ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Sunday, April 30, 2017

ግፍ ስንንከባከብ እንኖራለን ወይ? ስደት በዘመን? የተሰኘ አዲስ ዜማ (ቪድዮ)

ዜማው የተለቀቀው  ዛሬ በዘመን ተከታታይ ድራማ ክፍል ሁለት ላይ ነው።
የግጥሙ ደራሲ = አብርሃም ወልዴ
ድምፃዊት = ሜላት መንገሻ (በባላገሩ የድምፃውያን ውድድር 3ኛ የወጣች)



ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Thursday, April 27, 2017

አሜሪካ ወደ ጎንደር የሚደረጉ ጉዞዎች ላይ ጥንቃቄ እንዲደረግ ዛሬ መግለጫ አወጣች። USA warns citizens carefully consider travel to Gondar, Ethiopia በጎንደር የደረሱ የቦንብ ጥቃቶች ለማስጠንቀቂያው ምክንያት መሆናቸው ተጠቅሷል።

ጉዳያችን/Gudayachn
ሚያዝያ 19፣2009 ዓም (አፕሪል 27፣2017)

Source : AFP  Published: 27th April 2017 05:02 PM

ADDIS ABABA: The United States issued a warning Thursday to its citizens about travelling to a popular tourist region in Ethiopia after a string of grenade attacks targeting hotels and homes.

The US embassy in Addis Ababa said there had been four grenade blasts this month in Gondar, a city in the north known for its ancient castles.

A popular stop on Ethiopia's tourist circuit, Gondar was also the scene of anti-government protests last year that led to the declaration of a nationwide state of emergency.

"The embassy recommends US citizens carefully consider whether travel to Gondar is necessary at this time," the embassy said in a statement.

A spokesman for Ethiopia's government had no immediate comment.

While Ethiopia has enjoyed rapid economic growth in recent years and falling poverty rates, protests erupted in 2015 by communities disenchanted with the government of Prime Minister Hailemariam Desalegn.

Human rights groups say hundreds of people were killed and thousands arrested when security forces cracked down on the demonstrations.

The unrest erupted in the central Oromo region near the capital and then spread to Amhara in the north, including Gondar.

State-run Fana Broadcasting Corporate reported th is month that Ethiopia's human rights commission had submitted a report to parliament saying 669 people were killed in last year's protests, along with 63 security officers.

The unrest led parliament to declare a six-month state of emergency in October 2016, which was extended for another four months in March.


ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Monday, April 24, 2017

ሰበር ዜና - ሕወሓት ለሁለተኛ ጊዜ ለሁለት ተከፍሏል።አትሌት ኃይሌ ገብረ ስላሴ፣ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅ እና የኢትዮጵያ ጥንታዊ አርበኞች ሊቀ መንበር ለአስታራቂነት ተጠርተዋል።የክፍፍሉ አሰላለፍ ተለይቷል።

የህዝባዊ ወያኔ አርነት ትግራይ በውስጡ ያለው ቅራኔ ከፍተኛ ደረጃ መድረሱን እና አስታራቂዎችን እስከመማፀን እንደደረሰ አስተማማኝ መረጃ እንደደረሰው የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን ሚያዝያ 16፣2009 ዓም ፣ምሽት ባስተላለፈው የአጭር ሞገድ ራድዮ ፕሮግራሙ ላይ ገልጧል።ክፍፍሉ ኢትዮጵያን በመጠኑ በተሰጠ መብት እንግዛ ወይንስ በአዋጁ መሰረት ማሰርና በመግደል እንቀጥል? በሚል ልዩነት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

በሌላ በኩል የክፍፍሉ መነሻ በአስተዳደር ጉዳይ ላይ ብቻ ሳይሆን ከሀገሪቱ በተዘረፈ ጉዳይ ዙርያ የሁሉም እጅ ከመኖሩ አንፃር አንዱ ከአንዱ የተሻለ መሆኑን ለማሳየት የሚደረግ ጥረት እና በእዚሁም ሳብያ አንድኛው ቡድን ሌላውን ለማሰር ከማሰብ የተነሳ እንደሚሆን ሲነገር ሰንብቷል።

