ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, June 30, 2020

ሰበር ዜና -የሎሬንት ፀጋዬ ገብረመድህን ቤተሰብ ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴን አስከሬን ከቤተሰቦቻቸው ለመንጠቅ የሞከረው ጀዋር እና የድርጊቱ ፈፃሚዎች 35 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።


ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ 

(ጉዳያችን ዜና)

በጀዋር እና ግብረአበሮቹ ተግባር በርካታ የአምቦ፣የኦሮምያ እና ሌላውን ኢትዮጵያዊ አበሳጭቷል። 

ከእናቱ ወ/ሮ ጉደቱ ሆራ እና ከአባቱ አቶ ሁንዴሳ ቦንሳ ከአዲስ አበባ በስተ ምዕራብ 135 ኪሎሜትር ርቀት በምትገኘው በአምቦ ከተማ የተወለደው ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴ ትናንት ሰኔ 23/2012 ዓም በአዲስ አበባ ገላን ኮንደሚንየም አካባቢ ባልታወቁ ሰዎች መኪናው ውስጥ እያለ በተተኮሰ ጥይት በሚያሳዝን መልኩ ህይወቱ አልፏል።የድምፃዊው ሕይወት በእንዲህ ዓይነት መልኩ መቀጠፉ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ክፉኛ አሳዝኗል።ጉዳያችንም በድምፃዊ ሃጫሉ ሞት ላዘኑ ቤተሰቦቹ መፅናናትን ለሀጫሉም ዕረፍተ ነፍስን ትመኛለች።ድምፃዊ ሃጫሉ በኢትዮጵያ የስነ ፅሁፍ ታሪክ ትልቅ አሻራ ያስቀመጡትየአምቦው ተወላጅ  እና የሀገር ወዳዱ ሎሬንት ፀጋዬ ገብረመድህን ቤተሰቦች ጋር በአያቱ በኩል እንደሚገናኝ ከቤተሰቡ መረዳቱን አርቲስቱ በአንድ ወቅት በሰጠው መግለጫ ላይ ገልጦ እንደነበር ጉዳያችን ታስታውሳለች።

ይህ በእንዲህ እያለ ዛሬ ሰኔ 23/2012 ዓም የሃጫሉ ሁንዴሳን አስከሬን ቤተሰቦቹ ይዘው ወደ አምቦ በበርካታ ሕዝብ ታጅበው እየሄዱ ሳለ የቀድሞው የኦሮምያ ኔትወርክ ሚድያ ሥራ አስኪያጅ እና የአሁኑ የኦሮሞ ፈድራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አባል ከጥቂት ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን አስከሬኑን ከቤተሰቦቹ ለመንጠቅ ሙከራ ማድረጋቸው እና በምላሹም ከፌድራል ፖሊስ ጋር ግጭት መፈጠሩን ለማወቅ ተችሏል። በኢትዮጵያ ባሕል መሰረት አንድ ሰው ከእዚህ ዓለም በሞት ሲለይ አይደለም በሀገር ውስጥ ሆኖ በውጪ ሀገርም ቢኖር  አቅሙ እንደፈቀደ በትውልድ ቦታው መቀበር የነበረ ልማድ እና ባሕል ነው።የድምፃዊ ሃጫሉ  ቤተሰቦችም ይህንኑ ለማድረግ ወደ አምቦ መንገድ እንደጀመሩ ነው ጀዋር እና ግብረአበሮቹ አስከሬኑን ነጥቀው በመኪና በመጫን ህዝቡ የአስከሬን ዝርፍያ ያለውን ተግባር የፈፀሙት።

በእዚሁ የአስከሬን ነጠቃ ሙከራ ሳብያ በተከተሉ ሶስት ፍንዳታዎች መሰማታቸውን እና ቁጥራቸው እስካሁን ያልተገለጠ ኢትዮጵያውያን መጎዳታቸው ተሰምቷል።ከሞቱት ውስጥ ያፈነዱትን ጨምሮ ጉዳት ማድረሱ ነው የተገለጠው።ይህንኑ ተከትሎ የድምፃዊ ሃጫሉ አስከሬን ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ መገደዱን እና በኃላ በኤሊኮፍተር ወደ ትውልድ ከተማው አምቦ መወሰዱን ለማወቅ ተችሏል።ይህ በእንዲህ እያለ መንግስት ድምፃዊው ከተገደለበት ሰዓት ጀምሮ ማን እንደፈፀመው ሳይገለጥ የእርስ በርስ ግጭት እና ጠብ የሚፈጥር ቅስቀሳ ሲያደርግ የነበረው የኦሮምያ ሚድያ ኔትወርክ በፌድራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።በሌላ በኩል ከጀዋር ጋር አቶ በቀለ ገርባም በቁጥጥር ስር መዋላቸው የተሰማ ሲሆን በተለይ አቶ ጀዋርን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገው ተግባር ላይ የአቶ ጀዋር ጠባቂዎች በሙሉ ትጥቅ እንዲፈቱ የተደረገ ሲሆን በሂደቱ ላይ አንድ ፖሊስ ህይወቱን ማጣቱ ነው የተሰማው።

በነገራችን ላይ ድምፃዊ ሃጫሉ በተለያዩ ጊዜ በሰጣቸው መግለጫዎች የብዙዎችን ትኩረት የሳበ አርቲስት ነው።ከእነኝህ መግለጫዎቹ ውስጥ - ''ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው፣አይደለም የቴዲ አፍሮን የማሊንም ሙዚቃ እሰማለሁ፣''በማለት ከሚድያ ለተነሱለት ጥያቄዎች የመለሳቸውን ምላሾች አሁን ድረስ የምያስታውሱለት ብዙዎች ናቸው።በአንድ ወቅት ድምፃዊው፣ የጀዋርን እና በቀለ ገርባን አና አንዳንድ የኦሮሞ ዘውግ ፖለቲከኞች ከህወሓት ጋር የሚያደርጉትን መሞዳሞድ በግልጥ የወቀሰበት ጊዜም ነበር።ሌላ ጊዜ ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ ላይ በአንድ ወቅት ''ኦሮሞ አይደለም'' የሚል የሐሰት ዘመቻ ለከፈቱትም የሰጠው ምላሽ ''ዓቢይን አውቀዋለሁ ከሁላችንም ያልተለየ ኦሮሞ ነው።ዓቢይ ሀገር እየመራ ነው።ዛሬ በእርሱ ላይ የሚደረግ የስም ማጥፋት ዘመቻ ነገ ሌላ የኦሮሞ ሰው ስልጣን ላይ ቢመጣም የሚቀር አይደለም።ስለሆነም ማናቸውም በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ላይ የሚደረገውን የስም ማጥፋት ዘመቻ አንቀበልም።'' ማለቱ ይታወሳል።

የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለ ለአምስት ዓመታት በቀድሞው የህወሓት/ኢህአዴግ ስርዓት ታስሮ የነበረው ድምፃዊው ሃጫሉ የሚሰማውን ፊት ለፊት በመግለጥ ይታወቃል።በ36 ዓመቱ ሕይወቱን ያጣው ድምፃዊ ሃጫሉ ባለትዳር እና የሶስት ልጆች አባት እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።ለሀጫሉ ቤተሰብ መፅናናትን፣ለእርሱም እረፍተ ነፍስ ይስጥልን።
 


Monday, June 29, 2020

ሰበር ዜና - በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክርቤት በዛሬው የዓባይ ጉዳይ ስብሰባ ላይ የአሜሪካ ተጠሪ አምባሳደር ኬሊ ክራፍት ያደረጉት ሙሉ ንግግር ጉዳያችን አግኝታለች።ሙሉውን ያንብቡ። Breaking News - US Ambassador to UN, Kelly Craft's speech on the security council meeting of GERD, June 29/2020

''The United States takes note of the recent efforts of the African Union to facilitate additional discussions among the three countries on the GERD. We acknowledge the efforts by South African President Ramaphosa to bring this issue before the African Union bureau.'

Ambassador Kelly Craft Permanent Representative U.S. Mission to the United Nations

Ambassador Kelly Craft

===================
Ambassador Kelly Craft

Permanent Representative
U.S. Mission to the United Nations
New York, New York
June 29, 2020

AS DELIVERED

Thank you, Mr. President. Thank you for your efforts over the past several days to accommodate this important issue before the Security Council. Under-Secretary-General DiCarlo, we appreciate your insightful remarks.

Through our engagement as a facilitator and observer of the negotiations on an agreement for the filling and operation of GERD over the last several months, the United States understands and appreciates the importance of the Nile River to the histories and futures of Egypt, Ethiopia, and Sudan.

We have seen firsthand how the Nile is deeply intertwined with the national identities of Egypt, Ethiopia, and Sudan and how its future is of paramount importance to the livelihoods and the well-being of their peoples. I know firsthand, as President Trump has prioritized the GERD within our Cabinet.

The GERD poses a unique opportunity for this part of Africa, where precipitation droughts, desertification, and economic underdevelopment have befallen generations of people. An agreement on the GERD has the potential to transform a region that is home to over 250 million people, expanding economic opportunities through transboundary cooperation and regional integration. Increased food security, improved energy access, and expanded agriculture projects are just a few of the transformational benefits that the GERD can afford the region.

The considerable work by Egypt, Ethiopia, and Sudan over the last several months shows it is possible to reach a balanced and equitable agreement that takes into account the interests of the three countries if there is a commitment among all to do so. We commend the Government of Sudan and Prime Minister Hamdok’s administration for ongoing efforts to encourage this process and bring the parties together, including through hosting talks earlier this month.

The United States takes note of the recent efforts of the African Union to facilitate additional discussions among the three countries on the GERD. We acknowledge the efforts by South African President Ramaphosa to bring this issue before the African Union bureau.

We recognize that this issue is before the Council because time is short and the window to achieving such an agreement may be rapidly closing. We encourage all countries to build on their substantial progress in prior negotiations and the compromises that led to that progress, and further call on all countries to refrain from making any statements or taking any actions that would undermine the good will necessary to achieve an agreement.

We strongly believe that with constructive dialogue and cooperation a solution is within reach, and we reaffirm our commitment to remain engaged with the three countries until they conclude a final agreement.

We look forward to receiving further reports on this very important issue. Thank you.

የስምዖን ጉዳይ ተገቢው ምርመራ እና ፍትሕ ይፈልጋል

 ወጣት ስምዖን ደስታ (ፎቶ ኤንአርኮ)

(ጉዳያችን ሪፖርት)

ስምዖን ደስታ ይባላል።በኦስሎ፣ኖርዌይ ነዋሪ ነው።ስምዖን በስነ ምግባሩም፣በትምህርቱ እና ከሰዎች ጋር ባለው መግባባት ሁሉ የሚያውቁት ብቻ ሳይሆን በአንድ ቀን የተዋወቁት ሁሉ የሚወዱት ነው።በኦስሎ መካነ ቅዱሳን ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤት አባል እና በሚታዘዘው አገልግሎት ሁሉ  በማገልገል በምሳሌነት የሚጠቀስ ቅን ወጣት ነው።

ይህ ወጣት ባሳለፍነው ወር ማለትም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ግንቦት 17/2020 ዓም የኖርዌይ ብሔራዊ በዓል ቀን የሚከበርበት ዕለት እንደመሆኑ እርሱም የበዓሉን ዝግጅት ከቅርብ ባልንጀሮቹ ጋር ለማክበር በኦስሎ የከተማ አውቶብስ  እየሄደ ነበር። በመጨርሻም ''ልሳከር'' የአውቶብስ ጣብያ (የመውረጃ ቦታው) ሲደርስ እንደማንኛውም ተሳፋሪ ከአውቶብሱ ሲወጣ የገጠመው እጅግ አስደንጋጭ ጉዳይ ነበር። ስምዖን ለኖርዌይ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን (ኤንአርኮ) እንደ አውሮፓውያ አቆጣጠር ሰኔ  24/2020 ዓም እንደገለጠው እና ጋዜጠኛ አኔት ሁብሰን እንደዘገበችው -

'' ከአውቶብሱ እንደወረድኩ አንድ ሰው ወደ እኔ እየተጠጋ ፀያፍ ስድቦችን ሰደበኝ፣ከሰደበኝ ውስጥ አንተ የውጭ ሰው ነህ ወደ መጣህበት ተመለስ ! እና ሌሎች ይገኙበታል።በመቀጠል እጄን፣ክንዴን እና በመቀጠል ጥርሶቼ ላይ መላልሶ መታኝ'' ማለቱን ጠቅሳለች።

ስምዖን የእዚህ ዓይነት ጥቃት በአደባባይ ሰው እየተመለከተ በማያውቀው ሰው ከተፈፀመበት በኃላ ደም እየፈሰሰው እና አንድ ጥርሱን እንዲያጣ ተደርጎ እራሱን ለመከላከል ያደረገው ጥረትም ሳይሳካ ከወረደበት የከተማ አውቶብስ ማረፍያ ወደ ሆስፒታል ለመሄድ ተገዷል።ድርጊቱ የዘረኝነት ጥቃት ለመሆኑ ስምዖንም፣የኤንአርኮ ዘጋቢም ሆነ ጉዳዩን መመርመር የጀመረው የኖርዌይ  ፖሊስ ሁሉም በጋራ ያመኑበት ጉዳይ ነው።

ወንጀሉ የኖርዌይ ፖሊስ የመዘገበበት ክፍል (የወንጀሉ ''ካታጎሪ'') ''በቆዳ ቀለም እና ማንነት ላይ ያነጣጠረ የጥላቻ ንግግር እና ጥቃት'' በሚል ርዕስ ስር መሆኑን በእዚሁ በኤንአርኮ ዘገባ በተገለጠው መሰረት ለማወቅ ተችሏል።የኖርዌይ ፖሊስ ዳይሬክቶሬት የወንጀል ምርመራ ክፍል ''አክቲንግ'' ኃላፊ አስትሪድ ቡርገ፣ የኖርዌይ ፖሊስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኖርዌይ የእዚህ ዓይነቱ የዘረኝነት ጥቃቶች ላይ ትኩረት እንደሰጠ እና በማኅበረሰቡም ውስጥ የበለጠ ትኩረት እያገኘ እንደመጣ ለኤንአርኮ እንደገለጡለት ዜናው በተጨማሪ ያብራራል።

