ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, March 31, 2020

ጉዳያችን ዜና በ7 ደቂቃዎች - የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር እና ጠ/ሚ/ር ዓቢይ ተገናኙ፣በሱማሌ ሁለት የኢትዮጵያ ወታደሮች ተገደሉ ፣ደቡብ ሱዳን ተማሪዎች ከኢትዮጵያ አይወጡም

መጋቢት 22/2012 ዓም
============
https://www.youtube.com/watch?v=6JLgVegaGhY
ማሳሰቢያ - ከላይ የተዘገበውን ዘገባ የስቴት ዲፓርትመንት በሌላ ዜና ቀይሮታል።
ሰበር ዜና - ስቴት ዲፓርትመንት ዜናውን ቀየረው። የአሜሪካው ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ጋር ተገናኙ የሚለው ዜና፣በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ቀይሮታል!?

ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

Thursday, March 26, 2020

Tuesday, March 24, 2020

Corona-virus in Ethiopia ኮሮና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ሊያናጋ፣አገር ሊያፈርስ ይችላል።ጉዳዩ ከጤና በላይ ነው።እንዴት? መፍትሄውስ ምንድነው?

ለማዳመጥ ሊንኩን ይጫኑ


ጉዳያችን ሚድያ፣ኮሚኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት 
Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant

Monday, March 23, 2020

Sunday, March 22, 2020

የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች በመላው ዓለም ከሩብ ሚልዮን አልፏል።በሽታው በአስፈሪ ደረጃ እየጨመረ ነው።በኢትዮጵያ ሕዝቡን ከማንቃት ጎን አስገዳጅ ሕግም ያስፈልጋል።የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች ላይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች አሉ።



ጉዳያችን ሚድያ፣ኮሚኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት 
Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን አስመልክቶ የዓለም ጤና ድርጅት በሚያወጣው ወቅታዊ መረጃ መሰረት የተጠቂዎቹ ቁጥር ሩብ ሚልዮን አልፏል።የመጨመሩን ፍጥነት ለመረዳት ባሳለፍነው ሳምንት  በሐሙስ እና በዓርብ መሃል ብቻ 32 ሺህ ሕዝብ አዲስ ተጠቂ ሪፖርት የተደረገ ሲሆን በዓርብ ዕለት ከነበረው ቅዳሜ ዕለት በ26 ሺህ አዲስ ታማሚ ቁጥር ማደጉን ነው የዓለም ጤና ሪፖርት የሚያሳየው።በመሆኑም የዓለም ጤና ድርጅት እስከ ቅዳሜ መጋቢት 12/2020 ዓም ድረስ ወረርሽኙን አስመልክቶ የሚያሳየው ሪፖርት በዓለም ላይ በሽታው እንዳለባቸው የተረጋገጠው 292,142 ሰዎች ሲሆኑ፣ በሞት የተለዩ =12,784 (ከእነኝህ ውስጥ 1600 ያህሉ በአንድ ቀን ብቻ የተመዘገበ የሞት ቁጥር ነው)።

በኢትዮጵያ ሕዝቡን ከማንቃት ጎን አስገዳጅ ሕግም ያስፈልጋል።የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች ላይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች አሉ።


በአገር ደረጃ በከፍተኛ ደረጃ ከተጠቁት ውስጥ ለምሳሌ ጣልያንን ብንመለከት በሰው ልጅ አዕምሮ ከሚታወቁትም ሆነ ከማይታወቁት ምክንያቶች ሌላ በመጀመርያ ደረጃ የበሽታውን አደገኛነት በሚገባ አለመረዳት እና ችላ ማለት አንዱ ምክንያት መሆኑን በጣልያን ያሉ ኢትዮጵያውያን ሳይቀሩ እያስገነዘቡት ያለ ጉዳይ ነው።

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ መንግስት እየወሰዳቸው ያሉ መልካም ርምጃዎች የሚበረታቱ ናቸው።የትምህርት ቤቶች መዘጋት፣የመገናኛ ብዙሃን ትኩረት መስጠት፣የቴሌ እና የእምነት አካላት ውሳኔ ሁሉ ጥሩ ነው።ሆኖም ግን ከአደጋው አንፃር  አሁንም የሚቀሩ ጉዳዮች አሉ።በተለይ በሕዝቡ ዘንድ ያለው ግንዛቤ አሁንም የሚቀር ጉዳይ እንዳለ ለመረዳት በዩንቨርስቲ ደረጃ ያሉ መረጃውን በደንብ ያገኛሉ የተባሉ ሳይቀሩ ቸልተኝነት ሲያሳዩ መስማት ያስደነግጣል።ባሳለፍነው ቅዳሜ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ዜና ላይ በዩንቨርስቲ ዙርያ ያለውን ሁኔታ በዳሰሰ አንድ ዘገባ ላይ የደብረ ታቦር ዩንቨርስቲ መምህር ሲናገሩ ''እኛ ተማሪዎች ሲቀመጡም ሆነ ሲመገቡ ተራርቀው መቀመጥ እንዳለባቸው ስንነግራቸው እኛ ተለያይተን አናውቅም።ስንበላም ብቻችንን በልተን አናውቅም'' የሚል ምላሽ ማግኘታቸው አንዱ ለቸልታው ማስረጃ ነው።

እዚህ ላይ በዩንቨርስቲ ተማሪ ደረጃ ጥንቃቄው በእዚህ ደረጃ ከተገለጠ። በሌላው ሕዝብ ዘንድ በሚድያ ከምናየው በላይ ምን እያለ እንደሆነ ለማወቅ ቀላል ነው። በሌላ በኩል ወረርሽኙ ከውጭ እንደመምጣቱ፣የውጪ አገር ዜጎች የሚያዘወትሩባቸው የቱሪስት መዳረሻ አካባቢዎች እና በእዚያ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች እና የንግድ ቦታዎች ሁሉ ተገቢው ምርመራ ማድረግ እና  ቦታዎቹ ለውጪ ዜጎች ዝግ ማድረግ ተገቢ ነው።

አሁን ባለበት ሁኔታ ግን የማስተማሩን እና ሕዝቡን የማንቃት ሥራ ከመቀጠል ጎን ከጎን አስገዳጅ ሕግም ማውጣት አስፈላጊ ነው። የእዚህ አይነት ሕግ በአውሮፓ፣አሜሪካም ሆነ በራሷ በቻይናም የተተገበረ ነው።ለምሳሌ ወረርሽኙን ተከትሎ  መንግስት ለምያወጣው የመንቀሳቀስ ገደብ፣የጥንቃቄ አወሳሰድ ደንቦች፣የተሳሳቱ መረጃዎች በበሽታው ዙርያ ማሰራጨት እና  የዋጋ መጨመርን በተመለከተ ሁሉ በልዩ ቅጣት ስር ማካተት ካልተቻለ አንዳንዱ ራሱን መጠበቁ ክግዴታ ሳይሆን ከበጎ ፈቃድ  እና የራስ መብት አንፃር እያየው ቸልተኝነቱ እየበዛ ለሌሎች የማስተላለፍ አደጋው እንዳይጨምር ያሰጋል።ይህ ደግሞ አገራችንን ማቅ የሚያለብስ ብሔራዊ ሃዘን እንዳያለብሳት፣የመስርያው እና የመወሰኛው ጊዜ አሁን ነው።  


Friday, March 20, 2020

በኮሮና ቫይረስ ሳብያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት አገልግሎት እንዳይታጎል ቴክኖሎጂ መጠቀም!


የጉዳያችን ወቅታዊ መልዕክት! ንቁ! ትጉ!

በእዚህ ጽሁፍ ስር -

+ የኦስሎ መ/ቅ/ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን የቀጥታ ስርጭት አገልግሎት የሚያገኙበት ሊንክ ያገኛሉ።
+ ምዕመናን የቀጥታ ስርጭት በቤታቸው ሲከታተሉ እንዴት ሆነው መሆን አለበት? የሚል አጭር መረጃ ያገኛሉ።

ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳብያ  ከህዝብ ንክኪ ለመታደግ እና የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በውጪ አገራት የሚገኙ የዕምነት ቦታዎች በሙሉ ምዕመናን እንዳይገኙ መደረጉ ይታወቃል።ይህ ማለት ግን ለአገልግሎቱ ሌላ አማራጭ የለም ማለት አይደለም።ከችግሩ አንፃር የቤተ ክርስቲያን አባቶች እና አገልጋይ ምዕመናን ከመቼውም ጊዜ በላይ በተቻለ መጠን ለምዕመናን አገልግሎት ለማድረስ መጣር ያለባቸው ጊዜ አሁን ነው።ይህ ካልሆነ ትልቅ አደጋ በምዕመናን ሕይወት ላይ እንደሚደቀን በጥብቅ ሊያስቡት ይገባል።ምዕመናን ከልጆቻቸው ጋር ከቤት ሲውሉ ከመንፈሳዊው ጉዳይ ይልቅ አልባሌ ነገሮች እየተመለከቱ እንዲውሉ የሚያደርግ ከባድ የመንፈስ ዝለት እንዳይደርስባቸው እና በስጋም ሆነ በመንፈስ እንዳይጎዱ አብያተ ክርስቲያናት አገልግሎቱን በቀጥታ ስርጭት እንዲደርሳቸው ማድረግ አለባቸው።

ምዕመናን የቀጥታ ስርጭት እንዴት መከታተል አለባቸው?


ማሳሰቢያ = ከእዚህ በታች ያለው የጉዳያችን የግል ሃሳብ እንጂ የቤተ ክርስቲያን ስርዓት አንቀፅ እየተጠቀሰ የተፃፈ አይደለም።ነገር ግን የእንዲህ አይነት አዲስ ነገር ሲገጥም ቀድሞ መንገዱን ከማመልከት አንፃር ብቻ የተጠቆመ ነው።


ምዕመናን በቤታቸው የቀጥታ የቤተ ክርስቲያን የአገልግሎት  ስርጭት ሲከታተሉ የሚከተሉትን ነጥቦች መዘንጋት የለባቸውም።እነርሱም -


1) ተግተው እና ነቅተው መከታተል 

የቀጥታ ስርጭቱ ለምሳሌ ትምህርት፣ምህላ፣ወይንም ቅዳሴ ሲሰራጭ ቤታቸው ያሉ ሌሎች ሚድያዎች ማለትም ቴሌቭዥን፣ስልክ እና የመሳሰሉትን አጥፍቶ በህሊና ቤተ ክርስቲያን እንዳሉ አድርጎ መከታተል።ቅዳሴው እና ምህላውን ቢችሉ ከቤተሰብዎ ጋር ጫማ አውልቆ ስዕለ መድኃኔዓለም ወይንም ቅዱሳን ፊት ቆሞ በአንቃዕዶ ህሊና ልክ ቤተ ክርስቲያን እንዳሉ አድርጎ መከታተል።

