ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, January 31, 2023

ጠ/ ሚ/ር ዐቢይ ዛሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ቅዱስ ሲኖዶስ ለመክፈል የሞከሩ ሕገወጦችን አስመልከተው የተናገሩት ንግግራቸው በታሪክም በሕግም ያስጠይቃቸዋል።




በእዚህ አጭር ጽሑፍ ስር፣
  • የሞሰቡን ባለቤት ከራሱ ሞሰብ ላይ ቆንጥረው ያጎረሱትን እየቆጠሩ ከውለታ ቁጠርልኝ፣
  • ቤንዚን ማርከፍከፍ
  • ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቤተክርስቲያኒቱ ላይ የተፈጸመው ወንጀል የሚያስከትለው መዘዝ ገብቷቸዋል።
  • ሚኒስትሮች! የሃይማኖታችሁ ጉዳይ አይመለከታችሁም! ዝም በሉ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዛሬ ጥር 23፣2015 ዓም ሰላም እና ሃይማኖት በተመለከተ የተናገሩት በሚል በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የተናገሩት ንግግር በዋናነት ሰሞኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለሁለት ለመክፈል በኦሮምያ ክልል የተነሳውን ቡድን አስመልክተው የተናገሩት በታሪክም በሕግም ያስጠይቃቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በእዚሁ ንግግራቸው ፈጽሞ ፍትሃዊነት የጎደለው፣የህገወጦቹ ቃል አቀባይ እስኪመስሉ ድረስ በቤተክርስቲያኒቱ ላይ የተሞከረው የመክፈል ሙከራ የመንግስት ሚናው እና ቦታውን ያላሳየ ብቻ ሳይሆን ፈጽሞ ወገናዊነት የታየበት ከቃላቶቻቸው ድምጸት እስከ የህገወጦቹ ካሉት በላይ አስተዛዝነው ለማስረዳት የሄዱበት እርቀት ሁሉ በቤተክርስቲያኒቱ መከፍል ያላቸውን አቋም ማንም በግልጽ ሊረዳው የሚችለው ነው። እስኪ ከንግግሮቻቸው ውስጥ የሚከተሉትን እንመልከት።

የሞሰቡን ባለቤት ከራሱ ሞሰብ ላይ ቆንጥረው ያጎረሱትን እየቆጠሩ ከውለታ ቁጠርልኝ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በእዚህ ንግግራቸው መግብያ ላይ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንግስት ሰጠ ያሉትን መሬት እየሰፈሩ ከሌላው የእምነት ተቋማት ጋር ለማነጻጸር በእዚህም የመንግስታቸው ''ቸርነትን'' ለማሳየት ሞክረዋል። በመጀመርያ ይህ ተሰጠ ያሉት መሬት ማስረጃ የትነው ያለው? ሲቀጥል ይህ ንጽጽር በራሱ ሁለት መሰረታዊ ስህተቶች አሉት። አንድ፣ ኦርቶዶክሳዊው በራሱ ሃገር እንደምጽዋተኛ የሚታይ አይደለም።የራሱን ሞሰብ ላይ ያጎረሱትን እየቆጠሩ ከውለታ ቁጠሩልኝ መሰል ንግግር ትዝብት ላይ ይጥላል።አንድ መንግስት ለሺህ ዓመታት ለኖረች ቤተክርስቲያን መሬት ሰጠሁ ብሎ እንደ ታላቅ ውለታ የሚነገርባት ሃገር ኢትዮጵያ መሆኑ ያስገርማል። በሁለተኛ ደረጃ ክርስቶስ ባረገ በዓመቱ ክርስትናን የተቀበለች፣በአራተኛው ክ/ዘመን ክርስትና ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ የታወጀባት ሃገር ኢትዮጵያን የሰራች ቤተክርስቲያን የተሰጣትን መሬት ከሌሎች ጋር የማወዳደሩ አካሄድ ያውም በጠቅላይ ሚኒስትር ደረጃ የሆነ ለመፍጠር የተፈለገውን ስዕል ያሳያል።የስሌቱ አካሄድ በራሱ የትንሽነት አስተሳሰብ ሰለባነትን ያሳያል።

ቤንዚን ማርከፍከፍ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዛሬ ያደረጉት ንግግር እንደ መንግስት መሪ ነገሮችን በሁለት ዐይን የተመለከተ ሳይሆን ፍጹም አድሏዊ፣ሃላፊነት የጎደለው እና የህገወጥ ቡድኖችን ተግባር ለማንሞካሸት ሩብ ጉዳይ የቀረው ያህል ነው። እነርሱ ያሉት በቋንቋቸው የመማር ጥያቄ እንዳነሱ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ቤተክርስቲያኒቱ በቋንቋ በኩል ምን እየሰራች እንዳለች ለመናገር አልፈለጉም።በነገሩ ላይ ቤንዚን ይጨምርልኛል ያሉትን ብቻ እነርሱ ያሉት እያሉ አስተዛዝነው ሀገር በደም ለመንከር በህገወጥነት እና ፍጹም በሆነ ውንብድና ቤተክርስቲያኒቱን ለመክፈል የሞከሩትን ቡድኖች በመንግስት ሚድያ ለማስተላለፍ በጠቅላይ ሚኒስትር ደረጃ ይህንን ያህል በሃሰት ሲጋጋጡ ማየት ለትውልዱ አሳፋሪ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ህገወጥ ቡድኑ በመንግስታቸው የክልል ወታደር እንደሚታጀቡ፣ቤተክህነትን ሲጠብቅ የነበረ ፖሊስ እንዲነሳ የተደረገበትን ምክንያት፣አቡነ እስጢፋኖስ በጅማ ለንግስ እንደሄዱ ለምን ከአየር ማረፍያ ተይዘው ፖሊስ ጣብያ ታስረው እንደዋሉ፣ዛሬ በያቤሎ የመንግስታቸው ወታደሮች ቤተክርስቲያኒቱን ለመክፈል ሞክረው የተወገዙትን ግለሰቦች ህዝብ እንዲቀበል ሊያስገድዱ ሲሞክሩ ህዝብ እምቢ ማለቱን አልነገሩንም። በአጭሩ በዛሬው ንግግራቸው በቤተክርስቲያኒቱ ላይ በታሪኳ ደርሶባት የማያውቅ መንግስት የሚባል አካል ባለበት በሃገር ውስጥ ሆኖ ሲኖዶስ እከፍላለሁ ያለ ቡድን ድርጊትን '' እንደ እኔ ቀላል ጉዳይ ነው '' በማለት ሊያጣጥሉት የሞከሩበት እርቀት በራሱ ስለ ቤተክርስቲያኒቱ ያላቸውን ያልበሰለ ወይንም ሆን ተብሎ የማጣጣል አቀራረብ ያሳያል።ባጭሩ ንግግራቸው በችግሩ ላይ ቤንዚን ያርከፈከፈ እና ህገ ወጦችን አይዟችሁ ቀረሽ ንግግር በጣም የሚያሳፍር ነው።