የኖርዌይ ፖሊስ ዳይሬክቶሬት የወንጀል ምርመራ ክፍል ''አክቲንግ'' ኃላፊ አስትሪድ ቡርገ (ፎቶ ሸትል ግሩድ)

ለማጠቃለል የእዚህ ዘገባ ጸሐፊም ስምዖንን እንደሚያውቀው፣ ወጣቱ ፈፅሞ ከማንም ጋር ግጭት የመፍጠር ስብዕና ያለው ወጣት አይደለም።ወጣቱ በክርስትና ሃይማኖት የታነፀ እና እጅግ የሰከነ ስብዕና ያለው ወጣት ነው።በመሆኑም በስምዖን ላይ የእዚህ ዓይነት ጥቃት ፈፅሞ ሊፈፀምበት የሚገባ አይደለም።በስምዖን ላይ ብቻ አይደለም፣ድርጊቱ በማንም ላይ ሊፈፀም የማይገባ ድርጊት ነው።በመሆኑም ፖሊስ ተገቢ ምርመራ አድርጎ በወጣቱ ላይ የዘረኛ ጥቃት የፈፀመው ወንጀለኛ እና ተባባሪዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ እንዲያደረግ የሁሉም ፅኑ ፍላጎት ነው።


Friday, June 26, 2020

ሰበር ዜና - ኢትዮጵያ፣ግብፅ እና ሱዳን ዛሬ በመሪዎች ደረጃ ተነጋገሩ።በሁለት ሳምንታት ውስጥ የጋራ ሰነድ በባለሙያዎች እንዲዘጋጅ ተስማምተዋል።በእዚህ ስምምነት ኢትዮጵያ በለጠች? ወይንስ ተበለጠች? (ጉዳያችን አጭር ልዩ ዘገባ)


  • በዛሬው ድርድር ኢትዮጵያ በሶስት ጉዳዮች በልጣለች፣ግብፅ አንድ ጊዜያዊ ድል አግኝታለች። 

ዛሬ ዓርብ ሰኔ 19፣2012 ዓም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዓቢይ አሕመድ፣የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ እና የሱዳኑ ፕሬዝዳንት አብዱላህ ሃምዶክ በወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ፕሬዝዳንት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ራማፎዛ ሰብሳቢነት በቪድዮ ስብሰባ አድርገው ነበር። በስብሰባው ውጤት መሰረት ሶስቱም አገሮች በሕግ እና ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ የስምምነት ሰነድ የሚያዘጋጅ የባለሙያዎች ኮሚቴ ለመመስረት ተስማምተዋል።በእዚህ ስምምነት መሰረት ይህ ኮሚቴ በሁለት ሳምንታት ውስጥ ሰነዱን አዘጋጅቶ እንደሚያቀርብ ነው የተነገረው።የግብፅ እና የሱዳንን መንግሥታት በምንጭነት በመጥቀስ የዓለም ዜና አውታሮች ሮይተር፣ኤኤፍፒ፣ሳውዲ ፕሬስ፣ዴይሊ ኒውስ፣አሶሼትድ ፕረስ  እና የግብፁ አልሃራም ጭምር በዛሬው ስምምነት ላይ ማምሻውን የዘገቡ ሲሆን ከአሶሸትድ ፕሬስ ውጪ ኢትዮጵያ ከስምምነቱ በፊት ውሃውን አትሞላም እያሉ ማምሻውን ፅፈዋል።በኢትዮጵያ በኩል ግን እንዲህ የሚል ቃል ግን አልተገባም።እዚህ ላይ አሶሼትድ ፕሬስ ኢትዮጵያ ከስምምነት በፊት ውሃ አልሞላም አለች የሚል ቃል አለመፃፉ የሚያስመሰግነው ነው።አሶሼትድ ፕሬስ ከኢትዮጵያ በኩል እስካሁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ በትውተር ገፃቸው ላይ ''ጠቃሚ ውይይት አድርገናል'' ካሉት ውጪ የተሰጠ መግለጫ አለመኖሩን ነው የገለጠው።በመሆኑም የአሶሼትድ ፕሬስ ከሁሉ የተሻለ ዘገባ ነው ያቀረበው።ምክንያቱም ሌሎቹ የግብፅ እና የሱዳንን መንግሥታት እየጠቀሱ ነው የፃፉት እንጂ የኢትዮጵያን መግለጫ አላካተቱም።

እዚህ ላይ በዛሬው ስምምነት ላይ በሁለት ሳምንት ውስጥ ቴክኒካል ኮሚቴው ሰነድ ያዘጋጅ ማለት በሁለት ሳምንት ውስጥ ባዘጋጀው ሰነድ ስምምነት ካልተደረሰ የክረምቱ ውሃ እስኪያልፍ ውሃ አትሞላም ማለት ሊሆን አይችልም።በኢትዮጵያ በኩል ውሃው የሚተኛበትን ቦታ የመመንጠር ሥራ በእዚህ ሳምንት ተጀምሮ በአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ለማጠናቃቅ እየተሰራ መሆኑን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን በእዚህ ሳምንት አስታውቀዋል።ይህ ማለት እነኝህ ሁለት ሳምንታት ውይይት ተደረገም አልተደረገ ኢትዮጵያ የዝግጅት ጊዜዋ ነው።

የዛሬውን ድርድር ሂደት እና ትርፍ እና ኪሳራውን ለማስላት የግብፅ እና የኢትዮጵያ ዋና ግብ ምንድን ነበር? ብሎ መጠየቅ እና ምላሽ ማግኘት ያስፈልጋል።

በመጀመርያ የግብፅ ፍላጎት ምን ነበር? 

ግብፅ ዋና ዓላማዋ በአደባባይ ያለው ፍላጎት ውሃውን ሳንነጋገር አይሞላ ነው።የውስጥ ዓላማዋ ግን የዓባይ ግድብ የምስራቅ አፍሪካ የፀጥታ ችግር ነው በሚል ከነአካቴው በረጅም ጊዜ እንዲጠፋ ማድረግ ነው።ለእዚህም ዋና መንገድ ጠራጊ  ያደረገቸው የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክርቤት  እና የአረብ ሊግን ነበር።በሁለቱ ድርጅቶች በኩል ግድቡ የፀጥታ ችግር ነው የሚል ከፍተኛ ስጋት ፈጥሮ በሂደት የኢትዮጵያን ዕድገት ለማይፈልጉ ኃይሎች ግድቡን አሳልፎ መስጠት ነበር። 

የኢትዮጵያ ፍላጎት ምንድነው?

ኢትዮጵያ የግድቡ ውሃ ሙሌት በእዚህ ክረምት እንዳያልፍ ትፈልጋለች።ዋናው የረጅም ጊዜዋ ግብ ግን ግብፅም የግድቡን ወደ ሥራ መግባት አምና የምትቀበልበት አንድ ዓይነት ውል መግባት እና ያረጀውን የቅኝ ግዛት ውል እንድትጥል ነው።ከእዚህ ውጪ ኢትዮጵያ አንዴ ግድቡን ወደስራ ታስገባው እንጂ በአንድ ሺ መንገዶች ወደፊት ተፅኖ የመፍጠር መንገዶች አሏት።ግድቡን ጨርሳ ወደ ሥራ ማስገባቷ በራሱ ከግብፅ አልፎ መካከለኛው ምስራቅ ላይም እጇ ረዘመ ማለት ነው።ስለሆነም የኢትዮጵያ ዋና ግብ በምንም መንገድ ሄዶ ግድቡን ወደ ሥራ ማስገባት ነው።

ሁለቱም አገሮች ውጥረቱ እንዲበርድ የሚፈልጉባቸው ምክንያቶች ምንድናቸው?

 ግብፅ ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ውጥረት ቢያንስ በአሁኑ ወቅት መርገብ እንዳለበት የምታስብበት ምክንያት በቱርክ የሚደገፈው የሊብያ ኃይል  ሰሞኑን ትሪፖልን ዙርያ በግብፅ የሚደገፈውን ኃይል ከማፅዳቱ አንፃር ግብፅ ትልቅ የፀጥታ ስጋት ስለጋረጠባት እና ምጣኔ ሀብቷ ጀርባ የሆነው የቱሪዝም ንግዱ በኮሮና ወረርሽኝ ሳብያ ስለተዳከመ ከሊብያ እና ከኢትዮጵያ አንዱን መምረጥ የግድ የሚላት ጊዜ ላይ ነች።

ከቱርክ፣ኢራን እና ሩስያ ጋር በቀጥታ መጋጨት የማይፈልጉት ነገር ግን በሊብያ ጉዳይ ውስጥ በቀጥታ እንድትገባ ከጀርባ የሚገፋፏት የምዕራብ አገሮችም ፍላጎት ግብፅ በሊብያ ጉዳይ እንድትገባላቸው ነው።ስለሆነም ለግብፅ በአሁኑ ጊዜ የዓባይን ጉዳይ በአንድ ዓይነት ውል አስሮ ወደ ጊዜ የማይሰጠው የቅርብ አደጋ የሊብያው ጉዳይ ላይ ማተኮር የግድ አለባት።በእዚህ ሳምንት የግብፅ መገናኛ ብዙሃን እያወሩ ያሉት ሊብያውያን ግብፅ ጣልቃ እንድትገባ እየጠየቁ ነው የሚል ሰፊ ዘመቻ ላይ ነው የሰነበቱት።ይህ የሚያሳየው ግብፅ ወደ ሊብያ መዝመቷ እንደማይቀር ነው።ስለሆነም የዓባይ ግድብ ጉዳይ አሁን መርገብ እንዳለበት ግብፅ ታስባለች።መርገብ ያለበት ግን ግብፅ የተሸነፈች መስላ በሕዝቧ ውስጥ ታይታ ሳይሆን የሆነ ''የማርያም መንገድ'' ዓይነት ብታገኝ ማፈላለግ ላይ ነበረች።የዛሬው የመሪዎች ውይይት እንዳበቃ ኢትዮጵያ ውሃውን ሳንስማማ አትሞላም የሚለውን ዜና በማውራት ሕዝቧን ድል እንዳገኘች ለማውራት የመፍጠኗ ምስጢርም ይሄው ነው።

ኢትዮጵያ   ኢትዮጵያ አሁን ሽግግር ላይ እንደመሆኗ መጠን ምንም ዓይነት ግጭት ውስጥ (አስገዳጅ ካልሆነ በቀር) መግባት አትፈልግም።ምክንያቱም ውስጣዊ መረጋጋት እና ምርጫ ገና ይጠብቃታል።በሚፈጠሩ ግጭቶች ደግሞ ቢያንስ የግድቡን ወደ ሥራ የመግባት ዕድል ስለሚያደናቅፍ በተቻለ መጠን ዘለቄታዊ ሂደቱ ላይ አተኩራለች።


በእዚህ ስምምነት ኢትዮጵያ በለጠች? ወይንስ ተበለጠች?

በዛሬው ስምምነት ኢትዮጵያ ተበለጠች? ወይንስ በለጠች? የሚለውን ለመመልከት ግብፅ እና ኢትዮጵያ ምን ነበር የሚፈልጉት የሚለውን መመልከት ስለሚገባ ከላይ ይህንኑ አስመልክቶ በመጠኑ ለመግለጥ ተሞክሯል።ይህ በእንዲህ እያለ ግን ማወቅ ያለብን ጉዳይ ግብፅ በመጪው ሰኞ ሰኔ 29/2012 ዓም የሰርግ እና ምላሿ እንደሚሆን ጠብቃ ነበር።ይሄውም የተባበሩት መንግሥታት 15 የፀጥታው ምክርቤት አባላት ግብፅ እና ሱዳን በዓባይ ግድብ ዙርያ ያስገቡትን ደብዳቤ ጉዳይ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ተይዞ ነበር።በእዚህ ስብሰባ ምክር ቤቱ ቢያንስ ሁለቱ አገሮች እንዲወያዩ ኢትዮጵያም ውሃውን መሙላት ብታዘገይ ሊል እንደሚችል ይገመታል።ይህ ቢደረግላት ኖሮ ግን ግብፅ ይህንን ውሳኔ አንቀፅ እየጠቀሰች ለስህተቱ ምክንያት ኢትዮጵያ ነች በሚል በዲፕሎማሲው መንደር ለመለፈፍ ተዘጋጅታ ነበር።

ኢትዮጵያ ቀደም ብላም የግድቡ ድርድር በአፍሪካ ሕብረት በኩል ድርድር ሊደረግበት እንደሚገባ ገልጣለች።ከወራት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ  በደቡብ አፍሪካ ጉብኝት በሚያደርጉበት ወቅት ይህንን ሃሳብ ለደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት አቅርበው ነበር።በወቅቱ ኢትዮጵያ እና ግብፅ በአሜሪካ ድርድር እያደርጉ ነበር።

ስለሆነም ኢትዮጵያ ከዛሬው ድርድር ሶስት ድሎች አግኝታለች።ግብፅ ደግሞ አንድ ጊዜያዊ ድል አግኝታለች።

ኢትዮጵያ ያገኘችው -

1) ድርድሩን ከአሜሪካ ጉያ ወጥቶ ወደ አፍሪካ ሕብረት እንዲመጣ ማድረግ መቻሏ እና ግብፅም ወደ እዚሁ መድረክ እንድትመጣ ሆኗል።

2) ኢትዮጵያ በመጪው ሰኞ በፀጥታው ምክርቤት የውሃ መሙላቱ ጊዜ ቢረዝም የሚል ሃሳብ ከመሰጠቱ በፊት በአፍሪካ ህብረት በኩል በሁለት ሳምንት የቴክኒክ እና ባለሙያዎች ኮሚቴ እንዲመሰረት መስማማቷ ኢትዮጵያ ሁለት ጥቅም ታገኛለች፣አንዱ ሰኞ የፀጥታው ምክርቤት ሳይናገር ቀድማዋለች። የዛሬው ውይይት ውጤትም ለፀጥታው ምክር ቤት እንደሚላክ በዛሬው ውይይት ወቅት ለማወቅ ተችሏል።ሁለተኛ ውሃውን አልሞላም የሚል ቃል ሳትገባ በሁለት ሳምንታት ውስጥ የሚቀርብ ሰነድ ለማየት ተስማምታለች።