2) ከቤተሰብ ጋር ቀድሞ መወያየት

የቀጥታ ስርጭቱ ሲደረግ ቤት ውስጥ እንዴት መሆን እንዳለበት ቀድሞ ከቤተሰብ ጋር መምከር።ለምሳሌ ከእዚህ በፊት ከቤተሰብ ውስጥ ቤተ ክርስቲያን አዘውትሮ መሄድ ልማድ የሌለው ሰው ዛሬ ቆመህ አስቀድስ ወይንም ምህላ ቁም ማለት ሊከብደው ይችላል።ስለሆነም  በበጎ ህሊና ቀድሞ መነጋገር ካልቻለ አጭሩን የቀጥታ ስርጭት ጊዜ ቴሌቭዥን በማጮህ ወይንም በሌላ እንዳይረብሽ መነጋገር፣መቆም ካልቻለ ተቀምጦ እንዲከታተል መምከር ይህም ካልተቻለ ልጆች እና ከቤተሰቡ ፈቃደኛ የሆኑት በሚከታተሉበት ጊዜ ቢቻል ሌላውን የቤት ሥራ እያገዘ እንዲቆይ  ወይንም ሌላ አማራጭ ላይ  መመካከር።ሁሉ በፍቅር መሆን ስላለበት እንጂ በተቻለ ከቤተሰቡ ማንም ሳይነጠል በኅብረት አገልግሎቱን መካፈል በረከት  ስላለው  በተቻለ መድከም የሚገባው በህበረት መሳተፉ ነው።

ለማጠቃለል፣ይህ የፈተና ጊዜ ነው።ስለሆነም በፈተና ጊዜ የበለጠ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እና ያሉትን  አማራጮች ሁሉ ተጠቅሞ መትጋት ይገባል።ይህ ካልሆነ ሰይጣን የበለጠ የምያሰንፍበትን መንገድ እንደሚያስብ አውቀን ለእያንዳንዱ የቀጥታ ስርጭት ህሊናችንን ሰብስበን መከታተል፣ቤተሰባችንንም ሆነ ልጆቻችንን ከመንፈሳዊው አገልግሎት እንዳይርቁ ልንጠነቀቅ ይገባል። በሌላ በኩል ከእዚህ በፊት ቤተ ክርስቲያን ሄደን ለመገልገል ዕድሉን በተለያየ ምክንያት ያላገኘን፣ እግዚአብሔር እቤታችን ድረስ መጥቶ ሲፈልገን እኛ ኮምፑተር ከፍተን ለመገልገል ሰንፈን ከተኛን የራሳችን ስህተት መሆኑን ልንረዳ ይገባል።

በኦስሎ መካነ ቅዱሳን ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የቀጥታ ስርጭት የሚኖርባቸው ሰዓታት እና ቀን ከእዚህ በታች ይመልከቱ።

1) በዓቢይ ፆም ወቅት ዘወትር ረቡዕ እና ዓርብ በኦስሎ ሰዓት ከ17 ሰዓት (5pm) ጀምሮ የምሕላ ጸሎት
2) ዘወትር ዕሁድ ማለዳ  በኦስሎ ሰዓት አቆጣጠር ከ7 ሰዓት (7am) ጀምሮ የቅዳሴ ስነ ስርዓት የሚተላለፍ ሲሆን
ሁሉንም ለመከታተል በእዚህ ድረገጽ ከፍተው መከታተል ይችላሉ።

ድረ ገፁ http://www.eotcnor.no/  ወይንም 
http://www.eotcnor.no/live   የሚለውን ቢጫኑ መክፈት ይችላሉ።



ጉዳያችን ሚድያ፣ኮሚኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት 
Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant

Wednesday, March 18, 2020

በቅርቡ የተመሰረተው እና ከፍተኛ የወጣት ስብስብ እንዳቀፈ የተነገረለት እናት ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ አወጣ ሙሉ መግለጫውን ይዘናል።

Image result for enat party gudayachn
መጋቢት 07/ 2012 ዓ.ም

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የእናት ፓርቲ የአቋም መግለጫ

ተያይዘን እንድንድን እንጂ ተያይዘን እንዳንጠፋ ሁሉም የድርሻውን ይወጣ!

የኖቭል ኮሮና ቫይረስ (COVID-19) በአንድ የውጭ አገር ዜጋ አማካይነት ኢትዮጵያ ውስጥ መግባቱን እና የተጠቂዎችም ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የጤና ሚኒስቴር ባወጣው ይፋዊ መግለጫ አሳውቋል፡፡ ምንም እንኳ መንግሥት የዘገየ ቢሆንም ከዛሬ መጋቢት 07 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለ15 ቀናት በመላ ሀገሪቱ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችና ትላልቅ ስብሰባዎች እንዳይካሄዱ መወሰኑ አግባብነት አለው እንላለን። ይህ ወረርሽኝ ለአደጉት ሀገራት እንኳን ምን ያህል ፈታኝ እንደሆነ፣ በሽታውን ይከላከላሉ ተብለው የተቋቋሙ ተቋማት ሓላፊዎችንና ቤተሰቦቻቸውን ጭምር በማይታመን ሁኔታ እየተያዙ እንደሆነ ዐይተናል፣ ሰምተናል፡፡ ይህ ለእንደኛ ዓይነት በምጣኔ ሀብት እድገትና አኗኗር ባህላችን ተጋላጭ ሀገራት ምን ያህል ከባድና ውስብስብ ሊሆን እንደሚችል ማሳያ ነው፡፡ በፖሊሲያችንና ቀረቤታችን ምክንያት “አትምጡ፣ ቅሩብን!” ማለት የሚቻለን ባይሆንም ከመጡ በኋላ ግን አስፈላጊው ክትትል ተደርጓል ብለን አናምንም፡፡ ከጦር መሣሪያ በላይ አውዳሚ የሆነን ችግር እሱን “ተከታተልንበት” ካልነው ጉዞ ያነሰ እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡   

የሆነው ሆኖ "ችግር ብልሃትን ይወልዳል" እንዲሉ በእንዲህ ዓይነት ፈታኝ ወቅት ሀገርኛ መፍትሄዎችን እነ አባ መላን ይዞ መሻት፣ በዘርፉ የተማሩ ምኁራንን ወደ መድረክ በማምጣት ቀላል፣ የታሰበባቸውና አዋጭ መፍትሔዎችን እንዲጠቁሙ ማድረግ ይገባል፡፡ በየትኛውም ዓለም ኑሮን ለማሸነፍ የሚኖሩ ጠያቂ የሌላቸው ኢትዮጵያውያንን፣ በተለየ ሁኔታ ተጋላጭ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ይበልጥ ጥበቃ እንዲያገኙና ሲጎዱ ፈጥኖ መድረስ ተገቢነቱ ለነገ የሚባል አይደለም፡፡ የማኅበረሰብ አንቂዎችና መገናኛ ብዙኃን ተነሳሽነቱን በመውሰድ የተጠናና በባለሙያ የታገዘ ትንታኔ፣ ማስጠንቀቂያዎችንና የተረጋገጡ ዜናዎችን በማቅረብ የዘመቻ ሥራ መሥራት ለነገ የማይባል ሥራ ነው፡፡ የሃይማኖት አባቶቻችን በእንዲህ ያሉ ፈታኝ ወቅቶች ፈጣሪ ቁጣውን በምኅረት እንዲመልስ፣ ከጭንቁ የመወጫ ጥበቡን እንዲያመላክተን የጋራ ጸሎት በማወጅ የተጀመረው ጥረት በሁሉም ዘንድ ተጠናክሮ እንዲቀጥል፣ በየትኛውም ደረጃ የሚጎዱ ሰዎችን ለማገዝ ተከታዮቻችሁን ማነሳሳት ይገባል። 

በሌላ በኩል በእንዲህ ያሉ ጭንቅ ወቅቶች ተጠግተን የምንጸልይባቸው ቤተ እምነቶች ጥቃት አለፍ ሲልም ውድመት ባልተለመደ መልኩ መባባስ እናት ፓርቲን ያሳስባታል፡፡ ልንደኸይ፣ ልንራብ፣ ልንጠማ እንችላለን፡፡ ኢትዮጵያውያን መንፈሳችን ግን እንዴት ሊወሰድ ይችላል? ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን ሀብት ተርፏቸው፣ ሞልቷቸውና ደልቷቸው፣ ካለው ላይ ዘግነው መሣሪያ ገዝተው አይደለም ዘምተው ድል የነሱት፡፡ ይልቅ ተዝቆ የማያልቀውን የአሸናፊነት መንፈሳቸውን መንዝረው ነው ታሪክ ያቆዩልን፡፡ ይህ ከተወሰደብን በእውኑ ምን ይቀረናል? እየጠፋብን አልያም እየተወሰደብን ለመሆኑ ከምልክቶቹ አንዱ የሆነው እየታየ ነውና ያገባኛል በሚል ቁጭ ብለን ብንነጋገር መልካም ነው እንላለን፡፡ ስለሆነም በቅርቡ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ሞረት እና ጅሩ ወረዳ፣ እነዋሪ ከተማ የሙሉ ወንጌል ቤተ ጸሎት ቃጠሎ ከዚህ ለይተን አናየውምና በጥብቅ እናወግዘዋለን፡፡ ቆስቋሽ ምክንያቶች የሚባሉትን የአካባቢው የመንግስት ተሿሚዎች በመነጋገር እንዲፈቱና ጉዳዩ በሕግ አግባብ እንዲዳኝ ማድረግ ሲገባ ዳር ቆሞ በማየት የሆነው እንዲሆን በማድረጋቸው የራሳቸውን አስተዋጽዖ አበርክተዋል ብላ እናት ፓርቲ ታምናለች ፡፡ 
በአጠቃላይ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ማኅበረሰብ አንቂዎች፣ ሲቪክ ተቋማት፣ ምሁራን፣ የመገናኛ ብዙኃን ሓላፊዎችና ሙያተኞች፣ ይልቁንም መንግስትና የፖለቲካ ፓርቲዎች "ሳይቃጠል በቅጠል" ነውና በእንዲህ ያሉ የፈተና ወቅቶች ልዩነትን ወደጎን በመተው ተያይዘን እንድንድን እንጂ ተያይዘን እንዳንጠፋ በጋራ እንሥራ በማለት ጥሪዋን ታቀርባለች - እናት፡፡   

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን በቸርነቱ ይጠብቅልን!
እናት ፓርቲ

መጋቢት 07/2012 ዓ.ም





ጉዳያችን ሚድያ፣ኮሚኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት 
Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant

Monday, March 16, 2020

የግብፅ ፓርላማ ዛሬ ማክሰኞ በዓባይ ግድብ ዙርያ ለመነጋገር ድንገተኛ ስብሰባ ጠርቷል።

በእዚህ ዜና ውስጥ በተጨማሪ እነኝህ ሦስት ነጥቦች ላይ መረጃ ያገኛሉ።
  • የግብፅ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሳማህ ሐሰን ሽክሪ ማን ናቸው? 
  • የአረብ ሊግ ተከፋፍሏል 
  • ዲፕሎማሲው ያልሰራላት ግብፅ ቀጣይ ስልቷ ምንድነው?
=================
በግብፅ ፓርላማ የውጪ ጉዳዮች ኮሚቴ ሰብሳቢ ካሪም ሐሰን የግብፅ ፓርላማ ዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 8/2012ዓም ስብሰባ እንደጠራ ለግብፅ መገናኛ ብዙሃን ገልጠዋል። የፓርላማው ዋና የውይይት ጉዳይ በግድቡ ዙርያ  መሆኑን እና በተለይ ግድቡን በመገንባት ላይ ያሉ የውጪ ኩባንያዎች ላይ ቀጥተኛ እቀባ ለማድረግ መሆኑን እኚሁ የፓርላማ የውጪ ጉዳዮች ኮሚቴ ሰብሳቢ አብራርተዋል።በእዚህ መሰረት በኢትዮጵያ በዓባይ ግድብ ላይ የተሳተፉ ኩባንያዎቹ ግብፅ ውስጥ የስራ ውል ካላቸው  መንግስታቸው  እንዲያቆሙ እንዲያደርግ  እና ወደፊትም ሌላ የስራ ውል ግብፅ ውስጥ እንዳይሰጣቸው ለማድረግ ያለመ ስብሰባ ነው።

