ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, March 31, 2014

ኢህአዲግ/ወያኔ ሕዝብ ለማፋጀት የገነባውን 'የመርዝ ብልቃጥ' በያዝነው ሳምንት በሃያ ሚልዮን ብር ወጪ ይመርቃል።ምርቃቱ የሩዋንዳው የዘር ማጥፋት ግጭት ከተጀመረበት 20ኛ ዓመት ጋር ገጥሟል።ባጋጣሚ ወይስ ታስቦበት?

ኢትዮጵያን እየመራ የሚገኘው ኢህአዲግ/ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከቀን ወደ ቀን እርስ በርሱ እንዳይተማመን፣እንዲነቃቀፍ፣እንዲጠራጠር ከእዚህ ባለፈ ደግሞ ግጭት እንዲፈጠር እያደረገ 22 ዓመታትን ዘለቀ።ህዝቡ እለት ከእለት በገዢው መንግስት የሚወጠኑለትን የእርስ በርስ ማጋጫ ተንኮሎች እየተመለከተ ልቦናው በእጅጉ እየደማ ነው።

አንድ ወራሪ የውጭ ጠላት ሊሰራ የሚችለውን ያህል ህዝብን ከሕዝብ ጋር የማጋጨት ሥራ ኢህአዲግ/ወያኔ በትክክል ሰርቶበታል። የሃገሪቱን ፌድራል አስተዳደር በየትኛውም ዓለም ያልታየ ቋንቋን መሰረት ያደረገ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ደገሰላት።ፌድራላዊ አስተዳደር በዘመናዊው ዓለም አንዱ እና አማራጭ የአስተዳደር ዘይቤ ይሁን እንጂ በየትኛውም ሀገር መሰረት የሚያደርገው የመልክዓ ምድርን አቀማመጥ እና ታሪካዊ አሰፋፈርን ነው። እርግጥ ነው ጣልያን ሀገራችንን በወረረ ዘመን አሁን ወያኔ የሚጠቀምበትን የክልል አስተዳደር የመሰለ ቋንቋን መሰረት ያደረገ የአስተዳደር መዋቅር ዘርግቶ ነበር።

አንዳንዶች የአሁኑ ቋንቋን መሰረት ያደረገ አስተዳደር የብሔር ብሄረሰቦችን መብት ከማስከበር አንፃር የሚመስላቸው የዋሃን አይጠፉም።ግን ፈፅሞ አላማው ይህ ላለመሆኑ ብዙ ማስረጃ መጥቀስ ይቻላል።እርግጥ ነው የህዝብ ባህል ማለትም ቋንቋው፣አለባበሱ፣ታሪኩ ወዘተ ሊጠበቅለት እና ከለላ ማግኘት አለበት።ይህ ከለላ በማግኘት መብት  ስም ወንጀል ሲሰራ፣ቁርሾ በባትሪ እየተፈለገ ሲራገብ እና ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት ሲውል ነው ወንጀሉ።

ኢህአዲግ/ወያኔ ሕዝብ እርስ በርሱ በጎሳ ሲጋጭ መፍትሄ ለመፈለግ ከመነሳት ይልቅ ጉዳዩን ሲያባብስ እና ቤንዚን ስያርከፈክፍ ማየት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ዕለት ከዕለት የሚመለከተው ድራማ ሆኗል። ለእዚህም ብዙ አብነቶችን መጥቀስ ይቻላል። ለእዚህ ፅሁፍ ግን ሁለት ምሳሌዎችን እንጥቀስ -

1/  በዩንቨርስቲዎች ውስጥ ወጣቶች 'አንተ የእገሌ ነህ አንተ የእንቶኔ ነህ' ተባብለው ፀብ ሲነሳ ጉዳዩ የመጪው ትውልድ እና የአሁኑ ትውልድ አደገኛ አቅጣጫ ነው ብሎ የችግሩን ስር ለመፍታት ከመጣር እና የጉዳዩን አስከፊነት  በመገናኛ ብዙሃን ከመግለፅ እና ከማስተማር ይልቅ ፖሊስ ይልቁን ከአንድኛው ወገን ቆሞ ሌላውን ሲያስር እና ሲቀጣ መመልከት ዘግናኝ ተግባር ነው።

2/ ሕዝብ ለዘመናት ከኖረበት የእርሻ ቦታ ''የእገሌ ዘር ነህ'' ተብሎ በክልል መስተዳድሮች ጭምር ሲባረር ለጉዳዩ እንደ መንግስትነት ለመዳኘት ሳይሆን የሚሞከረው እንደ ቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ አባባል ''ቀድመው ባልተወለዱበት ሀገር መስፈር የለባቸውም'' እንደ አቶ አለምነህ የብአዴን ቢሮ ምክትል ኃላፊ ደግሞ ''የትዕቢት ልጋግ'' ነው የሚሉ መልሶችን መስማት እራስ ያማል።መሪዎቻችን እንዲህ እያሉ ከጉርዳፈርዳ እስከ አሶሳ፣ከአሶሳ እስከ ሐረር፣ ከሐረር እስከ ጅጅጋ፣ ከጅጅጋ እስከ ቦረና ጉጂ፣ ድረስ በብዙ አስር ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በኢህአዲግ/ወያኔ የጎሳ ፖለቲካ ተሰደዱ፣ተገደሉ።ይህ ሁሉ ሲሆን ግን መንግስት ጉዳዩን እንደ ትልቅ ችግር ሳይሆን እንደ አንድ የማስተዳደርያ ዘዴ እንደቆጠረው በ እርግጠኝነት መረዳት ይቻላል።

በያዝነው ሳምንት  በሃያ ሚልዮን ብር ወጪ የሚመረቀው የመርዝ ብልቃጥ 

በአርሲ ዞን በሂቶሳ ወረዳ ከሃያ ሚልዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያሰራውን  ''አኖሌ ሐውልት'' እና ሙዝዬም

የእርስ በርስ ግጭቶች ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲሻገሩ የሚጥረው ኢህአዲግ/ ወያኔ ለእርስ በርስ ጦርነቶች እየመረጠ ሃውልት ሲሰራ ከርሞ በእዚህ ሳምንት ደግሞ ለየት ያለ የጥፋት ድግስ የሚሆን ከመቶ አመታት በፊት ለመፈፀሙ ምንም አይነት የታሪክ ማስረጃ የሌለው በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን በአርሲ ዞን በሂቶሳ ወረዳ ተፈፅሟል ያለውን የታሪክ ምሁራን ያላረጋገጡትን የፈጠራ ታሪክ ከሃያ ሚልዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያሰራውን  ''አኖሌ ሐውልት'' እና ሙዝዬም  በእዚህ በያዝነው ሳምንት እንደሚመረቅ ኢቲቪ ዛሬ መጋቢት 22/2006 ዓም የዜና እወጃው ላይ አስታወቀ።የፈጠራው ታሪክ ከመቶ ዓመታት በፊት የአፄ ምኒልክ ሰራዊት የኦሮሞ ሴቶችን ጡት ቆርጦ ነበር እና ማስታወሻነቱ ለተቆረጡት ጡት እና እጅ ይሁን'' ይላል የሃውልቱ የመሰራት ምክንያትን ኦህዴድ /ኢህአዲግ/ወያኔ ሲናገር። አሳዛኝ የደረስንበት የዝቅጠት ዘመን።በየትኛውም ሀገር ውስጥ በቀደሙ መሪዎች ያውም ከመቶ አመታት በላይ ለሆነው ታሪክ ቀርቶ የቅርቦቹም ቢሆን ለተሰሩ ተገቢ ያልሆኑ ድርጊቶች ለመጪው ትውልድ የሚያቆይ የእልቂት ድግስ ከፋች ሃውልት አይሰራም። የሚጠጣ ውሃ፣ የምበላው ምግብ ለሌለው ሕዝብከ 20 ሚልዮን ብር በላይ አውጥቶ መበተን ምን የሚሉት ፈልጥ ነው?

አንድ መንግስት ሕዝብ ከህዝብ ጋር አብሮ የሚኖርበትን ዘዴ ሲቀይስ ልዩነትን እያጎላ ሳይሆን አንድነትን እያሳየ እና እያጎላ ሕዝብ በፍቅር እና በስምምነት እንዲኖር ይጥራል እንጂ እንዴት ከአሁኑ ትውልድ አልፎ ለመጪው ትውልድ ቂም ለማውረስ ተግቶ ይሰራል? ይህ ተግባር ማንን ይጠቅማል? ለመሆኑ ያለፉ ነገስታት በወቅቱ በነበረው የቅጣት መንገዳቸው ሁሉ የቀጡትን የቅጣት አይነት እየዘረዘርን ሃውልት ብንሰራ የቱን ከየቱ እንመርጣለን?

የሃውልቱ ምርቃት እንደ ትልቅ የሀገር ልማት ዛሬ ኢቲቪ ቀድሞ ዛሬ ይናገረው እንጂ ወቅቱ የሩዋንዳው እልቂት የተጀመረበት 20ኛ አመት ጋር ገጥሟል።በሚያዝያ 7/1994 ዓም  እስከ ሐምሌ/1994 ዓም እ ኤ አቆጣጠር የቆየው በቱትሲዎች እና በሁቶዎች መካከል የተደረገው እልቂት ከአምስት መቶ ሺህ በላይ ሕዝብ ሕይወት ቀጥፏል።የሩዋንዳው እልቂት በአንድ ሌሊት ድንገት የደረሰ ጉዳይ አይደለም።በሂደት አልፎ አልፎ በተነሱ ቁርሾዎች ጥርቅም ሳብያ መሆኑን መዘንጋት አይገባም።የዛሬ የባለ ሃያ ሚልዮን ሃውልት ገንቢዎችም ሆኑ አስገንቢዎች መዘንጋት የሌለባቸው  በሰሩት ሥራ ሁሉ የሚጠየቁበት ቀን እንደሚመጣ መጠራጠር አይገባም።የመርዝ ብልቃጡም ይሰበራል የፍርድ ቀኑም ይቆረጣል።

ጉዳያችን
መጋቢት 22/2006 ዓም





Thursday, March 27, 2014

በመንግስት የሚደገፈው የጎሳ ፖለቲካ እንደ 'አሜባ' እየተስፋፋ ነው።የመንግስትን የጎሳ ፖለቲካን ጨምሮ በየቦታው እያቆጠቆጡ ያሉትን የጎሳ አራማጆችን አደብ ማስገዛት የሚቻለው የተቃውሞ የፖለቲካ መስመሩን ሕዝብ ሲዘውረው ነው።