ሌላው በዛሬው ቤንዚን አርከፍካፊ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ላይ ያነሱት ''ባለፈው የትግራይ ጳጳሳት ያን ያህል ሲሉ ምንም ያልተባሉትን ዛሬ ሁሉም እየተነሳ'' በህገወጦቹ ላይ እጅ አበዛችሁ ለማለት ሞክረዋል። በመጀመርያ ደረጃ የትግራይ ጳጳሳት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተለየን ሲሉ ሁሉም ዝም ብሎ ነበር? እርግጠኛ ነዎት? ቅዱስ ሲኖዶስ ጉዳይን አስመልክቶ የተነጋገረበትን ጉዳይ ያውቃሉ? ከእዚህ ገጽ ጀምሮ ኢትዮጵያውያን በየደረጃው ዝም ነው ያሉት? በሌላ በኩል በሁለቱ መሃል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? የትግራይ ጳጳሳት ፓትርያሪክ በሌለበት ኢጲስ ቆጶስ እንሹም ብለው ተነስተዋል? ለመሆኑ በጠቅላይ ሚኒስትር ደረጃ ያለ ሰው ባልተረጋገጠ እና መረጃ በሌለው የፌስ ቡክ ወሬ ተመስርቶ እንዲህ ባለ ትልቅ የሃይማኖትም ሆነ የሃገር ጸጥታ ጉዳይ ላይ ''እገሌ ሲሆን ዝም ብላችሁ እገሌ ላይ ትወርዱበታላችሁ'' በማለት ቤንዚን ያርከፈክፋል?

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቤተክርስቲያኒቱ ላይ የተፈጸመው ወንጀል የሚያስከትለው መዘዝ ገብቷቸዋል።

በዛሬው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ላይ ሌላው ያነሱት መንግስታቸውን የሚቃወም ህዝባዊ ኃይል እንደሚነሳ በግልጽ ጠቁመው በአመጽ የምትመጡበትን መንገድ እንዳይሞከር የሚል በጣም የወረደ የማስፈራርያ አይሉት ሌላ ቃላት ተጠቅመዋል። ወታደራዊ መንግስት በ''ኩዴታ'' ጉዳይ የመጣ ስለነበር ማንም በእዚህ መንገድ ሊጥለው አልቻለም። ህወሃትም በሽምቅ ስለመጣ እነ ፕሮፌሰር ብርሃኑም አልቻሉትም በሚል ንግግር የተናገሩት ዐቢይ እኛም በምንም ብትመጡ እናቃለን በሚል የሚያሞኝ ንግግር አክለውበታል። ከእዚህ በተጨማሪ ጦርነት አስከፊ መሆኑን ለሚነሱባቸው ተቃዋሚዎች ለመምከር ከሞከሩ በኋላ አሁንም ለመግደል ወደ ከተማ እየመጡ ነው የተወሰኑ ይዘናቸዋል ብለዋል።

ስለሃይማኖት እና ሰላም የነበረው የርዕሳቸው ንግግር አመጽ እንደሚነሳ እና ቀጣዩ አመጽም በየት እንደሚመጣ እንደሚያውቁ እና እንደሚያከሽፉ ተናግረዋል። በመጀመርያ ደረጃ መንግስት የሰራውን ክፉ ሥራ ገብቶታል ማለት ነው? አመጽን ምን አመጣው? አመጽ እንደሚነሳ በምን አወቀ? አመጽ የከፋው እና የተከፋ ሕዝብ ይፈልጋል።መንግስት የገፋው እና የተገፋ ህዝብ መኖሩን በማወቁ ነው መንግስቴን ሊገለብጡ የሚነሱ አሉ ያሉት? የሰራውን የሚያውቅ ሁሌ መደንበሩ የተለመደ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቤተክርስቲያኒቱ ላይ አመራራቸው የሰራውን ስለሚያውቁ እና ይህም ሥራ ትክክል አለመሆኑ ግልጽ በመሆኑ ከህዝብ የሚነሳ ተቃውሞ እንደሚኖር ለማመላከት ተገደዋል።ባጭሩ በቤተክርስቲያኒቱ ላይ የተፈጸመው ወንጀል ገብቷቸዋል። በአደባባይ ቢክዱትም።

ሚኒስትሮች! የሃይማኖታችሁ ጉዳይ አይመለከታችሁም! ዝም በሉ!

ሌላው አስቂኝም ሆነ አስገራሚው የዛሬው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ የተፈጸመውን መንግስታዊ ድጋፍ የተቸረው ቅዱስ ሲኖዶስን የመክፈል ሙከራ አስመልክቶ ለሚነሱ ማናቸውም ጉዳዮች ሚኒስትሮች አንዳች እንዳይናገሩ አስጠንቅቀዋል። ይህንን ንግግር የሙስሊም ወንድሞቻችን ላይ ቢናገሩት ብላችሁ አስቡት።በሌላ አነጋገር አንተ ሚኒስትር ሆነህ የኦርቶዶክስ ተከታይ ብትሆንም ሃይማኖትህ ሲከፈል፣ህገወጦች በጎጥ ተነስተው ቤተክርስቲያንህን ለመክፈል ቢሞክሩ ዝም በሉ! የሚል አስገራሚ መልዕክት አስተላልፈዋል። ሚኒስትር ኢትዮጵያዊነትን ቢያስቀድም ኢትዮጵያን የሚያውቃት በእምነቱ ውስጥም መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዘንግተውታል።ኢትዮጵያ የሚኒስትር ቦታ አይደለም የንግስና ዘውዳቸውን አስቀምጠው ክርስቶስን ሊከተሉ ገዳም የገቡ መሪዎች ባለቤት ሃገር መሆኗን አሁንም እረስተውታል። ሚኒስትሮቹ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ምንም ሃሳብ መስጠት እንደማይችሉ የተናገሩበት ድምጸት በራሱ ያስገርማል። ይህ የነገሩን የትኩሳት ልክ፣በቤተክርስቲያኒቱ ላይ መንግስታቸው የሰራውን የመከፋፈል ወንጀል ዲግሪ እና ከምንም በላይ በሃይማኖቱ ያውም በግፍ ሊከፍሉት የመጡበትን እንዴት ባለ መግነጢሳዊ የኃይል ስሜት ህዝብ እንደቋያ እንደሚያስነሳ ማንም ተራ ሰው ያውቀዋል። ግፍ ተሰርቷል።የእግዚአብሔርን ቤት ከሓዋርያት መሰረት ጀምሮ የኖረ ከክርስቶስ የተገኘች ሲኖዶሳዊ አሰራር ላይ ከባድ ድፍረት ተፈጽሟል።ይህንን ደግሞ የፈጸሙት በመንግስት ቀጥተኛ ድጋፍ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሕገወጦቹ ሽፋን ለመስጠት በተፍጨረጨሩበት ንግግር ግልጽ ሆኗል።

