ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, August 30, 2017

የህወሓት መንግስት ወደ አናርኪስት መንግስት መቀየር እና ከፈረሱ ጋሪው የቀደመው የስርዓቱ የአዲስ ዓመት መርሃ ግብር

ጉዳያችን / Gudayachn
ነሐሴ 25/2009 ዓም (September 1/2017)

ኢትዮጵያ ውስጥ ነገሮች በወራት ሳይሆን በሳምንታት ውስጥ እየተቀየሩ ነው።በአገዛዙ ላይ የተነሳው ተቃውሞ ምኑንም ያህል ግድያ እና እስር ቢከተለውም ሕዝብ በበለጠ የተቃውሞ መንፈስ በገዢው ስርዓት ላይ ያለው ጥላቻ እየባሰ ብቻ ሳይሆን እንደ እሬት እየመረረ መጥቷል።በአንፃሩ ስርዓቱ የግፍ ጡጫ በማብዛት የአገዛዝ ዘመኑን የሚረዝም መስሎት እየታተረ ይገኛል።ከእዚህ ሁሉ ጋር ደግሞ በገዢው ስርዓት ወገን ያሉትም በእራሳቸው የመደናገር፣የመዋለል እና የመባዘን ስሜት ተደባልቆባቸው ምንም እንዳልሆኑ ሁሉ በአሸንዳ ዳንኪራ እራስን ለመደለል ሲሞከር ይስተዋላል። በተቃዋሚው ጎራ በኩል አድፍጦ ከሚሰራው እስከ በአደባባይ የሚፎክረው እያንዳንዱን የሀገር ቤት እንቅስቃሴ በእርሱ እንደተመራ ለመግለፅ መፎካከር ድረስ የሚታዩ ገፅታዎች አሉ።በኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ ከጎንደር እና ጎጃም በረሃዎች ያለው የታጣቂ እንቅስቃሴ እስከ ሱማሌ እና ኦሮሞ ድንበር የሚል ስም በተሰጠው ግጭት ገዢው ስርዓት እያፋፋመው እንደሆነ እየተሰማ ነው። የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት ከሚታሰበው በላይ እየደከመ ብቻ ሳይሆን እየደቀቀ ነው ለማለት ያስደፍራል።ይህ ደግሞ በመጪው አዲስ ዓመት በባሰ መልኩ እንደሚቀጥል ከግምት በላይ ማስቀመጥ ይቻላል።በቅርቡ በኦሮምያ በተደረገው አድማ ብቻ ብዙ ሺህ ኩንታል ቡና ለውጭ ሀገር ገበያ በወቅቱ መቅረብ አልቻለም።በዐማራ ክልል ከተሞች ለተከታታይ  ቀናት የተደረገው የቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ እና አድማውን ተከትሎ የተከሰተው የገበያ መቀዛቀዝ የሕዝቡን እና የመንግስትን የእየዕለቱ እንቅስቃሴ አውኮታል። 

ከላይ ከተጠቀሱት ክስተቶች በተጨማሪ የስራ ማቆም አድማዎቹን ተከትሎ ሕዝብ ለመንግስት ግብር እንደማይከፍል በግልፅ መናገር ጀምሯል።ሱቃቸውን ዘግተው የተቀመጡ እና በአድማው ተሳተፋችሁ ተብለው ሱቃቸው የታሸገባቸው የትራንስፖርት መኪናቸው ታርጋ ገንዘብ ሳይከፍሉ መውሰድ እንደማይችሉ የተነገራቸው እና ሌላም ተደማምሮ የምጣኔ ሃብቱ በሁሉም መልክ ተቃውሷል።የገበያ ስርዓቱ መቃወስ የምጣኔ ሃብቱን እንዳቃወሰው ሁሉ ሕዝብ ከነበረበት የኑሮ ደረጃ የበለጠ ወደ ታች እንዲወርድ፣ መንግስትም ያለው ገቢ እንዲያሽቆለቁል ምክንያት ሆኗል። ይህ ሁኔታ ከንበረው የፖለቲካ ውጥረት ጋር ተዳምሮ የህዝቡን ማኅበራዊ እንቅስቃሴ አውኮታል። እነኝህ የፖለቲካው ውጥረት፣የምጣኔ ሃብቱ መቃወስ እና የማኅበራዊ ኑሮ መናጋት የህወሓት መንግስትን ወደ አናርኪስት መንግስት ይቀይረዋል።መንግስቱን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያንም ወደ እዚሁ አደገኛ ደረጃ እንዳያደርሳት ያሰጋል።