ኢትዮጵያ በቅርብም ሆነ በሩቅ ጠላቶቿ የተደገሰላት ለዘመናት ሲውጠነጠን የነበረ የማጥፍያ ''ቦንብ'' በየቦታው መፈነዳዳት ጀምሯል።ጎሳን መሰረት ያደረገው አስተዳደር ለሁለት አስር ዓመታት ያህል ደጋግሞ  ሲወጋው የነበረው ኢትዮጵያዊነት በአንዳንድ ቦታዎች እየተጎዳ መሆኑን ምልክቶች እየታዩ ነው።

ትናንት ባህርዳር የመላው ኢትዮጵያ የስፖርት ውድድር ላይ በኦሮምኛ ተናጋሪ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ላይ በዋልጌ የከተማዋ ነዋሪዎች ተፈፀመ የተባለው ስብእናን የሚነካ ተግባር አሳፋሪ ብቻ ሳይሆን በድርጊቱ ፈፃሚዎች ላይ ተገቢው ቅጣት አስፈላጊ መሆኑን የሚያመላክት ነው።ኢትዮጵያ ተዘዋውረው የማይነግዱባት፣በፈለጉት ክልል ሄደው በህጋዊ መንገድ እርሻ ለማረስ  ቋንቋ የሚጠየቅባት ሃገር መሆኗ ሲያሳዝነን ከርሞ ዛሬ ደግሞ የስፖርት ውድድር ለማድረግ የማይቻልባት ሀገር መሆኗ የጊዜያችን አሳዛኝ ክስተት ነው።

ኢሕአዲግ/ወያኔ የመሰረተው የጎሳ ፖለቲካን ማዕከል ያደረገ ስርዓት የችግሮቹ አንቀሳቃሽ ሞተር መሆኑን መዘንጋት የለብንም።የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆኖ ነው እንጂ ሌላ ሃገር የኢህአዲግ አይነት የጎሳ ፖለቲካ የሚያራምድ መንግስት ቢገጥመው  22 ዓመታት አይደለም በ 6 ወራት ውስጥ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ እንደሚገባ ሳይታለም የተፈታ ነው።

 በሌሎች አፍሪካውያን ሃገራት ጎሳ እና ቋንቋን መሰረት ያደረገ የፖለቲካ ድርጅት መመስረት በሕግ የተከለከለ ነው፣እኛ ጋር ግን ይበረታታል።ይልቁን ለፍቃድ ቅድምያ የሚሰጠው በጎሳ ለተመሰረቱቱ ነው።በሃገራዊ መልክ የተደራጁ ፍቃድ ለማግኘትም ብዙ ፈተና አለባቸው።ለምሳሌ የሰማያዊ ፓርቲ ፍቃድ እንዲሰጠው አመልክቶ ለብዙ ወራት ሳይሰጠው ቆይቶ በእራሱ እውቅናውን ማወጁን ከገለፀ በኃላ ነው ፍቃድ የተሰጠው።

በሌሎች አፍሪካውያን በስልጣን ላይ ያለ ማንኛውም ሰው የመጣበትን ጎሳ የበላይነት በየመድረኩ ላይ መለፈፍ አይችልም።በኬንያ በዑጋንዳ ብንመለከት ሚኒስትሮች ይህንን ቢያደርጉ በሕግ ይቀጣሉ።እኛ ጋር ግን የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ የመጡበትን ብሔር መጥቀስ ብቻ ሳይሆን ከእዚህ ብሔር በመምጣታቸው ኩራት እንደሚሰማቸው ሕዝብ በተሰበሰበበት ያደረጉት ንግግር አሁንም ድረስ በብዙ ሰዎች እጅ ይገኛል።

 በሌሎች የአፍሪካ ሃገራ ውስጥ የአስተዳደር መዋቅሮች በተለይ ክልልሎች ቋንቋን መሰረት እንዳያደርጉ ጥንቃቄ ይደረጋል። ለምሳሌ ዑጋንዳን ብንመለከት የማዕከላዊው ቡጋንዳ ግዛት ውስጥ የምትገኘው የሀገሪቱ ዋና ከተማ ካምፓላ ከምዕራብ የመጡት ''መኛንኮሌ'' ሆነ ከሰሜን የመጡት ጎሳዎች እኩል በዜግነት ይኖሩበታል እንጂ በንጉሥ ደረጃ ያለው የቡጋንዳ ጎሳ የበላይነቱን አያሳይባትም።

ሌሎች ሃገራት በጎሳ ፖለቲካ ላይ ጥንቁቅ ናቸው።በእያንዳንዱ ሕግም ሆነ የሚድያ ሥራ ላይ የማይነኩ ቀይ መስመሮች ያሰምራሉ።እኛ ጋር ግን ቀዩን መስመር የሚረጋግጠው በጎሳ ላይ በተመሰረተ ሕግ የሚመራ የፖለቲካ መስመር ያለው መንግስት እራሱ ነው።ኢትዮጵያውያን ሳንጠፋ ልንቃወመው የሚገባን የመንግስት የጎሳ ፖለቲካ መስመርን ነው።ከመንግስት ሌላ በጎሳ ፖለቲካ በማናፈስ የምታወቁቱ የባሕርዳር ጥፋት ፈፃሚዎችን ጨምሮ፣በአምቦ ወረዳ አፈናቃዮች፣የጉርዳፈርዳ ውጡ ባዮች፣የቤንሻንጉል ባለግዜዎች፣የሐረር የነዋሪውን ሱቅ በእሳት አቀጣጣዮች፣በሱማሌ ክልል የኦሮምኛ ተናጋሪዎችን አሳዳጆች ወዘተ በትክክል አትከፋፍሉን ብለን መቃወም ስንችል ነው።

ድህነት በተስፋፋበት ሕብረተሰብ ውስጥ የጎሳ ፖለቲካ የነዳጅ ያህል እሳት አቀጣጣይ ነው።የከፋው እና ኑሮ የከበደው ሁሉ ብሶቱ ንግግሩ ይከብዳል። በእዚህ ላይ የጎሳ ፖለቲካ የሚያራምድ መንግስት ባለበት ሀገር።እናም መንግስት በቀዳሚነት ከጎሳ ፖለቲካ የወጣ እውነተኛ የፖሊሲ ለውጥ ያስፈልገዋል።ለእዚህ ለውጥ ዝግጁ ካልሆነ ግን ሕዝብ የጎሳ ፖለቲካ በቃን ብሎ የሚነሳበት ጊዜ ነው ማለት ነው።እናቶች ልጆቻችን በጎሳ ፖለቲካ አያልቁም! ወንዶች ለጎሳ ፖለቲካ አንተባበርም! አዛውንቶች የጎሳ ፖለቲካ አይጠቅምም! መንግስት ከጎሳ ፖለቲካ ይውጣ! መባል ያለበት ጊዜ ነው።የመንግስትን የጎሳ ፖለቲካን ጨምሮ በየቦታው እያቆጠቆጡ ያሉትን የጎሳ አራማጆችን አደብ ማስገዛት የሚቻለው የተቃውሞ የፖለቲካ መስመሩን ሕዝብ ሲዘውረው ነው።ይህ የሕልውና ጉዳይ ነው።

ጉዳያችን
መጋቢት 18/2006 ዓም 

Tuesday, March 25, 2014

ማኅበረ ቅዱሳን ማን ነው? (ቪድዮ)



ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

የቤተ ክህነቱ ችግር የቤተ መንግስቱ ችግር ሳይፈታ መፍትሄ እንደማያገኝ እነሆ ከተረጋገጠ ቆየ እኮ! በስመ ዶክመንተሪ ፊልም ሐሰት ቢከመር ቅንጣት ያክል የእውነት ጠብታ አይወጣውም። (የጉዳያችን አጭር ማስታወሻ)



በቤተ ክህነቱ ገንዘብ የሚደጎም ንግድ ያላቸው ሙሰኞች እጃቸው ቤተ መንግስቱ ድረስ አለ። እስክስታ ወራጆቹ የቤተ መንግስቱ ሰዎች በቤተ ክህነቱ ገንዘብ ሲሽሞነሞኑ አመታትን አስቆጠሩ።

'ቤተ ክህነቱ አስተዳደራዊ አሰራሩ ይስተካከል' ሲባሉ በጎሳ እና በጎጥ የተደራጁት የቤተ መንግስቱ እስክስታ ወራጆች እና አስወራጆች ያስነጥሳቸዋል።ሲፈልጉ ደግሞ በቅን እና በታማኝነት ቤተ ክርስቲያንን ሊያገለግሉ የተነሱትን ሁሉ ለማሳደድ 'ሰለፊ' እያሉ ያግዋራሉ።እራሳቸው 'ሰለፊ'  ለመሆናቸው አንድ ሺ መረጃዎች በአናታቸው ላይ ተሸክመው ካለ እፍረት መሄዳቸው ሳያንስ ሌብነታቸው እና ጎጠኝነታቸው የማይታወቅ እየመሰላቸው ሕዝብን ለማጭበርበር ይታትራሉ።

ቀድሞ ነገር ኢትዮጵያ እራሷ በዘረኛ እና ሙሰኛ መሪዎች እየማቀቀች ቤተ ክህነቱስ እንዴት ብሎ ይስተካከላል? የቤተ ክህነቱ ችግር የቤተ መንግስቱ ችግር ሳይፈታ መፍትሄ እንደማያገኝ እነሆ ከተረጋገጠ ቆየ እኮ! የቤተ ክህነቱ ሌቦች ቤተ መንግስቱ ውስጥ እየተርመሰመሱ ነዋ።

በስመ 'ዶክመንተሪ ፊልም' ሐሰት ቢከመር ቅንጣት ያክል የእውነት ጠብታ አይወጣውም።ስለእዚህ መፍትሄው ግልፅ እና ግልፅ ነው።ቤተ መንግስቱ ውስጥ የገቡ እስክስታ ወራጆች እና አስወራጆች የኢትዮጵያ በሆነው ነገር ላይ ሁሉ ለሰሩት ታሪካዊ ጥፋት ለፍርድ መቅረብ አለባቸው።ከእዚህ በላይ የቃላት ጋጋታ አያስፈልገውም።የዚህን ጊዜ የቤተ ክህነቱ ጎጠኞች ይከተሏቸዋል።

