================
  የኢትዮጵያሳተላይትቴሌቪዥን


__________________www.ethsat.com__________________
Holland : Washington DC : Addis Abeba

   

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ራድዮ  (ኢሳት) የተመሰረተበትን 10ኛ  ዓመት አስመልክቶ ከኢሳት ቦርድ የተሰጠ መግለጫ

የዛሬ አስር ዓመት የነበረውን የኢትዮጵያ ተጨባጭ እውነት መለስ ብለን ስናስብ ሀገራችን መፈናፈኛ በሌለው አፈና የተዘጋችበትና ሕዝባችን ምንም ዓይነት መረጃ እንዳያገኝ ዙሪያ ገባው የተደፈነበት የድቅድቅ ጨለማ ወቅት ነበር። ሕዝብን ከመረጃ በመነጠል አደንቁሮ ለመግዛት የተዘረጋውን የአፈና መረብ ለመበጣጠስና ያለመረጃ ፍሰት የሕዝብ ነጻነት ሊመጣ  እንደማይችል በተረዱ ቆራጥ የሕዝብ ወገንተኞች ጥረት የኢትዮጵያዊያን ሁሉ የጋራ ድምጽ ለመሆን  ኢሳት ሊወለድ ችሏል። የኢሳት መመስረት ለመረጃ አልባው ሕዝባችን ትልቅ ብስራት የነበረውን ያህል ድንቁርናንና አፈናን እንደ አይነተኛ የመግዢያ ዘዴ ለሚጠቀሙት ጨቋኞች ከፍተኛ መርዶ ነበር። በመሆኑም አፋኙ ገዢ ቡድን ስርጭቱን በማፈን፣ በዲፕሎማሲ፣ በገንዘብ ኃይል፣ በውስጥ ቡርቦራና በሌሎችም መንገዶች ተቋሙን ገና በጠዋቱ የማዘጋት የሞት ሽረት ዘመቻ የከፈተ ቢሆንም ሕዝባችን ነጻ መረጃ ማግኘት አለበት ብለው የተነሱት የሕዝብ ወገኖችና ከጀርባ በደጀንነት የተሰለፈው ደጋፊ ተባብሮ ተቋሙ በጠላቶች ዘንድ በተዘመተበት ሁኔታ ሳይወድቅ እነሆ አስር ዓመታትን መዝለቅ ችሏል። ኢሳት ከተመሠረተ በኋላ በአንድ በኩል ሰቆቃዊ በሆነ የመስዋእትነት መንገድ መረጃዎችን እየሰበሰበ ለሕዝብ በማድረስ፣  በሌላ በኩልም ከአፈና ሥርዓቱ ጋር ያደርግ የነበረው ግብግብ ፈታኝ የሚባል ብቻ ሳይሆን የሚገፋ በማይመስልበት በዚያ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ በሠራው ያልተቋረጠ የሕዝብ ወገንተኝነት ሥራ ሕዝባችን እንዲደራጅ፣ ለነጻነቱ እንዲታገልና መብቱን እንዲጠይቅ ብሎም እንዲያስከብር ከፍተኛ የማንቃት ሥራ  ለረጅም ጊዜ በብቸኝነት  ሠርቷል። 

የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዳር እስከዳር ላደረገው የአልገዛም ባይነት ትግል እና ተያይዞ ለተገኘው ሀገራዊ ለውጥ ኢሳት በመረጃ አቅራቢነትና አሰራጭነት በግንባር ቀደምነት ያደረገው አስተዋጾ ሁሉም የሚመሰክረው ሀቅ ነው። ኢሳት የጭቁኑ ሕዝባችን ድምጽ መሆን ብቻም ሳይሆን ሌሎች ሚዲያዎችም ፈለጉን ተከትለው እንዲከፈቱና እንዲስፋፉ በኢትዮጵያ ሚዲያ ታሪክ የፋና ወጊነት ሚናም የተጫወተ ነው። ኢሳት ከጽንሱ ጀምሮ ዓላማውን በሁለት ዙር ከፍሎ ነው የተንቀሳቀስውም። ኢሳትና ደጋፊዎቹ በመጀመሪያው ዙር ዓልመው የተገበሩት የወያኔ መራሹን አገዛዝ ከሕዝቡ ጫንቃ ማስወገድ ከሞላ ጎደል በስኬት ተገባዷል ማለት ይቻላል።

