ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, September 21, 2015

የመስቀል ደመራ በአል በኢትዮጵያ፣በኦስሎ፣ኖርዌይ እና በመላው ዓለም በመጪው እሁድ ይከበራል።


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ለዓለም በብቸኛ ቅርስነት ከጠበቀቻቸው የማይዳሰሱ ቅርሶች መካከል የመስቀል ደመራ በአል አንዱ ነው።የመስቀል ደመራ በአል ዛሬ ዛሬ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በመላው አለም ተሰደው በሚኖሩ በሚልዮን በሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አማካኝነት አለም የበአሉ ታዳሚ እየሆነ ነው።የውጭ ሃገራት የከተማ አስተዳደር የባህል ክፍል ኃላፊዎች በከተማቸው ከሚከበሩት በአላት ዝርዝር ውስጥ እያስገቡ አስፈላጊውን የማስተናበር አገልግሎት መስጠት የተለመደ ነው።የአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንም ከዘመን ዘመን በተለያየ ጊዜ ቢሆንም ሽፋን ይሰጡታል።ሆኖም ግን በአለም አቀፍ ደረጃ በአሉ በአግባቡ እንዲታወቅ እና በበቂ ሁኔታ አለም አቀፍ ሽፋን እንዲያገኝ ብዙ የሚሰሩ ስራዎች ይቀራሉ።በእርግጥ በአሉ በተባበሩት መንግሥታት የሳይንስ፣የትምህርት እና የባህል ኮሚሽን ''በዓለም የማይዳሰስ ቅርስነት'' መመዝገቡ ቤተ ክርስቲያኒቱ ለአለም ጠብቃ ቅርስ የማቆየቷ አንዱ ማስረጃ ነው።

በዘንድሮ የመስቀል ደመራ በአል ላይ ለመገኘት በሀገር ቤት የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያሪክ ብፁዕ አቡነ ቴዎድሮስ ካልዕ ወደ ሀገር ቤት እንደሚያመሩ ከአዲስ አበባ ተሰምቷል።የግብፅ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ግንኙነት የረጅም ጊዜ ታሪክ ያለው ነው።የእዚህ አይነቱ ጉብኝት ከፕሮቶኮል  እና በቀለማት ካሸበረቀ የአደባባይ በአል አከባበር ባለፈ በከፍተኛ የአስተዳደር ችግር ላይ የምትገኘውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቀና አባቶች እና ምእመናን  በግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የአስተዳደር እና የገንዘብ አያያዝ እና ቁጥጥር ዘዴዎች መንፈሳዊ ቅናት እንደሚያድርባቸው ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እስከ ባለስልጣናት እና ዋልጌ ነጋዴዎች ድረስ በተዘረጋ የሙስና መዋቅር ውስጥ ተዘፍቃ በከፍተኛ ችግር ላይ እንደምትገኝ የአደባባይ ምስጢር ነው።በቅርቡ ሀገር አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ህብረት ግልፅ፣ሰላማዊ እና ቁርጥ አላማ የያዘ ጥያቄ በማንሳት  በሙሰኛ የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች ላይ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ እና የቤተ ክርስቲያኒቱ  የማይገሰስ መንፈሳዊም ሆነ ሞራላዊ ልዕልና እንዲጠበቅ መጠየቁ ይታወቃል።ሀገር አቀፍ እንቅስቃሴው ከቤተ ክርስቲያን አባቶች አልፎ የመንግስት አካላትን በየደረጃው በጉዳዩ ላይ ተነጋግሯል።ይህ ጉዳይ ያስጨነቃቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ የበላይ አባቶችም የችግሩን ቅርንጫፎች በየንግግራቸው መሃል ለማንሳት ተገደዋል።ሆኖም ግን ችግሩን ለመፍታት የቆረጠ እርምጃ ሲወስዱ አልተስተዋሉም።

የመስቀል ደመራ በአል ከሀገር ውስጥ አልፎ በመላው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ በአንድ አደባባይ የሚያገናኝ፣ሕፃናትን እና ወጣቶችን ትንሿን ኢትዮጵያ የሚያሳያቸው እና እንዲናፍቁ የሚያደርጋቸው አንዱ አጋጣሚ ነው እና ልንንከባከበው ይገባል።ሀገር በወታደር፣በፖለቲካ እና በገንዘብ ብዛት ብቻ አንድ ሆኖ ከትውልድ ወደ ትውልድ አይሸጋገርም።እንደዛ ቢሆን ኖሮ በሀብት እና በጦር ኃይል የተነከሩ ሀገሮች በየዘመኑ እየተሰባበሩ ታሪካቸው አመድ አይሆንም ነበር።ሀገር በማኅበራዊ እሴቶቿ፣ሕዝብ ዋጋ በሚሰጣቸው የሃይማኖት ስርዓት ሁሉ አንድነቷ ሳይናጋ ትውልድ ተሻጋሪ ትሆናለች።በመሆኑም የመስቀል ደመራ የመሰሉ ብሔራዊ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ  
መገለጫቸው ጉልህ የሆኑ በአላት ፋይዳቸው ብዙ ነው።

ከእዚህ በታች የመስቀል ደመራ በአል ለምን ይከበራል? እውነተኛው የክርስቶስ መስቀል ወደሀገራችን እንዴት፣መቼ እና በማን መጣ? የሚሉትን እና በአሉ በዩኔስኮ  ( UNESCO) የተመዘገበበት ዘገባ የያዙ ማስፈንጠርያዎች (link) ከእዚህ በታች ማግኘት ይችላሉ።

ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
መስከረም 10/2008 ዓም (ሴፕቴምበር 21/2015)

Saturday, September 19, 2015

የአሜሪካ መከላከያ መስርያ ቤት (ፔንታጎን) በሩስያ የባልቲክ አቅጣጫ መስፋፋት አንፃር አዲስ የጦር እቅድ እያዘጋጀ ነው The Pentagon Is Preparing New War Plans for a Baltic Battle Against Russia

Photo - foreignpolicy.com
September 18, 2015

For the first time since the collapse of the Soviet Union, the U.S. Department of Defense is reviewing and updating its contingency plans for armed conflict with Russia.

The Pentagon generates contingency plans continuously, planning for every possible scenario — anything from armed confrontation with North Korea to zombie attacks. But those plans are also ranked and worked on according to priority and probability. After 1991, military plans to deal with Russian aggression fell off the Pentagon’s radar. They sat on the shelf, gathering dust as Russia became increasingly integrated into the West and came to be seen as a potential partner on a range of issues. Now, according to several current and former officials in the State and Defense departments, the Pentagon is dusting off those plans and re-evaluating them, updating them to reflect a new, post-Crimea-annexation geopolitical reality in which Russia is no longer a potential partner, but a potential threat.

“Given the security environment, given the actions of Russia, it has become apparent that we need to make sure to update the plans that we have in response to any potential aggression against any NATO allies,” says one senior defense official familiar with the updated plans.

“Russia’s invasion of eastern Ukraine made the U.S. dust off its contingency plans,” says Michèle Flournoy, a former undersecretary of defense for policy and co-founder of the Center for a New American Security. “They were pretty out of date.”

Designing a counteroffensive

The new plans, according to the senior defense official, have two tracks. One focuses on what the United States can do as part of NATO if Russia attacks one of NATO’s member states; the other variant considers American action outside the NATO umbrella. Both versions of the updated contingency plans focus on Russian incursions into the Baltics, a scenario seen as the most likely front for new Russian aggression. They are also increasingly focusing not on traditional warfare, but on the hybrid tactics Russia used in Crimea and eastern Ukraine: “little green men,” manufactured protests, and cyberwarfare. “They are trying to figure out in what circumstances [the U.S. Defense Department] would respond to a cyberattack,” says Julie Smith, who until recently served as the vice president’s deputy national security advisor. “There’s a lively debate on that going on right now.”

This is a significant departure from post-Cold War U.S. defense policy.

After the Soviet Union imploded, Russia, its main heir, became increasingly integrated into NATO, which had originally been created to counter the Soviet Union’s ambitions in Europe. In 1994, Moscow signed onto NATO’s Partnership for Peace program. Three years later, in May 1997, Russia and NATO signed a more detailed agreement on mutual cooperation, declaring that they were no longer adversaries. Since then, as NATO absorbed more and more Warsaw Pact countries, it also stepped up its cooperation with Russia: joint military exercises, regular consultations, and even the opening of a NATO transit point in Ulyanovsk, Russia, for materiel heading to the fight in Afghanistan. Even if the Kremlin was increasingly miffed at NATO expansion, from the West things looked fairly rosy.

After Russia’s 2008 war with neighboring Georgia, NATO slightly modified its plans vis-à-vis Russia, according to Smith, but the Pentagon did not. In preparing the 2010 Quadrennial Defense Review, the Pentagon’s office for force planning — that is, long-term resource allocation based on the United States’ defense priorities — proposed to then-Secretary of Defense Robert Gates to include a scenario that would counter an aggressive Russia. Gates ruled it out. “Everyone’s judgment at the time was that Russia is pursuing objectives aligned with ours,” says David Ochmanek, who, as deputy assistant secretary of defense for force development, ran that office at the time. “Russia’s future looked to be increasingly integrated with the West.” Smith, who worked on European and NATO policy at the Pentagon at the time, told me, “If you asked the military five years ago, ‘Give us a flavor of what you’re thinking about,’ they would’ve said, ‘Terrorism, terrorism, terrorism — and China.’”