ጉዳያችን
መጋቢት 16/2006 ዓም 

Monday, March 24, 2014

የኑሮ ውድነቱ እና የትናንቱ የኢህአዲግ ስብሰባ አስገራሚ ድምዳሜ

የኑሮ ውድነት መድረሻው አይታወቅም 

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የኑሮ ውድነት በብርሃን ፍጥነት እየተመነጠቀ ነው። አንዲት ፌስ ቡክ ፀሐፊ እንዳለችው እኛም ከሶስት እና አራት ዓመታት በፊት የነበረውን ዋጋ እየጠቀስን ለዛሬ ልጆች ''በእኛ ጊዜ እኮ በ 90 ሳንቲም የ 45 ሳንቲም መሄጃ 45 ሳንቲም መመለሻ ታክሲ እንጠቀም ነበር፣በእኛ ጊዜ እኮ አንድ ኪሎ ስጋ በ 22 ብር እንገዛ ነበር፣በ እኛ ጊዜ እኮ አንድ ብር ካለን በ 75 ሳንቲም እስክርቢቶ ገዝተን በ 25 ሳንቲም ጀላቲ ገዝተን ዘነጥ ብለን ጀላትያችንን እየመጠጥን ወደ ቤት እንመጣ ነበር።'' ልንል ነው ያለችውን ያነበብኩት ዛሬ ነው።

የኑሮ በብርሃን ፍጥነት ደረጃ መወደዱን ለማስረዳት ደግሞ ይህንን ስሌት ማሳየት ተገቢ ይመስለኛል።

1/ ዘመን= 1983 ዓ ም የአንድ ምሩቅ ደሞዝ 500 ብር (ከእዚህ ላይ የመንግስት ግብር እና የጡረታ ይቀነሳል)

በ1983 ዓም  1 ዶላር = 2.07  ሲሆን የአንድ ምሩቅ ደሞዝ 500 ብር  ወደ ዶላር ሲቀየር 250 ዶላር ይሆናል።
በእዚህ ዘመን ኑሮ እርካሽ ነበር። ለምሳሌ፣ የአንድ ኪሎ ስጋ ዋጋ 5 ብር ነበር። አዲስ አበባ የሸዋ ዳቦ ቤት አንድ ዳቦ በ 10 ሳንቲም ይሸጣል። በ 1 ብር ከ 50ሳንቲም  ሽሮ ወጥ ከተሰነገ ቃርያ ጋር አዲስ አበባ ይሸጥ ነበር። አንድ ሊስትሮ ፓስታ በስጎ ከዳቦ ጋር በ 1 ብር መመገብ ይችላል።ለእዚህ ብዙዎች ምስክር ናቸው።
በወቅቱ አንድ 200 ብር የሚያገኝ ጡረተኛ  በትንሹ የቤት ኪራይ ከፍሎ 5 የቤተሰብ አባላት ያስተዳድራል።ይህ ማለት ከወር ወር የጤፍ እንጀራ እየበሉ ማለት ነው።

2/ ዘመን 2006 ዓም የአንድ ተመራቂ ደሞዝ 1,400 (ከእዚህ ላይ የመንግስት ግብር እና የጡረታ ይቀነሳል)

ዛሬ አንድ ዶላር =19.37ሳንቲም ይመነዘራል።ዛሬ የአንድ ተመራቂ ደሞዝ ካልተጋነነ 1,400 ብር(መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች) ከእዚህ ላይ የመንግስት ግብር እና የጡረታ ይቀነሳል።ይህ  በዶላር 72  ይሆናል ማለት ነው። ይህ ማለት አንድ ምሩቅ የዛሬ 23 ዓመት ያገኝ የነበረው 250 ዶላር የነበረ ሲሆን አሁን እያገኘ ያለው ግን 72 ዶላር ብቻ ነው።ይህ ማለት አንድ ምሩቅ ከዩንቨርስቲ እንደወጣ ማግኘት ያለበት 4,840 ብር ነበር ማለት ነው።ይህም የኑሮ ውድነቱን የሚያግዝ ሳይሆን በልቶ ለማደር ብቻ ነው።ዛሬ የሸቀጦች ዋጋ ስንት ነው? ጤፍ ኩንታል 1,400፣ስጋ 90 ብር፣ወዘተ

በኑሮ ውድነቱ ላይ የትናንቱ አስገራሚው የኢህአዲግ ድምዳሜ

''የኑሮ መወደዱን ኢህአዲግ በስብሰባው ላይ አንስቶት ነበር'' ያለው የዛሬ ሰኞ መጋቢት 15/2006 ዓም የኢቲቪ ዜና ኢህአዲግ ''መፍትሄው ምርትን ማሳደግ ነው ብሏል '' ሲል ተናግሯል።ለመሆኑ -

- 'ማክሮ ኢኮኖሚክስ' ለዋጋ መናር መፍትሄውምርት ማሳደግ ብቻ ነው ይላል?
- የወለድ መጠን፣የብሔራዊ ባንክ የገንዘብ አቅርቦት፣የውጭ ምንዛሪ ከሀገር ውስጥ ገንዘብ ጋር ያለው ተመን፣የስራ      ዕድል ፈጠራ፣የግል ዘርፉ ተሳትፎ፣ ባጠቃላይ የ'ሞነተሪ እና የፊዚካል' ፖሊሲው ተፈትሿል?
- መንግስት ከአቅም በላይ የገባበት ፕሮጀክት ለምሳሌ በኢንፍራስትራክቸር ላይ እስከ 60 በመቶ በጀት እየበላ መሆኑ (ምንም እንኩዋን ኢንፍራ ስትራክቸር አስፈላጊ ቢሆንም በሕዝብ የኑሮ ጉሮሮ ላይ መምጣት አይገባውም) እና ሌሎች ጉዳዮች ለኑሮ ውድነቱ መንስኤ መሆናቸውን ኢህአዲግ አያውቃቸውም?
- ቅጥ ያጣው ሙስና የገበያ ስርዓቱን አላናጋውም?
- በምግብ ላይ የተጣለው የ ቫት ቀረጥ ድሃው በሀገሩ የሚመረተውን የጤፍ እንጀራ እንዲናፍቅ አላደረገውም?

ጠቅላይ ሚኒስትሩን የከበቡት ወደ ደርዘን የሚጠጉ አማካሪዎች 'ማክሮ ኢኮኖሚውን' መፈተሽ አልቻሉም? ለማንኛውም ኢህአዲግ ''የኑሮ ውድነቱን ለማሸነፍ ምርትን ማሳደግ ነው'' ብሏል። በቃ ብሏል።ኢህአዲግ ያለውን ደግሞ ማን ይሽረዋል? ''ማክሮ ኢኮኖሚው ይፈተሽ'' ብሎ የሚከራከር ደግሞ ፀረ-ልማት ሊባል ይችላል።የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ አቶ ሶፍያን አህመድ ስብሰባው ላይ እጃቸውን እንዳጣመሩ ተቀምጠው ይታያሉ።ከአንድም ሁለት ጊዜ በኢኮኖሚ ጉዳይ ላይ ትንታኔ ሲሰጡ  አይቻቸዋለሁ።ምንም አይነት ወረቀት ሳይመለከቱ የሚሰጡትን ትንታኔ ስመለከት የአቅም ችግር እንደሌለባቸው በአቅሜ ተረድቻቸዋለሁ።ጥያቄው ግን እሳቸውስ ይደመጣሉ ወይ? ነው።እሳቸውም ማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲው ይፈተሽ ብለው ተናግረው ተቆጥተዋቸው ይሆን እንዴ?

ጉዳያችን
መጋቢት 16/2006 ዓም 

‹‹ግዕዝ እንደ አንድ ቋንቋ መነጋገሪያ እስኪሆን ድረስ ወደኋላ አልልም›› መምህርት ኑኃሚን ዋቅጅራ


መምህርት ኑኃሚን ዋቅጅራ 28 ዓመቷ ሲሆን ተወልዳ ያደገችው በአዲስ አበባ መሳለሚያ አካባቢ ነው፡፡ ዕድገቷ በቤተ ክርስቲያን አካባቢ በመሆኑ ለግዕዝ ትምህርቷ መነሻ ሆኗታል፡፡

በደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ቅፅር ግቢ በቄስ ትምህርት የተጀመረው ትምህርቷ ዛሬ የግዕዝ መምህርት እንደትሆን አድርጓታል፡፡ የግዕዝ ቋንቋ ትምህርት በሚሰጥበት አቡነ ጐርጐርዮስ ትምህርት ቤት ከአንደኛ እስከ 10 ክፍል የሚያገለግል የመማርያ መጻሕፍት ከዚህ ቀደም አዘጋጅታ አበርክታለች፡፡ የካቲት 30 ቀን 2006 ዓ.ም. ደግሞ ማንኛውም የግዕዝ ቋንቋን ማወቅ የሚፈልግ የሚማርበት ‹‹ማህቶተ ጥበብ ዘልሣነ ግዕዝ›› የመጀመሪያ ክፍል መጽሐፍ አስመርቃለች፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ግዕዝን የሚያመሰጥሩ የሚያስተምሩና እንደ እማሆይ ገላነሽ ዓይነት ሴቶች ቢኖሩም ከግዕዝ መምህርነቷ በተጨማሪ በመጽሐፍ ከትባ ለማስቀመጥ የመጀመርያዋ ሴት መሆኗን መጽሐፉ በተመረቀበት ዕለት የተገኙት የግዕዝ መምህሩ ዜና እንዳለው ተናግረዋል፡፡ መምህርት ኑኃሚን በአማርኛ እንግሊዝኛ ቋንቋ ከቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ዲፕሎማ፣ በሥነ መለኮት ከቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ ዲፕሎማዋን አግኝታለች፡፡ በግዕዝ ሥራዎቿ ዙርያ ምሕረት ሞገስ አነጋግራታለች፡፡

ሪፖርተር፡- ወደ ግዕዝ ትምህርት እንዴት ገባሽ?

መምህርት ኑኃሚን፡- ልጅ ሆኜ ፊደል የቆጠርኩት መሳለሚያ አማኑኤለ ቤተክርስቲያን ውስጥ በሚገኘው ቄስ ትምህርት ቤት ነው፡፡ እስከ ዳዊት ድረስ እንደተማርኩ ግብረሰናይ ድርጅት መጥቶ ለችግረኛ ተማሪዎች ትምህርት ቤት አቋቋመ፡፡ አማኑኤለ ግቢ የነበርነውን የቄስ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በሙሉ የመጀመርያ ተማሪ አድርጐ ተቀበለንና አንደኛ ክፍል ገባን፡፡ የመደበኛውን ትምህርት እስከ 9፡30 እየተማርን የግዕዝ ትምህርቱን የምንፈልግ በግላችን ከ9፡30 አስከ 11፡00 ሰዓት መማር ጀመርን፡፡  

ሪፖርተር፡- ግዕዝ ያስተማሯችሁ ማን ናቸው?