3) ኢትዮጵያ ደረቅ ዲፕሎማሲ የምትከተል ሳይሆን ለሰላማዊ መግባባት ምን ያህል ርቀት እንደምትሄድ ዛሬ አሳይታለች።ግብፅ በሰሞኑ ሂደቷ ኢትዮጵያ ውሃ መቼም የመሙላት መብት የላትም አይደለም ስትል የሰነበተው።በአደባባይ ያለችው ውሃው የሚሞላው በእንዲህ ጊዜ ይሁን የሚል ''ውሃ የማይዝ'' የማዘናጋት ሂደት ነው የተከተለችው።ጉዳዩ ውጥረት በመፍጠሩም በሚል በመካከለኛው ምስራቅ ያሉ አገሮችም ሆኑ የሩቅ ተመልካቾች አላስጨነቃቸው ማለት አይቻልም። ስለሆነም ኢትዮጵያ በዛሬው ድርድር የሁለት ሳምንታት  ለጋራ ሰነድ ማዘጋጃ ጊዜ መስጠቷ ምን ያህል ጉዳዩ በሰላም እንዲፈታ ፍላጎት እንዳላት ያሳየችበት ዕድል ፈጥሯል።ውጥረቱንም አላልታዋለች።ለግብፅ የሚሻላት ግን ውጥረቱ ማየሉ እና የፀጥታው ምክር ቤት ያሉ ወዳጆቿም ጉዳዩ ዓለም አቀፍ የፀጥታ ችግር ነው ብለው ለማሳመን ጥሩ ምክንያት እንዲያገኙ ነበር።አሁን በሁለት ሳምንት መላላቱ ግን የፀጥታው ምክር ቤትም ጉዳዩ በአፍሪካ ሕብረት ተይዟል በሚል በመጪው ሰኞ ስብሰባውን ሊሰርዘው የሚችልበት አጋጣሚ ሁሉ ሊኖር ይችላል። 

ግብፅ ያገኘችው ጊዚያዊ ድል 
ግብፅ በዛሬው ድርድር ያገኘችው ድል ጊዜያዊ የሁለት ሳምንታት የፕሮፓጋንዳ ድል ነው።ይሄውም ውሃውን ሳንስማማ እንዳትሞሉ ብለን ነበር።ይሄው ይህንን አስፈፅመን መጣን በሚል ለህዝባቸው መንገር ነው።ቀደም ብሎ እንደተገለጠው ኢትዮጵያ ውሃውን ሳንስማማ ላለመሙላት ተስማማሁ የሚል ቃል አልሰጠችም።በሁለት ሳምንት ውስጥ አንድ ሰነድ ተዘጋጅቶ ሶስቱም ሀገሮች ሊስማሙበት ነው ቀጠሮ የተሰጠው።ኢትዮጵያም የግድቡን የስራ ሂደት አላቆመችም።ውሃው የሚተኛበት ቦታ ምንጠራም በአንድ ወር ውስጥ ለምፈፀም በእዚህ ሳምንት ስራው ተጀምሯል።

ኢትዮጵያ የማታልፈው ቀይ መስመር 

ኢትዮጵያ በዛሬው ስብሰባ ላይ የሁለት ሳምንታት ጊዜ ለአንድ የጋራ ሰነድ ማዘጋጃ ጊዜ ትስጥ እንጂ ከሁለት ሳምንታት በኃላ በሚዘጋጀው ሰነድ ላይ ካልተስማማች ውሃውን የመሙላቱን ተግባር ፈፅማ ልታቆም አይገባትም።ምክንያቱም ይህ ክረምት ውሃው በታቀደው መሰረት ካልተሞላ በአንድ ዓመት ውስጥ ብዙ ነገሮች ሊቀያየሩ ይችላሉ።ስለሆነም ዘንድሮ ውሃውን አለመሙላት ኢትዮጵያ ልትዘለው የማትችለው ቀይ መስመር ነው።በመሆኑም ውሃውን የመሙላት ጉዳይ ለድርድር ሊቀርብ የሚችል አይደለም።   

ለማጠቃለል፣የግድቡ ጉዳይ በሰላም ሁሉንም አገሮች በተለይ የኢትዮጵያን የራሷን የውሃ ሀብት የመጠቀም ሉዓላዊ እና የማይገሰስ መብቷን አስከብሮ  ስምምነት ላይ ቢደረስ ለኢትዮጵያም ሆነ ለአካባቢው የቀጠናው ሀገሮች መልካም ዜና ነው።በመሆኑም ''ዊን ዊን'' ድርድር እንዲሆን የሁሉም ምኞት ነው።ይህ ስምምነት ከተፈረመ እስከመቼውም ሰላም ይሆናል ማለት ግን አይደለም።ምክንያቱም ግብፅ የስልት ለውጥ አድርጋ የረጅም ጊዜ ዕቅድ አታወጣም ብሎ መናገር አይቻልም።ሆኖም ግን ኢትዮጵያ ኃይል መመንጨት ከጀመረ በኃላ ያላት አቅም ስለሚደረጅ የመደራደር አቅሟ በዚያው መጠን ስለሚያድግ ኢትዮጵያ አሁንም ተጠቃሚ ትሆናለች። በመጨረሻም የማኅበራዊ ሚድያው መንግስት በሚያደርገው የድርድር ውጣ ውረድ ላይ  ከውስጥ ያሉትን ነባራዊ ሁኔታዎች ሳያውቅ እና የመንግስትን ስልታዊ አካሄድ ሳይረዳ በስሜት በመሄድ ለሕዝብ የተሳሳተ መረጃ እንዳያደርስ መጠንቀቅ አለበት።

የዓባይ ግድብን በተመለከተ ኢትዮጵያ እያለች ያለውን በእንግሊዝኛ በሰባት ደቂቃዎች ጭውውት ቀርቧል።

Tuesday, June 23, 2020

Ethiopians great dam on Nile River is a source of peace and stability for the horn of Africa, Europe and the Middle East as a whole.

The Gibe III dam on the Omo River, Ethiopia (Mimi Abebayehu/CC BY-SA 4.0)
The Grand Ethiopian dam on Nile River (Photo - Global Construction-review)

Gudayachn special alert
June 23,2020 
==============

It is quite known that poverty leads to instability and insecurity.  The miserable lives of over Fifty million Ethiopians, living without any access to electric power had been a great threat of security both in Ethiopia and the horn. According to the 2018 world bank report, only 45% of Ethiopians have access to electricity.That means 55% of the ancient land population had already been disregarded from the basic civilization privilege of electric power in the 21st century. On the contrary, Egypt had fully satisfied the demand of electricity and utilizing the Nile river for agricultural production. 


Now the question of justice and mutual benefit is raised.That is without creating any hindrance to Egyptians normal life and all benefits  that they are obtaining from the Nile River, Ethiopia is on the way to use her own water resource through building a dam with her own domestic resource and generating an electric power. The dam building process had been confirmed positively by the International Environmental Impact Assessors (EIA). As a result, the negative impact of the dam to downstream countries (Sudan and Egypt) is almost null. Rather it will protect the annual erosion disasters which these countries had been suffering for a number of years. 


Currently, the Egyptian Government is trying to mislead the international community and its own people as if Ethiopia had plan to retain the water within her own territory. However, this is contrary to fact.As Ethiopian senior officials repeatedly confirmed that Ethiopia has never planned to retain the water within her territory. That means after passing through the dam to rotate the electric turbines, the water will continue to flow towards Sudan and Egypt.


Last but not least, you should not be surprised,when you hear that almost the whole people of the horn of Africa are waiting eagerly for the starting day of the dam to generate electric power. This is because the issue is not only a matter of generating power. It is more than above it.That is it will  stabilize the horn of Africa and the middle east through creating interrelated economic benefits.Because Ethiopia is not only using the generated electric power for her own domestic consumption, but the neighboring and even the middle east countries will also be accessed to get power. Therefore,it must not be undermined to take out millions from devastating poverty is nothing but it is a guarantee to peace and stability. This assurance of peace and stability is not only to the horn of Africa but to the middle east and  Europe. Because Ethiopia and the horn could create more jobs for the young generation. As the result the number of illegal refugees,originated from the horn,travelling to the Middle east and Europe will drop down tremendously.Therefore Ethiopian dam is key for the stability of peace and security for the horn of Africa,Europe and the middle east as a whole.


By Getachew Bekele
Gudayachn Editor
getachewb221@gmail.com


Monday, June 22, 2020

አውሮፓ እና አሜሪካ ተቀምጣችሁ የዓማራ የዘውግ ፖለቲካን በአክትቪዝም ስም ያጦዛችሁ እና ሀገር ቤት ያለውን አመራር እረፍት የነሳችሁ ይህንን ቪድዮ  ስትመለክቱ ምን ተሰማችሁ? 

ከላይ የተሰጠው  ርዕስ  የአርት ቲቪ ርዕስ አይደለም።
ምንጭ - አርት ቲቪ ሰኔ 15/2012 ዓም 


ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com

Saturday, June 20, 2020

በዓባይ ግድብ ዙርያ ግብፅ ወደ ፀጥታው ምክር ቤት እንድትሄድ የሚገፋት የጀርባ ምስጢር


ግብፅ የዓባይን ጉዳይ ወደ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ደጋግማ የምትወስደው አንዱ ዓላማ ግድቡን በኃያላኑ ቁጥጥር ስር እንዲገባ ነው::ግብፅ አሁን ባለው ሁኔታ በግድቡ ላይ ምንም ዓይነት የቀጥታ ወታደራዊ ጥቃት በመፈፀም የምታተርፈው ነገር እንደሌለ ታውቃለች።ምክንያቱም ወታደራዊ ጥቃት የሚያስከትለው ብዙ ውጪ አለ።ይሄውም ሌሎች ኃይሎችን ከኢትዮጵያ ጎን ለማቆም ከመጋበዙ በላይ የአፍሪካውያን ጋር የምትገባው ፍጥጫ በራሱ የመገለል አደጋ ያስከትልባታል።በውሃው ጉዳይ ላይ ያላትን የወደፊት ድርድር በበለጠ አበላሽቶ የካሳ ጥያቄ ንትርክ ውስጥም ይከታታል።በሌላ በኩል አሁን ባለው ሁኔታ የምስራቅ አፍሪካን ፖለቲካ የሚያምስ ሥራ መስራት ቀጠናውን ዙርያውን ለከበቡት የፅንፍ ኃይሎች ዕድል መስጠት መሆኑን ኃያላኑም ይረዳሉ።ስለሆነም ይህንን እርምጃዋን ቢያንስ አሁን አይደግፉላትም።ለምን? ቢባል ለቻይናም ሆነ ለአሜሪካ ዋነኛ የንግድ መተላለፍያ መስመር በእዚሁ አካባቢ ስለሚገኝ ሌላ ሊብያ እና ሶርያ ከመፍጠር የሚገኝ ትርፍ ለኃያላኑ የለም።በመሆኑም ብዙዎች እንደሚሉት የግብፅ አዋጪ መንገድ ከጀርባ ኢትዮጵያን ማዳከም ነው።የእዚህ ፅሁፍ መነሻ ግን ይህ አይደለም።ግብፅ ጉዳዩን ወደ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ምክር ቤት የመውሰዱ ጥረቷን ለምን ገፋችበት?  በሚለው መሰረታዊ ጥያቄ ላይ ነው።

 አሁን ባለው ሁኔታ ኃያላኑ እራሳቸው የሚፈሩት ትልቅ ጉዳይ  በግድቡ ጉዳይ እርስ በርስ እንዳያጋጫቸው እና የተፅዕኖ የመፍጠር አቅሙን አንዱ ለብቻው ጠቅልሎ እንዳይወስድ ነው።በዓባይ ግድብ ጉዳይ ላይ ከተጋጩ ደግሞ ግጭቱ ወደ የሚፈሩት የአፍሪካ ላይ ንጥቂያ ማደጉ አይቀርም::ይህ ደግሞ አንዳቸውም ሳይጠቀሙ አፍሪካውያን በሚጫወቱት ሁለት ካርድ ጠንክረው የመውጣት ወይንም የአንዱ ሙሉ ንብረት የመሆን ሁኔታ ይፈጠር እና መቶ ከመቶ የማጣት ዕጣ ለጊዜው በማን ላይ እንደሆነ ባልታወቀ አንዱ ሃያል ሀገር ላይ ይደርሳል።ይህ ማለት ቢያንስ አንዱ የሚያጣ ሃያል ሀገር የመሆን አደጋው ሁሉም ጋር እኩል ነው ማለት ነው።እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1884 እስከ 1885 ዓም  በበርሊን የተደረገው አፍሪካን የመቀራመት ኮንፍረንስ  ዓላማ ይሄው ዓይነት ነበር።ሁላችንም ከምናጣው ተከፋፍለን ትንሽ ትንሽ ይድረሰን የሚል ዓላማ ነበረው።ኮንፍረንሱ እርስ በርስ ላለመጋጨትም የረዳ ነበር።የዓባይ ጉዳይም ይሄው ነው።በተናጥል ቢሄዱ ኢትዮጵያ እና ግብፅ በመጨረሻ ተስማምተው ወይንም ኢትዮጵያ በዓላማዋ ፀንታ ጠንክራ ትወጣለች በእዚህም ሁሉም ያጡታል።ከእዚህ ይልቅ ወደ ፀጥታው ምክር ቤት ከመጣ ግን ሳይነጣጠቁ የድርሻቸውን ሚዛን እየጠበቁ ተፅዕኖ የመፍጠር አቅማቸውን እየተጠቀሙ ቢያንስ ኢትዮጵያ ጠንክራ እንዳትወጣ  ግብፅም ከተፅዕኗቸው ውጪ ሳትሆን ለመጫወት ይመቻቸዋል::በእዚህ ሁሉ መንገድ ስንመለከተው ግብፅ ጉዳዩን ወደ የፀጥታው ምክር ቤት እንድትወስደው ከኋላ የሚጎተጉቱ የሉም ማለት አይቻልም::በሌላ አነጋገር "ጉዳዩን ለብቻዬ እንዳየው አታድርገኝ::ሁላችንም በተሰበሰብንበት ሳሎን ይዘኸው ና!" እንደማለት ነው::

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1960 ተጀምሮ በ1968 ዓም የተፈፀመው እና ምርቃቱ ግን በ1971 ዓም የተከናወነው የአስዋን ግድብ፣ ግብፅ ከሰራች በኋላ በምዕራቡ ዓለምና በሩስያ መሃል ጦርነት ቀረሽ ፍጥጫ ነበር::የግብፁ የያኔው ፕሬዝዳንት ገማል ናስር ከሩስያ ጋር በመቆም፣ሩስያም በግልጥ ከግብፅ ጋር በመቆም የግድቡን ንብረትነት አረጋገጡ እንጂ የጦር መርከቦች ለውጊያ ተሰብቆባቸው ነበር።ሃያላኑ ያን ጊዜ እንዲህ መከፋፈላቸው የግድቡን ባለቤትነት ለግብፅ አስከበረ።