Warming to Moscow

The thinking around Washington was that Mikheil Saakashvili, then Georgia’s president, had provoked the Russians and that Moscow’s response was a one-off. “The sense was that while there were complications and Russia went into Georgia,” Smith says, “I don’t think anyone anticipated that anything like this would happen again.” Says one senior State Department official: “The assumption was that there was no threat in Europe.” Russia was rarely brought up to the secretary of defense, says the senior defense official.

Then came the Obama administration’s reset of relations with Russia, and with it increased cooperation with Moscow on everything from space flights to nuclear disarmament. There were hiccups (like Russia’s trying to elbow the United States out of the Manas base in Kyrgyzstan) and less-than-full cooperation on pressing conflicts in the Middle East (the best the United States got from Russia on Libya was an abstention at the U.N. Security Council). But, on the whole, Russia was neither a danger nor a priority. It was, says one senior foreign-policy Senate staffer, “occasionally a pain in the ass, but not a threat.”

Ochmanek, for his part, hadn’t thought about Russia for decades. “As a force planner, I can tell you that the prospect of Russian aggression was not on our radar,” he told me when I met him in his office at the Rand Corp. in Northern Virginia, where he is now a senior defense analyst. “Certainly not since 1991, but even in the last years of Gorbachev.” Back in 1989, Ochmanek thought that Washington should be focusing on the threat of Iraq invading Kuwait, not on the dwindling likelihood of Soviet military aggression. For the last 30 years, Ochmanek has shuttled between Rand, where he has focused on military planning, and the nearby Pentagon, where he has done the same in an official capacity: first in the mid-1990s, when he was the deputy assistant secretary of defense for strategy, and then for the first five years of Barack Obama’s administration, when he ran force planning at the Pentagon.

It was there that, in February 2014, Russian President Vladimir Putin caught Ochmanek and pretty much every Western official off guard by sending little green men into Crimea and eastern Ukraine. “We didn’t plan for it because we didn’t think Russia would change the borders in Europe,” he says. Crimea, he says, was a “surprise.”

War games, and losing

In June 2014, a month after he had left his force-planning job at the Pentagon, the Air Force asked Ochmanek for advice on Russia’s neighborhood ahead of Obama’s September visit to Tallinn, Estonia. At the same time, the Army had approached another of Ochmanek’s colleagues at Rand, and the two teamed up to run a thought exercise called a “table top,” a sort of war game between two teams: the red team (Russia) and the blue team (NATO). The scenario was similar to the one that played out in Crimea and eastern Ukraine: increasing Russian political pressure on Estonia and Latvia (two NATO countries that share borders with Russia and have sizable Russian-speaking minorities), followed by the appearance of provocateurs, demonstrations, and the seizure of government buildings. “Our question was: Would NATO be able to defend those countries?” Ochmanek recalls.

The results were dispiriting. Given the recent reductions in the defense budgets of NATO member countries and American pullback from the region, Ochmanek says the blue team was outnumbered 2-to-1 in terms of manpower, even if all the U.S. and NATO troops stationed in Europe were dispatched to the Baltics — including the 82nd Airborne, which is supposed to be ready to go on 24 hours’ notice and is based at Fort Bragg, North Carolina.

“We just don’t have those forces in Europe,” Ochmanek explains. Then there’s the fact that the Russians have the world’s best surface-to-air missiles and are not afraid to use heavy artillery.

After eight hours of gaming out various scenarios, the blue team went home depressed. “The conclusion,” Ochmanek says, “was that we are unable to defend the Baltics.”

Ochmanek decided to run the game on a second day. The teams played the game again, this time working on the assumption that the United States and NATO had already started making positive changes to their force posture in Europe. Would anything be different? The conclusion was slightly more upbeat, but not by much. “We can defend the capitals, we can present Russia with problems, and we can take away the prospect of a coup de main,” Ochmanek says. “But the dynamic remains the same.” Even without taking into account the recent U.S. defense cuts, due to sequestration, and the Pentagon’s plan to downsize the Army by 40,000 troops, the logistics of distance were still daunting. U.S. battalions would still take anywhere from one to two months to mobilize and make it across the Atlantic, and the Russians, Ochmanek notes, “can do a lot of damage in that time.”

Ochmanek has run the two-day table-top exercise eight times now, including at the Pentagon and at Ramstein Air Base, in Germany, with active-duty military officers. “We played it 16 different times with eight different teams,” Ochmanek says, “always with the same conclusion.”

The Defense Department has factored the results of the exercise into its planning, says the senior defense official, “to better understand a situation that few of us have thought about in detail for a number of years.” When asked about Ochmanek’s conclusions, the official expressed confidence that, eventually, NATO would claw the territory back. “In the end, I have no doubt that NATO will prevail and that we will restore the territorial integrity of any NATO member,” the official said. “I cannot guarantee that it will be easy or without great risk. My job is to ensure that we can reduce that risk.”

Protect the Baltics

That is, the Pentagon does not envision a scenario in which Russia doesn’t manage to grab some Baltic territory first. The goal is to deter — Defense Secretary Ashton Carter announced this summer that the United States would be sending dozens of tanks, armored vehicles, and howitzers to the Baltics and Eastern Europe — and, if that fails, to painstakingly regain NATO territory.

The Pentagon is also chewing on various hybrid warfare scenarios, and even a nuclear one. “As you look at published Russian doctrine, I do believe people are thinking about use of tactical nuclear weapons in a way that hadn’t been thought about for many years,” says the senior defense official. “The doctrine clearly talks about it, so it would be irresponsible to not at least read that doctrine, understand what it means. Doctrine certainly doesn’t mean that they would do it, but it would be irresponsible to at least not be thinking through those issues. Any time there is nuclear saber rattling, it is always a concern, no matter where it comes from.”

There is a strong element of disappointment among senior foreign-policy and security officials in these discussions, of disbelief that we ended up here after all those good years — decades, even — in America’s relations with Russia.

“A lot of people at the Pentagon are unhappy about the confrontation,” says the State Department official. “They were very happy with the military-to-military cooperation with Russia.” There are also those, the official said, who feel that Russia is a distraction from the real threat — China — and others who think that working with Russia on arms control is more important than protecting Ukrainian sovereignty. Not only would they rather not have to think about Moscow as an enemy, but many are also miffed that even making these plans plays right into Putin’s paranoid fantasies about a showdown between Russia and NATO or between Russia and the United States — which makes those fantasies, de facto, a reality. In the U.S. planning for confrontation with Russia, says the Senate staffer, Putin “is getting the thing he always wanted.”

Yet despite this policy shift, the distinctly American optimism is confoundingly hard to shake. “We would like to be partners with Russia. We think that is the preferred course — that it benefits us, it benefits Russia, and it benefits the rest of the world,” the senior defense official says. “But as the Department of Defense, we’re not paid to look at things through rose-colored glasses and hence must be prepared in case we’re wrong about Russia’s actions and plan for if Russia were to become a direct adversary. Again, I don’t predict that and I certainly don’t want it, but we need to be prepared in case that could happen.”

Provocation or preparation?

So far, the Pentagon’s plans are just that — plans. But they are also signals: to Russia that the United States is not sitting on its hands, and to Congress that America’s foreign-policy priorities have shifted drastically since the last Quadrennial Defense Review, which was released as the crisis in Ukraine was unfolding and barely mentioned Russia. It is also a signal that the Pentagon feels that sequestration hobbles its ability to deal with the new threat landscape. In his July confirmation hearing to ascend to the chairmanship of the Joint Chiefs of Staff, Gen. Joseph Dunford made headlines when he said that Russia posed an “existential threat” to the United States and said that America must do more to prepare itself for hybrid warfare of the type Russia deployed in Ukraine.

“It’s clearly a signal to the Hill,” says Smith. “When I come and ask for a permanent presence in Europe or money for a European presence, I don’t want you to say, ‘Gee, this is a surprise. I thought it was all about [the Islamic State].’” Dunford’s statement angered the White House, which saw it as potentially provocative to Moscow, but it was also a signal to everyone else. The commander in chief has the final say on whether to use these new contingency plans, but Obama’s days in office are numbered, and the Pentagon isn’t taking any chances.



ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

Thursday, September 17, 2015

ሰበር ዜና - የምዕራብ አፍሪካዊቱ ሀገር የቡኪና ፋሶ መንግስት ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ተደረገበት።


በአዲሱ መፈንቅል አድረጊ ወታደሮች የታገቱት ጊዚያዊ ፕሬዝዳንት  ካፋንዶ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ሌ/ኮ/ ኢሳቅ ዚዳ   Photo - BBC

የቡኪና ፋሶ ፕሬዝዳንታዊ ዘብ ከሰአታት በፊት መንግስቱን መቆጣጠሩን እና በድንገቱም አስር ሰዎች መሞታቸውን ለማወቅ ተችሏል።ቢቢሲ ወታደሮቹ የመንግስቱን የቴሌቭዥን ጣቢያ መቆጣጠራቸውን እና የእድገት እና የዲሞክራሲ ምክርቤት ፓርቲ መሪ ፕሬዝዳንት ብሌር ካምፓዌሪ ( B. Compaore) የቅርብ ሰው ጀነራል ግልበርት ዴንደረ ( Gen Gilbert Diendere) የሀገሪቱ መሪ እንደሚሆኑ ወታደሮቹ ማስታወቃቸው ተዘግቧል።

ጊዜያዊ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ፕሬዝዳንት ሚቸል ካፋንዶ ( Michel Kafando) እና ጠቅላይ ሚኒስትር ኢሳቅ ዝዳ  (Isaac Zida) ቀደም ብለው በካቢኔ ስብሰባ ላይ ሳሉ ድንገት ዘው ብለው በገቡ ወታደሮች መታገታቸው እና  የአስር ወራትን ያስቆጠረ ጊዜያዊ መንግስታቸው መፈፀሙ እንደተነገራቸው ተሰምቷል።የቀድሞ የቡኪና ፋሶ ቅኝ ገዢ  ፈረንሳይ ድርጊቱን ተቃውማለች። 

የአፍሪካ መሪዎች ዲሞክራሲያዊ አስተዳደርን በአግባቡ መዘርጋት ሲያቅታቸው የጦር ሰራዊቱ ሃገራቱ ''ወደ ባሰ ትርምስ ከመግባታቸው በፊት''በሚል ሰበብ የስልጣን ኮርቻውን ሲቆጣጠሩት ይታያል።በቅርቡ በምስራቅ አፍሪቃዊቷ ሀገር ቡሩንዲ ተመሳሳይ ያልተሳካ መፈንቅለ መንግስት ሙከራ መደረጉ እና ከእዚያን ጊዜ ወዲህም የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ካለፈው ለመማር አለመቻላቸው ሌላው አስገራሚ ጉዳይ ነው።


ጊዜያዊ መንግስቱን ከስልጣን ያወረዱት ጀነራል ዲያንደር (Gen Diendere )  
                        Photo - BBC 

ቅጥ ያጡ ጎጠኞች እና ሙሰኞች መሪዎችን ለማስወገድ ብዙ ሺዎች ከሚያልቁ እውነተኛ ወታደሮች ሃገርን ወደ ባሰ ትርምስ ከሚመሩ ጉልበተኞች ማዳናቸው ክፉ ሥራ አይደለም የሚሉ አሉ።የቡኪናው ጉዳይ ግን ከእዚህ የተለየ ይመስላል።ምክንያቱም ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ፕሬዝዳንት በመጪው ጥቅምት ወር ላይ በሚደረገው ምርጫ ስልጣን ያስረክባሉ ተብሎ ይጠበቅ ነበር።እውነት ሊያስረክቡ ነበር? ወይንስ እንደ ህወሃት ምርጫ አጭበርብረው ስልጣን ላይ ሊቀመጡ አስበው ነበር? የሚለው ጥያቄ እንዳለ ሆኖ።


ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
መስከረም 6/2008 ዓም (ሴፕቴምበር 17/2015)

የዜናው ምንጭ - ቢቢሲ ነው ( BBC)

Sunday, September 13, 2015

የአቶ ሞላ መጥፋት በህወሀት፣ሱዳን እና ሻቢያ መሃከል የሚፈጥረው አዲስ የፖለቲካ ትኩሳት እና አሰላለፍ (የጉዳያችን ጡመራ አጭር ማስታወሻ)



  • ''አቶ ሞላ አስገዶም ሱዳን ውስጥ ወደ አልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል።አብረውት የነበሩት ታጣቂዎች ትጥቅ ፈትተው ከሰላ ውስጥ ናቸው'' ሱዳን ትሪቡን ጋዜጣ 
  • ''ሞላ ከታጣቂዎቹ ጋር ኢትዮጵያ ገብቷል የሱዳን መንግስትን እናመሰግናለን'' ፋና ራድዮ


የትግራይ ሕዝብ ንቅናቄ ድርጅት (ትህዴን) ሊቀመንበር አቶ ሞላ አስገዶም ከነበሩበት ኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ ማምለጣቸውን አርብ ምሽት ላይ በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን ተዘግቧል።ይህንኑ ዜና መስከረም 2/2008 ዓም የኢህአዴግ/ህወሃት ልሳንነቱ የሚነገርለት ራድዮ ፋና ''ራሱን የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/ በማለት የሚጠራው እና በኤርትራ ውስጥ ሲንቀሳቀስ የነበረው የጦር ክፋይ ትናንት ወደ ሀገሩ ገባ።'' በማለት ዘግቧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሱዳን ታዋቂ የእንግሊዝኛ ጋዜጣ ''ሱዳን ትሪቡን'' የአቶ ሞላን ማምለጥ እና ኢትዮጵያን፣ሱዳንን እና ኤርትራን በምታዋስነው ሃምዳይት ከተማ አካባቢ ከኤርትራ ወታደሮች ጋር ግጭት እንደነበር እና የሱዳን ወታደሮች ሽፋን ሰጥተው ታጣቂዎቹ ትጥቃቸውን ለሱዳን ወታደሮች ማስረከባቸውን እና ወደ ሱዳን ከሰላ ግዛት በምትገኘው ዋድ-አል-ሂሉ ከተማ መወሰዳቸውን እና መሪዎቻቸው ወደ አልታወቀ የሱዳን ከተሞች መወሰዳቸውን ጋዜጣው አክሎ ያብራራል።

የአቶ ሞላ መጥፋት በህወሃት ፣ሱዳን እና ሻብያ መሃከል የሚፈጥረው አዲስ የፖለቲካ ትኩሳት

የትግራይ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ሞላ አስገዶም ሁለት የፖለቲካ ትኩሳቶችን እንደ አዲስ ሊቀሰቅሱ ይችላሉ።እነርሱም በሱዳን እና በኤርትራ መካከል ያለውን ግንኙነት ማሻከር እና በትግራይ ተወላጆች እና በኤርትራውያን መካከል አዲስ የበቀል ስሜት ሊፈጥር የመቻሉ ድንገት ነው።

በሱዳን እና በኤርትራ መካከል ያለውን ግንኙነት ማሻከር


በሱዳን እና በኤርትራ መካከል የነበሩ ይቆዩ ግንኙነቶች አንድ ጊዜ ሲሰምር ሌላ ጊዜ ሲደበዝዝ እና እንደ ኳታር ያሉ ሀገሮችን ሸምጋይነት እየጠየቁ ቀጥለዋል።ካለፉት ሁለት አመታት ወዲህ ግን የአቶ ኢሳያስ እጅ ደቡብ ሱዳን ውስጥ መገኘት እና ለደቡብ ሱዳን ፖለቲካ ከህወሃት ተቃራኒ መቆም ሁሉ ሱዳን ከኤርትራ ጋር ያላት ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲዋዥቅ አድርጎታል።

ይህ በእንዲህ እያለ ነው እንግዲህ ከኤርትራ አምልጠው ሱዳን ከሰላ ግዛት ገብተው እና በሱዳን ወታደሮች ተደግፈው እንደ ፋና አገላለፅ ኢትዮጵያ ገቡ የተባሉት የአቶ ሞላ ጉዳይ የሳምንቱ መጨረሻ ወሬ የሆነው።ይህ ማለት ሱዳን ቀድሞውንም ከሀወሃት ጋር ተነጋግራ ነበር ማለት ነው? ያልተነጋገረች ቢሆንስ ከኤርትራ እየተፈለገ መሆኑን ያወቀች ግለሰብን ኤርትራ ውስጥ ምን አይነት የፀጥታ ችግር እንደፈጠረ ሳታውቅ ለኢትዮጵያ አሳልፋ ትሰጣለች ማለት ነው?
በእዚህም በኤርትራ ላይ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በሚስጥር የደረሰችው ስምምነት አለ ማለት ነው? እነኝህ እና ሌሎች ጥያቄዎች በሙሉ በሱዳን እና በኤርትራ ማካከል የነበሩ ግንኙነቶችን የሚያጎድፉ ናቸው።በተለይ ሱዳን ላደረገችው አስተዋፅኦ ምስጋና አቀረበ የተባለው የህወሃት መንግስት በኤርትራ እና ሱዳን መካከል አዲስ ቅራኔ የሚፈጥር ነው።