ኢሳት በራድዮ ፕሮግራሙ ላይ እንደገለፀው ክፍፍሉን ተከትሎ በሕወሓት በእራሱ በተመረጡ የገለልተኛ ቡድን ደረግ የነበረው ሽምግልና ፍሬ ባለማስገኘቱ አትሌት ኃይሌ ገብረ ስላሴ፣ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅ፣ የኢትዮጵያ ጥናታዊ አርበኞች ሊቀ መንበር ልጅ ዳንኤል ጁቴ እና ነጋዴዎችን ያካተተ አስታራቂ ቡድን ለማስታረቅ ላይ ታች እያለ መሆኑ ተሰምቷል።

የክፍፍሉ አሰላለፍ

1ኛ/ በጀነራል ሳሞራ የኑስ የሚመራው ስር የሚገኙ : -

  - በወታደራዊ መረጃ ኃላፊ ሜጀር ጀነራል ገብሬ ዲላ ፣

 - የሜቴከ (ብረታብረት ኢንጂነሪንግ) ኃላፊ,

- የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አባይ ወልዱ እና 

- የአቶ መለስ ባለበት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ሲገኙበት 

2ኛ/ በአቦይ ስብሐት የሚመራው ቡድን ስር የሚገኙ : -

 - አቶ አባይ ፀሐዬ እና 

 - የደህንነት ኃላፊው አቶ ጌታቸው አሰፋ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።

3ኛ/ ዶ/ር ደብረ ፅዮን እና ዶ/ር አርከበ እስካሁን ከየትኛው ቡድን እንደተሰለፉ አልታወቅም።

የኢትዮጵያ አምላክ ይፈርዳል ሳይውል ሳያድር
በድምፃዊ ኃይልዬ ታደሰ



ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Thursday, April 20, 2017

ጆሮ ያለው ይስማ! "መታወቂያ" የተሰኘው የኢሳት አዲስ ዘጋቢ ፊልም የሩዋንዳን ተሞክሮ ያሳያል። (ዘጋቢ ፊልሙን ይመልከቱ)

The below Amharic language documentary film called "ID CARD" is made by Ethiopian Satellite Television (ESAT) on April 19, 2017. Rwandan case is still a lesson to the rest part of Africa.Thank you ESAT ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን (ኢሳት) ዩትዩብ ላይ የተወሰደ ሚያዝያ 112009 ዓም

ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Tuesday, April 18, 2017

በዋልድባ ገዳም ላይ ህወሓት ያደረገው ምስጢራዊ ስብሰባ እና ገዳሙን ለማፍረስ ያደረጋቸው እኩይ ተግባራት

አቶ ገብረመድህን አርአያ 

ከአቶ ገብረመድህን አርአያ 
የህወሓት መስራች፣ የፖሊት ቢሮ አባል እና የፋይናንስ ኃላፊ የነበሩ 
አሁን በስደት በአውስትራሊያ ነዋሪ 