ባጠቃላይ 

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ለደረሰው ሲኖዶስን የመክፈል ሙከራ በኢትዮጵያ ላይ የእርስ በርስ ጦርነት ከመጫር በላይ ከፍተኛ የጸጥታ ችግር እንደሚያመጣ ለመተንተን አልሞከሩም።ለምን? ለጸጥታ ጉዳይ አማካሪዎቻቸው እተወዋለሁ። ይህ የሃገር የጸጥታ ጉዳይ አይደለም? ይህ በኢትዮጵያ ጦርነት አያስነሳም? የሃገሪቱ መሪ ቀላል ጉዳይ ነው ብለው የሚነግሩን እንዴት ነው?  በመንግስታቸው የጸጥታ ኃይል ድጋፍ ጭምር ህገወጦቹ ጥበቃ እየተደረገላቸው ሳለ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በቅዱስ ፓትሪያሪኩ ግልጽ ጥሪ ለመንግስት አቅርባ  መንግስታቸው አንድም ዓይነት ''ኦፊሻል '' ምላሽ ሳይሰጥ የቤተክርስቲያኒቱ አባላትን የጸጥታ ሃይሎች እያሰሩ እና እየፈቱ እንደጅማ ሃገረ ስብከት ደግሞ ሃገረ ስብከቱ ለስብከተ ወንጌል የሚጠቀምባቸውን መኪናዎች ጭምር እንዳያንቀሳቅስ የመንግስታቸው መዋቅር ትዕዛዝ እንደሰጠ እያወቁ ጉዳዩን ለማጣጣል እና የኢትዮጵያን ህዝብ ለማሞኘት የሄዱበት የጅል መንገድ ዋጋ ያስከፍላል።ባጭሩ ጠ/ ሚ/ር ዐቢይ ዛሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ቅዱስ ሲኖዶስ ለመክፈል የሞከሩ ሕገወጦችን አስመልከተው የተናገሩት ንግግራቸው በታሪክም በሕግም ያስጠይቃቸዋል።የእግዚአብሔር ፍርድም ከበር ይጠብቃቸዋል።ኃይሉን ንቀውታል።አዛውንት ሊቃነ ጳጳሳትን እንደ ምናምንቴ ቆጥረው ጉዳዩን ሊያቃልሉት ሞክረዋል።የሚታዘባቸውን የኢትዮጵያን ህዝብ ቀላል ነው እያሉ ለመሸንገል ሞክረዋል። በድርጊቱ ግን አዛውንት መነኮሳት እንባቸው ፈሷል፣ወጣቶች ልባቸው ተቃጥሏል፣ታዳጊዎች ጳጳስ በሃገሩ ካለምንም ጥፋት መታሰሩን ሰምተዋል።ዛሬ ደግሞ የሃገሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ጉዳዩ እንደ እኔ ቀላል ነው ብለው ሲዘብቱ ተመልክተዋል።

===============///////========



Monday, January 30, 2023

የብልጽግና ፓርቲ ኢትዮጵያን የማስተዳደር አቅሙ የወደቀ ለመሆኑ ህዝብ ድምዳሜ ላይ እየደረሰ ነው።የአቡነ እስጢፋኖስ በጅማ ፖሊስ ጣብያ ታስረው መዋል ፓርቲው ክቡር ለሆነ የኢትዮጵያውያን ማኅበራዊ እሴት (''ሶሻል ቫልዩስ") ያለው የንቀት ደረጃ ህዝብ በሚገባ ለክቶበታል።

ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ የጅማ፣የም፣ ኮንታ፣ዳውሮ እና ሰሜን ጎንደር ሊቀጳጳስ

  • ይህ ጥያቄ የኢትዮጵያ ህዝብ አካል የሆነው ከ70 ሚልዮን በላይ የሆነ ቀረጥ ከፍሎ የሚያድረው ህዝብ በከፈልኩት ቀረጥ መንግስት ቤተክርስቲያኔን የመጠበቅ ግዴታህን ተወጣ የሚል እጅግ የከበደ ጥሪ ነው፣
  • ጅማን ህይወት የዘሩባት አቡነ እስጢፋኖስ ላይ የተፈጸመው ግፍ ብልጽግና በህዝብ ላይ ያለው የንቀት ጥግ ያሳያል።
  • የኢትዮጵያ ኦ/ ተ/ቤተክርስቲያን በተሞከረባት የመበተን ሙከራ አንጻር ቤተክርቲያኒቱ  እንደ ተቋም ምዕመናኖቿ ደግሞ እንደ የቤተክርስቲያን ልጅነት ሊወስዷቸው የሚገቡ ሁለት ስልታዊ እርምጃዎች ምን እና ምን ናቸው?
 
=========
ጉዳያችን
=========

ሰሞኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለመክፈል ያለመ ያልተሳካ ሙከራ ከተደረገ በኋላ በቤተክርስቲያኒቱ ላይ የሚደረጉት የሽብር ተግባራት ቀጥለዋል። የሽብር አፈጻጸሙ ደግሞ የቤተክርስቲያኒቱን አባቶች እና አገልጋይ ካህናት ለማሸማቀቅ እየተደረገ ያለው ሙከራ ከፍተኛ የህዝብ ቁጣ እየቀሰቀሰ ከመሆኑም በላይ በብልጽግና የሚመራው መንግስት ቤተክርስቲያኒቱን ህዝብ በከፈለው ቀረጥ የመጠበቅ ግዴታው ላይ ያሳየው ንዝህላልነት እና ንቀት የፓርቲው ሃገር የማስተዳደር አቅም ከአማካይ በታች እንደሆነ አስመስክሯል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ሲኖዶሱን ለመክፈል የሞከሩትን ስልጣነ ክህነት ከመሻሩ በላይ አሁንም ለንስሃ ተመልሰው ይቅርታ ከጠየቁ ጉዳዩ እንደሚታይ ጠቅሶ ጉባዔውን አጠናቋል። ይህ ውሳኔ ድንገት ደራሽ የሆነ እና ለአበበ ወይንም ለከበደ ተብሎ የሚለይ ሳይሆን ሃይማኖታዊ ጥያቄ ሲሆን በጉባዔ ቀርበው የሚያስረዱበት በቀጥታ ቤተክርስቲያኒቱን ለመክፈል የምዕመናንንን አንድነት ለመበተን የሚደረግ አደገኛ ሙከራን ደግሞ በፍጥነት ስልጣነ ክህነትን መሻር ነው። ይህ ቤተክርስቲያኒቱ ዛሬ የጀመረችው ሳይሆን ከሓዋርያት ጉባዔ ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ እና ዛሬም የምስራቃውያን አብያተክርስቲያናት የሚጠቀሙበት ነው።

ቤተክርስቲያኒቱ በቀኖናዋ መሰረት ይህንን ብትወስንም የህገወጦቹ ደጋፊ መሆኑን በሚያሳብቅ ደረጃ የተወገዙትን ልዩ የጥበቃ አገልግሎት ለመስጠት ሽር ጉድ ሲል የታየው የኦሮምያ ብልጽግና ልዩ ኃይል ነው። ይሄው ልዩ ኃይል ህገወጡ ሹመት በተደረገበት ቦታ ተገኝቶ የጥበቃ አገልግሎት ከመስጠት ጀምሮ ህገወጦቹን አንቀበልም ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ በግድ ለመላክ ያደረገው የከሸፈ ሙከራ ሁሉ የብልጽግና ፓርቲ በቤተክርስቲያኒቱ አንጻር እያሳየ ያለው አደገኛ መንገድ ግልጽ ያደርገዋል።