ስብሰባው እንዲጠራ ያደረጉት የፓርላማ አባላት ናቸው ያሉት የውጪ ኮሚቴው ሰብሳቢ ስብሰባው በተጨማሪ የዓለም ባንክ እና ሌሎች አበዳሪ አገሮች  ኢትዮጵያ በአሜሪካ የቀርበላትን ሰነድ እስካልፈረመች ድረስ ለኢትዮጵያ የሚሰጡትን ብድር እንዲያቆሙ የመጠየቅ ዓላማ እንዳለው ገልጠዋል።ይህ ስብሰባ የግብፁ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰሞኑን ከላይ ታች የሮጡበትን የዲፕሎማሲ ሩጫ ጉዳይም ይገመግማል።ግብፅ ከእዚህ በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዘመንም ለኢትዮጵያ ብድር እንዳይሰጡ የዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን እንዲሁም መንግስታትን ስትወተውት እንደነበር እና ልፋቷ ሁሉ መና እንደቀረ ይታወቃል።በእዚህ ወቅት ይህንን ማንሳቷም ፍሬ የሚያፈራ አይደለም።ምክንያቱም ኢትዮጵያን የአፍሪካ መግብያ በር በማድረግ አዳዲስ ኢንቨስትመንት ለመጀመር እቅድ የያዙ የምዕራብ አገሮች ኢትዮጵያን በእዚህ ወቅት ብድር በመንፈግ በጥቅማቸው ላይ ይቆማሉ ብሎ ማሰብ አይቻልም።በዛሬው እለት ሳይቀር ፋይናንሻል ታይምስ አሜሪካ በኢትዮጵያ የስኩዋር ኢንዱስትሪ ውስጥ በመግባት የቻይና ሚናን መጋፋት እንዳሰበች ፅፏል።ይህ ማለት ቻይናን ከገበያ ለማስወጣት የምዕራቡ ዓለም ሩጫ ላይ ባለበት ወቅት የግብፅ ፓርላማ ውሳኔ ውሃ የሚያነሳ አይሆንም። 

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን የግብፅ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሳማህ ሐሰን ሽክሪ  ከመካከለኛው ምስራቅ እስከ ፈረንሳይ ድረስ የኢትዮጵያን ግድብ እንዳይደግፉ ሰፊ የዲፕሎማሲ ሥራ ላይ ተሰማርተው ሰንብተዋል።ሚኒስትሩ ካደረጉት ጥረት አንፃር ያገኙት ውጤት ምንድንነው? ተብሎ ቢገመገም ግን ከአረብ ሊግ ''የወረቀት ነብር'' የሆነ የተለመደ ያልሰለጠነ መግለጫ ባለፈ የረባ ምላሽ ከአገራቱ አላገኙም። 

የግብፅ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሳማህ ሐሰን ሽክሪ ማን ናቸው? 



የግብፅ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሳማህ ሐሰን ሽክሪ  በዲፕሎማሲ ዘርፍ ልምድ እንዳላቸው ይነገራል።እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ጥቅምት 20/1952 ዓም እንደተወለዱ የሚነግርላቸው  የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሳማህ ሐሰን ሽክሪ በግብፅ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ ሥራ የጀመሩት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1976 ዓም  እንደነበር ጉዳያችን ባደረገችው አጭር ዳሰሳ ለመረዳት ችላለች።ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ በግብፅ ውጭጉዳይ ሚኒስቴር  ለሁለት ዓመት ከሰሩ በኃላ በለንደን የግብፅ ኢምባሲ ሶስተኛ ፀሐፊ ሆነው ተመደቡ።በመቀጠል በ1984 ዓም በአርጀንቲና የግብፅ ኤምባሲ አንደኛ ፀሐፊ ሆነው አገልገዋል።በቀጣይ ዓመታት በኒውዮርክ የተባበሩት መንግሥታት ኮንሱላር፣ በቅርቡ ያረፉት የቀድሞው የግብፅ ፕሬዝዳንት ሙባርክ የመረጃ እና ክትትል ፀሐፊ፣በኦስትሪያ የግብፅ አምባሳደር፣ በጀነቭ የግብፅ አምባሳደር፣እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2008 እስከ 2012 ዓም በአሜሪካ የግብፅ አምባሳደር እና በ2014 ዓም ጀምሮ እስካሁን የግብፅ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር  ሆነዋል። እዚህ ላይ የግለሰቡ የዲፕሎማሲ ልምድ ማስተባበል አይቻልም።ከእዚህ አንፃር ኢትዮጵያ ብዙ ልትማር ይገባታል።በተለይ በዘመነ ህወሓት የሳሳው የዲፕሎማሲ የሰው ኃይሏን አሁን በተገቢው መንገድ መልሳ ማጠናከር ይገባታል።እዚህ ላይ የረጅም ጊዜ የዲፕሎማሲ ልምድ ያላቸው ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ያለውን ክፍተት ለመሙላት የሚያሳዩት ተግባር አገር አኩሪ ነው።በቅርቡ በአፍሪካ አገሮች አንፃር በኬንያ እና ዑጋንዳ ያደረጉት ጉብኝት ተጠቃሽ ነው።

ለግብፁ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ይህ ሁሉ የስራ  ልምድ ግን በኢትዮጵያ ላይ ያለሙትን ለመፈፀም የሚፈልጉትን ውጤት አላመጣላቸውም።የሚንስትሩም ሆነ የመንግስታቸው ዋና ዓላማ በዲፕሎማሲው  ረገድ ግብፅ አጋር እንዲበዛላት ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን የማስፈራራት ዓላማም ነበረው።ሆኖም  የዘመኑ ተለዋዋጭ የዓለም ሁኔታ እና ኢትዮጵያ እያሳየች ያለው ውስጣዊ አንድነት እንዲሁም ብዙ አገሮች በእዚህ ጊዜ ከኢትዮጵያ ጋር ለመጣላት ዝግጁ ያልሆኑበት በርካታ ምክንያቶች እና አፍሪካ ላይ ያላቸው ፍላጎት በኢትዮጵያ ተፅኖ ውጪ እንደማይሆን መረዳታቸው የረጅም ጊዜ ልምድ ያላቸው ዲፕሎማት ጉዳዩ ቀላል እንዳልሆነ ሳይገባቸው አልቀረም።የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ከግብፅ ጋዜጠኛ ጋር በቅርብ ባደረጉት ቃለ ምልልስ  ''የአባይ ውሃ ምንጭ ያለው  እዚህ  አፍሪካ  ነው፣ ግብፅ ግን የምትዞረው መካከለኛው ምስራቅ እና ሌሎች አገሮች ነው።ከእዚህ ይልቅ ግብፅ ብዙ ጊዜዋን ውሃው ከሚመነጭበት ከኢትየጵያ እና አፍሪካ አገሮች ጋር ጊዜ ብታጠፋ ይሻላት ነበር'' እንዳሉት ግብፅ ጊዜዋን እያጠፋች ያለችው መካከለኛው ምስራቅ እና አሜሪካ ላይ ነው።

ግብፅ የዓባይ ምንጭ የምገኝባትን አፍሪካ ትታ የማይመለከታቸውን የመካከለኛው ምስራቅ እና አሜሪካንን ስትማፀን መቅረሟ ፍሬ እንዳላመጣ ዘግይተውም ቢሆን በማውቅ ይመስላል ግብፅ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ላይ ሱዳንን ማባባል የያዘችው እና አዲስ የውይይት ጥረት እንዲጀመር፣ሱዳን የማደራደር ጥረት እንድታደርግ በሹክሹክታ መጠየቅ የያዘችው።ሱዳን አሁን ባለባት የውጪ ምንዛሪ እጥረት እና የሽግግር መንግስቱ ካሉበት በርካታ አጣዳፊ ስራዎች አንፃር ጉዳዩ እንዲረግብ መፈለግዋ  አልቀረም።በሌላ በኩል የሱዳን በአረብ ሊግ ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያን የሚያወግዝ ሰነድ ላይ አልፈርምም በማለቱ ሳውዲ አረብያ ለሱዳን ልትሰጥ ያሰበችውን ገንዘብ እንደያዘችባት ነው የተሰማው።ገንዘቡ እንዲለቀቅ ደግሞ ግብፅ ሳውዲን ለማግባባት ለሱዳን ቃል በመግባት ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር እንድታደራድራት ግብፅ አልጠየቀችም ለማለት አይቻልም።በአረብ ሊግ አንፃር ሱዳን የወሰደችው ውሳኔ ግን ትክክለኛ እና ሳይንሳዊ ውሳኔ ነው።ሱዳን ያለችው ቃል በቃል ''አፍሮ አረብ በኢትዮጵያ እና በግብፅ የግድብ ጉዳይ ፈፅሞ መግባት የለበትም።ከገባም ገለልተኛ መስመር ይዞ የማስማማት ሚና ብቻ ነው።ይህ ካልሆነ ከፍተኛ ቀውስ ከመፍጠሩ በላይ ራሱ የአረቡ ዓለምን የሚከፋፍል አደገኛ ሁኔታ ይፈጥራል።የሌሎች ኃይሎችንም ይጋብዛል'' ነበር ያለችው። ይህ አባባል በረጅሙ ብተነተን ለሱዳን ትክክለኛ አባባል ራሱን የቻለ መፅሐፍ ይወጣዋል። ረጅም ልምድ አላቸው የተባሉት የግብፁ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ግን እያወቁ ልሞክረው ዓይነት ሩጫ ሱዳን እንዳለችው ያመጣላቸው ለውጥ የለም። ሌላው ቀርቶ ሞቅ ባለ መንገድ የተቀበሏቸው የተባበሩት ዓረብ ኢምረቶች ባለስልጣናት የግብፁ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ወደ አየር መንገድ ሲያመሩ ለኢትዮጵያ ሊሰጡ የነበረውን ለአነስተኛ እና ጥቃቅን ንግድ መርጃ የሚሆነውን የአንድ መቶ ሚልዮን ዶላር ገንዘብ ጉዳይ እስካሁን አልሰረዙም ይልቁንም ከኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እና ገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመፈራረም አፀኑት።  

የአረብ ሊግ ተከፋፍሏል 

ግብፅ ድምጿን አጥፍታ ኢትዮጵያን ልታስፈርም የፈለገችው ሰነድ በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ከተነቃባት በኃላ በቀጥታ ፊቷን ያዞረችው ወደ አረብ ሊግ ነበር።አረብ ሊግ መፎከር እና ምክንያት እና ሞራል ያለሽ  የዲፕሎማሲ አካሄዱ የታወቀ ስለሆነ እና በ21ኛው ክፍለ ዘመንም ልክ የአረብ እስራኤል ጦርነት ዘመን የሚያስብ ስለሆነ የአረብ ሊግን ውሳኔ ተከትሎ የዲፕሎማሲ ዕይታውን የሚቀይር አገርም ሆነ አህጉራዊ ድርጅት የለም።ምክንያቱም የአረብ ሊግ በራሱ ሌላው ቀርቶ የልብያና የሶርያን ጉዳይ በአግባቡ ይዞ ከኃያላን አገሮች ጣልቃ ገብነት ማዳን ያቃተው ደካማ አስተሳሰብ የተሞላ ድርጅት መሆኑ ፀሐይ የሞቀው ነው። 