የዋልድባ ገዳም በህዋሓት መሪዎች በዓይነ ቁራኛ የወደቀው ገና ትገሉ እንደተጀመረ ነው። የዋልድባ ገዳም የህወሓት መሪዎች እንዲወድም ሃሳብ ያቀረቡት 1973 መጨረሻ አካባቢ ሲሆን፣ አቅማራ ተብሎ በሚጠራ ቦታ በውቅቱ የህወሓት መናኸሪያ ነበር። በተመቤን ውስጥ የሚገኘው ቦታ በፕሮፓጋንዳ /ቤት ተሰብስበው ወሰኑ፤ በስብሰባ የነበሩት አመራር ፖሊት ቢሮው በሙሉ ነበር። እነሱም፣ ስብሃት ነጋ፣ አረጋዊ በርሄ፣ ገደይ ዘርአጽዮን፣ አባይ ፀሃየ፣ ስዩም መስፈን እና መለስ ዜናዊ ነበር። በወቅቱ /ኮሚቴ የነበሩ ናቸው።Ato Gebremedhin Araya former TPLF leadership member
በዚህ ስብሰባቸው የዋልድባን ገዳም እጣ ፈንታ ወሰኑ። ዋልድባ እንዲወደም የወሰኑት በዚህ ስብሰባቸው ነበር። የዋልድባ ገዳም ለብዙ መቶ ዘመናት የቅዱሳን፣ ብፁአን፣ ባህታውያን፣ ቀሳውስት፣ አባቶች፣ ደናግል፣ ዲያቆናት ወዘተ ሰፈር በመሆን በኢትዮጵያ ቅዱስና በታሪክ ትልቅ ምእራፍ የያዘ ገዳም ነው። ይህ ቅዱስ ገዳም የቅዱሳን ማረፊያ በመሆኑ በታላቅነቱ የሚታወቅ ነው። ገዳሙ የታነጸው 12ኛው ክፍለ ዘመን በብፁእ ወቅዱስ አቡነ ዮሴፍ ነው። ቅዱሳን ወደኢትዮጵያ እንደገቡም ያረፉበት፣ የተሰባሰቡበት ቦታ እንደሆነ በርካታ አማንያን ይናገራሉ። ዋልድባ ገዳም ታሪካዊ ቅርሶች፣ የግዕዝ ብራና፣ ታላላቅ መጻሕፍት፣ ጥናታዊና ታሪካዊ መዛግብት የሚገኙበት ስፍራ ነው።

የህዋሓት ሴራ በዋልድባ ገዳም ላይ
ከዚህ ቀጥየ የማቀርበው ፀረ ዋልድባ ገዳም የሆኑትን፣ ከላይ ስማቸው የተዘረዘረውን የህዋሓት ፖሊት ቢሮ መሪዎች 1973 በአቅማራ፣ ተምቤን የወጠኑትን ፀረ ዋልድባ ሴራ ነው። በብዙ ታጋዮች የሚታወቅ፣ በይበልጥም ከፍተኛ የሕዝብ ግንኙነት መሪዎች፣ የስለላ ታጋዮች፣ የክፍል መሪዎች ወዘተ በትክክል የሚያውቁት ሴራ ነው። በስብሃት ነጋ ተነግሮናል፣ ስለዚህ ድብቅ ምስጢር አይደለም። ለሕዝብና ለተራ ታጋይ ግን ድብቅ ምስጢር ነበር።
ከላይ የተጠቀሱት የህወሓት መሪዎች የዋልድባን ገዳም በተመለከተ ብዙ ከተነጋገሩበት በኋላ ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት በሚከተሉትን ምክንያቶች አድርገው ወሰኑ፤

