ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Sunday, April 26, 2020

የሰንበት በረከት - ዘወትር ዕሁድ በየሳምንቱ በአውሮፓ ያሉ ምዕመናን በሙሉ በአውሮፓ ሰዓት አቆጣጠር ከ17 (5pm) እስከ 19 (7pm) ሰዓት ከቤታቸው ሆነው በቀጥታ እየተያዩ በአንድ ጉባኤ የሚታደሙበት ጉባኤ መረጃ እና የትንሣኤ መዝሙር


- በዛሬው መርሃግብር መጋቢ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ትምህርት ይሰጣል።

በዘመነ ኮሮና ወረርሽኝ ብዙ ምዕመናን ያጡት አንዱ ጉዳይ በአንድ ጉባኤ ተሰብስቦ የእግዚአብሔርን ቃል መማር ነው።በአውሮፓ ግን ቀላል መንገድ አለ።ዘወትር ዕሁድ ከቤትዎ ሆነው ከቤተሰብዎ ጋር ወይንም ብቻዎን የሚማሩበት በአውሮፓ ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ምዕመናን በአንድ ጉባኤ የሚታደሙበት የትምህርት፣የመዝሙር የአገልግሎት ጉባኤ ከተጀመረ ሳምንታት ሆነውታል።

በጉባኤው ላይ ከየትኛውም የዓለም ክፍል መሳተፍ የሚችሉ ሲሆን በአውሮፓ የሚኖሩ በተለይ ባያመልጣቸው ይመከራሉ። በጉባኤው ላይ ከአገር ቤት እና ከልዩ ልዩ የዓለማችን ክፍሎች አገልጋዮች እየገቡ ትምህርት ሰጥተዋል፣ዝማሬ አሰምተዋል። በቅርቡ ዘማሪ ይልማ ኃይሉን ጨምሮ መምህር ብርሃኑ አድማስ እና ሌሎች አባቶች አገልግለዋል።በዛሬው ጉባኤ ደግሞ መጋቢ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ይገኛሉ።

ወደ ጉባኤው በዩቱብ እና ሪንግ ሴንትራል በመግባት በቀጥታ መከታተል  ይችላሉ።
ዩቱብ ሊንክ

ዝርዝሩን ከስር ካለው ፖስተር ላይ ይመለከቱ።ከፖስተሩ ስር የትንሣኤ መዝሙር ይመልከቱ።


የዲያቆን ፍሬዘር  ደሳለኝ መዝሙር 


ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

No comments:

ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።