ይህ ብቻ አይደለም በደቡብ ሱዳን ጉዳይ ላይ አዳዲስ አሰላልፍ የምትፈልገው አሜሪካ ከሱዳን ጋር የሚኖሩ ግጭቶች ለኤርትራ ከአሜሪካን ጋር ግንኙነት ለማደስ ጥረት እያደረገች ነው እየተባለ ሰሞኑን የሚነገረው ዜና አዲስ ኃይል ይጨምራል።ሱዳን እራሷን ከኢትዮጵያም ሆነ ከኤርትራ ወገን ባለመሆን ገለልተኛነትን ለማራመድ ስለሚቸግራት አጣብቂኝ ውስጥ የመግባት እድሏ ትልቅ ነው።በእዚህ ሁሉ መካከል ግን ኤርትራ ውስጥ የመሸጉት የህወሃት ተቃዋሚ ኃይሎች  አመቺ የመጠናከርያ ዕድል እንደተከፈተላቸው ለማወቅ ይቻላል።ይሄውም አቶ ኢሳያስ ሙሉ ኃይላቸውን በጸረ-ሱዳን እና ህወሃት መንገዳቸው ከኢትዮጵያ የነፃነት ኃይሎች ጋር በጠነከረ መንገድ እንዲቆሙ የሚያደርጋቸው ነው።


በትግራይ ተወላጆች እና በኤርትራውያን መካከል አዲስ የበቀል ስሜት ሊፈጥር የመቻሉ ድንገት

የአቶ ሞላን በሱዳን በኩል አድርጎ መሸሽ በተመለከተ ከህወሃት መንደር እና ከኤርትራ ተወላጆች በኩል የሚሰሙት በሁለቱ መካከል ያሉ እልሆች እና የበለጠ መካረር ተከስቷል።ህወሃት በመንደሩ ለአንድ ዓመት ያህል የሰራሁት ''ኦፕሬሽን'' ነው የሚል እና ''አቶ ኢሳያስ ስር ሆነን አቶ ኢሳያስን ጉድ ሰራናቸው'' የሚል ከበሮ ሲያሰማ በኤርትራ ተወላጆች በኩል ደግሞ  በተለይ ጉዳዩን አስመልክተው ሃሳባቸውን በማህበራዊ ሚድያ የሚገልፁትን ስንመለከት በትግራይ ተወላጆች ላይ ከፍተኛ ጥላቻ  እንደነበራቸው እና ቀድሞውንም ትግራዮችን ማስጠጋት አልነበረብንም የሚል መልክት ሲተላለፍ ለመመልከት ይቻላል። 

በአንድ ማህበራዊ ድረ-ገፅ ላይ በተለይ አንዲት ኤርትራዊት እንደፃፈችው ''የአስመራን መንገዶች ያቆሸሸው ሞላ ከእነ ሰራዊቱ መልቀቅ ነበረበት እነርሱ  እንደ ሌላው ኢትዮጵያዊ በክብር ሊታዩ አይገባም ሌላው ኢትዮጵያዊ የሰለጠነ ነው፣ ወዘተ'' የሚሉ ፅሁፎችን አስነብባለች።ይህ ሁሉ የሚያሳየን በ1990 ዓም '' የአይናችሁ ቀለም አላማረኝም ብለን ኤርትራውያንን የማባረር መብት አለን'' ብለው ቃል በቃል የተናገሩት አቶ መለስ እና ንግግራቸውን ተከትሎ ከ70 ሺህ በላይ የሚሆኑ ንፁሃን ትውልደ ኤርትራውያን በግፍ ከተባረሩበት ድርጊት ጋር ተያይዞ እና አሁን አቶ ሞላ ምናልባትም (ገና ጉዳዩ በዝርዝር ስላልታወቀ) በትግራይነት ስሜት ብቻ ያስጠለሏቸውን ከድተው የመሄዱ ሂደት ቅራኔዎቹን ያባብሳሉ እንጂ ምንም አይነት የማብረድ ሁኔታን አያሳዩም።

በመጨረሻ ግን የአቶ ሞላ መሸሽም ሆነ ክህደት የሚያሳየው መጪው ጊዜ በኤርትራ የመሸጉትን የነፃነት ኃይሎች ጥንካሬን የሚያመጣ እንጂ ምንም አይነት ጉልህ ተፅኖ የለውም ማለት ይቻላል።ለእዚህም ምክንያቶቹ የትህዴንን ሰራዊት ጨምሮ አርበኞች ግንቦት 7፣የአፋር ንቅናቄ እና የአማራ ንቅናቄ በአንድነት ጥምረት መፍጠራቸው እና አቶ ሞላ ይብሱን የበለጠ ጉዳት በነፃነት ኃይሎች ላይ ሊፈጥሩ የሚችሉበት ዕድል በአጭሩ መሰናከሉ የሚሉትን መጥቀሱ ይበቃል።ህወሃት መቼም ቢሆን በጊዜያዊ እይታ ላይ ብቻ መመርኮዙ እና ቀጥሎ የሚመጣውን የመመልከት ችግር ስለሚያጠቃው ከሰሞኑ ቀድሞ አሸባሪ ሲለው የነበረውን ''ሀገር ወዳድ'' እያለ በማሞካሸት እና ሻብያ ያሰበውን አዲስ ሴራ አገኘሁ የሚሉ ፕሮግራሞችን በቲቪ ደጋግሞ በማሳየት የህዝብን የነፃነት ጥያቄ ለማድበስበስ ይሞክር ይሆናል።ሆኖም ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከእሩብ ክ/ዝመን በላይ ይታለላል ብሎ ማሰብ ዘበት ነው።ላለፉት ሃያ አራት አመታት የነበሩ የህወሃት ተመሳሳይ የፕሮፓጋንዳ ዜማዎች አሁን ላይ ይሰራሉ ማለት ዘበት ነው።የሚሆነው ግን አቶ ኢሳያስም የበለጠ የኢትዮጵያን የነፃነት ኃይሎች የመደገፍ ሥራ በበለጠ እንዲገፉበት የኢትዮጵያ የነፃነት ሃሎችም ሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ የበለጠ ለነፃነት ትግሉ እንዲነሱ ከማድረግ ያለፈ አንዳች ፋይዳ አይኖርም። 

ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG
መስከረም 3/2008 (ሴፕቴምበር 14/2015)

Wednesday, September 9, 2015

የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ከአውሮፓውያን ጋር ያለው ልዩነት መንስኤ እና ትክክለኛ መሰረቱ


--------------------
ጉዳያችን ልዩ ጥንቅር 
===========
የዘመን መስፈሪያዎች

እግዚአብሔር «ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ፣ ለዕለታት፣ ለዘመናትና ለዓመታት ምልክት ይሆኑ ዘንድ» / ዘፍ.1. 14- 15/ የፈጠራቸውን የፀሐይንና የጨረቃን እንቅስቃሴ መሠረት ያደረጉት መስፈሪያዎች ናቸው፡፡ እነዚህም፤

ሀ. ዕለት 

አንድ ዕለት አንድ ቀንን /የብርሃን ክፍለ ጊዜን / እና አንድ ሌሊትን /የጨለማ ክፍለ ጊዜን/ ያካተተ ፀሐይ አንድ ጊዜ ከወጣች በኋላ ተመልሳ እስክትወጣ ድረስ ያለውን ጊዜ የያዘ ነው፡፡ በአሁኑ ዕውቀታችን አንድ ዕለት ምድር በራሷ ዛቢያ አንድ ጊዜ የምትሸከረከርበት ጊዜ ነው፡፡

ለ. ውርኅ

ወርኅ ማለት በግእዝ ጨረቃ ማለት ነው፡፡ አንድ ወርኅ የሚባለው ጊዜ ሙሉ ጨረቃ ከወጣች በኋላ ድጋሚ እስከምትወጣ ድረስ ያለው ጊዜ ነው፡፡ በአሁኑ ዕውቀታችን / በጥንቱም ጨምሮ/ ይህ ጨረቃ መሬትን አንድ ጊዜ ዙራ ለመጨረስ የሚፈጅባት ጊዜ ነው፡፡ አንድ ወር ሃያ   ዘጠኝ ተኩል ዕለታትን ይፈጃል፡፡
   
ሐ. ዓመት

አንድ ዓመት ማለት መሬት አንድ ጊዜ በፀሐይ ዙሪያ ለመዞር የሚፈጅባት ጊዜ ነው፡፡ ይህም 365 ከ1/4 / ሦስት መቶ ስድሳ አምስት ቀን ከሩብ/ ዕለታት ይፈጃል፡፡ይህ ከመታወቁ በፊትም ግን የዓመት ጽንሰ ሓሳብ ነበር፡፡ ፕሮፊሰር ጌታቸው ኃይሌ የፅንሰ ሐሳቡን አመጣጥ እንዲህ ያስረዳሉ፡፡
ሰዎች ርዝመታቸው እኩል የሆኑ ሁለት  ሻማዎችን ሠሩና ልክ ፀሐይ ስትወጣ /ቀኑ ሲያልቅና ሌሊቱ ሲጀምር/  አንዱን ሻማ አበሩት፡፡ልክ ፀሐይ ስትወጣ እሱን አጠፋና ሌላውን / ሁለተኛውን/ ሻማ አበሩት፤ ጧት ፀሐይ እንደገና ስትወጣ / ሌሊቱ አልቆ ሌላ ቀን ሲጀምር/ ሻማውን አጠፉት፡፡ አሁን እንግዲህ ከየሻማዎቹ /ከሁለቱ ሻማዎች/ ምን ያህል እንደተቃጠለላቸው ሲያስተያዩት ከሁለቱ ሻማዎች የተቃጠለው እኩል አለመሆኑን ተመለከቱ በዚህም የቀኑና የሌሊቱ ርዝማኔ እኩል አለመሆኑን ተረዱ፡፡