1. በሰሜን ኢትዮጵያ የክርስትና መስፍፋት ዋና መሰረቱ በዋልድባ ገዳም እየተማሩ የሚወጡት ናቸው። በተለይ በትግራይ የሚገኙት አብያተ ክርስትያናት መሪዎች በዚሁ ገዳም የተማሩ ናቸው። ቀሳውስት፣ ዲያቆናት በዚሁ ገዳም የተማሩ ናቸው። ይህ ገዳም እያለ የክርስትና ሃይማኖት ከትግራይ ውስት ለማስወገድ አይቻልም። ለወደፊቱ ከድል በኋል ለምናቋቁመው የትግራይ መንግሥት ትልቅ መሰናክል የሚሆኑት የእስልምና እና የክርስትና ሃይማኖቶች ናቸው። ስለሆነም ዋልድባ ገዳም የክርስትና ሃይማንቶት መፈልፈያ ስለሆነ ከምንጩ ማድረቅ አለብን በማለት የህወሓት ፖሊት ቢሮ አባላት፣ ማለትም፣ ስብሃት ነጋ፣ አረጋዊ በርሄ፣ ግደይ ዘርአጽዮን፥ አባይ ፀሃየ፣ ስዩም መስፍን እና በወቅቱ /ኮሚቴ የነበረው መለስ ዜናዊ በገዳሙ ላይ ውሳኔ አስተለለፉ። ውሳኔውም፤
2. በገዳሙ ተንቀሳቃሽ ንብረትና የማይንቀሳቀስ ንበርት ላይ ጥናት ማካሄድ፤
3. የገዳሙ ሃላፊዎችን ስም ዝርዝር ማጥናትና ማሳወቅ፣
4. የዋልድባ ገዳም ግምጃ ቤት ውስጥ የሚገኙትን ቅርሳ ቅርስ፣ ጥንታዊ መጽሐፍትና መዛግብት በዝርዝር ማጥናት፣
5. የገንዘቡን ክምችትና ቦታውን አጥንቶ ማሳወቅ። ይህንን ሁሉ በረቀቀ ስለላ ማጥናትና መከታተል የፖሊት ቢሮው ሃላፊነት ይሆናል ተብሎ ተወሰነ።
ለዚህ ጥናት ወደ ዋልድባ ገዳም አስርገን የምንልከው ታጋይ ቢያንስ ቢያንስ የድቁና ማእረግ ያለው፣ የቤተክረስቲያን ትምህርት ያለውና ያጠናቀቀ ታጋይ መሆን አለበት በማለት የህወሓት አመራር በአቅማራው ስብሰባ ወሰኑ። በዚህ ስብሰባ ሃላፊነቱ የተሰጠው ለስብሃት ነጋና ለግደይ ዘርአጽዮን ነበር። ሁለቱ የፖሊት ቢሮ አባላት፣ የህወሓት ሊቀመንበር እና /ሊቀመንበር ናቸው። በውሳኔው መሰረት ወደ ሥራቸው ተሰማሩ። ይህን የሥራ ሃላፊነት የተረከቡት የቤተ ክህነት ብቁ እውቀት ያለው ሰው ማግኘት ካባድ ቢሆንባቸውም፣ በየዞኑ የሚገኙትን የሕዝብ ግንኙነት ታጋይ ሃላፊዎችን በማነጋግር በምስጢር ደብዳቤ በመላላክ ብዙ ጊዜ ፈጁ። 

1974 መጨረሻ አካባቢ በተምቤን አውራጃ ጣንቋ አበርገሌ ውስጥ የድቁና ማእረግ ያለው ብቁ ወጣት ዲያቆን ተገኘ። አበርገሌ ተወልዶ ያደገ፣ የቤተ ክህነት ትምህርቱን ያጠናቀቀ ቀዳሽ ነው። ዘመናዊ ትምህርት የለውም። የዞኑ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበረውና አራት ጓዶቹን አሰባስቦ ድርጅታችን ህወሓት እናንተን ለትግል ይፈልጋችኋል ተብለው ተገደው ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ (02) ተላኩ። ይህ የቤተ ክህነት ድቁና ያለው ወጣት ልዩ ዳብዳቤ ለአስገደ ግብረስላሴ ተላከለት። በደብዳቤው የተካተተው ለልዩ ሥራ ስለሚፈለግ ጥሩ እንክብካቤ እንዲደረግለት የሚል ነበር። 02 አስልጣኞችም በተላከው ደብዳቤ መሰረት ተንከባክበው ያዙት። የአንድ ወር ወታደራዊ ትምህርቱን አጠናቀቀ። ይህ ታጋይ በርሄ መብራህቱ ይባላል። 

