ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, February 28, 2022

የዩክሬን ጉዳይ ለምን የምዕራቡ ዓለም ግልጥ ጥፋት ውጤት ሆነ? በሚል የዛሬ 7 ዓመት በቺካጎ ዩንቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር ጆን ማርሽመር የሰጡት ድንቅ ሌክቸር Why is Ukraine the West's Fault? watch the Prof.John Mearsheimer lecture on Ukraine in 2015.

On September 25, 2015, the University of Chicago released the tremendous lecture video of Prof.John J. Mearsheimer. Professor John J. Mearsheimer is a professor in Political Science and Co-director of the International Security Policy at the University of Chicago. 

This video is visited by over 11 million viewers.

የዩክሬን ጉዳይ ለምን የምዕራቡ ዓለም ግልጥ ጥፋት ውጤት ሆነ? በሚል የዛሬ 7 ዓመት በቺካጎ ዩንቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር ጆን ማርሽመር  የሰጡት ድንቅ ሌክቸር ይመልከቱ። ቪድዮውን ከ11 ሚልዮን በላይ ተመልካች ተመልክቶታል።የወቅቱ የዩክሬን ጉዳይ ከስሩ ያብራራል።ተያያዥ የጂኦፖለቲካ ጉዳዮች ያብራራል።



Monday, February 21, 2022

ዛሬ በኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተመረጡት የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች እነማን ናቸው?

•••••••••••••

ጉዳያችን / Gudayachn

•••••••••••••••••
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማህበረሰቡ ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዕጩ ኮሚሽነሮችን እንዲጠቁም በማድረግ ከ600 በላይ ዕጩ ኮሚሽነሮች መጠቆማቸውን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ከእነዚህ ውስጥም ምክር ቤቱ ለኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዕጩ ኮሚሽነር ይሆናሉ ያላቸውን 42 ግለሰቦች ህብረተሰቡ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ዝርዝራቸውን ይፋ ማድረጉም ይታወቃል፡፡

ምክር ቤቱ ከማህበረሰቡ የተገኘውን ግብዓት መሰረት በማድርግ መስፈርቱን በከፍተኛ ደረጃ አሟልተዋል ያላቸውን 11 ኮሚሽነሮች ሾሟል።

እነርሱም፦

1.መስፍን አርዓያ ፡

የትምህርት ደረጃ፡ ፒ ኤች ዲ በአእምሮ ህክምና

የስራ ልምድ ፡ በአእምሮ ህክምና ዘርፍ ከ30 አመታት በላይ ያገለገሉ፣ ከ30 በላይ ጥናታዊ ጽሁፎችን ያሳተሙ፣ ብሄራዊ የኤች አይ ቪ ሴክሬታሪያት እንዲቋቋም ከፍተኛ ጥረት ያደረጉ፣ በተለያዩ የሀገራችን ከፍሎች በመዘዋወር ሆስፒታሎችን የመሩ፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና በአማኑኤል ሆስፒታሎች በኃላፊነት ያገለገሉ፣ በተለያዩ ሀገራዊ የሰላም መድረኮች በሚያቀርቧቸው አስተማሪና መካሪ ሀሳቦች በመነሳት ለሀገራዊ መግባባት እየሰሩ ያሉ፡፡

2. ወይዘሮ ሂሩት ገብረስላሴ ፡

የትምህርት ደረጃ: በህግ ማስተርስ ዲግሪ ያላቸው
የስራ ልምድ፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ልዩ መልእክተኛ ሆነው ያገለገሉ፤ የተለያዩ መንግስታዊ ያልሆኑ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ የሰሩ

3. ዶክተር ተገኘወርቅ ጌቱ

የትምህርት ደረጃ: ፒ ኤች ዲ እና ሁለት ማስተርስ በኢኮኖሚክስና ፖለቲካ
የስራ ልምድ፡ በተመድ ልማት ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ሆነው ያገለገሉ፤ በሀገራት የልማት ፕሮግራሞች የመሩ፤ በርካታ ፅሁፎችን ያበረከቱ፤ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ያስተማሩ፤ የልማት ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ያገለገሉ፤ ግጭቶችን ለመፍታት አለም አቀፍ ተሞክሮ ያላቸው፤የተመሰከረ የአመራርና የአስተዳደር ክህሎት ያላቸው