ቀደም ብለውም የቀኑና የሌሊቱ ርዝማኔ በተለያዩ ወቅቶች የተለያየ መሆኑን ልብ ብለው ነበርና ይህንን ሙከራቸውን ሲቀጥሉ በቀኑና በሌሊቱ ርዘማኔ / በሚቃጠለው የሻማዎቹ መጠን/ መካከል ያለው ልዩነት ከወቅት ወቅት የተለያየ እንደሆነ ተመለከቱ ይህን ሙከራቸውን ሲቀጥሉ ግን በየ182 /ተኩል/ ዕለቱ ቀኑና ሌሊቱ እኩል የሚሆኑባቸው ሁለት ዕለታት በዓመት ውስጥ እንዳሉ ተገነዘቡ፡፡ እነዚህ ዕለታት አንዱ የሙቀት ወራት ከመጀመሩ በፊት የሌላው ደግሞ የቅዝቃዜው ወራት ከመጀመሩ በፊት የሚመጡ ናቸው፡፡ ስለዚህ የቀኑና የሌሊቱ ርዝመት አንድ ጊዜ እኩል ሁኖ ደግሞ በዚያው ወቅት እኩል እስከሚሆን ድረስ ያለውን ጊዜ ማለትም / 182 ተኩል + 182 = 365/ ዕለት አንድ ዓመት አሉት፡፡ አሁን ባለን ግንዛቤ ምድር በራሷ ዛቢያ እንደተሽከረከረች በፀሐይ ዙሪያ ትዞራለች፡፡ ምድር በፀሐይ ዙሪያ የምትዞረው ወደ ጎን 23 ተኩል ዲግሪ ያህል አጋድላ ነው፡፡ ይህ የቀንና የሌሊት ርዝመት መለያየትም የሚከሰተው በዚህ ማጋደል ምክንያት ነው፡፡

እንግዲህ በአጠቃላይ ዋናዎቹ የጊዜ / የዘመን/ መስፊሪያዎች ዕለት፣ ወር እና ዓመት ናቸው፡፡ ሦስትቱም ተመላላሽ ክስተቶችን / ለምሳሌ የፀሐይን መውጣት/ መሠረት ያደረጉ ናቸው፡፡ እነዚሀ ተመላላሽ ክስተቶች አንድ ጊዜ ከተከሰቱ በኋላ ደግመው እስኪከሰቱ የሚፈጁት ዘመን ወይም ጊዜ  ዓውድ ይባላል፡፡ ዓውድ ማለት ዙሪያ፣ ክብ፣ እንደ ቀለበት ዙሮ የሚገጥም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ዓውድ ማለት ክስተቶቹ አንድ ጊዜ ከተከሰቱ በኋላ ደግመው እስኪመጡ ድረስ ያለው ጊዜ ማለት ነው፡፡

በዚህ መሠረት ከላይ ያየናቸው ሦስት መስፈሪያዎች / ዕለት፣ ወርኀ፣ ዓመት/ ዓዕዋዳት / ዓውዶች/ የሚወጡበት ጊዜ ዓውደ ዕለት፣ ዓውደ ወርኀ፣ ዓውደ ዓመት ይባላሉ፡፡
መጀመሪያ ላይ ሰዎች እነዚህን ሦስቱን መስፈሪያዎች /ዓዕዋዳት/ /በተለይም ቀንና እና ወርን/ ለየብቻቸው ይጠቀሙባቸው ነበር፡፡ ከዚህን ያህል ቀን፣ ከዚህን ያህል ወር በኋላ /በፊት/ እያሉ ጊዜን ይለኩ ነበር፡፡

እነዚህ ሦስቱን በቅንብር /በቅንጅት/ ለመጠቀም ሲፈለግ ግን የዘመን አቆጣጠር ስሌት ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም አንድ ወር 29 ከግማሽ ቀን ነው፡፡
እንዲሁ እንዳለ ለመቁጠር ቢፈለግ የመጀመሪያው ወር ጠዋት ላይ ቢጀመር ሁለተኛው ወር ምሽት ላይ ይጀምራል፣ ሦስተኛው ደግሞ ድጋሚ ጠዋት ላይ ይጀምራል፤ ይህን ለመቅረፍ ወሩን ሙሉ  ሰላሳ ቀን ቢያደርጉት ከትክክለኛው ወር /የጨረቃ ዐውድ/ ግማሽ ቀን ይተርፋል፤ 29 ቀን ብቻ ቢያደርጉት ደግሞ ግማሸ ቀን ይጎድላል፡፡ አንድ ዓመት 365 ከሩብ ዕለታት አሉት፡፡

ዓመትን በወራት ለመቁጠር ቢፈለግ፤ ዓመቱን 12 ወር ቢያደርጉት የዓመቱ /የዕለታት ቁጥር /29.5X12=354/ ብቻ ይሆናል፡፡ ይህም ከትክክለኛው ዓመት /365-354=11/ ዕለታት ያህል ያንሳል፡፡ 13 ወር ቢያደርጉት ዓመቱ /365X13=385.5/ ቀናት ይሆናል ይህም ከትክክለኛው ዓመት /383.5-365=19/ ቀናት ያህል ይበልጣል፡፡
ስለዚህ እነዚህን መስፈሪያዎች በቅንጅት ለመጠቀም ይህንን አለመጣጣም የሚፈታ ቀመር /የዘመን አቆጣጠር ሥርዓት/ ያስፈልጋል፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች የተለያዩ የዘመን አቆጣጠሮች ተዘጋጅተዋል፡፡

የአይሁድ ዘመን አቆጣጠር

የአይሁድ ዘመን አቆጣጠር እያንዳንዳቸው 29 እና 30 ዕለታት ያሏቸው 12 ወራት አሏቸው፤


ተ.ቁ
የአይሁድ ወራት
የዕለታት ብዛት
ወራቱ በእኛ
1
ኒሳን
30
መጋቢት/ ሚያዝያ
2
ኢያር
29
ሚያዝያ/ ግንቦት
3
ሲዋን
30
ግንቦት/ ሰኔ
4
ታሙዝ
29
ሰኔ/ ሐምሌ
5
አቭ
30
ሐምሌ/ ነሐሴ
6
አሉል
29
ነሐሴ/ መስከረም
7
ኤታኒም
30
መስከረም/ ጥቅምት
8
ቡል
29/30
ጥቀምት/ ኅዳር
9
ከሴሉ
30/29
ኅዳር/ ታህሳስ
10
ጤቤት
29
ታህሳስ/ ጥር
11
ሳባጥ
30
ጥር/ የካቲት
12
አዳር 1
29
የካቲት/ መጋቢት

እነዚህ የዓመቱ 12 ወራት በአጠቃላይ 354 ያህል ብቻ ዕለታት ይኖሯቸዋል፡፡ ይህም በትክክለኛው ዓመት በ11 ዕለታት ያህል ቢያንስም አዲስ ዓመት ይጀምራሉ፡፡ ልዩነቱ በሁለት ዓመታት 22 ዕለታት፣ በሦስት ዓመት ደግሞ 33 ዕለታት ያህል ይሆናል፡፡ ስለዚህ በየሦስት ዓመቱ ከአስራ ሁለተኛው ወር ጳጉሜን በፊት አንድ ሌላ ወር ይጨምሩና ጨምረው የዓመቱን የወራት ቁጥር ዐሥራ ሦስት ያደርጉና ልዩነቱን ያስተካክሉታል፡፡

የኢትዮጵያውያንና የግብጻውያን ዘመን አቆጣጠር

የሀገራችን ኢትዮጵያ እና የጥንት ግብጻውያን /ዛሬም ድረስ የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የምትጠቀምበት በሀገር ደረጃ የምትጠቀም ኢትዮጵያ ብቻ ነች/ የዘመን አቆጣጠር ተመሳሳይ ነው፡፡ ሁለታችንም እኩል ሰላሳ ቀናት ያሏቸው 12 ወራት አሉን፡፡ እነዚህ 12 ወራት / 12X30=360/ ቀናት አሏቸው እነዚህ ቀናት በትክክለኛው ዓመት በ/365.25-360=5.25/ ቀናት ያንሳሉ፡፡ ይህንንም 5 ቀናት / በ4 ዓመት አንድ ጊዜ 6 ቀናት/ ያሏትን 13ኛ ወር በመጨመር ያስተካክሉታል፡፡የኢትዮጵያውያን እና የግብጻውያን ወሮች ስም እንደሚከተለው ነው፡፡

ተ.ቁ
የግብጽ ወሮች
የኢትዮጵያ ወሮች
1
ቱት/ዩት
መስከረም
2
ባባ/ፓከር
ጥቅምት
3
ሀቱር
ኅዳር
4
ኪሃክ/ከያክ
ታኅሣሥ
5
ጡባ/ቶቢር
ጥር
6
አምሺር/ሜሺር
የካቲት
7
በረምሃት
መጋቢት
8
በርሙዳ
ሚያዝያ
9
በሸንስ
ግንቦት
10
ቦኩሩ
ሰኔ
11
አቢብ
ሐምሌ
12
መስሪ
ነሐሴ
13
ኒሳ/አፓጎሜኔ
ጳጉሜን
/ባሕረ ሐሳብ፣ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ ፣ገጽ.65/