በርሄ መብራህቱ ከማሰልጠኛው ጣቢያ አስወጥተው ሰው በማያገኘው አንድ ገበሬ ቤት ደበቁት። በዚሁ ድብቅ ቦታ የሚገናኘው ከኪሮስ ሃይለ (ወዲ ሃይለ) ጋር ብቻ ነበር። ኪሮስ ሃይለ የወታደራዊ ማሰልጠኛ አስትዳዳሪ ሃላፊ ነው። አስፈላጊ እንክብካቤም አደረገለት። ከአስር ቀናት በኋላም ካንድ ትልቅ አመራር ጋር እንደሚገናኝ ነገረው። ከማንም ሰው ጋር እንዳይገናኝ አስጠነቀቀው። እንዲሁ እያለ 13 ቀናት በኋላ ስብሃት ነጋ መጥቶ እዛው ድብቅ ቤት ተገናኙ። ስብሃት ነጋና በርሄ መብራህቱ 9 ቀናት አብረውት በመቆየት ስብሃት ታጋይ ዲያቆን በርሄ መብራህቱ ወደ ዋልድባ ገዳም ለስለላ እንደሚላክና እገዳሙ ወስጥ ገብቶ የስለላ ጥናቱን እንደሚያካሂድ፣ ምን ምን መስራት እንዳለበት አሰለጠነው። የሚፈጸሙትን ተግባራትም በዝርዝር አስጠናው። ከሚፈጽማቸው ተግባራት መካከል፣ በዋልድባ ገዳም ያሉትን ጥናታዊ ቅርሶች፣ የብራና መጻህፍት፣ መዛግብት፣ የገዳሙን የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረት፣ ዋና ግምጃ ቤቱ ወስጥ ያለውን ወርቅ ወዘተ የሚቀመጥበትን፣ የዋልድባ ገዳም ሃላፊዎችን ስም ዝርዝር፣ ቀሳውስት፣ ዲያቆናትና ሌሎች አስፈላጊ ናቸው የምትላቸውን ስም ማሳወቅ ወዘተ ተብሎ ተነገረው። ይህንን ጥናት ወደኛ ለማስተላለፍ ጥሞናና ጊዜ የሚጠይቅ ሥራ መሆኑን ማወቅ አለብህ። መኖሪያህ ገዳሙ ውስጥ ነው። ቀናት የፈጀ ገለጻውን ትምህርቱን ሲጨርስ ከሳምንታት በኋላ እንገናኛለን ተባለ። ግደይ ዘርአጽዮን መጥቶ ያነጋግርሃል በማለት ለጊዜው ተሰናበተው። ግደይ ዘርአጽዮን ከሁለት ቀን በኋላ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ በመሄድ ኪሮስ ሃይለን በማግኘት ኪሮስ ሃይለም ታጋይ በርሄ መብራህቱን ወደተደበቀበት ቦት ይዞ በመሄድ አገናኘው። ግደይም ለቀናት ታጋይ በርሄ መብራህቱን ስለ ስለላ ሥራው አሰለጠነው። መገናኛው የምስጢር ቃል ኮድ መሆኑን አስረግጦ አስተማረው። ከማን እንደሚገናኝ፣ የምስጢር ኮዱ ስብሃት ተመልሶ ስለሚገናኝህ ይነግርሃል በማለት ተሰናበተው።

ስብሃት ነጋ ከሳምንት በኋላ ተመልሶ መጣ። ሲመጣም በቀረጢት የተቋጠሩ እቃዎችን ይዞ መጣ። ከረጢቱን ፈትቶ ለታጋይ በርሄ መብራህቱ አሳየው፤ መስቀል፣ የቄስ ጥምጥምና ቆብ፣ የቄስ ዘንግ፣ መቁጠሪያ፣ ጭራ፣ ሙሉ የቄስ ልብስ፣ ጋቢ ወዘተ ለአንድ ቄስ የሚያስፈልገውን ሁሉ በተሟላ ሁኔታ ሰጠው። ታጋይ በርሄ መብራህቱም የመጣለትን ተረከበ። ከአሁን በኋላ ስምህ አባ ገብረሥላሴ ነው። ዋልድባ ገዳም ስትገባ አባ /ሥላሴ መሆንህን አስተዋውቅ። በርሄ መብራህቱን እርሳው ተባለ፣ በጉዳዩም ላይ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው። ከኔም ሆነ ከግደይ ዘርአጽዮን ጋር የምትገናኝበት የምስጢር ኮድ ይህ ነው ብሎ ሰጠው። የሚላኩልህን መልእክቶች ተቀበል፣ የተሳሳተ ኮድ ከሆነ አትቀበል፣ የሚመጣውን ሰው ሁሉ አታነጋግር ተባለ። ከአንተ ጋር የሚገናኘው ብስራት አማር ብቻ ነው። ሲመጣ አስተዋውቅሃለሁ። በዓመት ሁለት ጊዜ ብቻ ትገናኛላችሁ። የተገኘውን ምስጢር ሁሉ ጽፈህና አሽገህ ትልክልናለህ። ከኔም ሆነ ከግደይ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ በምስጢር በአካል በደብቅ ቦታ እንገናኛለን ተብሎ መመሪያ ተሰጠው።