4. አምባሳደር ዶክተር አይሮሪት መሃመድ

የትምህርት ደረጃ: ፒ ኤች ዲ በህግ የስራ ልምድ፡አምባሳደር ሆነው ያገለገሉ፤ በተለያየ የሀላፊነት ቦታ የሰሩ

5. ወይዘሮ ብሌን ገብረመድህን

የትምህርት ደረጃ: ማስተርስ ዲግሪ

የስራ ልምድ፡የህግ መምህር የነበሩ፤ ያለም አቀፍ ልማት ማዕከል ቢሮ ሀላፊ የነበሩ፤ በቀይ መስቀል ማህበር ውስጥ በአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ በህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ሆነው የሰሩ፤ በሰብአዊ መብት ኮሚሽን እያገለገሉ ያሉ፤

6. ዶክተር ዮናስ አዳዬ

የትምህርት ደረጃ: ፒኤችዲየስራ ልምድ፡ ተመራማሪ እና አሰልጣኝ

7. አቶ ዘገየ አስፋው

የትምህርት ደረጃ: በህግ የማስተርስ ዲግሪ
የስራ ልምድ: ላለፉት 40 አመታት ለሀገራቸውና ለህዝባቸው የሚችሉትን ሁሉ አገልግሎት የሰጡ

8. አቶ መላኩ ወልደማሪያም

የትምህርት ደረጃ: በህግ የመጀመርያ ድግሪ
የስራ ልምድ፡ ጠበቃና የህግ አማካሪ፣ በህዝባዊ ተቋማት በርካታ ሁኔታ አገልግሎት የሰጡ፣ በሽግግር መንግሰት ምክር ቤት በህግ አማካሪነት፤ በመንግስት ምክር ቤት በህግ ባለሙያነት፤ በኢትዮጵያ ሠብዓዊ መብት ጉባኤ (ኢሠመጉ) ዋና ፀሀፊነት፤ በልማት ማህበራት በአመራርነት የሰሩ፡፡

9. አምባሳደር መሃሙድ ድሪር

የትምህርት ደረጃ : በህግ የማስተርስ ድግሪ
የስራ ልምድ፡በምክር ቤት አባልነት፤ በአምባሳደርነት፤ በሚንስትርነት፤ በከፍተኛ አማካሪነት፤ በኢጋድ አስተባባሪነት፤ በሱዳን ልዩ መልእክተኝነትና በአፍሪካ ቀንድ ሰፊ ልምድና እውቀት ያላቸው።

10. አቶ ሙሉጌታ አጎ

የትምህርት ደረጃ፡ በህግ የማስተርስ ዲግሪ
የሥራ ልምድ፡ ለ 4 ዓመታት በከፋ ዞን የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ እና ፕሬዚዳንት፣ በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ ጠ/ፍ/ቤት ዋና ሬጅስትራርነት ለአንድ ዓመት የሰሩ፣ በዳኝነት ለሰባት ዓመት የሰሩ፣ በም/ ፕሬዚዳትነት ለሁለት ዓመትና በፕሬዚዳንትነት ለ8 ዓመታት ያገለገሉ

11. ዶክተር አምባዬ ኦጋቶ

የትምርት ደረጃ: በሶሻል አንትሮፖሎጂ ፒኤችዲ
የስራ ልምድ፡ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች በመምህርነት እና በአሁኑ ሰዓት በሰላምና ዲያሎግ ከፍተኛ አማካሪነት እያገለገሉ ያሉ ፤ በማክስ ፕላንክ የስነ ህዝብ ጥናት ተቋም ያገለገሉ እና በዚሁ ተቋም የማህበራዊ አንትሮፖሎጂ ተቋም በግጭትና ውህደት ክፍል ውስጥ የድህረ ዶክትሬት ጥናት አድርገዋል::

ምንጭ - ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን

Saturday, February 19, 2022

ጉዳያችን ከኢትዮጵያ ማኅበረሰብ (ኮሚኒቲ) በኖርዌይ ጋር በተባበር በኦስሎ የተዘጋጀው የዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ የኪነጥበብ ዝግጅት