አናርኪዝም ህገ ወጥነት የሰፈነበት፣ ህገ ወጥነቱ ለመሰረታዊ የሞራል ህጎችም የማይታዘዝ፣ማንም ጉልበተኛ በዕለቱ ባወጣው መመርያ የሚመራው ስርዓት መገለጫ ነው። በእርግጥ የህወሓት መንግስት ላለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት እነኝህ ጠባዮች አልታዩበትም ማለት አይቻልም። ሆኖም ግን ላለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት የታዩት ህገ ወጥ ፀባዮች በሕዝቡ ሕግ አክባሪነት እና አንገት ደፍቶ የመመታት ፀባይ ተሸፍኖ ቆይቷል። ከእንግዲህ ወዲህ ግን ስርዓቱ የበለጠ ሕግ አክባሪ ለመምሰል ቢሞክርም የሚያመጣው ለውጥ ስለማይኖር የአናርክዝም ፀባዩን ሕዝብ በገሃድ በመንግስት ላይ በመግለፅ ተቃውሞውን ይቀጥላል።ይህ ሁኔታ ደግሞ ወደ አደገኛ መልክ ከመቀየሩ በፊት በሁሉም መንገዶች ተፈትኖ ኢትዮጵያን አሁን ላለችበት አደገኛ ደረጃ ያደረሳትን የህወሓት መራሹን መንግስት በባለአደራ መንግስት መቀየር እና የኢትዮያን ህልውና ማስከበር ቀዳሚ አጀንዳ ሊሆን ይገባል።ይህንን ለማድረግ ደግሞ ከጦር ሰራዊቱ ጀምሮ የከበደ ኃላፊነት ያለባቸው አካላት የቤት ስራቸውን በሚገባ መወጣት ይኖርባቸዋል።

ከፈረሱ ጋሪው የቀደመው የአዲስ ዓመቱ መርሃ ግብር 

የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ አሁን ያለበት ደረጃ እንዲደርስ የህወሓት መንደርተኘንት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ ውጤት መሆኑ እየታወቀ እና የአድልዎ የጭቆና ደረጃው ቅጥ ባጣበት በእዚህ ወቅት ህወሓት የአዲስ ዓመትን ተሻግሮ የሚነሳው የህዝብ ቁጣ ስላስፈራው ብቻ የአዲስ ዓመት መደለያ መርሃ ግብር ''የከፍታ ዘመን'' በሚል አዲስ ዘመቻ ጀምሯል።ነገሩ '' የቸገረው ምንትስ ይአጌባል አይነት ካልሆነ በቀር በእዚህ አይነት መልክ በዓል ከማክበር በፊት ከህዝብ ጋር መታረቅ በሚገቡ መሰረታዊ ነጥቦች ተስማምቶ መታረቅ ቢቀድም ነገሩ ባማረ ነበር።የመንግስት ቃል አቀባይ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ከትናንት በስቲያ በኢትዮጵያ ለቀጣይ ቀናት እያንዳንዱን ቀን የሕፃናት፣የአረጋውያን፣የንባብ፣የአረንጉአዴ ልማት፣የመከባበር ቀን፣ ወዘተ ተብሎ መሰየሙን እና በልዩ ሁኔታ እንደሚከበሩ አስታውቀዋል።የቀናቱ ስያሜ በራሳቸው የሚስቡ ስሞች ይዘዋል።እነኝህ ቀኖች ላለፉት 26 ዓመታት ሥራ ላይ እንዲውሉ የጠየቁ ወደ እስር ቤት ሲወረወሩ መክረማቸው የታወቀ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የአዲስ ዓመት አከባበሩ መንገድ በእራሱ ''ከፈረሱ ጋሪው ያስቀደመ'' መርሃ ግብር ነው። የእዚህ አይነቱ መርሃ ግብር ልጆቹ እስር ቤት ለሚማቅቁበት ሕዝብ፣ የችርቻሮ ሱቁ ለታሸገባት እናት፣ በስደት ልጆቹ ድንበር አልፈው በረሃ የሚንከራተቱ እና  ለናፈቁት አረጋዊ የሚሰጠው ስሜት የለም።