ኃያላኑ ከአስዋን ተምረው የኢትዮጵያን ግድብ ከኢትዮጵያም ከግብፅም ተፅዕኖ ወጥቶ እነርሱ የሚያሽከረክሩት እንዲሆን ዛሬ ከያኔው ተምረው የሚመክሩ አማካሪዎች የሏቸውም ማለት አይቻልም።ቁምነገሩ ኢትዮጵያም አካሄዱን ቀድማ የመረዳቷ ቁምነገር ነው።ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ግብፅም ብትሆን ብልህነቱ ቢኖራት በፍትሃዊ አጠቃቀሙ ላይ ከኢትዮጵያ ጋር ተስማምታ፣ኢትዮጵያም ቃል በገባችው መሰረት ግብፅን የሚጎዳ ነገር እንደማታደርግ እያሳየች ተባብረው መቀጠል ነው ያለባቸው።የግብፅ መንግስት ጃልጅልነት የሚታየውም እዚህ ላይ ነው።በድርድሩ ተስማምቶ የኃያላኑን መጎተት አቁሞ መጠቀም የተሻለ መንገድ ነው።ኢትዮጵያ እንድትዳከም ግድቡ በኃያላኑ የእጅ ዙር ተፅዕኖ ስር እንዲወድቅ ወደ ተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክርቤት ይዞ መሮጥ ለራሷ ለግብፅም በረጅም ጊዜ የሚያመጣው ጥቅም የለም።

የኃያላኑ እንደፈለጉ በተናጥል በግድቡ ጉዳይ ላይ እንዳይገቡ ሌላው ስጋት የሚሆነው የዓባይ ግድብ ጉዳይ በአፍሮ ዓረብ መሃል የተቀመጠ ወሳኝ የማዕዘን ድንጋይ መሆኑ ነው።የዓባይ ግድብ ጉዳይም ወደ አፍሮ አረብ ፍጥጫ አደጎ ኃያላኑ ወደ አንዱ በግልጥ አድልተው ቢቆሙ በአፍሪካም ሆነ በአረብ ሀገራት ያለው ጥቅማቸውን የሚያውክ ሁኔታ እንደሚፈጠር ያውቃሉ::ስለሆነም ነገሩ በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት እየተንከባለለ ቢቆይና አስፈላጊ ሲሆን ተጽዕኖ የሚያሳርፉበት ጉዳይ እንዲሆን ይፈልጋሉ::የግብፁ ውጪ ጉዳይ ሚንስትር ስሌትም የኃያላኑም ዕሳቤ ይህ ነው የሚሆነው።አሜሪካም ሆነች ቻይና ለመጪው ዘመናቸው በአፍሪካ ሀብት ላይ ካልተንጠላጠሉ ኢንዱስትሪዎቻቸው በጥሬ ዕቃ ችግር እንደሚጎዱ ያውቃሉ።በቅርቡ ትራምፕ ወደ 9ሺህ የሚሆኑ የአሜሪካ ወታደሮች ከጀርመን እንደሚወጡ ሲናገሩ ያሉት ወደፊት ትኩረታቸው ወደ አፍሪካ እና እስያ እንደሆነ እና የአሜሪካ ወታደሮችም ለሁለቱ አህጉሮች እንደሚፈለጉ የሰጡት ፍንጭ የሃያላኑን መጪ አቅጣጫ አመላካች ነው።አፍሪካ ሲነሳ ደግሞ ኢትዮጵያ አለች።ኢትዮጵያ ስትነሳ የዓባይ ግድብ አለ።

በሌላ አንፃር ግን የግብፅ ወደተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት መሮጥ በራሱ በተባበሩት መንግሥታት በኩልም ተቀባይነት አላገኘም። የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ በቅርቡ ያሉት፣ ሶስቱ ሀገሮች በራሳቸው መፍታት አለባቸው የሚል ነው::በመሰረቱ አንድ ጉዳይ ወደ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት የሚሔደው ቢያንስ በአህጉራዊ ድርጅቶች ታይቶ ነው::ግብፅ ይህ ጠፍቷት ሳይሆን አሁንም ከኋላ ሆነው "ይዘሽው ነይ!" የሚሏት የኃያሉን ቃል በማመን ነው::ግብፅ የዓባይ ግድብ ጉዳይ በሃያላኑ እጅ እንዲወድቅ እና ግጭት ተፈጥሮ በሰላም ማስከበር ስም በገላጋይነት ቢገቡ ሁሉ ምኞቷ ነው።በእዚህም ለዘለቄታው ኢትዮጵያ ተጠቅማ ጠንክራ ከምትወጣ ይልቅ እንድትዳከምላት ካላት የረጅም ጊዜ ዕቅድ አንፃር ነው።ስለሆነም አሜሪካ ብቻዋን እጇን እንድታስገባ ያደረገችው ጥረት ሁሉ በምትፈልገው መጠን ባለመሳካቱ አሁን ቢያንስ ሃያላኑ በቡድን በተፅኗቸው ስር እንዲገባ እንደ ገፀ በረከት ለመስጠት የጅራት ማወዛወዝ ሥራ እየሰራች ነው።ይህ ግን ኢትዮጵያ ውስጣዊ አንድነቷን እስከጠበቀች ድረስ ፈፅሞ አይሳካም። 

ባጭሩ ግን የዓባይ ጉዳይ አሁን ኃያላኑን የሚያጋጭ ጉዳይ እንዳይሆን እና ምስራቅ አፍሪካን የሚያናጋ እንዳይሆን መጨነቅ አለ::ጭንቀቱ ኢትዮጵያ እንዳትጎዳ አይደለም::ሌላ ሊብያ እና የመን ከመጣ የንግድ ጥቅማቸው ይጎዳል::የአንዱ ኃያል በተናጠል ለመቆጣጠር ይንቀሳቀሳል፣ይህ ደግሞ ከባድ ግጭት ያመጣል::ዓባይ ግድብን ተቆጣጠርክ ማለት ግብፅ ላይ ቢያንስ በጎ ተፅኖ አለህ ማለት ነው።ግብፅ ላይ ተፅኖ አለህ ማለት የዓለም በርካታ የንግድ መስመር የሚንቀሳቀስበትን መተላለፍያ ላይ ተፅኖ አለህ ማለት ነው።ይህ ጉዳይ ደግሞ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ስታመነጭ የኤሌክትሪክ ሽያጭ በምትሰጣቸው አገሮች ላይ ሁሉ ተፅኖዋ ያድጋል።ከእዚህ ሁሉ በላይ ግን በአሁኑ ጊዜ ኤሌክትሪክ ማለት ከነዳጅ በላይ ነው።በቅርብ ዓመታት የዓለማችን ተሽከርካሪዎች በሙሉ ወደ ኤሌክትሪክ አየቀየሩም ማለት አይቻልም።ስለሆነም ለኢትዮጵያውያን የዓባይ ግድብ ጉዳይ የሞት እና የሽረት ጉዳይ መሆኑን መረዳት ይገባል።

በመጨረሻ ግን የወቅቱን የዲፕሎማሲ መስመር በተመለከተ በእዚህ ሁሉ መሃል ግን የኢትዮጵያ አብራ ከግብፅ ጋር አለመጮህ ባንድ በኩል ጥሩ ይመስላል።አብረህ ስትጮህ እና ስትመላለስ ነገሩ እንዲጋጋል የሚፈልገው ወገን ይጠቀማል።ግብፅ አሁን ጉዳዩ የዓለም ፀጥታ አካል ነው ብላ ለማሳመን ነው የምትሞክረው።ስለሆነም ኢትዮጵያ አብራ ማዳመቅ አለመቻሏ ሳያበሳጫት አይቀርም።በሌላ በኩል ግን ኢትዮጵያ ቢያንስ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች ጥሩ አረብኛ የሚናገሩ እና የዲፕሎማሲው ልምድ ያላቸው ልዩ ልዑካን አባላት መርጣ ልካ ሃገራቱን በሚገባ ስለጉዳዩ መንገር እና በእየሃገራቱ ላሉት ሚድያዎች በአረብኛ እና በእንግሊዝኛ መግለጫ መስጠት አለባት።ከአዲስ አበባ ከሚወጣ መግለጫ ይልቅ ይህ ብዙ ሥራ ሊሰራ ይችላል።


ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Friday, June 19, 2020

Egypt’s historic and natural claims fallacy over the Nile


Sudan Tribune News Paper
June 19,2020
=============

There has been interminable historic conflict and tension between Ethiopian and Egypt over the Nile water. The cause for this historic disagreement is Egypt’s unjust claim to exclude Ethiopia from using the Nile.Egyptian politicians vehemently argue that Egypt, a country that contributes nothing to Nile’s water, has both natural and historical right to exclusively use the river. They argue to the extent that any drop of water that is taken from the river against their will would draw bloody war.Ethiopia, a country that contributes 85 percent of Nile’s water rejects their claim.

It seems, Egyptian politicians’, activists and moguls chauvinism over their military power and the Nile water eroded their understanding of history and reality. This clouded their mind from seeing the fact that Ethiopia has a stronger historic and natural rights claim than Egyptians themselves do. Moreover, they used several tactics to derail Ethiopia’s claim. Among others, they exaggerated Ethiopia’s claim to the extent that the GERD would starve their nation. Nevertheless, they should understand that their bourbon might cost them a lot.

Egyptians claim that they have historic and natural right over the Nile ignoring the fact that both history and nature gratifies the water to Ethiopia. Naturally, Ethiopian owns 85% of the rivers water. In addition, historically the Blue Nile has always been Ethiopians. The Holy Bible further supports this fact. In the Holy Bible, the Blue Nile is named“Gehon”. This river is one of the four rivers that parted from the river that flows in Eden. God allowed this river to flow over Ethiopian soil and fetch its creatures that live in the Ethiopian territory. It offered the river for Ethiopians because God wanted His children that live in the Ethiopian territory to prosper using the water. While this being the case, Egypt’s claim to decide on Ethiopia’s right to use the water remains unnatural. This proves that Egypt’s claim is against both history and natural law.

Despite these, Egyptian politicians falsely allege to the entire world claiming that Nile’s water is their only source of lifeline. They construct their argument ignoring rainfall and underground water as their source of livelihood. I do not understand way Egyptian politicians hide the fact that Egypt is the fourth richest country in underground water resources in Africa. Egypt owns more than 55,200 km3 underground water. Compared to Ethiopia’s 12,700 km3 ground water reserve, Egypt’s resource is very high. Moreover, at this point, it seems important to cite that Egypt uses less than 20 per cent of its total underground water resource potential. Even more, among the 20 per cent, they use they largely use the one found in the Nile aquifer system.

The natural rhetoric of Ethiopia calls for using from Nile’s surplus. What Ethiopia asks to impound in its Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD) is the share Egypt misuses and/or wastes. For instance, a scientific study undertaken over Lake Nasser shows that annually between 10 to 16 billion m3 water evaporates from lake. This counts for 20-30% of Egyptian income from the Nile River. This is an amount Egypt may substantially reduce using several scientific remedies. Moreover, what Ethiopia asks to annually fill dam is far below what Egypt annually discharges unused to the Mediterranean Ocean.

If one sees the figures, Ethiopia’s demands only 4.9 billion m3 water from the Nile in the first year impoundment. Its highest claim for the second year is13.5 billion m3 of water. This amount is below what Egypt loses due to evaporation on Lake Nasser. Even more, it is far below what Egypt floods into the Mediterranean Sea.

Witnessing all the above facts, it is easy to understand that deep in their heart Egyptian politicians knew that Ethiopia, in using Nile’s water, does in no way call starvation on their soil. They knew Ethiopia intended neither to wholly arrest the Blue Nile, nor suppress Egypt’s water need. They understand that what Ethiopia asks for is water that allows its dam to generate electricity. They know that the dam is necessary to give basic electricity reach a portion of Ethiopia’s more than 40 per cent population with no access to electricity. They recognize that the dam may relieve millions from starvation from hanger in Ethiopia. In general, they knew that what Ethiopia needs is the recognition of its citizens’ natural and historic right to equitably use the Nile.

Seeing all the above, a person should ask “Why Egyptian politicians and activists get furious when they hear about Ethiopians building their Renaissance Dam so that they may use Nile nimiety?”. There seems to be a perfectly fit answer to this question. Egyptian politicians and elites obstinate against all rational arguments. They want to see a weak and a poor Ethiopia. Unless this is the reality, why would Egyptians take Ethiopia’s gain as a loss while they are losing nothing?

=================

Writer Birat Teklu

Bisrat is a Lecturer of Law at the Ethiopian Civil Service University. He is also a senior Consultant and Attorney-at-Law at Bisrat&Beliyu Law Office. He can be reached at teklubisrat@gmail.com.

Tuesday, June 16, 2020

Saturday, June 13, 2020

ማንም ሊሰራ የማይችልባት ሌሊት ሳትመጣ አሁኑኑ የኢ/ኦ/ተ/ ቤ/ክርስቲያን የ24 ሰዓት የቴሌቪዥን የቀጥታ ሥርጭትና የስቱዲዮ ግንባታ ግዴታዎን ይወጡ።

ከጊዜው ካልተማርን ከማን እንማራለን? 