ግብፅ የአረብ ሊግ መግለጫ ከአጋርነት ያለፈ ሥራ እንደማይሰራ ምናልባት ከኢትዮጵያ ጋር የሚነሳ ግጭት ካለ ብቻ ከጎኗ እንደሚቆም ከማሰብ ባለፈ አሁን ለምትፈልገው ሥራ እንደማይደርስ ገብቷቷል። በሌላ በኩል ራሱ የአረብ ሊግ ውስጡ የተከፋፈለ ለመሆኑ ከግብፅ የበለጠ የሚያውቀው የለም። ለመከፋፈሉ ሁለት ማስረጃዎች መጥቀስ ይቻላል።አንዱ በሶርያ፣በሊብያ እና በየመን ጉዳዮች የአረብ ሊግ አባላት ወጥ የሆነ ዕይታ የሌላቸው መሆናቸው ብቻ ሳይሆን በቅርቡ በደማስቆ የአረብ ሊግ  ቢሮ ለመክፈት ጉዳይ ላይ ሳይቀር ዱላ ቀረሽ ፀብ ተነስቷል።ሌላው የመክፋፈሉ ምልክት ደግሞ የግብፁ ውጪ ጉዳይ  ሚኒስትር የመካከለኛ ምስራቅ የሰሞኑ ጉዞ ነው።

 የአረብ ሊግ በሰሞኑ መግለጫ እንዲሁም ቀደም ባሉት ወራት የአረብ ሊግ ፓርላማ ኢትዮጵያን ለማስፈራራት የሞከረባቸው መግለጫዎች እያሉ፣የግብፁ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ግን ደብዳቤ ይዘው በሊጉ አባል አገሮች ዋና ከተሞች ሲዞሩ ነው የከረሙት።ይህ ማለት የአረብ ሊግ የሚያወጣው መግለጫ የመካከለኛው አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና መንግስታትን ሙሉ የተስማማ ሃሳብ እንዳልሆነ ያሳያል።ለእዚህ ነው የግብፁ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአረብ ሊግ መግለጫም በኃላ በየአገራቱ እየዞሩ  መንግስታቱን መማፀን የያዙት።ይህ ማለት ግን ከመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ውስጥ ኢትዮጵያን እንደ ስጋት የሚያዩ የዘመናት የኢትዮጵያ ባላንጣዎች የሉም ማለት አይደለም።እነኝህ አገሮች በኢትዮጵያ ላይ ዱላ የምያስነሳ ማናቸውም ምክንያት ካገኙ ምንም ከማድረግ የሚመለሱ አይደሉም።

ኢትዮጵያን በተመለከተ የግብፅ ቀጣይ ስልት ምንድነው?

ግብፅ ሰሞኑን የዞረችበት የዲፕሎማሲ ጥረት ከመካከለኛው ምስራቅ እስከ ፈረንሳይ የዘለቀ ቢሆንም ከአገራቱ የቀዘቀዘ ስሜት፣በውስጣቸው ትኩረት የሚሰጡት በርካታ ውስጣዊ ጉዳይ መኖር፣ሰሞኑን የተነሳው የኮሮና ቫይረስ ብሔራዊ አደጋ ከመሆኑ አንፃር እና የነዳጅ ዋጋ እጅግ በመውረዱ ሳብያ (ዛሬ በበርሜል እስከ 20 ዶላር) መውረድ ሳብያ የግድቡ ጉዳይ ግብፅ የፈለገችውን  ያህል ትኩረት ሊስብላት አልቻለም።ጉዳዩ ትኩረት አለመሳቡ በራሱ ደግሞ ለኢትዮጵያ የሚያመጣው ጥቅም አለ። ይሄውም በእዚህ ወቅት በፍጥነት ግድቡን የመገንባቱን ሂደት ማፋጠን እና በቶሎ መጨረስ ነው። ይህ በእንዲህ እያለ የግብፅ ቀጣይ ስልት ሊሆን የሚችለው በኢትዮጵያ የውስጥ ክፍተቶች ውስጥ መስራት እና ኢትዮጵያን ከውስጥ ለማተራመስ መስራት ነው።

እዚህ ላይ የወታደራዊ እርምጃው ግብፆች ሊሞክሩት አይችሉም።ምንያቱም አንዳች አይነት የወታደራዊ ሙከራ ቢደረግ 85% የዓባይ ወንዝ የሚመነጭባት አገር ኢትዮጵያ በውሃው ላይ ሌላ የፈለገችውን አማራጭ የአፀፋ እርምጃ የማትወስድበት ምንም ምክንያት የለም። ይህ ደግሞ ከረጅም ጊዜ አንፃር ለግብፅ የሚያዋጣ አይደለም። ስለሆነም የግብፅ ዋነኛ ሥራ የሚሆነው በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ ገብቶ በእጅ አዙር መፈትፈት ነው። ይህንን ደግሞ እየሄደችበት ለመሆኑ በአሜሪካን አገር መሰረቱን ያደረገው ዘሀበሻ በዛሬ ዜናው  የሱዳኑ የቀድሞ የስለላ ከፍተኛ ባለስልጣን  እና ከቀድሞው የኢትዮጵያ ደህንነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ ጋር የቅርብ ወዳጅ ነበሩ የተባሉት ሰው ሜጀር ጀነራል ሳላህ አብደላ ጎሽ  ግብፅ መግባታቸው መረጃው እንደደረሰው ዘግቧል። ባለሥልጣኑ  በዋናኝነት ከግብፅ የደህንነት መስርያቤት ጋር በጋራ የሚሰሩት ኢትዮጵያን የማተራመስ ሥራ ለመስራት መሆኑን ዜናው አክሎ ዘግቧል።

ይህ የግብፅ ተግባር ደግሞ ላለፉት ሃምሳ ዓመታት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ እጃቸውን ማስገባታቸው እና ኢትዮጵያ አንገቷን ቀና አድርጋ እንዳትሄድ ለማድረግ የሙሉ ጊዜ ሥራ ካደረገችው ሰንብታለች።ስለሆነም የግብፅ ቀጣዩ ስልት ከዲፕሎማሲው ጎን በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ገብቶ ኢትዮጵያን መረበሽ  መሆኑን መረዳት ይገባል። 

ባጠቃላይ ግብፅ እንደምንም አግባብታ ኢትዮጵያን በግድቡ ዙርያ ልታስፈርም የፈለገችው ሰነድን ኢትዮጵያ ባትፈርምስ የሚል አማራጭ ሃሳብ ሳትይዝ ኢትዮጵያ አዘናግታ ከመጨረሻው ስምምነት መቅረቷ በግብፅ መንግስት ውስጥ መደናበር አልፈጠረም ለማለት አይቻልም።ይህ መደናበር ደግሞ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ ይዘው ከአገር አገር እንዲዞሩ ማድረጉ ጥሩ ማሳያ ነው።ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከዙረቱ በኃላ የኢትዮጵያን ቦታ በሚገባ የለኩት ይመስላል።ኢትዮጵያን በአሁኑ ጊዜ መንካት እስራኤልንም ሆነ ሩስያ የሚይዙትን መስመር ለማወቅ አስቸጋሪ መሆኑ ለግብፅ መንግስት ግልጥ ሆኗል። ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ የአፍሮ-ዓረብ ዲፕሎማሲ ሚዛን መሆኗን ያለማወቅ ችግር በግብፆች ውስጥ ነበር። በተለይ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ሰላም መሆኗ በኢትዮጵያ ጥቅም ላይ የሚረማመድ አገር ቶሎ ለማግኘት አስቸጋሪ ሆኗል ለግብፆቹ።ስለሆነም አሁን ግብፅ ትንሽ ጊዜ መግዛት እና ኢትዮጵያን ሊያጠቃ የሚችል ሁነኛ ጠላት ማፈላለግ  እንዳለባት ገብቷታል።ለእዚህ ደግሞ የውስጥ ውጥረቶች እና ቅራኔዎችን በደንብ መተንተን እና ማጥናት እንዳለባት ገብቷታል። ለእዚህም ልምድ አላቸው የተባሉትን የቀድሞ የሱዳን የደህንነት ከፍተኛ ባለስልጣን ወደ አገሯ ተርታ ለመመካከር ወስናለች። ይህ በእንዲህ እያለ ግን ግብፅ በአርባ ዓመት ታሪኬ አይቼ አላውቀውም ያለችው የጎርፍ እና የመብረቅ አደጋ ሃያ ሰው እንደገደለባት ገልጣለች።ግብፅ ውሃው ከላይ ነው የሚመጣው።የኢትዮጵያ ሕዝብም ሆነ መንግስት የግብፅን ሕዝብ የመጉዳት ዓላማ እንደሌለው ይልቁንም ግድቡ መሰራቱ ለግብፅም ጥቅም እንደሆነ እንዲያውቁት ደግሞ ማን በነገራቸው?

ጉዳያችን ሚድያ፣ኮሚኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት 
Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant


ከኢትዮጵያ አንፃር በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሊታዩ የሚገባቸው ሶስቱ የኮሮና ቫይረስ መተላለፍያ መንገዶች (ጉዳያችን ልዩ )


ጉዳያችን ሚድያ፣ኮሚኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት 
Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant

ዓለማችንን እያናወጠ ያለው የኮሮና ወረርሽኝ በኢትዮጵያም ስጋት መደቀኑ አይቀርም።ከእዚህም አንፃር የበሽታው አደጋ የሚመጣበትን መንገድ የዓለም ጤና ድርጅት እና የምዕራብ አገሮች በሽታው ይመጣበታል ብለው ከተቆሙባቸው መንገዶች ብቻ የበሽታውን መምጫ መንገዶች መገደብ ስህተት ነው።የዓለም ጤና ድርጅት እና የምዕራብ አገር ሚድያዎች የሚያሰራጩት በሽታውን የምንከላከልባቸው መንገዶች አብዛኛው የዓለም ሕዝብ ከሚኖርበት አኗኗር ዘይቤ ጋር በተለይ ሁኔታዎች ተሟልቶለት ከሚኖረው ሕዝብ አንፃር የምጎድሉትን መንገዶች ብቻ ነው።ስለሆነም እስካሁን ባብዛኛው እየተነገር ያለው እጅ መታጠብ፣ሲያስነጥሱ ወደሌላ ሰው እንዳይተላለፍ የሚደረጉ ጥንቃቄዎች እና በትንፋሽ እንዳይተላለፍ ጥንቃቄ ማድረግ የሚሉት ይጠቀሳሉ።

ሆኖም ግን እነኝህ ምክሮች እና ፖስተሮች እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አገሮች ጋር ካሉት የባሕል እና የአኗኗር ዘይቤ አንፃር የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ቃኝቶ ተጨማሪ እርምጃዎች መውሰድ አለበት።ከእነኝህ እርምጃዎች ውስጥ ሶስቱ ከኢትዮጵያ አንፃር መቃኘት ያለባቸው ይመስሉኛል። እነርሱም -

