ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, February 21, 2022

ዛሬ በኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተመረጡት የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች እነማን ናቸው?

•••••••••••••

ጉዳያችን / Gudayachn

•••••••••••••••••
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማህበረሰቡ ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዕጩ ኮሚሽነሮችን እንዲጠቁም በማድረግ ከ600 በላይ ዕጩ ኮሚሽነሮች መጠቆማቸውን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ከእነዚህ ውስጥም ምክር ቤቱ ለኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዕጩ ኮሚሽነር ይሆናሉ ያላቸውን 42 ግለሰቦች ህብረተሰቡ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ዝርዝራቸውን ይፋ ማድረጉም ይታወቃል፡፡

ምክር ቤቱ ከማህበረሰቡ የተገኘውን ግብዓት መሰረት በማድርግ መስፈርቱን በከፍተኛ ደረጃ አሟልተዋል ያላቸውን 11 ኮሚሽነሮች ሾሟል።

እነርሱም፦

1.መስፍን አርዓያ ፡

የትምህርት ደረጃ፡ ፒ ኤች ዲ በአእምሮ ህክምና

የስራ ልምድ ፡ በአእምሮ ህክምና ዘርፍ ከ30 አመታት በላይ ያገለገሉ፣ ከ30 በላይ ጥናታዊ ጽሁፎችን ያሳተሙ፣ ብሄራዊ የኤች አይ ቪ ሴክሬታሪያት እንዲቋቋም ከፍተኛ ጥረት ያደረጉ፣ በተለያዩ የሀገራችን ከፍሎች በመዘዋወር ሆስፒታሎችን የመሩ፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና በአማኑኤል ሆስፒታሎች በኃላፊነት ያገለገሉ፣ በተለያዩ ሀገራዊ የሰላም መድረኮች በሚያቀርቧቸው አስተማሪና መካሪ ሀሳቦች በመነሳት ለሀገራዊ መግባባት እየሰሩ ያሉ፡፡

2. ወይዘሮ ሂሩት ገብረስላሴ ፡

የትምህርት ደረጃ: በህግ ማስተርስ ዲግሪ ያላቸው
የስራ ልምድ፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ልዩ መልእክተኛ ሆነው ያገለገሉ፤ የተለያዩ መንግስታዊ ያልሆኑ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ የሰሩ

3. ዶክተር ተገኘወርቅ ጌቱ

የትምህርት ደረጃ: ፒ ኤች ዲ እና ሁለት ማስተርስ በኢኮኖሚክስና ፖለቲካ
የስራ ልምድ፡ በተመድ ልማት ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ሆነው ያገለገሉ፤ በሀገራት የልማት ፕሮግራሞች የመሩ፤ በርካታ ፅሁፎችን ያበረከቱ፤ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ያስተማሩ፤ የልማት ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ያገለገሉ፤ ግጭቶችን ለመፍታት አለም አቀፍ ተሞክሮ ያላቸው፤የተመሰከረ የአመራርና የአስተዳደር ክህሎት ያላቸው

4. አምባሳደር ዶክተር አይሮሪት መሃመድ

የትምህርት ደረጃ: ፒ ኤች ዲ በህግ የስራ ልምድ፡አምባሳደር ሆነው ያገለገሉ፤ በተለያየ የሀላፊነት ቦታ የሰሩ

5. ወይዘሮ ብሌን ገብረመድህን

የትምህርት ደረጃ: ማስተርስ ዲግሪ

የስራ ልምድ፡የህግ መምህር የነበሩ፤ ያለም አቀፍ ልማት ማዕከል ቢሮ ሀላፊ የነበሩ፤ በቀይ መስቀል ማህበር ውስጥ በአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ በህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ሆነው የሰሩ፤ በሰብአዊ መብት ኮሚሽን እያገለገሉ ያሉ፤

6. ዶክተር ዮናስ አዳዬ

የትምህርት ደረጃ: ፒኤችዲየስራ ልምድ፡ ተመራማሪ እና አሰልጣኝ

7. አቶ ዘገየ አስፋው

የትምህርት ደረጃ: በህግ የማስተርስ ዲግሪ
የስራ ልምድ: ላለፉት 40 አመታት ለሀገራቸውና ለህዝባቸው የሚችሉትን ሁሉ አገልግሎት የሰጡ

8. አቶ መላኩ ወልደማሪያም

የትምህርት ደረጃ: በህግ የመጀመርያ ድግሪ
የስራ ልምድ፡ ጠበቃና የህግ አማካሪ፣ በህዝባዊ ተቋማት በርካታ ሁኔታ አገልግሎት የሰጡ፣ በሽግግር መንግሰት ምክር ቤት በህግ አማካሪነት፤ በመንግስት ምክር ቤት በህግ ባለሙያነት፤ በኢትዮጵያ ሠብዓዊ መብት ጉባኤ (ኢሠመጉ) ዋና ፀሀፊነት፤ በልማት ማህበራት በአመራርነት የሰሩ፡፡

9. አምባሳደር መሃሙድ ድሪር

የትምህርት ደረጃ : በህግ የማስተርስ ድግሪ
የስራ ልምድ፡በምክር ቤት አባልነት፤ በአምባሳደርነት፤ በሚንስትርነት፤ በከፍተኛ አማካሪነት፤ በኢጋድ አስተባባሪነት፤ በሱዳን ልዩ መልእክተኝነትና በአፍሪካ ቀንድ ሰፊ ልምድና እውቀት ያላቸው።

10. አቶ ሙሉጌታ አጎ

የትምህርት ደረጃ፡ በህግ የማስተርስ ዲግሪ
የሥራ ልምድ፡ ለ 4 ዓመታት በከፋ ዞን የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ እና ፕሬዚዳንት፣ በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ ጠ/ፍ/ቤት ዋና ሬጅስትራርነት ለአንድ ዓመት የሰሩ፣ በዳኝነት ለሰባት ዓመት የሰሩ፣ በም/ ፕሬዚዳትነት ለሁለት ዓመትና በፕሬዚዳንትነት ለ8 ዓመታት ያገለገሉ

11. ዶክተር አምባዬ ኦጋቶ

የትምርት ደረጃ: በሶሻል አንትሮፖሎጂ ፒኤችዲ
የስራ ልምድ፡ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች በመምህርነት እና በአሁኑ ሰዓት በሰላምና ዲያሎግ ከፍተኛ አማካሪነት እያገለገሉ ያሉ ፤ በማክስ ፕላንክ የስነ ህዝብ ጥናት ተቋም ያገለገሉ እና በዚሁ ተቋም የማህበራዊ አንትሮፖሎጂ ተቋም በግጭትና ውህደት ክፍል ውስጥ የድህረ ዶክትሬት ጥናት አድርገዋል::

ምንጭ - ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን

No comments:

ኢትዮጵያ በዘመናዊ ታሪኳ ታላቅ ተልዕኮ የሚኖረው ሀገራዊ የምምክር ኮሚሽን በተመለከተ ምን ያህል እናውቃለን?

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ኮሚሽን አማካሪ ኮሚቴ አባላትን ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል ባካተተ መልኩ አዋቅሯል። በእዚህ ጽሑፍ ስር የሚከተሉት ነጥቦች ምላሽ ያገኛሉ፡  ኮሚሽኑ እንዴት ተመሰረተ?  የኮሚሽኑ 11 ኮሚሽነሮች እንዴት ተመ...