ጅማን ህይወት የዘሩባት አቡነ እስጢፋኖስ ላይ የተፈጸመው እስር ብልጽግና በህዝብ ላይ ያለው የንቀት ጥግ የሚያሳይ ነው።

ብጹዕ አቡነ እስጢፋኖስ፤ የጅማ፣የም፣ ኮንታ፣ዳውሮ እና ሰሜን ጎንደር ሊቀጳጳስ ባለፈው ቅዳሜ ለጅማ ደብረ ኤፍራታ ቅድስት ማርያም ካቴድራል የምረቃ መርሐ ግብር ላይ ለመገኘት ጅማ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በኦሮምያ ክልል ፖሊስ ለጥያቄ እንፈልጋችኋለን ተብለው ፖትሮል በያዙ አካላት ወደ ጅማ ፖሊስ መምሪያ ተወስደው በበዓሉም ላይ ሳይገኙ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ተደርጓል። ጅማን በልማት ለማሳደግ የአቡነ እስጢፋኖስን ያህል የለፋ ላለመኖሩ ክርስቲያኑ አይደለም የሙስሊም ማኅበረሰብ የሚመሰክረው ነው።አቡነ እስጢፋኖስ በጅማ ሃገረስብከት ባገለገሉባቸው ዓመታት ውስጥ ጅማ ከተማ ብቻ ተቀምጠው ያገለገሉ አባት ብቻ አይደሉም። ከጅማ ውጭ የሚገኙ ቦታዎችን በሞተር ሳይክል ሳይቀር እየተመላለሱ የሙስሊሙን ማኅበረሰብ ሳይቀር ድጋፍ ያደረጉ አባት ናቸው። ዛሬ ላይ ግን የብልጽግና መንግስት ህይወት በዘሩባት ከተማ ያሰሩትን ቤተክርስቲያን እንዳያስመርቁ ከአየርማረፍያ ተወስደው ፖሊስ ጣብያ እንዲታሰሩ ተደረገ። ለእዚህ ለተፈጸመ ግፍ አሳሪው ዋጋውን መከፈሉ አይቀርም።

የኢትዮጵያ ኦ/ ተ/ቤተክርስቲያን በተሞከረባት የመበተን ሙከራ አንጻር ቤተክርቲያኒቱ  እንደ ተቋም ምዕመናኖቿ ደግሞ እንደ የቤ/ክርስቲያን ልጅነት ሊወስዷቸው የሚገቡ ሁለት ስልታዊ እርምጃዎች 

የኦሮምያ ብልጽግና ከጽንፈኛ የክልሉ ኃይሎች ጋር ሆኖ የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን ለመክፈል ያደረገው የከሸፈ ሙከራ በአባቶች ላይ የሽብር እና የማሰር ግፍ ብቻ ሳይሆን የፈጸመው ቤተክርስቲያኒቱ በግልጽ (በኦፊሻል) ለመንግስት የቤተክርስቲያኒቱን ደህንነት የማስጠበቅ ግዴታውን እንዲወጣ በቅዱስ ፓትሪያሪኩ ብጹዕ አቡነ ማትያስ ባለፈው እሁድ ጥር 21፣2015 ዓም ላደረጉት ጥሪ አንዳችም ምላሽ አልሰጠም። ይህ ጥያቄ እና ጥሪ የአቡነ ማትያስ ወይንም የሌላ አባት ድምጽ አይደለም። ''ኦፊሻል" ጥያቄው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ድምጽ ነው። ይህ ከ70 ሚልዮን በላይ የሚሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ድምጽ እና ጥያቄ ነው። ይህ ጥያቄ የኢትዮጵያ ህዝብ አካል የሆነው ከ70 ሚልዮን በላይ የሆነ ቀረጥ ከፍሎ የሚያድረው ህዝብ በከፈልኩት ቀረጥ መንግስት ቤተክርስቲያኔን የመጠበቅ ግዴታህን ተወጣ የሚል እጅግ የከበደ ጥሪ ነው። ይህንን ጥሪ አለመስማት ጅልነትም ነው።ይህንን ጥሪ ችላ ብሎ ህገወጦቹን በልዩ ኃይል ለማስጠበቅ መንደፋደፍ ህዝብን የመናቅ አደገኛ ደረጃ ነው። 

አሁን የቤተክርስቲያኒቱ ልጆች ብቻ ሳይሆኑ የሙስሊሙም ማኅበረሰብ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ላይ እየተፈጸመ ያለው ቤተክርስቲያኒቱን ለመክፈል የሚደረገው ሙከራ ከመስመር ያለፈ ብቻ ሳይሆን በትዕቢት የተወጠረ መሆኑ በግልጽ እየታየ ነው። ለእዚህ ምላሽ እንዲሆን ግዙፍ የተቃውሞ ሰልፎች በመጪው ረቡዕ በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ከሚደረገው ሰልፍ በተጨማሪ በመጪው ዕሁድም ግዙፍ ሰልፎች በመላው ዓለም ኢትዮጵያን ጨምሮ ይደረጋሉ።ይህ የብልጽግና ፓርቲ በመላው ዓለም በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ላይ እየሰራ ያለውን የንቀት እና የጥላቻ ተግባር የሚያጋልጥ ነው።

ከእዚህ በተጨማሪ ግን ቤተክርስቲያኒቱ እንደ ተቋም፣ምዕመናን እንደልጅነት የሚሰሯቸው ሁለት ቁልፍ እና ስልታዊ ስራዎች ሊኖሩ ይገባል።

ቤተክርስቲያኒቱ እንደተቋም አሁን ለገጠማት ችግር መስራት የሚገባት ሁለት ጉዳዮች ናቸው። አንዱ እራሷን በፍጥነት ንብረቷን እና የሰው ኃይሏን በፈጠነ ዘመናዊ መንገድ መያዝ እና ማስተዳደር።ይህንን ደግሞ ለምሳሌ በአጭር ጊዜ የቤተክርስቲያኒቱን አጥብያዎች እና አድባራት እንዲሁም ገዳማት አስተዳደር በአይቲ ማገናኘት ይህንንም ሥራ ለቤተክርስቲያኒቱ ልጆች መስጠትና ውጤት ማምጣት ይገባል። ይህም የገንዘብ አስተዳደሩን ብቻ ሳይሆን የሪፖርት ፍሰት እና መረጃዎች በማዕከል ቤተክህነት በቶሎ ለማቀላጠፍ ይረዳዋል።

ሁለተኛው ቤተክርስቲያኒቱ በፍጥነት መከወን ያለባት ከእህት አብያተክርስቲያናት ጋር እና ከምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት ጋር ተከታታይ ግንኙነቶች ማድረግ እና ያሉባትን ተግዳሮቶች ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲያዊ ጫና በብልጽግና ላይ እንዲደረግ ማድረግ እና የአቅም ግንባታዋ እንዲታገዝ ማድረግ ነው። 