የሚቀጥለውና ሁለተኛው ዙር የኢሳትና የደጋፊዎቹ ሥራ በኢትዮጵያና በአካባቢዋ ወደፊት ተራማጅ፣ ዲሞክራቲክ፣ የበለጸገና  ፍትሐዊ ሕብረተሰብን ለመገንባት በሚደረገው ጉዞ ተቀዳሚ የመረጃና የዕውቀት ምንጭ ሆኖ የመገኘት የረጂም ጊዜ ራዕይ ላይ የተመሰረተ ነው። ከራዕዩ ለመድረስም በኢትዮጵያችን ንቁና ብሩህ የሆነ ዜጋን ማፍራትን ግድ ይላል። ኢሳት በተሰማራበት የሚዲያ ማምረትና ማከፋፈል ሥራ አማካኝነት፤

  • በባህል ብዛሃነትና በእጅጉ በካበተ ታሪካዊ ማንነት ላይ የተመሠረተ፣
  • በሀገሩና በዓለም ጉዳይ ላይ በበቂ መረጃ ያለው፣
  • በሀገሩ ህብረተሰባዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ላይ ሙሉ ተሳትፎ የሚያደርግ፣
  • ለዲሞክራሲያዊ እሴቶችና መርሆች የጸና አቋም ያለው ዜጋ ማፍራትና ማበራከትን እንደዋና  የሥራው ዓላማና ተልዕኮ አድርጎ ሥራ ጀምሯል።
 እነዚህን ጥልቅ ማህበራዊ ለውጦች እውን ለማድረግ  በሚዲያ በኩል የሚያስፈልጉትን ግብአቶች ቀስበቀስ ለማሟላት ኢሳት ከአሁን ጀምሮ በውስጥ አደረጃጀት፣ በዘመናዊ ማነጅመንት፣ በፕሮፌሽናል ጋዜጠኝነትና በልዩ ልዩ የፕሮግራም ይዘቶች ፈጠራና ስርጭት ክህሎት የሚያስፈልጉትን የሰውና የቁሳቁስ ዓይነቶች የማግኘት ተግዳራቶች ተገንዝቦ መሄድ እንዳለበት ያውቃል። በአሁኑ ወቅት የኢሳት ቦርድና የኢሳት ልዩ ልዩ የሥራ ዘርፎች ኢሳትን ወደዚህ ብቃት የሚሸጋግሩትን ተግባሮች እያከናወኑ ይገኛል። 
በመሆኑም በዚህ መልክ ዛሬ በጠንካራ መደላድል ላይ የምንተክለው ኢሳት ከትውልድ ትውልድ በአርአያነት የሚያገለግል የሕዝብ ተቋም እንደሚሆን እንተማመናለን።
ዛሬ የኢሳትን አስረኛ ዓመት በምናስብበት ወቅት ዓለምን የገጠመው የኮሮና ወረርሽኝ በሀገራችን የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ሕዝባችን ከተገቢው ምንጭ የመረጃ አቅርቦት እንዲያገኝና ግንዛቤ እንዲሰፋ የሚዲያ  ሚናውን በተገቢው ለመወጣትና ሕዝቡን ለማገልገል ያለመታከት እየሠራ ይገኛል። 
በመጨረሻም ከፍ ባለ አጽኖት የምናነሳው ታላቅ ቁም ነገር ቢኖር ኢሳት ፈተና ባልተለየው የአስር ዓመት ጉዞው ወቅት በሀገር ውስጥ መረጃ ከማቀበል አንስቶ በጋዜጠኝነት፣ በካሜራና ቴክኒክ፣ በአስተዳደር ብዙዎች ተዘዝሮ የማያልቅ ዋጋ ከፍለዋል። በመላው ዓለም ያሉ ደጋፊዎች በዚህ ሁሉ ጊዜ የጀርባ አጥንት ሆነው ተቋሙን ለዛሬ አብቅተዋል። በዚሁ አጋጣሚ ሁላችሁንም እንኳን ለኢሳት 10ኛ ዓመት ምስረታ አደረሳችሁ እያልን ያለእናንተ ድጋፍ ኢሳት አስር ዓመት ሊዘልቅ የሚችልበት አቅም አልነበረውምና  ላደረጋችሁት ታሪክ የማይረሳው አስተዋጽኦ በኢትዮጵያ ሕዝብ ፊት ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርብላችኋለን። 
ስናጠቃልልም የኢሳት ራዕይ የጋራ ሀገራችንንና ሕዝባችን ነው። የምንጓዘው መንገድ ከመጣንበት ይረዝማል። ሀገራችን ስጋትም ተስፋም የተፋጠጡባት ናት። በዚህ ዓይነት ሀገር ፈተና ውስጥ ባለችበት ወቅት እንደኢሳት አይነት ስለሁላችንም ሀላፊነት የሚሰማው ሚዲያ የግድ ይላል። ነገ ለምናልማት ኢትዮጵያም ጠንካራ ሀገራዊ የጋራ ራዕይ ያለው ሚዲያ አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ግድ ነው። ኢሳት ሀገራዊ የሚዲያ ሀላፊነቱን የሚወጣ ጠንካራ ተቋም እንዲሆን በሙሉ ልብ እየሠራን መሆኑን እያረጋገጥን ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ኢሳትን በመደገፍ ረገድ እንደትናንቱ ሁሉ ዛሬም አብራችሁን እንድትቆሙ ጥሪ እናደርጋለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ!! 
ኢሳት የኢትዮጵያ ሕዝብ አንደበት፣ ዓይንና ጆሮ ሆኖ ይቀጥላል!!
የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ራድዮ (ኢሳት) ቦርድ            




ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Wednesday, April 22, 2020

የኤልሳቤጥ ከበደ ታፋ በሐረር ፖሊስ ከአዲስ አበባ ታፍና መወሰዷ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ብቻ ሳይሆን በሴቶች ላይ የተፈፀመ ወንጀልም ነው።


Ethiopian Elizabeth Kebede Tafa (attorney) is illegally imprisoned by Harar Regional police in Ethiopia for over two weeks.The sole reason for her imprisonment was her comment on social media regarding the illegal status of the Harar Regional administration in Ethiopia. Human Right Organizations are expected to speak out loudly about her right of expression.

ኤልሳቤጥ ከበደ የሕግ ባለሙያ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ከአንድ ሳምንት በፊት በሐረር ያለውን አስተዳደር የሕግ ክፍተት በተመለከተ በማኅበራዊ ሚድያ አስተያየት ሰጠች።በእዚህ አስተያየቷ በቪድዮ በተደገፈ ማብራርያዋ የሐረር ምክር ቤትም ሆነ ተግባርና ኃላፊነት በተመለከተ ከሙያዋ አንፃር ማብራርያ ሰጥታለች።ሆኖም ግን ማብራርያውን ከሰጠች በኃላ የሐረር ክልል ፖሊሶች እንደሆኑ የተናገሩ ሰዎች ከአዲስ አበባ በግድ ይዘዋት ሄደው በሐረር እስር ቤት እንድትገባ ሆናለች።ጉዳዩን አስመልክተው የተቃወሙ  በጣት የሚቆጠሩ አክትቪስቶች ቢኖሩም የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንም ሆነ ማዕከላዊ መንግስት ጉዳዩን በቸልታ ተመልክቶታል።ይህ ደግሞ ወደፊት ክልሎች በክልላቸው ላይ ለሚፈፀሙ ኢሰብአዊ  መብት ተግባራት ሁሉ በቸልታ እንዲመለክቱ የሚያደርግ አደገኛ አካሄድ ነው።