1) የጥርስ መፋቅያ እንጨት እና የጥርስ ቡርሽ አጠቃቀም 

በኢትዮጵያ በከተማ በአዟሪዎች እየዞሩ የሚሸጡት እና ከፍተኛ የእጅ ንክኪ ያለባቸው፣ቀኑን ሙሉ ለአቧራ ተጋልጠው የሚውሉ የጥርስ መፋቅያ እንጨቶች አሉ።በገጠርም እነኝህን  እንጨቶች የሚጠቀሙ ሁሉ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው።ጥንቃቄው ለምሳሌ በጥቂቱ በሙቅ ውሃ አፅድቶ መጠቀም ሊሆን ይችላል።ሌላው በከተማም ያለው ይህ በውጭ ያሉትም ችግር ሊሆን ይችላል። የጥርስ መፋቅያ ቡርሾች ናቸው።እነኝህ ቡርሾች የሚቀመጡበት አቀማመጥ በተለይ ቫይረሱ ለ12 ሰዓታት ድረስ በውጭ ከመቆየቱ አንፃር ከመጠቀማችን በፊት ማፅዳት ፣ተጠቅመን ስናስቀምጥም በአግባቡ መሆን እንዳለበት መረዳት ይገባል።

2) የጆሮ ኩክ ማፅጃ አጠቃቀም 

በኢትዮጵያ በተለይ በገጠር ፣በከተማም ያለ ችግር ነው የጆሮ ኩክ ለማፅዳት ማናቸውንም ነገር የመጠቀም መጥፎ ልማድ አለ።ተማሪዎች በከተማም ጭምር  ጆሮን ለማፅዳት በእስክርቢቶ ክዳን፣በዶሮ ላባ፣እና በመሳሰለው መጠቀም የተለመደ ነው።ይህ የቫይረሱን ወደ ሰውነት ክፍል የመግባት እድሉን ይጨምረዋል።በተለይ በሽታው ከፍተኛ የሙቀት ሁኔታ ስለማይችል እንደጆሮ፣አፍንጫ እና ጉሮሮ ያሉት አካባቢዎች ተስማሚ የሙቀት ልክ ለቫይረሱ ስለሚሰጡት አመቺ ቦታዎቹ እንደሆኑ ባለሙያዎች ይመክራሉ።ስለሆነም በኢትዮጵያ ከእዚህ ልማድ አንፃር ምክር የሚያስፈልግ ይመስለኛል።

3) ጫት

በኢትየጵያ እየተስፋፋ የመጣው እና በአረብ እና የአውሮፓ አገራት በአደገኛ ዕፅነት የተመደበው ጫት አንዱ የኮሮና ቫይረስ መተላለፍያ እንደሚሆን መገመት ይቻላል። ጫት በአንድ ቀን ውስጥ ከሚቆረጥበት ማሳ ጀምሮ እስከ ተጠቃሚው ሰው እስከሚደርስ ብዙ ያልታጠቡ እጆች እየነካኩት የሚያልፍ ነው።መጨረሻ ላይ ተጠቃሚዎች አጠብነው ብለው በውሃ ቢይርሱትም የኮሮና ቫይረስን ለማጥፋት እንደማይችል የታወቀ ነው።ስለሆነም በኢትዮጵያ አንዱ እና ዓይነተኛ የኮሮና ቫይረስ ምክንያት ጫት እንደሚሆን መገመት ቀላል ነው። አንዳንድ አክትቪስቶች እጅ መታጠብ እንዴት እንደሆነ ከሚነግሩን የምያስፋፉትን እና እራሳቸውም እየቃሙ ሲያስተዋውቁት የከረመውን ጫት ጎጂ መሆኑን ለሕዝብ ቢነግሩት ጥሩ ነበር።

ባጠቃላይ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የአንድ በሽታ መከላከያ መንገዶችን ቀጥታ የዓለም ጤና ጥበቃ ወይንም የምዕራብ አገሮች የጤና  ፖስተሮች እንዳለ ከመጠቀም ባለፈ በኢትዮጵያ አንፃር ካለው ልማድ የበለጡ አደገኛ ሁኔታዎች አሉ ወይ? ብሎ ጠይቆ የምክር አሰጣጡን ሁኔታ መቃኘቱ ተገቢ ነው በማለት ጉዳያችን ሃሳቧን ታካፍላለች።

======================/////=============


Thursday, March 12, 2020

የዛሬው የኢትዮጵያ የፓርላማ ውሎ አድልዎ እና መገለሉ ከጎሳዊ መልክ ይልቅ በኃይማኖትም መሆኑን ያመላከተ ስርዓት በኢትዮጵያ እያቆጠቆጠ ለመሆኑ አመላካች ነው።



  • ይህ ጉዳይ ኢትዮጵያውያን የበለጠ እንዲነጋገሩበት ሁኔታው መንገድ ከፍቷል።
  • የክልል ባለስልጣናት፣የዞን ኃላፊዎች፣የወረዳ ባለስልጣናት፣ሚኒስትሮች፣ኮሚሽነሮች፣የመምሪያ ኃላፊዎች ሲሾሙ መስፈርቱ ምን ነበር? 
  • በኢትዮጵያ አንድ ሰው ምን ያህል ዕውቀት፣ልምድ እና ችሎታ ቢኖረውም የኦሮቶዶክስ ክርስቲያን አማኝ በመሆኑ ብቻ ከስልጣን እየተገፋ ነው? 
  • ጉዳዩ ጠለቅ ላለ ምርምር ይጋብዛል።የዛሬው የፓርላማው ውሎ አንድ ደውል በኢትዮጵያውያን ጆሮ አቃጭሏል
  • ኢትዮጵያ የአንዱ ወገን ወይም የሌላው አይደለችም።ሁሉም እኩል መብት አለው።ትውልዱ አገር በጣሳ እየሰፈረ የሚሰጠው ወይንም የሚነፍገው ፓርላማ አይፈልግም።
  • በልበሙሉነት አገሩን መረከብ እንዳለበት ይህ ትውልድ ከምንጊዜውም በላይ ከገባው ዛሬ ነው። 

===================
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት የቦርድ አባላት ሹመትን አጽድቋል።በእዚህ መሰረትም ምክር ቤቱ ከቀረቡለት ዘጠኝ ግለሰቦች ውስጥ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ኦባንግ ሜቶ እና ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ይገኙበታል።የምክር ቤቱ አባላት ውስጥ የተወሰኑቱ የሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን ሹመት ሲቃወሙ ታይተዋል።ሆኖም ግን አብላጫው በድምፅ ብልጫ በመደገፉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ባቀረቡት መሰረት የሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ሹመት አልፏል።

የተወሰኑ የፓርላማው አባላት የተቃወሙበት ምክንያት ግን የሚጠቁማቸው  ሁለት ግልጥ ጉዳዮች አሉ። እነርሱም -


1ኛ) ፓርላማው በፅንፈኛ አክቲቪስቶች ማኅበራዊ ሚድያ ከማየት ያለፈ ብዙም ብስለት የሌላቸው ሰዎች በውስጡ መያዙን  


በፓርላማው ውስጥ የሙሐዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤልን ሹመት የተቃወሙት የፓርላማው አባላት፣
 የዲያቆን ዳንኤል ክብረትን ለፕሬስ ድርጅት የሚመጥን ፣ከሃያ ዓመታት በፊት የስነፅሁፍ ምሩቅ መሆኑን አላነሱም። የፓርላማው አባላት ዳንኤል የፕሬስ ስራን የሚያውቀው እና በስራው ውስጥ ከሃያ አምስት ዓመታት በላይ የስራ ልምድ እንዳለው አላነሱም። የፓርላማው አባላት ዳንኤል ከደርዘን በላይ መፃሕፍ ማሳተሙ ከፕሬስ ድርጅት ሥራ ጋር በቀጥታ የተቆራኘ የአሰራር ልምድ እንዳለው አላነሱም።ዳንኤል በኢትዮጵያ በመንግስት ያልተሞከረውን ለኢትዮጵያ የለፉ ሰዎች የሚሸለሙበት በጎ ሰው የተሰኘ የሽልማት ድርጅት እንዲመሰረት ሃሳብ ከማመንጨት እስከ ተግባራዊ ሥራ ድረስ እየሰራ መሆኑን አላነሱም።የፓርላማው አባላት ዳንኤል በመላው ዓለም ከአንድ መቶ አገሮች በላይ ተዘዋውሮ ከፍተኛ የፖለቲካ ፣የማኅበራዊ እና የባሕል ልምዶች ማግኘቱን አልተነፈሱም።

በእርግጥ የእዚህ ዓይነቱ የሙያ ጥያቄ ሊነሳ የሚችለው የሚያነብ እና የሚያገናዝብ የፓርላማ አባል ሲኖር ነው።በአክቲቪስት ፌስ ቡክ ላይ ከጧት እስከ ማታ ተጥዶ ውሎ ለሚያድር እና እውቀት ማለት የማኅበራዊ ሚድያ ብጥቅጣቂ  ፅሁፍ እንደ የዕውቀት ምንጭ አድርጎ ለሚወስድ የፓርላማ አባል የእዚህ ዓይነቱ ማገናዘብ ፈፅሞ አይጠበቅም።


2ኛ) እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው የሚፈሩ የፓርላማ አባላት 


በፓርላማው ውስጥ በሙሐዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ላይ ሹመቱን ተቃውሞ ያነሱት የዳንኤል እግዚአብሔርን መፍራቱን ነው።በእነርሱ አገላለጥ የሃይማኖት ሰው ስለሆነ የፕሬስ ድርጅቱ ለኢትዮጵያ ለሁሉም የሚያገለግል ስለሆነ ...የሚል አነጋገር የተጠቀሙ የፓርላማው አባል ነበሩ።ይህ በራሱ አስቂኝ፣ሞራላዊነት የጎደለው እና አድልዎ እና መገለሉ ከጎሳዊ መልክ ይልቅ በኃይማኖትም መሆኑን ያመላክታል።


በመጀመርያ ደረጃ ለኃላፊነት የሚሾም ሰው ሃይማኖትን አክባሪ፣አገሩን ወዳጅ መሆኑ ዋና መስፈርት መሆን የለበትም ወይ? የተወሰኑት የፓርላማ አባላት ሃይማኖቱን መከተሉ እንደሚያዳላ ሊናገሩ ሞክረዋል።እዚህ ላይ ሃይማኖት ያለው ነው ወይንስ የሌለው አድልዎ የሚያውቀው? ሃይማኖትህን ስታከብር ሳዳላ ሰው ባያየኝ እግዚአብሔር ያየኛል ትላለህ።ሃይማኖትህን ሳታከበር እና እግዚአብሔርን ሳትፈራ ሰውንም አታፍርም።ስለሆነም ''ሆዴ ይሙላ፣ደረቴ ይቅላ'' ብለህ በአድሎ የተሞላ ሥራ ላይ ትጠመዳለህ። ኢትዮጵያስ ላለፈው ግማሽ ክ/ዘመን ጠፍቶባት የኖረችው እና ለእዚህ ሁሉ ቀውስ የተዳረገችው  እግዚአብሔርን የማይፈሩ ወደ ቤተ መንግስቱ መግባታቸው አይደለም እንዴ?  ደግሞስ አሁን በስልጣን ላይ ያሉት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ጀምሮ ያሉት ባለስልጣናት በክርስትና ወይንም በእስልምና እምነት ውስጥ የጠለቁ እና ባመኑበት እምነታቸው ያጠበቁ አይደሉም ወይ? ይህ በራሱ ክፋቱ ምንድነው?


