ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, March 10, 2014

ባለፉት 22 ዓመታት የጎሳ ፖለቲካ አስከፊ ገፅታ ከታየባት ከተማ ውስጥ አንዷ ሐረር ነች።(የጉዳያችን አጭር ማስታወሻ)ምንጭ - ጉዳያችን ጡመራ (Gudayachn Blog) http://gudayachn.blogspot.no/2014/03/22-733.html

ሐረር የብዙ ብሔረሰቦች መኖርያ ትሁን እንጂ እያስተዳደሯት ያሉት ቋንቋን ብቻ መሰረት ያደረገው የኢህአዲግ የጎሳ ድርጅት ነው።በችሎታ እና በግለሰቦች መብት ላይ ያልተመሰረተው የጎሳ ፖለቲካ ሕዝቡን ቁም ስቅል ካሳየው ሰነበተ።ድርጅቱ የክልሉን ነዋሪዎች እንደ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ያለመመልከት አዝማምያዎች ከተስተዋለበት እና በተግባር ማሳየት ከጀመረ ቆይቷል።የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በጥመቀት፣በደመራ እና በንግስ በዓላት ከሚደርስባቸው እንግልት ባሻገር በክልሉ ውስጥ ከሶስት ትውልድ በላይ የኖረውን ነዋሪ ሰርቶ የመኖር መብቱን አሳጥቶታል። ብዙዎች ወጣቶችም ሐረርን ትተው ወደሌሎች ቦታዎች ለመሰደዳቸው ምክንያት ሆኗል።ከአያት ቅድመ አያቶቻቸው ጀምረው የኖሩባትን ሐረርን ትተው የወጡ ቢናገሩት ያምራል።

የኢህአዲግ/ወያኔ የጎሳ ፖለቲካ የኢትዮጵያን ሕዝብ እርስ በርሱ ካጋጨባቸው ቦታዎች አንዱ እና ማሳያ የምትሆነው ሐረር ነች።ምናልባት በሐረር ላይ ጥናት ቢደረግ ቅድመ ኢህአዲግ እና ድህረ ኢህአዲግ የጎሳ ፖለቲካ ለሀገራችን ያመጣው ኪሳራ ከትርፉ የበለጠ መሆኑን ለማየት ያመቻል።እናም ዳጎስ ያለ ጥናት ለመስራት ያሰባችሁ ለትውልድ አስቀምጡልን። ሐረር ጥሩ ናሙና ማሳያ ነች።

ትናንት ምሽት በሐረር ከተማ የተነሳው እሳት ብዙ ሲንከባለሉ የመጡ የከተማዋን ችግሮች አሳይቷል።ዛሬ በወጡ ዘገባዎች መሰረት የሐረር ነዋሪ እሳቱን ያስነሳብን የክልሉ መንግስት ነው ይላል። ከእዚህ በፊት የክልሉ መንግስት ቦታውን እንደሚፈልገው እና ነጋዴዎቹ እንዲነሱ ጠይቆ ነበር።የእሳት አደጋ ዘግይቶ ነው የደረሰው።
ከእሳቱ የተረፈውን ነጋዴዎች እንዳያወጡ ፖሊስ ከልክሏል።ህዝቡ ዛሬ ሰኞ መጋቢት 1/2006 ዓም ተቃውሞውን ሲገልፅ ውሏል።ብዙ ሰው መታፈሱ እየተነገረ ነው።

ጉዳያችን መጋቢት 1/2006 ዓም

No comments:

መንግስት ከዲፕሎማሲያዊ መፋዘዝ ይውጣ! የአረብ ሊግ በአባይ ግድብ አንጻር የወሰነውን የጸብጫሪነት ተግባር በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የምላሽ መግለጫ ብቻ የሚበቃ ሊሆን አይገባም።መንግስት ያልሰራው ግዙፍ ስራ ኢትዮጵያን ለአደጋ እንዳያጋልጣት ያሰጋል።

የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና መስሪያቤት መንግስት በፍጥነት ሊሰራቸው የሚገቡት አምስት ወሳኝ ዲፕሎማሲያዊ ተግባራት ========= ጉዳያችን አለርት ========= የአረብሊግ አንዱ የሚታወቅበት መለያው እንደባዶ ቆር...