የኢትዮጵያ ዘመን አቈጣጠር ኢትዮጵያዊ ነው ከሌላ የተቀዳ አይደለም 


የኢትዮጵያ እምነታዊ ባህል የሚወረሰው በሦስት ዐይነት ጠባይ ነው። አንዱ ሕገ ልቡና ይባላል። ከመጽሐፍ በፊት የነበረ ነው። ከአበው ቃል በቃል የተወረሰ ነው። ሁለተኛው በሕገ ኦሪት ከኦሪት የተቀዳ ነው። ሦስተኛው በሕገ ወንጌል ከወንጌል የተማርነው ነው። እና በሦስት ዐይነት ጠባይ የሚመራ ነው። በዚህ ዐይነት ከወረስናቸው በዓላት ማለት በሦስቱም ጠባያት ከወረስናቸው በዓላት የየራሳቸው መልክ ያላቸው አሉ። ለምሳሌ ልደት፥ ጥምቀት፥ ዕርገት፥ ደብረ ታቦር እነዚህን የመሳሰሉት ከወንጌል የተማርናቸው ናቸው፤ በብሉይ የሉም። ፋሲካ፥ በዓለ ጰራቅሊጦስ ደግሞ ከኦሪት የተማርናቸው ናቸው። የዘመን መለወጫ በዓል ግን ከሕገ ልቡና ቃል በቃል ተምረን፥ በኦሪት የመጽሐፍ መሠረት አግኝተንለት በወንጌልም አጽንተን ይዘነው የኖርነው ሦስት የሥራ ዘመን ክፍል የተላለፈና እዚህ የደረሰ ነው። እኛ የዘመን መለወጫ ብለን በሀገራችን ባህል የምናከብረው ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር የተገኘበት፥ ብርሃን፥ ጊዜ፥ ዕለት፥ ሰዓት የተፈጠሩበት፤ ለብርሃን፥ ለጊዜ፥ ለዕለት፥ ለወር ለዓመት ጥንት መሠረት የሆነ ቀን ነው። ይህንን ሁሉ በማስገኘት እግዚአብሔር ራሱን የገለጠበት፥ ዓለምን በመፍጠር ከሃሊነቱን ያረጋገጠበት ቀን ነው ብለን ነው የምናከብረው። ስለዚህም ጥንተ ብርሃን፥ ጥንተ ዕለት፥ ጥንተ ጊዜ፥ ጥንተ ፍጥረት ርእሰ ዐውደ ዓመት ብለን ነው የምናከብረው። በዚህ ስያሜ በዓሉ ርእሰ ዐውደ ዓመት፥ ቅዱስ ዮሐንስ፥ የዘመን መለወጫ ብለን እናከብረዋለን።

ቅዱስ ዮሐንስ


የኢትዮጵያ ዘመን መለወጫ በዓል ሌላው ስሙ ቅዱስ ዮሐንስ ይባላል። ቅዱስ ዮሐንስ የሚባልበትም ሁለት ጠባይ አለው። አንዱ፤ መጥምቁ ዮሐንስ በሄሮድስ አንቲጳስ ጊዜ ከጳጉሜን ቀን ጀምሮ ታስሮ ሰንብቶ በመስከረም ቀን ዐሳብ ስለ ተቆረጠበትና በመስከረም ቀን እንዲሞት ውሳኔ ስለ ተሰጠበት አንገቱን በሰይፍ ተቆርጦ ስለ ሞተ ሊቃውንት ይህንን በዓል እሱ ራሱ ለኦሪትና ለወንጌል መገናኛ መምህር ስለ ነበረ ይህም በዓል ላለፈው ዘመን መሸኛ፥ ለሚመጣው ዘመን መቀበያ እንዲሆን ብለው በመስከረም ቀን እንዲከበር ስላደረጉ በሱ ስም ቅዱስ ዮሐንስ እየተባለ ይጠራል። በሁለተኛው ግን ከአራቱ ወንጌላውያን አንዱ ወንጌላዊ ዮሐንስ የተሰየመበት ስለ ሆነ በአቆጣጠርም ተራ ወደ ኋላ ተመልሶ ቢቈጠር ዓለም የተፈጠረበት ዘመን በዘመነ ዮሐንስ እንዳጋጣሚ ሆኖ ስለሚገኝ ቅዱስ ዮሐንስ ተብሎ ይጠራል።

ዕንቍጣጣሽ


በዚያም ጊዜ የነበሩ ኖኅና ልጆቹ ሰማዩ በደመና በመክበዱ ምክንያት ማየ አይኅ እንደገና ይመጣ ይሆን፥ የጥፋት ውሃ እንደገና ይዘንም ይሆን እያሉ ሲደነግጡ ከርመው በመስከረም ወር መጀመሪያ ላይ ሙሉ የፀሓይ ብርሃን ስላዩ፥ ምድር በአበባ አሸብርቃ ስለ ተገለጠችና በዚህም የእግዚአብሔርን ቸርነት፥ የቃል ኪዳኑን መጽናት ስለ ተረዱ ይህንን በዓል ቀድሞ ከአባቶቻቸው እንደ ወረሱት ያው ጥንተ ብርሃን፥ ጥንተ ዓመት፥ ጥንተ ዕለት አድርገው አክብረውታል። ሲያከብሩትም እንግጫ ነቅለው፥ አበባ ጐንጕነው መጀመሪያ መሥዋዕት ይሠዉነት ከነበረው ቦታ ሄደው ለእግዚአብሔር ገጸ በረከት አቅርበው ከዚያ በኋላ ግን እርስ በርሳቸው የአበባ ስጦታ በመለዋወጥ አክብረውታል። ሲያከብሩትም ዕንቍጣጣሽ በሚል ቃል እውነት የመልካም ሞኞታቸውን ይገላለጡበት ነበር። ዕንቍጣጣሽ ማለትንም ብዙ ታሪክ ጸሓፊዎች በልዩ ልዩ መልክ ተርጕመውታል። እንዲያውም ንጉሡ ሰሎሞን ለሳባ ንግሥት የዕንቍ ቀለበት ሰጥቷት ነበርና «ዕንቍ ለጣትሽ» ማለት ነው ብለው የጻፉ ብዙ ሰዎችም አሉ፤ የሚናገሩም አሉ። ነገሩ ግን እንዲህ አይደለም። ዕንቍጣጣሽ ማለት ተንቈጠቈጠ፥ አንቈጠቈጠ ከሚለው ቃል ተወስዶ ምድር በአበባ አጌጠች፥ ሰማይም በከዋክብት አሸበረቀ እንደ ማለት ሰማይን በከዋክብት ያስጌጠ አምላክ ምድርንም በአበቦች አጎናጸፋት ለማለት የተሰጠ ቃል ነው እንጂ ስለ ሳባ ንግሥት የተሰጠ አይደለም። ሁለተኛም አባቶቻችን ኢትዮጵያን በሙሉ ሀብት ተረክበዋት ነበርና፤ «ዕንቍ ዕጣ ወጣሽ፤» ሲሉ ወደ አገራቸው ሲገቡ ለአገራቸው መታሰቢያ አድርገው የተጠቀሙበት ቃል ነው ይባላል። በመሠረቱ ግን የጥፋት ውሃ ቀርቶ ምድር ጸንታ፥ አበባ ቋጥራ፥ ፍሬ ለመስጠት ተዘጋጅታ መገኘቷን የሚያበሥር ቃል ነው።

መስከረም 

መስከረም የሚባለው ወርም ኖኅ በመርከብ ውሥጥ በነበረ ጊዜ እንደ ዕብራውያን አቈጣጠር ሰባተኛ በሆነው በመስከረም ወር መጀመሪያ ላይ መርከቢቱ አራራት ከሚባለው ተራራ ላይ ዐርፋ ምድር ጨብጣለች። በግእዝ ቋንቋ መርከብ መስቀር ይባላል። ከዘመን ብዛት በኋላ «» ወደ «» ተለውጦ መስከረም ተባለ እንጂ መስቀርም ምድር አገኘች፥ መርከብም ምድር ነካች ለማለት የተሰጠ የወሩ ስያሜ ነው።

ርእሰ ዐውደ ዓመት 


የምንለው፤ ዐውድ ማለት በግእዙ ቋንቋ ዙሪያ፥ ክብ የሆነ ነገር ማለት ነው። የዓመት ጠቅላላ ቀኖች መሠረታውያን ቀኖች የሚባሉት ሦስት መቶ ስድሳ አራት ቀኖች ናቸው። እነዚህም በኀምሳ ሁለት ሱባዔ ተከፍለው ለእያንዳንዱ ቀን በዓመት ውስጥ ለሰባቱ ዕለታት ኀምሳ ሁለት ኀምሳ ሁለት ቀን ይደርሳቸዋል። ከነዚህ ቀኖች የተሳሳበ የሴኮንድ፥ የደቂቃ፥ የሰዓት ዕላፊ ተጠራቅሞ ሦስት መቶ ስድሳ ዐምስተኛዋን የዘመን ማገጣጠሚያ ቀን ያስገኛል። ይህቺ ቀን እንግዲህ ዙሪያ፥ ክብ መግጠሚያ ናት ማለት ነው። በዚህች ቀን አማካይነት ወደ ዐዲሱ ዘመን መጀመሪያ እንተላለፋለን። ይህቺ ቀን ዕለት አዕዋዲት፥ ዕለተ ምርያ የመዘዋወሪያ ቀን ወይም የመጨረሻ ቀን ተብላ ትጠራለች። በአራት ዓመት ደግሞ ከዚህች መሳሳብ የምትገኝ አንዲት ቀን ትመጣለች። ሦስት መቶ ስድሳ ስድስተኛ። ይህቺ ቀን ዕለተ ሰግር ትባላለች። መረማመጃ ማለት ነው። አንድ ቀን ታስተላልፋለች። እንግዲህ እነዚህን ሁለቱን ቀኖች ተከትሎ የሚመጣው ቀን የዘመን መጀመሪያ፥ የዘመን ክብ መነሻና መድረሻ ተብሎ ርእሰ ዐውደ ዓመት ተብሎ በግእዙ ይጠራል። እነዚህ ቀኖች በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ተጠቃለው አንድ ጊዜ የሚገኙ ናቸው።

የኢትዮጵያ ቍጥር መሠረቱ የመፅሐፍ ቅዱስ አካል የሆነው መጽሐፈ ሔኖክ  ነው። መጽሐፈ ሔኖክ በ፲፱፥ ፳፥ ፳፩ እና ፳፪ ምዕራፎች የሚሰጠን የፀሐይን፥ የጨረቃን ጉዞ መነሻ አድርጎ የወሮችን፥ የዕለታትን፥ የዓመታትን መነሻ፥ መድረሻ፥ መዘዋወሪያ ብተታቸውን፥ ጥንታቸውን ነው የሚያሳየው። ስለዚህም በሔኖክ ቍጥር የወር ቀኖች ቍጥር ሠላሳ ናቸው። በሦስት በሦስት ወር ግን አንድ ቀን ትከተላቸዋለች። እና ዓመቱ ለአራት ይከፈላል። በዘጠና አንድ በዘጠና አንድ ቀን። ጠቅላላው ይሄ ድምር ሦስት መቶ ስድሳ ስድስት ቀን ይመጣል። ይህ ካለቀ በኋላ አንዲት ቀን ለዘመን ማገጣጠሚያ ዕለተ ምርያ የምትባለው ትመጣለች። እንግዲህ በኢትዮጵያውያን ቍጥር ወሩ ከሠላሳ አያንስም፤ ከሠላሳ አይተርፍም። ለዓመቱም ሦስት መቶ ስድሳ ዐምስት ቀን መደበኛው አቆጣጠር ነው ማለት ነው። ይህ ነገር በአውሮፓውያን ቍጥርም አለ። ግን እነሱ ከዓመት ወሮች ሰባቱን ሠላሳ አንድ ሠላሳ አንድ አድርገው አራቱን ደግሞ ሠላሳ ሠላሳ አድርገው አንዷን ወር ሦስቱን ዓመት ሃያ ስምንት፥ በአራተኛው ዓመት ሃያ ዘጠኝአድርገው ያጣጧታል። 

እንግዲህ የአቀማመጡ ለውጥ ካልሆነ በስተቀር በቍጥር አካሄድ ዞሮ ዞሮ የዓመት ቀኖች ሦስት መቶ ስድሳ ዐምስት ወይም ሦስት መቶ ስድሳ ስድስት በመሆን አንድ ሆነዋል ማለት ነው። ልዩነቱ ግን የአቀማመጥ ለውጥ ነው። በኢትዮጵያ አቈጣጠር ግን ጠቅላላውን ፲፪ ወሮች መደባቸው ሠላሳ ብቻ ነው። እነዚያ በሔኖክ መጽሐፍ በጣልቃ ገብነት የነበሩት አራት ቀኖች ተጠቅለው ጳጉሜን በሚባል በዓመቱ መጨረሻ ላይ ተገኝተዋል። ዐምስተኛዪቱ ቀንም ከእነሱ ጋር ተገኝታለች። ይህም ለቍጥር ተራ ቅምር መቅናት የተደረገ እንጂ ቀኑን የሚለውጥ ምንም ነገር የለበትም። እና ከእነዚህ ቀኖች በኋላ የምናገኘው ቀን ርእሰ ዐውደ ዓመት ይባላል። ይህንን በዓል ከአዳም ጀምሮ እስከ ኖኅ ድረስ የነበሩ ዐሥሩም አበው በዐሥሩ ትውልድ እስከ ማየ አይኅ ድረስ ሲያከብሩት እንደ ቆዩና ኋላም የኖኅ ልጆች ከአባታቸው ተቀብለው ሲያከብሩት እንደ ነበረ ኩፋሌ የተባለው መጽሐፍ በምዕራፍ ያስረዳናል። እንግዲህ ኢትዮጵያ ይህንን ቀን የወረሰችው ከአበው ነው የምንለው በዚህ ምክንያት ነው።
  

የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ከሌሎቹ የሚለይባቸው መሰረታዊ ምክንያቶች  እና ከኢትዮጵያውያን እና አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ትክክለኛው የቱ ነው? 


ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ የዘመን አቆጣጠር መለያየትን መነሻ እንዲህ በማለት ያብራራሉ፤ «ክብ የሆነ ነገር ሲከብ ከየትኛውም ቦታ መጀመር ይቻላል፤ የዘመን አቆጣጠር /ዓውደ ዓመትም/ ይኸው ነው፡፡ ዋናው ነገር አንድ ታላቅ ታሪካዊ ድርጊት ፈልጎ እርሱን መነሻ ማድረግ አንድ ታላቅ ታሪካዊ ድርጊት ፈልጎ እርሱን መነሻ ማድረግ ነው፤ የዘመን አቆጣጠሮቹም ልዩነት መንስኤው ይኸው ነው» ይላሉ፡፡ ባሕረ ሐሳብ፣ ጌታቸው ኃይሌ፣ ገጽ.65/ ለምሳሌነትም ሮማውያን የሮም ከተማ የተቆረቆረችበትን ጊዜ መነሻ ማድረጋቸውን/ በኋላም ታላቁ እስክንድር የነገሠበት ዘመን የዘመን ቆጠራ መነሻ ሆነው እንደነበር ይጠቅሳሉ፡፡ መሐመድና ተከታዮች ከመካ ወደ መዲና ያደረጉትን ስደት መነሻ የሚያደርገው ኢስላማዊ  የዘመን አቆጣጠርም ሌላው ተጠቃሽ ነው፡፡
የአይሁድን አቆጣጠር ትተን ከላይ ያየናቸው ሁለቱ የዘመን አቆጣጠሮች /የምዕራባውያኑ የጁልየስ ጎርጎርዮሳዊ አቆጣጠርና የኢትዮጵያና የግብጽ አቆጣጠር/ ሁለቱም ዘመንን የሚቆጥሩት ከክርስቶስ ልደት መነሻ አድርገው ነው፡፡ ይሁን እንጂ እኛ ዛሬ 2008 ዓ.ም ነው ስንል እነርሱ ደግሞ 2015 ዓ.ም ነው ይላሉ፡፡ በመካከሉ የ7  ዓመታት ልዩነት አለ፡፡ እንግዲህ ጥያቄው ትክክለኛው የትኛው ነው? የሚለው ነው፡፡

ጉዳዩ መጻሕፍትን ሊያጽፍ የሚችልና በእርግጥም የተጻፉበት ቢሆንም ለማሳያ ያክል ሁለት ነገሮች እንመልከት፤

1. አሁን ባለው የምዕራባውያን አቆጣጠር ከሄድን ሄሮድስ የሞተው 4 ዓመት ቅ.ል.ክ (ቅድመ ልደተ ክርስቶስ) ነው፡፡ ሄሮድስ የሞተው ጌታ ተወልዶ በስደት ሦስት ዓመት ያህል በግብጽ ከቆየ በኋላ ነው፡፡ ይህ ማለት በእርሱ አቆጣጠር ጌታ የተወለደው በ7 ዓመት ቅ.ል.ክ ነው ማለት ነው፡፡ እንግዲህ ጌታ በትክክል በተወለደበት በአንድ ዓ.ም እነርሱ ጌታ ሰባት ዓመት ሆኖታል ይላሉ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ትክክለኛውን ቁጥር ለማግኘት አሁን ካላቸው ቁጥር ላይ ሰባት ዓመት መቀነስ አለባቸው፡፡

2. ፍላቪየስ ጆሴፈስ የተባለው የአይሁድን ታሪክ የጻፈው ሊቅ እንደመሰከረው ጌታ የተወለደበት ዓመት ነው ተብሎ በወንጌል ላይ የተጻፈው የቆጠራ ዓመት /ሕዝቡ ሁሉ የተቆጠረበትን ዘመን /ሉቃ.2.1/ በጎርጎሪያን ዘመን አቆጣጠር «7 ዓመተ እግዚአ /A.D/ ላይ ነው፡፡» በማለት መረጃ ትቶልናል ይህ ማለት ደግሞ ከምዕራባውያኑ ዘመን አቆጣጠር ላይ 7 ዓመቶች የግድ መቀነስ አለበት ማለት ነው፡፡ ያ ሲደረግ ደግሞ የኛን ዘመን አቆጣጠር ያመጣል፡፡

የዘመን መለወጫ ቀን ልዩነት


ሁለተኛው ጉዳይ የዘመን መለወጫ ወርና ዕለት ልዩነት ነው፡፡ እኛ መስከረም  1 አዲስ ዓመት ስንጀምር እነርሱ በ January 1 / በእኛ ታኅሣሥ 23/ አዲስ ዓመት ይጀምራሉ፡፡ ይህ ከየት የመጣ ልዩነት ነው?
የእኛ እና የግብጻውያን አቆጣጠር እዚህ ጉዳይ ላይ ከአይሁድ አቆጣጠር ጋር ይስማማል፡፡ በአይሁድ አቆጣጠር የመጀመሪያው ወር ኒሳን የሚባለው /በእኛ መጋቢት/ ሚያዝያ/ ነው፡፡
«ይህ ወር የዓመቱ የመጀመሪያ ወር ይሁናችሁ፣ በዚህም ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን የአንድ ዓመት ተባዕት ላይ ወስደው ይረዱ፡፡ . . .»/ዘፀ.12.1-14/ ተብሎ የተሰጣቸውን የፋሲካ በዓል የሚያከብሩት በዚህ ወር ነው፡፡
ይሁን እንጂ አዲስ የዓመት በዓል አድርገው የሚያከብሩት «የሰባተኛው ወር የመጀመሪያ ቀን ዕረፍት ይሁናችሁ፡፡ በዚሁ በመለከት ድምጽ የሚከበር የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ መስዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርቡ እንጂ የተለመደ ተግባራችሁን አታከናውኑበት» /ዘሌ.13.23-25/ ተብሎ የተሰጣቸው የሮሽ ሆሻና፣/የመለከት በዓል ወይም በዓለ መጥቅዕ/ ተብሎ የሚጠራው በዓል ነው፡፡ ይህም ማለት አዲስ ዓመት የሚያከብሩት በሰባተኛው ወር በኢታኒም ወር /በእኛ መስከረም ጥቅምት/ ነው፡፡
በቤተክርስቲያናችንም ትምህርት ዓለም የተፈጠረው መጋቢት 29 ቀን ነው፡፡ መስከረም ደግሞ ከመጋቢት ጀምሮ ሲቆጠር ሰባተኛው ወር ነው፡፡ ይህም ከአይሁድ ዘመን አቆጣጠር ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡
አይሁድስ ቢሆኑ የመጀመሪያው ወር እያለ አዲስ ዓመትን ለምን በሰባተኛው ወር ያከብራሉ ለሚለው ጥያቄ ሁለት ዓይነት ምላሾች /ምክንያቶች/ ይሰጣሉ፡፡ የመጀመሪያው ምክንያት «ሰባተኛው ወር ኖኅ ከመርከብ የወጣበት ወር በመሆኑ ይህ የአዲስ ዓመት መጀመሪያ ተደርጎ መከበር በመጀመሩ ነው» የሚል ነው፡፡ በዘመን መለወጫ ዕለት ልጃገረዶች አበባ እና ለምለም ሣር መያዛቸው ርግቢቱ ለኖኅ ካመጣችው ለምለም ወይራ /ቄጠማ/ ጋር ተያይዞ የተጀመረ መሆኑን ይናገራሉ፡፡
ሁለተኛው ደግሞ መስከረም የቀንና የዕለቱ ርዝመት እኩል የሚሆኑበት ወር በመሆኑ ነው የሚል ነው፡፡ የመስከረም 1 ቀን ስንክሳር «የተባረከ የመስከረም ወር የግብጽና የኢትዮጵያ ዓመታት ወሮች ርእስ ነው፤ የቀኑ ሰዓትም ከሌሊቱ ሰዓት የተስተካከለ ዐሥራ ሁለት ነው» ይላል፡፡
እዚህ ላይ ማስተዋል የሚገባው ሌላው ጉዳይ በቤተክርስቲያናችን ትምህርት እመቤታችን ጌታን የጸነሰችው መጋቢት 29 ቀን ነው፡፡ ይህም ቅዱስ ጳዉሎስ ፣የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት ተወለደ» /ገላ.4.4/ እንዳለው የ5500 ዘመኑ ፍጻሜ /ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ/ ነው፡፡
ጽንሰትን መጋቢት 29 ካልን በኋላ ልደትን ታህሣሥ 29 ቀን እናከብራለን፡፡ ከመጋቢት 29 እስከ ታህሣሥ 29 ድረስ 9 ወር ከ5 ቀን ነው፡፡ /ጳጉሜን ጨምሮ/፡፡ ጳጉሜ 6 በምትሆንበት ጊዜ ደግሞ ታህሣሥ 28 ቀን ልደት ስለሚከበር አሁንም በመሐሉ ያለው ጊዜ 9 ወር ከአምስት ቀን ይሆናል፡፡

ማጠቃለያ  


በመጨረሻም የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ፍፁም መፅሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት ያለው ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የሚቆጥር መሆኑን እንጂ እንደ ዘመኑ ነገስታት ፍላጎት በታሪክ ክስተትን መሰረት ያደረገ አለመሆኑን ከተረዳን ይህንን ሃሳባችንን የሚያጠናክርልን የሳምንታንት እና የወራት ስያሜዎቻችንን እንዲሁም የልሎቹ የቀን አቆጣጠር ምንጭን ከ እዚህ በታች ባሉት ሰንጠረዦች እንመልከት።ለምሳሌ እነኚህ የሳምንታንት ልዩነቶች አውሮፓውያን ከጥንት ከነበረ አምልኮት ጋር የትዛመደ ሲሆን የእኛ ግን እግዚአብሔር አለምን መፍጠር ከጀመረ የመጀመርያ ቀን ስንል እሁድ ማለታችንን ሁለተኛ ቀን ስንል ሰኑይ (ሰኞ) ማለታችንን ወዘተ እንረዳለን።

ማኅበረ ቅዱሳን አውደ-ርዕይ 2000 ዓም
ማኅበረ ቅዱሳን አውደ-ርዕይ 2000 ዓም
ማኅበረ ቅዱሳን አውደ-ርዕይ 2000 ዓም

አሮጌው ዘመን ተጠናቆ አዲሱን ልንቀበል ቀናት ቀርተውናል። የሮማ ካቶሊክ ፓፓ ቤኔዲክት 16ኛ ''የናዝሬቱ እየሱስ'' በተሰኘ መፅሐፋቸው አሁን አውሮፓውያን የሚጠቀሙበት የክርስቶስ የልደት ዘመን ትክክለኛ እንዳልሆነ ሲገልጡ እንዲህ ብለዋል-
“The calculation of the beginning of our calendar—based on the birth of Jesus—was made by Dionysius Exiguus, who made a mistake in his calculations by several years,”  ''ከጅምሩ የቀን አቆጣጠራችን ክርስቶስን ተወለደ ያለበት ዘመን መሰረት (በእክስጉሥ የተቀመረው) የብዙ አመታት የስሌት ስህተት አለው'' ብለዋል። (http://www.charismanews.com/world/34714-pope-says-jesus-birth-date-is-wrongይህ ከአንድሚልዮን ኮፒ በላይ እንደተሸጠ የተነገረው መፅሐፍ ላይ ፓፓው ይህንን ይበሉ እንጂ ስህተቱን
 ለማረም እና ወደ ትክክለኛው ወደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ለመምጣት የደፈረ እስካሁን አልታየም።ወደፊት ግን ይጠበቃል። 


ጉዳያችን 
ይህ ፅሁፍ በእዚሁ ጡመራ በጳጉሜን  2/2006 ዓም፣ ጳጉሜን 5/2007 ዓም በእዚሁ በጉዳያችን ገፅ ላይ ወጥቶ ነበር።ዛሬም አስተማሪ ስለሆነ እንደገና ወጥቷል።
=====================

ፅሁፉ የተጠናቀረባቸው ምንጮች  -

1/ አዲስ ጉዳይ መፅሄት እትም፣መስከረም 2004 

2/ አለቃ አያሌው ታምሩ ትምህርት http://www.aleqayalewtamiru.org/new_year_2003.html


3/ ማኅበረ ቅዱሳን ድህረገፅ http://www.eotc-mkidusan.org/site/-mainmenu-24/--mainmenu-26/30----

4/ደጀ ሰላም መስከረም 11/ 2011 http://www.dejeselam.org/2011/09/blog-post_11.html#more

5/ማኅበረ ቅዱሳን 2000 ዓም አውደ ርዕይ 

6/ ባሕረ ሐሳብ፣ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ






ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።