በኢትዮጵያ ካሉት ክልሎች ውስጥ ላለፉት ሰላሳ ዓመታት ፍትሃዊ ያልሆነ የስልጣን ክፍፍልም ሆነ የነዋሪውን ቁጥር ያላማከለ የፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊ እና ማኅበራዊ ግልጋሎቶች ያሉበት ይሄውም አካሄድ በተደጋጋሚ ለተፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት የሆነበት  መሆኑ እየታወቀ፣ይህንኑ ፀሐይ የሞቀውን ጉዳይ ከሕግ አንፃር የተናገረችውን ኤልሳቤትን ያውም ከአዲስ አበባ ድረስ ታፍና ስትወሰድ በዝምታ ማለፍ ለማዕከላዊ መንግስትም ሆነ ለሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ከፍተኛ ክስረት ነው። ኤልሳቤጥ ሐረር ፍርድ ቤት ብትቀርብም የዋስ መብቷ ተነፍጎ እንደገና ቀጠሮ ተሰቶባታል።ይህ ሁሉ የሆነው ደግሞ ሃሳብን መግለጥ እንደወንጀል ተቆጥሮባት ነው። 

ባጠቃላይ በኤልሳቤጥ  ላይ የተፈፀመው ሕግ የጣሰ ድርጊት መታረም አለበት።ድርጊቱ የመናገር እና ሃሳብን የመግለጥ መብትን ብቻ የሚጋፋ ሳይሆን የሐረር ክልል አስተዳደር ለሴቶች ያለውን የተሳሳተ እና ዝቅ አድርጎ የማየት ደካማ አስተያየትም የሚያመላክት ነው።በአሁኑ ጊዜ መንግስት ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ በርካታ ወንጀለኞች እንዲለቀቁ በሚያደርገበት ጊዜ የሐረር ክልል አስተዳደር ሃሳቧን ገለጠች ብሎ ወደ እስር የወሰዳት የሕግ ባለሙያ ኤልሳቤጥ ከበደ የዋስ መብት እንድታጣ የተደረገበት አካሄድ ተራ የማሸበር እና ነገ ሌሎች በክልሉ የሚፈፀሙትን በርካታ ወንጀሎች ተድበስብሰው  እንዲያልፉ ለማድረግ የሚሞከር የማስፈራርያ ተግባር አካል ነው።
አሁንም ኤልሳቤጥ እንድትፈታ መንግስትም ሆነ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ድርጅት እንዲሁም ሌሎች ድምፃቸውን ሊያሰሙ ይገባል።የሐረር ክልልም እየሄድበት ያለው ሕገወጥ አካሄድ ሊታረም እና አጠቃላይ ክልሉ ከለውጡ ወዲህ እየሄደባቸው ያሉት መንገዶች ሁሉ ውስጥ  የውጪ አካላት አማካሪዎች ላለመኖራቸው የማጣራቱ ሥራ  የመንግስት ተግባር እና ኃላፊነት ይሆናል።ኤልሳቤጥ ግን ሃሳቧን ከመግለጥ ሙሉ መብቷ ጋር በፍጥነት መፈታት አለባት።
  

Monday, April 20, 2020

‘Ethiopia is my home’: Syrian chefs build new lives fuelled by shawarma

ኢትዮጵያ የእኔ ቤት ነች - በኢትዮጵያ ሶርያዊው ስደተኛ ለብሃር በስደተኝነት ከመጣባት ኢትዮጵያ ያገኘውን መልካም ነገር ይነግረናል።
ምንጭ- ዘናሽናል 
Source - The National
  • Ethiopia's asylum policies have made the country a rare refuge for Syrians fleeing conflict