ይህ ጊዜ ከወንጌል በላይ በራሱ ሰባኪ ነው።ዓለም ምንም ዓይነት ኃይል ከእንቅስቃሴዋ የማይገታት መስላ ትታይ ነበር።የአሜሪካ፣የአውሮፓ እና የሩቅ ምስራቅ የሽርክና ገበያዎች (''ስቶክ ኤክስቼንጅ'') ለአንድ ቀን የሚገታቸው ያለ አይመስላቸውም ነበር።የምድራችን ግዙፍ የመዝናኛ ቦታዎች ከአስረሽ ምችው ለአፍታም የሚያቆማቸው ነገር ይመጣል ብለው አላሰቡም።በሺዎች የሚቆጠሩ አይሮፕላኖች በሰማይ ላይ ከመብረር የሚገታ እና ዝናብ እንደመታት ዶሮ መሬት ይዘው የሚቆዩ አልመሰላቸውም ነበር።ሁሉም ግን በአንድ ምሽት ቆመ።ደግሞ ሁሉም የቆሙት በግዙፍ በሚያስፈራ እና አካላዊ ቁመናው በሚያስደነገጥ አካል አይደለም።በዓይን በማይታይ እጅግ ረቂቅ በሆነ ፈጣሪው ብቻ እንዴት እንደተፈጠረው በሚያውቀው ረቂቅ ኮሮና በተባለ ቫይረስ ቆመ።ኃያላን የተባሉት ከምስኪኖቹ ጋር እኩል አቆማቸው።በገንዘብ ኃይላቸው የተኩራሩት ገንዘባቸው ከረቂቁ ቫይረስ የማያስጥል ሆነ።ካለፈ ታሪክ ይልቅ አሁን እየሆነ ያለው በራሱ ከወንጌሉ በላይ አስተማሪ ነው።

''ማንም ሊሰራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች'' ዮሐንስ ወንጌል 9፣4

ጊዜው አስተማሪነቱ የመስርያ ጊዜ ነገ ሳይሆን አሁን መሆኑን ነው።ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ዮሐንስ ወንጌል 9፣4 ላይ ''ማንም ሊሰራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች'' በማለት ሐዋርያትን አስጠንቅቆ ነበር።ከእርሱ ጋር እያሉ ቀላል የመሰላቸው ጉዳይ ሁሉ እርሱ በአይሁድ እጅ ከተያዘባት ሐሙስ ምሽት እስከ ትንሣኤው ድረስ ያሉ ምሽቶች ክርስቶስን አውቀዋለሁ፣ከእርሱ ጋር ነበርኩ ማለት በአይሁድ ዘንድ ሞት የምያስከትል ነበር። ጊዜው ከወንጌሉ በላይ አስተማሪነቱ የሚጎላው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን በእዚህ ዓመት እንዴት ያቺ የማይቻልባት ምሽት እንደመጣች ስንመለከት ነው።ቅዳሴ በፈለጉ ሰዓት ሄዶ ማስቀደስ፣ማኅሌት መቆሙ፣መቁረቡ እና ተሰብስቦ በአንድነት ወንጌል መማሩ ሁሉ  የማይቻልባት ሌሊት ላይ ነን።

አሁንም ይህንን ዕድል እንዳናጣው እንፍጠን!

አሁንም ባለው መንገድ ለመጠቀም መዘግየት ሌላ ሊሰሩ የማይችሉባት ሌሊት እንዳትመጣ መንገድ ይከፍታል።ሕዝበ ክርስቲያኑ በአሁኑ ጊዜ በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ ወደ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ሄዶ የመማር፣የማስቀደስ እና በአጠቃላይ ከቤተክርስቲያን በአካል ቀርቦ ማግኘት ያለበትን መንፈሳዊ አገልግሎት ሁሉ ለማግኘት የማይችልበት ጊዜ ላይ ነን።ለእዚህ ደግሞ በአማራጭነት የተወሰደው የዘመናዊ መገናኛ መጠቀም ነው።ከዘመናዊው መገናኛ ውስጥ ደግሞ ቴሌቭዥን ለብዙ ሕዝብ የመድረስ ዕድል አለው።አሁን ባለንበት ዘመን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን  ከሐምሳ ሚልዮን በላይ ምዕመን ይዛ ከሱዳን እስከ አሜሪካ እና አውስትራሊያ ድረስ በመላው ዓለም ተሰራጭታ ከ24 ሰዓታት ያነሰ ጊዜ የሚያስተላልፍ ቴሌቭዥን ሊኖራት አይችልም።

ስለሆነም አንዳንዶች ዛሬ ነገ እያሉ፣የቀሩት መረጃው ስለሌላቸው ይህንን የማኅበረ ቅዱሳንን ቴሌቪዥን የቀጥታ ሥርጭትና የስቱዲዮ ግንባታ በሚገባ ደረጃ አልደገፉ ከሆነ ይፍጠኑ።መስበክ ባይችሉ የሚሰብኩት እንዲሰብኩ በማድረግም ፅድቅ አለ።እናቶቻችን ቤተ መቅደስ ገብተው ባይቀድሱ፣የአብነት ተማሪዎች የሚመገቡትን በማዘጋጀት፣ካህናቱን ፈትለው በማልበስ ፅድቅን አትርፈዋል።እርስዎ ለጥቂት ደቂቅዎች ጊዜ ሰጥተው አነሰ በዛ ሳይሉ አሁኑኑ ድጋፍዎን ያድርጉ።ይህ ቁልፍ ጉዳይ ነው።ነገ ሊሰሩባት የማይችሉባት ሌሊት ሳትመጣ አሁን ግዴታዎን ይወጡ።ላልሰሙ ይንገሩ። 

እንዴት? በየት በኩል  ይደግፉ?

ከእዚህ በታች ካሉት አራት  አማራጮች ለመደገፍ በሚመቸዎት በአንዱ ይደግፉ 

1) በጎፈንድሚ

ወይንም  

2) በቀጥታ ለእዚሁ አገልግሎት በሚውሉት በእነኝህ የባንክ ሂሳቦች በማስገባት  

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፡1000010822657
ወጋገን ባንክ ፡ 395950/CO1/27
አቢሲኒያ ባንክ ፡ 4753388
ዳሸን ባንክ ፡ 0088872166011
አዋሽ ባንክ : 01304800017700

ወይንም 

3) ሰኔ 21 በቤትዎ በተዘጋጀ ሐዊረ ሕይወት ጉባኤ ለመሳተፍ ጥቂት በመስጠት ለረጅሙ ስጦታ የሚዘጋጁበት ዕድልም ተመቻችቷል።
ይህንን ሊንክ ከፍተው ይጠቀሙ 

ወይንም 

4) በፔይ ፓል ለመክፈል ይህንን ሊንክ ይክፈቱ 

የፔይ ፓሉ ሊንክ ከማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማዕከል ሊንክ (https://eu.eotcmk.org/site/) ላይ የቴሌቭዥን እና ራድዮ አገልግሎት ከሚለው ሊንክ ''ዶኔት'' የሚለውን ሲጫኑ ያገኙታል።

+++++++++++++++++++++++++++++
የድርሻችንን እንወጣ ቪድዮ ማስታወቂያ ሊንክ 
ምንጭ = ከማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቭዥን ዩቱብ የተወሰደ 
Wednesday, June 10, 2020

ብጹዕ አቡነ ኤልያስ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውን እና ወገኖቻቸውን እንዲረዱ ልዩ መልዕክት አስተላለፉ! ድሆችን አትርሱ! (ቪድዮ)


ብጹዕ አቡነ ኤልያስ፣የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና በአውሮፓ አህጉረ ስብከት የሰሜን አውሮፓ እና ስካንድንቭያን ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የወቅቱን ወረርሽኝ በተመለከተ ለምዕመናን ያስተላለፉት ልዩ መልዕክት  - ድሆችን አስቡ! 
ከቪድዮው ስር ብጹዕነታቸው  በጎጃም ስለተፍጠረው የሃይማኖት ቅሰጣ በተለከተ ያወጡትን መግለጫ ይመልከቱ  
ጉዳያችን GUDAYACHN 

Monday, June 8, 2020

በኢትዮጵያውያን የጋራ መድረክ በኖርዌይ አስተባባሪነት የተጠራው ስብሰባ በስቶኮልም የኢትዮጵያ ኤምባሲ የፖለቲካ፣ኢኮኖሚ እና ዲያስፖራ ጉዳዮች ኃላፊ እና ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ባለሙያዎች በተገኙበት በኦስሎ ተካሄደ።በእዚህ ጽሁፍ ውስጥ የሚከተሉትን ያገኛሉ 
>> ''የዓባይ ግድብ የሚመጣው ትውልድን ዕጣ የሚወስን የአሁኑ ትውልድ የሚከፍለው ዕዳ ነው'' ዶ/ር ሙሉጌታ በረደድ ሃይድሮሎጅስት ኢንጅነር 
>> ''ከኢትዮጵያ 12 ዋና ዋና ወንዞች ውስጥ 10ሩ ከኢትዮጵያ ውጪ የሚሄዱ ናቸው።ከኢትዮጵያ ስፋት 1ሚልዮን 1መቶ ሺህ ስኩኤር ኪሎሜትር ስፋት ውስጥ  ውኃማ አካሏ 0.7% ነው።''  ዶ/ር አሸናፊ ሰይፉ 
>> ''በኮቪድ 19 የተያዙ ሰዎች ላይ በቅርብ እየታየ ያለው የማሽተት እና የመቅመስ ስሜታቸው የቀነሰበት ሁኔታ ታይቷል'' ዶ/ር አንተነህ መኩሪያ ።
>> ''በአባይ ተፋሰስ ዙርያ የተፈረመው ውል ስድስት አገሮች ፈርመዋል፣አራቱ በፓርላማ አፅድቀዋል፣በፓርላማ ያፀደቁት ስድስት ሲሆኑ አስገዳጅ ሕግ ሆኖ ይወጣል'' አቶ ተስፋዬ ይታይህ በስቶኮልም የኢትዮጵያ ኤምባሲ የፖለቲካ፣ኤኮኖሚ እና ዲያስፖራ ጉዳዮች ካውንስል ሚኒስትር።

+++++++++++++++++++++++++++++ 

የስብሰባው መግቢያ 

መሰረቱን በኖርዌይ ያደረገው የኢትዮጵያውያን የጋራ መድረክ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ግንቦት 30/2012 ዓም (ጁን 7/2020 ዓም) በ''ጎቱሚቲንግ'' የመገናኛ መረብ አማካይነት ስብሰባ አካሂዶ ነበር።የስብሰባው ሁለት አጀንዳዎች ማለትም በዓባይ ግድብ ጅኦ-ፖለቲካ ጉዳይ እና የዲያስፖራው ሚና እና  የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በጤና፣በማኅበራዊ እና በምጣኔ ሃብት ባመጣው በሚያመጣው ችግር ዙርያ ላይ ያተኮሩ ነበሩ።

በስብሰባው መጀመርያ ላይ የኢትዮጵያውያን የጋር መድረክ፣ በኖርዌይ መንግስት በሕጋዊ መልክ የተመዘገበ የየትኛውንም የፖለቲካ ድርጅት ሃሳብ የማያንፀባርቅ ነገር ግን በሲቪክ ድርጅትነት እየሰራ እንደሚገኝ የተገለጠ ሲሆን፣ ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ ብቻ የጋራ መድረኩ ባዘጋጃቸው የውይይት መርሃግብሮች ዙርያ በአስተባባሪዎቹ በአቶ ጌታቸው እና አቶ ወርቁ ቀርበዋል።በእዚህም መሰረት መድረኩ ላለፉት አራት ዓመታት ብቻ በብሔር ፖለቲካ እና በኢትዮጵያዊነት ዙርያ፣ በሶሻል ካፒታል በተመለከተ፣በኢትዮጵያ የተነሳው ሕዝባዊ አመፅ ዙርያ፣በለውጡ አንደምታ ዙርያ፣የምርጫ ሴናርዮ ዙርያ፣በኖበል ሽልማት ስነስርዓት ሂደት ላይ በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሚና፣በስብስባ አዳራሾች ያካሄደ ሲሆን ከእዚህ በተጨማሪ የጠረንጴዛ ዙርያ ውይይት በተለያየ የፖለቲካ አመለካከቶች ዙርያ  ማድረጉ ተብራርቷል። የጋራ መድረኩ እነኝህን ውይቶች ሲያዘጋጅ ሁሉንም በነፃ የተከናወኑ እና አዳራሾችንም ባብዛኛው በነፃ እያፈላለገ መስራቱ እና ላለፉት አራት ዓመታት ለተወሰኑ የአዳራሽ ክራይ ብቻ የነበሩበት ወጪዎች ከስምንት መቶ ክሮነር ያልበለጠ መሆኑም ተወስቷል።

''የዓባይ ግድብ የሚመጣው ትውልድን ዕጣ የሚወስን የአሁኑ ትውልድ የሚከፍለው ዕዳ ነው'' ዶ/ር ሙሉጌታ በረደድ ሃይድሮሎጅስት ኢንጅነር 

የዓባይን ግድብ በተመለከተ መግቢያ መንደርደርያውን ዶ/ር ሙሉጌታ በረደድ ያቀረቡ ሲሆን።ዶ/ር ሙሉጌታ ማስተርሳቸውን በዓባይ ጉዳይ ላይ ያጠኑ፣ዶክትረታቸውን ደግሞ በሃይድሮሎጂ ኢንጂነሪንግ አጠናቀው በአሁኑ ጊዜ በኖርዌይ በሚገኘው መልቲ ኮንሰልት ድርጅት ውስጥ በከፍተኛ ኃላፊነት እየሰሩ እንደሚገኙ በስብሰባው መግቢያ ላይ ተገልጧል።እርሳቸውም በመግቢያ ማብራሪያቸው ላይ በዓባይ ዙርያ ቀደም ብለው የተደረጉ ስምምነቶች ትውልድ የሚገድቡ ስምምነቶች ነበሩ ካሉ በኃላ አሁን ግድቡ ያለበት ደረጃ አበረታች መሆኑን ገልጠው ግድቡ የሚመጣው ትውልድን ዕጣ የሚወስን የአሁኑ ትውልድ የሚከፍለው ዕዳ መሆኑ መታወቅ አለበት ብለዋል። 

ዶ/ር ሙሉጌታ ግብፆችን አስመልክተው ሲያብራሩ ባብዛኛው ራሳቸውን እንደተጠቂ አድርገው ማቅረብ ለምደዋል ካሉ በኃላ ጊዜው ቀድሞ ማጮህ ቀድሞ ያሰማል በሚል በዲያስፖራቸው 'ዊንግ' አማካይነት እየተጠቀሙ እንደሚገኙ አብራርተዋል።በመጨረሻም በመግቢያ ነጥቦቻቸው ላይ ዶ/ር ሙሉጌታ ኢትዮጵያውያን በዓባይ ግድብ ጉዳይ ብዙ ማለት አለብን፣እውነትኛውን ነገር ለቀሪው ዓለም ማሳወቅ ተገቢ መሆኑን አበክረው ተናግረዋል።

