ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, July 30, 2015

Breaking news - Ethiopian foreign minister has confirmed as Ethiopian main opposition leader Prof.Birhanu Nega Joins his armed comrades in Eritrea (ጉዳያችን Gudayachn News)


Dr. Tewodros Adhanom

On July 29/2015, on his interview with VOA (Voice of America Amharic service), Dr.Tewoedros Adhanom, foreign minister of Ethiopia has confirmed  Ethiopian main opposition leader Prof.Birhanu Nega Joins his armed comrades in Eritrea. On his interview he mentioned ''ይሄው ግንቦት ሰባት ብርሃኑ ነጋ አስመራ ገባ ተባለ እሺ ገባ...'' '' It was said that Ginbot 7 leader Birhanu Nega has entered Asmara, ok it was mentioned he has entered (Asmara)...'' Dr. Tewodros Adhanom.

It was recalled that ''Patriotic Ginbot 7'' has already launched new offensive against TPLF regime from the norther part of Tigray and Gonder provinces of Ethiopia. According to reliable sources the fighting is still continuing. The regime is sending more troops to these particular areas. To read more about Prof.Birhanu Nega joins his armed comrades, please click here.


ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
July 31/2015 (ሐምሌ 24/2007 ዓም)

Tuesday, July 28, 2015

የፕሬዝዳንት ኦባማ የሰሞኑ ጉብኝት ምን አስተምሮን አለፈ? (የጉዳያችን ማስታወሻ)

 ''እኛ ለራሳችን እንበቃለን፣እናንተን አንፈራችሁም፣በፈቀድነው ጊዜ ከኛ ቦታ (ጋራዎች) እንደ ድንጋይ እንንዳችለን'' እቴጌ ጣይቱ ከአድዋ ጦርነት አስቀድመው ለጣልያን መልክተኛ የተናገሩት  

''ጣይቱ ብጡል'' ከተሰኘው መፅሐፍ የተወሰደ 

 አሁን በምንኖርበት ዓለም ውስጥ ሁኔታዎች በፍጥነት ከመለዋወታቸው አንፃር ትኩረት፣የቅድምያ ትንበያ እና ስልታዊ አሰራሮች በእጅጉ የሰፈኑበት ነው።የቀደሙት ትውልዶቻችን በዘመናቸው የገጠማቸውን ፈታኝ ሁኔታ ሁሉ በፅናት፣በቆራጥነት እና በብልሃት ተወጥተው አሁን ላለነው ትውልድ አስረክበውናል።ባለፉት ዘመናት የነበሩ የውስጥ የስልጣን ሹክቻዎች እና የባዕዳን ጣልቃ ገብነት በዘመኑ ከነበረው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በተጣጣመ እና የእራሱን መልክ ይዞ ኢትዮጵያን ፈትኗታል።ሆኖም ግን በዘመኑ የነበረው ትውልድ እና የኢትዮጵያ መሪዎች ቅድምያ ለሀገራቸው፣ለእምነታቸው እና ለሞራላዊ ልዕልና የሚሰጡ ስለነበሩ የገጠሟቸውን ፈተናዎች በሙሉ ለማለፍ ችለዋል።

ሐምሌ 19/2007 ዓም እሁድ ምሽት የአሜሪካው  ፕሬዝዳንት ኦባማ ከኬንያ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት እና በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ንግግር ለማድረግ አዲስ አበባ ገቡ።የፕሬዝዳንቱ ጉብኝት ዋና ዋና አላማዎች ሶስት ናቸው።እነርሱም የመጀመርያው ኢትዮጵያ በሱማልያ ሰራዊቷን ለተጨማሪ አመታት እንድታዘምት እና በአንፃሩ አሜሪካ የገንዘብ፣ቁሳቁስ እና የጦር መሳርያ እርዳታ እንደምታደርግ ለማግባባት፣ሁለተኛው እየገፋ የመጣውን የቻይና የአፍሪካን መቆጣጠር ለመግታት እና ሶስተኛው የአሜሪካ ''አሻንጉሊት'' መንግስት ናቸው ተብለው የሚታሙትን የህወሓት፣የኡጋንዳው እና የኬንያ መንግስታትን በተቻለ መጠን የማሻሻያ የጥገና ለውጥ በማድረግ በውስጣቸው ያለውን ውጥረት እንዲያረግቡ ለማግባባት የሚሉ ናቸው።

እዚህ ላይ ልብ ማለት የሚኖርብን ቁም ነገር አሜሪካ በአሁኑ ወቅት ከማንኛውም ጊዜ በላይ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የምትገኝበት ወቅት ነው።የመጀመርያ የውጥረቷ ምንጭ በሀገር ውስጥ ያለው የማኅበራዊ እና የምጣኔ ሀብት አለመረጋጋት፣የሩስያ ምስጢራዊ አካሄድ በማናቸውም ጊዜ ግጭት በሚያስነሳ መልክ ተንጠልጥሎ መቆየቱ፣የመካከለኛው ምስራቅ እና የሰሜን አፍሪካ (ግብፅን ጨምሮ) ያለው አለመረጋጋት እና ወዴት እንደሚያመራ በቀላሉ መተንበይ አለመቻሉ የሚሉት ይጠቀሳሉ።በእነኝህ ሁሉ ሁኔታዎች ነው እንግዲህ አቶ ኦባማ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ ወደ ሆነችው ኢትዮጵያ የመጡት።''የተራበ ልጅ ምግብ አይመርጥም'' እንደሚባለው በእዚህ ጊዜ ለአሜሪካ ጥቅም የሚጠቅሙ ጉዳዮች ላይ አጋር መፈለግን በአንድ በኩል፣ በሌላ በኩል ደግሞ በኃይል የአምባገነንነት ቀንበር የተጫነባቸው የአፍሪካ ህዝብን በደፈናው አግልሎ ከአምባገነኞቹ ጋር ብቻ ተነጋግሮ መምጣት የሚያስከፍለውን ዋጋ ያውቃሉ እና በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ስለ መልካም አስተዳደር፣ሙስና እና ዲሞክራሲ ንግግር ማድረግ አስፈላጊነት ተወሰነ።የእዚህ አይነቱ ''ሁለት እግር አለኝ ብሎ ሁለት ዛፍ ላይ የመውጣት''ሙከራ አሜሪካንን ዋጋ የሚያስከፍላት ጉዳይ እንደሆነ ማንም አይስተውም።ጥቅምን ፈልጎ በምሽት ከአምባገነኖች ጋር መደነስ፣ሲነጋ ደግሞ የዲሞክራሲ እጦት የሚያመጣውን ጉዳት ላይ ንግግር ማድረግ ለአሜሪካ የሚፈይደው ጉዳይ እንዳለ በጊዜ የምናየው ነው። 

የኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃነት በፕሬዝዳንት ኦባማ ወይንም በሌላ የባዕድ ኃይል አይገኝም 

አሁን ያለንበትን ጊዜ ኢትዮጵያን የሚመሯትን መሪዎች ከመቼውም ጊዜ በላይ የማናምንበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።ሕዝብ ብዙ አይኖች አሉት።ይህ ክፉ እድልም ሆነ እጣ ነው።ስለአንዲት እና የተባበረች አሜሪካ የሚሰብኩን ኦባማ ኢትዮጵያ ላይ ስላለው የጎሳ ፖለቲካ አደጋ ለመንገር አልደፈሩም።ይህ ማለት ግን ኢትዮጵያን በመከፋፈል አሜሪካ ሁል ጊዜ ተጠቃሚ ነች ብሎ ማሰብ በተለይ በእዚህ ጊዜ ትክክል ላይሆን ይችላል።የሱማልያ፣የደቡብ ሱዳን የኤርትራ ጉዳዮችን ለመዘወር ኢትዮጵያ አይነተኛ መሳርያ ሆና እንድታገለግል ይፈለጋል። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ እራሷን አጠናክራ በአካባቢያዊም ሆነ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ አለምን የምትሞግት  ሆና እንድትወጣ አይፈለግም።የእዚህ አይነቱ የኢትዮጵያ ጥንካሬ ምናልባትም ኢትዮጵያ በ1950ዎቹ እና 60ዎቹ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር አፍሪካውያን ከቅኝ ግዛት እንዲወጡ የረዳችውን ያህል አሁን አፍሪካ ዙርያዋን ከከበባት የተፈጥሮ ሃብቷን ለመበዝበዝ ከቆሙ ከሩቅ ምስራቅ እስከ አሜሪካ ድረስ ካሰፈሰፉ ኃይሎች የማዳን ሚና እንዳትጫወት ይፈራል።ይህ የሚሆነው ደግሞ በቅድምያ እራሷን ማቆም ከቻለች ስለሆነ በተቻለ መጠን መንጥቃ እንዳትወጣ እንደ ወያኔ ያለ ከፋፋይ ኃይል ጋር መወዳጀቱ እንደ አንድ ስልት በባእዳን ዘንድ ተይዟል።

