ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, September 7, 2015

ሰበር ዜና - አርበኞች ግንቦት ሰባትን ጨምሮ አራት በኤርትራ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች የጋራ ንቅናቄ ዛሬ ጳጉሜ 2/2007 ዓም መሰረቱ።የንቅናቄው ስም የኢትዮጵያ ሀገር አድን በዲሞክራሲ የጋራ ንቅናቄ ተብሏል።



ኢሳት ቴሌቭዥን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ሰኞ ለማክሰኞ ከእኩለ ሌሊት በኃላ ከለሊቱ 7 ሰዓት ከ30 ላይ ባሰራጨው የቴሌቭዥን ስርጭት ላይ የሚከተለው ዜና ተነቧል።

በኤርትራ የሚንቀሳቀሱ አራት በትጥቅ ትግል የተሰማሩ ኃይሎች በዛሬው እለት የጋራ ንቅናቄ መሰረቱ እነርሱም

1ኛ/ የአፋር ድርጅቶች የጋራ ንቅናቄ፣

2ኛ/ የትግራይ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣

3ኛ/ የአማራ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ እና

4ኛ/ አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ

ዛሬ በጋራ ለመስራት በመስማማት የኢትዮጵያ ሀገር አድን በዲሞክራሲ የጋራ ንቅናቄን  መመስረታቸውን አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ሀገር አድን በዲሞክራሲ የጋራ ንቅናቄ ዛሬ በይፋ ሲመሰረት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋን ሊቀመንበር፣አቶ ሞላ አስገዶምን ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡን ለማወቅ ተችሏል።በሌላ በኩል ከአራቱ አባል ድርጅቶች የተውጣጣ የጋራ ሰራዊት መመስረቱ ተገልጧል።የኢትዮጵያ ሕዝብ ሳይወድ በግድ የህዝባዊ አመፅ እንዲቀበል ተገዷል ያለው የሀገር አድን ንቅናቄ  መግለጫ የህዝባዊ ሀርነት ትግራይን አገዛዝ ለማስወገድ የጋራ እንቅስቃሴውን በይፋ መጀመሩን አስታውቁአል።በቀጣይ ሌሎች የነፃነት ኃይሎችን ለማካተት ውይይት እየተደረገ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገልፀዋል።አራቱ የሀገር አድን ንቅናቄ አባል ድርጅቶች ከዛሬ ጀምሮ የነፃነት ትግሉን እንዲምያፋፍሙት አስታውቀዋል።

የዜናው ምንጭ ኢሳት ቴሌቭዥን ሰበር ዜና ጳጉሜ 3/2007 ዓም (ኦገስት 8/2015)

ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

No comments: