Tuesday, June 2, 2026

7ኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ግንቦት 24፣2018 ዓም በከፍተኛ የሕዝብ ተሳትፎ ተጠናቋል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በሰባተኛው ብሔራዊ ምርጫ ድምፅ ሲሰጡ።

  • ስለምርጫው ዝርዝር ጉዳይ ምን ያውቃሉ?

✓ ሰባተኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ 42 ፓርቲዎች እና 73 የግል ተወዳዳሪዎች ለተለያዩ ምክር ቤቶች ዕጩዎች የቀረቡበት ነው።

✓ በዚህ ምርጫ በአጠቃላይ 2,198 ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሁም 8,736 ለክልል ምክር ቤቶች መቀመጫዎች በዕጩነት ቀርበው ተወዳድረዋል።

✓ በዚህም በምርጫው የተወዳደሩት አጠቃላይ ዕጩዎች ቁጥር 10,934 ዕጩዎች መሆናቸውን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መረጃ ያመለክታል።

✓ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለክልል ምክር ቤቶች ከፍተኛውን ዕጩዎች ያቀረቡት ሦስት ፓርቲዎች ናቸው።

✓  በዚህም ገዢው ብልጽግና 2,950 ዕጩዎችን በማቅረብ ቀዳሚ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) 1,256 እና ሦስተኛው ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት 1,032 አቅርበዋል

✓ ሌሎች ፓርቲዎች እና የግል ተወዳዳሪዎችም በተለያየ ቁጥር ለተለያዩ ምክር ቤቶች መቀመጫ ለማግኘት ዕጩዎችን በምርጫው ላይ እንዲወዳደሩ አቅርበዋል።

 ✓ በአማራ ክልል ከሚገኙ 138 የምርጫ ክልሎች መካከል በስምንቱ ምርጫ እንደማይደረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀደም ብሎ ማስታወቁ ይታወሳል።

✓ በአማራ ክልል ድምጽ የማይሰጥባቸው 8ቱ የምርጫ ክልሎች በደቡብ እና ምዕራብ ጎንደር፣ በአምባሰል እንዲሁም በደጋ ዳሞት የሚገኙ መሆናቸው ተገልጿል።

✓ በትግራይ ክልል ከሌሎች የአገሪቱ ክልሎች ጋር በአንድ ላይ ምርጫ አልተካሄደም።

 ✓ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢዋ ወ/ሮ ሜላተወርቅ ሰኞ ዕለት ድምጽ በማይሰጥባቸው ስምንት የምርጫ ክልሎች ወደፊት እንዲመርጡ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

✓ በትግራይም 38 ወንበሮች ክልሉ በምርጫ ቦርድ በተቀመጠው የምርጫ ሒደትና ሕግ መሰረት የሚካሔድና ወንበሮቹ ክፍት ሆነው ይጠብቃሉ።

✓ ትናንት ግንቦት 24፣2018 ዓም የተደረገው ብሔራዊ ምርጫ 501 ዕጩዎችን ወደ የሕግ መወሰኛው ወይንም የተወካዮች ምክርቤት የሚያስገባና ምስክርም 25፣2019 ዓም በሚከፈተው የኢትዮጵያ ምክርቤት አዲሱ መንግስት ሥራ ይጀምራል።

✓ በእዚህ ምርጫ የኢትዮጵያን የመንግስት ስሪት ምርጫውን በማደናቀፍ ዕቅድ ተግባር የሸረቡ የቅርብና የሩቅ ቡድኖች በኢትዮጵያ ሕዝብ ጥንቁቅና የቆረጠ የምርጫ ተሳትፎ በእጅጉ ተበሳጭተዋል።

በሰባተኛው የኢትዮጵያ ምርጫ የተሳተፉ ብሔራዊና የክልል ፓርቲዎች ዝርዝር:-

ምንጭ:- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ምንጭ:- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ







የኢትዮጵያ ወዳጅ ንጉስ ልጅ ዛሬ ከእዚህ ዓለም አረፉ። ለኖርዌይ ትልቅ የሃዘን ቀን ሆኗል።Norway's King Harald V has died at the age of 89

በዚህ አጭር ዘገባ ውስጥ የሚከተሉትን ያገኛሉ። ስለ ንጉስ ሃራልድ በጥቂቱ የንጉስ ሃራልድ አባት ንጉስ ኦላቭ እና ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ የት ተዋወቁ? ንጉስ ሃራልድ አምስተኛ የኖርዌይ ንጉስ ===================...