ይህ ማለት የኢትዮጵያ ሕዝብ ለነፃነት የሚደረገው ትግልን የሚገዳደሩት የሀገር ውስጥ ''ሆድ አደር'' እና ጎጠኞች ብቻ ሳይሆኑ ከስልታዊ ጥቅም አንፃር ኢትዮጵያ የተዳከመች ሆና እንድትኖር ማድረግ ቢያንስ ባለፉት 100 አመታት ውስጥ የታየ ጉዳይ ነው።በአስራ ዘጠነኛው ክ/ዘመን ሁለተኛ አጋማሽ ጀምሮ ያሉትን ሁኔታዎች ብናጤን ከጥቅማቸው አንፃር ባእዳን ኢትዮጵያን ማዳከም   እንደ አንድ ስልት ሲጠቀሙበት እንመለከታለን።ለእዚህም አብነት የሚሆኑን የአድዋ ጦርነት፣የ1928 ዓም ዳግመኛ የኢጣልያ ወረራ ላይ የዓለም መንግሥታት በኢትዮጵያ ላይ ማደም፣በአፄ ኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት የተሰሩ የተለያዩ ደባዎች፣በ1967 ዓም የሱማልያ ወረራ ወቅት አሜሪካ ኢትዮጵያን ላለማስታጠቅ የወሰደችው እርምጃ፣አመታት የፈጁት የሰሜን ጦርነቶች በከፍተኛ ደረጃ በባእዳን ወጪ መካሄዱ እና አሁን በዘመናችን ደግሞ በጎሳ የተደራጀ መንግስትን በመደገፍ እና ኢትዮጵያን የመከፋፈል ተግባር ላይ በተዘዋዋሪ እጃቸውን የከተቱ መንግስታትን መጥቀስ ይቻላል። 

'አሜሪካናይዜሽን'' እና ''አይሮፓናይዜሽን'' ሆኖ የወጣ ትውልድ አፍርተናል

ከላይ የተጠቀሱት ታሪኮችን እና አሁን ያለውን የዓለም ነባራዊ ሁኔታ ስንመለከት ''በሰጥቶ መቀበል'' ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ካልሆነ በቀር ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ጠንክራ እንዳትወጣ የሚኮረኩማት በብዛትም ሆነ በአይነት ለእድገቷ በጎነት ካላቸው በእጅጉ ይበልጣሉ።እዚህ ላይ ማስተዋል የሚገባን ከጊዜ ጋር በተናበበ መልኩ ኢትዮጵያ በጥቅሟ ላይ የማይደራደር መንግስት በፍጥነት ካልኖራት በቀር እጅግ አደገኛ ሁኔታዎች መከሰታቸው አይቀርም።ለእዚህም አይነተኛው እና አንዱ ምክንያት በእዚህ ዘመን የሚኖር ትውልድ የቀደሙት አባቶቹ የአለምን ፖለቲካ ከሚረዱበት አቅም በእጅጉ ያነሰ እና የጀርባ ድርጊቶችን የመተንተንም ሆነ የማወቅ ችሎታው ያነሰ መሆኑ ነው።ለእዚህም ዋነኛ መክንያቶቹ ባዕዳውያን ለእረጅም ጊዜ በአዲሱ ትውልድ ላይ የሰሩት ተከታታይ ግን ደግሞ  የጠለቀ የስነ-ልቦና ዘመቻ  ነው።በእዚህ የስነ-ልቦና ዘመቻ ሳበያ በከፍተኛ ደረጃ ከሚገኝ ምህር እስከ ዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍል ድረስ የተጠቃ ስለሆነ በሀገሩ የአምባ ገነኖችን ታግሎ ነፃነቱን ከመቀዳጀት ይልቅ ምዕራባውያንን እያሞገሰ በትምህርት ክህሎቱ ''አሜሪካናይዜሽን'' እና ''አይሮፓናይዜሽን'' ሆኖ የወጣ ትውልድ አፍርተናል።የእዚህ አይነቱ ትውልድ መገለጫዎች እና የሚያመጣው ጉዳት እንዲሁም የችግሩ መፍትሄ በተመለከተ በእዚህ አጭር ፅሁፍ ለመዘርዘር አይቻልም።ውጤቱን ግን ስንመዝነው ግለኝነት፣እራስን ብቻ የማየት ሃገርን እና ህዝብን የመመልከት እንዲሁም ኃላፊነትን የመረዳት ችግር አንዱ እና አይነተኛው የውጤቱ መገለጫ ነው።

በመሆኑም ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ለማስቀጠል እና ለመጪው ትውልድ ጎሰኘነት እና ድህነትን ላለማውረስ ኢትዮጵያዊነትን አስቀድሞ ለነፃነት ከመነሳት ባነሰ አንድም አማራጭ የለም።ኢትዮጵያ እንድትሆን የምንፈልገውን ለማግኘት በመፃፍ፣ጋዜጣ በማተም፣ለፍትሃዊ ምርጫ በመታገል የሚፈለገው ውጤትን ማግኘት አልተቻለም።ለእዚህ ዋነኛው ምክንያት ደግሞ  ፍፁም የሆነ የጎጥ ስርዓት መሰረታዊ ባህሪ ምክንያት እና የባዕዳን በገንዘብ፣በምክር እና በሎጀስቲክ ሁሉ ከፍተኛ ድጋፍ ስለሚያገኝ ነው።በእዚህ ሁሉ ውስብስብ ዓለም ውስጥ ከእኛ በላይ ለእኛ ማን ሊቆም ይችላል? 

ለኢትዮጵያ ከኢትዮጵያውያን በላይ ማንም ሊቆም አይችልም 

የኢትዮጵያ ጉዳይን ባዕዳን አደባባይ፣ዋይት ሃውስ በር ላይ፣ወዘተ የተጮሁት የነፃነት ድምፆች እና አምባገነኑን የኢህአዴግ/ወያኔ መንግስት አትደግፉ የሚሉት አቤቱታዎች ሁሉ ባእዳኑ ለኢትዮጵያ እና ለህሊናቸው ተገዝተው እንዲመለሱ ሳይሆን ያደረጋቸው  ለጥቅማቸው የበለጠ የሀገራችንን አንድነት እና ህልውና ሊያናጋ በሚችል መልክ የበለጠ ከፋፋይ የጎሳ የፖለቲካ መርዝ ከሚረጨው ስርዓት ጋር ሲተባበሩ ተስተውለዋል።