------------------------
ጉዳያችን / Gudayachn
===============
ዛሬ የካቲት 12/2014 ዓም ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ በተገኙበት ልዩ የኪነጥበብ ዝግጅት ቀርቧል።በዝግጅቱ ላይ ዶ/ር በድሉ ከእዚህ በፊት ካሳተሟቸው መጻሕፍት ውስጥ የተመረጡ ግጥሞችን ያቀረቡ ሲሆን በዝግጅቱ ላይ ሌሎች የኪነጥበብ ዝግጅቶች ቀርበዋል።ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ መምህር፣በልዩ ልዩ የኪነጥበብ ዝግጅቶች ሞጋች የሆነ ሃገራዊ ጽሁፎችን ከማቅረባቸው እና አነቃቂ ንግግር በማድረግ ከመታወቃቸው በላይ እነኝህን ሃሳቦች በመጻህፍ አሳትመዋቸዋል።ዶ/ር በድሉ በቅርቡ በኢትዮጵያ በሚመሰረተው የውይይት እና እርቅ ኮሚሽን ዕጩዎች ውስጥ 40ዎቹ ውስጥ ገብተዋል።

በዛሬው ጉዳያችን ከኢትዮጵያ ማኅበረሰብ (ኮሚኒቲ) ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ዝግጅት ልዩ እንግዳ ሆነው የተገኙት ዶ/ር በድሉ ከእዚህ በፊት ከፍተኛ ትምህርታቸውን በተከታተሉባት ኖርዌይ መገኘታቸው ያስደሰታቸው መሆኑን ገልጠው በኪነ ጥበቡ ዙርያ የነበራቸውን ገጠመኝ እና ከተሳታፊዎች የተነሱላቸው በተለይ ወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች አስመልክተው የግል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። በእዚሁ ዝግጅት ላይ የሚከተሉት ሌሎች ዝግጅቶችም ለዕይታ ቀርበው ታዳሚው በእጅጉ ተምሮባቸዋል።ከዶ/ር በድሉ ዝግጅቶች በተጨማሪ የሚከተሉት ዝግጅቶች ቀርበዋል። እነርሱም 
  • ''አድዋን ከዓይናችን ፊት ፋቁት '' በሚል ርዕስ በዶ/ር በድሉ ተደርሶ በአርቲስት አበራ የቀረበው ተውኔት በቪድዮ ታይቷል።
  • የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ (ኮምዩኒቲ) እንኳን ደህና መጡ አቀባበል በኮሚኒቲው ሰብሳቢ አቶ ልዑል ለዶ/ር በድሉ የአበባ ስጦታ ተሰጥቷል።
  • የመርሓግብሩ አስተናባሪ አቶ ዳዊት ስለ ዶ/ር በድሉ በአጭሩ የስራ እና የትምህርት ሁኔታ በአጭሩ አቅርቧል።
  • ዶ/ር በድሉ ካሳተሟቸው የግጥም መጻሕፍት የተመረጡ ግጥሞች ለታዳሚው አቅርበዋል።
  • ወ/ሮ አዲስ ግጥሞች አቅርባለች።
  • አርቲስት እንዳለ የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህንን ''ጴጥሮስ ያችን ሰዓት '' የሚለውን ግጥም በቃሉ አቅርቧል።
  • ድምጻዊት ጽናት አንድ ዜማ አቅርባለች (የድምጻዊ ጽናት ዜማ ከስር ቪድዮ ይመልከቱ)
  • በኖርዌይ ነዋሪ የሆነው ''የአምስት ጉዳይ'' መጽሃፍ ደራሲ ያሬድ ዶ/ር በድሉ ጋር በሃገርቤት የነበረውን ትዝታ እና ግጥም አቅርቧል።
  • ''ህዝብ እና መንግስት እየተሰዳደቡ አረቄ ይጠጣሉ'' በሚል ርዕስ አጭር ተውኔት በአርቲስት አበራ በቪድዮ ታይቷል።
  • በመጨረሻም ከተሳታፊዎች በወቅታዊ ሁኔታ እና በእርቅ ኮሚሽን ጉዳይ ዙርያ ጥያቂዎች ተነስተው ሃሳብ ተሰጥቶባቸዋል።
ከእዚህ በታች ድምጻዊት ጽናት በዝግጅቱ ላይ ያቀረበችው ዜማ እና ከ50 በላይ የሚሆኑ በዝግጅቱ ላይ የነበሩ በጉዳያችን የተነሱ ፎቶዎች ያገኛሉ።


ድምጻዊት ጽናት 







































































የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...