ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, February 7, 2022

ህወሓት፣በቅዱስ ሲኖዶስ ስር ሆነው ትግራይ ለሚገኙ ጳጳሳት ከቅዱስ ሲኖዶስ እንዲለዩ ትዕዛዝ ሰጥቷቸዋል።ዓላማው የትግራይ ገዳማትን ለግብጽ ለማስረከብም ያለመም ነው።

 
ህወሃት ጳጳሳትን ሰብስቦ ትዕዛዝ ሲያስተላልፍ። ጳጳሳት ከፖለቲካ መሪዎች መመርያ ሲቀበሉ (ትግራይ)

👉የትግራይ ካህናት ሃይማኖት ወይንስ ህወሃት? ወሳኝ የነፍስ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል።
👉የትግራይ ገዳማት እና አድባራት ሃይማኖታቸውን እንደሚመርጡ የኢትዮጵያ ህዝብ ያምናል።
👉ሃይማኖት በፖለቲካ ሸቀጥ ውስጥ እንደማትውል የትግራይ ካህናት የተማሩት ከህወሃት አይደለም።ከጥንታዊቷ ሃይማኖታቸው ነው። አሁን ህወሃት በነፍስ ጉዳይ ላይ መጥቷል።
👉የትግራይ ካህናት ህወሃትን ፖለቲካህን ወደ ሃይማኖታችን አታስገባ ሊሉት ይገባል።

===================
ጉዳያችን/Gudayachn
===================

የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ከቤተክርስቲያን ላይ እንዲያወርዱ ያዘዘው ህወሃት፣በቅዱስ ሲኖዶስ ስር ሆኖ ትግራይ ለሚገኘው ቤተ ክህነት ከኢትዮጵያ እንዲገነጠል ትዕዛዝ ሰጥቷል።ሽብርተኛው ህወሃት ቀድሞም በጠላትነት የፈረጃትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ለ27 ዓመታት ያህል ቅዱስ ሲኖዶስን ለሁለት ከፍሎ፣በጎሳ ፖለቲካ በርዞ እና በሙስና አምሶ ወደ መቀሌ ከሄደ በኋላ አሁን የመጨረሻ ካርዱን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ መዟል። ይሄውም ትግራይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከቅዱስ ሲኖዶስ እንዲለይ ትግራይ የሚገኙ ጳጳሳት እና ጥቂት ካህናትን ጠርቶ ዶ/ር ደብረጽዮን እና አለቃ ጸጋዬ በተገኙበት ባሳለፍነው ሳምንት ውስጥ የህወሃትን ውሳኔ ገልጠውላቸዋል።

ይህ ብዙ ትንተና የሚፈልግ አይደለም።ድርጊቱ በራሱ ገላጭ ነው። የስብሰባው ጠሪ ህወሃት ነው።በስመ ምክክር ተደርጎ ተወሰነ ይባል እንጂ ውሳኔውን ነው ያሳወቃቸው።በውሳኔው ላይ አብረው የሰሩ ካህናት የሉም ማለት አይቻል ይሆናል።የትግራይ አድባራት እና ገዳማት በነጻነት የወሰኑት ውሳኔ ነው ወይ? ብሎ ለመደምደም እንደማይቻል ግን ግልጥ ነው።የእዚህ ዓይነቱን የትግራይ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የመመስረት ሃሳብ አመንጪው ህወሃት እና በስሩ ያሉ በውጭ ያለው መዋቅሩ ነው። በእዚህ ስራ ላይ ውስጥ ውስጡን ሲሰሩ እና በአውሮፓ እና አሜሪካም ተመሳሳይ የመገንጠል ስራ ሲያሴሩ ነበር። ሆኖም ግን አብዛኛው የትግራይ ህዝብ እንደጠበቁት ከተንኮላቸው ጋር አብሮ አልሄደላቸውም። ጉዳዩ በሙስና፣በዘረኝነት እና በወንጀል ውስጥ ያሉት የሚያመላልሱት የውስጥ ጉዳይ ሆኖ ሰንብቷል።

ህወሃት በቀጥታ ለባዕዳን ያደረ እና ኢትዮጵያን ለማፍረስ ዕቅድ ያለው፣የማፍረስ ስራውንም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለመጀመር ሲሰራ መኖሩ የአደባባይ ምስጢር ነው። ይህንን የትግራይ ካህናት ጠንቅቀው ያውቃሉ።ሃይማኖት በፖለቲካ ሸቀጥ ውስጥ እንደማትውል የትግራይ ካህናት የተማሩት ከህወሃት አይደለም። አሁን ህወሃት በነፍስ ጉዳይ ላይ መጥቷል።የትግራይ ካህናት ህወሃትን ፖለቲካህን ወደ ሃይማኖታችን አታስገባ ሊሉት ይገባል።

