ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, August 11, 2011

Mosvold: A Norwegian Name for Quality in Ethiopia.The company was run by Mr. Torrey Mosvold, a versatile businessman in 1940s...


Mosvold: A Norwegian Name for Quality in Ethiopia.The company was run by Mr.


 Torrey Mosvold, a versatile businessman in 1940s...

የምስጋና አና የ ወቀሳ ባህላችን


የ ምስጋና ባህላችን ገና ብዙ ይቀረዋል።ወቀሳችንም እንዲሁ:: ለ አዚህ ማሳያ  አዲስ አበባ ንግድ ሥራ ኮሌጅ ሳለሁ አንድ መምህራችን ክፍል ውስጥ ያሉን  አይረሳኝም እውነተኛ ታሪክ ስለሆነ አስተማሪም ነው።መምህሩ ከ አንግሊዝ ሀገር የ ፒአችዲ ዲግሪአቸውን አንደያዙ እኛ ክፍል መመደባቸው ነበር:: እኛም ከ ብላቴ ተመልሰን ግራ በተጋባችው አዲስ አበባችን  ውስጥ ፖለቲካ ፖለቲካ አየሸተተን ትምርት ጀመርን:: ኮሌጁ በ  በወቅቱ በሌሎች የትምህርት ዘርፎች እንጂ በ አንግሊዝኛ የ ፒአችዲ ዲግሪ ያለው   መምህር ገና  ማግኘቱ ነበር:: እናም  ግቢው ውስጥ ከተከበሩ መምህር አንዱ ክፍላችን ሲመጡ ከ ትምርታቸው ይልቅ ምክራቸው ያስደስተን ነበር:: በ ሳምንት አንድ ቀን ''አንግሊሽ ደይ'' ብለው ስለ ጥናታዊ ፅሁፍ አቀራረብ ያስተማሩን ለ ብዙዎቻችን ቀጣይ የ ዩንቨርስቲ ትምርት ላይ በሁዋላ እንድናመሰግናቸው አርጎናል::  እናም አኝህ የቀለም አባታችን  ባላቸው ጊዜ የ ህብረተሰባችንን ባህል ጥሩውን በጥሩነት፣ ማረም ያለብንን ደሞ ከ አርማቱ ጋር አየነቀሱ ያወጉን ነበር።
አንድ ቀን ታድያ ክፍል ሁላችንም  አንዳንድ አንቀፅ ፅሁፍ በወረቀት ላይ  ፅፈን ከ ተማሪው መካከል ሶስት  ተመርጠው ካነበቡ በሁዋላ በ ሶስቱ ፅሁፎች ላይ ሁላችሁም ሃሳብ እንድንሰነዝር አደረጉ። ከ ግማሽ ሰዓት በሁዋላ ሶስት ልጆች ተመርጠው አነበቡ አኛም ሃሳብ መስጠት ጀመርን። ከ አስራ አምስት በላይ ልጆች የሰጡትን ሃሳብ መዘገቡ። ሁሉም ሃሳቦች ታድያ በ ፅሁፎቹ ላይ ስህተቶችን አየነቀሰ፣አንዲህ ቢሆን ኖሮ፣ይሄ ቢስተካከል፣አዚህ ላይ ተሳስቷል፣ወዘተ የሚሉ ነበሩ።በሁአላ ዶክተሩ አንዲህ አሉን።-
            ''አዚህ ፅሁፍ ላይ ሁላችሁም ማለት ይቻላል የቀረበውን ፅሁፍ ስህተቱን ብቻ ነው ያወራችሁት። አንዴት ከ አንድ ነገር ላይ ትንሽ  ጥሩ ነገር ይጠፋዋል?አንድ የሚደነቅ ነገር ከ ሶስቱም ልጆች የለም? አያችሁ ችግሩ የ እናንተ ብቻ አደለም ያደግንበት ህብረተሰብ ነው:: በጎውን የ ማበረታታት እና  የ  ማመስገን ባህላችን እንዲሁም  ወንጀል ሲሰራም የመቃወም እና የመውቀስ ባህላችንም   በ አጅጉ ተጎድቷል። በመጀመርያ በጎውን አና ጥሩውን ጎን አውርቶ ቀጥሎ ይሄ ይስተካከል ማለት በ ሌላው ዓለም የተለመደ ነው።በተቀረው አለም አንድ ነገር ሲወቅሱ ከ በጎ ጎኑ ይጀምሩ እና መስተካከል ያለበትን ያስከትላሉ:: አኛ ግን የመጣንበት ሕብረተሰብ የ ማመስገን ባህሉ ስለተጎዳ ሁሌ ወቀሳ ለምደናል።ምሳሌ ልንገራችሁ  እናቶቻችን ጥሩ ዶሮወጥ ይሰሩ እና ለ ባላቸው  ሲያቀርቡ  'እንደነገሩ ነው የሰራሁት እስኪ የ እገሊ አባት እነሆ ይብሉ' ይላሉ።ለትህትና አልያም ቀምሶ ይፍረድ ብለው ነው አንጂ በጣም የተጠበቡበት አና የለፉበት ወጥ መሆኑን እና መጣፈጡን ያውቃሉ።