ምዕመናን እንደልጅነት ሊያከናውኑት የሚገባው አንዱ እና ዋና ተግባር ሃገራዊ በሆኑ ቤተክርስቲያኒቱንም ልጆቿንም ሰላም እየነሳ ያለው እና የጽንፍ ኃይሎችን ጉልበት እየሰጠ ያለው የጎሳ ፖለቲካን በሃገር አቀፍ ደረጃ በመቃወም ዘመቻ ማድረግ ነው። ይህንን የጎሳ ፖለቲካ የኢህአዴግ አባል የነበሩት የብልጽግና አባላት ሲሳሱለት እየታየ ነው። ከአሁን በኋላ ግን የጎሳ ፖለቲካ ውስጥ ኢትዮጵያ ተነክራ ከቆየች የእያንዳንዱ ሰው ህልውና ብቻ ሳይሆን የመጪው ትውልድ አደጋ በመሆኑ የጎሳ ፖለቲካን በመቃወም በመላ ሃገሪቱ ምዕመናን እንደልጅነት ቤተክርስቲያን ደግሞ በአስተምሮቷ እንደተቋም በግልጽ እና በአደባባይ በመቃወም መላው የኢትዮጵያ ህዝብን ከጎኗ የምታቆምበት ጊዜ አሁን ነው። የጎሳ ፖለቲካን እንዴት እንደሚነቅል የሱማሌ፣የደቡብ፣የአፋር፣የቤኒሻንጉል፣የአማራ፣ኦሮሞና ትግራይ ክልል ህዝብ ሁሉ የሚያስነሳው እየጠበቀ ነው። አሁን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አስተምሮቷም ክርስትናም የጎሳ ፖለቲካ ተቃራኒ በመሆኑ ይህንን መልካም ሥራ ምዕመናኖቿ በግልጽ ወጥተው ግዙፍ ንቅናቄ የሚፈጥሩበት ጊዜ አሁን ነው።

ባጠቃላይ የብልጽግና ፓርቲ የኢትዮጵያን መልካም እሴቶች ውስጥ አንዱ የሆነው እና ኢትዮጵያን በሁሉ መልክ ሰጥታ ለዘመናት ያሻገረች የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን አንጻር ያሳየው የመበተን ሙከራ እጅግ አስጸያፊ ብቻ ሳይሆን በስጋም በነፍስም ትልቅ ድፍረት ነው።ድፍረቱ የተሰጠውን መንግስታዊ ኃላፊነት ህዝብን እና ከህዝብ በሰበሰበው ቀረጥ የህዝብ የሆነ ሃይማኖትን የመጠበቅ ግዴታ ከመወጣት ይልቅ ህገወጦችን እያደራጀ ቤተክርስቲያኒቱን ለመግፋት ሲሞክር ማየት አሳዛኝ ነው።ምናልባት የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በወታደራዊው መንግስትም ሆነ የህወሃት መንግስት ወደ ስልጣን ሲመጡ ቤትክህነቱን ለመቆጣጠር የሄዱበትን እርቀት ብልጽግና እንደ የልማድ ትምህርት ወስዶ ያንኑ ሊሞክር ያስብ ይሆናል። ይህ  ግን ዘመኑን ያለመዋጀት ችግር ነው።በ21ኛው ክ/ዘመን ላይ ያለችው የዛሬዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በ1966 ዓም ሆነ በ1983 ዓም እንዳለችው ያለች አይደለችም። ዛሬ በሚልዮን የሚቆጠሩ ልጆቿ ተደራጅተዋል ብቻ ሳይሆን ለመስዋዕትነት የተዘጋጁ ሚልዮኖች በሙሉ ልብ ከቤተክርስቲያን ጎን የቆሙበት ጊዜ ነው። ዛሬ በሚልዮን የሚቆጠሩ ልጆቿ በመላው ዓለም ተጽዕኖ ፈጣሪ ብቻ ሳይሆኑ የአንዳንዶቹ ሃገሮች የደም ስርም ጭምር ናቸው። በቤተክርስቲያኒቱ ላይ ለሚሞከር ምንም ዓይነት የመበተን እና የመከፋፈል ሙከራ የሚያስከትለው መዘዝ ቀላል አይደለም።ባጭሩ የ1966 እና 1983 ዓም ስሌት ዛሬ ላይ እንደማይሰራ ብልጽግና ግልጽ ካልሆነለት ግልጽ ሊሆንለት ይገባል።የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አንድነቷን ማክበር የኢትዮጵያን አንድነት ማክበር ማለት ነው። በእዚህ መንገድ ብቻ ነው ቤተክርስቲያኒቱ የልማት አጋር አድርጎ ሃገር በጋራ ማሳደግ የሚቻለው። ከእዚህ ውጭ የሚያስኬድ አንዳችም መንገድ የለም።
====================///////=====================

Sunday, January 29, 2023

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በተመለከተ ዛሬም ወሳኙ ጉዳይ ውስጣዊ አስተዳደራዊ መዋቅሯን ማዘመን አና ማቀላጠፍ ነው።የውጪው ፈተናዋ አስከምፅአት ቀን ድረስ የሚኖር ነው።(የጉዳያችን የዛሬም ጩኸት አንድ ነው!)


  • የዛሬ አስር ዓመት ምን ይገጥመናል ብሎ መፃፍ አና ዛሬ ይሄ ሆነ ሲባል ስሜትን በቁጣ አየገለፁ መናደድ ይለያያሉ።ጉዳያችን የዛሬው ቀን እንደሚመጣ ከአስር ዓመታት በላይ ጽፋለች።የጽሑፎቹን ሊንኮች ከስር ያገኛሉ።

  • አሁን ያሉት ቤተክርስቲያንቱን የመግፋት ድርጊቶች ችግር ብቻ ሳይሆን ያለው ለቤተክርስያንቱ ዕድል ይዞ የሚመጣ መልካም አጋጣሚም ነው።

======

ጉዳያችን 

====== የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በምእመናኖቿ ብቻ ሳይሆን በስርጭትም ሆነ በማኅበራዊ አና ምጣኔ ሃብታዊ መለኪያዎች በኢትዮጵያ ግዙፍ አካል ነች። ይህንን እውነታ መጋፋቶች መሬት ላይ ያለውን አውነታ መቀየር አይቻልም።አሁን ያሉት ቤተክርስቲያንቱን የመግፋት ድርጊቶች ችግር ብቻ ሳይሆን ያለው ለቤተክርስያንቱ ዕድል ይዞ የሚመጣ መልካም አጋጣሚ ነው።የቤተክርስቲያኒቱ አስተምሮ ላይ ያሉ ግንዛቤዎች በአዲሱ ወጣት ትውልድ ዘንድ መደናበር የለም።ወዴት መሄድ አለብን፣አንዴት ቤተክርስቲያንን አናልማ ውዥንብር የለም።የቤተክርስቲያኒቱ ውጫዊ ተግዳሮቶች መነሻ መሰረታዊ ባህሪዎች የመለየት ችግር የለም።አነኝህ ሥራዎች ላለፉት ዓመታት በጥራት ግንዛቤ የወሰደ ከ70 ሚልዮን በላይ ምዕመን አለ።አሁን ያሉት ችግሮች የሚነሱት ከቤተክህነት አና ከመንግስታዊ የፖለቲካ አካላት መሆናቸው የችግሩ ስብጥር እና ጥግ በራሱ የተሰበሰበ መሆኑ ለመፍትሄዎቹ ግልፅ ያደርጋቸዋል። ይህንን ሁሉ በፍጥነት ለመመከት ግን ቤተክርስቲያኒቱ ውስጣዊ መዋቅሯን በፈጠነ መልክ ማዘመን መቻል ይጠይቃል።ይህንን ደግሞ ቁርጠኘነቱ እና በጎ ፈቃዱ ከቤተክህነት በኩል ካለ የቤተክርስቲያኒቱ ልጆች ለሥራው ዝግጁ ናቸው።