ባጠቃላይ ሃይማኖት ያለው ሰው እግዚአብሔርን ይፈራል።እግዚአብሔርን የሚፈራ ደግሞ አድልዎ አያውቅም።የእዚህ ዓይነት ሰው ከአገሩ አልፎ ስለሰው ልጆች የሚጨነቅ ነው የሚሆነው።አሁን ያለው የኢትዮጵያ ፓርላማ ላለፉት ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ የነበረው የለውጥ ሂደት ላይ በጎ ተፅኖ በመፍጠሩ እናመሰግነዋለን።የዛሬው የተወሰኑ (ሁሉም አይደሉም) በሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ላይ በሃይማኖቱ ምክንያት ብቻ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቡትን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት  የቦርድ አባልነት ሊያስቆሙ የመሞከራቸው ጉዳይ ግን አንድ ጉዳይ ግልጥ ማድረጉን ሕዝብ እየተነጋገረበት  ነው።ይሄውም  አድልዎ እና መገለሉ ከጎሳዊ መልክ ይልቅ በኃይማኖትም መሆኑን።ይህ ጉዳይ ኢትዮጵያውያን የበለጠ ሊነጋገሩበት ሁኔታው መንገድ ከፍቷል።የክልል ባለስልጣናት፣የዞን ኃላፊዎች፣የወረዳ ባለስልጣናት፣ሚኒስትሮች፣ኮሚሽነሮች፣የመምሪያ ኃላፊዎች ሲሾሙ መስፈርቱ ምን ነበር? በኢትዮጵያ አንድ ሰው ምን ያህል ዕውቀት፣ልምድ እና ችሎታ ቢኖረውም የኦሮቶዶክስ ክርስቲያን አማኝ በመሆኑ ብቻ ከስልጣን እየተገፋ ነው? ጉዳዩ ጠለቅ ላለ ምርምር ይጋብዛል።የዛሬው የፓርላማው ውሎ አንድ ደውል በኢትዮጵያውያን ጆሮ አቃጭሏል? ኢትዮጵያ የአንዱ ወገን ወይም የሌላው አይደለችም።ሁሉም እኩል መብት አለው።ትውልዱ አገር በጣሳ እየሰፈረ የሚሰጠው ወይንም የሚነፍገው ፓርላማ አይፈልግም።በልበሙሉነት አገሩን መረከብ እንዳለበት ይህ ትውልድ ከምንጊዜውም በላይ ከገባው ዛሬ ነው። 



ጉዳያችን ሚድያ፣ኮሚኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት 
Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant

Sunday, March 8, 2020

የእናት ፓርቲ ተመሰረተ።መስራች ጉባኤውን ዛሬ በአዲስ አበባ ላይ በተሳካ መልኩ አከናውኗል።የተመራጮች ስም ዝርዝር ይዘናል።


  • የፖለቲካ፣የሰላም እና ደህንነት (Peace and Security) ምሑሩ ዶ/ር  ኃይለየሱስ ሙሉቀን ፕሬዝዳንት፣የምጣኔ ሃብት ምሁሩን ዶ/ር ሰይፈስላሴ አያሌውን ደግሞ ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ ጉባኤው መርጧል።
ዛሬ በጠቅላላ ጉባኤ ከቀረቡት አማራጮች ውስጥ የፀደቀው የእናት ፓርቲ ዓርማ 

ዛሬ ዕሁድ የካቲት 29፣2012 ዓም በአዲስ አበባ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የስብሰባ ማዕከል የመስራች ስብሰባውን ያካሄደው አዲሱ እናት ፓርቲ የፓርቲውን ሎጎ በጠቅላላ ጉባኤው ያፀደቀ ሲሆን፣ የስራ አስፈፃሚ አባላትን፣የላዕላይ ምክር ቤት አባላትን፣ የሂሳብ ክዋኔ ኦዲት ኃላፊዎች እና የሕግ ስርዓት ጉዳዮች ኃላፊዎችን መርጧል።የእናት ፓርቲ አደራጆች በዛሬው መስራች ጉባኤ ላይ የፓርቲው መመስረት ያስፈለገበትን ምክንያት ሲያስረዱ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ችግሮች በሶስት ጉዳዮች ተተብትበው መያዛቸውን እና ለእዚህም በቂ መፍትሄ ፖለቲካው  መስጠት ያለመቻሉን በዋናነት ያስቀምጣሉ። እነርሱም -


1. ፖለቲካዊ ችግሮች፣ 

በሀገራችን የሚታየው የፖለቲካ ስሪት ብዙ የሀገራችንን ችግሮች መፍታት ሲገባው በአሉታዊ መልኩ መገኘቱ። ኅብረተሰቡን በቋንቋ፣ በጎሳ ፣ በሰፈር፣ ወዘተ የሚከፋፍል በመሆኑ በሕዝቦች መካከል አብሮ የመኖር እሴትን መሸርሸሩ።

2. ማኅበራዊ ችግሮች፣ 

የሀገራችንን ማኅበረሰብ በማኅበራዊ ጉዳይ በፍቅር ፣ በመተሳሰብ ፣ በመቻቻል እና በመከባበር በጋራ ሀገራችን መኖር ሲገባን ግራ በገባው ትርክት ሰዎች መሰደዳቸው፣ መፈናቀላቸው፣ የግለሰቦች ሀብትና ንብረታቸው ከፍተኛ ጉዳት ላይ መውደቁ፣ የሃይማኖት ተቋማት የደኅንነት አደጋ ላይ መውደቃቸው፣ የሰዎች የመኖር ዋስትና ስጋት ላይ መውደቁ፣ በየጊዜው ብዙ ሰዎች መገደላቸው፣ ወዘተ የሀገራችንን ሕዝቦች የማኅበራዊ የሕይወት ትስስር አደጋ ላይ መውደቁ። 

3. ኢኮኖሚያዊ ችግሮች፣ 

የሀገራችን የኢኮኖሚ ግባት የኢትዮጵያውያን ሕዝቦች ዕለት ተዕለት ኑሮን ለማሸነፍ የማያስችል፣ ከገቢ ይልቅ ወጪን እንዲንር በማድረግ የሰዎችን የመኖር ተስፋ ያቀጨጨ ስለሆነም መፍትሔ የሚያስፈልገው ስለሆነ።

በአጠቃላይ የሀገራችን ፖለቲካ ሦስቱንም (ፖለቲካዊ ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ) ጉዳዮች በጥምረት ለመፍታት የተዘጋጀ አለመሆኑ። እናት ፓርቲን እንዲመሰረት አስገድዷል፣ ይላሉ በምስረታ ላይ ያሉ ወገኖቻችን ።

በእዚሁ ፍፁም ዲሞክራሲያዊ እና የመስራች ጠቅላላ ጉባኤው አባላት በንቃት እንደተሳተፉበት በተነገረው ስብሰባ ላይ አሁን ላሉት የፓርቲው መዋቅሮች ከቀረቡለት ዕጩዎች ክዚህ በታች የተዘረዘሩትን የመስራች ጉባኤው ተሳታፊዎች  መምረጣቸውን ጉዳያችን ከአዲስ አበባ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል።በእዚህም መሰረት የፅህፈት ቤት አባላት  -

1)  የፓርቲው ፕሬዝዳንት =       ዶ/ር ኃይለየሱስ ሙሉቀን
2)  የፓርቲው ም/ፕሬዝዳንት =  ዶ/ር ሰይፈ ስላሴ አያሌው እና
3) የፓቲው ጠቅላይ ፀሐፊ =  አቶ ጌትነት ወርቁ የተመረጡ ሲሆን እንደ ቅደም ተከተላቸው በደረጃ ተለያይቶ ነገር ግን ሁሉም ከ400 በላይ ድምፅ አግኝተዋል።


በእናት ፓርቲ መስራች ጉባኤ ላይ ከተሳተፉት በከፊል 

በእዚህም መሰረት የፕሬዝዳንቱ፣ም/ፕሬዝዳንቱ እና ፀሐፊው የትምህርት እና የስራ ልምድ ሁኔታ በአጭሩ እንደሚከተለው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።


1)ፕሬዚዳንት፡-  ኃይለኢየሱስ ሙሉቀን (ፒኤችዲ)

ዶ/ር ኃይለኢየሱስ፣ የመጀመሪያ ድግሪ በፖለቲካል ሳይንስ ተመርቀዋል፡፡ 
2ኛ ድግሪ peace and security ተምረዋል፡፡
3ኛ ድግሪ peace and security ተምረዋል፡
በፓለቲካል ሳይንስ በመምህርነት፣ በተመራማሪ እና በማማከር ሠርተዋል፡፡
በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ተዘዋውረው አስተምረዋል፡፡ 
አትራፊ ባለሆነ ድርጅት በሓለፊነት ጭምር ሠርተዋል፡፡
አሁን በሓላፊነት፣ በማስተማርና በምርምር ሥራ እየሠሩ ይገኛሉ፡፡

2) ም/ፕሬዚዳንት፡- ሰይፈሥላሴ አያሌው (ፒችዲ)

ዶ/ር ሰይፈሥላሴ፣የመጀመሪያና ሁለተኛ ድግሪ በኢኮኖሚክስ ተምረዋል፡፡ 
3ኛ ድግሪ በኢኮኖሚክስ ሠርተዋል፡፡
በኢንፎርሜሽንና ኮምኒኬሽን፣ ፕሮግራሚንግ ዓለምአቀፍ ሥልጠናዎችን ወስደዋል፡፡ 
GPS ማጎልበትና ማላመድ ሥራ ሠርተው በማጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ 
በተለያዩ ተቋማት በሓላፊነትና በኢክስፐርትነት ሠርተዋል፡፡ 
በአሁኑ ወቅት  “መሪ” የሚባል የ GPS ዘዴን ለሀገራቸው አስተዋውቀዋል፡፡ 
አሁን GPS እና Navigation company በመክፈት እየመሩ ይገኛሉ፡፡ 

3)  ጠቅላይ ጸሐፊ፡-  አቶ ጌትነት ወርቁ 

አቶ ጌትነት፣የመጀመሪያና ሁለተኛ ድግሪ በሒሳብ ተመርቀዋል፡፡ 
ሁለተኛ ድግሪ በኢኮኖሚክስ ተምረዋል፡፡ 
በግልና መንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማስተማር በምርምር ሠርተዋል፡፡ 
በግል ተቋማት በሓላፊነትና በኢክስፐርትነት ሠርተዋል፡፡
አሁንም በማስተማር ምርምርና ሓላፊነት እየሠሩ ይገኛሉ፡፡


የሕግ ስርዓት ጉዳዮች  ሆነው የተመረጡ -

1)  አቶ ሰለሞን (በአንደኝነት) እና

2)  አቶ ለሜሳ (በሁለተኛነት)

ሂሳብ ክዋኔ ኦዲት


1)  ኢንጅነር ዓቢይ (በአንደኝነት)
2)  አቶ ተመስገን (በሁለተኛነት)

ለሥራ አስፈፃሚ አባልነት የሚከተሉት ተመርጠዋል።

1)   አቶ ፍሬው፣

2)  አቶ ኪሮስ፣
3) አቶ አበበ፣
4) አቶ ማቲያስ፣
5)  መምህር ሳሙኤል፣
6)  ወ/ት ዓለም፣
7)  አቶ ታከለ፣
8)  አቶ ዓይነሰው፣
9)  አቶ ሰለሞን፣