አሁን የለበስከውን ልብስ ለብሰህ እስከ ተከዜ ትሄዳለህ። ተከዜን ከተሻገርክ በኋላ የለበስከውን ልብስ አውልቀህ ሙሉ የቄስ ልብስህን ትለብሳለህ። የዱሮው ልብስህን ተመልሰህ እኛን ለመገናኘት ስትመጣ የቄስ ልብስህን ደብቀህ የዱሮ ልብስህን ለብሰህ እንገናኛለን። ሰው በማያገኘው ጥሩ ቦታ ደብቀው ተባብለው በዚሁ ተለያዩ። አባ /ሥላሴም ዋልድባ ገዳም ገቡ። ታጋይ በርሄ መብራህቱ (አባ /ሥላሴ) ገዳም ገብተው ሰፈሩ። 1975 እስከ ሐምሌ 1983 8 ዓመታት ዋልድባ ገዳም የኖረው ታጋይ በርሄ መብራህቱ ሰላዩ በዋልድባ ገዳም የሚታወቀው አባ /ሥላሴ ሲሆን የተሰጣቸውን የስለላ ተግባር በተሳካ ሁኔታ ቀጠሉበት። በዋልድባ ገዳም አባ /ሥላሴን የሚያውቋቸው የገዳሙ አባላት በርካታ ናቸው። ቢሆንም፣ ገዳሙን ለማጥቃት በህወሓት የተላኩ ሰላይ መሆናቸውን ግን አያውቁም። ስምንት ዓመት በገዳሙ ሲኖር ማንነቱ እንዳይታወቅ በጥንቃቄ የኖረ ሰላይና መልእክተኛ ነው። ታጋይ በርሄ መብራህቱ (አባ /ሥላሴ) በዋልድባ ገዳም ባካሄደው የስለላ ጥናቱ ለስብሃት ነጋና ለግደይ ዘርአጽዮን በማስተላለፍ ዋልድባ ገዳምን ለካባድ ጥፋትና ውድመት የዳረገ ሰው ነው። ከግደይ ዘርአጽዮን በማለሊት ምስረታ ጉባኤ በሃሐምሌ 1977 ቢባረርም፣ ሰላዩን በተገቢው መንገድ አሰጥኖታል። 

አባ /ሥላሴ (ታጋይ በርሄ መብራህቱ) በሚያስተላልፈው የስለላ መልእክቶች በብስራት አማረ እጅ በመላክ ለስብሃት ነጋና ለውውይት ለዘርአጽዮን ይደርሳል። ከዚሁ በመነሳት የሚፈለገውን ጥቃት ሁሉ በስምንት ዓመታት ቆይታው ገዳሙ ከሚጠቀምባቸው የምንጭ ውሃ እስከ እርሻ መሬት፣ በብዛት የጋማ ከብትና ማንኛውንም ሃብት በዝርዝር አሳልፈው የሰጡና ያስተላለፉ ሰላይ ዛሬ ገዳሙ እየደረሰበት ያለው መፍትሄ የሌለው ውድቀትና ችግር የአባ /ሥላሴ (ታጋይ በርሄ መብራህቱ) የስለላ ውጤቶች ናቸው። በወቅቱም ቢሆን በብስራት አማረ የሚመራው አፋኝና ሽብርተኛ ገዳይ ቡድን አድፍጠው በመጠባበቅ ብዙ ብፁአን አባቶችን፣ ቀሳውስቶችን፣ በርካታ ዲያቆናትን ደብዛቸውን አጥፍቷል። ሙታኖችን ገዳሙ ይቁጠራቅቸው። ለዚህ ሁሉ ወንጀል ተጠያዎቹ ስብሃት ነጋና ግደይ ዘርአጽዮን ናቸው።
ዛሬ በዋልድባ ገዳም ላይ እየደረሰ ያለው ጥፋትና ውድመት በስብሃት ነጋና በግደይ ዘርአጽዮን በታቀደ የስለላ መረብ ምክንያት ነው። በጠቅላላ ለጥንታዊውና ባለታሪኩ ገዳም መውደም ተጠያዊዎቹ የህወሓት ከፍተኛ መሪዎች ናቸው። ለጥፋት ውሳኔው ዋናዎቹ ተባባሪዎች፣ አረጋዊ በርሄ፣ አባይ ፀሃየ፣ ስዩም መስፈን እና በወቅቱ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል የነበርው መለስ ዜናዊ ናቸው። በዋልድባ ገዳም ዛሬ እየደረሰ ላለው ውድመት የገዢው ስርዓት ህወሓት ሙሉ ለሙሉ በሃላፊነት ተጠያቂ ናቸው። ወንጄሎቻቸውም፤

1. ታላቅና ባለ ታሪክ የሆነውን የዋልድባን ገዳም አውድመዋል፣
2. ብዙ ብፁአን አባቶችን፣ ባህታዊያንን፣ ቀሳውስትን ገድለዋል፣ አጥፍተዋል፣
3. የዋልድባን ገድም ጠቅላላ ሃብታና ንበረት ዘርፈዋል አስዘርፈዋል፣
4. ጥንትዊ የብራና መጽሐፍት፣ የታሪክ መዛግብትን ወዘተ ዘርፈዋል፣ አስዘርፈዋል፣
5. የገዳሙን ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀስ ሃብትና ንብረት፣ የጋም ከብቶች፣ የእርሻ ቁሳቁሶችን ወዘተ በህወሓት ባለሥልጥናት በጉልበት ወስደዋል።

በሥልጣን ላይ ያለው ፋሽስትና ሽብርተኛ ህወሓት ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛቱ ሰር ከጣላት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በዋልድባ ገዳም እየደረሰ ያለው ፋታ የሌለው ጥቃት ስብሃት ነጋና ግደይ ዘርአጽዮን በሸረቡት ተንኮል የዋልድባ ገድማ ጥፋት እንደቀጠለ ነው። ዛሬ የዋልድባ ገዳም በውድመት አፋፍ ላይ ተንጠልጥሎ ይገኛል። ክብሩና እና ህልውናው ተገፎ የባንዳዎችና የህወሓት አመራር የግል ንብረታቸው አድርገውታል።

የዚህ ቅዱስ ቦታ ጥቃትና ውድመት፣ ሃብታና ንብረት መዘረፍ፣ የብፁአን አባቶች ሕይወት መጥፋት ወዘተ ተጠያቂው ህወሓት ነው። የዚህ ፋሽስትና ዘራፊ መሪዎች ሁሉ ለቅዱስ ገዳሙ መጥፋት በሕግ ተጠያቂዎች ናቸው።

ከአቶ ገብረመድህን አርአያ 
የህወሓት መስራች፣ የፖሊት ቢሮ አባል እና የፋይናንስ ኃላፊ የነበሩ 
አሁን በስደት በአውስትራሊያ ነዋሪ 

ጉዳያችን GUDAYACHN

 www.gudayachn.com

በኢትዮጵያ የእገታ ወንጀል ተሳታፊ አራት አካላት ናቸው። ለችግሩ የመፍትሄ አካላት ሁለት ናቸው።ሁለቱ አካላት ምን ይስሩ?

======= ጉዳያችን ======= በኢትዮጵያ ዜጎችን እያገቱ ገንዘብ የሚቀበሉ ወንጀለኞች ከተራ ወንጀለኝነት አልፎ በታጣቂ ቡድኖች የገንዘብ ማግኛነት መዋል ብቻ ሳይሆን ዜጎችን የማሸበርያ ፋሺሽታዊ ተግባር ሆኗል። እገታ የ...