መምህርት ኑኃሚን፡-  በጠልሰም ሥራ የአርት ፕሮፌሰር መጋቢ ሚስጥር ጌድዮን መኰንን ናቸው፡፡ ዛሬ ለደረስኩበት የግዕዝ ዕውቀት መሠረቱን ያስያዙኝ እሳቸው ናቸው፡፡ ከሕፃንነት ጀምሮ ግዕዝ አስተምረውኛል፡፡ 11ኛ ክፍል እስክደርስ ድረስ ግዕዙን ከእሳቸው እየተማርኩ ነበር፡፡ 11ኛ ክፍል እያለሁ እሳቸው በማረፋቸው ሊቀ ህሩያን መሃሪ አስተምረውኛል፡፡ እሳቸውም ብዙም ሳይቆዩ ነው ያረፉት፡፡

ሪፖርተር፡- ምን ያሀል ተማሪዎች ነበራችሁ?

መምህርት ኑኃሚን፡-  መደበኛ ትምህርት ላይ ብዙ ሆነን ነው የተማርነው፡፡ ግዕዙን በተጨማሪ የተማርነው ግን ጥቂት ነን፡፡ መምህራችን የሥነ ምግባር ጉዳይ ላይ ጠንካራ ናቸው፡፡ ግዕዙን ስንማር መሳሳት ያስቀጣል፡፡ ኃይለኛ ስለነበሩ ወላጆች ልጆቻቸውን ከትምህርት ቤት ማስቀረትን መርጠው ነበር፡፡

ሪፖርተር፡- እንዴት ልትቀጥይ ቻልሽ?

መምህርት ኑኃሚን፡- በትምህርቱ እንድገፋ ከጐኔ የነበሩት እናቴና ወንድሜ ናቸው ፡፡ ሐረር ያለው ወንድሜ የግእዝ ዕውቀት ብዙም ባይኖረውም ደብዳቤ ስጽፍለት በግዕዝና በአማርኛ እንዲሆን ያዘኝ ነበር፡፡ የፈተና ውጤት ይዤ ስገባም ቤተሰቦቼ አስቀድመው የሚያዩት የግዕዝና የሥነ ምግባር ውጤቶቼን ነበር፡፡ የግዕዝ ትምህርቴን እንድተው የአካባቢው ሰዎች እናቴን ቢወተውቷትም ፈቃደኛ አልነበረችም፡፡ ተገረፍኩኝ ብላ የምትቀር ከሆነ ራሷ ትወስን ነበር የምትላቸው፡፡ ሁሌም መምህር ተማሪዎቹ ውጤታማ እንዲሆኑለት ነው የሚቀጣው እኔም እንደትቀር አልፈልግም ትል ነበር፡፡ ቤተሰቦቼ ብርታት ሆነውኝ የግዕዙን ትምህርት ልቀስም ችያለሁ፡፡

ሪፖርተር፡- ሁለቱ የግዕዝ መምህራን ካረፉ በኋላ ትምህርቱን እንዴት ቀጠላችሁ?

መምህርት ኑኃሚን፡- ግቢው ውስጥ ግእዙን እስከ 11ኛ ክፍል የተማርኩት እኔ ብቻ ነበርኩ፡፡ መምህራኑ በሞቱ በዓመቱ የግዕዝ መምህር ቅጥር ማስታወቂያ ወጣ፡፡ ለውድድሩ የቀረብነው እኔና ሰባት መሪ ጌታዎች ነበሩ፡፡ አንድ ሴት ሰባት ወንድ ማለት ነው፡፡ በየገጠሩ ከውሻ ጋር እየተባረሩ ግዕዝ ከተማሩ ሰዎች ጋር እንዴት ትወዳደሪያለሽ በሚል ፈተና ገጥሞኝ ነበር፡፡ ቦታውን ያገኛል ተብሎ የተጠበቀውም ከመሪ ጌታዎቹ ውስጥ ነበር፡፡ መጋቢ ሚስጥር ጌድዮን ገና ተማሪ እያለን ያሉኝን ያስታወሰኝ ወቅት ነበር፡፡ ቅኔ ማህሌት ውስጥ ሴት መግባት ስለማትችል ከዛ ልንቀስም የምንችለውን ዕውቀት ለማግኘት ፈተና ነበር፡፡ መምህራችን ‘ወንድ ብትሆኑ ስሜን ታስጠሩ ነበር’  ይሉን ነበር፡፡ አባቴን ሁሌም ሴት ልጅ ስም አታስጠራም እንዴ? እያልኩም እጠይቀው ነበር፡፡ ‘ዋቅጅራ ተብሎ የኔ ስም የሚጠራው የአንቺ አባት ስለሆንኩ አይደል’ ይለኛል፡፡ በፈተናው ወቅትም ከአካባቢዬ የገጠመኝ ፈተና ይኸው ነበር፡፡ ሆኖም ፈተናውን አልፌ በደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የግዕዝ መምህርት ሆኜ በ1994 ዓ.ም. ተቀጠርኩ፡፡ ሁለት ዓመት እንዳስተማርኩ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ማንኛውም መምህር የመምህርነት ትምህርት ማስረጃ ከሌለው ማስተማር አይችልም የሚል መመርያ አወጣ፡፡ እዚያው እያስተማርኩ ቅድስተ ማርያም ዩኒቨርሲቲ ገብቼ በ1999 ዓ.ም. በአማርኛ፣ እንግሊዝኛ ቋንቋ ዲፕሎማ ያዝኩ፡፡ 2000 ዓ.ም. ላይ በግዕዝና በሥነ ምግባር ትምህርት ዙርያ የሌሎች ሃይማኖት ተከታዮች ላይ ተፅዕኖ ትፈጥራላችሁ በሚል የካቴድራሉን ትምህርት ቤት ለመገምገም ከትምህርት ቢሮ ባለሙያዎች መጡ፡፡ ሁለቱንም ትምህርት የማስተምረው እኔ ስለነበርኩ የመንፈሳዊ ሥነምግባር ትምህርት በፍላጐት ብቻ የሚሰጥ መሆኑን፣ የግዕዝ ትምህርቱ ደግሞ የወንበር ትምህርት ማለትም ውዳሴ ማርያም፣ ገድላት፣ ተአምራትን ያካተተና የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ብቻ የሚመለከት በመሆኑ የእምነቱ ተከታዮች ብቻ የሚማሩትን ሳይሆን የግዕዙን ቋንቋ ትምህርት እንደማንኛውም አንድ የኢትዮጵያ ቋንቋ እንደሚማሩት አብራራሁ፡፡ የማስተምርበትን ወርሃዊና ዓመታዊ የትምህርት ዕቅድ አሳየኋቸው፡፡ ትምህርቱ ተከፋፍሎ የሚማሩበትን የኮምፒውተር ጽሑፍም አዩ፡፡ ገምጋሚዎቹ ስለግዕዝ ትምህርት የነበራቸው ግንዛቤ ከእምነቱ ጋር ብቻ የተያያዘ፡፡ ሆኖም ግዕዝ የወንበርና የቋንቋ ተብሎ የተከፈለ ተማሪዎቹም የሚማሩት የቋንቋውን ክፍል ብቻ መሆኑን አስረዳኋቸው፡፡ ከተማሪዎቹ ያገኙት መልስም ስለግዕዝ ቋንቋ ብቻ እንደሚማሩ ነበር፡፡  

ሪፖርተር፡- ካንቺ ከተረዱ በኋላ አስተያየታቸው ምን ነበር?

መምህርት ኑኃሚን፡- ስለምንሰጠው ግዕዝ ቋንቋ ትምህርት ካስረዳኋቸው በኋላ እስከምን ድረስ ትዘልቂበታለሽ ነበር ያሉኝ፡፡ የአምላክ ፈቃድ ቢሆን የግዕዝ ቋንቋ ትምህርት አገር አቀፋዊ እንዲሆን ነው የምመኘው፡፡ ግዕዝ አገር አቀፍ ቋንቋ መሆን እንደሚችል አምናለሁ፡፡ አገር አቀፍ ቋንቋ ባይሆን ኖሮ በብሔራዊ ደረጃ የግዕዝ ቋንቋ ፈተና አይሰጥም ነበር፡፡ የግዕዝ ቋንቋ የተመቻቸ የትምህርት መሠረት ቢኖረው ማንኛውም ተማሪ መማር የሚችለው ነው አልኳቸው፡፡ ገምጋሚዎቹ ሀሳቤን ሲረዱ በክፍል በክፍል ከፋፍለሽ በመማርያ መጽሐፍ መልክ ብታዘጋጀው በኢትዮጵያ ደረጃ ጠቃሚ ይሆናል፡፡ በዚሁ ብትቀጥይ ጥሩ ነው አሉ፡፡ ባለሙያዎቹ አስተያየቱን ከሰጡኝ በኋላ በሒደት ከአንደኛ እስከ 10 ክፍል በየክፍሉ የተከፋፈለ የግዕዝ ቋንቋ መማርያ መጻሕፍት አዘጋጅቼ በማኅበረ ቅዱሳን አቡነ ጐርጐርዮስ ትምህርት ቤት ጥቅም ላይ እየዋለ ነው፡፡    

ሪፖርተር፡- ማኃቶተ ጥበብ ዘልሣነ ግዕዝ አንደኛ መጽሐፍ ለማዘጋጀት ያነሳሳሽ ምንድን ነው?

መምህርት ኑኃሚን፡- ሦስት መሠረታዊ ነገሮችን ይዤ ነው፡፡ ደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል እያለሁ ከትምህርት ቢሮ ከመጡት ገምጋሚዎች የግዕዝ ቋንቋን በቋንቋነቱ አብዛኛው ሰው እንደማያውቀው ተረዳሁ፡፡ ስለዚህ የግዕዝ ቋንቋን ማንኛውም ሰው መማር እንደሚችል ለማሳየት በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንም ቋንቋውን በአደራ ተቀብላ እየተጠቀመችበት እንጂ የግሌ ነው ብላ እንዳልያዘችውና ማንኛውም ሰው እንደ አንድ ቋንቋ መማር እንደሚችል ለማሳወቅ ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ግዕዝ ቋንቋን ማንኛውም ሰው መማር ይችላል፡፡ መሠረታችንም የግዕዝ ፊደል ነው፡፡ ያላወቅነው እንዴት እንደምንግባባበት ነው፡፡ ፊደል የቆጠረ ሁሉ አጠቃቀሙን ካለማወቅ እንጂ ግዕዝን ተምሯል፡፡ ሆኖም ከልጅነታችን ፊደል ቆጥረን እንጂ የግዕዝ አገባቡን ስለማናውቀው ግዕዝ ሞቷል የሚሉ አሉ፡፡ ግዕዝ እንዳልሞተ የተማርነውና እየተማርነው ያለ እንዲሁም እየተጠቀምንበት መሆኑን ለመግለጽ ነው፡፡ ግዕዝ የኢትዮጵያ ቋንቋ እንደሆነ ለማሳወቅ ነው፡፡ ሦስተኛው ያጣኋቸውን መምህሬን መጋቢ ምስጢር ጌድዮን መኰን ለማሰብ ነው፡፡  

ሪፖርተር፡- መጽሐፉን ስታዘጋጂ ያጋጠሙሽን ችግሮች ብትጠቅሽልን?