ከአዲስ ዓመቱ መርሃ ግብር በፊት የፖለቲካ መድረኩ ቢፀዳ፣ ሕዝብ የመናገር እና የመፃፍ በመንግስት የሚወከልበት የውክልና ደረጃው በእውነተኛ የዲሞክራሲ መንገድ እንዲሆን የመተማመኛ ሥራ ቢሰራ እና የከሸፈው ደም አፋሳሹ እና ከፋፋዩ የህወሓት ፈድራሊዝም ፖሊሲ በእውነተኛ እና አድሏዊ ባልሆነ የፈድራል ስርዓት መተካቱ ቢቀድም ከህዝብ መተማመኛ በተገኘ ነበር። አሁን ግን '' ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት'' አይነት ሥራ እየተሰራ ነው።

ባጠቃላይ ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት ደረጃም ከሁሉም አቅጣጫዎች ነገሮችን ለመመዘን ብንሞክር በህወሓት ውስጥ ያለች ኢትዮጵያ ከባለፈው አሳዛኝ የውርደት ዘመኖቻችን በባሰ መንገድ እራሱ ህወሓትም ሆነ ሃገሩ ወደ አናርኪዝም ወይንም የባሰ ስርዓተ አልበኝነት የማምራቱ ሂደት በጣም ሰፊ ነው።አንዳንዶች ህወሓት አንዳንድ ጥገናዊ ለውጥ ካደረገ ነገሮች ሊስተካከሉ ይችልሉ የሚል የፖለቲካ ቂላቂልነት የሚያጠቃቸው ይኖራሉ።ጥገናዊ ለውጥም ሆነ ''የከፍታ ዘመን'' እየተባለ ድግስ ቢዘጋጅ መሰረታዊ የፈድራሊዝም ፅንሰ ሃሳብም ሆነ የፖለቲካ፣ወታደራዊ፣ምጣኔ ሃብታዊ እና የደህንነት ክፍሉ ሁሉንም ኢትዮጵያ በሚወክሉ የፖለቲካ ኃይሎችም ሆነ ሕዝብ ካልተደለደለ እና የመገናኛ ብዙሃኑ ፍፁም ነፃነት ካልተጎናፀፉ የኢትዮጵያ እድገት የሚያመጣ ለውጥ ይገኛል ብሎ መጠበቅ እራስን መደለል ብቻ  ነው። ህወሓት የእራሱም ሆነ የውጭ አማካሪዎች እየቀጠረ የፖለቲካ ትኩሳት የማብረድ የተለያዩ ስልቶችን ሲቀይስ የኖረ ነው።ሕዝብ ግን አሁን ባለበት ደረጃ መልሶ የመታለል አቅም ይኖረዋል ተብሎ አይገመትም።ባጭሩ ሌሎችን መፍትሄዎች ወደጎን ብሎ የእዚህ አይነቱ ድብብቆሽ ጫወታ ላይ ብቻ ህወሓት በማትኮር እጁን ለማፍታታት ከሞከረ ወደ ለየለት የአናርኪዝም ስርዓት መቀየሩ እና የእራሱንም ባለስልጣናት ማዘዝ ወደማይችልበት ከመድረሱም በላይ ሕዝብ በእራሱ መንገድ በሚሄድባቸው እራሱን ከአናርኪስት መንግስት ለመጠበቅ በሚያደርገው እራስን የመከላከል ትንቅንቅ ሃገሩ ባጠቃላይ ወደ አናርኪዝም ደረጃ የመገፋቱ አደጋ ቅርብ ነው።ለእዚህ ነው አሁን ላለው ምስቅልቅል ሁኔታ የጦር ኃይሉ እራሱን አደራጅቶ ሙሰኞች እና ኢትዮጵያን የከዱ ባለስልጣናት ለፍትህ የማቅረብ ግዴታ ከሕዝብ እና የፖለቲካ ኃይሎች ጋር  ተባብሮ የባለ አደራ መንግስት የመመስረት ግዴታ እንደሚኖርበት ተደጋግሞ ለመናገር የሚሞከረው።አናርኪዝምን ለመቅደም ኢትዮጵያን ከህወሓት ማላቀቅ ቸል የሚባል ተግባር አይደለም።  