በመሆኑም የኢትዮጵያ የነፃነት ትግል በአዲስ አቅጣጫ እና አካሄድ መሄድ ያለበት ጊዜ ቢኖር አሁን ነው።በአሁኑ ወቅት ለነፃነት ትግል ህዝብን በመምራት ላይ የሚገኙት የፖለቲካ ኃይሎችን በአቅም፣በገንዘብ እና በእውቀት መርዳት ብሎም  በቀጥታ እገዛ ማድረግ አንገብጋቢው ወቅታዊ የኢትዮጵያ ጥሪ ነው።ይንንም ለመከወን የሚከተሉት ነጥቦች እጅግ አስፈላጊ ናቸው። እነርሱም - 
  1. እኛነታችንን በኢትዮጵያዊነት ቅኝት በአግባቡ መቃኘት።ይህ ማለት ያለፈ ማንነታችንን እና ክብራችንን እንዲሁም  የመከባበር እና የመተሳሰብ ባህላችንን ማስፈን፣
  2. ኢትዮጵያን መልሶ ከማቆም እና ያለፉ የታሪክ ስህተቶችን በማይደግም መልኩ የነፃነት ትግሉን መቀየስ፣
  3. ከየትኛውም አቅጣጫ የሚመጣ የባእዳንን ፍላጎት ማጋለጥ እና መታገል።ይህ ማለት ከየትኛውም የባዕዳን ኃይሎች የነፃነት ትግሉን በሚደግፍ መልኩ የሚሰጡ ድጋፎችን መግፋት ይገባል ማለት አይደለም።
  4. የማንንም የባዕድ ኃይል ተፅኖ የሚገዳደር አቅም በእራስ መፍጠር፣
  5. ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን አደገኛ ሁኔታ ላልተረዳው ወገን በሙሉ በሚገባ ማስገንዘብ፣ማስረዳት እና ወደ ሥራ እንዲገባ ማገዝ፣
  6. አንድ ሰው አሁን ባለንበት የቴክኖሎጂ ዘመን ብዙ የመስራት አቅም እንዳለው ማስገንዘብ እና በውጭ ሃገራት ሁሉ  ተፅኖ ፈጣሪ ማህበረሰብ እንዲኖር መስራት እና 
  7. በሀገር ጉዳይ ማንም ዝም እንዳይል ማድረግ፣ማብቃት እና ቸልተኘንትን በህብረተሰቡ ውስጥ ለመዝራት የሚፈልጉትን ማረም፣መምከር እና ወደ እውነታው ኢትዮጵያን መልሶ ለማቆም ለሚደረገው የነፃነት ትግል እንዲቆሙ ማብቃት  የሚሉት ናቸው።
ባጠቃላይ ኢትዮጵያን በሚስጥር የሚሸጥ መንግስት ስልጣን ላይ እስከቆየ ድረስ የእኛነታችን አሻራ መጥፋቱ የማይቀር ብቻ ሳይሆን ለከፋ ባርነት የአሁኑን ብቻ ሳይሆን መጪውንም መዳረግ የእረጅም ጊዜ ክስተት አይሆንም።ዛሬ በዓይናችን የምናየውን የቅጥፈት ምርጫ ዲሞክራሲያዊ ነው ያሉን ባእዳን፣እየራበን አደጋችሁ እያሉ የተሳለቁብን ''መሪዎቻችን''፣እያሰሩን አንድም ያሰርነው የለም እያሉ ያላገጡብን እና በባእዳን ያስላገጡብን፣እህቶቻንን  በእየአረብ ሃገራቱ ሲሸጡ ያሻሻጡ የአራት ኪሎ ቅምጥሎች ኢትዮጵያን ደብዛዋን ለማጥፋት ከባእዳን ጋር ሌት ተቀን እየደከሙ ለመሆናቸው ከባሕርያቸው፣እየሰሩ ካሉት ሀገር የማፍረስ ሥራ እና የባእዳኑ በሀገራችን የውስጥ ጉዳይ ገብተው የመፈትፈት ተግባር ሁሉ በቀላሉ መረዳት ይቻላል።ከኢትዮጵያውያን በላይ ለኢትዮጵያ የሚመጣ ወትሮም አልነበረም ወደፊትም አይኖርም።ከነፃነት መለስ ምንም የመነጋገርያ ቦታ ሊኖረን አይገባም።የሰሞኑ የፕሬዝዳንት ኦባማ ጉብኝትም ያመላከተን አንድ እና አንድ ነገር ብቻ ነው።ይሄውም የነፃነት ትግሉን ከመደገፍ በላይ ምንም አማራጭ የለም።


                ሐምሌ 22/2007 ዓም (ጁላይ 29/2015)

Monday, July 27, 2015

ፕሬዝዳንት ኦባማ በኢትዮጵያ የሰፈነው ስርዓት ከጠበቁት በላይ አስደንግጧቸዋል።አቶ ሃይለማርያም የኢትዮ-አሜሪካንን የእረጅም ጊዜ ግንኙነት ለገዢው ፓርቲያቸው ፖለቲካ ሲሉ ለማደብዘዝ ሞከሩ።(የጉዳያችን አጭር ማስታወሻ)

ፕሬዝዳንት ኦባማ አዲስ አበባ ሲገቡ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ለማየት ሲጋፉ 

ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት እየመራት ያለው ስርዓት ዲፕሎማሲ፣ፕሮቶኮል፣አቀራረብ፣አቅም እና የውጭ ተሞክሮ ያነሰው፣ ብቻ ሳይሆን ''አያውቁብኝም'' ባይ እና አይን ያወጣ ውሸት በመዋሸት አለምን ያታለለ የሚመስለው መንግስት መሆኑን በእያንዳንዱ የኦባማ ጉብኝት ሂደት መረዳት ትችላላችሁ።

ፕሬዝዳንቱ (አቶ ኦባማ ማለቴ ነው) የእውቀት እና በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ላይ የመረጃ ክፍተት አለባቸው ብዬ አላምንም።ጉዳዩ የጥቅም ጉዳይ ስለሆነባቸው ደግሞም ለሀገራቸው መስራት የሚገባቸውሥራ ስላለ እንጂ።በኢትዮጵያ ያለው የአምባገነንነት እና ሕዝቡን ያገለለ ስርዓት ከጠበቁት በላይ የከፋ መሆኑን ማወቃቸው እና መደንገጣቸውን ለማወቅ ከፈለጋችሁ ዛሬ ከአቶ ሃይለማርያም ጋር የሰጡትን መግለጫ መመልከት ብቻ በቂ ነው።ፕሬዝዳንቱ ከእዚህ በፊት በቀልድ እና በልበ ሙሉነት የሚያሳዩት የመግለጫ አሰጣጥ መንገድ ሁሉ አቶ ኃይለ ማርያም ጎን ቆመው ማምጣት አለመቻላቸው ቀድመው ከነበራቸው ግንዛቤ በላይ ኢትዮጵያ በጣም አደገኛ በሆነ አምባገነን ስርዓት ስር መሆኗ እና መጪው ጊዜም አሳሳቢ መሆኑን እንደገባቸው በግልፅ ይነበብባቸዋል።

በሁኔታው አስከፊነት ተበሳጭተዋል።ይህንን ብስጭታቸውን ለአቶ ሃይለማርያም አጥብቀው መንገራቸውን ለመግለፅ ደግሞ ''ከአቶ ሃይለማርያም ጋር በጥብቅ ተነጋግረናል'' የሚለውን ቃላት በመጠቀም ብቻ ሊያልፉት ሲሞክሩ ተስተውሏል።ኦባማን እያስተናገደ ያለው የኢህአዴግ/ህወሓት ቡድን ከመቼውም ጊዜ በላይ የተጋለጠበት ወቅት ላይ ነው።እንዴት? ከነገ የኦባማ የአፍሪካ ህብረት ንግግር በኃላ እንመለሳለን።በነገራችን ላይ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የፕሬዝዳንቱን እና የአቶ ኃይለማርያምን መግለጫ ምሽት ላይ ለሕዝቡ ሳይተረጉም እንዳለ እንግሊዝኛውን ብቻ አቅርቦታል።ይህም ፕሬዝዳንቱ ጋዜጠኞች እና ተቃዋሚዎችን በዲሞክራሲ ሂደቱ ላይ አሳታፊ ማድረግ የገዢ ፓርቲውን ነው የሚጠቅመው  የሚለው ንግግር እና ሌሎች የኢትዮያ ሕዝብ እንዲሰማቸው የማይፈለጉትን እንደለመዱት ለመቆራረጥ ጊዜ አላገኙም።ንግግሩን ለነገ እንዳያስተላልፉት እና ነገ ቆራርጠው እና ቀጥለው እንዳያቀርቡት ደግሞ ትዝብት ፈሩ።ስለሆነም የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን አስር ሚልዮን የሚሆን ጥሩ እንግሊዝኛ ተናጋሪ ለሌላት ሀገር እንዳለ አቀረበው።

እዚህ ላይ ኦባማ ''ኢህአዴግን በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠን መንግስት'' የምትል ቃል መጠቀማቸው የዓለም አቀፍ ማህበረሰብን የሚያስደነግጥ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ከስድብ ያነሰ ንግግር አይደለም።ጉዳዩ ግን የአፍ ወለምታ መሆኑን መረዳት እና ጉዳዩ የቆሸሸ እና የሞራል ልዕልና የራቀው አቀራረብ ለመሆኑ ምንም ማስረጃ መደርደር አይገባውም።ፕሬዝዳንቱ እራሳቸው ጉዳዩን የሚያስተባብሉት ዋሽግተን ሲደርሱ ለመሆኑ ከሰሞኑ የምናየው ነው።የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል የፕሬዝዳንቱን ይህንን ቅጥፈት የትሞላበት ንግግር በመቃወም ለፕሬዝዳንቱ ክብር በቤተ መንግስት በሚደረገው የእራት ግብዣ ላይ እንደማይገኙ አስታውቀዋል።የሰማያዊ ፓርቲ እርምጃ ሚልዮን ኢትዮጵያውያንን ያስደሰተ እና ታሪካዊም ነው።

ኢህአዴግ/ወያኔ በኩል አሁን ለሚድያ ግልፅ ሆነው እየታዩ ያሉት ሁኔታዎች ግን የኢትዮጵያና የአሜሪካንን ዲፕሎማሲ ማጠናከር ላይ ያተኮረ የአንድ ጤነኛ መንግስት ሥራ አይደለም።በእዚህ አይነቱ ተግባር ላይ ኢህአዴግ/ህወሓት እንዳልጠተመደ ለማወቅ የዛሬውን የአቶ ሃይለማርያም ቃል ብቻ መጥቀሱ ይበቃል።