''ከኢትዮጵያ 12 ዋና ዋና ወንዞች ውስጥ 10ሩ ከኢትዮጵያ ውጪ የሚሄዱ ናቸው።ከኢትዮጵያ ስፋት 1ሚልዮን 1መቶ ሺህ ስኩኤር ኪሎሜትር ስፋት ውስጥ  ውኃማ አካሏ 0.7% ነው።'' ዶ/ር አሸናፊ ሰይፉ 

በመቀጠል በውይይት መድረኩ ላይ በሰፊው  ያቀረቡት ዶ/ር አሸናፊ ሰይፉ ሲሆኑ እርሳቸውም በሃይድሮሎጅስትና ኢንቫይሮመንት የፔኤች ዲ ዲግሪ ያላቸው ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ከውሃ ጋር በተያያዙ ፕሮጀክቶች ላይ እና በተለያዩ ዩንቨርስቲዎች እያስተማሩ ይገኛሉ።ዶ/ር አሸናፊ የጀመሩት ኢትዮጵያ ከስፋቷ 1ሚልዮን 1መቶሺህ ስኩአር ኪሎ ሜትር ውስጥ  0.7% የሚሆነው ብቻ ውሃማ ሲሆን በእዚህ ብቻ ነው የውሃ ማማ የምንባለው።በእዚህ አንፃር ኖርዌይን ስንመለከት 5% መሆኑን ገልጠዋል።የኢትዮጵያ ቶፖግራፊ ከዝቅተኛ ቦታ እስከ ከፍተኛ ቦታ ድረስ በመሆኑ ለውሃ አጠቃቀም አመቺ መሆኑን ገልጠው ብዙ ውሃዋ በምድረ ገፅ ላይ ከዝናብ መጥቶ የሚያልፍ ስለሆነ መገደብ የግድ አስፈላጊ ነው ብለዋል።በመቀጠልም ኢትዮጵያ ካሏት 12 ዋና ዋና ወንዞች ውስጥ 10ሩ ከኢትዮጵያ መንጭተው ወደ ሌላ አገር የሚሄዱ መሆናቸውን ማወቅ አለብን ብለዋል።ዶ/ር አሸናፊ የኢትዮጵያን ሁኔታ ሲያብራሩ በአሁኑ ጊዜ 11% ብቻ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻ ዘመናዊ የውሃ ማውረጃ ያለው ሽንትቤት ተጠቃሚ ነው።የኢትዮጵያ የሃይድሮ ፓወር አስተዋፅኦ ከአጠቃላይ የኃይል ጥያቄ ውስጥ 11% ብቻ ነው የቀረው ኃይል አሁንም የሚገኘው ከደን ወዘተ የሚገኝ መሆኑን ገልጠዋል።

ዶ/ር አሸናፊ የኢትዮጵያ ወንዞች ውስጥ ሶስቱ ማለትም አባይ፣ተከዜና ባሮ ብቻ 70% የወንዝ ውሃ ይሸፍናሉ ያሉ ሲሆን።የኢትዮጵያ 1/3ኛ የቆዳ ሽፋን የሚሸፈነው ደግሞ በእነኝህ ወንዞች ተፋሰስ ስር  መሆኑን አብራርተዋል።በመቀጠል የዓባይ ግድብን በተመለከተ ማብራርያ ሲሰጡ ግድቡ 175 ሜትር ከፍታ፣1874 ስኩኤር ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን በ13 ተርባይነር 5150 ሜጋዋት በሰከንድ ማመንጨት ይችላል ብለዋል።በመቀጠል ዶ/ር አሸናፊ የገቡት ከግድቡ ጋር በተያያዘ የነበሩ ውሎች ላይ ነው። 

በዓባይ ዙርያ ከተደረጉት ውሎች ውስጥ የ1891 ዓም በእንግሊዝ እና ጣልያን መሃል ተከዜ ወንዝ ላይ ያደረጉት ስምምነት ጣልያን ምንም ልማት እንዳትሰራ የሚያግድ ነበር።በ1906 ዓም በእንግሊዝ እና በቤልጅየም መሃል የተደረገው ደግሞ በኮንጎ ወንዝ ላይ ምንም ሥራ እንዳይሰራ የሚያግድ ነበር።ይህ ከእኛ የራቀ ቢሆንም የኮሎኒያል ውሎች የሚያሳይ ነው።ሌላው በ1959 ዓም በሱዳንና ግብፅ መሃል የተደረገው ኢትዮጵያን ያገለለ ውል ነው።ግብፅ አሁን ድረስ የምትጠቅሰው ይህንን ውል መሆኑን ያወሱትዶ/ር አሸናፊ፣በወቅቱ በንጉሡ ዘመን ኢትዮጵያ ይህንን ውል በኦፊሴል ተቃውማለች ብለዋል።ሌላው የኢንተቤ ውል የሚባለው በ2010 ዓም የተደረገው ሲሆን ለኢትዮጵያ የሚጠቅም ውል የሚባለው ዋናው ውል ግን በመጋቢት 2015 ዓም ላይ የኢትዮጵያ፣ግብፅ እና ሱዳን ግድቡን በጋራ እናለማለን የሚለው ውል ነው። ይህ ውል ለኢትዮጵያ ትልቅ በር የከፈተ ነው። በቅርቡ ግብፆች ለማምለጥ የሚሞክሩት ከእዚህ ከ2015ቱ ውል ነው በማለት አብራርተዋል።

ወደፊት መደረግ ባለበት ጉዳይ ላይ አስመልክተው ዶ/ር አሸናፊ ሲያብራሩ ኢትዮጵያ በዋናነት ግድቡን መጨረስ እና የመደራደር አቅሟን ማሳደግ ወሳኙ ጉዳይ ነው ብለዋል። በመቀጠልም እስካሁን ያጣነው የራሳችንን ሀብት በጋራ የመጠቀም መብት ነው ያጣነው።ግድቡ ኢትዮጵያን ከእርሻ መር ኢኮኖሚ ወደ ማኑፋክቸሪንግ ኢኮኖሚ የሚያሻግር እና የውጭ ምንዛሪ ለማፍራት ወሳኝ ነው ብለዋል።ግብፅ ከፍተኛ የከርሰ ምድር ውሃ ያላት ሀገር መሆኗን ያብራሩት ዶ/ር አሸናፊ እኛ የመሬት ላይ ውሃችንን  መጠበቅ የግድ መሆኑን ገልጠዋል።በመጨረሻም ዶ/ር አሸናፊ የዓባይ ግድብ ዙርያ በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ምሑራን መንግስትን የሚያማክሩበት እና ስለ ግድቡ እውነተኛውን ገፅታ ለዓለም የሚያሳዩበት  የሙያተኞች ስብስብ መኖሩን ገልጠው ድረ ገፁም http://www.eipsa1.com/cms/ መሆኑን ለተሰብሳቢዎቹ አስረድተዋል።ዶ/ር አሸናፊም የእዚሁ የባለሙያዎች አካል መሆናቸውን ገልጠው የዕለቱን ገለጣ አጠናቀዋል።

በመቀጠል በተሰጡት አስተያየቶች በኖርዌይ ከፍተኛ የውሃ ባለሙያ ኢትዮጵያውያን መኖራቸው ተጠቅሶ እነኝህ ሃይድሮሎጅስቶች በኖርዌይ ብቻ ሳይሆን በስካንድንቭያን አገሮች ደረጃም መደራጀት እና የድፕሎማሲውን ሥራ ቢሰሩ ብዙ ውጤት ማግኘት እንደሚቻል ተገልጧል።

''በኮቪድ 19 የተያዙ ሰዎች ላይ በቅርብ እየታየ ያለው የማሽተት እና የመቅመስ ስሜታቸው የቀነሰበት ሁኔታ ነው ።'' ዶ/ር አንተነህ መኩሪያ 

ከዓባይ ጉዳይ በመቀጠል በኢትዮጵያውያን የጋራ መድረክ ስብሰባ ላይ የቀረበው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በጤና፣በማኅበራዊ እና በኢኮኖሚ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ዙርያ ነበር።በዚህ ዙርያ ያቀረቡት ዶ/ር አንተነህ መኩርያ ነበሩ። ዶ/ር አንተነህ መኩርያ አገራቸውን በጀት አብራሪነት በኢትዮጵያ አየር ኃይል ውስጥ ያገለገሉ፣ ከዝነኛው የሕክምና ዩንቨርስቲ ፓዝናን የሕክምና ዩንቨርስቲ የሜዲካል ዶክትሬታቸውን ያገኙ እና በአሁኑ ጊዜ በኖርዌይ የተለያዩ ሆስፒታሎች በሕክምና ሙያ እያገለገሉ የሚገኙ ከፍተኛ ባለሙያ ናቸው። 

ዶ/ር አንተነህ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በተመለከተ የህመሙ ስሜት ከ2 እስከ 7 ቀኖች እንደሚታይ ገልጠው በቅርቡ የታዩ ውጤቶች ደግሞ በአንዳንዶች ላይ የማሽተት እና የመቅመስ ስሜታቸውን፣ የመቀነስ አልፎ አልፎም የማቅለሽለሽ ስሜት የታየባቸው መኖራቸውን ጠቁመዋል።በመቀጠልም እስከ ስብሰባው የተደረገበት ቀን ድረስ በኖርዌይ 8542 ሰዎች፣ በስዊድን ደግሞ 44 ሺህ ሰዎች መያዛቸውን ገልጠው፣በሁለቱ አገሮች መሃል ያለው ልዩነት የመጣው የፖሊሲ ልዩነት መሆኑን እና ኖርዌይ ቀድማ ጥንቃቄ ስታደርግ ስዊድን ደግሞ መዘግየቷ ያስከተለው መሆኑን አብራርተዋል።በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ስንመለከት በ10% በፍጥነት የማደግ ሁኔታ እየታየበት መሆኑን የገለጡት ዶ/ር አንተነህ በኖርዌይ ለምሳሌ የማኅበራዊ ትስስሩ በጠነከረበት ማኅበረሰብ ውስጥ እስከ 7 ቤተሰብ የተያዘበት ታሪክ መኖሩን ገልጠዋል።

ዶ/ር አንተነህ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ያለውን ሁኔታ ሲያብራሩም በኢትዮጵያ በሽታው ለፍቶ አዳሪውን፣ቱሪዝምን እና የአየር አገልግሎቱን በሌላው ዓለም እንደታየው ሁሉ መጉዳቱን ገልጠው፣በዋናነት መመርያዎችን ማክበር አስፈላጊ መሆኑን አስምረውበታል።በመቀጠልም ስነልቦናዊ ተፅኖው ለሌሎች በሽታዎች ስለሚዳርግ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። በሌላ በኩል የኮሮና ወረርሽኝ ከጤና ባሻገር በኢኮኖሚ ላይ እያደረሰ ያለው ጉዳት የምናየው ሲሆን ሌላው አስቸጋሪ የሚያደርገው ከኮሮና በኃላ የሚመጣው አስቸጋሪ ጊዜ መሆኑን አብራርተዋል።ይሄውም በዓለም ዓቀፍ ጥናቶች የሚያሳዩት ኮሮና ቢጠፋም ከ12 እስከ 18 ወሮች የሚፈጅ ትግል ዓለምን ከኮሮና በፊት ወደነበረችበት ቦታ ለመመለስ እንደሚጠይቅ ገልጠዋል።

በመፍትሄነት ዶ/ር አንተነህ ያስቀመጧቸው ነጥቦች ውስጥ የቤተሰብ በግልጥ መወያየት፣ሕፃናትን ማስተማር፣ቤተሰባዊ ትስስር በመጠበቅ ፈጠራን ማዳበር የሚጠቀሱ ሲሆኑ በተጨማሪ በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ርቀት ከመጠበቅ ጋራ በኢትየጵያ ኤምባሲ የተመሰረተው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የተመለከተውን ግብረ ኃይል ማገዝ፣አስፈላጊ የህክምና ቁሳቁሶችን አሰባስቦ ወደ አገር ቤት መላክ፣ማኅበራዊ ግዴታን መወጣት፣አዳዲስ ሃሳቦችን ማመንጨት እና በቅርቡ የተመሰረተው የኢትዮ ኖርዲክ ኢትዮጵያውያን የሕክምና ባለሙያዎች ማኅበር ማጠናከር እና የምታውቁትን ኢትዮጵያዊ የህክምና ባለሙያ ወደ እዚህ ማኅበር ማምጣት ጠቃሚ ነው ብለዋል።ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ የሕዝቡን ስነ ልቦና ለመጠበቅ የማማከር ሥራ አስፈላጊ መሆኑን በማስመር ዶ/ር አንተነህ የዕለቱን ማብራርያ አጠናቀዋል።

በመቀጠል ከተሳታፊዎች  ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ የነጭ ሽንኩርት፣ዝንጅብል ጥቅም፣በኖርዌይ የውጭ ዜጎች በብዛት ተጠቅተዋል ስለተባለው እና በሽታው በሰገራ ይተላለፋል ወይ? የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተው ዶ/ር አንተነህ ነጭ ሽንኩርት እና ዝንጅብል የመሳሰሉትን በተመለከተ ያድናሉ የሚል ጥናት የለም።ሆኖም ከመያዝ በፊት ግን እንደማንኛውም ሚንራል እና ንጥረ ነገር እንዳለው ምግብ የመከላከል አቅምን በያዙት ንጥረ ነገር ሊያሳድጉ ይችላሉ በአዳኝነታቸው ግን የተረጋገጠ ጥናት የለም ብለዋል።በመቀጠልም በአንዳንድ የአፍሪካ አገሮች አልኮል እንደሚያድን ይናገራሉ ይህ ግን ስህተት ነው ብለዋል ዶ/ር አንተነህ።በሌላ በኩል ሰገራ በተመለከተ በመጀመርያ ቫይረሱ ውጪ ብዙ የመቆየት ዕድል ስለሌለው ከእዚህ አንፃር ማየቱ ተገቢ ሲሆን በእዚህ ዙርያም በቂ ጥናት አለመደረጉን ገልጠዋል። በመጨረሻም ዶ/ር አንተነህ ያሰመሩበት ጉዳይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ላይ በተደረገ ጥናት በዋናነት የቫይታሚን ዲ  እጥረት ታይቷል። ስለሆነም ቫይታሚን ዲ አንዱ እና አስፈላጊ መሆኑን ማወቅ ይገባናል ብለዋል።

