------------------------
ጉዳያችን / Gudayachn
===============
ዛሬ የካቲት 12/2014 ዓም ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ በተገኙበት ልዩ የኪነጥበብ ዝግጅት ቀርቧል።በዝግጅቱ ላይ ዶ/ር በድሉ ከእዚህ በፊት ካሳተሟቸው መጻሕፍት ውስጥ የተመረጡ ግጥሞችን ያቀረቡ ሲሆን በዝግጅቱ ላይ ሌሎች የኪነጥበብ ዝግጅቶች ቀርበዋል።ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ መምህር፣በልዩ ልዩ የኪነጥበብ ዝግጅቶች ሞጋች የሆነ ሃገራዊ ጽሁፎችን ከማቅረባቸው እና አነቃቂ ንግግር በማድረግ ከመታወቃቸው በላይ እነኝህን ሃሳቦች በመጻህፍ አሳትመዋቸዋል።ዶ/ር በድሉ በቅርቡ በኢትዮጵያ በሚመሰረተው የውይይት እና እርቅ ኮሚሽን ዕጩዎች ውስጥ 40ዎቹ ውስጥ ገብተዋል።
በዛሬው ጉዳያችን ከኢትዮጵያ ማኅበረሰብ (ኮሚኒቲ) ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ዝግጅት ልዩ እንግዳ ሆነው የተገኙት ዶ/ር በድሉ ከእዚህ በፊት ከፍተኛ ትምህርታቸውን በተከታተሉባት ኖርዌይ መገኘታቸው ያስደሰታቸው መሆኑን ገልጠው በኪነ ጥበቡ ዙርያ የነበራቸውን ገጠመኝ እና ከተሳታፊዎች የተነሱላቸው በተለይ ወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች አስመልክተው የግል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። በእዚሁ ዝግጅት ላይ የሚከተሉት ሌሎች ዝግጅቶችም ለዕይታ ቀርበው ታዳሚው በእጅጉ ተምሮባቸዋል።ከዶ/ር በድሉ ዝግጅቶች በተጨማሪ የሚከተሉት ዝግጅቶች ቀርበዋል። እነርሱም
- ''አድዋን ከዓይናችን ፊት ፋቁት '' በሚል ርዕስ በዶ/ር በድሉ ተደርሶ በአርቲስት አበራ የቀረበው ተውኔት በቪድዮ ታይቷል።
- የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ (ኮምዩኒቲ) እንኳን ደህና መጡ አቀባበል በኮሚኒቲው ሰብሳቢ አቶ ልዑል ለዶ/ር በድሉ የአበባ ስጦታ ተሰጥቷል።
- የመርሓግብሩ አስተናባሪ አቶ ዳዊት ስለ ዶ/ር በድሉ በአጭሩ የስራ እና የትምህርት ሁኔታ በአጭሩ አቅርቧል።
- ዶ/ር በድሉ ካሳተሟቸው የግጥም መጻሕፍት የተመረጡ ግጥሞች ለታዳሚው አቅርበዋል።
- ወ/ሮ አዲስ ግጥሞች አቅርባለች።
- አርቲስት እንዳለ የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህንን ''ጴጥሮስ ያችን ሰዓት '' የሚለውን ግጥም በቃሉ አቅርቧል።
- ድምጻዊት ጽናት አንድ ዜማ አቅርባለች (የድምጻዊ ጽናት ዜማ ከስር ቪድዮ ይመልከቱ)
- በኖርዌይ ነዋሪ የሆነው ''የአምስት ጉዳይ'' መጽሃፍ ደራሲ ያሬድ ዶ/ር በድሉ ጋር በሃገርቤት የነበረውን ትዝታ እና ግጥም አቅርቧል።
- ''ህዝብ እና መንግስት እየተሰዳደቡ አረቄ ይጠጣሉ'' በሚል ርዕስ አጭር ተውኔት በአርቲስት አበራ በቪድዮ ታይቷል።
- በመጨረሻም ከተሳታፊዎች በወቅታዊ ሁኔታ እና በእርቅ ኮሚሽን ጉዳይ ዙርያ ጥያቂዎች ተነስተው ሃሳብ ተሰጥቶባቸዋል።
ከእዚህ በታች ድምጻዊት ጽናት በዝግጅቱ ላይ ያቀረበችው ዜማ እና ከ50 በላይ የሚሆኑ በዝግጅቱ ላይ የነበሩ በጉዳያችን የተነሱ ፎቶዎች ያገኛሉ።
ድምጻዊት ጽናት
No comments:
Post a Comment