''አሳልፈናል ክፉ ደጉን፣
ቃል ኪዳን አለው (እኛ ኢትዮጵያውያንን ለማለት ነው) እንዳይለየን'' ቴዎድሮስ ካሳሁን 

ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Monday, August 21, 2017

ማኅበረ ቅዱሳን በሚቀጥለው ሳምንት መጨረሻ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያተኮረ በዓይነቱ ልዩ እና የመጀመርያ ዓለም አቀፍ የጥናት ጉባኤ ስዊድን ውስጥ ያካሂዳል።ጉዳያችን / Gudayachn ዜና 

በጉባኤው ላይ የሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን እና የውጭ ሀገር ተወላጅ ምሁራን ከአዲስ አበባ ዩንቨሲቲ ፣ ካምብሪጅ ዩንቨርሲቲ እንግዝ፣ሉንድ ዩንቨርሲቲ ስዊድን፣ስታቫንገር ዩንቨርሲቲ ኖርዌይ፣ሴንት ፒተርስበርግ ዩንቨርሲቲ ሩስያን ጨምሮ የሚመጡ ሲሆን በተለያዩ ርዕሶች የሚያቀርቡት የጥናት ወረቀቶች ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጣቸው መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ስር የበጎ ፍቃድ አገልጋይ ምዕመናን የተመሰረተው እና ከሁለት አስር አመታት በላይ ለቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ እድገት እየተጋ የሚገኘው ማኅበረ  ቅዱሳን ነሐሴ 27 እና 28/2009 ዓም (ሴፕቴምበር 2 እና 3/2017 ዓም ከሉንድ ዩንቨርሲቲ ጋር በተባበር በስዊድን፣ሉንድ ከተማ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አስተዋፅኦ ለዓለም ላይ ያተኮረ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ያካሂዳል።ማኅበረ ቅዱሳን  በዋናው ማዕከሉ ስር የጥናት እና ምርምር ማዕከል የተሰኘ ክፍል ያለው ሲሆን ይህ ክፍል በእየጊዜው ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጋር ተያያዥነት ያላቸው በርካታ የጥናት እና ምርምር ስራዎች የተሰሩበት ሲሆን የምርምር ውጤቶቹ በማዕከሉ አዳራሽ በሚዘጋጁ ጉባኤዎች እያቀረበ በምሁራን ሃሳብ እንዲዳብሩ ማድረጉ ይታወቃል።የማኅበረ ቅዱሳን ጥናት እና ርምር  ማዕከል በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ እና በተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ በምርምር ሥራ የሚያገለግሉ ምሁራንን ያካተተ የእራሱ የሆነ የአማካሪ ቦርድ እና  ኢድቶርያል ቦርድ ኮሚቴ ያለው ሲሆን ክፍሉ በእየወሩ የተለያዩ የምርምር ውጤቶች የሚቀርቡበት የህዝብ ጉባኤ አለው።

