- ስለምርጫው ዝርዝር ጉዳይ ምን ያውቃሉ?
✓ ሰባተኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ 42 ፓርቲዎች እና 73 የግል ተወዳዳሪዎች ለተለያዩ ምክር ቤቶች ዕጩዎች የቀረቡበት ነው።
✓ በዚህ ምርጫ በአጠቃላይ 2,198 ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሁም 8,736 ለክልል ምክር ቤቶች መቀመጫዎች በዕጩነት ቀርበው ተወዳድረዋል።
✓ በዚህም በምርጫው የተወዳደሩት አጠቃላይ ዕጩዎች ቁጥር 10,934 ዕጩዎች መሆናቸውን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መረጃ ያመለክታል።
✓ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለክልል ምክር ቤቶች ከፍተኛውን ዕጩዎች ያቀረቡት ሦስት ፓርቲዎች ናቸው።
✓ በዚህም ገዢው ብልጽግና 2,950 ዕጩዎችን በማቅረብ ቀዳሚ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) 1,256 እና ሦስተኛው ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት 1,032 አቅርበዋል
✓ ሌሎች ፓርቲዎች እና የግል ተወዳዳሪዎችም በተለያየ ቁጥር ለተለያዩ ምክር ቤቶች መቀመጫ ለማግኘት ዕጩዎችን በምርጫው ላይ እንዲወዳደሩ አቅርበዋል።
✓ በአማራ ክልል ከሚገኙ 138 የምርጫ ክልሎች መካከል በስምንቱ ምርጫ እንደማይደረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀደም ብሎ ማስታወቁ ይታወሳል።
✓ በአማራ ክልል ድምጽ የማይሰጥባቸው 8ቱ የምርጫ ክልሎች በደቡብ እና ምዕራብ ጎንደር፣ በአምባሰል እንዲሁም በደጋ ዳሞት የሚገኙ መሆናቸው ተገልጿል።
✓ በትግራይ ክልል ከሌሎች የአገሪቱ ክልሎች ጋር በአንድ ላይ ምርጫ አልተካሄደም።
✓ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢዋ ወ/ሮ ሜላተወርቅ ሰኞ ዕለት ድምጽ በማይሰጥባቸው ስምንት የምርጫ ክልሎች ወደፊት እንዲመርጡ እንደሚደረግ ገልጸዋል።
✓ በትግራይም 38 ወንበሮች ክልሉ በምርጫ ቦርድ በተቀመጠው የምርጫ ሒደትና ሕግ መሰረት የሚካሔድና ወንበሮቹ ክፍት ሆነው ይጠብቃሉ።
✓ ትናንት ግንቦት 24፣2018 ዓም የተደረገው ብሔራዊ ምርጫ 501 ዕጩዎችን ወደ የሕግ መወሰኛው ወይንም የተወካዮች ምክርቤት የሚያስገባና ምስክርም 25፣2019 ዓም በሚከፈተው የኢትዮጵያ ምክርቤት አዲሱ መንግስት ሥራ ይጀምራል።
✓ በእዚህ ምርጫ የኢትዮጵያን የመንግስት ስሪት ምርጫውን በማደናቀፍ ዕቅድ ተግባር የሸረቡ የቅርብና የሩቅ ቡድኖች በኢትዮጵያ ሕዝብ ጥንቁቅና የቆረጠ የምርጫ ተሳትፎ በእጅጉ ተበሳጭተዋል።
በሰባተኛው የኢትዮጵያ ምርጫ የተሳተፉ ብሔራዊና የክልል ፓርቲዎች ዝርዝር:-
ምንጭ:- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድምንጭ:- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ



No comments:
Post a Comment