ኢትዮጵያ ከ3 ሺህ ዓመታት በላይ ስትኖር የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ እያለፈች ነው።ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ በ34 ዓም ከገባ በኋላ እስከ ዘመነ መሳፍንት የእርስ በርስ ጦርነቶች ጊዜ ሁሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እንደ ተቋም እና አገልጋይ ካህናቶቿ እንዴት የዘመኑን ፈተና እንዳለፉት ያውቃሉ።መኳንንቱ ሲዋጉ የአብነት ተማሪዎች (በተለምዶ የቆሎ ተማሪ የሚባሉት) ከትግራይ ሸዋ፣ከሽዋ ጎንደር እና ሌሎች ቦታዎች ሁሉ እየሄዱ ካለምንም የዘር ልዩነት አንድነታቸውን ጠብቀው በኋላም የኢትዮጵያን አንድነት አስጠብቀው ኖረዋል።በእዚህ ዓይነት የተማሩት ናቸው በኋላ የቤተክርስቲያኒቱ ጳጳሳት፣ኢጲስቆጶሳት፣ቀሳውስት እና ዲያቆናት ሆነው ህዝቡን በእምነቱ አጽንተው ለምድራዊ የእርስ በርስ ጦርነት ሳይሆን ለነፍስ የጽድቅ እና ኩነኔ ጉዳይ ትኩረት ሰጥተው ያሻገሩት። ዛሬም ከስር ያሉት ካህናት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ጥለው በመሄድ ጽድቅ እንደሌለ ማንም ነጋሪ አይፈልጉም።ሃይማኖቱ በራሱ አስተማሪ ነው።ሆኖም ግን ህወሃት ከ30 ዓመታት በላይ በቤተክርስቲያኒቱ ላይ የሾማቸው የፖለቲካ ሹመኞች በክህነት ስም ህዝቡን ለመለያየት ሊያስገድዱት ይሞክራሉ። በሙከራቸው ሁሉ ግን ከእግዚአብሄር ተጣልተው እራሳቸውን መጋጨት ከሌለባቸው የማዕዘን ራስ ከተባለ ከክርስቶስ ጋር ይጋጫሉ እንጂ አንዳች አያተርፉበትም። 

ህወሃት ተስፋ ቆርጧል።ተስፋ በመቁረጡም ነው የመጨረሻ ያለውን የሃይማኖት ካርድ የመዘዘው።በእዚህም እመራዋለሁ የሚለውን የትግራይን ህዝብ እንደማያውቀው በድጋሚ ተጋልጧል።የትግራይ ጠቅላይ ቤተክህነት ይመስረት የሚለው የህወሃት ትዕዛዝ ህወሃት ለግብጽ የትግራይን ገዳማት ለመሽጥ ከገባው ፕሮጀክት ውስጥ የሚካተት ነው።የትግራይ ህዝብ በቶሎ ነቅቶ ሁኔታዎች እንዲስተካከሉ ካላደረገ ህወሃት የአክሱም ጽዮን ላይ የያዛቸው ድብቅ ፕሮጀክቶች ለባዕዳን አሰጥቶ በምትኩ ዓለም አቀፍ ድጋፍ የማግኘት ዕቅድ ሁሉ ያካተተ መሆኑ እየተነገረ ነው።ይህንን ደግሞ እምነት የለሹ ህወሃት ከእዚህ የበለጠ እንጂ ያነሰ እንደማያቅድ ግልጥ ነው።ጠቅላይ ቤተክህነት ብሎ ጥቂት ከሄደ በኋላ፣ ጳጳስ በግብጽ ለማሾም እና ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ድርጎ ሊቀበል ያለመ ነው። ይህንን የህወሃት ካድሬ ካህናትን ትተን የትግራይ ገዳማት እና አድባራት ይቀበሉታል ወይ? ተገደው አስፈጻሚ የሚሆኑ እና አልፈጽምም የሚሉ የሚደርስባቸው ቅጣት እንደሚኖር ይታወቃል።ሆኖም ቅዱስ መጽሃፍ የሚያስተምረን  ''ሥጋን የሚገድሉትን አትፍሩ።ይልቁንም ሥጋንም ነፍስንም በገሃነም የማጥፋት ስልጣን ያለውን ፍሩ'' ነው እና ህወሃትን በእዚህ ጊዜ የማይቃወም እና በሃይማኖት ጉዳይ አትግባ! የማይል ሃይማኖተኛ ነኝ ለማለት አይችልም።
==============////===========
  

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...