አቶ ኃይለማርያም ዛሬ ከፕሬዝዳንት ኦባማ ጋር በሰጡት መግለጫ 'ከአሜሪካን  ጋር የኢኮኖሚ ትብብር የተጀመረው በቅርቡ ነው''ሲሉ ተደምጠዋል።አንድ ጤነኛ መንግስት ያለው ሀገር መሪ የዲፕሎማሲ ግንኙነቱን ለማጠናከር ትንሹን ግንኙነት አጉልቶ እና አጠንክሮ ማቅረብ አንዱ ተልኮውና ያልታመመ አቀራረብ ነው።አቶ ሃይለማርያም ግን በአለቆቻቸው ልክ በተሰፋ የተሳሳተ ''የዲፕሎማሲ ጥብቆ'' ውስጥ ስለሆኑ እና ሁሉን ነገር ኢህአዴግ/ህወሓት ጀመረው ለማለት ከመፈለጋቸው የተነሳ ''ከአሜሪካን  ጋር የኢኮኖሚ ትብብር የተጀመረው በቅርቡ ነው'' ሲሉ ተደመጡ ያውም የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ፊት።

ይሁን  እንጂ አሜሪካኖች በኢትዮጵያ መዋለ ንዋይ ማፍሰስ ከጀመሩ ከግማሽ ክ/ዘመን በላይ ያስቆጠረ ለመሆኑ ጥቂት መረጃዎችን ማገላበጥ ብቻ  በቂ ነው።በዘመነ ደርግ ሂደቱ ቢቆምም።ሌላው አቶ ሃይለማርያም ለዲፕሎማሲ ማጉያ ከ115 ዓመታት በላይ የቆየውን ዲፕሎማሲያዊ የግንኙነታችንን ረጅም ታሪክ ማንሳት ሲገባቸው ጉዳዩን በጨረፍታ አልፈውት መድረኩን የጃጀ ኢህአዴጋዊ አስተሳሰብ ሊያንፀባረቁበት ፈለጉ።ግንኙነቱ የተጀመረው አሁን ይመስል 'ከአሜሪካን  ጋር የኢኮኖሚ ትብብር የተጀመረው በቅርቡ ነው'' ብለው ሊያሞኙን ሞከሩ።

ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ዲፕሎማሲ ግንኙነት የጀመሩበትን 100ኛ ዓመት ያከበሩት በ2003 ዓም እንደፈረንጆች አቆጣጠር ሲሆን አሁን 112 ዓመታትን አስቆጥረዋል።በእንዲህ አይነቱ መድረክ ላይ አንድ ሀገር እመራለሁ የሚል መንግስት ንግግሩን የሚጀምረው ከመቶ ዓመት በላይ የዲፕሎማቲክ ግንኙነት እንዳለን በመግለፅ እና ይህንን በማጉላት መሆን ሲገባው ይህንን ማንሳት ለኢህአዴጋውያን አፄ ምንሊክን፣ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴን ያስታውስባቸዋል እና የእረጅም ጊዜ ግንኙነታችንን በማውሳት ዲፕሎማሲውን ከማጠናከር ይልቅ አቶ ሃይለማርያም ባላዋቂ አቀራረብ ግንኙነቱን ''አጋድመው አረዱት'' እና ''ከመጣችሁ አጭር ጊዜ ነው'' አሏቸው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ፣የአለማያ ዩንቨርሲቲ ምስረታ ሂደት ላይ አሜሪካኖችበንጉሡ ዘመን የእራሳቸውን አስተዋፅኦ አድርገዋል።አሁንም እነኝህን አንስቶ መናገር ኢህአዴግ/ወያኔ ''ኢትዮጵያን ዛሬ ፈጠርኩ'' የሚለውን የበሰበሰ አስተሳሰብ ስለሚነካበት ሲያስበው ይደናገጣል።በመሆኑም አቶ ሃይለማርያም ሳያነሱት ቀሩ ወይንም እንዳያነሱ ማስጠንቀቅያ ተሰጣቸው።ይህ ባይሆን ኖሮ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያለ ማንም ባለሙያ አፅኖት ተሰጥቶት እንዲነሳ ሃሳብ የሚሰጠው ከእነኝህ ነጥቦች እንደሚሆን ማሰብ ከባድ አይደለም።እርግጥ ነው ይህ በካድሬ እና በጎጥ የምትመራ ሃገርን አይመለከትም።

በፕሬዝዳንት ኦባማ የአንድ ቀን ቆይታ፣የፕሮቶኮሉን መዘባረቅ እና ከአየር መንገድ ጀምሮ የባለስልጣናቱ በአግባቡ ተሰልፎ ፕሬዝዳንቱን ከመጠበቅ ይልቅ አሰላፊ እንደሚፈልጉ ሕፃናት አቶ ኦባማን ለማየት ሲንጠራሩ ስመለከት  የኢህአዴግ/ህወሓት ባለስልጣናት ዓለም አቀፍ ተሞክሮ ማነስ፣በራስ የመተማመን የሞራል ልዕልናቸው ሁሉ  መውረዱ ብቻ ሳይሆን አሳፋሪ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።ስነ-ስርዓት የሚባል ነገር የለም እንዴ?

የኬንያው ፕሬዝዳንት ''እኛ ኬንያውያን ከአሜሪካ የማንጋራቸው ባህላዊ እሴቶች አሉ ለምሳሌ የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ'' ያሉበትን ንግግር በተመለከትንበት ማግስት፣ በእራሱ የአፍሪካ ድምፅ መሆን የሚገባት ኢትዮጵያ አሁን ባሉት መሪዎቿ ከደረጃ በታች በሆነ አቀራረብ ተወክላ ማየት ሌላው አሳዛኝ ክስተት ነው።በኬንያ እና በኢህአዴግ/ህወሓት መካከል የተስተዋለው የልዩነት መጠን ለመግለፅ ቀላል ምሳሌ ሆኖ የታየኝ  የእግር ኳስ ቡድን ነው።በሰሞኑ የአቶ ኦባማ መስተንግዶ ኢህአዴግ/ወያኔ አንድ ዓለም አቀፍ ተሞክሮ የሌለው የእግር ኳስ ቡድንን ያህል ሲርበተበት፣ የኬንያው ፕሬዝዳንት አቀራረብ እና በእራስ መተማመንን ስመለከት የዓለም አቀፍ ተሞክሮ ያለው  የእግር ኳስ ቡድንን ልዩነት ያህል ተለያይተውብኛል።

ኢትዮጵያ አዋቂዎቿን በሙሉ የገፋባት፣ያሰደደባት እና ያሰረባት ኢህአዴግ/ወያኔ እንደማይወክላት በተግባር የምታሳይበት ቀን እሩቅ አይሆንም።ኦባማ ግን ኢትዮጵያን ትተው ሲሄዱ ጥሩ ነገር እየሸተታቸው እንደማይሆን መረዳት ይቻላል።ፕሬዝዳንቱ ቀድሞ ከነበራቸው መረጃ በላይ በጉብኝታቸው ወቅት ካሰቡት በላይ ሀገራችን አስከፊ ደረጃ ላይ መሆኗን  ይረዳሉ።ለነገሩ የእርሳቸው መረዳትም ሆነ አለመረዳት ፋይዳው ለሀገራቸው ነው።ለኢትዮጵያ ወሳኙ እና እጣዋን የሚወስነው የእራሷ አንጡራ ህዝቧ ነው።ኢትዮጵያ ከዘረኝነት፣ፍትህ ማጣት እና ከፋፋይ ስርዓትን በሕዝብ ፍቃድ በተመሰረተ መንግስት ከመቀየር መለስ  ስለምንም ነገር መነጋገር የሚቻልበት ደረጃ ላይ አይደለችም።ነፃነት ከሁሉ በፊት ሊቀድም ይገባል።


ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
ሐምሌ 21/2007 ዓም ( ጁላይ  28/2015)

Friday, July 24, 2015

''ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አንዱ ጆሮው ፈፅሞ አይሰራም ሆኖም አሳሪዎቹ ወደሀኪም ቤት ሊወስዱት ፈቃደኛ አይደሉም'' ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም ትናንት ወደ ዝዋይ እስር ቤት ሄደው ከጠየቁት በኃላ የፃፉት ልብ የሚነካ ፅሁፍ