When Maetz Lebhar visited Ethiopia for a conference on dairy products in 2015, he did not expect to be calling the country his home within the space of a year.
Attracted by the market potential of products from his native Syria, including accessories to make shawarma, the 37 year old returned the following year hoping to find a local partner to help expand his business, perhaps in the form of opening a restaurant. It wasn’t long before the work trip turned into a permanent visit.
“I lost my extended family in the [Syrian] conflict and all our properties turned to ashes. I made Ethiopia my home as my circumstances changed in the blink of an eye”, he told The National.
“In Addis, I have been welcomed and I have managed to make my living selling the delicacies of my home.”
Mr Labhar works as a chef in a local restaurant and earns ETB30, 000 a month (USD 950) close to the annual average wage of $985.
Ethiopia currently hosts one of the largest refugee populations in the world, at over one million refugees, mostly from Eritrea, South Sudan, Somalia and Yemen. Now Syrians are joining their ranks, attracted by favourable asylum laws.
So far, more than one million Syrians have been displaced from their homeland by the nine-year conflict. They constitute a third of the world’s refugee population, with their numbers reaching 5.6 million by the end of last year, according to the UN.
Adna Mohammed, 42, has experienced considerable success since moving to Ethiopia in 2013. The father of one owns a popular shawarma restaurant in Bole, a business district of capital Addis Ababa.
The Damascus native is now married to an Ethiopian woman and is fluent in Amharic, the national language. He has no interest in returning to Syria, he said.
"I will probably be a foreigner if I did,” he said.
“All I had has perished and it will bring bad memories of families and friends who are no longer there. Ethiopia is my home”.
Until lockdown measures due to the coronavirus pandemic, Mr Mohammed’s business was doing well.
“I used to have a booming business where I sold about 150 plates a day. These days, I sell about a dozen or so”, he said, looking over empty seats usually occupied by young people.
“I am hopeful the virus will be contained and we go on living our regular lives”.
Many more Syrians have followed in Mr Mohammed and Mr Lebhar’s footsteps. The Ethiopian Immigration, Nationality and Vital Events Agency, counts the total Syrian population in the country as 315 people as of 2019.
But the number is suspected to be significantly higher; hundreds driven to flee by the Assad regime’s latest offensive in Idlib. They arrive on tourist visas and now, having exhausted their legal stay, can be seen begging in crowded areas all across Ethiopia, many accompanied by young children.
"I know migrants who consider begging as the only option to make easy money as they find their footing in Ethiopia”, Mr Lebhar said.
“But with little safety nets and pressure to eat and support a family, some have little choice, giving little regards for their own safety in what is too many, still a foreign land”.
In January 2019 the state banned street begging. The deputy head of Ethiopia's immigration office told the Associated Press at the time that Syrian presence on the streets was becoming a “burden”.
UNHCR contacted unregistered Syrian refugees last year and provided information on the asylum procedure, the body’s spokesperson in Ethiopia Kisut Gebreegziabher said. “Only a few of them came and applied for asylum with the Ethiopian government”, he added.
Those who do register are given assistance, he said.
“The financial assistance is meant to cover their daily needs, including housing. They are additionally supported with their educational and health care needs,” he added.
Airport workers told The National there are also dozens of Syrians stuck at Bole International Airport, missing the required documents for entry and denied access to the country. Most arrivals come from Syria via Sudan, Turkey and Egypt, they say.
Ethiopia allows refugees to work and their children to attend its public schools. But many of these progressive policies did not anticipate accommodating an influx of Middle Eastern refugees, rather the usual flow from the likes of South Sudan, Eritrea and Somalia.
Last year, Ethiopia passed legislation granting refugees the right to work and earn citizenship status through a naturalization process, a decision welcomed by UNHCR and the European Union. The latter funded the construction of industrial parks in a bid to provide employment opportunities in Ethiopia, thus reducing the influx of migrants to Europe.
New arrangements are also being made by ARRA to refugees coming from Middle East countries, understanding the tension in the region.


ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Friday, April 10, 2020

የእናት ፓርቲ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወቅትና ከወረርሽኙ በኃላም ከግንዛቤ መግባት አለባቸው ያላቸው ጉዳዮች በተመለከተ ባለ ሦስት ነጥብ የመፍትሔ ሃሳቦች የያዘ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ ላከ።(የደብዳቤውን ሙሉ ይዘት ይዘናል)


በቅርቡ የተመሰረተው እና ከከፍተኛ ምሁራን ባለሙያዎች እስከ ገበሬዎች ድረስ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች አባላት እንዳሉት የሚነገረው የእናት ፓርቲ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን አስመልክቶ ሶስት የመፍትሄ ሃሳቦች የያዘ ደብዳቤ ዛሬ ሚያዝያ 2፣2012 ዓም መላኩን ጉዳያችን ተረድታለች።የደብዳቤው ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያንብቡ። (ፎቶ ኮፒው በጥራት ካልተነበብልዎት፣ከኮፒው ስር በጥራት የተለጠፈውን ያንብቡ)