መምህርት ኑኃሚን፡- ብዙ ተቸግሬያለሁ፡፡ የመጀመርያው የግዕዝ መምህሬ ሲያስተምሩን በቃል ነው፡፡ በቃል የተማርኩትን ወደ መጽሐፍ ለመቀየር መረጃ ያስፈልገዋል፡፡ ብዙ መጻሕፍት ማየት ነበረብኝ፡፡ እስከ 900 ብር አውጥቼ የኪዳነ ወልድ ክፍሌን ፅፌ ከእኔ ለተሻሉ የቤተክርስቲያን ምሁራንና አባቶች ሳስተችና ሳስገመግም ብዙዎቹ የተባበሩኝ ቢሆንም ጊዜ ወስዶብኛል፡፡ መጽሐፉ እንዲታተም ለማኅበረ ቅዱሳን የገባው በ2002 ዓ.ም. ነው፡፡ የወጣው ደግሞ 2006 ዓ.ም. ላይ ነው፡፡ መጽሐፉን ለማሳተም ስፖንሰር ለመሆን የፈቀዱ ሰዎች ሲዲውን ለማየት ከወሰዱ በኋላ ጠፍቶባቸዋል፡፡ ከማኅበረ ቅዱሳን 2003 ዓ.ም. ለመጀመርያው እትም ተብሎ የተከፈለኝም 5 ሺሕ ብር ነው፡፡ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ያዘጋጀሁትን የግዕዝ ቋንቋ መማርያ መጻሕፍት ያለምንም ክፍያ ነው በአቡነ ጐርጐርዮስ ትምህርት ቤት ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው፡፡ ማበረታቻ ተብሎ ግን 4 ሺሕ ብር ተሰጥቶኛል፡፡ ሆኖም የልፋቴን ዋጋ አላገኘሁም፡፡ የ9ኛ እና የ10ኛ ክፍል የግእዝ መማርያ መጽሐፍ አዘጋጅቼም ማኅበሩ እየተጠቀመበት ነው፡፡ በሌላ በኩል በምፈልገው መጠን ሕዝቡ እጅ አልደረሰም፡፡ ከዚህ አንፃር ማኅበረ ቅዱሳን ለሕዝቡ በስፋት በሚያሠራጭበትና እኔም ተጠቃሚ የምሆንበትን መንገድ እንዲያሳውቀኝ በደብዳቤ ጠይቄያለሁ፡፡

ሪፖርተር፡- በግዕዝ ዙርያ እስከምን ድረስ ለመሄድ አስበሻል?

መምህርት ኑኃሚን፡- ግእዝ እንደ አንድ ቋንቋ መነጋገሪያ እስኪሆን ድረስ ወደኋላ አልልም፡፡ ብዙ ነገሮቻችንን ስናይ ከግዕዝ ቋንቋ ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ እኔ እዚህ ደርሻለሁ፡፡ ነገ የሚመጣው ትውልድ ከእኔ በተሻለ ቋንቋውን እንዲጠቀምበት እፈልጋለሁ፡፡  

ምንጭ - ሪፖርተር  ዕሁድ መጋቢት 14/2006 ዓም 

Saturday, March 22, 2014

Eng Yilkal is barred from boarding his flight to the US Sat, 03/22/2014 - 04:14 — Semayawi party


The below statement is found from Semayawi Party web http://semayawiparty.org/Eng%20Yilkal%20is%20barred%20from%20boarding%20his%20flight%20to%20the%20US
Semayawi Party Chaiman, Eng Yilkal Getnet was barred from boarding his flight to the United States on Friday, March 21, 2014 at Addis Ababa airport. He was scheduled to fly to the US to attend a fellowship program of the Young African Leaders Initiative of the United States State Department. Eng. Yilkal was told to see a TPLF supervisor by airport crew right before boarding time where he was told he would not be flying. His luggage was unloaded from the plane and he stayed at the airport for more than 3 hours thereafter questioned by TPLF agents. He has returned back to his home after 2:00am local time Saturday.

.......................////////.........................////////............................/////////............................/////////..................

Friday, March 21, 2014

ኢትዮጵያዊቷ ፕሮፌሰር ሰገነት ቀለሙ በዓለም ዙርያ ካሉ 1000 ሳይንቲስቶች ውስጥ ከተመረጡት ከዓለም አምስቱ ምርጥ ሳይንቲስቶች ከአፍሪካ እና አረብ ሃገራት ደግሞ ብቸኛ ሆነው የ 2014 ዓም የዩኔስኮ 'ሎሬአል' ሽልማት አሸናፊ ሆኑ።

ፕሮፌሰር ሰገነት ቀለሙ

ፕሮፌሰር ሰገነት ቀለሙ በዓለም ላይ ካሉት አምስቱ ምርጥ ሴት ሳይንቲስቶች ውስጥ አንዷ እና በአፍሪካ እና ከአረብ ሃገራት ብቸኛ ሆነው የተመረጡ መሆናቸውን የዩኔስኮ ድረ-ገፅ ገልጧል።

ድረ-ገፁ አክሎም  የምርጫውን ሂደት ሲያስረዳ አንድ ሺህ ዓለም አቀፍ ሳይንቲስቶች ኔትዎርክ አማካይነት ምርጫውን እንደሚያደርግ፣ በመጨረሻ አስራ ሁለት አባላት ባሉት ዓለም አቀፍ ሳይንሳዊ ማኅበረሰብ (International Scinitfic Community) አማካይነት ውሳኔ እንደሚያገኝ ያብራራል።

ፕሮፌሰር ሰገነት ቀለሙ መቀመጫውን ናይሮቢ ኬንያ ያደረገው በአካባቢ ስነ-ምህዳር ላይ የሚሰራው  International Center for Insect Physiology and Ecology (ICIPE) ዳይሬክተር ጀነራል ሆነው ይሰራሉ።

ዩኔስኮ ሽልማቱን አስመልክቶ የሰጠውን ዜና ከእዚህ በታች ባለው ሊንክ ይመልከቱ።
http://www.unesco.org/new/fileadmin/MULTIMEDIA/HQ/SC/pdf/PressR_L-OREAL_UNESCO_2014_EN.pdf

ጉዳያችን
መጋቢት 12/2006 ዓም 

Thursday, March 20, 2014

የኖርዌይ ህገ መንግስት ከፀደቀ በመጪው ግንቦት አጋማሽ ላይ 200ኛ ዓመቱ ይከበራል።በኖርዌይ የምንኖር ኢትዮጵያውያን በዓሉ ኖርዌይ ከኢትዮጵያ ጋር የነበራትን መልካም ግንኙነት የምናሳይበት ጥሩ አጋጣሚ ነው።

የኖርዌይ ህገ መንግስት አርቃቂ መስራች አባቶች ግንቦት 17/1814

በዘመናዊው ዓለም ከአሜሪካ ቀጥሎ ለሰው ልጆች በሚያጎናፅፈው መሰረታዊ  መብት  በምሳሌነቱ ይነሳል።እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ ግንቦት 17/1814ዓም  መፅደቁ የሚነገረው ህገ መንግስት እስካሁን በየዘመኑ ዘመን አመጣሽ የህዝብ ፍላጎት ጋር ለማስታረቅ ሲባል 400 ጊዜ ማሻሻያዎች ተደርገውበታል።የፖለቲካ ፓርቲዎች ''ይህ ሕግ የሚቀየረው በመቃብሬ ላይ ብቻ ነው'' እያሉ እንደሚያስፈራሩን የአፍሪካ ፓርቲዎች አይደለም።አስተሳሰቦች ይከለሳሉ፣ይቀየራሉ።ኢትዮጵያ ሃገራችን ህገ መንግስቷ ብቻ ሳይሆን ሰንደቅ ዓላማዋ እና ብሔራዊ መዙሯ በየዘመኑ በሚነሱ ገዢዎቿ ሲቀየሩ ማየት አሳዛኝ ነው።በመንግስትነት ከአውሮፓውያን ከሶስት ሺህ አመታት ለበለጡ ዘመናት ዘልቀናል።ሁሉን ያቀፈ መሰረታዊ ግን በየዘመኑ ሊሻሻል የሚችል ህገ መንግስት ግን 'የለንም'።
ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ስላሴ በኖርዌይ ጉብኝት 1954 ዓም እ ኤ አቆጣጠር የኖርዌይ ጋዜጣ 

መልሼ ደግሞ የለንም ወይ? ብዬ እጠይቃለሁ።ከሺህ ዓመታት በላይ የፍትሐ ነገስት በሥራ ላይ መዋል።ይሄው ሕግ እንደ ፈረንሳይ ለመሳሰሉት ሀገራትም ሆነ ለዓለም አቀፍ ሕግ ያደረገው አስተዋፅዖ ሁሉ ሲታሰብ 'የለንም ነበር' ከማለት ''በነበረን ላይ አዳብረን መጠቀም አልቻልንም'' የሚለው የተሻለ አባባል ይመስለኛል።ለሁሉም ግን ኖርዌይ የ 200 ዓመት ህገ መንግስት በዓል ደመቅ ተደርጎ ይከበራል።
ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ስላሴ በኖርዌይ ጉብኝት 1954 ዓም እ ኤ አቆጣጠር የኖርዌይ ጋዜጣ

በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም በዓሉ ላይ የኢትዮጵያውያን እና የኖርዌይ ግንኙነትን የቆየ ታሪክ የያዘ መርሐ ግብር ማዘጋጀት ይገባቸዋል።ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ስላሴ የአሁኑ የኖርዌይ ንጉስ አባት ሃኮን ጋር በመጀመርያ የተገናኙት በጣልያን ወረራ ወቅት እንግሊዝ ሀገር ሲሆን በኃላ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ህዳር 1954 ዓም ንጉሡ  ኖርዌይ፣ኦስሎን ሲጎበኙ ወዳጅነቱ ጠንክሯል።ኖርዌይ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ሲመሰረት የሰው ኃይል ስልጠናን ጨምሮ ድጋፍ ካደረጉ ሃገራት ግንባር ቀደምም ነች።በመሆኑም እነኝህን የቆዩ ግንኙነቶች የሚያሳዩ የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይ ማዘጋጀት እና የኖርዌይ ወዳጆቻችንን እና የመገናኛ ብዙሃንን በመጋበዝ ብዙ ማለት ይቻላል።

መልካም በዓል ኖርዌይ

ጉዳያችን መጋቢት 11/2006 ዓም 

Wednesday, March 19, 2014

በኩዌት የሰሞኑ የኢትዮጵያውያን ችግር ከሳውዲው በተለየ አይን እንየው።ከሰሞኑ ክስተት ጋር በተያያዘ ምን ይደረግ?