በእስር የሚማቅቀው ጋዜጠኛ ተመስገን ከሚንከባከባቸው ሕፃናት ጋር 

ከእዚህ በታች ያለው ፅሁፍ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም የዝዋይ እስር ቤትን በእዚህ ሳምንት ከጎበኙ በኃላ የፃፉት ፅሁፍ ነው።
ዝዋይ እስር ቤት
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም
ሐምሌ 17/2007
ሐምሌ 16/2007 ዓ.ም. ለአሥር ወራት በእስር ላይ የቆየውን ጋዜጠኛ፣ ተመስገን ደሳለኝን (ከኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር ዝምድና የለውም፤) ለመጠየቅ ወደዝዋይ ወህኔ ቤት ሄጄ ነበር፤ የወሕኒ ቤቱ ባለቤቶች ማረሚያ ቤት ይሉታል፤ ማረሚያ ቤት ማለት ሀሳቡን በነጻነት የሚገልጽና በሀሳቡም ከወያኔ ጋር በሎሌነት ለመተዳደር የማያመች ሲሆን የቀናውን በጉልበት የሚያጎብጡበት ማለታቸው ነው፤ ማረም ማለት ቀጥታውን ማጉበጥ ነው፤ እንዴት እንደሚያጎብጡት ላሳያችሁ፤--
1. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ እስረኞች ሰዎች በመሆናቸው ሰብአዊ ደኅንነታቸውና ክብራቸው ሁልጊዜም እንዲጠበቅላቸው ያስፈልጋል፡፡
2. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ እስረኞች ሁሉ ከመሰቃየትና ከመጉላላት በጸዳ አያያዝ እንዲጠበቁ ይደነግጋል፤
3. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ አንድ እስረኛ ዘመዶቹና ወዳጆቹ ከሚኖሩበት በጣም ርቆ አይታሰርም፤
4. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ የታመመ እስረኛ ሙሉ ህክምናና አስፈላጊውን መድኃኒት ሁሉ ማግኘት አለበት፤
5. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ እስረኞች በአእምሮና በመንፈስ የሚያድጉበት ትምህርትን የማግኘት፣ መጻሕፍትን የማግኘት መብቶች አሏቸው፤
6. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ ማንኛውም እስረኛ በእምነቱ መሠረት አምልኮቱን የመፈጸምና የሃይማኖቱን መጻሕፍት የማንበብ መብት አለው፤
7. የኛን እንተወውና በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ ማንኛውም እስረኛ ዘመዶቹና ወዳጆቹ እንዲጎበኙት መብት አለው፤
8. እስረኞች የእስር ጊዜያቸውን ጨርሰው ከወህኒ ቤት ሲወጡ ትክክለኛ የማኅበረሰቡ አባሎች ሆነው እየሠሩ ለማኅበረሰቡ እድገት ድርሻቸውን እንዲያበረክቱ ማሰናዳት ያስፈልጋል፤
በዝዋይ እንዳየነውና እንደተነገርነው የእስረኞች ሁኔታ በጣም የሚያሳዝንና ከላይ የተዘረዘሩትን የሰብአዊ መብቶች የሚጥስ ነው፤ ጤንነት ዋና ነገር ነውና በሱ እንጀምር፤ ተመስገን ደሳለኝ ወንጀል የተባለበት የፖሊቲካም ሆነ የማኅበረሰብ እምነቱን እያፍረጠረጠ በመጻፉ ነው፤ (በ1992 ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ባደረግሁት ንግግር ‹‹አትፍሩ›› ብለሃል ተብዬ ተከስሼ ነበር!) እንዲያውም ክሱን አስቂኝ የሚያደርገው መንግሥትን ነቅፈሃል የሚል መሆኑ ነው፤ ሦስት ዓመት እስራት ተፈረደበት፤ ይግባኝ ተከለከለ፤ አሁን ከታሰረ አሥር ወራት ሆኑት፤ ተመስገን በጣም ከታመመ ጥቂት ቆየ፤ አንደኛ አንዱ ጆሮው በጭራሽ አይሰማም፤ ሁለተኛ ከባድ የወገብ ሕመም ስላለበት መተኛትና መቀጥም በጭንቅ ሆኖበታል፤ ሆኖም አሳሪዎቹ ወደሀኪም ቤት ሊወስዱት ፈቃደኛ አይደሉም፤ ከዚያም በላይ መድኃኒት ከውጭ ሲመጣለት ይከለክላሉ፤ እኔም የወገብ ሕመም ስላለብኝ የወገብ ሕመሙን የሚያቀልለትን መድኃኒት ወስጄለት ነበር፤ አንድ አሥር አለቃ መድኃኒቱን አየና ከለከለ፤ መልሼ ይዤው መጣሁ፤ እንዲህ ያለውን ውሳኔ የሚያደርጉ ሁሉ ወያኔዎች ናቸው፡፡

ከተመስገን ጋር ትንሽ ጊዜ ቆይተን በዚያው በዝዋይ የታሰሩ ሌሎች ጋዜጠኞችን ለመጠየቅ መጀመሪያ ተፈቅዶልን ስለነበረ ወደዚያ ስናመራ አንድ ሹም መሳይ መጥቶ ወታደሮቹን ለብቻ ለብቻ በስም እየጠራ በመንሾካሾክ ትእዛዝ ይሰጣል፤ እየተንሾካሾከ ለአንዱ ትእዛዝ ሰጥቶ ሌሎቹን እንዳናይ ከለከለንና ተመለስን፤ ምክንያቱን ብንጠይቅ በአንድ ጊዜ መጠየቅ የሚቻለው አንድ እስረኛ ብቻ ነው ተባልን፤ ቅን መንፈስ ለጎደለውና ለሙስና ለተጋለጠ አሠራር ጥሩ ምሳሌ ነው፤ በመንሾካሾክ የሚሰጠውም ትእዛዝ ዓላማው ያው ይመስላል፤ ወያኔ በሰዎች ላይ እንዲህ ያለ ጭካኔ ማሳየት የሚፈልገው ለምንድን ነው?

በዝዋይ እስር ቤት ትምህርትም እንደመድኃኒት የተጠላ ነገር ነው፤ ለተመስገንም ሆነ ለሌሎች መጻሕፍት አይገቡላቸውም፤ ለምን? ብዬ ስጠይቅ አንዱ ጠባቂ ‹‹ለእውቀት የሚሆን መጽሐፍ ይገባል፤›› አለኝ፤ የእውቀትን ፍቺ ለመጠየቅ ስሞክር ቶሎ ግራ መጋባቱን አየሁና ተውሁት፤ እሱም እንዳያውቅ ስለሚፈልጉ፣ አለቆቹ የእውቀትን ፍቺ ጠበብና ቀለል አድርገው አስተምረውታል፤ ሎሌ ትእዛዝን በሹክሹክታ እየተቀበለ ማስፈጸም እንጂ፣ እውቀት አያስፈልገውም፤ እዚህ ላይ ምናልባት በደርግ ጊዜ በእስር ቤቶች የነበረውን የትምህርት መስፋፋት ማንሣት ይጠቅም ይሆናል፤ በደርግ ዘመን ብዙ የተማሩ ሰዎች ታስረው ስለነበረ እረስበርሳቸው እየተማማሩ አንዳንድ ሰዎች ጀርመንኛና ፈረንሳይና ቋንቋዎች፣ ግእዝና ታሪክ እየተማሩ ወጥተዋል፤ በተለይ በሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ወህኒ ቤቶች አንደኛ ሲወጡ እንደነበረ አስታውሳለሁ፤ ዛሬ በወህኒ ቤቶች ትምህርት ክልክል ነው፤ በቃሊቲ ሁለት የትምህርት ሙከራዎች ከሽፈውብናል፤ አንድ ጊዜ ኦሮምኛ ለመማር የፈለግን ሰዎች ተሰባስበን ተከልክለናል፤ ሕግ ለመማርም ጀምረን ታግደናል፤ እንዲሁም ጂምናስቲክ በቡድን መሥራት ክልክል ነበር፤ ማናቸውም እውቀት አደገኛ ነው! ታዲያ ማረሚያ ቤት የሚሉት ማንን ለማታለል ነው? ማረሚያ ቤት እንዲሆን በመጀመሪያ አሳሪዎቹ መታረም አለባቸው!
እንደተመስገን ደሳለኝ፣ እንደአብርሃ ደስታ፣ እንደእስክንድር ነጋ፣ ከዞን ዘጠኝም በፈቃዱ ኃይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አቤል ወበላ፣ አጥናፉ ብርሃኔ ገና አልተለቀቁም፤ በተጨማሪም ከእስልምና በኩል የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባሎች ዛሬም እንደታሰሩ ነው፤ የመፍትሔ አፈላላጊዎችን ማሰር ነገሩም ግራ ነው፡፡
በመጨረሻም መነሣት ያለበት አንድ አደገኛ አዝማሚያ አለ፤ ፖሊስ የሚባለው ፍርድ ቤት ከሚባለው ጋር ያለው ግንኙነት ሕግ የሚባለውን ከጨዋታ ውጭ አድርጎታል፤ ፍርድ ቤት የሚባለው እስረኛ እንዲፈታ ፖሊስ የሚባለውን ሲያዝ እንደማይፈጸም በተደጋጋሚ ታየ፤ ይህ የመጨረሻው የውድቀት ምልክትይመስለኛል፤ቆም ብሎ ማሰብና አስፈላጊውን የለውጥ እርምጃ መውሰድ የሚያስፈልገው አሁን ነው፡፡

ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

Sunday, July 19, 2015

Prof. Berhanu Nega Chairman of Patriotic-Ginbot 7 Joins His Armed Comrades in Eritrea (GUDAYACHN special note with latest photos)

Ethiopian armed opposition group Patriotic-Ginbot 7 chair person Professor Birhanu Nega Joins his army comrades in Eritrea.