የ ጠመቁትን ጠላም ይቀዱና   ቀመስ አርገው 'አስኪ ይቺን አፍዎ ላይ አርጉአት ለውሃ ጥም ብትሆን ባይጣፍጥም   ከ ውሃ ይሻላል ' ብለው ይሰጣሉ። ምግቡን የበላውም ሆነ ጠላውን የጠጣው ባል ሆየ  ግን ሲቀምሰው ቢጣፍጠውም በውስጡ 'አንዴት ይጥማል!' ብሎ ባፉ  ግን  ሚስቱንም አያመሰግንም  ዝም ብሎ መብላት ነው::በሃሳቡ ዛሬ 'ባለሙያ ካልኩዋት ነገ ደሞ ኩራትዋ አይቻልም' ብሎ ያስባል እንጂ ያበረታታል ብሎ አያስብም ።ልጆችም አናቶቻቸው ሲመሰገኑ ሲሞገሱ አላዩም ፣እራሳቸው ልጆቹም አየተመሰገኑ ስላላደጉ ሌላውን ለማመስገን ለማድነቅ አና ለማበረታታት የሚይዘን የ ባህል ችግር ተጎጂዎች ይሆናሉ።ካሁን ካሁን ያደንቃል ብላ ስጠብቅ የነበረች ሚስትም ሳይደነቅላት ሲቀር እርሱ ልማዱ ነው::  ጥሩ አርጌ ብሰራው ባልሰራው! አያለች ታስባለች።ባልም አንዲሁ ነው ዛሬ ሚስቴን ላስደስታት ብሎ የማትወደውን ነገር ትቶ፣በ ጊዜ እቤቱ ገብቶ ጥሩ አባት ሲሆን፣ አልፎም ለ ሚስቱ የምትወደውን እቃ ገዝቶ ሲመጣ ውስጧ እያወቀ አና እየተደሰተች በ አንደበት ግን ብዙም ትኩረት እንዳልሰጠች መስላ መቅረብ በ ህብረተሰባችን እንደ ባህል ተለምዷል። እኛ ዛሬ ብናመሰግን ለነገ ይኩራራል ወይም ትኩራራለች ብለን እናስባለን።በተቃራኒው ግን ነገ ለ በለጠ ሥራ አንዳይተጋ እያረግነው መሆኑን ልብ አንልም።  አሁን ከ እነኝህ ፅሁፎች ውስጥ አንድ ጥሩ ነገር አውጥቶ ከመናገር ይልቅ በሙሉ አስተያየቶቻችሁ ሁሉ ካለ አንዳች ምስጋና ትችቶች ብቻ የሆኑት ለ አዚህ ነው'' ብለው ያወጉን አስካሁን አይምሮዬ ላይ አለች። አሁን አሁን ሳስበው ያኔ ዶክተሩ አለብን ያሉን ችግር  በ ሥራ ቦታ፣በ ፖለቲካ፣ማህበራዊ፣ባህላዊ አና ሃይማኖታዊ ተቁአሞቻችን እየተንሰራፋ መሆኑ ይታየኛል። አኔ ደሞ የምለው የማመስገን ባህላችን ብቻ ሳይሆን ስህተት እየሰራ፣እየሰረቀ፣እየዋሸ ፣ፀሐይ የሞቀውን ማታለል አየፈፀመ   ያለውን ሁሉ ለመውቀስ አና 'አካፋን አካፋ' የማለት ባህላችን ሁሉ በ አጅጉ ተጎድቷል።ይሄው ባህላችንም በ አየ ተቁአሞቻችን ውስጥ ተንሰራፍቶ እንዳላዩ የማየት አባዜ ተጠናውቶናል። በ ቤተ አምነቱ ውስጥ የሚሰራውን ግፍ እና ሸፍጥ ቤተ አምነቱ ውስጥ ያለው እያየ እንዳላየ ያልፈዋል።ከ ውጭ ያለውም አማኙም ሆነ ግድግዳ ላይ እንደተለጠፈ ወረቀት እያየ ያለው ወቃሽ ከሳሽ እንዳላይ ያለው መንግስትም ምንም እንዳልተፈፀመ ይመለከታል። የማመስገን ባህላችን ብቻ ሳይሆን የመውቀስ ባህላችንም፣አውነቱን የመናገር እና ለማስተካከል ቆርጦ የመነሳት ባህላችንም ተጎድቷል።ጥቂቶች ተናግረውልን መስዋእት ተቀብለው እንዲያልፉ እና የድል አጥቢያ አርበኛ መሆን ደስታችን ነው:: ከባህላዊ እሰቶቻችን አኩዋያ በደንብ መፈተሽ እና ቀድሞ የነበሩንን በጎዎቹን መያዝ ብሎም ማጎልበት ይገባናል:: በ ልማድ እያሳደግናቸው የቆዩ እንዳይሆኑ እና በሁዋላ በባሰ ደረጃ ሃገራዊም ሆነ ተቁዋማዊ ጉዳት እንዳያስከትሉ ማሰብ እና ያለብንን የመውቀስ ባህል እንደማመስገኑ ሁሉ ማረሙ ተገቢ ነው። ይህ የመውቀስ ባህላችን ግን ካለ አንዳች ይሉኝታ  አንድ ቦታ መቆም አለበት።''ችግርን ማወቅ በራሱ የመፍትሄ ግማሽ መንገድ ነው'' አንዲሉ ::
ኦስሎ
ጌታቸው

በኢትዮጵያ የእገታ ወንጀል ተሳታፊ አራት አካላት ናቸው። ለችግሩ የመፍትሄ አካላት ሁለት ናቸው።ሁለቱ አካላት ምን ይስሩ?

======= ጉዳያችን ======= በኢትዮጵያ ዜጎችን እያገቱ ገንዘብ የሚቀበሉ ወንጀለኞች ከተራ ወንጀለኝነት አልፎ በታጣቂ ቡድኖች የገንዘብ ማግኛነት መዋል ብቻ ሳይሆን ዜጎችን የማሸበርያ ፋሺሽታዊ ተግባር ሆኗል። እገታ የ...