በኩዌት አንዲት አትዮጵያዊት የአሰሪዋን ልጅ ገድላለች በሚል በኢትዮጵያውያን ላይ አንዳንድ ችግሮች እየተፈጠሩ መሆኑ እየተሰማ ነው።ሟች ኩዌታዊት ደግሞ  የዩንቨርስቲ ተማሪ መሆኗ እና በተለይ የኩዌት የስፖርት ሚኒስትር ልጅ መሆኗ ሁኔታውን አክርሮታል።

የኩዌት ጉዳይ ከሳውዲው በተለየ መልክ መታየት ያለበት ይመስለኛል። ኩዌት ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ግንኙነት እንደ ሕዝብ ጠንከር ያለ ነው።ረጅም ግንኙነት ብቻ ሳይሆን በተለይ በደርግ ዘመን በኢራቅ ወረራ ሳብያ ኢትዮጵያ ከኩዌት  መቆሟ በኩዌታውያን ዘንድ ከፍ ያለ ዋጋ ተሰጥቶታል። ለእዚህም ነው ኩዌት ከ ኢራቅ እጅ እንደወጣች ልዑካንን ልካ ኢትዮጵያን ማመስገን ብቻ ሳይሆን ለቦሌ አየር ማረፍያ ተርሚናል ማስፋፍያ ከሰላሳ ሚልዮን ዶላር በላይ ያፀደቀችው በደርግ ዘመነ መንግስት ነው።ፕሮጀክቱ ደርግ ከወደቀ በኃላም እንዲከናወን ቃሏን ጠብቃለች።ኩዌት  ኢትዮጵያን የምታይበት የተሻለ አይን አላት።አሁን በኩዌት ከሰማንያ ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን እንዳሉ ይነገራል።

ከሰሞኑ ክስተት ጋር በተያያዘ ምን ይደረግ?

ከሰሞኑ ክስተት ጋር በተያያዘ መከናወን ያለባቸው ሁለት ነገሮች ይመስሉኛል -

1/ ኩዌት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በመጀመርያ  ሕይወቷ ላለፈው የኩዌት ወጣት ማዘናቸውን መግለፅ አለባቸው።ይህ ተገቢ ነገር ነው።ወጣቷ የዩንቨርስቲ ተማሪ ሕይወቷ አልፎ ስለሷ ማዘናቸውን ሳይገልፁ ስለበደል ቢወራ የሚሰሙ ኩዌታውያን አይኖሩም።እንደሚባለው ከሆነ ኢትዮጵያውያን ይባረሩ የሚል ሰልፍም በተውሰኑ ሰዎች ተዘጋጅቶ ነበር። ይህ የወጣቷ መሞት የፈጠረው የቁጣ ስሜት ነው።ለምን ተቆጡ? ማለት አይቻልም።በመሆኑም ኢትዮጵያውያን በኮሚኒቲያቸው አማካይነት ከፍተኛ የሀገሪቱን አካላት በማግኘት በሁኔታው ማዘናቸውን መግለፅ እና ገድላለች ለተባለቸው ወጣት ጠበቃ ማቆም ብሎም ነገሩ የሚድያ ሽፋን እንዲያገኝ ማድረግ ተገቢ ነው።በተለይ ኢትዮጵያውያን በሞተችው ልጅ ማዘናቸውን በሚድያ እንዲገለፅ እና ህዝቡ እንዲያውቅ ማድረግ አለባቸው።

2/ የመንግሥታት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ዞሮ ዞሮ የወሳኝነት ሚና ስለሚኖረው መንግስት ከፍተኛ ልዑክ ልኮ ኢትዮጵያውያን በግድያው ማዘናቸውን መግለፅ እና በቀሩት ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰው ከስራ መፈናቀል እንዲቆም እንዲደረግ ባልታወቁ ኩዌታውያን ተገላለች የተባለችው ኢትዮጵያዊት ጉዳይ እንዲጣራ ቢጠይቅ እና ወደሀገራቸው መመለስ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መጀመር አለበት ብዬ አስባለሁ።

ከእዚህ በተለየ ግን እንደ ሳውዲ አረብያ በማኅበራዊ ድረ-ገፆች ቸኩለን የኩዌትን ሕዝብ ወደመውቀሱ ባንሄድ ለእዚህ ጊዜው ገና ነው ብዬ አስባለሁ።ኩዌት ኢትዮጵያውያንን ታከብራለች።በእያንዳንዱ ጉዳዮች ላይ እንደ ሕዝብ እሰጥ አገባ መቀያየር  እንደ ሀገርም የኢትዮጵያን  ወዳጆችን ማጣት ነው። ከእዚህ ደግም ተጠቃሚ የለም።እንደዘለቄታ ግን በአረብ ሃገራት ያሉ ኢትዮጵያውያን ከሚጠቀሙት የምጎዱበት መንገድ እስከ በዛ ድረስ ያለቻቸውን እየያዙ ወደሃገራችው የሚገቡበት መንገድ መፈለግ ይገባል። በታወቀ የፖለቲካ ችግር ምክንያት መግባት የማይችሉት ደግሞ ወደሶስተኛ ሀገር እንዲገቡ የሚመቻችበትን ሁኔታ መፈለግ ሌላው መንገድ ይሆናል።እስኪ ስለ ኩዌት የበለጠ ግንዛቤ ይላችሁ ደግሞ አክሉበት።

ጉዳያችን
መጋቢት 11/2006 ዓም 

Tuesday, March 18, 2014

The Hypocrisy of the West: Eritrea & Crimea


March 18, 2014
by Messay Kebede

The West is deploring the referendum in Crimea and threatening to apply economic sanctions against Russia, believed to be the instigator of the unfolding Ukrainian crisis. Some Western politicians even go the extent of advocating direct military aid so that Ukraine can oppose military resistance to the Russian aggression. The referendum, which is supposed to lead to the reintegration of Crimea into the Russian Federation, is characterized by the West as illegal. From what I was able to gather, the reasons why the referendum is considered illegal include the followings. (1) Ukraine is an independent and sovereign country; (2) the referendum takes place with a strong presence of Russian military force in Crimea; (3) the referendum does not offer Crimea the choice of remaining within Ukraine.
What beats everything is that the West did not raise any concern about legality when Eritrea seceded from Ethiopia in 1993, even though all the reasons enumerated to contest the referendum in Crimea were also present in Ethiopia. Thus, ( 1) Ethiopia is an independent and sovereign nation; (2) the referendum was conducted in the presence of the victorious EPLF army; (3) The choice to remain  part of Ethiopia under a new political arrangement was not offered to Eritreans, nor was Ethiopia given the opportunity defend its legitimate position and interests, except through the TPLF government. The latter had no legality other than the power of arms and was already dead set to expel Eritrea from Ethiopia as a dangerous rival to the TPLF hegemony in Ethiopia. Yet, though conducted under such faulty conditions and in direct violation of the sovereignty of Ethiopia, the referendum was declared “fair and free” by the UN Observer Mission.

One thing is sure: we Ethiopians should remember the Western condemnation of the Russian initiative. If, as says the West, the conduct of a referendum in a situation preventing free expression and in an independent and sovereign country is illegal, then undoubtedly the rejection of the referendum in Crimea equally questions the legality of the Eritrean secession. The flaws that make the secession of Crimea illegal are also those that disqualify the Eritrean referendum. This is not to say that Ethiopia should start a war to recover Eritrea, but that it is not compelled to accept its independence so long as it believes, now in accordance with the West, that the referendum was illegal.

Surprising as it may seem, the West is saying that the feeling of the concerned people does not matter as much as the legality of the process. Even if Crimeans in their majority want to be part of Russia, they cannot do it in violation of the national sovereignty of Ukraine. Of course, what explains the application of different criteria is that Russia is a rival superpower while Ethiopia is a poor and weak country. Everything must be done to stop the expansion of Russia. By contrast, nobody should lose sleep over the fragmentation, in direct violation of its national sovereignty, of a country as weak as Ethiopia.

Sunday, March 16, 2014

የክሬምያን ጉዳይ የተቃወመው የምዕራቡ አለም የተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ የጣሰውን የኤርትራን ''ሪፍረንደም'' ለምን በቸልታ አለፈው? የዓለም አቀፍ ሕግ እኩል መስራት አለበት።አሁንም አልረፈደም።

When UN and the west talk about Crimea, it should not also forget its negligence mistake on Eritrea referendom of 1993 against UN resolution (September 15/1952 resolution no.390-A(V) which separate from main land Ethiopia.
ክሬምያ ከዩክሬን ተነጥላ የሩስያ አካል ለመሆን ዛሬ መወሰኗን የዜና ዘገባዎች እያወጡ ነው።እንደ ዘገባዎቹ ከሆነ ዘጠና ሶስት ከመቶ የሚሆነው ሕዝብ ደግፏል።በብዛኛው የሩስያ ትውልድ ያላቸው እንደሆኑ የተነገረላቸው የግዛቲቱ ነዋሪዎች ለውሳኔው እርግጠኛ ነበሩ።

የምዕራቡ አለም በአንፃሩ ሩስያ ከወረራ ያልተናነሰ ድርጊት ፈፅማለች።ዩክሬን ነፃ ሀገር ነች።ሉዓላዊነቷ ሊደፈር አይገባም በማለት ደጋግሞ ገልጧል።ፕሬዝዳንት ኦባማም ይህንኑ በደደጋጋሚ አስተጋብተዋል።
ጉዳዩ የአለም አቀፍ ሕግን ከተለያዩ ማዕዘኖች እንዲታዩ የሚያደርግ መሆኑ አይቀርም።የአለም አቀፍ ሕግ በአለማችን ላይ የሚከወኑ ታሪካዊ ክንውኖችን (historical cases) እየአቀፈ መሄዱ የሚጠበቅ ነው።