በዋናው ማዕከል ስር የሚገኘው የማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማዕከል የጥናት እና ምርምር ክፍል የተዘጋጀው በመጪው ሳምንት መጨረሻ በአማርኛ እና እንግሊዝኛ ቋንቋዎች የሚደረገው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለዓለም ያበረከተቻቸው ቅርሶች ላይ የሚያተኩረው ጉባኤ  የሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን እና የውጭ ሀገር ተወላጅ  ምሁራን ከአዲስ አበባ ዩንቨሲቲ ፣ ካምብሪጅ ዩንቨርሲቲ እንግዝ፣ሉንድ ዩንቨርሲቲ ስዊድን፣ስታቫንገር ዩንቨርሲቲ ኖርዌይ፣ሴንት  ፒተርስበርግ ዩንቨርሲቲ ሩስያን ጨምሮ የሚመጡ ሲሆን በተለያዩ ርዕሶች የሚያቀርቡት የጥናት ወረቀቶች ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጣቸው መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ፕሮፌሰር ሳሙኤልሮቢንሰን "የኢትዮጵያ ሃይማኖታዊ ቅርሶች ለዓለም ክርስትና ያደረጉት አስተዋፅኦ" በሚል ስር የጥናት ወረቀታቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን ፣ፕሮፌሰር ደቪድ ፊልፕሰን በበኩላቸው " የኢትዮጵያ ቤተ ክህነታዊ ቅርሶች ታሪክ" በሚል ርእስ ስራቸውን ለጉባኤተኛው ያካፍላሉ።ከእዚህ በተጨማሪ እውቁ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የማኅበራዊ ሳይንስ ተመራማሪው ዶ/ር የራስ ወርቅ አድማሴ ስራዎች የጉባኤው ሌሎቹ ድምቀት የሚሰጡት እንደሚሆኑ ከወድ\ዲሁ ለመረዳት ተችሏል።ጉባኤው የእራሱ ድረ ገፅ የከፈተ ሲሆን ገፁን ለመጎብኘት ይህንን  ይጫኑ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ዘመናት ከመሻገሯ እና ለኢትዮጵያም ሆነ ለአፍሪካ እድገት ያላት ሚና ከፍተኛ ቢሆንም እስካሁን በእንደዚህ አይነት ደረጃ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ስታዘጋጅ ይህ የመጀመርያ ነው።ከማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማዕከል የጥናት እና ምርምር ክፍል  የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ይህ ጉባኤ በሚቀጥለው ዓመት ሁለተኛ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ተብሎ በሌላ ሀገር እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል። ጉባኤው ኢትዮጵያን እና ቤተ ክርስቲያንን በዓለም አቀፍ መድረክ የሚያስተዋውቅ ሲሆን ከምርምር ውጤቶቹ የሚገኙት ግብአቶች ለቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ እድገት የራሳቸውን ጉልህ ድርሻ እንደሚኖራቸው ይታመናል።


በሌላ ቤተ ክርስቲያንን የተመለከተ ዜና ደግሞ ማህበረ ቅዱሳን ከመጪው መስከረም 1 ቀን ጀምሮ የቴሌቭዥን ስርጭቱን እንደሚጀምር ለማወቅ ተችሏል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከ40 ሚልዮን ምእመናንን ይዛ የእራሷን ተከታዮች የምትደርስበት የራድዮም ሆነ ቴሌቭዥን ጣቢያዎች የሏትም።በመሆኑም የማኅበረ ቅዱሳን  የቴሌቭዥን ስርጭት የእራሱ በጎ ሚና እንደሚኖረው ይገመታል። በማኅበሩ ድረ ገፅ ላይ አዲሱን የቴሌቭዥን ስርጭት አስመክቶ የወጣው ዘገባ እንደሚያመለክተው ስርጭቱ በአማርኛ፣ኦሮምኛ እና ትግርኛ የሚቀርብ ሲሆን በቀን ለሁለት ሰዓታት ያህል የአየር ሰዓት ይኖረዋል።ማኅበሩ ካሁን በፊት በኢቢኤስ የቴሌቭዥን ጣቢያ በሳምንት ለአንድ ሰዓት በአማርኛ ቋንቋ ሲያስተላልፍ የነበረው መንፈሳዊ መርሐ ግብር በልዩ ልዩ ምክንያት ከተቋረጠ በኋላ በየሳምንቱ ለሁለት ሰዓታት በኢንተርኔት ቴሌቭዥን በሚያሠራጫቸው መንፈሳዊ ዝግጅቶቹ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ትምህርተ ወንጌል ሲያቀርብ ቆይቷል።በአሌፍ የቴሌቭዥን ጣቢያ የሚሰራጨው ስርጭት በሚከተሉት የሳተላይት መስመር በኩል እንደሚገኝ ዜናው አክሎ ያብራራል።የሳተላይት መስመሩም 
Aleph Television Nilesat (E8WB)
Frequency: 11595
Polarization: Vertical
Symbol Rate: 27500
FEC: 3/4
መሆኑን ከማኅበሩ ድረ ገፅ ላይ ለመረዳት ተችሏል።