መስራች ጉባኤው ላይ ለመሳተፍ በማለዳ የተገኙ ብዙ ነበሩ።ከአዲስ አበባ ውጪ የተወከሉም እንዲሁ።

ለፓርቲው የላዕላይ ምክር ቤት የሚከተሉት ተመርጠዋል። እነርሱም  -

1)  ዶ/ር መሰሉ፣

2)   ወ/ት አስማሩ፣
3)   ዶ/ር ታመነ፣
4)   ዶ/ር ናሁ ሰናይ፣
5)   ዶ/ር ወንድወሰን፣
6)   አቶ መኩርያ፣
7)   ኢንጅነር ማቲያስ፣
8)   አቶ ጌታሰው፣
9)    አቶ ብርሃኑ፣
10)  ወ/ት ጉዳዩ፣
11)  አቶ ሮቤል፣
12)  አቶ ካሳሁን፣
13)  አቶ አሰፋ፣
14)  ወ/ት ናሆሚ፣
15)  ኢንጅነር ደሳለኝ፣
16)  አቶ ተመስገን፣
17) ወ/ሮ ሜሮን  ሆነው ተመርጠዋል።

እናት ፓርቲ በዛሬው የመስራች ስብሰባ ላይ በዋናነት የመጠፋፋት ፖለቲካ በኢትዮጵያ ዳግም እንዳያንሰራራ እና ላለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ የኖረው ህዝብን ከህዝብ የሚከፋፋል ''የእኛ እና የእነርሱ'' የሚሉት የፖለቲካ አካሄዶች እንዲያበቃ እንደሚሰራ ተወስቷል።

በመጨረሻም ተመራጮች  በሙሉ በታማኝነት እና በትጋት እንደሚያገለግሉ እና የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ ቃል ገብተዋል። (ከስር ቪድዮውን ይመልከቱ)



ጉዳያችን ሚድያ፣ኮሚኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት 
Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant

Friday, March 6, 2020

የእናት ፓርቲ ምስረታ በመጪው ዕሁድ አዲስ አበባ ላይ ይከናወናል።የ21ኛው ክ/ዘመንን ኢትዮጵያ ከሚያሻግሩ ፓርቲዎች ውስጥ እንደሚሆን ታምኖበታል።ፓርቲው ሁሉንም ብሔር፣ዕምነት እና ክልል ያሳተፈ እንደሆነ ተነግሯል።

ጉዳያችን ልዩ ዜና 

  • ለፖለቲካ በቁጥር  ብዙኃን፣በተሳትፎ ተመልካች  እና ወጣት የሆነው  የኢትዮጵያ ሕዝብ ክፍል ወደ መካከለኛው የፖለቲካ ዓውድ መጥቷል።
  • The Silence Majority of Ethiopians are organizing under the new forming party, ENAT PARTY


የአንዲት አገር የነገ ዕጣ በምን ላይ እንደተመሰረተ ለማወቅ፣በዛሬው ወጣት ርዕይ እና ፍላጎት ላይ የተመሰረተ  ሥራ እየተሰራ መሆኑን እና አለመሆኑን  መመልከቱ በቂ ነው።የብዙ አገሮች የዕድገት ምስጢር የተመሰረተበት አንዱ ምሰሶም ይሄው ነው።የትውልዱን ርዕይ እና ፍላጎት በተቃረነ መንገድ የሚሄዱ የፖለቲካ፣ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ሂደቶች እና ፖሊሲዎች  ሁሉ ውጤታማ የመሆናቸው ዕድል እጅግ የመነመነ ነው።

በኢትዮጵያ ፖለቲካም ላለፉት አርባ አምስት አመታት የቀጠለው የፖለቲካ ሂደት፣አዲሱን ትውልድ ፖለቲካውን እንዲሸሽ፣እንዳያምን እና በተሳትፎ የራሱን ገንቢ ሚና እንዳይጫወት እንቅፋት ሆኖበት ኖሯል።ይህ ሁኔታ ግን አሁን የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል፣እንደዜጋ የድርሻችንን መወጣት አለብን፣ከየትኛውም ብሔር፣ዕምነት እና ክልል ያላደላ ከምርም ኢትዮጵያን  ያለ እና ሁሉንም የሚያከብር ብሎም 21ኛውን ክ/ዘመን ኢትዮጵያን አሻግሮ በክብር ለትውልድ የማስረከብ ኃላፊነቱን ለመወጣት ያለመ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ በመጪው ዕሁድ የካቲት 29/2012 ዓም በአዲስ አበባ፣ስድስት ኪሎ በሚገኘው የስብሰባ ማዕከል  የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ታዛቢዎች በተገኙበት መስራች ስብሰባውን እንደሚያካሂድ ለጉዳያችን የደረሰው መረጃ ያመለክታል።በመስራች ስብሰባው ላይ ሁሉንም የኢትዮጵያ ክልሎች፣ብሔሮች እና ዕምነቶች የሚወክሉ ኢትዮጵያውያን ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ወጣቶቹ የእናት ፓርቲ አስተባባሪዎች ለጉባኤ ዝግጅት በንቃት እየሰሩ ነው።

''እዚህ ላይ ኢትዮጵያ ከመቶ በላይ የሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች እያሉ ተጨማሪ ለምን አስፈለገ? ብሎ የሚጠይቅ ይኖራል'' ያለው አንድ የእናት ፓርቲ አደራጅ ኮሚቴ አባል ሲያብራራ '' ይህ አስተሳሰብ የፓርቲዎች ቁጥር መብዛት በራሱ የኢትዮጵያን ሕዝብ የመወከል አቅማቸው ያደገ አድርጎ መውሰድ የሚነሳ የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው።'' በማለት ያብራራል።

ከእዚህ በተጨማሪ በጉዳያችን መረጃ መሰረትም የእናት ፓርቲ ሁሉን አቃፊነት፣የኢትዮጵያን መሰረታዊ ችግሮች ከመረዳት፣ ለችግሮች በቂ መፍትሄ ከመስጠት አቅም፣ፍላጎት እና ቁርጠኝነት አንፃር  የእናት ፓርቲ የራሱን አገራዊ ድርሻ እንደሚወጣ ከብዙ ጉዳዮች አንፃር አመላካች ጉዳዮች አሉ።የእናት ፓርቲ ከእዚህ በፊት ጊዜያዊ የዕውቅና ሰርተፍኬት ከኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ያገኘ ሲሆን በመጪው ዕሁድ የሚያደርገው አስር ሺህ በላይ ፊርማ አስፈርሞ ዋና እውቅና ሰርተፍኬት የሚያገኝበትን ሂደት ነው።የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አስር ሺህ የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብ ያልቻሉ ፓርቲዎች ከመጪው ነሐሴ የምርጫ ሂደት ውጪ እንደሚሆኑ እና ቀነ-ገደቡም በቀናት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ማሳወቁ ይታወሳል። ጉዳያችን ለእናት ፓርቲ መልካም የምስረታ ጉባኤ ትመኛለች።

የእናት ፓርቲ ጊዚያዊ ዕውቅና ከኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አግኝቷል።

ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

Tuesday, March 3, 2020

Press release on USA Secretary of Treasury`s Statement of 28th Feb 2020 on the Grand Ethiopian Renaissance Dam

የአሜሪካ የግምጃ ቤት ቢሮ የዓባይን ግድብ አስመልክቶ ሰሞኑን ላወጣው መግለጫ፣ የኢትዮጵያውያን ዓለም ዓቀፍ የዓባይ ልማት ድጋፍ ባለሙያዎች ማኅበር መግለጫ አውጥቷል።

=====================

Ethiopian International Professional Support for Abbay (EIPSA)
                                                                                                                                                   
 02 March 2019
Ethiopian International Professional Support for Abbay (EIPSA) is an independent and voluntary association of professionals of Ethiopian-origin specializing in relevant disciplines, and residing in several countries across the world. The founding principles of EIPSA include conducting scientific assessments on issues concerning the transboundary water management and use on the Nile. EIPSA has advocated for regional cooperation that will ensure mutual benefit among the riparian states with fair and equitable utilization of the waters of the Nile for the last seven years.
To that effect, EIPSA has produced a significant body of research outputs that is informative on Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD) filling scenarios, the benefits of the GERD to the sustainable and equitable utilization of the resource, the benefits and conditions of cooperation, and alternative instruments that could contribute to trading energy and other derivative outputs across the riparian states. 
EIPSA is also a body that is duly aware of the fact that Ethiopia`s utilization of the Nile is a right, necessity, and not mere development agenda. With a severely impoverished population, and majority of its population having no access to electricity, Ethiopia requires little justification to tap into the massive hydropower generating potential of the Nile. Given this, the GERD has been passionately supported by the Ethiopian people who entirely financed the project out of what little they have. The GERD also brings the multiple dividends of regulating water flows in downstream countries, improving energy access in the region, and improving environmental conditions. EIPSA’s support of the GERD comes from this rationale.  
Given this, EIPSA has been keenly following the efforts of the Secretary of the Treasury first as observers and later as facilitators in the tripartite negotiations between Egypt, Ethiopia, and Sudan, regarding the GERD. EIPSA appreciates the offer made by the Secretary of the Treasury to observe and to facilitate the negotiation process such that the parties get closer to getting into an agreement on the matter. However, the Statement that was put out by the Secretary of the Treasury on 28th Feb 2020 has come as a complete shock to EIPSA. It appeared that Secretary of the Treasury made a leap of roles from being an observer and facilitator to a partisan Arbitrator, with a statement denying Ethiopia`s right to the use of the waters of the Nile and undermining its sovereignty.
With due respect to the Secretary of Treasury, EIPSA would like to note that the statement is ridden with factual errors. Although the statement refers to the document signed by Egypt as an ‘agreement’, given that Egypt is the only body that signed the document among the three negotiating parties, the document, by definition, fails to be an agreement. Furthermore, the statement states that the ‘agreement’ provides for the resolution of all outstanding issues on the filling and operation of the GERD. EIPSA finds it baffling that the Secretary of the Treasury Department apparently making a judgment on what is a satisfactory resolution to the outstanding issues, without Ethiopia’s opinion on the matter. 
EIPSA also found the statement to be condescending to Ethiopia as it states that the United States shares the concerns of Egypt and Sudan regarding unfinished work on the safe operation of the GERD and that Ethiopia needs to implement all necessary dam safety measures in accordance with international standards before filling begins. This statement runs in contrast to the fact that Ethiopia has addressed all dam safety related issues during the International Panel of Experts process and that Egypt and the Sudan had expressed their appreciation under Principle 8 of the Declaration of Principles, which Ethiopia will continue to implement.
Furthermore, EIPSA found the stance by the Secretary of the Treasury that “…final testing and filling should not take place without an agreement” rather unacceptable. Needless to say, trying to dictate a sovereign nation on what it should/should not do on its grounds is tantamount to undermining its sovereignty. Specific to the matter at hand the statement goes against the Agreement on the Declaration of Principles on the GERD of March 2015 that the leaders of Egypt, Ethiopia and the Sudan signed to guide their discussion on the GERD.
EIPSA is also of the view that the incidents of 27-28 February 2020 seemed rushed for no reason and too invested in getting the agreement done so quickly given that the Secretary of the Treasury remains a mere observer/facilitator. Given that Ethiopia has notified the negotiating parties and indeed the Secretary of the Treasury in due time that it needs more time to prepare for the meeting, the negotiation process could have accommodated Ethiopia’s request for courtesy reasons, if not for that fact that the negotiation is about the GERD-a dam that is being built in Ethiopia. That said, EIPSA believes Ethiopia would have no objections to the Secretary of the Treasury holding bilateral meetings separately with representatives from Egypt and Sudan, as it did in those two days. What EIPSA found rather mysterious is the need for the Secretary of the Treasury to take the steps that it took that finally culminated in a statement that EIPSA, as pointed out above, finds unpalatable on many grounds.
Given this, EIPSA would like to stress that:
  • It rejects the Statement by the Secretary of the Treasury of the United States of America on the GERD released on 28th February 2020.
  • EIPSA also calls for the Secretary of the Treasury to withdraw its statement as soon as possible.
  • It also requests the Secretary of the Treasury to resign from negotiators’ role and stop the unfair and unjust pressure on Ethiopia, and the use of intimidating words and expressions.
  • given the gross biasedness with which the mediation process was handled by Secretary of the Treasury, EIPSA would like to call upon the international community to show solidarity with Ethiopia.
Finally, EIPSA holds the view that the three countries should aim for maximizing the joint gains from the Nile and the sustainable use of the resource for the good of the current and future generations in all the riparian countries. Indeed, attempts to secure individual benefits at the expense of others is a thing of the past; is a recipe for endless conflicts; and most importantly leaves out benefits that would be reaped otherwise. Given this, EIPSA believes the best way forward for the Ethiopia, Egypt and Sudan will be to continue the negotiations in the spirit of fairness, mutual respect, and with no interference from outsiders what so ever.