===========================
ለክቡር /ዐቢይ አህመድ
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር
አዲስ አበባ 
ጉዳዩ- ኢትዮጵያዊ እሴቶቻችንን ተጠቅመ ከመጣብን መዓእንውጣ 

የኖብል ኮሮና ቫይረስ(CoVID-19)በይፋ መገኘቱ ከተገለፀበት ለት ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ቫይረሱ ተያዙ ዎች ጥር ቀስ በቀስ ያሻቀበ ሄዶ 1.5 ሚሊዮን ደርሷልየሟቾችም ቍጥር ከ80 ሺህ አልፏልሀገራችንም ታማሚዎች ቍጥር ከ50 ንዳለፈ ውቋልማኅበረሰባችን ጤና ተቋማት ሄዶ የመመርመር ባህሉ በሽታ በእጅፀናበት ብቻ መሆኑና የምርመራ ማእከላት አነስተኛ ከመሆናቸው የተነሳ የተመረመረው ሰው ቍጥር አነስተኛ በመሆኑ ቫይረሱ የተያዘው ሰው ቍጥር ኦፊሴል ከሚነገረው ከፍ ሊል ንደሚችል መገመት አዳጋች አይደለምካለን የምጣኔ ሀብት እድገትአነስተኛ የሐኪሞች ቍጥርውስን የመመርመሪያ መሣሪያ ላይ የጠነከረ ማኅበራዊ መስተጋብር ሲጨመርበት የችግሩ ስፋት 
ያስጨቃል፡ 
አሁን በጤናችን በኩል የመጣ ጠላት ጋር ጦርነት ውስጥ ነንመሽነፍ ደግሞ የኢትዮጵያውያን ባህል አይደለምሥነልቡናችንም አይፈቅድምይህ ከሆነ መጪው ትውልድ ይታዘበናልሪክም ፈርድብናልዚህ ገድ ሎች ሀገራት ህን ርነት ከመቆጣጠር ኳያ ዘየዱትን መላ መመልተገቢ ሲሆን የወረርሽኙ መነሻ ሆነችው ይናበኋላም ጃፖን ንዴት አድርገው ረርሽኙ በተከሰተበት ግዛት ንዲገደሎም በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ ንዳደረጉ ትምህርት መውሰድ ሻል፡ 
ረርሽን ከአፍሪካ አህጉር ንጻር ሲታጅግ ፈታኝ መሆኑ አሌ ይባልምአኗኗር ዘይቤየማኅበረሰብ ቁርኝትጤና ሽፋንየሐኪምና ታማሚ ምጣኔየሕክምና መሣሪያ እጥረት ባለበት ኔታ ምን ህል አደጋ ሆን እንደሚችል መረዳት መረዳት አያዳግትምዚህ አስቸጋሪ ወቅት እኛ አፍሪካውያን በአጠቃላይ ኢትዮጵያውያን በተናጠል የምንኮራባቸው ሌሉቹም ህጉራት ተምሳሌት ሊሆኑ የሚችሉ የማኅበረሰብ እሴቶች አሉንለምሳሌ እድርድርጎኡቡንቱ... የመሳሰሉ እምቅ እሴቶች ማኅበረሰቡ ከሚመጡበት ማንኛውም ችግርና አደጋ መተሳሰብመረዳዳትበአንድነት አንድ የጋራ ዓላማ የሚቆምበት ዘመን ጠገብ መሣሪዎቹ ናቸው፡ 
