Friday, May 29, 2026

ከሰባተኛው የኢትዮጵያ ምርጫ በቀጣይ የሚታዩ የሚታዩት ሦስት እውነታዎች

ኢትዮጵያ 7 ኛው የሕዝብ ተውወካዮች ምክርቤት ምርጫ ሰኞ ግንቦት 24፣2018 ዓም ታካሂዳለች።ይህንን ምርጫ አንዳንዶች ሊያቃልሉት እና በለሆሳስ ሊያልፉት ይሞክራሉ።ሌሎች ደግሞ ምርጫው ይልቅ ነው ብቅ ፉክክር አልታየበትም ይላሉ።የቀሩት ሞቅ ሞቅ አላለልንም ይላሉ።እነኝህኞቹ ተፎካካሪዎች የሆኑ የድራፍት ቤት መነጋገርያ የሆኑ ቃላት ሲቀያየሩ ካላዩ ደስ የማይላቸው ናቸው።

ይህ ምርጫ ግን የኢትዮጵያን መጻኢ መንገድ የሚያቀና ነው።ምርጫው ከ ሀምሣ ሚልዮን በላይ ሕዝብ የሚሳተፍበት ሲሆን ለመጀመርያ ጊዜ በዲጂታልም ጭምር የሚከናወን ምርጥ ነው።

በእኔ ዕይታ ይህ 7ኛው የኢትዮጵያ ምርጫ ተከትሎ ሦስት እውነታዎች ለኢትዮጵያ ያመጣሉ።

እነርሱም:-

፩) ኢትዮጵያ ከጎሳ ፖለቲካ ማዕበል ቀዝፋ ወጥታ ወደ ሕብረብሔራዊ አንድነት የምትሸጋገርበት ነው።

፪) በጎሳ ፖለቲካ የቆሰለችው ኢትዮጵያ ቁስሏ መጥገግ የሚጀምርበት ነው።

፫) በሁለት እግሯ ለመቆም የምትጥረው ኢትዮጵያ ከባሕር በር የተገለለችበትን የክህደት ካባ አውልቃ በሁለት እግሮቿ ቆማ ተጽዕኖ ፈጣሪነቷ ዳግም የሚታይበት ጅማሮ ነው።

ሃተታ አላበዛም እነኝህ ሦስት እውነታዎች ዛሬ ያልገባን የዛሬ አምስት ዓመት ይገባናል።

ባሳለፍነው ሳምንት ኢትዮጵያውያን በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት ደግፈው ተሰልፈዋል።ለሀገራችን በጎ የሚታየንን ከመውቀስ ኢትዮጵያ ያለፈችበትን፣አሁን የቆመችበትንና ለነገ ያቀደችውን መረዳቱ ጥቅም አለው።

ፎቶ ይናገራል።

































ከሰባተኛው የኢትዮጵያ ምርጫ በቀጣይ የሚታዩ የሚታዩት ሦስት እውነታዎች

ኢትዮጵያ 7 ኛው የሕዝብ ተውወካዮች ምክርቤት ምርጫ ሰኞ ግንቦት 24፣2018 ዓም ታካሂዳለች።ይህንን ምርጫ አንዳንዶች ሊያቃልሉት እና በለሆሳስ ሊያልፉት ይሞክራሉ።ሌሎች ደግሞ ምርጫው ይልቅ ነው ብቅ ፉክክር አልታየበትም ይ...