The Armed group has vast support both inland and abroad. It is recalled that Washington based Ethiopian Satellite television- ESAT has disclosed  armed struggle has already began last week in the northern part of Ethiopia near to Eritrea and Sudan border.

Many believe the situation will bring political change in Ethiopia plus good lesson to the West  to adjust their policy towards the dictator ruling party of TPLF. Otherwise the possibility to loose their long-aged relation ship with Ethiopian people will be very real. On the other hand, Horn of Africa political analysts and Human Rights organisations, are confused with Obama visit to Ethiopia next week. One analyst says President B.Obama visits to Ethiopia is nothing but it is a good indicator of American foreign policy's failed part regarding Ethiopia. 

For your information, the hot news in Kenya, currently, is about President Obama's visit to Nairobi. But in Addis Ababa the situation is vis-versa. Many Ethiopians believe and agree  as President Obama's visit is to show his solidarity with ''African-North Korean'' minority ethnic-based group TPLF which declared as if it won 100% of the last May,2015 election. 

Therefore confirmed information forwarded from the ancient land-Ethiopia is that the hot news in the whole nation is not President Obama's visit to Addis.It is the beginning of fierce fighting in the norther part of Ethiopia between Patriotic-Ginbot 7 army and TPLF.

Here below is the latest photos of Prof. Birhanu Nega arrival at Eritrea. 

Source of Photos = ''ESAT'' face book, ''Zehabesha'' and ''Satenaw'' websites 










 ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

(July 20/2015)

Saturday, July 18, 2015

ሀገራችን ከመሸጧ በፊት መድረስ የዜጎች ግዴታ ነው! ኢትዮጵያ በኢህአዴግ ዘመን ከውጭ በተበደረችው ብድር ሳብያ በዓለም ላይ አደጋ ከተጋረጠባቸው 14 ሃገራት ዝርዝር ውስጥ መግባቷን የዓለም ባንክ አስታወቀ።

ኢትዮጵያ የገባችበት ብድር ከፍተኛ ቢሆንም የመሰረታዊ ፍላጎቶችን በዋና ከተማ ደረጃም ማዳረስ አልቻለችም  በቢልዮን የሚቆጠር ዶላር የት ገባ?

አንዲት ሀገር ከጠቅላላ ምርቷ 30 ከመቶው ከለጋሽ ተቋማትና ሃገራት የሚገኝ ብድር ላይ ከተመሰረተ ከፍተኛ የዕዳ ቀውስ ውስጥ እየገባች መሆኗን ያማለክታል ያለው የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ የብድር መጠኗ ከጠቅላላ ምርቷ አሁን 45 በመቶ ሲሆን በጥቂት ጊዜያት ውስጥ 65 በመቶ ይደርሳል በማለት የአደጋውን አሳሳቢነት ያመላክታል።
==================================================================
የብድር ጉዳይ አዲሱ የዓለማችን ሃገራትን የማንበርከክያ መሳርያ እየሆነ ነው።በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት የሀገራት ብድር በሁለት ጎራ በተከፈሉ ኃይሎች መካከል በነበረ ፍትግያ ሳብያ የማምለጫውም ሆነ ፋታ ለማግኘት የመደራደር አቅም ነበረ።አሁን ባለንበት ዓለም ግን የእዚህ አይነቱ ዕድል አይታይም።ለእዚህም አይነተኛ ምሳሌ የምትሆነው ግሪክ ነች።የግሪክ የብድር ቀውስ የምጣኔ ሀብቷን ከማድቀቁም በላይ የሀገሪቱን የውስጥ ፀጥታ ያናጋ እና በቅርቡ በሕዝብ በተመረጠውን መንግስቷ እና በሕዝቡ መካከል መተማመንን ያጠፋ አሁንም ይሄው የብድር ቀውስ መሆኑ ይታወቃል።

ኢትዮጵያ በኢህአዴግ/ወያኔ የ24 ዓመታት የስልጣን ዘመን ሀገሪቱ በታሪክ አይታ የማታውቀው ዕዳ ውስጥ ተዘፍቃለች።ብድሩ ለልማ ሥራ ውሎ ቢሆን ጥሩ ነበር።ሆኖም ግን የዓለም የገንዘብ ድርጅቶችም ሆኑ የእራሱ የመንግስት ኦዲተር ሪፖርት የሚያሳየን አንድ ነገር ነው።ይሄውም አብዛግኛው በአሁኑ ትውልድ እና በመጪው ትውልድ ስም የሚፈፀመው ብድር በጥቂት ባለስልጣናት እና ሙሰኛ አጋሮቻቸው ወደውጭ ሃገራት መወሰዱ የአደባባይ ሚስጥር መሆኑ ነው።''ግሎባል ፋይናንስ ኢንተግሪቲ'' ባለፈው ዓመት ባወጣው ዘገባ ኢትዮጵያ በአስር ዓመታት ውስጥ ብቻ በሕገ ወጥ መንገድ 16.5 ቢልዮን ዶላር በተለያየ መንገድ መውጣቱን በምሬት ገልጧል።ሀገር በእድገት መንገድ ላይ ነው የሚባለው አብዛኛውን የልማት ሀብት በሀገር ውስጥ አፍርቶ ቀሪውን በብድር ወስዶ የልማት ፕሮጀክት ሲሰራ ነው እንጂ እስከ 65 በመቶ የሚሆን የሀገሪቱን ሀብት በብድር ላይ ጥሎ በብድር የተገኘውንም ገንዘብ ለጥቂት ቅምጥል ባለስልጣኖች እና አጋሮቻቸውም ኪስ ማድለብያ እያደርጉ ሀገሪቱን ወደ ባሰ ድህነት መክተት ከወንጀል ተጠያቂነት አያድንም።ባለፉት 5 ዓመታት የትራንስፎርሜሽን እቅዱን እየሰራን ነው ያለው ስርዓቱ ሚያዝያ 2/2006 ዓም የ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ባቀረበው የአምስት ዓመት ትራንስፎርሜሽን ክንውን ላይ ከተባለው ግብ ኢትዮጵያ መድረስ አለመቻሏን አምኗል። የምክር ቤቱ ብቸኛ ተቃዋሚ አቶ ግርማ ''ቀድሞውንም ዕቅዱ በአግባቡ ያልታሰበበት ለመሆኑ አሁን ላለበት ውጤት መብቃቱ በራሱ ምስክር ነው'' ብለዋል።

ይህ ሁሉ ሆኖ ነው እንግዲህ ሀገራችን በብድር ላይ ብድር እየተወሰደ ዛሬ ከ14ቱ በብድር ብዛታቸው አደጋ ላይ ከወደቁ የዓለም ሃገራት ተርታ አሰለፋት።በነገራችን ላይ ''ደፋሮቹ'' የስርዓቱ አውራዎች አሁንም ለሌላ 5 ዓመት የትራንስፎርሜሽን እቅድ እያቀድን ነው ብለው መሰብሰባቸው ይታወቃል።ምናልባትም ነሐሴ መጨረሻ ላይ ለሕዝቡ ማባበያ ያቀርቡት ይሆናል።እውነታው ግን በአሁኑ ትውልድ እና በመጪው ትውልድ ስም ብድር ተበደሩ፣ግልፅነት እና ተጠያቂነት የሌላቸው የልማት ፕሮግራምቀረፅን አሉ፣መሰረታዊ መርሆዎችን ያልተከተሉ ፕሮጀክቶች አስተዋወቁ በፕሮጀክቶቹ ስም ገንዘብ ወደ ውጭ ሸሸ።በመጨረሻ ብድር የመመልስ አቅም የሌላት ብቻ ሳይሆን አሁን ላለው አስመጪ ነጋዴ የውጭ ምንዛሪ ማቅረብ የማይችል ብሔራዊ ባንክ አስታቅፈው ቁጭ አሉ።

ፅሁፌን ከመደምደሜ በፊት ለእዚህ ፅሁፍ  መንደርደርያ የሆነውን የ''ዘጋርድያን'' ዘገባ መሰረት አድርጎ የ''አዲስ አድማስ'' ጋዜጣ ዛሬ ቅዳሜ ሐምሌ 11/2007 ዓም ለንባብ ያቀረበው ዘገባ ከእዚህ በታች ይመልከቱት ዘንድ እጠይቃለሁ።