አህጉራችንም ሆነ ሀገራችን ከገጠማቸው ችግር መውጣት የመንግስት ርሻ መሆኑ ቢታወቅም ነዚህን እሴቶች በአግባቡ መጠቀም የገጠመንን ተና መወጣት የምናደርገውን ጥረት በእጅጉ ረዳልወረርሽኙ ከዚህ ሰፋ የሚያስከትላቸው አሉታዊ ተጽዕኖዎች ንደ የቤት ኪራይ መጨመርየገበያ ዋጋ መናርየደሞዝ መቋረጥየቤት መልቀቅየሚላስ የሚቀመስ ማጣት ሆነ ሎች ያያዥ ችግሮች በኢትዮጵያዊ እሴቶቻችን የሚፈዳዮች ናቸውየማኅበረሰባችን ችግር ማኅበረሰባችን መፍትሔ ገኛል ሚለው ሳቤ ለቄታዊ መፍትሔ ከማምጣቱ ባሻገር ማኅበረሰቡ ዳዩን ባለቤትነት ንዲይዘው ደርጋል ብለን እናምናለንዚህም፡ 
በመጀመሪያ ወረርሽኙ በሀገር አቀፍ ረጃ እንዳይስፋፋና ከቁጥጥር ውጭ እንዳይሆን የበሽታውን ሥርጭት ለበት መገደብ ሻል፡ከዚህ አኳያ በሀገር ቀፍ ደረጃ የሚተገበር ባለሙያዎች ተጠናና ያለውን ባራዊ ሁኔታ በውል ገናዘበ ንቅስቃሴን የመገደብ ሥራ /Declaring Total Lock-down/ ያስፈልጋልሲሆን ግን የማኅበረሰቡን የመኖር ሕልውና ማገናዘብ አለበት ንላለንደተግባር ሲገባም ከእጅ ደአፍ ኑሮ የሚገፋው ማኅበረሰብ እጅጎዳልዚህ ጊዜ ኢትዮጵያዊ እሴቶቻችን በተግባር ማዋል ለመጫው እጅጉን ይጠቅማልበዕለት ምግብ እርዳታ ለማለፍ የሚገደዱ ዜጎች ቍጥር የቀበሌአስቸኳይ ስልክ እንዲመዘገብ ወይንም ጎረቤቱ እንዲያስመዘግበው ማድረግበሌላ ኩል ደግሞ ደቡ በሚጸናበት ጊዜ ሁሉ የአንድን ሰው ዕለት ምግብ የዕለቱ መሸፈን የሚችለውን የኅብረተሰክፍል እንዲሁ መመዝገብ ስፈጋልይህ ሥራ ሕዝቡ ዕለት ምግብ ጆታ በማበርከት የቀኑ መትጋትን ይቅ መንግሥት የራሱን ተሽከርካሪዎች ጨምሮ ቃደኛ ለመኪናዎችንና ሎች ማጓጓዣ ልቶችን ማስተባበር የዕለት ምግብ ርዳታው ከለጋሾች ደሚፈግበት ማድረስን መደበኛ ሥራ ማድረግ ጠይቃል፡ 
በሁለተኛ ደረጃ ዘመናዊውን ክምና ሀገር ቀሉ ዳበረ የሕክምና ጥበብ በማጣመር መፍትሔ መሻት ነው፡፡ እንደእኛ ይነት ነባር እውቀትና በባህል ሕክምና ሺህ ዓመታት ሠራበት ለኖረ ማኅበረሰብ ጊዜውን ትሩፋት መጠበቅ ንዳለ ሆኖ እገረ መንገዱን ባሩን እውቀትና አዋቂዎች መዝገብ ለጥ ገለጥ ማድረግ ነገ የሚባል ይደለምዳፍነነው ለኖርን ይህ ንኳን መንገዱ ጅም ነው ቢባል ከየባህሉና መልክዓ ምድሩ የሚበቅሉ ለእንዲህ ዓይነት ረርሽኝ መታገያ አቅም የሚሆኑ አዝርእትን አፈላልጎ የትግሉ አካል ማድረግ ተገቢ ነውበዚሁ አጋጣሚ የባህል ክምና ግና ሥርዓት በጅቶለት ከዘመናዊው ይንስ ጋር ቀናጅቶ የሌላው ወገን ይሁንታ እንዳለ ሆኖ ሲያዋጣን ግን በፍጥነት መጠቀሙ አስፈላጊ ነው 