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን በተመለከተ በጉዳያችን ላይ የወጡት ጽሑፎች መለስ ብሎ ለማየት ለሚፈልግ ከብዙ ጥቂቶቹን ብቻ ከአዚህ በታች ርዕሶቹን አና የተፃፉበትን ጊዜ (እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር)  ከስር ለማካፈል ሞክርያለሁ። ዛሬም ትኩረት የሚያስፈልገው ውስጣዊ የመዋቅር ማዘመን አንጂ በክርስቶስ ዘመን የነበረው አና  ክርስቶስ ተመልሶ አስከሚመጣ የሚኖረው  የውጭ ፈተና አይደለም። ይህ ማለት ውጫዊ ፈተናዎች በሙሉ ችላ ይባሉ ማለት አይደለም።የአንድ ተቋም ህልውና ግን አደጋ ላይ የሚወድቀው በውጫዊ ተፅዕኖ ሳይሆን ከውስጣዊ የአሰራር፣የመዋቅር አና የአቅም ግንባታ አለመጠናከር ነው።ቤተክርስቲያኒቱ  የውስጡን ስታጠናክር በፍጥነት የውጭውን ፈተና መመከት ብቻ አይደለም በጎ ተፅዕኖ የመፍጠር አቅሟን የሚጨምር ፈጣን አቅም ከመቅፅበት በራሱ ይመጣል።


ከአዚህ በፊት  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ፈተናዎች በተመለከተ ጉዳያችን ላይ ከወጡት ውስጥ የሚከተሉትን ለናሙናነት አቀርባለሁ።ማንም ሰው ጉግል ላይ ርዕሶቹን በመፃፍ ብቻ አያንዳንዱን ጽሑፍ በቀላሉ ማንበብ ይችላል።

የጉዳያችን የዛሬ መልዕክትም አንድ ነው። የኢትዮጵይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን  በቀላሉ ገፍቶ ኢትዮጵያን ማስቀጠል ፈፅሞ አይቻልም። የአርሷን ያህል የትህትናም ሆነ የፀጋ ባለቤት አሁንም የለም።ይህ ማለት የሌለውን የራሴ የሚለው የማመን መብቱን መጋፋት ወይንም ዝቅ አድርጎ ማቅረብ ማለት አይደለም።አውነታውን ማንም የማይነቀንቀው ሀቅ ነው።


ከእዚህ ቀደም በጉዳያችን ላይ የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን በተመለከተ ከወጡት ጽሑፎች ውስጥ የጥቂቶቹ ርዕሶች እና ሊንኮች : =


ርዕስ = የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ችግር በማያዳግም መልኩ ለመፍታትት ሁሉም ይነሳ! (ሚያዝያ፣2019 ዓም እኤአ)


ርዕስ = በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ላይ ሰሞኑን የነበረው ሁኔታ ለቤተክርስቲያን የደወል ድምጽ ነው::ወደፊት ምን ይሰራ? (መስከረም 6፣2019 እኤአ)

ርዕስ = የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞችን ሁሉን አቃፊ የሆነ ፖለቲካዊ ዕሳቤ መሰረት ያደረገ የፖለቲካ ፓርቲ በመመስረት እና ሚናውን በማስፋት የኢትዮጵያ ህልውናን በትክክል ማረጋገጥ ይቻላል። (ጉዳያችን ሃሳብ) መስከረም 16፣2019 እኤአ የተፃፈ።


ርዕስ = የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ደህንነቷን ለመጠበቅ በፍጥነት መውሰድ የሚገባት ሁለት የመፍትሄ ርምጃዎች (የጉዳያችን ሀሳብ) (ህዳር 16፣2010 እኤአ የተፃፈ) 


ርዕስ = በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ላይ የሚታየው የመንግስት አያያዝ በኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ጦርነት ሊያስነሳ ይችላል (ጉዳያችን ልዩ እና ወቅታዊ ) (መስከረም 2019 ዓም እኤአ የተፃፈ)


ርዕስ = በጅማ ዩንቨርስቲ የ ኦርቶዶክስ ተማሪዎች ላይ ከ ሰሞኑ የተፈፀመ ግፍ (GUDAYACHN EXCLUSIVE ) (ጥር 2013 እኤአ የተፃፈ)


===============////=========

Tuesday, January 24, 2023

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ለመክፈል የተሞከረው ሙከራ በሁሉም ክልል በሚገኙ የቤተክርስቲያኒቱን ልጆችና አባቶች ዘንድ ከመቼውም ጊዜ በላይ እጅግ የጠነከረ ህብረት እና አንድነትን ፈጥሯል።



  •  በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ብቻ ሳይሆን በሙስሊሙም ማኅበርሰብ ዘንድ ቤተክርስቲያኒቱን ለመክፈል የሚደረገው ሙከራ ከፍተኛ ቁጣን ፈጥሯል።
  • ንዝረት የተኛ ነርቭ ያነቃቃል።
  • ቤተክርስቲያን ተሸንፋ አታውቅም ሊከፋፍሏት የሞከሩትን ሁሉ ግን አለት ሆና ስታደቅ በታሪክ ታይቷል።
  • ቅዱስ ሲኖዶስ የነገውን አስቸኳይ ስብሰባ ህገወጦቹን ከማውገዝ ባለፈ የቤተክርስቲያኒቱን አስተዳደራዊ ሁኔታ ለማዘመን ከምር ከምዕመናን ጋር መክሮ ወደ ሥራ የሚገባበት መሆን አለበት። ይህንን የአንድነት ስሜት መጠቀም ይገባል።

==========
ጉዳያችን ምጥን
=========
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን የተለያየ ምክንያት ለራሳቸው እየሸጎጡ በከንቱ ጥላቻ ውስጥ የሚንገዋለሉ መኖራቸው የአደባባይ ምስጢር ነው።ኢትዮጵያን ከነፊደልዋ፣ከነታሪኳ፣ባሕሏ እና ነጻነቷ እንድትቆይ ሃላፊነት ወስዳ በሰራች እና ለትውልድ ሃገር የማሸጋገር ሥራ ላይ ቀዳሚ ሚና በመጫወቷ በሚያምኑት እምነት መለየት ወይንም ኢትዮጵያን በማስቀደሟ የባንዳነት ዛራቸው የሚያጓራባቸው እንዲሁም ቀርበው ሳያውቋት በርቀት በስማ በለው በቡና ላይ ወሬ ሊተርኳት የሚሞክሩ ሁሉ በቤተክርስቲያኒቱ ላይ ጣታቸውን ይቀስራሉ።