''በአባይ ተፋሰስ ዙርያ የተፈረመው ውል ስድስት አገሮች ፈርመዋል፣አራቱ በፓርላማ አፅድቀዋል፣በፓርላማ ያፀደቁት ስድስት ሲሆኑ አስገዳጅ ሕግ ሆኖ ይወጣል'' አቶ ተስፋዬ ይታይህ በስቶኮልም የኢትዮጵያ ኤምባሲ የፖለቲካ፣ኤኮኖሚ እና ዲያስፖራ ጉዳዮች ካውንስል ሚኒስትር 

በመጨረሻ በቀረቡት ጉዳዮች ዙርያ እና በኢትየጵያ መንግስት ፖሊሲ በኩል ያሉት ሁኔታዎች ላይ ማብራርያ የሰጡት አቶ ተስፋዬ ይታይህ በስቶኮልም የኢትዮጵያ ኤምባሲ የፖለቲካ፣ኤኮኖሚ እና ዲያስፖራ ጉዳዮች ካውንስል ሚኒስትር ነበሩ።አቶ ተስፋዬ በቅድሚያ የኢትዮጵያውያን የጋራ መድረክ በኖርዌይ ይህንን ዝግጅት በማዘጋጀቱ አመስግነው በውይይቱ ላይ የተሳተፉ እና ጥናታዊ ዝግጅታቸውን ያቀረቡትን ምሁራንን  አመስግነዋል።በመቀጠልም የዓባይ ግድብ በተመለከተ እንግሊዝ ሱዳን እና ግብፅ በቅኝ ግዛት ዘመን ውል እንዲገቡ ያደረገችው በዋናነት በማንቸስተር የነበረው የጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎቹ በዓባይ ላይ ከሚመረተው ጥጥ ተጠቃሚነታቸው እንዳይጎድ መሆኑን ገልጠዋል።ከእዚህ በመቀጠል የአባይ ተፋሰስ አገሮች ውስጥ ስድስቱ የፈረሙት ውል በአራቱ አገሮች ፓርላማዎች  የፀደቀ ሲሆን በቀሩት ሁለቱ አገሮች ፓርላማ ሲፀድቅ አስገዳጅ ሕግ ሆኖ እንደሚወጣ ገልጠዋል። ቀደም ብሎ በዶ/ር አሸናፊ የቀረበው የመጋቢት 2015 ዓም ውል አስር አንቀፆች ያሉት ሲሆን ውሉ በዋናነት የተፋሰሱ አገሮች የጋራ ተጠቃምነትን የሚያጎላ መሆኑን አቶ ተስፋዬ አብራርተዋል።

የግብፅ መንግስት ባለፈው የተባበሩት መንግሥታት ስብሰባ ላይ አልሲሲ (የግብፅ ፕሬዝዳንት) የአሜሪካውን ፕሬዝዳንት ትራምፕን አደራድረን ማለታቸውን ያስታወሱት አቶ ተስፋዬ።ድርድሩ በአግባቡ ባለመሄዱ  ኢትዮጵያ እንዳልተስማማችበት ያያችሁት ጉዳይ ነው ያሉት አቶ ተስፋዬ በቅርቡ ደግሞ ግብፅ ወደድርድር እንመጣለን ማለታቸውን ሰምተናል ብለዋል።ሱዳንን አስመልክቶ አቶ ተስፋዬ ሲያብራሩ፣ ሱዳን በቅርቡ ወደ ፀጥታው ምክር ቤት የላከችው ደብዳቤ ላይ የኢትዮጵያን የመልማት መብት ሳይነካ የግድቡ ደህንነት ጉዳይ የተመለከተ ሃሳብ የያዘ ነው።ኢትዮጵያ ግን በሐምሌ ወር የግድቡን የተወሰነ ክፍል ትሞላለች ቀሪውን  ደግሞ በሚቀጥለው ዓመት ይሞላል ያሉት አቶ ተስፋዬ ግብፅ ጉዳዩን ወደ ውስብስብ ዲፕሎማሲ ለመውሰድ ትሞክራለች፣ዘመቻው ደግሞ በራሳቸው ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ሁሉ የታገዘ ነው ብለዋል።

አቶ ተስፋዬ ማብራሪያቸውን በመቀጠል ኢትዮጵያውያንም የፐብሊክ ዲፕሎማሲ መስራት እና በውጭ ያለ ኢትዮጵያዊም የእየሀገሩ የፓርላማ ሰዎች ጨምሮ እውነታውን ማስረዳት አስፈላጊ መሆኑን አበክረው ተናግረዋል።እውነታው ደግሞ ኢትዮጵያ ከ70% በላይ ሕዝብ አሁንም መብራት የሌለው፣የውሃ ማማ እንባል እንጂ አብዛኛው ሕዝብ በቂ ውሃ የሌለው ነው።ግብፅን ብንመለከት ግን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የሕዝቧን የውሃ እና የኤሌክትሪክ ፍላጎት አሟልታለች።ስለሆነም ይህንን እውነታ ለሌላው ዓለም መንገር ያስፈልጋል ያሉት አቶ ተስፋዬ በቅርቡ በስዊድን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ምሑራን የስዊድንን ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አግኝተው በግድቡ ዙርያ እና በኮቪድ 19 ዙርያ መወያየታቸው ጥሩ አብነት መሆኑን ጠቅሰዋል።በኢትየጵያ መንግስት በሁሉም መስክ ጥረቱ እንደቀጠለ እና ቀደም ብሎ በውጪ ጉዳይ ሚኒስትር የተመሰረተው የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ውስጥ የኢትዮጵያ የተለያዩ ቤተእምነቶች ያሉበት ቡድን አሁንም አለ ብለዋል።

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በተመለከተ አቶ ተስፋዬ በኢትዮጵያ የተደረጉትን ቅድመ ጥንቃቄዎች ካወሱ በኃላ ኤምባሲያቸው የኮቪድ 19 ግብረ ኃይል በስካንድንቭያ አገሮች ባሉ ኢትዮጵያውያን እያስተባበረ ሲሆን በእዚህም መሰረት እስካሁን 675 ሺህ ክሮነር ከስዊድን እና ኖርዌይ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተሰብስቧል ብለዋል።በሕክምና ቁሳቁስ በኩል ደግሞ 270 ሺህ ብር የሚያወጣ ቁሳቁስ መገኘቱን አቶ ተስፋዬ ገልጠዋል።በመጨረሻም አቶ ተስፋዬ በድጋሚ መድረኩን እና የተሳተፉ ምሁራንን አመስግነው ወደአገር ቤት የሚላኩ የህክምና ቁሳቁስ ላይ እና ግድቡን በተመለከተ የተቀናጀ የዲፕሎማሲ ሥራ ከኢትዮጵያውያን እንደሚጠበቅ አፅኖት ሰጥተው  ገለፃቸውን አጠናቀዋል። 

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተመለከቱ አስተያየት ከተሰጠ በኃላ የኢትዮጵያውያን የጋራ መድረክ በኖርዌይ ወደፊት የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኖርዌይ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር በጋራ የሚመካከሩበት መድረክ እንደሚያመቻች ተገልጦ በዕለቱ ለተሳተፉት ተሰብሳቢዎች፣ጥናታዊ መረጃዎችን ላቀረቡ ምሁራን እና ለኢትዮጵያ ኤምባሲ ኃላፊ ምስጋና ከኢትዮያውያን የጋራ መድረክ በኖርዌይ ከቀረበ በኃላ የዕለቱ ስብሰባው ተፈፅሟል።

 
ጉዳያችን ሚድያ፣ኮሚኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት 
Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant
Gudayachn Multimedia, Kommunikasjon og Konsultent 

Tuesday, June 2, 2020

ኢትዮጵያ ተጠባባቂ ጦር ማሰልጠን አለባት።በሱዳን በኩል በኢትዮጵያ ላይ እጃቸውን ሊሰነዝሩ የሚያስቡ የአረብ አገራት ለኢትዮጵያ ስጋት ሆነዋል። (ጉዳያችን ልዩ ዘገባ)


>> ''ግድቡ ለሱዳን አደጋ ሊሆን ይችላል'' ሱዳን ለተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክርቤት የላከችው  መልዕክት፣
>> ሱዳን ዛሬ አዲስ መከላከያ ሚኒስትር ሾማለች፣
>> ''ከቱርክ፣ኢራን እና እስራኤል በኃላ ኢትዮጵያ የአረቡን ዓለም ሰብራ ልትገባ ነው?'' ሚድል ኢስት ሞንተር ዛሬ ማክሰኞ የፃፈው

ሰሞነኛው የአሜሪካ ስፕሪንግ 

የዓለም ፖለቲካ በፍጥነት እየተቀየረ ነው።የኮሮና ወረርሽኙ ተፅዕኖ በሀገሮች ግንኙነት፣በሕዝብ ማኅበራዊ ኑሮ እና የምጣኔ ሃብቱ ሚዛን ሳያሳክረው የሚያልፍ አይመስልም።የሰሞኑ የአሜሪካ የውስጥ ቀውስ ከኮሮና ወረርሽኝ በላይ ፖለቲካዊ ቀውስ ውስጥ ገብታለች።ፕሬዝዳንት ትራምፕ ራሳቸው የሴራ ፖለቲካ ውስጥ እንደገቡ የሚናገሩ የአሜሪካንን ፖለቲካ የሚያውቁ ሰዎች ናቸው።ዛሬ ግንቦት 25/2012 ዓም በአልጀዚራ ቀርቦ የወቅቱን የአሜሪካ ፖለቲካ ላይ ሃሳብ የሰጠ ምሑር ያለውም ይሄንኑ ነው።ትራምፕ ሰሞኑን የተነሳውን የአፍሪካ አሜሪካውያን የመብት ትግል (ከአረብ ስፕሪንግ ስሙን ወስደው  የአሜሪካ ስፕሪንግም የሚሉት አሉ) ትራምፕ ሆን ብለው ያደረጉት እና የሚፈልጉት ነው ነበር ያለው።ለእዚህ ምክንያቱን ሲሰጥ ደግሞ በኮሮና ወረርሽኝ አያያዛቸው ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ስለገቡ፣የአፍሪካ አሜሪካውያን መነሳት ትራምፕ አካራሪ የቀኝ ኃይሎች ደህንነት እንዳይሰማቸው ስለሚያደርግ በእዚህ በመጪው ሕዳር ወር በሚደረገው ምርጫ የብዙ ነጭ አሜሪካውያንን ድጋፍ እንደሚያገኙ ያስባሉ ብሏል። 

የፕሬዝዳንቱ አካሄድም ነገር የሚያበርድ ሳይሆን ግጭት የሚያካርር ነው።የመብት ተሟጋቾቹን ''ግራ ክንፍ አክራሪ፣የአገር ውስጥ ሽብርተኞች እና አናርኪስቶች'' ያሏቸው ፕሬዝዳንቱ ዛሬ ደግሞ መፅሐፍ ቅዱስ ይዘው አንድ ቤተክርስቲያን ፊት ቆመው ታይተዋል። ይህ ድርጊታቸው በተለይ ጉዳዩን ሃይማኖታዊ ሽፋን ለመስጠት ወይንስ የትኛውን ዕምነት ለመንቀፍ እንዳሰቡ ስትመለከቱ በእውነትም አሜሪካ በግልጥ ልዩነት የሚጭር ፕሬዝዳንት ላይ እንደወደቀች መረዳት ቀላል ነው።

ግልገል የአካባቢ ኃያላን መነቃቃት 

የአሜሪካ በእዚህ ደረጃ መታመስ የሚፈጥረው ሌላ ጉዳይ የግልገል ኃያላን መንግሥታትን መነቃቃት ነው።ከባሕረሰላጤው ጦርነት በኃላ አሜሪካ የመካከለኛውን ምስራቅ ከእጇ እንዳይወጣ መንገድ የሶርያ  አደገኛ አማፅያንን ለመደገፍ የሄደችበት እርቀት እና ሂደቷ የሩስያን ጣልቃ ገብነት መጋበዙ ነው። የሩስያው ፕሬዝዳንት ፑቲን ''ሶርያ ሊብያ አይደለችም።በሊብያ የደረሰው በሶርያ አይደገምም'' በሚል ከሶርያ ማዕከላዊ መንግስት ጋር እስከመጨረሻው ቆመዋል።በመቀጠል አሜሪካ ያደረገችው የመካከለኛው ምስራቅ ግልገል ኃያላን እንዲነቃቁ ማድረግ ነው።ለእዚህም ሳውዲ አረብያ እና የተባበሩት ዓረብ ኢምረቶች የመሳሰሉ መንግሥታት ለጆሮ በሚከብድ ደረጃ ዘመናዊ የጦር መሳርያ አስታጠቀቻቸው። በተለይ ለሳውዲ አረብያ ያስታጠቀቻት ዘመናዊ የጦር አይሮፕላኖች የሳውዲ አየር ኃይል አባላት በአግባቡ ያልተለማመዷቸው እና ለትንሽ እክል ፔንታጎን እየደወሉ የሚጠይቁት መሆኑ ነው የሚነገረው። እነኝህን ግለገል የአካባቢ ኃያላንን ለማጠናከር አሜሪካ ትኩረት ከመስጠቷ የተነሳ በስምንት ዓመታት ውስጥ ሁለቱም የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ፕሬዝዳንት ኦባማ እና ትራምፕ ሳውዲ አረብያን ጎብኝተዋል። የአሜሪካ በሳውዲ የጦር ሰፈር ያላት ከመሆኑ አንፃር እና ዋና ዓላማዋ የኢራን እና የቱርክን መስፋፋት እንድትገታላት ቢሆንም፣ግልገል ኃያልነቷን በሌሎች የአፍሪካ ቀንድ አገሮች ላይ ብታሳይም እንደማስታገሻ ጉርሻ እንዳላየች ዝም አትልም አለማለት አይቻልም። 

የግብፁ ፕሬዝዳንት አልሲሲ፣የሳውዲው ንጉስ ሳልማን እና ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሳውዲ ግንቦት፣2017 ዓም እኤአ (ፎቶ የሳውዲ ዜና አገልግሎት)