 Ethiopian International Professional Support for  Abbay (EIPSA)




ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Monday, March 2, 2020

ትውልዱ በፍጥነት ተደራጅቶ የሰለጠነ ፖለቲካ አካል መሆን ይገባዋል።ጊዜ የለም!

ጉዳያችን ሚድያ፣ኮሚኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት 
Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant




ወቅታዊው አካባቢያዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ 

ኢትዮጵያ በወሳኝ ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ የአቅጣጫ ለውጥ ዳር ላይ ትገኛለች።ይህ ጊዜ አገሪቱ በ21ኛው ክ/ዘመን የሚኖራት መልክ የሚወስን ወሳኝ ጊዜ ነው።የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ቀንድም፣የመካከለኛው ምሥራቅም ሆነ የመላው ዓለም ፖለቲካ የሆነ የለውጥ አፋፍ ላይ ያለ ይመስላል።የአፍሪካ ቀንድን ብቻ ብንመለከት የሩቅም ሆኑ የቅርብ አገሮች ወታደራዊ ሰፈሮቻቸውን ከኤርትራ እስከ ሱማልያ እየኮለኮሉ ነው።ቱርክ ግዙፍ ፕሮጀክቶች በሱማሌ ውስጥ እየገነባች ነው።የመካከለኛ ምስራቅ የኩአታር እና የኢራን ባንድ በኩል በሌላ መስመር የሳውዲ ቡድን ተፋጠዋል።የመረጃ መመነታተፋቸው ከረቀቀው የሳይበር ጦርነት እስከ አደባባይ ደርሷል።

የኔቶ አባል ቱርክ በሶርያ ከሰሞኑ በተለየ መልክ የያዘችው ዘመቻ ከሩስያ ጋር ሳይቀር አፋጧታል።በሌላ በኩል የቱርክ ለአውሮፓ ያላት ስልታዊ አቀማመጥ እና ለምዕራቡ ዓለምም አለመታመን እንዲሁም በአልታሰበ ጊዜ የሩስያ እና ኢራን ስልታዊ ጥምረት የመፍጠር አደጋ ለአውሮፓ ስጋት እንደሆነ ነው።ባሳለፍነው ሳምንት የቱርክ መንግስት ከፍተኛ አማካሪ ለቢቢሲ ሲናገሩ ቱርክ በቅርቡ በእርሷ ጋር የሚገኙትን ከአንድ ሚልዮን የሚበልጡ ስደተኞች ወደ ምዕራብ አውሮፓ እንዲሄዱ እንደምትፈቅድ ሲያብራሩ  ''እኛ ድሮም የስደተኞች ፖሊሲ ለውጥ አላደረግንም።ድንበሩን እንከፍትላቸዋለን'' ነበር ያሉት። ቱርክ ምዕራቡን የምታስፈራራው በስደተኛ ጎርፍ የመምታት አቅሟን በማሳየት ነው።የአውሮፓ ህብረት ከእዚህ በፊት  ቱርክ ስደተኞቹን እንዳታሳልፍ በገንዘብ እየደጎመ አስታግሷት ነበር።ከሰሞኑ ግን እኝሁ ከፍተኛ አማካሪ ሲናገሩ ''ስደተኞቹ  የምዕራባውያን የክፋት ሰለባዎች ናቸው።ምዕራባውያን ክፉ ስራቸው  ውጤቶች ናቸው'' በሚል ቃላት መናገራቸው  የቱርክ አካሄድ ወዴት እንደሆነ ለማወቅ አዳጋች አድርጎታል።

በሌላ በኩል የዓለም ምጣኔ ሀብት በከፍተኛ ሁኔታ አደጋ አንዣቦበታል።ለእዚህ ዋናው ምክንያት ደግሞ የትራምፕ የንግድ ጦርነት ከሜክሲኮ እስከ ቻይና መዝለቁ ብቻ ሳይሆን የቻይናው ኮሮና ቫይረስ ጉዳይም ጭምር ነው።ቻይና የዓለማችን ግዙፍ ምጣኔ ሀብት አንቀሳቃሽ ነች።የአውሮፓ አገሮች ሳይቀሩ የቻይና ዕዳ አለባቸው።እዳው ደግሞ በንግድ ግንኙነት የሚጣጣ ተደርጎ የታሰበ ነበር። አሁን በኮሮና ቫይረስ ሳብያ የቻይና ተፅኖ ቀላል አይደለም።በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ አገሮች ኢኮኖሚ ተፅኖ ይኖረዋል።አፍሪካውያን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2002 ዓም ከቻይና የነበረባቸው ዕዳ 1ቢልዮን ዶላር ብቻ የነበረ ሲሆን በ2019 ዓም ወደ 142 ቢልዮን ዶላር አሻቅቧል።ከእዚህ ውስጥ 42 ቢልዮኑ የአንጎላ ዕዳ ብቻ ነው።ስለሆነም የቻይና ጉዳይ በተለይ በኮሮና ቫይረስ ሳብያ ቀውሱ ከተባባሰ የአፍሪካ ምጣኔ ሀብት አደጋ ይዳረግበታል።የኢትዮጵያም እንዲሁ።

ትውልዱ አባቶቹ በሙቱላት አገር እንደ ፍልስጤማውያን 'የአገር ስጡኝ' ልመና ላለመግባት፣ በፍጥነት ተደራጅቶ የሰለጠነ ፖለቲካ አካል መሆን ይገባዋል።

ከላይ ለማንሳት እንደተሞከረው አገራዊ፣አካባቢያዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች የሚያሳዩት ሊመጡ ከሚችሉ ፖለቲካዊ፣ምጣኔ ሃብታዊ እና ማኅበራዊ ቀውሶች  ለመውጣት ትውልዱ ከፖለቲካው ዓለም በመራቅ የተጣለበትን የተረት ቡልኮ አውልቆ በአዲስ መልክ እና የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል ስሜት ተደራጅቶ የዘመናዊው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሂደት አካል መሆንን የሚጠይቅ ጊዜ ላይ መሆናችንን ነው። ዘመናዊ ፖለቲካ ዘመኑ የሚጠይቀው ፖለቲካ በሚለው ይወሰድልኝ።በዓለም ላይም ሆነ በአካባቢያችን የሚከሰቱት ክስተቶች ለቀረው ዓለም ቀውስም ሆነ ዕድል ቢሆኑ ይህ ትውልድ ግን ያለበት ኃላፊነት የራሱን ድርሻ ለመወጣት ተደራጅቶ የፖለቲካው አካል በመሆን የፖሊሲ አውጪነቱን እና በራሱ ዕድል ላይ ሌሎች እንዲወስኑ ተቀምጦ መጠበቅ ሳይሆን የእርሱ ድምፅ እንዲሰማ ተደራጅቶ የፖሊሲ አውጪው አካል መሆን ነው።


ስለሆነም በመጪው ነሐሴ ይደረጋል ለተባለው ምርጫ የዳር ተመልካች በመሆን እና የፖለቲካውን ሜዳ ለፅንፍ የጎሳ እና አክራሪ ኃይሎች በመልቀቅ ኢትዮጵያ አገሩን እንዳያጣ መጠንቀቅ ይገባዋል።በኢትዮጵያ ካሉት የፖለቲካ ድርጅቶች ቁጥራቸው በመቶዎች ይቆጠሩ እንጂ ኢትዮጵያን እንደኢትዮጵያ ለማሻገር  የሚመኙት እና በአንፃራዊ መልኩም ቢሆን አቅም አላቸው የሚባሉት  አራት አይሆኑም።ይህ ማለት አሁንም ኢትዮጵያ ቃላት ከመቶ ሚልዮን በላይ ሕዝብ ውስጥ ድምፁ ያልተሰማ እና ኢትዮጵያ እንዴት መቀጠል እንዳለባት የራሱ ሃሳብ፣ሕልም እና አቅም ያለው ትውልድ አለ ማለት ነው። ይህ ትውልድ ደግሞ መደራጀት የወቅቱ ጥይቄ መሆኑን ማመን አለበት።ኢትዮጵያውያን በጋራ አሳባቸው ሲደራጁ ደቂቃ አይፈጅባቸውም። የሰለጠኑ፣የሚሰሩትን የሚያውቁ እና ስረ መሰረታቸው በማይበጠስ ሕብረት የተሳሰረ ነው።ጥምቀት ሲደርስ ማንም ጡሩንባ አይነፋላቸውም፣ ለመውሊድ ሲሰበሰቡ ደውል አይጠብቁም፣ለደመራ ከዓመት ወር እና ሰዓት ሳያዛንፉ ሲገኙ መካሪ አይፈልጉም።የሚያደርጉትን ያውቃሉ።

ለማጠቃለል ይህ ትውልድ ኢትዮጵያን የማስቀጠል እና ክብሯን በ21ኛው ክ/ዘመን ፈተና አሻግሮ፣ ጠብቆ ማስቀጠል እና ለልጆቹ ማውረስ አለበት። ይህንን ለማድረግ ደግሞ መደራጀቱ ወሳኝ ነው።ለመደራጀቱ ከዘገየ ግን ነገ እንደ ፍልስጤማውያን 'አገር ስጡኝ' ብሎ የሚለምን እንዳይሆን የዛሬ ሥራ ዛሬ መሰራት አለበት።ከጎሳ ክፍፍል በራቀ መልኩ፣ኢትዮጵያዊ ሕብረ ብሔርነቱን አክብሮ እና ማንነት መሰረቱን ሳይነቅል ለሚሰራው ሥራ ሁሉ ደግሞ ሕዝብም እግዚአብሔርም አብረውት ናቸው።



ጉዳያችን GUDAYACHN

ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።