በቤተክርስቲያኒቱ ላይ ያለው የጥላቻ ደረጃ በመንግስታዊ መዋቅር ውስጥ እንደ የሊባኖሱ ሂዝቦላ ተሸሽጎ የፋሺዝም ተግባር የሚይራምደው ከኦነግ ሸኔ ጀምሮ በባዕዳን ድርጎ የሚንቀሳቀሱ የሃይማኖት ያልሆኑ ግን ሃይማኖት መሰል ስብስቦች ሁሉ በቤተክርስቲያኒቱ ላይ የሸረቡት ተንኮል ሁሉ ምዕመኑ ሳያውቀው ቀርቶ አይደለም። ሁሉን እየሰማ እንዳልሰማ፣ እየተመለከተ እንዳልተመለከተ የሃገር ጉዳይ ይቅደም እያለ አልፎታል። ሆኖም ግን ቤተክርስቲያኒቱን ለመክፈል በከፍተኛ ወጪ ባለ ኮከብ ሆቴል የሚያርፉ መነኮሳትን ሰብስቦ እና በዘር እና በመንደር ተደራጅቶ የቤተክርስቲያኒቱ ከፍተኛ አካል የሆነውን ቅዱስ ሲኖዶስ ለመክፈል የድፍረት ድፍረት ይፈጸማል ብሎ የገመተ የለም። የሆነው ግን ይሄው ነው።ዐይን አውጣነት፣ሸፍጥ እና ክህደት በተሞላበት መንገድ ቅዱስ ሲኖዶስ ከሚያውቀው ውጪ ኢጲስ ቆጶሳት ሾመናል የሚሉ አካላት ሲነሱ መንግስታዊ አካል ጉዳዩ ከፍተኛ የጸጥታ ችግር እንደሚያመጣ እያወቀ እና የሃገሪቱ ትልቁንና ጥንታዊውን ተቋም በህገወጦች በእዚህ ደረጃ ለመግፋት ሲሞከር አንድም የህጋዊውን ሲኖዶስ ደህንነት ለማስጠበቅ የተንቀሳቀሰ እና ህገወጦቹን ለመውቀስ የተሰማ እንቅስቃሴ አሁንም ከመንግስት በኩል አልተሰማም።
ይልቁንም በዛሬው ዕለት የተሰማው መንግስት ጥበቃ ያደርግ የነበረበትን የቤተክርስቲያኒቱን ከፍተኛ አካላት ቦታዎች ሁሉ ፖሊሶቹ እንዲነሱ ማድረጉ ነው የተሰማው።

ይህ ሁኔታ የፈጠረው ሁኔታ ግን ከእዚህ በፊት ባልታየ እና ባልተሰማ ደረጃ በሁሉም ክልል የሚገኙ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተከታዮች እና አባቶች መሃል እጅግ ከፍተኛ ህብረት እና አንድነት ተፈጥሯል።''ክርስቲያን እና ሚስማር ሲመቱት ይጠብቃል '' እንዲሉ በአሁኑ ጊዜ ከሁሉም በላቀ መልኩ እየተሰራ ያለው ደባ በኦሮምያ ክልል የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ተረድተውታል። ድርጊቱ በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ብቻ ሳይሆን በሙስሊሙም ማኅበርሰብ ዘንድ ቤተክርስቲያኒቱን ለመክፈል የሚደረገው ሙከራ ከፍተኛ ቁጣን ፈጥሯል።ንዝረት የተኛ ነርቭ ያነቃቃል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ለመክፈል የተሞከረው ሙከራ በሁሉም ክልል ላሉ የቤተክርስቲያኒቱን ልጆችና አባቶች የጠነከረ ህብረት እና አንድነትን ፈጥሯል።በቤተክርስቲያኒቱ እና በምዕመናኖቿ ላይ እየተፈጸሙ ያሉት በደሎች ምን ዓይነት ቁጣ አስከትለው እንደሚያልፉ እና የት እርቀት ድረስ ሊከፋፍሏት የሞከሩትን እንደሚያሽቀነጥራቸው አሁን ግምቱን ማስቀመጥ ቢከብድም ከታሪክ የምንማረው ግን አንድም ቀን ቤተክርስቲያን ተሸንፋ እንደማታውቅ ብቻ ሳይሆን ሊያጠፏት እና ሊከፋፍሏት የሞከሩትን ሁሉ አለት ሆና ስታደቃቸው መኖሯን ነው።

በመጨረሻም ቅዱስ ሲኖዶስ ነገ አስቸኳይ ምልዐተ ጉባዔው ቤተክርስቲያኒቱን ለመክፈል የሞከሩትን ጉዳይ አጀንዳ አድርጎ ይወያያል።ከውይይቱ በኋላ የሚሰጠው ውሳኔ የምዕመናንም ውሳኔ ሆኖ ይቀጥላል።ከእዚሁ ጋር በማስከተል ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን አስቸኳይ ስብሰባ በህገወጦቹ ላይ ሲኖዶሳዊ ውሳኔ ከማሳለፍ በላይ የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደራዊ ጉዳዮች ለማዘመን የሚሰሩ ሥራዎች እንዲቀጥሉ የሚያደርግ ውሳኔ እና ቁርጥ የሥራ ሂደት ማስኬድንም አብሮ ሊያስብበት ይገባል።አጋጣሚው መልካም ነው።የቤተክርስቲያኒቱን አስተዳደራዊ ሁኔታ ማዘመን የምዕመናንም የአባቶችም ጥያቄ ነው።ይህንን የአሁኑን በምዕመናንና አባቶች መሃል የተፈጠረርውን እጅግ የጠነከረ ህብረት እና አንድነት እና በቤተክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለው የጥቃት ቁጭት መልካም አጋጣሚ ነው።ይህንን ስሜት እና ሁኔታ መጠቀም ብልህነት ነው። 

ቤተክርስቲያንን አንተውም ከቶ! መዝሙር



Thursday, January 12, 2023

የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር በቋንቋ ዙርያ ያሳለፈው ውሳኔ አረብኛን ሲያካትት ከኢትዮጵያ አልፎ በአውሮፓና ካናዳ ዩንቨርሲቲዎች የሚሰጠውን የግዕዝ ቋንቋ በስርዓተ ትምሕርቱ ውስጥ አለማካተቱ ታሪካዊ ስህተት ብቻ ሳይሆን በደል ነው። አሁንም ማረም አለበት።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በቋንቋ ጉዳይ ውሳኔ የሰጠበት ስብሰባ
 (ፎቶ ፋና ብሮድካስቲንግ)
  • ፖሊሲ ሕዝብ ያድናልም፣ይገድላልም። 
  • ግዕዝ በትምሕርት ቤቶች እንዲሰጥ ህዝብ መጠየቅ አለበት።
  •  መንግስትም ምላሽ መስጠት አለበት። 
=======
ጉዳያችን
=======
የአዲስ አበባ ክልል አስተዳደር ካቢኔ በአዲስ አበባ የሚገኙ ተማሪዎች የሚማሩትን የቋንቋ ዓይነት በተመለከተ ውሳኔ ማሳለፉ ዛሬ ተነግሯል። ዜናውን አስመልክቶ ፋና ብሮድካስቲንግ እንዲህ ዘግቦታል።