የውጭ ብድር እዳ ኢትዮጵያን ያሰጋታል ተባለ

አዲስ አድማስ 
Saturday, 18 July 2015 10:55
Written by  
 ስጋት ከተጋረጠባቸው 14 ሀገራት ውስጥ ተካታለች
• ሴኔጋል፣ ታንዛኒያ፣ ኡጋንዳ፣ሞዛምቢክ በዕዳ ተዘፍቀዋል

      የውጪ ብድር እዳ ኢኮኖሚያቸውን ሊፈታተን ይችላል የሚል ስጋት ከተጋረጠባቸው 14 የአለም አገራት ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን ዘ ጋርዲያን የአለም ባንክን ሪፖርት ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ በአሁን ወቅት ኢትዮጵያ ከፍተኛ የብድር እዳ እንዳለባት የጠቀሰው ሪፖርቱ፤ ከአጠቃላይ አገራዊ ምርቷ 45 በመቶ የሚሆነው ከብድር የተገኘ ገንዘብ እንደሆነ ጠቁሞ፤ በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ይህ አኃዝ ወደ 65 በመቶ ሊያሻቅብ እንደሚችል ጠቁሟል፡፡ ከለጋሽ ተቋማትና ሃገራት የሚገኝ ብድር ለአጠቃላይ አገራዊ ምርት ያለው አስተዋጽኦ ከ30 በመቶ በላይ ከሆነ ሀገራት ወደ ከፍተኛ የእዳ ቀውስ እያመሩ መሆኑን እንደሚያመለክት የጠቆመው ሪፖርቱ፤ ኢትዮጵያም በዚህ የአደጋ ቀጠና በከፍተኛ ደረጃ ከገቡ 14 የአለም  ሀገሮች መካከል ተጠቅሣለች።  ከፍተኛ የውጭ እዳ ውስጥ ተዘፍቀዋል የተባሉት 14 ሀገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ ቡታን፣ ኬፕ ቨርዲ፣ ዶሚኒካ፣ ጋና፣ ላኦስ፣ ሞሪታኒያ፣ ሞንጐሊያ፣ ሞዛምቢክ፣ ሣሞኣ፣ ሣኦቶሜ ፕሪንቼቤ፣ ሴኔጋል፣ ታንዛኒያ እና ኡጋንዳ ናቸው፡፡ በሌላ በኩል 24 የአለም ሀገሮች የውጭ እዳቸው በሚያሰጋ ደረጃ እየጨመረና ወደ አደጋው ቀጠናም እየተንደረደሩ ነው በሚል ተጠቅሰዋል፡፡ 

አንዳንድ በአስጊ ደረጃ እዳ ውስጥ ተዘፍቀዋል የተባሉ ሀገራት፣ የተበደሩትን ገንዘብ ለተገቢው አላማ መጠቀም አለመቻላቸው ለቀውስ እንደዳረጋቸው በሪፖርቱ የተጠቆመ ሲሆን በዚህ ረገድ ጋና ምሣሌነት ተጠቅሳለች፡፡ ሌሎችም አዋጭ የሆነ የብድር አመላለስ ስርአት ባለመከተላቸው የችግሩ ሠለባ እየሆኑ እንደመጡ የጠቆመው ሪፖርቱ፤ እነዚህ ሀገራት ከዚህ እዳ የሚወጡበትን መንገድ ካላጤኑ ከፍተኛ ቀውስ ሊገጥማቸው ይችላል ብሏል፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ የግል ኩባንያዎችና መንግስታት አለም ባንክን ከመሳሰሉ አበዳሪ ተቋማት ከ2009 እ.ኤ.አ ጀምሮ በየአመቱ የሚበደሩት ገንዘብ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ነው ተብሏል፡፡ በ2013 እ.ኤ.አ የአለም ሀገራት አጠቃላይ የብድር መጠን 11.3 ትሪሊዮን ዶላር ሲሆን በ2014 13.8 እንዲሁም በዘንድሮው አመት 14.7 ትሪሊዮን ዶላር መሆኑን ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡ 
የአዲስ አድማስ ጋዜጣን ዘገባ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ።


ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
ሐምሌ 11/2007 ዓም (ጁላይ 18/2015)

Thursday, July 16, 2015

Thursday, July 9, 2015

Ethiopia - Out of over Hundred thousands of political prisnors less than ten of them are released. Doese it give sence to Ethiopians and International Community? ''በኢትዮጵያ በስድስት የፌድራል፣በአንድ መቶ ሃያ የክልል እና በአያሌ ድብቅ እስር ቤቶች ውስጥ ከመቶ ሺህ በላይ እስረኞች ይገኛሉ'' ዓለም አቀፍ የእስረኞች ጥናት ማዕከል።ከእነዚህ ውስጥ ከአስር ያነሱትን መፍታት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ምን አይነት ስሜት ይሰጠዋል? የእስረኞቹስ ጥያቄዎች ተመለሱ?






ኢትዮጵያ በስነ-መንግስት ታሪክ ፍርድ እና ፍትህ አዋቂ መሪዎች የምታውቅ ሀገር ነበረች።የቀደመውን በሙሉ ጥላሸት ቀብቶ የመኖር ስልት የሚከተለው በስልጣን ላይ የሚገኘው ጎጥን መሰረት ያደረገ መንግስት ወደ ስልጣን ሳይመጣ  በፊት በነበሩት ዘመናት ውስጥ ሁለት አይነት ዘመናትን ማሳለፋችንን ለማወቅ ይቻላል።አንደኛው የዘመናዊው የፍትህ ስርዓት ሳይተዋወቅ ሲሆን ሁለተኛው ዘመናዊው የፍትህ ስርዓት ከተዋወቀ በኃላ ያለው ነው።እዚህ ላይ ''ዘመናዊ'' ምን ማለት ነው? ''ዘመነ'' ለማለት መስፈርያዎቹ ምን ምን ናቸው? የሚሉትን ጥያቄዎች ለጊዜው አቆይተናቸው ነው። 

በቀደሙቱ እንበል እስከ ሃያኛው ክ/ዘመን መግቢያ ድረስ የፍትህ ስርዓት መሰረት የሚያደርገው ሶስት ነገሮችን  ነው።እነርሱም  ሃይማኖታዊ መሰረት፣ የስልጣን መዋቅር እና የተፈጥሮ ክህሎት ናቸው።ሕዝብ ፍርድ ሲፈልግ ወደ ሃገረ ገዢው፣የሃይማኖት አባት ወይንም ወደ ተፈጥሮ ክህሎት  ወደታደሉት የሀገር ሽማግሌዎች ይሄዳል።ከእነኝህ ውስጥ ግን የማሰር እና የመፍታት ስልጣን ያለው የአካባቢው ሀገረ ገዢው ሲሆን ሃገረ ገዢው የፈረደው ፍርድ ያልተስማማው ወደ ወረዳ ሃገረ ገዢው ከዝያም ማለፍ ከፈለገ ቀን ጠብቆ እስከ ንጉሡ ድረስ  አቤቱታውን የማድረስ ሁኔታ ነበር።ይህ ማለት ወቅቱ ፍርድ ያልተገመደለበት ነው አልያም ጥቂቶች በገዛ ስልጣናቸው ፍርድ አላጣመሙም ማለት አይደለም።አሁን ኢህአዴግ/ወያኔ ከሚሰራው የማን አለብኝነት ተግባር ጋር ስናነፃፅረው ግን የህሊና ዳኝነትን እና ይሉኝታን  ፈፅሞ ከግንዛቤ ያላስገባ የፍትህ ሂደት ያየነው በእዚሁ ስርዓት ነው።

ለምን እንደታሰሩ ያላወቁት እንዴት እንደተፈቱም አልተነገራቸውም 

ለምን እንደታሰሩ ያላወቁ፣በድንገት ሲፈቱም እንዲሁ ለምን እንደተፈቱ ያልተነገራቸው፣ከእድሜያቸው አስፈላጊ የነበረውን
 የወጣትነት ጊዚያቸውን አሳልፈው ከእስር የተፈቱት ኤዶም ካሳዬ፣ ዘላለም ክብረት፣ አስማማው ሃይለጊዮርጊስ፣ ተስፋለም ወልደየስ
 አራጌ ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ ርዕዮት ዓለሙ እና ምናልባትም ከሰሞኑ ለሚፈቱት ሁሉ ደስታን ለመግለፅ የግድ በእስር ቤት ውስጥ 
ማለፍን አያስፈልግም።ለቤተሰብ እና ለወዳጅ ዘመድ ቀርቶ ለማንም ኢትዮጵያዊ የተፈፀመባቸው ግፍ ልብ ያደማል።ኢህአዴግ/ወያኔ
 ሀገር ሲያሸብሩ፣በውጭ ሀገር መሰረታቸውን ካደረጉ ኃይሎች ጋር ሲፃፃፉ አገኘሁ፣ኢ-ሜይላቸውን ስከፍተው እገሌን ሰላም አሉ እና 
የመሳሰሉትን እያነሳ ፍርድ ቤት አንገላታቸው።ለምሳሌ የዞን 9 ጦማሪዎችን ከ30 ጊዜ በላይ ፍርድ ቤት አመላልሷቸዋል።