ሦስተኛው ጊዜ ሲያልፍ /Post Corona/ የምንሆነው ከአሁኑ መታሰብ አለበትየሀገሪቱ ምጣኔ ሀብትየአልሚው ሁኔታየማኅበረሰቡ ሥነልቡናየአምራች ይሉ መሥራት ፍላጎትየሸማቹ ፍርሃትየተማሪው የመማር ግጁነትግም ማኅበራዊ ቅርርብ... ዘተ ተጎዳ ሥነልቡናና ንደአዲስ በሚጀመር ኳኋን ነው የሚመለሱትይህም የችግሩ አካል ንደሚሆን አድርጎ ማሰብና ከወዲሁ ትልቅ ሥራ መሥራትን ጠይቃልዚህም ሃይማኖት ተቋማት የሰውን ሥነልቡና ከፍ በማድረግና ባለበት ሁኔታ ከፈጣሪው ጋር ማገናኘት የሚወጡት ሚና ቀላል ይሆንምና የተጀመረው ሀገር አቀፍ ጸሎት መልካም ሆኖ አሁንም የፖኬጁ ካል የሚሆኑ ቀሪ መርሐ ግበሮች (በክርስትናው ቅዳሴየሰንበታት አምልኮዎችየሰሙነ ሕማማት ክዋኔዎችእስልምናው እንደ ጁምዐ ላትየረመዳን ጾም ክዋኔዎች) በብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ቀጥታ ሥርጭት ሽፋን ንዲያገኙ ማድርግ ስፈላጊ ነውበሌላ ኩል ሥነልቡና ዋቂዎችየፍልስፍና ምሑራንደማጭ ኢትዮጵያውያን ጊዜና ሁኔታው መቻችቶላቸው ደመድረኩ እንዲመጡዳይ ተኮር ሥራ ንዲሠሩ ማድረግ ዜው የሚጠይቀው ነውየምጣኔ ሀብት ምሑራንችግር ጊዜ መውጫ ሀሳብ ላቸውን እነአባ መላን ይዞ ነገ የሚሆነውን በትክክል መተንበይና መውጫ መንገዱንም በመተለም የምጥ ስሩን ማሳጠር ለብን፡ 
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር
ይህን የመጣብንን ታላቅ ፈተና መሻገር መላ ማበጀት በእርስዎና በዙሪያዎ ባሉ ለሥልጣኖች ጫንቃ ላይ ንዳልወደቀ ፖርቲያችን ጠንቅቆ ይረዳልእንዲያውም እኛን ጨምሮ ብዙ ከፊት ሰልፈው የአቅማቸውን በማድረግ ጦርነቱ ፊታውራሪ መሆን የሚችሉ ወጣቶች ስላሉ ሊኮሩሊጠቀሙባቸው እንደሚችሉ ንነግርዎት በደስታና ቃል መግባት ጭምር ነውኖም ታሪክ አጋጣሚ የዚህች ሀገራችን መራር በእርስዎ እጅ በወደቀበት አሁኑ ወቅት ዛሬ ብዙዎች መዳን ይም ልቂት ምዎ ወርቅ ቀለም ፃፍ ወይንም ታሪክ ተወቃሽ ያደርግዎ የሚያስችል ሥራ የሚሠሩበት ጊዜ ነው፡፡ ስለሆነም የሕዝባችንን የዳበረ እሴት ተጠቅመን ሀገራችን ከተጋረጠባት ርነት በድል ተሻግራ ብሩህ ነገን የምታይ እንድትሆን ሁሉም ሓላፊነቱን ንዲወጣና ስፈጊው እርምጃ አስቸኳይ ንዲወሰድ ለብን ዜግነት ዴታና እንደ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ ናሳስባለን፡ 
ጣሪ ትዮጵያን ጠብቅ 

ይለኢየሱስ ሙሉቀን (/
ፕሬዚዳንት  
ግልባጭ 
- ሁሉም መገናኛ ብዙኃን አካላት ባሉበት 




በኢትዮጵያ የእገታ ወንጀል ተሳታፊ አራት አካላት ናቸው። ለችግሩ የመፍትሄ አካላት ሁለት ናቸው።ሁለቱ አካላት ምን ይስሩ?

======= ጉዳያችን ======= በኢትዮጵያ ዜጎችን እያገቱ ገንዘብ የሚቀበሉ ወንጀለኞች ከተራ ወንጀለኝነት አልፎ በታጣቂ ቡድኖች የገንዘብ ማግኛነት መዋል ብቻ ሳይሆን ዜጎችን የማሸበርያ ፋሺሽታዊ ተግባር ሆኗል። እገታ የ...