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው በ2ኛ አመት 8ኛ መደበኛ ስብሰባው ከብዝሃ ቋንቋ ካሪኩለም ጋር በተያያዘ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

ካቢኔውም በመደበኛው ስብሰባ የብዝሃ የቋንቋ ስርዓተ ትምህርትን አስመልክቶ የኮተቤ ትምህርት ዩንቨርሲቲ ሲያስጠናው የቆየውን አዲሱን ካሪኩለም አስመልክቶ የተወያየ ሲሆን ዩንቨርሲቲው ባስጠናው ጥናት ዙርያ ሰፋ ያለ የተለያዩ የህዝብ ( የተማሪ ወላጆችን ጨምሮ) ምክክሮችና ውይይቶች ሲካሄዱበት ቆይቶ በዛሬው እለት በጥናቱ በቀረቡት ምክረ ሃሳቦች ዙርያ ውሳኔውን አሳርፏል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

1ኛ:- በአዲሱ ስርዐተ ትምህርት ጥናት መሰረት በአፋን ኦሮሞ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ለሚማሩ ተማሪዎች አማርኛ እንደ ተጨማሪ (ሁለተኛ ) ቋንቋ እንዲሰጥ

2ኛ:- በአማርኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ለሚማሩ ተማሪዎች ደግሞ አፋን ኦሮሞ እንደ ተጨማሪ (ሁለተኛ )ቋንቋ እንዲሰጥ

3ኛ:- ከ7ኛ ክፍል ጀምሮ በሁሉንም የከተማው ትምህርት ቤቶች ሁሉንም የትምህርት አይነቶችን በእንግሊዘኛ መማር እንዲችሉ እንዲደረግ

4ኛ:- ለ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎች አረብኛና ፈረንሳይኛ በሃይስኩል ደረጃ አማራጭ ትምህርት ሆኖ እንዲቀጥል፡፡

5ኛ:- የቅድመ አንደኛ ደረጃ የትምህርት መጀመሪያ እድሜ ከ4 ዓመት እንዲሆን

6ኛ:- በአዲሱ የስርዓተ-ትምህርት ማዕቀፍ መሰረት 11ኛ እና 12ኛ ክፍል የስራ እና ቴክኒክ ትምህርት በተለያዩ አመራጮች እንደሚማሩ በሚያስቀምጠዉ መስረትና ከፍተኛ ሀብት የሚፈልግ በመሆኑ ከቴክኒክና ሞያ ኮሌጆች በክላሰተር በቅንጅት እንዲሰጥና በተጠናው ጥናት መሰርት ወደ ግንባታ እንዲገባ እንዲደረግ

7ኛ:- የግል ት/ቤቶችን የመፅሐፍት እጥረት ለመቅረፍ በሽያጭ ለማቅረብ ለመጽሓፍት ህትመት የተዘዋዋሪ ፈንድ 250 ሚሊየን ብር ተጨማሪ በጀት እንዲፈቀድ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በዚህም መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ ከኦሮምያ ክልል ለኦሮምኛ ቋንቋ ማስተማርያነት በውሰት ተወስዶ ተግባራዊ ሲደረግ የነበረው ስርአተ ትምህርት በአዲሱ ስርዐት ትምህርት የሚተካ ይሆናል። ይላል ዜናው።


የካቢኔው ውሳኔ ተማሪዎች የተለያዩ ቋንቋዎች እንዲማሩ መደረጉ ባልከፋ።ችግሩ ግን ኢትዮጵያውያን ስለራሳቸው ታሪክ፣ሳይንስ፣ሃይማኖት፣ፍልስፍና፣አስተዳደር እና ሕግ ጭምር የተጻፉ መጻህፍትን እንዳይመረምሩ የግዕዝ ቋንቋ እንዲማሩ አለማድረጉ ታሪካዊ ስህተት ብቻ ሳይሆን በደል ነው።አረብኛ የሃይማኖት ቋንቋ ብቻ እንዳልሆነ ሁሉ፣የግዕዝ ቋንቋ የሃይማኖት ቋንቋ ብቻ አይደለም። ከኢትዮጵያ አልፎ የዓለም ታሪክ የሚገኝበት ጥልቅ ምስጢር ያለው እና ኢትዮጵያውያን በዓለም ላይ የነበራቸው ኃያልነት ሁሉ የተደበቀበት ነው።የአውሮፓ እና አሜሪካ ተመራማሪዎች በግዕዝ የተጻፉ መጻሕፍትን እያጋዙ የወሰዱት ከመድሃኒት እስከ የጠፈር ምርምር በርካታ ጽሑፎች ስላገኙበት ነው።


የግዕዝ ቋንቋ በአሁኑ ጊዜ በጀርመን፣ካናዳ፣አሜሪካና ሩስያ ዩንቨርሲቲዎች እየተሰጠ ነው።ባለቤቷ ኢትዮጵያ ግን በትምሕርት ቤቶቿ መስጠት አቅቷታል።የግዕዝ ትምህርት ለተማሪዎች ለመስጠት የመምሕራን ችግር ፈጽሞ የለም።ሆኖም ግን የአረብኛና ፈረንሳይኛ መምህራን ለማግኘት ኢትዮጵያ ከውጭ መምህራንን መቅጠር ያስፈልጋታል። ቋንቋ መማር ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርኩት የሕዝብ አቅም በምጣኔ ሃብትም ሆነ በማኅበራዊ ግንኙነቱ ያጠናክረዋል እንጂ አይጎዳም።ነገር ግን ግዕዝን የሚያህል የራስን ቅርስ አጥፍቶ እና ትውልድ እንዳይማረው አድርጎ መሄድ ታሪካዊ ስህተት ብቻ ሳይሆን በደል ነው። ፖሊሲ ህዝብ ይገድላልም ያድናልም። የግዕዝ ትምህርት በትምሕርትቤቶች አለመስጠት ኢትዮጵያውያን ታሪካቸውን እንዳያውቁ እና የነበራቸውን ሃገር በቀል ዕውቀት ለራሳቸው እንዳይጠቀሙ ከማድረግ ባለፈ ለዓለም በኩራት ስለራሳቸው እንዳይናገሩ የማድረግ እኩይ ተግባር ነው።ግዕዝ በትምሕርት ቤቶች እንዲሰጥ ህዝብ መጠየቅ አለበት። መንግስትም ምላሽ መስጠት አለበት። 

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...