''ዎል ስትሪት'' ግንቦት 20/2017 ዓም እኤአ ባወጣው ዘገባ አሜሪካ በእዚህ ወቅት ለሳውዲ አረብያ ወታደራዊ ትጥቅ ለማቅረብ በፕሬዝዳንት ትራምፕ አማካይነት የተስማማችው 110 ቢልዮን ዶላር የሚያወጣ እንደሆነ ዘግቧል።እነኝህ የትጥቅ መዥጎድጎዶች ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ያላትን ተፅኖ ለማድከም ነው ቢባልም የእነሳውዲን ልብ ግን ማሳበጡ አልቀረም።ለእዚህም ነው የመካከለኛው ምስራቅ ጥምር ጦር በሚል ከኤርትራ (ኤርትራ ብታስተባብልም) እስከ ሱማሌ ጠረፍ መስፈር የያዙት።ይህ አካሄድ ለኢትዮጵያ አስጊ ሁኔታ ነው።

 ኢትዮጵያን ለማጥቃት ሱዳን ብቸኛ የአረብ አገሮች አማራጭ 

ሱዳን ከእዚህ በፊት በጉዳያችን ላይ የዓባይ ግድብን፣የሱዳን እና የአፍሪካን ቀንድ--- በሚለው ርዕስ ስር እንደተገለጠው ሱዳን አጣብቂኝ ውስጥ ያለች አገር ነች።ትርፍ እና ኪሳራዋን ስታሰላው ዞራ ዞራ እንደፈለጉ ሊያሽከረክሯት የሚችሉት አገሮች አረቦቹ እንደሆኑ ይገባታል።ለእዚህ ዋነኛ ምክንያቱ ደግሞ በውስጧ ያሉት ፅንፈኛ ኃይሎች የፖለቲካ ስልጣን ላይ ባይታዩም አሁንም በወታደራዊ መዋቅር እና በከፍተኛ የሀብት ደረጃ ላይ አሉ።ስለሆነም የአሁኑ የሱዳን ሽግግር  መንግስት የሚያደርገው እና የጦር አበጋዞቹ የሚሰሩት ላይገናኝ ይችላል።የትዕዛዝ ሰንሰለቱም የተዘባረቀ እና አገሪቱን ማን እንደሚመራ ያማይታወቅበት ሁኔታ ወደፊት እንዳያጋጥም ወይንም ሌላ አረብ-መር መፈንቅል ሊያጋጥማት ይችላል።በቅርቡ አልባሽርን ከስልጣን ያስወገደው የሱዳን አብዮት ከተደረገ በኃላ የተላያዩ የጦር መሪዎች እና የፖለቲካ ፓርቲዎች አንዱ የኩአታር፣ሌላው የሳውዲ ተብለው በግልጥ ታውቀው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ በመሀከል ገብተው ካስታረቁት እና ለጊዜው የተሳካ የመሰለው የሽግግር ሂደት በእነኝህ አገራት ደጋፊ ኃይሎች የተወጠረ መሆኑ ነው አሁንም ድረስ የሚነገረው።

ሱዳን በያዝነው ሳምንት ውስጥ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያ እና ግብፅ አንድ ዓይነት የተናጥል እርምጃ እንዳይወስዱ የሚል ደብዳቤ ፃፈች የሚለው ዜናም የእዚህ ሁሉ ተቀጥያ ነው። ይህ ውትወታ የግብፅ እና የአረብ አገሮች ውትወታ መሆኑ ግልጥ ነው።ለአካባቢው ፀጥታ ስጋት አለብኝ ብላ ሱዳን እንድትጮህ የሚያደርጉት እነኝሁ አካላት ናቸው። ይህ በእንዲህ እያለ ሱዳን በእዚሁ ደብዳቤዋ ላይ ሌላም ዘባርቃለች።ይሄውም ከእዚህ በፊት ግድቡ  በክረምት ወራት የነበረውን የጎርፍ አደጋ ያበርድልኛል እንዳላለች፣ አሁን ግን ግድቡ በአግባቡ ካልተሞላ ለሱዳንም ''ሪስክ'' (አደጋ) አይኖረውም ማለት አይቻልም፣የሚልዮን ሱዳናውያንን ሕይወት አደጋ ይጥላል ብላለች ሲል የዘገበው አልሃራም የግብፁ ጋዜጣ በዛሬው ግንቦት 25/2012 ዓም ዘገባው ነው።ይህ ብቻ አይደለም ሱዳን የጦር አለቆቿን በምዕራብ ጎንደር በኩል ልካ ጥቃት ለመፈፀም ሞክራ የጦር አበጋዞቿን ሕይወት ከኢትዮጵያ ሰራዊት በኩል በተሰጠ የአፀፋ ምት መመለሷ እና ጉዳዩ ገና አለመብረዱ ነው የተነገረው።ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 25/2012 ዓም ደግሞ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እና የዓማራ ክልል የፀጥታ ጉዳይ ኃላፊዎች የሱዳን ኢትዮጵያን ድንበር መጎብኘታቸው ተነግሯል።ይህ በንዲህ እያለ የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጉዳዩን አስመልክቶ ባለፈው ሳምንት ላይ በሰጠው መግለጫ  የኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን በሰላማዊ ንግግር መፍታት እንደሚያስብ ገልጧል።

በሌላ በኩል ደግሞ ሱዳን ዛሬ ግንቦት 25/2012 ዓም አዲስ የመከላከያ ሚኒስትር ሾማለች።አዲሱ መከላከያ ሚኒስትር ሜጀር ጀነራል ኢብራሂም ያሲን ሲሆኑ ሚኒስትሩ በቅርቡ በደቡብ ሱዳን ጉብኝት ላይ ሳሉ በድንገት ያረፉትን የሱዳን መከላከያ ሚኒስትር  ጀነራል ጋማል አልድን ይተካሉ።አዲሱ መከላከያ ሚንስትር በ1958 ዓም በካርቱም የተወለዱ ሲሆን ከዮርዳኖስ ሙታህ ዩንቨርስቲ በወታደራዊ ሳይንስ በመጀመርያ ዲግሪ መመረቃቸው እና በ2010 ዓም እኤአ ጡረታ ወጥተው የነበረ እና አሁን ተመልሰው የተሾሙ  መሆናቸውን ጉዳያችን ለመረዳት ችላለች።ይህ በእንዲህ እያለ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር የገባችው መጠነኛ ግጭት ብቻ ሳይሆን በዳርፉር ግዛቷ ጀበል ማራ በተባለ አካባቢ ከሽምቅ ተዋጊዎች ጥቃት እንደደረሰባት ለማወቅ ተችሏል።የአዲሱ መከላከያ ሚኒስትር  የሹመት ስነ ስርዓት ሲካሄድ ጀነራል እብራሂም ያሲን የሽግግር መንግስቱን ዓላማዎች እንደሚያስፈፅሙ በኮሮና ወረርሽኝ ሳብያ አፍና አፍንጫቸውን እንደሸፈኑ  ቃል መግባታቸውን ለማወቅ ተችሏል።

                                     ዛሬ ግንቦት 25/2012 ዓም የተሾሙት አዲሱ የሱዳን መከላከያ ሚኒስትር 


''ከቱርክ፣ኢራን እና እስራኤል በኃላ ኢትዮጵያ የአረቡን ዓለም ሰብራ ልትገባ ነው?'' ሚድል ኢስት ሞንተር ዛሬ ማክሰኞ የፃፈው

 ''ከቱርክ፣ኢራን እና እስራኤል በኃላ ኢትዮጵያ የአረቡን ዓለም ሰብራ ልትገባ ነው?''  በማለት በጥያቄ አርዕስት የሰጠው የዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 25/2012 ዓም  በሚድል ኢስት ሞንተር ላይ የወጣው ፅሁፍ በሱዳን እና በኢትዮጵያ ድንበር መካከል ያለው ግጭት ላለፉት አስር ዓመታት የነበረ እና ችግሩ ድንበራቸውን ስላላካለሉ ብቻ መሆኑን ያወሳል።ሆኖም ይላል ሚድል ኢስት ሞኒተር የአሁኑ ግጭት የተለየ የሚያደርገው የድንበር ግጭት ብቻ ሳይሆን ዲፕሎማሲያዊ ግጭትም በካርቱም እና በአዲስ አበባ መሃል ይዞ መምጣቱ እና እንደ ከዚህ በፊቱ ሁሉ ከጀርባ በመደበኛ ሰራዊቱ በሚደገፍ በሽፍቶች መሃል የተደረገ ግጭት ሳይሆን በሁለቱም አገሮች መደበኛ ሰራዊት መሃል የተደረገ ግጭት መሆኑን ያትታል።ይህንን ተከትሎ የሱዳን ከፍተኛ የጦር መኮንኖች በመቀጠልም የሱዳኑ ሽግግር መንግስት አብደላ ሃምዶክ ግጭቱ የተፈጠረበትን ቦታ መጎብኘታቸው እና መልዕክቱ ሱዳን ለሉዓላውነቷ የማትደራደር ነች የሚል መልዕክት ለኢትዮጵያ መንግስት ለማስተላለፍ መፈለጋቸው መሆኑን ሚድል ኢስት ሞንተር ያወሳል። እዚህ ላይ የኢትዮጵያ ከፍተኛ መኮንኖች የግጭቱን ቦታዎች ሄደው ስለማየታቸውን ሚድል ኢስት ሞኒተር ምንም አላለም። ምናልባት ዘገባው ገና ዛሬ ከመሆኑ አንፃር ለሕትመቱ  አልደረሰለት ሊሆን ይችላል።

ሚድል ኢስት ሞኒተር የኢትዮጵያ አካሄድ ''በአገር ውስጥ የፖለቲካ እና ምጣኔ ሃብታዊ ድል በማስመዝገብ፣ዓለም አቀፍ ግንኙነቷን በማጠናከር፣በአካባቢው ኃይል ሆና ለመውጣት ታስባለች።ይህንን ደግሞ በአረብ የውሃ መብት (ዓባይን መሆኑ ነው) እና በሱዳን ሉዓላዊነት ኪሳራ ለማሳካት ታስባለች'' ብሏል 
''It apparently believes that with its political and economic achievements at home and the expansion of its international relations abroad, it will be able to go ahead and become a major regional power, even if this comes at the expense of Arab water rights and the sovereignty of its neighbour Sudan።''

ሚድል ኢስት ሞኒተር ቀጠለ ''አዲስ አበባ የኢራንን፣ቱርክን እና እስራኤልን የአረቡን ዓለም  በስልት፣የመልከዓ ምድር፣የውሃ እና የፀጥታ ኃይል ስረ-መሰረት እንዴት መቦርቦር እንደሚቻል  በሚገባ አጥንታለች።'' ብሏል።
''Addis Ababa has studied the Iranian, Turkish and Israeli penetrations of the Arab world’s strategic, geographical, water and security depths''

ኢትዮጵያ ተጠባባቂ ጦር ማሰልጠን ያስፈልጋታል

በእዚህ ፅሁፍ መግቢያ ላይ እንደተገለጠው የአሜሪካ በውስጥ ጉዳይ መወጠር ለብዙ ግልገል  ሃያላን መንግሥታት መልካም ዕድል ይፈጥራል።ዕድል የሚለው ቃል በትክክል ባይገልጠውም መደናበር ይፈጥራል የሚለው ሊስማማ ይችላል።የመካከለኛው ምስራቅ አንዳንድ አገሮች እና ግብፅ አሁን ዓለም አቀፍ ሕጎች የሚጣሱበት፣የነዳጅ ምርት በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሳቢያ የዓለም ምጣኔ ሀብት በመውረዱ በነዳጅ የበለፀጉ አገሮች አሁን ያላቸውን እያወጡ ሌላ አገሮች ለመውረር እና የውስጥ የፖለቲካ ቀውሳቸውን ለማስቀየስ የሚጥሩበት ወቅት ነው።በሌላ በኩል የቱርክ፣ኢራን እና ሳውዲ አረብያ መሃከል ያለው ፍጥጫ በራሱ የአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካን ወደ አዲስ ትኩሳት የሚከት ሊሆን ይችላል።ሌላው ቀርቶ ኃያላኑም ቢሆኑ ከወረርሽኙ በኃላ የምጣኔ ሃብቱ ጦርነት እና የግዙፎቹ ዓለም አቀፍ ኮርፖሬሽኖች ገቢ መውረድ እና መክሰር በራሱ  ምጣኔ ሀብታቸውን ወደ ጦርነት ኢኮኖሚ ቀይረው አዳዲስ ፍጥጫ ከቻይና፣ሩስያ እና ቱርክ ጋር አይገቡም ማለት አይቻልም።በእዚህ ሁሉ መሃል ኢትዮጵያ በዓባይ ግድብ ሳብያ የመካከለኛው ምስራቅ አንዱ ካርድ እርሷ ጋር እንዳለ ግልጥ ሆኗል።ስለሆነም ይህንን ካርድ በሚገባ እንድትጫወተው የተጠባባቂ ጦር በፍጥነት ማሰልጠን አስፈላጊ ይሆናል።ወደፊትም ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ወጣቶች ብሔራዊ ውትድርና ሰልጥነው መቀመጥ አንዱ ግዴታ መሆኑ ሊታሰብበት ይገባል።ሰልጥነው የጨረሱ የተሻለ የትምህርት እና የስራ ዕድል እንዲያገኙ ማድረግ ብቁ ዜጋ የማፍራት አንዱ እና አስፈላጊ ጉዳይ ነው።ዛሬ በሰለጠኑት አገሮች ሳይቀር ወጣቶች ብሔራዊ ውትድርና ሰልጥነው ወደ ቤተሰቦቻቸው ይመለሳሉ። በእዚህም ንቁ እና የፈጠራ ችሎታ ያለው ወጣት አፍርተዋል።እኛ ሀገር ያለው የብሔራዊ ውትድርና በደርግ ዘመን ያተረፈው ''ጥቁር ስም'' በአዲስ ስም መቀየር ሳያስፈልግ አይቀርም። የሆነው ሆኖ ጊዜው የሚያሳየው ኢትዮጵያ ተጠባባቂ ጦር ማሰልጠን እንዳለባት ነው።ኢትዮጵያ ውስጣዊ የፖለቲካ ሰላሟን እስካረጋጋች ድረስ እና በግድቡ ዙርያ ያላት ባለቤትነት አስጠብቃ እስከሄደች፣እንዲሁ የጦር ኃይሏን በተተኪ ኃይል ካጠናከረች፣አሁን ለኢትዮጵያ የተሻለ ጊዜ እንደሆነ ምንም አያጠራጥርም።ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com