በወጣቶቹ ላይ ከተፈፀሙት ግፎች ውስጥ ማህሌት ፋንታሁንን  በእኩለ ሌሊት እየጠሩ  እራቁቷን ሆና አይኗ ተሸፍኖ እያሸማቀቁ እና ፀያፍ ስድብ እየሰደቡ ያልሰራችውን በግድ እንድትፈርም አድርገዋታል።ርዕዮት አለሙ ከደረሰባት የእስር ቤት ስቃይ በተጨማሪ የይቅርታ ደብዳቤ እንድትፈርም ብዙ ፈተና ደርሶባታል፣የጡት ህመም ገጥሟት ሕክምናውን እንዳታገኝ ተደርጋለች።የእስር  ጊዜዋ ባለፈው ጥቅምት ላይ ያለቀ ቢሆንም በእስር እንድትቆይ ቤተሰብ እንዳይጎበኛት ተደርጋ ቆይታለች።

ፍርድ ቤት ነፃ ያለውን ከመንገድ ጠብቀው ያስሩታል።አንድ ቀን የጦርነት ፊልም በአግባቡ አይቶ የማያውቅ የዋህን  ቦንብ ሊያፈነዳ ሲል ያዝነው ብለው እስር ቤት ይወረውሩታል።ሲታሰሩ ያማያውቁ፣ለምን እንደታሰሩ ያልተነገራቸው፣ሲፈቱም ድንገት ተጠርተው ''ዕቃህን ሰብስበህ ወደ ቤት ሂድ'' ተብለው በግልምጫ የሚነገርባት ምድር ኢትዮጵያ ነች።የወጣትነት ጊዜውን በእስር ቤት ያቃጠለ፣ለምን መጀመርያ በሐሰት ከሰሳቹህኝ? ብሎ መጠየቅ የማይቻልባት ሀገር ነች ኢትዮጵያ። ቤተሰብ እንዳትመጣ ሲባል የሚቀርባት፣ና! ሲባል የሚሄድባት፣ለዓመታት በእስር ቤት ልጁ ሲሰቃይ ኖሮ በድንገት ልጅህን ውሰድ ሲባል የሚወስድባት ነች ኢትዮጵያ።

እንደ ዓለም አቀፍ የእስረኞች ጥናት መረጃ  (http://www.prisonstudies.org) መሰረት ኢትዮጵያ ብዙ ሺዎች አሁንም በእስር ቤት የሚማቅቁባት ነች። እዚህ ላይ ስለ እስረኞች ስናወራ የፖለቲካ እስረኞችን እንጂ በወንጀል ምክንያት የታሰሩትን እያወሳሁ አለመሆኑን ልብ በሉልኝ።ከእዚህ በታች በኢትዮጵያ የሚታወቁ  (በርካታ የድብቅ እስር ቤቶች መኖራቸውን መረጃውም ይጠቅሳልና) የእስረኞችን ቁጥር ያስቀምጣል።መረጃው በእራሱ ደግሞ ውሱንነት እንደሚኖርበት ስናስብ የእስረኞች ቁጥር ከእዚህ በእጅጉ የበለጠ መሆኑን እንረዳለን።ይህ በእንዲህ እንዳለ ይህ ፅሁፍ ሲፃፍ በእስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞችን በመጠኑ ለመዘርዘር ልሞክር።እዚህ ላይ ከአምቦ ግጭት እሰከ ወልቃይጥ፣ከግምቢ ወለጋ እሰከ ኡጋዴን እና አፋር አያሌዎች በእስር ላይ መሆናቸውን መዘንጋት አይገባም።በመሆኑም ከእዚህ በታች የተዘረዘሩት ከማህበራዊ ድረ-ገፅ አበበ ቶላ ላይ የተወሰደ ብቻ መሆኑን አንባቢ ሊገነዘብ ይገባል።

1 - ተመስገን ደሳለኝ 
2- እስክንድር ነጋ 
3- ናትናኤል መኮንን 
4- አንዳለም አራጌ
5- ውብሽት ታዬ
6- አበበ ቀስቶ
7- ሃብታሙ አያሌው
8- ዳንኤል ሺበሺ
9- አብርሃ ደስታ
10- የሽዋስ አሰፋ
11- ዘላለም ወርቅአገኘሁ
12- አቤል ዋበላ
13- ናትናኤል ፈለቀ
14- በፍቃዱ ሃይሉ
15- አጥናፍ ብርሃኔ
16- ፍቅረማርያም አስማማው
17- እየሩሳሌም ተስፋው
18- ብርሃኑ ተክለያሬድ
19- ኦልባና ለሌሳ
20- ቴድሮስ አስፋው
21- ማትያስ መኩርያ
22- ብሌን መስፍን
23- ተዋቸው ደምሴ
24- ንግስት ወንዳፈራሁ
25- ሜሮን አለማየሁ
26- ደሴ ካህሳይ
27- ናትናኤል ያለምዘውድ
28- ሰንታየሁ ቸኮል
29- ማስተዋል ፈለቀ
30- ንግስት ወንድይፍራው
31- ሂሩት ክፍሌ
32- እማዋይሽ አለሙ
33- ሰለሞን ከበደ
34- የሱፍ ጌታቸው
35- አቡበከር አህመድ
36- አህመዲን ጀበል
37- ያሲን ኑር
38- ካሚል ሸምሱ
39- በድሩ ሁሴን
40- ሼህ መከተ ሙሄ
41- ሳቢር ይርጉ
42- መሐመድ አባተ
43- አህመድ ሙስጠፋ
44- አቡቡከር አለሙ
45- ሼህ ሙኒር ሁሴን
46- ሰኢድ አሊ ጁሃር
47- ሙባረክ አደም
48- ካሊድ ኢብራሂም
49- ሙራድ ሽኩር
50- ኑር ቱርኪ
51- ሼህ ባህሩ ኡመር
52- አንዳርጋቸው ጽጌ
53- ጀነራል ተፈራ ማሞ
54- ጀነራል አሳምነው ጽጌ
55- ኮነሬል አለሙ መኮንን


በኢትዮጵያ ያሉት እስረኞች ብዛት በመቶ ሺዎች የሚቆጠር መሆኑን እና በኢህአዴግ/ወያኔ ዘመን እንዴት እያደገ እንደመጣ የዓለም አቀፍ እስረኞች ጥናት ማዕከል ኢትዮጵያ ውስጥ እስከ አለፈው ዓመት ድረስ የሚገኙ እስረኞችን ቁጥር ያወጣበት ዘገባ  ዓለም አቀፍ የእስረኞች ጥናት ማዕከል International  Center for Prisnors Study (ICPS) ይመልከቱ።

በመጨረሻም ለማጠቃለል ማንም የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኝ የሚል ሰው ሊገነዘበው የሚገባው።ከእስረኞች መታሰር እና መፈታት ባለፈ እስረኞቹ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ የጠየቁት ጥያቄ ምላሽ አገኘ ወይ? የሚለው ቁልፍ ጥያቄ ነው ሊሰመርበት የሚገባው።ስርዓቱ የስልጣን መቆያ መንገድ ያደረገው የጎሳ ፖለቲካ ፖሊሲ ተቀየረ? ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል አለ? የዲሞክራሲ ጥያቄው ተመለሰ? በምርጫ መንግስት መቀየር እንችላለን? ወይንስ ዛሬም 100% እየተባለ እየተቀለደ ነው? የፍትህ ስርዓቱ ምን ያህል ነፃ ነው? አንድ ዜጋ ምን ያህል የፍትህ ስርዓቱ ላይ ይተማመናል? ምጣኔ ሃብቱ፣የፖለቲካ ስልጣኑ፣የወታደራዊ አመራሩ ሁሉ በአንድ ጎጥ ስር ነው ወይንስ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል ያሳትፋል? እና ሌሎች ቁልፍ ጥያቄዎች ከእስረኛ መፍታት እና ማሰር ሂደት በላይ የገዘፉ እና ለእስሩ ዋነኛ እና ቁልፍ ምክንያቶች ናቸው።ርትዮት የታሰረችው፣እስክንድር ወህኒ የወረደው ሌሎች አያሌዎች ፍዳ የሚቀበሉበት ጉዳይ ከላይ በመጠኑ የተጠቀሱት እና ሌሎች ጉዳዮች ናቸው።

ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
ሐምሌ 2/2005 ዓም (ጁላይ 9/2015)

ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።