ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, March 25, 2014

የቤተ ክህነቱ ችግር የቤተ መንግስቱ ችግር ሳይፈታ መፍትሄ እንደማያገኝ እነሆ ከተረጋገጠ ቆየ እኮ! በስመ ዶክመንተሪ ፊልም ሐሰት ቢከመር ቅንጣት ያክል የእውነት ጠብታ አይወጣውም። (የጉዳያችን አጭር ማስታወሻ)በቤተ ክህነቱ ገንዘብ የሚደጎም ንግድ ያላቸው ሙሰኞች እጃቸው ቤተ መንግስቱ ድረስ አለ። እስክስታ ወራጆቹ የቤተ መንግስቱ ሰዎች በቤተ ክህነቱ ገንዘብ ሲሽሞነሞኑ አመታትን አስቆጠሩ።

'ቤተ ክህነቱ አስተዳደራዊ አሰራሩ ይስተካከል' ሲባሉ በጎሳ እና በጎጥ የተደራጁት የቤተ መንግስቱ እስክስታ ወራጆች እና አስወራጆች ያስነጥሳቸዋል።ሲፈልጉ ደግሞ በቅን እና በታማኝነት ቤተ ክርስቲያንን ሊያገለግሉ የተነሱትን ሁሉ ለማሳደድ 'ሰለፊ' እያሉ ያግዋራሉ።እራሳቸው 'ሰለፊ'  ለመሆናቸው አንድ ሺ መረጃዎች በአናታቸው ላይ ተሸክመው ካለ እፍረት መሄዳቸው ሳያንስ ሌብነታቸው እና ጎጠኝነታቸው የማይታወቅ እየመሰላቸው ሕዝብን ለማጭበርበር ይታትራሉ።

ቀድሞ ነገር ኢትዮጵያ እራሷ በዘረኛ እና ሙሰኛ መሪዎች እየማቀቀች ቤተ ክህነቱስ እንዴት ብሎ ይስተካከላል? የቤተ ክህነቱ ችግር የቤተ መንግስቱ ችግር ሳይፈታ መፍትሄ እንደማያገኝ እነሆ ከተረጋገጠ ቆየ እኮ! የቤተ ክህነቱ ሌቦች ቤተ መንግስቱ ውስጥ እየተርመሰመሱ ነዋ።

በስመ 'ዶክመንተሪ ፊልም' ሐሰት ቢከመር ቅንጣት ያክል የእውነት ጠብታ አይወጣውም።ስለእዚህ መፍትሄው ግልፅ እና ግልፅ ነው።ቤተ መንግስቱ ውስጥ የገቡ እስክስታ ወራጆች እና አስወራጆች የኢትዮጵያ በሆነው ነገር ላይ ሁሉ ለሰሩት ታሪካዊ ጥፋት ለፍርድ መቅረብ አለባቸው።ከእዚህ በላይ የቃላት ጋጋታ አያስፈልገውም።የዚህን ጊዜ የቤተ ክህነቱ ጎጠኞች ይከተሏቸዋል።

ጉዳያችን
መጋቢት 16/2006 ዓም 

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...