ከስር የሚገኘው የቪድዮ መዝሙር ርዕስ - ቤተ ክርስቲያንን አንተውም ከቶ 
በማኅበረ ቅዱሳን የመዝሙር ልዑክ Wednesday, August 9, 2017

የኢትዮጵያ አምላክ እንዲነሳ እንባ አዋጡ! (የጉዳያችን መልዕክት)

ኢትዮጵያ አምላክ አላት።የሁሉም አምላክ እንደሆነ ሁሉ በተለይ የኢትዮጵያ አምላክም መሆኑን የነገረን ደግሞ ከ40 ጊዜ በላይ በቅዱስ መፅሐፍ ስሟ እንዲጠራ ያደረጋት ሀገር ኢትዮያ ነች።ይህ ያለንበት ወቅት (ከነሐሴ 1 እስከ 16፣2009 ዓም) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ስርዓት መሰረት ከሰባቱ ዋና የፆም ወቅቶች ውስጥ አንዱ ነው።ፆሙ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የትንሣኤ እና የእርገት ምስጢርን ለሐዋርያት በሁለት ዙር ሱባኤ  ከእግዚአብሔር ምስጢሩን የተገለጠላቸው ወቅት ነው።ኢትዮጵያ እና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፊት ለፊት የሚነጋገሩ ምስጢረኞች ናቸው።ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ስላሴን ጨምሮ ከእሳቸው በፊት የነበሩ የኢትዮጵያ  መሪዎች በእግዚአብሔር የሚያምኑ በድንግል ማርያም አማላጅነት የተጠቀሙ ነበሩ።አንዳንዶች እግዚአብሔርን በሚገባ ስለማያውቁት ወይንም ከስንፍና የተነሳ ስለድካማቸው መሸፈኛ እግዚአብሔርን ማመን የመሸነፍ እና የተስፋ መቁረጥ ምልክት ይመስላቸዋል።ጉዳዩ ግን በተቃራኒው ነው።አባቶቻችን እና እናቶቻችን ኢትዮጵያን ለትውልድ ሲያስተላልፉ መንገዳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር አድርገው እንጂ በትዕቢት መንገድ ተጉዘው አልነበረም።

ቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ይህ የፍልሰታ ፆምን የዓመት እረፍት ወስደው  ድሬዳዋ ኪዳነ ምሕረት አልያም መስቀል አደባባይ የሚገኘው ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን 15ቱንም ቀኖች እያስቀደሱ ያሳልፉ ነበር።በተለይ ድሬዳዋ በወረዱበት የፍልሰታ ፆም ወቅት እርሳቸውን በፍጥነት ለማግኘት የመጣ የውጭ ሀገር ልዑክ ድሬዳዋ መውረድ ነበረበት።ኢትዮጵያ የተሰጣት ፀጋ ይህ ነው።ከእግዚአብሔር ጋር መንገዱን ያላስተካከለ ቤተ መንግስቷ ውስጥ ቢገባ እንደታወከ ይኖራል።በደርግ ዘመንም ሆነ አሁን አራት ኪሎ የሆነውን እያየን ነው።

ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ጊዜ አንድ ሱባኤ አይደለም በርካታ ሱባኤዎች ይፈልጋል።ሕዝብ በጎሳ በተከፋፈለ ችግር ነው።ከወዲህ በጎሳ የሚከፋፍል በመንግሥትነት ተሰይሞበት ያሰቃየዋል፣ ከማዶ በእየጎሳው የተደራጁ ድርጅቶች የነገ አንደነቱን ሊያጨልሙበት ሲሯሯጡ ይታያሉ።በእግዚአብሔር ዕርዳታ ሰው በጥረቱ የሚፈታው ጉዳይ አለ። ሰው ምንም ያህል ቢሮጥ በእግዚአብሔር ብቻ እና ብቻ የሚሰራ ሥራ አለ።ስለ ኢትዮጵያ ማንባት ጥቂት እንባ ማዋጣት ከእግዚአብሔር ጋር መንገዷን ያስተካክላል።ለዘመናት መላ ያጣችበትን የቤተ መንግስቷን ጉዳይ መልክ ያስይዘዋል።መልክ የምያስይስዘው ከሰማይ ወርዶ አይደለም።የሕዝብን ልብ ያፀናል፣ፍቅር ይሰጣል፣አሸናፊ ያደርገዋል።ይህ ብቻ አይደለም። የኢትዮጵያን ሕዝብ ልብ አፅንቶ፣በአንድ አቁሞ፣የሚወደው መሪ አውጥቶ ኢትዮጵያን ለመጪው ክፍለ ዘመን ነፃነቷን፣አንድነቷን፣እምነቷን እና ብልፅግናዋን አምጥቶ ያሻግራታል።እግዚአብሔር በቸርነቱ፣ ድንግል ማርያም በአማላጅነቷ የኢትዮጵያን ምስጢር እንድትፈታ ትንሽ ትንሽ እንባ እናዋጣ። እንደ እውነቱ ለመናገር ማናችንም ስለ እራሳችን እና ቤተሰባችን እንፀልይ ይሆናል።ጥያቄው  ከልብ ጊዜ ሰጥተን የኢትዮጵያ ጉዳይ ብለን እየፀለይን ነው ወይ? የሚለው ነው።ከሆነ መልካም።እርግጥ ነው ቀን ከሌሊት የሚፀልዩ በግልጥም በስውርም የሚኖሩ የእግዚአብሔር ወዳጅ ቅዱሳን የሚኖሩባት ነች ኢትዮጵያ። የእዚህ ማስታወሻ ዋና አላማ ግን ስለ ካህናቱ፣መነኮሳቱ ለማውራት አይደለም።ከእዛ በታች ስላለነው ምእመናን ሁሉ ነው።እስኪ የኢትዮያን ጉዳይ ፍታው ብለን ትንሽ ትንሽ እንባ እናውጣ። እግዚአብሔር በኢትዮጵያ እና በሕዝቧ ላይ የተነሱባትን ባያንበረክክ በእዚህ እንፈትነው።

ከስር ቪድዮ "ቅያሜው ይቅርና አምላክ ሆይ ታረቀን" በዘማሪ ይልማ ኃይሉ (ያድምጡት)ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Monday, August 7, 2017

መንግስት በእራሱ ለውጥ ማምጣት ካልቻለ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደገና አጠቃላይ ተቃውሞ ሊነሳ ይችላል ሲል የሰብዓዊ መብት ተመልካች ድርጅት (ሁማን ራይትስ ዋች) አስታወቀ።

የዓለም ሰብአዊ መብት ተመልካች ድርጅት ኢትዮጵያን አስመልክቶ ዛሬ በድረ-ገፁ ላይ የፃፈውን ከእዚህ በታች ይመልከቱ።
  • Government Should Use Reform, Not Force, to Avoid More Protests
  • ...Without  efforts and meaningful reform, it is just a matter of time before they start protesting again. 

August 7, 2017 4:10PM EDT
Ethiopia’s parliament has just lifted the country’s 10-month-long state of emergency. The government’s emergency powers brought mass detentions, politically motivated criminal charges, and numerous restrictions on people’s movement and communication. While the end is welcome news, thousands remain in detention without charge, none of the protesters’ underlying grievances have been addressed, and politically motivated trials of key opposition leaders, artists, journalists, and others continue.
In October 2016, at the beginning of the state of emergency, the government promised “deep reform” in response to the year-long protests that left over 1000 people dead. The reforms included tackling corruption, cabinet reshuffles, and a dialogue with what was left of opposition political parties. The government also pledged youth job creation and good governance. But these are not the fundamental issues that protesters raised during the hundreds of rallies between November 2015 and October 2016. The government has largely redefined protester grievances in its own terms, ignoring more fundamental demands to open up political space, allow dissent, and tolerate different perspectives that are critical in such a large and ethnically diverse country. It has also failed to conduct even a remotely credible investigation into security force abuses since the protests began.
Impunity for security forces remains a major concern. The Ethiopian Human Rights Commission’s two investigations into the protests and a recent speech by their chair – which both echoed the government’s misleading allegations of the extent of violence by protesters and its inaccurate portrayal of protester grievances – underscore longstanding concerns over the commission’s independence. Accountability matters – not only for corruption, but for security force abuses. Ethiopia’s repeated unwillingness to meaningfully investigate and hold its security forces to account is why Human Rights Watch and others have long argued that an international investigation is crucial.
Even though it was abusive and overly broad, Ethiopia’s state of emergency gave the government a window to address citizens’ grievances without the shadow of imminent protests. But the government missed that opportunity. Suppressing grievances through brutal force is more likely to provoke instability than to ensure Ethiopia’s long-term stability.
The government should release those arbitrarily detained or subject to politically motivated charges, including opposition politicians like Dr. Merera Gudina, Oromo Federalist Congress chairman. Many protesters, including those who were held in Ethiopia’s “rehabilitation camps” during the state of emergency, have told me that without such efforts and meaningful reform, it is just a matter of time before they start protesting again. 