ከእነኝህ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች አንዱ የኤርትራ ጉዳይ ነው።ከክሬምያ በበለጠ የኤርትራን ጉዳይ ውሳኔ ያሳለፈበት እና መልሶ በጠበንጃ ኃይል ለመጣው ኢ ፒ ኤል ኤፍ የተባበሩት መንግሥታት ባልታዘበበት ያንኑ ውሳኔውን በሌላ ውሳኔ ባልቀየረበት ሁኔታ ''ነፃነት ወንስ ባርነት'' ተብሎ የተጠየቀው ሕዝብ በፍርሃት ተሸብቦ ድምፅ እንዲሰጥ ሲደረግ የተባበሩት መንግሥታትም ሆነ ምዕራባውያን ወደፊት የሚመጣው የዓለም አቀፍ ሕግ ተቃርኖ ብዙም ያስታወሱት አይመስልም።ከእዚህ በፊት በክሬምያ ጉዳይ የተባበሩት መንግሥታት አልተወያየበትም፣የፀጥታው ምክርቤትም  አልመከረበትም የኤርትራን ጉዳይ ግን መክሮበት ውሳኔ አሳልፎበታል።እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር መስከረም 15/1952 ዓም በውሳኔ ቁጥር 390-A(V) ኤርትራ ከኢትዮጵያ እንዳትለይ ይልቁን በፈድሬሽን እንድትዋሃድ ወስኗል።

እዚህ ላይ ብዙዎች የሚያነሱት የኢህአዲግ/ወያኔ መንግስት በራሱ ተስማምቶ ነበር የተባበሩት መንግሥታት ምን ማድረግ ይችላል? የሚል ሃሳብ ነው።የተባበሩት መንግሥታትም ሆነ የምዕራቡ አለም ጉዳዩን ማጤን የሚገባው ከአንድ በስልጣን ላይ ካለ መንግስት ፍላጎት አንፃር ሳይሆን ከአለም አቀፍ ዘለቄታዊ ሰላም አንፃር  እና የአለም አቀፍ ውሳኔዎች ከመከበር አንፃር ብቻ መሆን ይገባው ነበር።ግን አልሆነም።ዛሬ  ክሬምያ ስትነሳ ኤርትራ ላይ የታየው ቸልተኝነት እና በሺህ የሚቆጠሩ ተወላጆች በስደት እና በመከራ እንዲማቅቁ መደረጉ አሁንም የአለም አቀፉ ሕብረተሰብ የሚጋራው ኃላፊነት እንዳለ እያስታወሰ መሆን ይገባዋል።

ኮለኔል ጎሹ ወልዴ የቀድሞው መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለአሜሪካ ምክርቤት የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ቀርበው ሰለጉዳዩ የሰጡትን ምስክርነት እና ማሳሰብይ ቪድዮው ላይ ይመልከቱ።



ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

Wednesday, March 12, 2014

በኢትዮጵያ ጉዳይ የዲያስፖራው ተሳትፎ ሲፈተሽ -''እንወያይ'' ከኢሳት ጋር ቃለ መጠይቅ

 ቪድዮውን ለመክፈት ይህንን ሊንክ ይጫኑ

click the link - ESAT Eneweyay March 11, 2014 Ethiopia | ESAT Tube

 ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

Monday, March 10, 2014

ባለፉት 22 ዓመታት የጎሳ ፖለቲካ አስከፊ ገፅታ ከታየባት ከተማ ውስጥ አንዷ ሐረር ነች።(የጉዳያችን አጭር ማስታወሻ)



ምንጭ - ጉዳያችን ጡመራ (Gudayachn Blog) http://gudayachn.blogspot.no/2014/03/22-733.html

ሐረር የብዙ ብሔረሰቦች መኖርያ ትሁን እንጂ እያስተዳደሯት ያሉት ቋንቋን ብቻ መሰረት ያደረገው የኢህአዲግ የጎሳ ድርጅት ነው።በችሎታ እና በግለሰቦች መብት ላይ ያልተመሰረተው የጎሳ ፖለቲካ ሕዝቡን ቁም ስቅል ካሳየው ሰነበተ።ድርጅቱ የክልሉን ነዋሪዎች እንደ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ያለመመልከት አዝማምያዎች ከተስተዋለበት እና በተግባር ማሳየት ከጀመረ ቆይቷል።የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በጥመቀት፣በደመራ እና በንግስ በዓላት ከሚደርስባቸው እንግልት ባሻገር በክልሉ ውስጥ ከሶስት ትውልድ በላይ የኖረውን ነዋሪ ሰርቶ የመኖር መብቱን አሳጥቶታል። ብዙዎች ወጣቶችም ሐረርን ትተው ወደሌሎች ቦታዎች ለመሰደዳቸው ምክንያት ሆኗል።ከአያት ቅድመ አያቶቻቸው ጀምረው የኖሩባትን ሐረርን ትተው የወጡ ቢናገሩት ያምራል።

የኢህአዲግ/ወያኔ የጎሳ ፖለቲካ የኢትዮጵያን ሕዝብ እርስ በርሱ ካጋጨባቸው ቦታዎች አንዱ እና ማሳያ የምትሆነው ሐረር ነች።ምናልባት በሐረር ላይ ጥናት ቢደረግ ቅድመ ኢህአዲግ እና ድህረ ኢህአዲግ የጎሳ ፖለቲካ ለሀገራችን ያመጣው ኪሳራ ከትርፉ የበለጠ መሆኑን ለማየት ያመቻል።እናም ዳጎስ ያለ ጥናት ለመስራት ያሰባችሁ ለትውልድ አስቀምጡልን። ሐረር ጥሩ ናሙና ማሳያ ነች።

ትናንት ምሽት በሐረር ከተማ የተነሳው እሳት ብዙ ሲንከባለሉ የመጡ የከተማዋን ችግሮች አሳይቷል።ዛሬ በወጡ ዘገባዎች መሰረት የሐረር ነዋሪ እሳቱን ያስነሳብን የክልሉ መንግስት ነው ይላል። ከእዚህ በፊት የክልሉ መንግስት ቦታውን እንደሚፈልገው እና ነጋዴዎቹ እንዲነሱ ጠይቆ ነበር።የእሳት አደጋ ዘግይቶ ነው የደረሰው።
ከእሳቱ የተረፈውን ነጋዴዎች እንዳያወጡ ፖሊስ ከልክሏል።ህዝቡ ዛሬ ሰኞ መጋቢት 1/2006 ዓም ተቃውሞውን ሲገልፅ ውሏል።ብዙ ሰው መታፈሱ እየተነገረ ነው።

ጉዳያችን መጋቢት 1/2006 ዓም

Sunday, March 9, 2014

ነፃነት እንፈልጋለን! የዛሬ የኢትዮጵያ ሴቶች ድምፅ በአዲስ አበባ አውራ ጎዳናዎች (ቪድዮ)

ከ እዚህ በታች የተፃፈው ፅሁፍ የተገኘው ከሰማያዊ ፓርቲ ፌስ ቡክ ገፅ ላይ ነው።እንዲህ ይነበባል -

''ለነጻነት የሮጡት ታሰሩ ዛሬ በተካሄደው የሴቶች 5ሺሜትር ሩጫ ላይ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ‹‹ለነጻነት እንሩጥ›› በሚል መሪ ቃል የተለያዩ ፖለቲካዊ ጥያቄዎችን በማንሳት ተሳታፊውን ሲያነቃቁ ውለዋል፡፡ በሩጫው ላይ ከተነሱ ጥያቄዎችና መፈክሮች መካከል ርዕዮትና ሌሎች የህሌና እስረኞች ይፈቱ፣ መብትን መጠየቅ አሸባሪነት ከሆነ አሸባሪዎች ነን፣ ውሃ ናፈቀን፣ መብራት ናፈቀን፣ ነጻነት፣ እኩልነት፣ ፍትህ፣ ዴሞክራሲ፣ ውሸት ሰለቸንና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡ ከመነሻው የጀመረው የተቃውሞ ድምጽ እስከ ማብቂያው የቀጠለ ሲሆን ሲከታተሏቸው የዋት ፖሊስና የደህንነት ኃይሎች ሩጫውን ጨርሰው ሲገቡ አስረዋቸዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የሩጫው ተሳታፊዎች ታስረው ይገኛሉ፡፡''


ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

Friday, March 7, 2014

Eritrea is inviting Russia to intervene on Horn of Africa.Two critical questions to USA and Russia before formulating their foreign policy. (GUDAYACHN BLOG's short note)



''We and the region, in our view, suffered from the absence of Russia for a quarter of century. Russia was busy with its internal issues and it went through a stage that can be considered difficult and complicated.'' Eritrean president Isayas Afewerki advisor Yemane Gebreab on February 17, 2014, the Arabic section of the RT Russian television interviewed.

Does it mean Eritrea is inviting Russia to intervene on Horn of Africa? It is a very direct statement.Yes Eritrea is calling Russia.

The regional super power nation-Ethiopia is a key and determinant nation on an over all political,Economical and social condition of the Horn.Its relative economy, over 90 million people resource and its influential power on Africa politics through Africa Union head quarter in Addis Ababa could confirm Ethiopia's capacity to be listened properly.

While on the other hand, Ethiopians have bitterly explained their tired and loose of confidence on TPLF leadership.This was disclosed to international community both in 2005 election and diasporas peace full demonstration against the current regime in Ethiopia. TPLF's  ethnic based politics could never fit for ancient and culturally coherent people of Ethiopia.After 23 difficult years, ethnic-politics is keeping to destabilised  the nation. This is quite clear and screaming fact.

The same situation with different approach of dictatorship, the people living in Eritrea are also facing the same. Thousands have flee isolated and cruel rule of Isayas Afewerqi and his regime.Last month Isayas has emphasised as if it were dream to think any opposition party on the soil of Eritrea.

Therefore the two critical questions need to be forwarded to both Russia and USA regarding their foreign policy formulation on the horn of Africa. These are -

  •  How could  Russia formulate its foreign policy to interfere on Horn of Africa through both dictators (TPLF and EPLF)? It must be noted that both of them are under full scale of lack of confidence with their own people. Quarter of century is more than enough to evaluate a state which sized power with out sharing to its opponents.
  • How far could the west specially USA is dare to ignore and give a chance to its 'modified' dictators (some years back Isayas and late-Meles were 'good boys of the west') to keep on joking and playing in the name of Democracy in 21st century? where is think-tank?



ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
March 6/2014
Oslo, Norway

Thursday, March 6, 2014

''ሁሉን ትተን ተከተልንህ'' ሐዋርያት ''ሁሉን ይዘን ተከተልንህ'' የአሜሪካ ፕሮቴስታንት ሰባክያን።

የፕሮቴስታንት ሰባክያኑ የ 20 ሚልዮን ዶላር የግል ጀት ጨምሮ የ 8 ሚልዮን ዶላር ቤት ባለቤት ናቸው።ሌሎቹ ሀብቶች ተቆጥረው አያልቁም።የገንዘባቸው  ምንጭ ደግሞ  ከቀረጥ ነፃ የሆነው የቤተ ከርስቲያን ገንዘብ ነው።ዘገባውን ተከታተሉት።''ሁሉን ትተን ተከተልንህ'' ሐዋርያት  ''ሁሉን ይዘን ተከተልንህ'' የአሜሪካ ፕሮቴስታንት ሰባክያን።



ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

Tuesday, March 4, 2014

ብሔርን ወይንም ቋንቋን መሰረት ያደረጉ የመገናኛ ብዙሃን ብዙ ዕርቀት የማይሄዱባቸው ሶስት ምክንያቶች



በሀገራችን ፖለቲካዊ፣ምጣኔ ሃብታዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ የመገናኛ ብዙሃን ከሃገር ቤት ውጭ  ይገኛሉ።እነኝህ የመገናኛ ብዙሃን የቴክኖሎጂ ዘመን ነውና ወደ ሀገር ቤት የሚደርሱባቸው በርካታ አማራጮች ሊኖራቸው ይችላል።እነኝህን የመገናኛ ብዙሃን ባብዛኛው በግልፅ የተቀመጠ ነው እና የኢድቶርያል ፖሊሲ ዓላማቸውን እና ግባቸውን መለየት ብዙም ከባድ አይደለም።

በእዚህ መሰረትም የመገናኛ ብዙሃኑን በሁለት ክፍል መክፈል ይቻላል።የመጀመርያዎቹ ብሔራዊ ኢትዮጵያዊነትን የሚያራምዱ ሲሆኑ የተቀሩት የመጡበትን ጎሳ ቋንቋ መሰረት አድርገው የተመሰረቱ ናቸው።ዛሬ ለማንሳት የምፈልገው ግን ብሔርን ወይንም ቋንቋን መሰረት ያደረጉ የመገናኛ ብዙሃን ብዙ ዕርቀት የማይሄዱባቸው ሶስቱን ምክንያቶች ነው።

ምክንያት 1
የጎሰኛነት ስሜት እንደ 'ኩፍኝ' ነው ይለቃል የሃገራዊ ስሜት ግን የተዳፈነ ፍም ነው።


በአንድ የተወሰነ ርዕዮተ አለም ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ አስተሳሰብም ሆነ በሰፈርተኝነት ላይ የተመሰረተ ሥራ የአንድ ሰሞን ግርግርታ ናቸው።የኩፍኝ በሽታ በትክክል ይመስላቸዋል።ኩፍኝ የአንድ ሰሞን በሽታ ነች።ካልታከመች አደገኛ ነች።ከታከመች ግን የትም አትደርስም።በዘመነ ደርግ ስለሶሻሊዝም ስህተት ለአንድ የቀበሌ ጥበቃ መናገር እስከሞት የሚያደርስ ፍርድ ሊያሰጥ ይችላል።በወቅቱ ገዳዩ ስለመግደሉ እርግጠኛ ነበር።ከአመታት በኃላ ኩፍኙ አልፉ ሲመለከተው ግን ስህተቱ ይታየዋል።የብሔር ስሜት እና መሰረቱ እርሱን ያደረገው ሚድያም ይሄው ነው።
ዛሬ እሞትለታለሁ ያለው የሰፈር ስሜት ነገ በኢትዮጵያዊነት እስኪማረክ ብዙ ይባልለታል።ያኩራራል።ያስደስታል።በሂደት ግን መማርያ ይሆናል።
የሃገራዊ ኢትዮጵያዊነት ስሜት ግን ጥብቅ የሆነ ማኅበራዊ፣ስሜታዊ እና ዘመናዊ እሴቶችን ይዞ ከውስጥ እየፈነቀለ ጥላቻ ላይ በረዶ ይከልስበታል።እናም ሚድያ ዘለቄታዊውን እንጂ ጎሳዊ ስሜት ይዞ መሄድ አያዋጣውም።

ምክንያት 2 

ጎሰኘነት የጎሳውን ስሜት ለመኮርኮር ይጥራል።ሃገራዊ ስሜት ግን ዓለምን ይኮረኩራል።


በጎሳ ላይ የተመሰረተ ሚድያ ሁል ጊዜ እጁም፣እግሩም መላ ሰውነቱ የጎሳውን ውሎ፣ብሶት፣ትልቅነት ወዘተ አግንኖ ለማቅረብ ይጥራል።ስራው ሁሉ የጎሳውን ስሜት ለመኮርኮር ነው።ሃገራዊ ስሜትን የሚያንፀባርቅ ሚድያ ግን አቅርቦቱ ሁሉ ሃገሩን አልፎም አካባቢውን ከፍ ሲል ደግሞ ዓለምን ይኮረኩራል።የሚነሱት ጉዳዮች የሌሎችን ሃገራት ጥቅም እና ጉዳት ስለሚመለከት ትኩረት ይስባል።እርግጥ ነው የጎሳ ጥቅም የሌሎችን የሚነካባቸው ብዙ መንገዶች ይኖራሉ።በሀገራት ደረጃ ስናየው ግን ብሔራዊ ጉዳይ ላይ ያተኮረውን ቅድምያ የሚሰጡባቸው ብዙ መንገዶች አሉ።

ምክንያት 3
ጎሰኝነት ሲነሳ ብዙ አጃቢ አለው።ሃገራዊው ስሜት ግን ከመነሻው ይልቅ እየቆዩ የሚቀላቀሉት ይበልጣሉ።


የጎሰኝነት ስሜት ይዘው የሚነሱ ሚድያዎች መነሻቸው ላይ የጎሳቸውን ስሜት በእጅጉ ይኮረኩራሉ።ለእዚህም ምክንያቶች አሉት።እነርሱም የጎሳቸውን ኩራት በእጅጉ ከፍ ያደረጉ ተደርገው በመጀመርያ ላይ ይታያሉ።እየቆየ ግን እራሱን የተለየ አድርጎ ሲያስብ የነበረው ጎሳ እራሱን ለብቻው መነጠሉ ውበቱን ሳይሆን የጎደሉትን መሰረታዊ ዘመናዊ አስተሳሰቦች እየጎሉ ሲመጡ በመጀመርያ እጁን የሚያነሳበት እና የምቃወመው ሲያከብረው ወደነበረው ''የጎሳዬ'' ወዳለው 'ጎሰኛ' ሚድያ ይሆናል።ቀድሞ ነገር የብዙሃን መገናኛ የሚለው ፅንሰ ሃሳብ ጎሳ የሌለው ለሁሉም የሚያገለግል ማለት ነው።ጎሳውን የለየ ሚድያ እንዴት ብሎ ከጊዝያዊ ስኬት ባለፈ ውጤታማ ሊሆን ይችላል?

ባጠቃላይ የጎሰኝነት ስሜቶች እና ኃይሎች አንዴ በፓርቲ መልክ ሌላ ጊዜ በሚድያ መልክ ሲፈልጉ ደግሞ በንግድ ድርጅት መልክ ቢከሰቱም መጨረሻ አሸናፊው ኢትዮጵያዊነት ነው።ይህ ፉከራ አይደለም ከላይ የተጠቀሱት ምክንያቶች ከበቂ በላይ ናቸው።አምባገነንነት፣ፋሽዝም፣ናዚዝም መሰረታቸው ርዕዮተ ዓለም አይደለም ጎሰኝነት እና የእኔ ዘር ይበልጣል ነው።መነሻቸው ላይ የናዚው ሂትለርም ሆነ የፋሺሽቱ ሞሶሎኒ  ሺዎችን በንግግራቸው አስደምመዋል፣አስፈንጥዘዋል፣ለጎሳቸው ኩራት መሰል በርካታ ቁራጥራጮች  ወርውረዋል።ነገር ግን ይህ ሁሉ ሁካታ ከአምስት አመታት በላይ አልዘለቀም የእውነት ኃይሎች ተነሱ። አሸነፉት።አሳሳቢው የእውነት ኢትዮጵያዊነት ስሜትን ያነገቡቱ ምን ያህል ፀንተው ይቆማሉ? ነው።ሁሉም ሊፀና፣ሊቆምለት እና ሊያግዝ የሚገባውም ኢትዮጵያዊነትን ያነገቡትን ሚድያዎች ነው።ይህ እስከሆነ ድረስ ኢትዮጵያዊነት አሸንፎ ይወጣል።አሁንም ተረት አይደለም።
 
ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

የካቲት 25/2006 ዓም

Monday, March 3, 2014

የኢትዮጵያ አብያተ መንግሥታት በገና ይደረደርባቸው ነበር።''እግዚአብሔርን በበገና አመስግኑት'' መዝ 150፣3 በገና ድርደራ (ቪድዮ)

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ምሳሌነት የፆመውን ታላቁን (ዓቢይ) ፆም ከጀመረች ሁለተኛ ሳምንት ሆናት።በገና በተለይ በፆም ወቅት  ይደረደራል።ህሊና ይሰበስባል።ከሥጋ አልፎ ለነፍስ ደስታ ይሰጣል።

እስከ ቅርብ ዘመን ድረስ የኢትዮጵያ ቤተ መንግስት እንዲህ የፆም ወራት ሲመጣ በገና ክፉኛ ለምዶ ነበር።ምሽት ከእራት በኃላ መሪዎቿ ለጥቂት ሰዓትም ቢሆን በገና ያስደረድሩበት ነበር።በበገና ድርደራ አጋንንት ይርቃሉ።ቅዱስ ዳዊት የሳኦልን እርኩስ መንፈስ ያሸንፍበት የነበረው በበገና ድርደራ ነበር።ይህንን ያወቁ የኢትዮጵያ መሪዎች በተለይ በአቢይ ፆም ወቅት ቤተመንግስቱን ከበገና ድርደራ ፆም አያሳድሩበትም ነበር። በገና!





ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

በኢትዮጵያ የእገታ ወንጀል ተሳታፊ አራት አካላት ናቸው። ለችግሩ የመፍትሄ አካላት ሁለት ናቸው።ሁለቱ አካላት ምን ይስሩ?

======= ጉዳያችን ======= በኢትዮጵያ ዜጎችን እያገቱ ገንዘብ የሚቀበሉ ወንጀለኞች ከተራ ወንጀለኝነት አልፎ በታጣቂ ቡድኖች የገንዘብ ማግኛነት መዋል ብቻ ሳይሆን ዜጎችን የማሸበርያ ፋሺሽታዊ ተግባር ሆኗል። እገታ የ...