ጉዳያችን GUDAYACHN

 www.gudayachn.com

Sunday, August 6, 2017

ሃዘን ጎሳ የለውም።ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው።አባታቸውን፣እናታቸውን ወይንም ልጆቻቸው ከተገደሉባቸው ጋር አብረን እንዘን።

ጉዳያችን/Gudayachn 

ኢትዮጵያ ላለፉት አርባ ዓመታት የፖለቲካ ስልጣን  ለማስጠበቅ ሲባል ብቻ የመብት ጥያቄ ያነሱ ሁሉ በአደባባይ ሲገደሉ ኖረዋል።በህወሓት የሚመራው መንግስት ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ የኢትዮጵያውያን እንባ አልቆመም።በተለይ ባለፉት 10 ወሮች ውስጥ በአስር ሺዎች ወደ እስር ቤት ሲጋዙ ብዙ መቶዎች (ቁጥሩ ከእዚህም እንደሚልቅ ይታመትናል) በአደባባይ በስርዓቱ ወታደሮች ተገድለዋል።በጎንደር፣ነቀምት፣አምቦ፣ባህርዳር፣አዲስ አበባ፣ኮንሶ፣ቴፒ እና ሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ቤተሰብ ሃዘን ላይ ነው።

ነገ ነሐሴ 1፣2009 ዓም በባህርዳር ከተማ ልክ የዛሬ ዓመት ባዶ እጃቸውን የመብት ጥያቄ ባነሱ ነዋሪዎች ላይ ጨካኞቹ የስርዓቱ ወታደሮች እና በጎሳ ስሜት እራሳቸውን  የተበተቡ ታጣቂዎች ከኮንደምንየም ቤቶች መስኮቶች ላይ ሁሉ በማድፈጥ በ60 ደቂቃዎች ውስጥ ከ50 ያላነሱ የከተማው ነዋሪዎች እንደቅጠል የረገፉበት ቀን ይታሰባል።በባህር ዳር ከተማ ሥራ የማቆም ጥሪ የተጠራ ሲሆን ጉዳዩ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊንም የሚመለከት ጉዳይ መሆኑ እሙን ነው።
ሃዘን ጎሳ የለውም።ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው።አባታቸውን፣እናታቸውን ወይንም ልጆቻቸው ከተገደሉባቸው ጋር አብረን እንዘን።በኢትዮጵያ የትኛውም ክፍል በግፍ በአገዛዙ ሕይወታቸው የተቀጠፈውን ሰማዕታት እንዘክራቸው።

ቪድዮ:  በፕሮፌሰር አሽናፊ ከበደ “እረኛው” የተሰኘው በመሳርያ ብቻ የተቀናበረ ሙዚቃ። 
                

ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

ኢትዮጵያ በዘመናዊ ታሪኳ ታላቅ ተልዕኮ የሚኖረው ሀገራዊ የምምክር ኮሚሽን በተመለከተ ምን ያህል እናውቃለን?

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ኮሚሽን አማካሪ ኮሚቴ አባላትን ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል ባካተተ መልኩ አዋቅሯል። በእዚህ ጽሑፍ ስር የሚከተሉት ነጥቦች ምላሽ ያገኛሉ፡  ኮሚሽኑ እንዴት ተመሰረተ?  የኮሚሽኑ 11 ኮሚሽነሮች እንዴት ተመ...